Telegram Web Link
# ጦቢያ ግጥም በጃዝ 102ኛ ምሽት ጥር 6 ዕሮብ

ቦታ:- ራስ ሆቴል
መግቢያ :-100 ብር
ሰዓት: 11:00

@wegoch
@balmbaras
ጥር 8, በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል
ክፍት የስራ ቦታ መፅሐፍ
ይመረቃል !
ለውብ ቀን!
💚

የጧቱ ፍንዳታ
💣💣


አዲስ አባባ። ከሩፋኤል ወደ ፒያሳ ለመጓዝ የታክሲ ወረፋ ይዣለሁ። ተራየ ደርሶ ከፊት
ካለው ጋቢና ተቀመጥኩ። ጉዞ ተጀመረ። መንገዱን ገና ከማጋመሳችን አካባቢው በከፍተኛ
የፍንዳታ ድምጽ ተናወጠ። ሾፌሩ ሁለት እጆቹን ከመሪው ላይ አንስቶ የታክሲው ጣሪያ ላይ
ሰቀላቸው። በግዳጅ ከዘመተበት የጦር ቀጠና አምልጦ ለባላንጣው ጦር እጅ በመስጠት
የተማረከ ምልምል ወታደር መሰለ። እኔም በተራየ ያበደረውን ሰው አይቶ በድንጋጤ
እንደሚሸማቀቅ ዜጋ ሾፌሩን እያየሁ ሁለት እጆቼን ጆሮዎቼ ውስጥ ወተፍኳቸው።
በአካባቢው ይስተዋል የነበረው የትራፊክ እንቅስቃሴ ለቅፅበት ቀጥ አለ። «አዲስ አባባ/
ፊንፊኔ/ሸገር/በረራ/ ወ.ዘ.ተ የቀንና የማታ ጭልፊቶች ስለበዙ መስታወት ከፍተህ
ሞባይል አትጎርጉር» ተብሎ የተነገረኝን ምክር ዘንግቼ አንገቴን በመኪናው መስኮት መዝዤ
በማውጣት አየሩን ቃኘሁት። የነዋሪው የፊት ገፅታ ለአፍታ ያህል ፍርሃት የጎበኘው
ይመስላል። በነገራችን ላይ አካባቢውን ያናወጠው ፍንዳታ የመኪና ጎማ ነበር ።
ሞባይሌ ሳይሰረቅ የመኪናውን መስታወት ዘግቼ ከዚህ በታች የመጣልኝን ሃሳብ ከጎኔ
ለነበረው ጓደኛየ እንዲህ አወራሁት :-
.
.
ከሴፕቴምበር አስራ አንዱ የሽብር ጥቃት በኋላ አሜሪካን መራሹ ኃይል በአፍጋኒስታን
የመሸጉ ኃይሎችን ድባቅ ለመምታት በሚል በዘመኑ አሉ የተባሉ የጦር መሳሪያዎችን
በግዙፍ የጦር መርከቦቹ ጭኖ ሀገር የማውደም ተልዕኮውን ለማሳካት ጥሮ ነበር። ወቅቱ
መቀመጫውን ኳታር (ደውሐ) ያደረገው የአልጀዚራ የዐረብኛ ቴሌቪዥን ጣቢያ አያሌ
አድማጭ ተመልካቾችን በማፍራት ሰፊ ተቀባይነት ያገኘበት ነው። የዲሽ ሳህኖች የቤት
ቆርቆሮ ላይ እንደተሰጣ ብቅል እዚህም እዚያም እንደ አሸን ፈልተው የሚታዩበት ጊዜ ነበር።
በዚያ ወቅት ከተስተዋሉ ክስተቶች መካከል የማይረሳኝ የሶሪያና የስፔን ጣምራ ዜግነት
የነበረው ጋዜጠኛ ተይሲር ዐሉኒ ነው። የአፍጋኒስታን ሰንሰለታማ ተራራዎች ላይ እንደ ጦጣ
እየወጣ ዘገባዎችን የሚያስተላልፍ ብርቱ ጋዜጠኛ። የታንክ አፈ ሙዝ ላይ ተቀመጦ መረጃ
የሚያቀብል ትንታግ ጋዜጠኛ። በቀንደሃር ግዛት በምትገኝ የገጠር መንደር ውስጥ ያቀረበው
ዘገባ በህሊናየ ማህደር ላይፋቅ ተቀምጧል። ጋዜጠኛው ዘገባውን እያስተላለፈ ካለበት ቦታ
ትንሽ ፈንጠር ብሎ ነጫጭ አህዮች እየነዱ የሚጫወቱ ህጻናት ይታያሉ። ስፋቱ አንድ
ኮንዶሚኒየም ማቆም የሚችል የተደረመሰ መሬት በአቅራቢያው አለ። ይህ ስንጥቅ መሬት
ጥልቀቱ ከሶስት ሜትር በላይ ነው። መሬቱ የተደረመሰው በአሜሪካ መራሹ ኃይል
አማካኝነት ከሰማይ ቁልቁል በሚጣል ፈንጅ ነው። ተይሲር ዐሉኒ ወደ ህጻናቱ ተጠጋ።
ስለአፍጋኒስታን ህዝብ አይበገሬነት በአግራሞት ተውጦ ይናገራል። «አፍጋኒስታን ገራሚ
ሀገር ናት። ህዝቡ ከድህነት እና ኢማን ውጭ ሌላ አንዳች ነገር የለውም» ብሎ የተናገረው
ድምፁ እስከ አሁን ድረስ በጆሮየ ያቃጭላል። ወደ ህጻናቱ ይበልጥ ቀረበ። ሰማዩ ቅኝት
በሚያደርጉ የጦር ጀቶች ድምፅ እየታረሰ ነው። ተይሲር ዐሉኒ አርጩሜ ይዞ አህያ
የሚነዳውን ህጻን እየጠየቀው ነው። «እዚህ አካባቢ ስትጫወቱ አትፈሩምን?» እያለ። ህፃኑ
ፈገግ ብሎ «ለምደነዋል፤ በዚህ የተደረመሰ መሬት ላይ የፈጋውን ፈንጅ በቅርብ ርቀት ሆነን
ስንመለከት ከቁብ አልቆጠርነውም» አለው።
እኔ ግን መሃል አዲስ አባባ ሩፋኤል አካባቢ የፈነዳ የመኪና ጎማ ልቤን በፍርሃት አንደኛው
ሰማይ ላይ ወስዶ ሲመልሳት እንዴት እንደነበርኩ እኔና እኔን የፈጠረኝ ብቻ ነን
የምናውቀው። የበሬ ግንባር የምታህል አካባቢ በመኪና ጎማ ፍንዳታ እንዲህ ከተናጠች
እርጥብና ደረቁን የማይለየው ጦርነት ቢከሰት ኖሮ በጭንቀት ወደሰማይ ያረገችው ልቤ
መመለሻዋ ይርቅ ነበር።
የኃይማኖትም ሆነ የፖለቲካ የፌስ ቡክ አርበኞች ሆይ!
ኳስ በመሬት አድርጉ። ሀገር አረጋጉ። በቃል አትዋጉ። ፈጣሪ የማንችለውን ነገር
እንዳያሸክመን ሰበብ አትሁኑ። ጦርነት ይቅርና የመኪና ጎማ በፈነዳ ቁጥር እንደ ህጻን
ዳይፐር የምንፈልግ የፈሪ ስብስቦች ብዙ መሆናችንን አስቡ። የአባቶቻችንን የጀግንነት ወኔ
የወረሰ ትውልድ ያለ ይመስል ቀረርቶ አታብዙ። የጦርነት መጨረሻው በፈረሰች ከተማ
መሃል ከሞት ተርፈው የመድፍ ቀለሃ ላይ ቡና የሚወቅጡ ሰዎችን ማየት ብቻ ነው። እሱም
የሚሆነው የቡና ማሳው ተቃጥሎ ካልወደመ ነው። ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር ብቻ ሳትሆን
የፈሪዎችም ጭምር ናት። ስለዚህ እየፈራን የመኖር መብታችንን በናንተ ጀግንነት ለመሸፈን
አትሞክሩ። ጀግንነታችሁን የማጋባት ግዴታ የጣለባችሁ አካል ያለ ይመስል ፌስቡኩን
የሽምቅ ውጊያ ቀጠና አታድርጉት።


አሁን ርዕሱን መለስ ብላችሁ አንብቡትማ ... ያስጨንቃል አይደል? የፌስ ቡክ አርበኞችም
ወግ ከዚህ የዘለለ አይደለም።

ምንጭ:- መሀመድ

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለውብ ቀን!
💚

በሃሳብ መንገድ ላይ
Written by ተመስገን


ሰውየው በሺ ከሚቆጠሩት የእምነት ክፍሎች ያንደኛው ‹ፓስተር› ነበር፡፡
‹ነቢያችን› እያሉ ይጠሩታል፡፡ ‹አጋንንት ያስለቅቃል፣ ሕሙማን ይፈውሳል›
በማለት የሚመሰክሩለት ብዙ ናቸው፡፡ እሱ ግን ከዛም በላይ ሃይል እንዳለው
ይሰማዋል - ሙታንን የማስነሳት፡፡ ‹‹እግዜር በህልሜ ተገልጦ ለዚህ ተግባር
እንደ ተመረጥኩ ነግሮኛል›› ባይ ነው፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ ይህን ችሎታውን
የሚያሳይበት አጋጣሚ ድንገት ብቅ አለለት፡፡… በየሶስት ዓመቱ በታላቁ
ስታዲየም የሚዘጋጀው ታላቅ ጉባኤ፡፡
የዚያን ቀን ፓስተራችን ስለ ታላቁ አምላክ ሃይልና ስልጣን በታላቅ መንፈስ
ሰበከን:: ቀጥሎም ሙታንን የማስነሳት ተዓምር እንደሚከናወን አበሰረን፡፡
አዳዲስ አማኞች እንዳይደናገጡ ካሳሰበ በሁዋላም…
‹‹ከናንተ መሃል ሞቶ መነሳት የሚፈልግ እጁን ያውጣ›› ሲል ጠየቀ፡፡ በሺ
የሚቆጠሩ ሰዎች ብድግ አሉ - ‹‹…‹እኔ!›፣ ‹እኔ!›… እያሉ፡፡ አራት የተመረጡ
ምዕመን ወደ መድረኩ ወጡ:: ፓስተሩም ያዘጋጀውን መሳሪያ አስመጥቶ
በየተራ ገደላቸው፡፡ ከአፍታ ጸጥ፣ እረጭ በኋላ ወደ መጀመሪያው አስከሬን
ጣቱን ቀስሮ፡- ‹‹በየሱስ ስም ተነስና ቁም!›› በማለት አዘዘ፡፡… አልተነሳም፡፡
እንደገና ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ፡፡ አልተንቀሳቀሰም፡፡ ‹‹ምናልባት ዱዳ
የነበረ ሰው ይሆናል›› … ሲል አሰበ፡፡ ወደ ሁለተኛው ሟች ተጠግቶ እንደ
በፊቱ ተጣራ፡፡… አልሆነም፡፡ ሶስተኛውንና አራተኛውንም ሞከረ:: ያው ነው::
ሽጉጡን ወደ ራሱ አዙሮ ቃታ ሳበ፡፡ እሱም አልሰራም፡፡ ጥይቱ አልቋል፡፡
የተኩስ ድምፅ የሰሙ በጥበቃ ላይ የነበሩ ፖሊሶች ባይደርሱ ኖሮ፣ ‹ነቢያችን›
እንደ ማርያም ጠላት ተቀጥቅጦ ይሞት ነበር - በተከታዮቹ፡፡… እንደ ሞሶሎኒ፡፡
… ወስደው አሰሩት፡፡ እስር ቤት እያለ አንድ ቀን እግዜርን ህልሙ ውስጥ
አገኘው፡፡
‹‹ምነው ‹ጉድ› አደረግኸኝ?››
‹‹ምን አጠፋሁ?››
‹‹ሙታንን ታስነሳለህ ብለኸኝ አልነበር?››
‹‹በደንብ እንጂ!››
‹‹ታዲያ ምነው አቃተኝ?››
‹‹የአንተ ጥፋት አይደለም››
‹‹ያንተ ነው?››
‹‹የኔም አይደለም››
‹‹እና?...››
‹‹… ጥፋት ሳይሆን ፍላጎት ነው፡፡… የመብት ጉዳይ!››
‹‹ማለት?››
እግዜር ትንሽ አሰበና የሆነውን ነገረው፡፡
‹‹ኦኬ፣ ኦኬ… አይሲ›› አለ ፓስተሩ… በመደነቅ፡፡ ‹‹… ታዲያ እኔ መታሰር
አለብኝ?›› ለማለት አፉን ከመክፈቱ ባነነ፡፡ … የሆነው ነገር ምን ነበር?
* * *
ካለፉት ሳምንታት ባንደኛው አዲስ አድማስ ርዕሰ አንቀጽ ያደረጋት አሪፍ
‹ታሪክ› ነበረች፡፡… ሰውየው ያጠፋው ወይም የበደለው ነገር የለም:: ሌሎች
ሰዎች ግን ወደ እሱ እየጠቆሙ ‹‹እሱ ነው፣ እሱ ነው!›› በማለት ጣታቸውን
ቀሰሩበት:: ሰውየውም መንገደኞቹን እየተመለከተ ‹‹ምናልባት ያጠፋሁትን
ረስቼ ይሆናል እንጂ ይኸ ሁሉ ሰው እንዴት ይሳሳታል?›› በማለት አሰበና
በማያውቀው ነገር ራሱን ጥፋተኛ አደረገ፡፡
ወዳጄ፤ ኢ-ፍትሃዊ በሆነው ቶታሊቴሪያን (Totaliteriam) ሥርዓት፤ እንደ
ራስህ ሳይሆን እንደ ሌሎች እንድታስብ ትገደዳለህ፡፡ ታላቁ ፈላስፋ ባሩክ
ስፒኖዛም በወጣትነቱ የገጠመው ፈተናም ተመሳሳይ መንፈስ ነበረው፡፡
ሆላንድ በስደት የኖረው የአይሁድ ማህበረሰብ ዕምነት ተቋም
(Synagogue) የልጃቸው ታላላቅ ሀሳቦች ተናነቃቸው፡፡ የውሸት ክስ
ቀምመው ከጉባኤ መማክርቱ ፊት አቆሙት፡፡… እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ1656
ዓ.ም፡፡ …ያኔ ሃያ አራት ዓመቱ ነበር፡፡
‹‹እግዜር እንደ ሰው የሰብዓዊ አካላት (Matter) ውቁር ሊሆን ይችላል፣
መላዕክቶች የቅዠት ምስል (Hallucination) እንጅ እውን ሆነው የሚገለፁ
ፍጥረታት አይደሉም፣ ነፍስ የምንለው ህላዌ ሰብ ከስጋና በሕይወት ከመኖር
ተነጥሎ ለዘለዓለም የሚቆይ ተዓምረ ክስተት አይመስለኝም፣ ከሞት በሁዋላ
ሕይወት ስለመኖሩ በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰ ነገር የለም›› ብለህ ለጓደኞችህ
የተናገርከው እውነት ነው ውሸት ሲሉ ጠየቁት፡፡ ‹‹ምን እንደመለሰላቸው
አልታወቀም፡፡›› ይልና ፀሐፊው፤ ነገር ግን ለወደፊቱ ግላዊ ሀሳቡን በውስጡ
ይዞ፣ ቢያንስ በሌሎች ሰዎች ፊት ለአይሁዳዊ እምነት ታማኝ መስሎ
እንዲታይ፣ ለዚህም በየዓመቱ አምስት መቶ ዶላር ምንዳ ሊሰጡት
መወሰናቸውን እንዳሳወቁት ያትታል፡፡
ስፒኖዛ ግን የዕድል (fate) ጉዳይ ሆኖ አፈጣጠሩ ለአይሁድ ትልቅነት ሳይሆን
ለዓለም በመሆኑ መደለያቸውን አጣጥሎ በፀናው ሀሳቡ ቆመ፡፡ ጉባኤውም
ሕገ ደንባቸውን መሰረት አድርጎ ‹ይገለል› (Excommunicated ይሁን)
የሚል ፍርድ አሳለፈበት፡፡
በታላቅ ስነ ሥርዓት የተከናወነው የዚህ ፍርድ ሂደት እስራኤልን፣ አምላኳንና
ሕገ መጽሐፏን ለመጠበቅ የተደረገ ውሳኔ መሆኑን ይዘረዝራል:: በፈላስፋው
ላይ ከተላለፈው የእርግማንና የውግዘት መዓት በተጨማሪ ከማንኛውም
እስራኤላዊ ጋር በጽሑፍም ሆነ በቃል ግንኙነት እንዳያደርግ፣ ማንኛውም
ዓይነት አገልግሎት እንዳይሰጠው፣ ከማንም የማህበረሰቡ አባል ጋር በአንድ
ጣራ ስር እንዳይኖር፣ እሱ ካለበት ቦታ ቢያንስ አራት ሜትር መራቅ
እንደሚገባና ጽሑፎቹን ማንበብ ክልክል እንደሆነ ይደነግጋል::
ስፒኖዛ በታላላቅ ሀሳቦቹ ምክንያት ከሚወዳቸው ወገኖቹ ተገለለ፣ ራቀ፣ ከስራ
ተፈናቀለ፣ ብቸኛ ሆነ፡፡ ይህም ሳይበቃ በአንድ የማህበረሰቡ ሥነ መለኮት
አጋፋሪ የግድያ ሙከራ ተደረገበት፡፡ ተረፈ እንጂ፡፡
‹‹There are few Places in this world where it is safe to be a
philosopher›› በማለት የጻፈው ያኔ ነው፡፡ ፍሬደሪክ ኒች፤ ኢየሱስን
‹‹የመጨረሻው ክርስቲያን በመስቀል ላይ የሞተው ነው›› ብሎ ሲጽፍለት ብዙ
ሊቃውንት ስፒኖዛን እንዴት ‹ረሳው?› በማለት ተገርመዋል፡፡
ወዳጄ፡- በዚህ ዘመን ሕገ ደንብ፣ ሕገ መንግሥት ወዘተ በሚል ሽፋን ታላላቅ
ሀሳቦችን ለማኮላሸት መሞከር አይቻልም፡፡ የአንዱንና የሁሉን ዜጋ መብት
የማያከብር ሕግም ሆነ ደንብ አለም አቀፋዊ፣ ሰብዓዊ፣ ተፈጥሯዊና
ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ባገናዘቡ ሕጎች ሊሻሻል ወይም ሊተካ ግድ ነው፡፡
በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ፍ/ቤት ቀርበው ‹‹ወንጀሉን
የፈፀምነው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ነው›› የሚል አስደንጋጭ
መልስ ሲሰጡ ሰምተን አፍረናል፡፡ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ምን ማለት
እንደሆነ አልገባቸውም።
* * *
ወደ ጨዋታችን ስንመለስ፡- አስከሬኖቹ ያልተነሱት በዚህ አጭር ዕድሜ
በክልል ተፈርጀን፣ እየተጨቃጨቅን ከምንኖር እስከ ዕለተ ምፅዓት ሁሉም
እኩል በሆነበት መካነ መቃብር መቆየት ይሻለናል በማለታቸው ነበር፡፡
በነገራችን ላይ ‹‹ብዙ ጠንቋዮችና አዋቂ ነን ባዮች ጋ ሄጄ የተለያዩ ነገሮችን
ነግረውኛል:: ማናቸውም ግን ፖሊስ መሆኔንና ላስራቸው እንደመጣሁ
ሊያውቁ አልቻሉም፡፡›› በማለት የፃፈልን ማን ነበር?
ሰላም!!

ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
“ተከፍቶ ያልተከፈተ”
Written by ከቃል ኪዳን

አእምሮው ውስጥ እንደ እስረኛ ከአንዱ ጥግ ወደ ሌላው ጥግ
እየተመላለሱ፤ እግራቸውን የሚያፍታቱት ሀሳቦቹ፤ ፔርሙስ ከመሰለው
የሙዚቃ ማጫወቻ ውስጥ እንደ እንፋሎት የሚወጣውን ዜማ መልዕክት
ተከትለው በስልት ያረግዱ ጀመር፡፡ ሙዚቃውን በትውውቅ የጫነለት የፊልም
ማከራያ ባለቤት የሆነው አብሮ አደግ ጓደኛው ነው፡፡ እስከ ዛሬ ጓደኛው እሱን
እንጂ አእምሮው ዉስጥ እየተርመሰመሱ የሚያጨናንቁትን ሀሳባት የሚያውቅ
አይመስለውም ነበር፡፡
ከሙዚቃው ማጫወቻው አንድ የድሮ የአማርኛ ዘፈን ተንጠፍጥፎ ካበቃ በኋላ
አንዲት ሴት ‹ጥሎብኝ፣ ጥሎብኝ…› እያለች ታዜም ጀመር፡፡ ቅንድቡን ወደ
ላይ ወጥሮ፤ የሙዚቃ ማጫወቻውን እየገላመጠ፡-
‹‹እሺ አንቺን ደግሞ ምንድን ነው የጣለብሽ?›› አለ፡፡ አጠያየቁ ዘፋኞቹ ሁሉ
ተራ በተራ እየመጡ ‹ጥሎብኝ› እያሉ ስሞታ ያቀረቡለት ይመስላል፡፡ ዘፋኟ
እንዳልሰማችው ሆና መዝፈኗን ቀጠለች፡፡
የተቀመጠበት የተወላገደ ሶፋ ወገብ እስኪንጣጣ ድረስ ትከሻውን እያፍታታ
አዛጋና ሲጋራ አንስቶ አቀጣጠለ፡፡ የሟች አጎቱን ክፍል ከወረሰና ብቻውን
ማደር ከጀመረ በኋላ፤ ልክ እንደ በፊቱ ሲጋራ ለማጤስ፤ አገልግሎት መስጠት
ወዳቆመው የአያቱ ኩሽና መሄድ አቁሟል፡፡
የአጎቱ ክፍል ውስጥ ከሙዚቃ ማጫወቻዋ በስተቀር ከእሱ በዕድሜ
የሚያንስ የቤት ዕቃ የለም፡፡ አልጋው፣ የተቀመጠበት ሶፋ፣ የልብስ
ቁምሳጥኑ፣ ማብሰያ ዕቃዎቹን ሁሉ ሰልቅጦ፤ ሆዱን አሳብጦ እንደ ዘንዶ
ያንቀላፋው ገዳዳ ብፌ፤ ግድግዳው ላይ የተሰቀለው የያሲር አራፋት ፎቶ፤
ነብስ ካወቀ ጀምሮ የሚያውቃቸው ናቸው፡፡
አሁን የተቀመጠበት ሶፋ ላይ አጎቱ ተቀምጦ፤ በዝርግ ሰሀን ላይ ሠፍሮ
የሚሰጠውን በእርድ የበጨጨ ሩዝ፤ ወለሉ ላይ ቁጭ ብሎ እየሠለቀጠ፤
ከያሲር አራፋት ፎቶ ጋሽ ያሲንን ፈልፍሎ ለማውጣት ይሞክር በነበረበት ጊዜ
እንኳን እነዚህ የቤት ዕቃዎች በጉልምስና ዕድሜያቸው ላይ ነበሩ፡፡
ሲጋራውን ትንሽ ሳበና ጠራርጎ አጨሰ እንዳይባል እንደፈራ ሁሉ፤ የቀረውን፤
ስኒዋ ከተሰበረ በኋላ አሽትሬ የሆነችው የስኒ ማስቀመጫ ላይ በጣቶቹ
እየረገጠ አጠፋው:: ዘፋኚቱም ‹ጥሎብኝ› የሚለውን ቃል፤ እያገላበጠች፤
ዜማውን አጠፋችና ሙዚቃዋን ጨረሰች፡፡
‹‹ጥሎብኝ!›› አለ ድንገት፡፡ ‹‹ጥሎብኝ! ጥሎብኝ!›› ቃሉን ደጋገመውና
እንዳጠፋው ሲጋራ የጨለመ ፈገግታን ፈገግ አለ፡፡
ጥሎበት ቀይ ሴት ይወዳል፡፡ በተለይ ቀይ፣ ቀጭን ሴት ታስደነግጠዋለች፡፡
ከሠርገኛው የፍቅር ህይወቱ ቀይ፣ ቀይ የሆኑትን ሴቶች እየመረጠ ነው፤
ስላሳለፈው የፍቅር ህይወት የሚያወራው፡፡ ቀይ ሴትና ድንቡሽቡሽ ያለ ጠይም
ወንድ ልጅ የትዳር ህይወቱ ግቦች ናቸዉ:: ስለ ነገ ሲያስብ የፈጣሪን ‹ጋዋን›
ተውሶ፤ እራሱ ባበጃጀው ‹ላቦራቶሪ› ውስጥ ከጥቁር ቆዳውና ደንዳና ሰውነቱ
ዘር ወስዶ በሚያገባት ቀይ፣ ቀጭን ሴት ላይ ዘርቶ፤ ድንቡሽቡሽ ያለ ጠይም
ልጅ ያበቅላል፡፡ ወተት የመሰለችውን ሴት ወስዶ፤ ከቡናው ገላው ጋር
አዋህዶ፤ ድንቡሽቡሽ ያለ ‹ማኪያቶ› ይጨምቃል፡፡ ከጉርምስናው በኋላ ይሄን
ንድፈ ሀሳቡን ወደ ተግባር ሊለውጥ አይጥ ያላደረጋት ቀይ ሴት ሠፈሩ ውስጥ
ተፈልጋ አትገኝም፡፡ ችግሩ ግን ሀሳቡ ሊሠምርለት አልቻለም፡፡
ቀዩ የፍቅር ታሪኩ፤ እንደ ውሃ ጋን በሁለት ቀይ ሴቶች ጀርባ ላይ ያረፈ ነው፡፡
የመጀመርያዋ ቀይ ሴት የልጅነት ፍቅሩና ፍቅር ምን እንደሆነ ያስተማረችው
ናት፡፡ ሁለተኛዋ ደግሞ አሁን ላለው ምርጫው መለኪያ አድርጎ ያስቀመጣትና
ማፍቀር ምን ማለት እንደሆነ አሳየችኝ የሚላት ሴት ናት፡፡
እነዚህ ሁለት ሴቶች ከሌሎቹ ቀያይ ሴቶችና ቆጠራ ውስጥ ከማይገቡት
ሌሎች ቀይ ያልሆኑ ሴቶች በላይ በትዝታው ውስጥ ግዘፍ ነስተው
ተቀምጠዋል፡፡ ስለ ፍቅር በሚያወጋበት ጊዜም፤ እንደ ርዕሰ ጉዳዩ ዓይነት
እየተቀያየሩ፤ የወጉን ቅድምያ ያገኛሉ፡፡ እነሱን የሚቀድም ግን ማንም የለም፡፡
ከመንፈቅ በፊት የተለየችው የመጨረሻዋ ፍቅረኛው እንኳን በወጉ ውስጥ
እራስ የመሆን ዕድል አግኝታ አታውቅም:: ስለ እሷ የሚጠይቀው ሰው ቢመጣ
እንኳን በእነዛ ሁለት ሴቶች በኩል ካላቋረጠ እሷ ጋ አይደርስም፡፡
ሁለቱን ቀያይ ሴቶቹን ተራ በተራ አስታውሶ ሲመለስ በረጅሙ አዛጋና ሌላ
ሲጋራ አውጥቶ ለኮሰ፡፡ ይሄኔ አያቱ ቢያዩት ኖሮ ምግብ ሲበላ እንደሚያደርጉት
‹‹ሁሉንም ሲጋራ ለኩፈህ፣ ለኩፈህ ከምትጥል አንዱን በደንብ አታጨስም?
የሲጃራም እኮ ግፍ አለው!›› እያሉ ሊቆጡት ይችሉ ነበር፡፡
ሲጋራውን መጦ ጭሱን ሲተፋ፤ የተዘፈነ ሳይሆን የተተፋ የሚመስል ሙዚቃን፤
የሙዚቃ ማጫወቻው መትፋት ጀመረ፡፡
‹‹ግቢበት በልቤ፤ ግቢበት በልቤ
ላንቺ አይደለም ወይ እንዲህ መንገብገቤ›› የሚል፤ ገና ያልወጣ የሚመስል
ሙዚቃ ከፔርሙሱ፤ ጓል እንደበዛበት በሶ ቦጭ፣ ቦጭ እያለ መፍሰስ ጀመረ፡፡
‹‹ቆይ እንዴት ትግባ? ወይ መዝፈኑን ትተህ ደብዳቤ ጻፍላት›› አለ በቁጣ፡፡
ወጣቱ ዘፈኑንም ሆነ ዘፋኙን ያለዛሬም ሰምቶት አያውቅም:: በዘፈኑና በዘፋኙ
ቢናደድም፤ ዘፋኙ በሻካራ ድምጹ እየደጋገመ ግቢበት በልቤ የሚላት ነገር
ሀሳብ ውስጥ ከተተችው፡፡
ማፍቀርን አስተማረችኝ ከሚላት ፍቅረኛው ጋር የተለያየ ሰሞን፤ ልቡ ተሠብሮ
ክፍሉን ዘግቶ ተኝቶ ሳለ፤ ብዙ የልብ መሠበር መከራን ያሳለፈችው አክስቱ
ክፍሉ ድረስ መጥታ ‹‹ልብህን ክፍት አድርገህ ከጠበቅህ ትክክለኛው ሰውዉ
ይመጣል›› ብላው በሩን ክፍት ጥላበት ወጣች፡፡ በሩን ክፍት አድርጋ
የሄደችው ምስጢር ለመመስጠር ነው ብሎ አስቦ፣ ልቡን ሊከፍት ሦስት ቀን
ከተጋደመበት አልጋ ተነሳ፡፡
‹‹ትንሳኤ ልብ ሥቡራን!›› አለ በራፉ ላይ ቆሞ ወደ ዋናዉ ቤት ለመግባት
ከውፍረቷ ጋር ትግል የገጠመችውን አክስቱን እየቃኘ፡፡
አክስቱ ልጅ አገረድ ሆና ባለመገኘቷ የልጅነት ባሏ ጀርባዋ ሰምበር
እስኪያወጣ ድረስ በጉማሬ አለንጋ ገርፎ፤ በሱ ላይ መሀሉ ተቧጦ የወጣለትን
ደፎ ዳቦ አሳዝሎ (መሀሉን ቧጦ ያወጣው ድፎ ዳቦው እንዳይከብዳት
አዝኖላት ይሆን?)፤ እግሯን በዱላ ሠብሮ ወደ ቤተሰቧ ከላካት በኋላ፤ ያገሬው
ጎረምሳ እየተቀባበለ፤ ከሰባት ዓመት በፊት ላገባችው ባሏ አስረከባት:: አሁን
በመጨረሻ ትዳር መሥርታ፤ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ያበቃት ልቧን ክፍት
አድርጋ መጠበቋ እንደሆነ ለእህቷ ልጅ በምስጢር ነግራው ሄደች፡፡ ኧረ
እንደውም ሦስት ቀን ሙሉ እንደ መቃብር የዘጋውን በሩን፤ መዝጊያውን
አንከባላለት ሄደች፡፡
ከዛ በኋላ የልቡን መዝጊያዎች፣ የሲኦልን ደጃፎች ያህል ወለል አድርጎ
ከፈታቸው፡፡ በወንድ አቅሙ የልቡን ወለሎችና ግድግዳዎች እበት
ለቀለቃቸው፡፡ ፍቅረኛው ሠብራው የሄደችውን ልቡ ውስጥ ያለውን ዙፋን
በዘነዘና ቀጥቅጦ ጠገነውና የለበሰውን ግምጃ አውልቆ አለበሰው፡፡ ከዛም
ጭሳጭሱን አጫጫሰና እንደ ሴት አዳሪ የልቡ በር ላይ ቆሞ የልቡን ንግስት
ይጠብቅ ጀመረ፡፡
ልቡን ክፍት አድርጎ ትክክለኛዋን ሴት መጠበቅ ከጀመረ ብዙ ጊዜያት
ተቆጥረዋል:: በዚህ መሀል ‹ባዶ ልብ በክረምትን› እቤቱ ቁጭ ብሎ
ላለማንጎራጎር ብዙ አዛጋሚዎችን ቢያፈራም፣ ከአዛጋሚዎቹ መሀል ግን
ለአንዷም ቢሆን የልቡን መግቢያ ሊያሳያት አልፈቀደም፡፡ ችግሩ ግን ሁለተኛዋ
ቀይዋ ፍቅረኛው አሳይታው የሄደችው ከፍታ ላይ የምታደርሰውን ቀይ ሴት
ማግኘት አልቻለም፡፡
ከሀሳቡ በፍጥነት ሲመለስ ‹ጠይም ናት ጠይም መልከ ቀና በውበት ያጌጠች›
እያለ ጥላሁን ሲያዜም ደረሰ፡፡ ‹‹የጥላሁን እውነተኛ ምርጫ ግን የትኛዋ ሴት
ናት? ዛሬ ጠይም ናት ይላል፤ ነገ ስለ ቀይ ዳማዋ ይዘፍናል፤ ተነገወድያ ስለ
ቀይዋ፤ ከዛ ስለ ጥቁ
ሯ…›› ሲል አጉተመተመ::
ጠይምና መልከ ቀና የሆነቺውን አሁን አብሯት ያለውን ወይም አብራው
ያለችውን ሴት እየፈራት ነው፡፡ እንዳይወዳት ጠይም ናት:: ጸባይዋ ግን ሸጋ
እንደሆነ አምኗል፡፡ አክስቱም አያቱም ሁሉም ወደዋታል፡፡ አዛጋሚዬ ናት
እንዳይል ካሰበው በላይ አብራው አዝግማለች:: ፈጽሞ አይደክማትም፡፡ እሱ
ነገሯ ነው እያስፈራው ያለው፡፡
ሴት ፊት ሲነሷት ስትሸሸ ነው የሚያውቀው:: ይህቺ ሴት ግን ምን አስባ
እንደሆነ ሊገባው አልቻለም፡፡ እስካሁን የገፋቸው ሴቶችን ክስ ይዛ ነገረ
ፈጃቸው ሆና የመጣችም ይመስለዋል:: አንድ ቀን ልቡ መግቢያ እንደሌለው
ነገራት፡፡ የዛኑ ቀን ወደ ልቡ መግቢያ ልታበጅ ቁፋሮዋን ጀመረች፡፡ እንድትሸሽ
ማድረግ ስላልቻለ መሸሽ ጀመረ፡፡
የጥላሁን ሙዚቃ ከማብቃቱ ቤቱ ተንኳኳና ድብልብል አክስቱ እየተድበለበለች
ገባች፡፡ ቀና ብሎ አያትና ሙዚቃ ማጫወቻውንና በእጁ የያዘውን ሲጋራ
አጠፋፋ፡፡
‹‹የጥላሁንን ሙዚቃ ስሰማ እኮ ወንድሜ ያለ ሁላ ነው የመሰለኝ፡፡ ነብሱን
ይማረው!›› አለችው፡፡
‹‹ኮሌክሽን ሙዚቃ አስጭኜ ነው፡፡›› አላት እንድትቀመጥ ወንበሩን
እየለቀቀላት፡፡ ስትቆም ብዙ ነገር ስለምትከልል በጣም ትከብዳለች፡፡
‹‹እኔ እሄዳለሁ ቁጭ በል፡፡ ሰላም ልልህ ነው የመጣሁት፡፡››
‹‹ቁጭ በይ እንደውም ላዋራሽ ስፈልግሽ ነበር›› አላት ሄዶ መሬት
የተጋደመው ፍራሽ ላይ እየተቀመጠ፡፡
‹‹ምነው በሰላም?›› አለችው ሄዳ ፍራሹ ላይ ከጎኑ ለመቀመጥ
እየተንፈራገጠች፡፡ ደግፎ ሊያስቀምጣት አብሯት ትንሽ ተወራጨ፡፡ እንደ
ምንም ተደላድላ ተቀመጠችና የሚላትን ለመስማት ሳይሆን የምትነግረውን
ለማወቅ በጉጉት ተመለከተችው፡፡ እሱ ግን የሚነግራትን ለመስማት
እንደጓጓች አስቦ፡-
‹‹ልብህን ክፈት አልሺኝ ልቤን ከፈትሁ፡፡ ግን ልቤ ውስጥ የምትገባ ሴት ላገኝ
አልቻልሁም:: ቆይ ምን ያህል ነው መጠበቅ ያለብኝ?›› አላት ጥበቃ
እንዳሰለቸው አናቱን እያወዘወዘ፡፡
‹‹ይህቺን ልጅ አሁንም አልወደድካትም ማለት ነው?›› አለችው በትዝብት፡፡
‹‹እሷን ተያት! ʻታይፔʼ አይደለችም አልኩሽ እኮ!? ደግሞ ትናንት
ያልወደዱትን፤ ዛሬ መውደድ ይቻላል እንዴ?››
‹‹ለምን አይቻልም? ያላየኸውን ማየት ስትጀምር…አልገብቶህ የነበረው
ሲገባህ…››
‹‹እኔ በመላመድ በሚመጣ ፍቅር አላምንም:: ፍቅር እንደወረደ ሲሆን ነው
የእውነት የሚሆነው፡፡ ቀይ ቆንጆ ሴት አይቼ ድንግጥ ስል ነው ፍቅር እንደሆነ
የማምነው፡፡ በመላመድ የሚመጣው ፍቅር ሳይሆን አብሮ፣ ተቻችሎ የመኖር
ክህሎት ነው፡፡›› ንግግሯን ነጠቃት:: ንግግሩን ሰምታ ስታበቃ አክስቷ እራሷን
በአሉታ ነቀነቀች፡፡
‹‹እውነቴን ነው፡፡ እሺ ቆይ መላመድ ፍቅር መሆን ቢችል ይሄን ያህል ቆይተን
ለምን አልወደድኳትም? ሳልፈልግ አብሬአት መሆንን ግን ችዬበታለሁ!››
‹‹እንዳልወደድካት በምን እርግጠኛ ሆንክ? እስከዛሬ አብረሀት የቆየኸው
ስለወደድካት ቢሆንስ? ከሌሎቹ ሴቶች ጋር ለምን ከሳምንት በላይ መቆየት
አቃተህ?›› አክስት መስቀለኛ የመሰለ ጥያቄ ጠየቀች፡፡ ግራ ተጋብቶ
ተመለከታት፡፡
‹‹እንዴ እራሷ እኮ ናት ጥብቅ ያለችብኝ!››
‹‹እየደወሉ እየጠሩ ጥብቅ አለችብኝ ብሎ ነገር አለ እንዴ? አልወደድኳትም
ማለት እኮ አለመውደድ አይደለም፡፡››
‹‹እና ወደድኳት ማለት ነው?››
‹‹እሺ ቀይ አለመሆኗን ተወውና ከእሷ የምትጠላውን አንድ ነገር ንገረኝ?››
አክስት አፍጥጣ ጠየቀቺው፡፡ ግራ በመጋባት ትንሽ ሲያስብ ቆየና፡-
‹‹እንዴ! ቆይ የምጠላላት ምንም የለም ማለት እወዳታለሁ ማለት ነው
እንዴ?››
‹‹እንደዛ ማለቴ አይደለም፡፡››
‹‹እናስ?›› አቋረጣት፡፡
ለመነሳት እየተንደፋደፈች ‹‹ያንተ ችግር…›› አለችና ንግግሯን በእንጥልጥል
ትታ ተንደባላ ተነሳችና ቆመች፡፡
‹‹ቆይ ʻታይፔʼ ያልሆነችን ሴት አለመውደዴ ችግር ነው እንዴ?›› አላትና ቀጥ
ብላ እስክትቆም ጠብቆ ሄዶ ፊቷ ተገተረ፡፡
‹‹ችግርህ ልብህ እንጂ ዓይኖችህ አልተከፈቱም፡፡ ልብ ካላየ ዓይን አያይም
ይባላል:: ዓይን ካላየም ልብ አያይም! ልብህን ከፍተህ ጠብቅ ስልህ
ዓይኖችህ የተከደኑ ይሆናሉ ብዬ አልጠበቅሁም ነበር፡፡››
በቆመበት ጥላው ወደ በሩ አመራች፡፡ ግራ በመጋባት በደመነፍስ ተከተላት፡፡
በሩ ጋ ደርሳ ቆመችና፡-
‹‹ቀይ ሴት ትፈልጋለህ፡፡ ቀይ ሴት አትፈልግ ልልህ አልችልም፡፡ ግን ከቀይ
ሴት ቆዳ ጀርባ የጠቆረ ልብ ሊኖር እንደሚችል ማወቅ አለብህ:: በተቃራኒ
ጥቁር ብለህ ከምትሸሻት ሴት ቆዳ ጀርባ፤ አንተ አይተህ የምትደነገጥላትን
ቀይ ሴት ቆዳ የሚያስንቅ ንጹህ ልብ ሊኖር ይችላል:: ደግሞስ አንተን ብቻ
ይህቺና ያቺን እያልክ የምትመርጥ፤ መራጭ ማን አደረገህ? ቢገባህ ይህቺ
ሴት አንተን በመምረጧ እራሱ ዕድለኛ ነህ!››
ጥላው ከክፍሉ ወጥታ ሄደች፡፡ ከፍታ የገባችውን በር አልዘጋችውም፡፡
በቆመበት በሩን ክፍት ጥላው የሄደችው ዛሬም አንዳች ነገር ለመመስጠር
አስባ ይሆናል ሲል አሰበ:: ወደ ሶፋው ተመልሶ ተቀመጠና ሙዚቃ
ማጫወቻውን ከፈተ፡፡ ጥላሁን ‹ጠይም ናት ጠይም መልከቀና› የሚለውን
ዘፈኑን ካቆመበት ቀጠለ፡፡ እሱ ግን ‹ልቤን ብቻ ከፍቼ ዓይኖቼን ከድኛለሁ
እንዴ?› ሲል አዲስ ሀሳብ ማሰብ ጀመረ፡፡

"ናካይታ"💚

#ምንጭ :- አዲስ አድማስ ጋዜጣ

@wegoch
@wegoch
የራሔል እንባ
Written by አገኘሁ አሰግድ

አጭር አጭር ልብወለድ
የራሔል እንባ


ደስ ብሏታል! የህይወት ትርጉሟን ብትጠየቅ “እሱ ነው” ብላ
የምትመልስበት ልጇ፣ ዛሬ ሁለት ዓመት ሞላው፡፡ ለልደቱ የሚያስፈልጉትን
ነገሮች ከከተማ ለመግዛት ልትወጣ ነው፡፡ ልጇ ተኝቷል፡፡ ይዛው ብትሔድ
ገዝታ ከምትመለሰው ዕቃ ጋር ስለማይመቻት፣ ለጐረቤቷ ለሀዊ አደራ ሰጥታ
ሄደች፡፡
*
ከልጇ አባት፣ ከኤርሚያስ ምርር ያለ ፍቅር ነበራት፡፡ “አያገባኝ ይሆን?” በሚል
ጥርጣሬ ሳትነግረው አረገዘች፡፡
ማርገዟ ግድ ብሎት እንደሁ እንጃ በአንዱ ቀን እንደሚያገባት ነገራት፡፡ በዛው
እለት ከሰዓት ኤርሚ በመኪና ተገጨ፡፡ ሬሳውን አመጡላት:: ታላቅ ደስታና
ሃዘን፣ ግማሽ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ጐበኝዋት፡፡ … ዛሬ የፍቅሯ ቅሪት
የሆነው የሁለት ዓመት ልጇ ብቻ ነው ያላት - አቤት ስትወድደው!!
*

የምትፈልገውን ገዛዝታ ወደ ቤቷ እያመራች፣ ሰፈሯ መዳረሻ ላይ ጩኸት
የሰማች መሰላት:: እርምጃዋን አፈጠነች፡፡ በትክክል ጩኸት ሰምታለች፡፡
የበለጠ ፈጠን ፈጠን አለች፡፡ ቤቷን ከርቀት ተመለከተችው፤ “የፈጣሪ ያለህ!”
የሚል ቃል ከአንደበቷ ወጣ፡፡ ትልቅ ቁሳዊ ሃብቷ የሆነው ቤቷ፣ በእሳት
ይንበለበላል፡፡ እንደ ደመራ ጧ ብሎ እየነደደ ነው፡፡ ባላት ሃይል እየተጣደፈች
ወደ ቤቷ ገሰገሰች፡፡
… ጐረቤቶቿ እሳቱን ለማጥፋት ይተጋሉ:: አካባቢው የጩኸት ሰፈራ ቦታ
መስሏል:: ዙሪያዋን ማተረች፡፡ አንድ ነገር በአዕምሮዋ አቃጨለ - ልጇስ!!
“ልጄስ!?” ስትል ጮኸች፡፡ የሰሟት ተደናገጡ፡፡ ይሄ ለነሱ አዲስ ነው፡፡ ልጇ፣
ልጇ… ያ ሲኮላተፍ የሚወዱት ህፃን … ያ የሁሉ ዓይን የሚሳሳለት ልጅ የት ነው
ያለው? ከእሳቱ መሃል ሊሆን ይችላል? ምነው ታዲያ እስካሁን ድምፁን
አልሰሙም? … ባለ በሌለ አቅማቸው እሳቱ ላይ ተረባረቡ፡፡ ከደቂቃዎች
በኋላ፣ እሳቱ ጠፋ:: ጥቂት ሰዎች ወደ ውስጥ ዘለቁ፣ ዙሪያቸው በጭስ
ተሸፍኖ ለማየት ያዳግታል፡፡
እናት ከውጭ ሆና ትጣራለች፣ ትጮሃለች፡፡ ልጇን አደራ ያለቻትን ሀዊን
ትፈልጋት ገባች፡፡ ሀዊ ምልክቷም የለ!
ወደ ውስጥ የዘለቁት ሰዎች ከጭሱ እየታገሉ ይፈልጋሉ፤ ህፃን ሙሴን፡፡
“እዚህ …እዚ…ጋ…” ሲል ተጣራ አንድ ወጣት፣ ወደ ኋላ እያፈገፈገ:: ሁሉም
ወደ እሱ መጡ፡፡ የገጠማቸው፣ የሚሰቀጥጥ ትዕይንት ነበር፡፡
*
“ኧረ እባካችሁ ልጄን…!?” ራሔል በዙሪያዋ ያለውን ሁሉ ትጠይቃለች፡፡ ወደ
ቤቱ ገብተው የነበሩት ሰዎች አንድ ነገር በጨርቅ ተጠቅልሎ እንደያዙ እጅብ
ብለው ወጡ፡፡ ራሔል ወደ ሰዎቹ ቀረበች፡፡ አተነፋፈሷ ልክ አይደለም:: ሰዎች
በጨርቅ የሸፈኑትን ለመግለፅ የፈሩ ይመስላል፡፡ አስፈሪ ድባብ…፡፡ በመሃል
አንድ አባት በሚንቀጠቀጥ እጃቸው ጨርቁን ገለጡት:: በእሳት የጠቆረ፣
ተለብልቦ የከሰለ የሰው ገላ፡፡ ከላዩ ጭስ የሚተን የህፃን ሙሴ ሰውነት፡፡
ከብቸኝነት ባህር ያሻገራት ሙሴ! የራሄልን ህይወት የሚመራው ሙሴ!
ራሔል ጮኸች፣ ጮኸች…! እንደ እብድ አደረጋት፡፡
ታላቅ ሀይል የተሞላች ዓይነት ለያዥ አስቸገረች፡፡ እልጇ በድን ላይ
ትወድቃለች፣ ትዘላለች፣ ትፈርጣለች … እንደ ምንም ይይዟታል፡፡
ሁኔታዋን እያዩ፣ ድንቡሽቡሽ ልጇን እያሰቡ የሚያለቅሱ ብዙ ነበሩ፡፡ የሙሴ
በድን ግን ተጋድሟል፣ ከቃጠሎ የተረፈ ለአፍንጫ የሚከረክር ሽታ ብቻ ሆኖ፡፡
ራሔል … አቅሟ ዝልፍልፍ አለ … እግሯ በዝለት መንቀጥቀጥ ጀመረ፡፡
መጮህዋን ግን አላቋረጠችም፡፡
ደግፈው ከአንድ ዛፍ ሥር አስቀመጧት:: በተቆራረጠ ድምፅ “ኤርሚዬ …
ኤርሚ … መሄድህ ሳያንስ … ልጃችንንም ጠራኸው? … እሺ … እኔስ ማን
አለኝ? ከእንግዲህ ማን አለኝ?” መልስ የምትጠብቅ ዓይነት አፍታ ትቆይና
የማይሰማ ነገር ታወራለች፡፡
የሚንከራተቱ ዓይኖቿ፤ ዙሪያውን ከተበታተኑት ዕቃዎች መሃል አንድ ስዕል ላይ
አረፉ፡፡ የገብርኤል ስዕል ነበር፡፡ ሶስቱን ደቂቅ ከእሳት ሲያወጣ፡፡ የሷ ልጅ
ከሶስቱ ህፃናት መካከል የለም! በእሳት የጠለሸውን ስዕል እያየች ገብርኤልን
ታዘበችው፡፡
ምነው የእሷን ልጅ ከእሳት አላወጣውም? ልጇ ምን አጥፍቶ ነበር? ለጣኦት
የተሰዋ ምግብ መቼ ቀመሰ? ገብርኤልን በውስጧ ስትጠላው ይሰማታል፡፡ …
በመሃል አንድ ነገር ጭንቅላትዋን መታው፡፡ ወደ ከተማ ከመሄዷ በፊት
አብርታ የወጣችው ሻማ ትዝ አላት፡፡ ሳታጠፋው ነበር የሄደችው፡፡ አዎ ያ ሻማ
ነው ልጇን ያቃጠለው:: ወደ ገብርኤል ምስል አይኗን ስትመልስ፣ ገብርኤል
የሚስቅባት መሰላት - የለበጣ ሳቅ፡፡ ብሽቀት ተሰማት፡፡ ብሽቀቷ ሳቅን ወለደ፣
ግራ የሚያጋባ ሳቅ፡፡ በዙሪያዋ ያሉት ግራ ተጋቡ፡፡ ትስቃለች፣ ታቆምና እንደገና
ከት ብላ ትስቃለች - ጨለማ ውስጥ መወርወር የፈጠረው ሳቅ፡፡ … ፍንጥር
ብላ ተነሳች … ተነስታ መሮጥ ጀመረች:: ተከትለው ሊይዝዋት አልቻሉም፡፡ …
ሮጠች … ሮጠች … ለጊዜው ወዳልታወቀ ዓለም፡፡
*

ህዳር 12 ጠዋት፡፡ እዚህም እዛም የተለኮሰ ቆሻሻ፡፡
በመንገዱ መሃል የምትጮህ፣ የምትለፈልፍ፣ ወዲህ ወዲያ የምትሮጥ ሴት፡፡
“ኧረ ተቃጠላችሁ! … ኧረ … እሳት…!...” የጀመረችውን አረፍት ነገር
ሳትጨርስ “ልጄን … ልጄን … ልጄን አውጡልኝ፣ እሳት በላው ልጄን … ኡኡ…”
እየተሯሯጠች የተቀጣጠሉትን ቆሻሾች ለማጥፋት ትሞክርና ያቅታታል፣
ዙሪያዋን እያየች ትጮሃለች፡፡ ስራዬ ብሎ የሚያያት የለም፡፡ ከተማው
ለምዷታል፡፡ እሳት ስታይ ልምዷ ነው፣ በተለይ ህዳር ላይ፣ ህዳር ሲታጠን፡፡
***
#ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ

ውብ ጁምኣ!💚

@wegoch
@wegoch
ለቅዳሚታችን!
❤️

የቦርድ ሊቀ መንበሩ
Written by Administrator


ኤልያስ የሆስፒታሉ እንግዳና መቀበያ አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጦ፣
ስሙ እስኪጠራ እየተጠባበቀ ነው፡፡ ይህ አዲስ ሆስፒታል ከተቋቋመ አመት
እንኳን ያልሞላው ቢሆንም፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝነኛ ለመሆን የበቃው
በምንም ሳይሆን፣ አሉ የተባሉ አገሪቱ ያፈራቻቸውን ሃኪሞች በውድ ገንዘብ
መቅጠር በመቻሉ እንደሆነ ኤልያስ ከሁነኛ ሰው ሰምቷል። ሌላው ይህን
ሆስፒታል ልዩ የሚያደርገው የፕላስቲክ ሰርጀሪ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ
ብቸኛው ሆስፒታል በመሆኑም ጭምር ነው፡፡ የኤልያስ አመጣጥም ዋናው
ምክንያት ይኸው ነበር፡።
ከወር በፊት መልካም መልካም የነበረው ፊቱ፤ የተጨማደደ የጨርቅ ኳስ
ስለመሰለ፣ የተጠየቀውን ከፍሎ የቀድሞ ገፅታውን ለማስመለስ ቆርጦ
ተነስቷል፡፡ የሕክምናው ቦርድ ሊቀመንበር ከመጀመርያው እንዳልወደደው
መግለጽ እንወዳለን፡፡ ‹‹የባንክ ሂሳብ ደብተርህንና አንዳንድ ማንነትህን
የሚገልጽ ማስረጃ አምጣ?” ባለው መሰረት፤ መታወቂያውንና የኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ ሰሜን ቅርንጫፍ የቁጠባ ሂሳብ ደብተሩን ይዟል፡፡ የባንክ ደብተሩ
ተቀማጭ ሂሳብ፣ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ ብር ከሃያ
አምስት ሳንቲም ጥሪት እንዳለው ያሳያል። እንግዲህ ህክምናው ምን ያህል
ወጪ እንደሚፈጅ አሁን ነው የሚለየው፡፡ መቼም ይሄን ገንዘብ አንድ የሕንጻ
ጥበቃ ሰራተኛ ‹እንዴት በስድስት ወራት ውስጥ ሊያፈራ ቻለ? ብሎ መጠየቅ
ከማንኛውም ማሰብ የሚችል ሰው የሚጠበቅ እንደሆነ ምንም ጥርጥር
የለውም፡፡ እኛም ይህንን ለማብራራት ዝግጁ ነን፡፡
የወር ደሞዙ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር የሆነው የሰላሳ አምስት አመቱ
ኮበሌ ኤልያስ ተሰማ፤ ከቤት ኪራይ፤ ከምግብና ከአረቄው (አንዳንድ
ወጪዎቹን ሳይጨምር) ውጭ ከደሞዙ ምንም አይተርፈውም፡፡
ሕንጻው ስር ካለው ምድር ቤት፣ ሁለት ፎቆች ወደ ታች - ሶስት መቶ መኪኖች
ሲያድሩ ጠባቂው እሱ ነው፡፡ ታዲያ አንድ ቀን ከሕንጻው ሰባተኛ ፎቅ ላይ
የሚኖር ሃብታም፤ ጀሪካንና የፕላስቲክ ቱቦ ይዞ መጣና የመኪናውን የነዳጅ
ታንከር ከፍቶ ጎማውን ወደ ታንከሩ ሰዶ፣ በአፉ ነዳጁን በመሳብ ወደ ጀሪካኑ
ሲቀደ ተመለከተ፡፡ ቱጃሩ ወደ አስር ሊትር ያህል ቀዳና ጀሪካኑን ይዞ ወደ ፎቅ
ወጣ። ከዚያ ቀን በኋላ የኤልያስ የሲሳይ በር ተከፈተ ማለት ይቻላል።
ከሚጠብቃቸው መኪኖች ውስጥ እሩብ ያህሉ የነዳጅ ታንከራቸው ቁልፍ
የለውም፡፡ በቀን ከሃምሳ መኪኖች ከአንድ ሊትር እስከ አምስት ሊትር መቅዳት
ጀመረ፡፡ ከግብረ አበሮቹ ጋር ከህንጻው እያወጣም አንዱን ሊትር በሃያ ብር
ይቸበቸብ ያዘ፡፡ ይሄም በጣም አስደሳችና የማይነጥፍ የገቢ ምንጭ ሆነለት፡፡
ለስድስት ወራት ያህል ሁኔታው ሳይቋረጥ ቀጠለ፡፡ ልክ የዛሬ ወር ያልተጠበቀ
ነገር ተፈጠረ፡፡ የገቢ ምንጩ ድንገት ተቋረጠ፡፡ ነገሩ እንዲያው ዝም ብሎ
አልነበረም የቆመው፡፡ የሱ ያልነበረው ነገር ከሱ ሲሄድ፤ የሱ የነበረውንም
ይዞበት ጭምር ነው የሄደው፡፡
አንድ ቀን እንደለመደው አንዱን መኪና ከፍቶ ጎማውን ወደ ታንከሩ ካስገባ
በኋላ ነዳጁን ሲመጥ፣ አፉና ፊቱ ላይ ተደፋ፡፡ ያኔ ፊቱ በእሳት ተጠበሰ፡፡
የላይኛው ከንፈሩ፣ አፍንጫውና አገጩ እንዳልነበሩ ሆኑ፡፡ መልከ መልካሙ
ኤልያስ፤ ሌላ አሰቃቂ ፍጡር መሰለ፡፡
ቀን ላይ ባለመኪናው አንድ ጀሪካን ነዳጅ ይዞ ወደ አንድ የሕንጻ መሳርያ ጎራ
ብሎ ነበር፡፡ የገዛውን ገዝቶ ሲወጣ፣ አጠገቡ የሱ አይነት ቢጫ ጀሪካን
ሰልፈሪክ አሲድ የያዘ የሌላ ገበያተኛ ጀሪካን መሬት ላይ ተቀምጧል፡፡
ባለመኪናው ሂሳብ ሲከፍል ሌላው ገበያተኛ፣ የባለመኪናውን ነዳጅ የያዘ
ጀሪካን የራሱ መስሎት ይዞት እብስ አለ፡፡ ባለመኪናው ከፍሎ ሲጨርስ፣ አሲድ
የያዘውን የሱ ያልሆነ ጀሪካን ይዞ ከሱቁ ወጣ፡፡ መኪናውን ምድር ቤት ሕንጻው
ጋ አቁሞ፣ ወደ ቤቱ ከመሄዱ በፊት በጀሪካን የነበረውን አሲድ ወደ መኪናው
የነዳጅ ታንከር ገለበጠው፡፡ እንግዲህ ያንን አሲድ ነበር ኤልያስ የተጋተው፡፡
***
ሆስፒታሉ ውስጥ ተራውን ሲጠብቅ የነበረው ኤልያስ፤ ስሙ ተጠራና የቦርዱ
ሊቀ መንበር ወዳለበት ዘጠኝ ቁጥር ቢሮ አመራ:: ፊቱ በስካርቭ ቢሸፈንም
ጉዳቱ ክፉኛ ስለነበር፤ ሊደብቀው አልቻለም፡፡ ሰው ሁሉ አፍጦ ያየዋል፡። ወደ
ቢሮው ገባና ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡
ጉረኛው የሆስፒታሉ የቦርድ ሊቀ መንበር ገና እንዳየው ነበር የጠላው፡፡
ሃይሉንና ስልጣኑን እሱ ላይ ለማሳየት ቆርጦ የተነሳ ይመስላል፡፡ ነገሩ
ሥራው፤ እንደ ትልቅ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ያደርገዋል፡፡ ግን ይህ ሆስፒታል
ከሌሎች በምን ይበልጣል? በምንም፡፡ የፕላስቲክ ሰርጀሪ ህክምና ስላለው
ብቻ እንጂ ሌላ ምን አለው? ምንም!
‹‹ጉዳቱ ከባድ ስለሆነ ሕክምናው ቀላል አይደለም›› አለ ጉረኛው የቦርድ ሊቀ
መንበር፤ መነጽሩን ወደ ላይ ገፋ እያደረገ፡፡ ‹‹ባደረግነው ምርመራ ብዙ
ድካምና ጥበብ የሚጠይቅ ሕክምና የሚያስፈልገው እንደሆነ ደርሰንበታል።
ስለዚህ ሕክምናው የሚጠይቀው ወጪ ይህን ያህል ነው” አለና፤ ትልቅ አሃዝ
የተጻፈበት ወረቀት ሰጠው - እየተጀነነ፡፡ ኤልያስ ወረቀቱን ተቀብሎ በግርምት
አትኩሮ ተመለከተው፡፡ ሊቀ መንበሩ የባንክ ደብተሩን አልተመለከተም፡፡ ታዲያ
እንዴት ይህንን ቁጥር ሊጽፍ ቻለ? አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ስድስት
ሺህ ብር ከሃያ አምስት ሳንቲም፡፡ ኤልያስን ወደ ተፈጥሮ መልኩ ለመመለስ
የተጠየቀው ገንዘብ የባንክ ደብተሩ ላይ የሰፈረው ነው - እቅጯን!

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ ጀባ!

#ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ጥሩምባ እና ሀርሞኒካ_የሞኝ ንፅፅር

Jan 19, 2020
  |   Written by   
ታመነ መንግስቴ
  |  
ሕብረተሰብ / social


"ጥምቀትና ሃርሞኒካ"ብሎ ነገር አይገባኝም።እቃው(ሀርሞኒካ ማለቴ ነው) ተወልዶ ያደገው በምዕራቡ ዓለም ነው።እነሡ ዘንድ ለብዙ ነገር ያገልግላል።ለእኛ ደግሞ በዓመት አንድ ቀን ዓለምን በምናስደምምበት የአደባባይ በዓላችን-ጥምቀት ላይ ሲንጫጫ ይውላል።

ለነገሩ ይህ የሚሆነው የምትደልቅበት አታሞ በጠፋት አዲስ አበባችን ነው።እዚህ ሸገር በተለይም በተንጣለለው የጃንሆይ ሜዳ ጥምቀትን በዕለቱ ሃርሞኒካ መንፋት "ችሎታ ነው" አሉ።(አይ መቻል እቴ!)

የልቅ የሞኝ ንፅፅሬን ትቸ፤ አገር ወዳበቀለው፣ልዩ ክብር ወዳለው፣ልብ ወደሚያማልለው የጥሩምባ
ወሬ ልውሰዳችሁ።መቸስ ድምፁ ጆሮ የሚያናጋን ሰው "ጥሩምባ አፍ"ብላችሁት ታውቁ ይሆናል።ይህም የጥሩምባን ድምፀ ልዕልና ወካይ ነው።እናም እንደጥምቀት ባሉ ሺዎች በሚሰባሰቡባቸው በዓላት የተዋጣለት ኩነት አድማቂ ለመሆኑ ምስክር ነው።እዚህ ላይ መቶ ሃርሞኒካ ከማንጫጫት በአንድ ጥሩምባ መገላገልን ያዙልኝ።

በነገራችን ላይ ጥሩምባ የአገሬ ሰው ባለውለታ የትንፋሽ ሙዚቃ መሳሪያ ነው።"የመንደሩ ጥሩምባ ነፊ"የምትለዋ ቅጥያ እንዲሁ አልመጣችም።ዛሬም ድረስ የብዙ እድሮች ባለውለታ ጥሩምብየ ነው።ታዲያ አዲስ አበቤ የሃዘን ጊዜ ጓዱን አንዴት በደስታ ቀን በሃርሞኒካ ይለውጠዋል?

እዚህ ላይ ጥሩምባ የማስታወቂያ(የእድር መጥሪያ) ዜማ ብቻ ያለው ሊመስላችሁ ይችላል።ግን ምስጢሩ ያለው በጥበበኛው ስለሆነ እንጅ ጥሩምባ ብዙ ነው።በእኔ መንደር ጥሩምባ ለለቅሶ፣ለሰርግ፣ለበዓላት እንዲሁም ነገረ ስራችን ሁሉ ዘመቻ ነውና ለልማትም ያገለግላል።ዛዲያ(ታዲያ ማለቴ ነው) በየ አገልግሎቱ ዜማው ይለያያል።"እንዴት?" ካላችሁኝ፤ገጠሬ ጠቢብ ነው።

አያቴ የጥምቀት 'ለት በጥሩምባ ይጠበብበታል።ሌማት ተደግሶ ሲበላ፣ሲጠጣ ይዋልና የሉባው ጊዮርጊስ ወደ መንበሩ እንደገባ ለአያቴ ሸጋ ጥሩምባ ይሰጠዋል።ከዚያ ያለ ምንም አቀንቃኝ(ዘፋኝ) የጥሩምባውን ስልተ ምት በመቀያየር ብቻ የደብሩን ኮበሌ ከልጃገረድ ጋር ጮቤ ማስረገጥ ነው።

"ኧረ እርየ እርየ፤ኧረ እርየው መላ
ጎጃም ተገበየ ፍቅርና ተድላ!"

ይሄን ግጥም አያቴ በጥሩምባ ብቻ ያወርደዋል።የጥምቀት'ለት ማለት በገጠር ፌሽታ ነው።ጥሩምባም በዕለቱ ባለ ውለታ ነው።
እናም ጥምቀትን በሚመስል ዐለም ያደነቀው ፤ወዶት የመዘገበው ክቡር ኢትዮጵያዊ በዓል ላይ ጃንሜዳን በሚያህል ግዙፍ የአራዶች አደባባይ፣ብቻ ብቻ በኩራታችን ቀን መጤ ኳኳታን ከአገር በቀሉ ጥሩምባችን ማስቀደማችን ደስ አይልም።ለዚህም ነው ጥሩምባንና ሃርሞኒካን ማነፃፀር የሞኝ ጠባይ ነው ማለቴ፤ምክንያቱም፦ሸሞንሟና ሚስቱን ከጅል ውሽማው ጋር ያወዳደረ እሱ ሞኛሞኝ ነውና!



፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ይቆየን!





Copyright ©2020 All rights reserved | This site is owned by NConsults

@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን!
💚



#ፍቅል
(መንግስቱ መርሃጽዮን)
ስጋ እወዳለሁ! ስጋ የሌለበት ምግብ ቅጠል ፣ ቅጠል ነው የሚለኝ! ግን ምን ያደርጋል የእኔ
ስጋ ወዳድነትና የስጋ ዋጋ አልገናኝ ብለው የስጋ አምሮቴን የማስታግሰው በወር ወይም
በሁለት ወር አንዴ ቢበዛ ሁለቴ ነው! በአሁኑ ግዜ ባለው የስጋ ዋጋ መናር የተነሳ ቁርጥ
አምሮኝ ልቆርጥ ቢለዋ አንስቼ ስገዘግዝ ለስጋው የከፈልኩት ዋጋ ስጋውን ሳይሆን ቢላው
ስጋዬን የሚቆርጠኝ ያህል እየተሰማኝ ነው። ሆኖም ግን ስጋ መብላት አላቆምኩም።
ደሞዝተኛ ነኝ! የግብርም፣ የግድብም፣ የበላሁት ብድርም ተቀናንሶለት የቤት ኪራይ ከፍዬ ፣
የታክሲ መድቤ፣ ለእናቴ ጡረታ ቆርጬ ለቀለቤና ለድራፍት የምትሆን ትንሽ ገንዘብ ነች
የምትተርፈኝ። ከእርሷ ላይ ደሞ ለስጋ ከተነሳላት .........።
ቅዳሜ ግማሽ ቀን ሰራለሁ። ዛሬ ግን ስብሰባ ስለነበር "በድፍን ቅል አይጥ ገባች" አይነት
ጉንጭ አልፋ ውይይት አይሉት ሙግት ስዳረቅ አርፍጄ ከቢሮ እንደወጣሁ ገና እኩለ ቀን
ሳይሆን የፀሀይዋ ግለት መሀል አናቴን እየፈጀኝ ቁጭ ብዬ ጫማዬን አስጠረግኩ።
ጫማ እድለኛ ነው! አርጅቶም፣ እንደኔ ባለ እግረኛ እግር ተረግጦም፣ በባለግዜዎች
ረግጦም ባጠቃላይ ረግጦም ሆነ ተረግጦ፣ አልያም ረጋግጦ ተወልውሎ ሲቀባባ ይወዛል።
ድህነትና ተስፋ ማጣት ያጎሳቆለው ፊት ግን ምን ቢቀባቡት አይወዛም። ችግሩ ጥልቅ ነዋ!
ህመሙ ከቆዳ ይጠልቃል! ጉዳቱ የነብስ ነው።
ከኮሌጅ ከተመረቅኩ ስንት ዓመት ሆነኝ? እሯ........! ሚስት ሳላገባ ፀጉሬ ገባ፣ አይኖቼን
ባይኔ ሳላይ በመነፅር ታገዘ፣ ። ምነው ግን ይህ ብሶት ቢቀርብኝ??
ከገባሁበት ሆቴል በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ በመታጠብ ያረጠብኴቸውን እጆቼን እያራገፍኩ
ክትፎ አዘዝኩ።
"ኖርማል፣ ስፔሻል?" አስተናጋጇ ጠየቀቺኝ
"ኖርማል፣ ኖርማል" አልኩ አስረግጬ
"ጥሬ፣ ለብለብ፣......" አላስጨረስኳትም
"ጥሬ!"
ያዘዝኩት እስኪቀርብ ወጪ ወራጁን እያየሁ ድምቅ ብላ የተወለወሉ መጫሚያዎቼን
ያጠለቁ ረዣዥም እግሮቼን አነባብሬ በሃሳብ ስዛብር አንዲት ብርማ ቆንጆ የቤት መኪና
ወደ ሰፊው ግቢ ገብታ ጥላ ተሻምተው ከቆሙ ሌሎች ሁለት መኪኖች ጎን ስትቆም
ከመስተዋቷ ላይ አርፎ የሚንፀባረቀው የፀሀይ ጨረር ዓይኖቼን ስለወጋኝ በስተግራዬ ካለው
ወንበር ላይ ቦታ ቀይሬ ቁጭ አልኩ። ያዘዝኩትም ምግብ ስለቆየ ከዚህችው መኪና ውስጥ
ወዳሉት ጥንዶች ሳልፈልገው አይኖቼም ቀልቤም አርፎ ነበርና ሁኔታቸው ገርሞኝ ነበር።
ሁለቱም ደጋግማው ወደ እኔ እያዩ የሆነ ነገር ያወራሉ። ትንሽ ዘግየት ብዬ ስመለከትም
አይኖቻቸው እኔ ላይ ደሞ መልሰው እርስ በእርሳቸው ይሆናል። የቀረበልኝን ምግብ
ለመጀመር እንደወተት ከነጣው እንጀራ ጥግ ላይ ሚጥሚጣ በትኜ በለምለሙ እንጀራ
የናፈቀኝን ክትፎ ጠቀም አድርጌ ጠቅልዬ አንዴ እንደጎረስኩ በዚህችው መኪና ውስጥ
ከሚያሽከረክረው ጎን ተቀምጣ የነበረችው ወጣት ልጅ ከመኪናው ወርዳ እኔ ወዳለሁበት
ስትመጣ ውበቷን እያየሁ የሰርቅ ዳንዔል "ቆንጆዎቹ" የሚለው ከረዥም አመታት በፊት
ያነበብኩት መፅሀፍ ትዝ እያለኝ ነበር።
እረ ይሄ ብቻ አይደለም! "The beautiful ones are not yet born" የሚል አንድ ልብ
ወልድም ማንበበቤ ትዝ አለኝ። ይቺን አይነት ቆንጆ ልጆች መወለዳቸውን ቢያይ ኖሮ ያ
ጋናዊ ደራሴ ቆንጆዎቹ መወለዳቸውን የሚገልፅ ሌላ መፅሀፍ ባስነበበን ነበር።
ከመስተዋቱ ላይ ተብረቅርቆ ወንበር ካስቀየረኝ የፀሀይ ነፀብራቅ ይልቅ በደመቀ ፈገግታ
ወደ እኔ የምትራመደውን ሳይሆን የምትሰፈውን ወጣት ሴት ላይ አይኖቼን ተክዬ ሶስተኛ
ጉርሻዬን እንደጎረስኩ ለካ ወደኔው ኖሮ የምትመጣው የበረንዳውን ደረጃ እየወጣች
"ጋሼ!?" አለቺኝ ። ግራ ተጋብቼ ግራና ቀኜን ተገላመጥኩ። ከጠረጴዛዬ ላይ ከተቀመጠው
ክትፎ የያዘ ትሪ እና ከውሃ በብርጭቆ በቀር ማንም የለም።
ፍልቅልቅ ብላ እየሳቀች ከፊት ለፊቴ ቆማ
"ጋሼ እንዴት ነህ? አላወቅከኝም አይደል?" ተጠምጥማ ሳመቺኝ ። ግራ በመጋባት ቆሜ
ተሳምኩላት።
"ይ.....ይቅርታ ተሳስተሽ እንዳይሆን። አላወቅኩሽም! "
"እኔ አውቄሀለሁ! ይባስ ብላ አቅፋኝ አንገቴ ስር ገብታ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ግራ ገባኝ።
ካንገቴ ተላቃ
አይኖቿ ላይ አርጋው የነበረውን ቡናማ የፀሀይ መነፅር አውልቃ እንባ ባረጠባቸው ሌጣ
አይኖቿ እያየቺኝ
" አሁንስ? አወቅከኝ?" ፈገግ እንደማለት ብላ ጠየቀቺኝ።
"አምላ..............ኬ! ፍ........ቅር!?" አልኳት ሰውነቴን እንደመንዘር እያለው። አሁን እኔ ነኝ
ያቀፍኳት ። ሳላውቀው እንባዬ ወረደ ።
"ፍቅር!? " ድንጋጤ ወሮኝ ቀጠልኩ 'በህልሜ አይደለም አይደል? " አልኳት።
"ኖ! አይደለም ጋሼ!? እውን ነው! " መኪናውን ያሽከረክር የነበረው መልክ መልካም ወጣት
ምን ግዜ ካጠገባችን መጥቶ እንደቆመ ሳላውቅ ጥቅልል ናፕኪን ሲሰጣት ከውስጡ መዛ
መጃመሪያ ለእኔ ሰጥታኝ ስታበቃ ለርሷም ወስዳ አፍንጫዋንና አይኖቿን አባበሰችበት።
"ተዋወቀው ጋሼ? ሄኖክ ይባላል! እጮኛዬ ነው" በአክብሮት እጅ ነስቶኝ ተዋወቅን።
"አምላኬ! እንዴት አወቅሺኝ ግን? ስንት ዓመት ሆነው? ሃያ አይጠጋውም" ጠየኳት።
እንደልጅነቷ ተሽኮርምማ ሳቀችና አሁን ሃያ ሁለት ዓመት ሆነኝ። ያኔ ስታውቀኝ ስድስት
አመት አልሞላኝም ነበር" ብላኝ አትኩራ አየቺኝና አይኖቿ እንባ ሞልተው መልሳ እቅፍ አርጋ
ሳመቺኝ። ከትላልቅ ዓይኖቿ ወፋፍራም የእንባ ዘለላዋች እርግፍ፣ እርግፍ ሲሉ ፊቷን አባብሳ
"ጠረንህ እንዳለ ነው! ያኔ መጀመሪያ ቀን አቅፈህ ይዘኽኝ ሄደህ " ምን ልግዛልሽ?" ስትለኝ
"አቡ ወለድ" ስልህ ምን እያልኩ እንደሆነ መለየት አቅቶህ ግራ ስትጋባ። ልክ የዛን ለት
አቅፈህ ደባብሰህ ስትስመኝ የነበረው ደስ የሚል ጠረንህ ዛሬም እንዳለ ነው። እየበላህ?!
አለቺኝ። ምግቡን ትቼ ከእነኛ ልዩ አይኖቿ ውስጥ የኔን የወጣትነት ዘመን፣ የእርሷን
የጮርቃነት ግዜ እንደ ፊልም ወደ ኋላ አጠንጥኜ እያየሁ ።
*
*
*
ፍቅርን የማውቃት ትኩስ የኮሌጅ ተመራቂ ሆኜ ግቢውን እንደለቀቅኩ ስራ እስካገኝ ድረስ
ከተጠጋሁባቸው የእናቴ ዘመዶች ቤት በከረምኩበት ግዜ ነበር። ከዚሁ ዘመዶቼ ቤት ፊት
ለፊት ካለ የቆርቆሮ አጥር ከነበረ ግቢ ውስጥ የግቢውን በር ገርበብ አርጋ የምትቆም
በግምት አራት ወይም አምስት ዓመት የሚሆናት ቅላቷ ወደ ቢጫነት የሚያደላ፣ ስስና ሉጫ
ፀጉር የነበራት ፣ ሌባ ጣቷን ትናንሽ ከናፍሯን ፈልቅቃ በማፈር ስሜት አፉዋ ውስጥ
የምትከት ልጅ ነበረች። ስገባና ስወጣ በትንሹ በተከፈተው በር በኩል ብዙ ግዜ ቆማ
ስለማያት በአይን ተላምደን
"ሚሚዬ ደና ነሽ?" እላታለሁ። አትመልስልኝም። ይልቅ ትሽኮረመምና ዝም ብላ እስክርቅ
ታየኛለች። ትንሽ ሰነባብቶም ድንገት ያላየኋት ከሆነ
"ጋሼ?!" ስትል ትጠራኝና እንደገና ደግሞ አፍራ ትሽኮረመማለች። አዘውትራ በር ላይ
የመቆሙዋ ሚስጥር ግራ ሲገባኝ አንድ ቀን ለታ ቆም አልኩና
"ሚሚዬ ነይ እስኪ?" አልኳት ። አመነታች። ተሽኮረመመች፣ ግቢ ውስጥ ወደ ኋላዋ አየች
ትንሽ ቆይታ መጣች። እቅፍ አርጌ ስሚያት
"ማነው ስምሽ?" ስል ጠየኳት። ጠቋሚ ጣቷን አፏ ውስጥ ጨምራ ለራሷ ብቻ በሚሰማ
ድምፅ አቀርቅራ
"ፍቅል" አለቺኝ
"ማን?" ለማጣራት ጠየኳት።
"ፍቅል" ደገመችው
"ኦውውውው! ፍቅር ነው ስምሽ?" አሁንም እፍረትና መሽኮርመም እንደያዛት አቀርቅራ
"ሃዎ" አለቺኝ። ቁጢጥ ካልኩበት ሆኜ እንዳለሁ
"ለምንድነው ሁሌ እዚህ ቆመሽ የማይሽ?" ቀና ብላ አይታኝ
"አባዬን እየጠበኩ" አለቺኝ ተኮላትፋ በሚጣፍጥ አን
ደበቷ ። ቀና ስትል ነበር እስከዛሬ ልብ
ብዬ ያላየሁትን ለየት ያለ ቀለም ያላቸውን አይኖቿን ያስተዋልኩት። አንደኛው ቡናማ ሲሆን
ሌላኛው ሰማያዊ ነበር። በሁኔታው ተገርሜ
"ዓይኖችሽ ደሞ እንዴት ነው የሚያምሩት!? ደስ ሲሉ! እንዳንቺ አይነት ዓይኖች በኖሩኝ"
ስላት የልጅነት ፊቷ እንደሙሉ ጨረቃ ሲበራ አስተዋልኩት። ያልጠኑ ለጋ እጆቿን አፈራርቄ
እየሳምኩ
"አባትሽ የት ሄዶ ነው የምትጠብቂው?"
"ዘመቻ!" አለቺኝ
"ዘመቻ ምንድነው?" አልኳት። አልመለሰቺልኝም። እኔም አላስጨነቅኳትም ። በስተማዶ
ያለውን ሱቅ እያየሁ
"ምን ልግዛልሽ?" ስላት መልስም ሳትሰጠኝ ከግቢ ውስጥ
"ፍቅር! የት ነው ያለሺው?" የሚል ድምፅ ስትሰማ ከእጄ ውስጥ ሹልክ ብላ ወደ ግቢ
ለመግባት ስትጣደፍ ካንዲት እንደ ጅማት ከቀጠነች ፣ ሻርፕ ነገር ካጣፋችና፣ አከታትላ
አፏን በሻርፗ አፍና ከምትስል ሴት ጋር ተገጣጠመች።
"አትውጪ አላልኩሽም?" ተቆጣቻት።
"እንደምን አደርሽ? እናቷ ነሽ? አትቆጫት እኔ ሰላም በይኝ ብያት ነው ። በአይን ስንተዋወቅ
ቆየን፣ ዛሬ ነይ ጨብጭኝ ብያት ነው" አልኳት እየሳ'ኩ።
*
*
እናቷን አስፈቅጄ አቅፊያት ባሻገር ወደሚገኘው ሱቅ ይዣት ሄጄ
"ምንድነው የምትፈልጊው?" አልኳት
"አቡወለድ" ድምፆን ዝቅ አርጋ አቀርቅራ ስለምታወራ በመከራ ነበር የሰማኋት። እሱንም
ባለሱቁ ከድር አግዞኝ ነው። አንዳንድ ሰው ጎበዝ ነው። እንደ ልሳን መተርጎም የልጅ አፍን
መተርጎም ይችላል። ነገሩ ሁለቱም የመላእክት ቋንቋ አይደል!
ግን ግን ጣፋጭ ልጅነታችንን ማነው የሚነጥቀን? ኮልታፋ አንደበት፣ ንፁህ ልብ፣ ጭንቀት
አልባ ኑሮ፣ ቅዠት አልባ እንቅልፍን ማነው የሚወስድብን??? ልጅነቴ፣ ልጅነቴ፣........
ብስኩቱን ብቻ አልነበረም የጋበዝኳት ፍቅርን። ምሪንዳም ጭምር እንጂ! አባቴ ከሰጠኝና
ቆጥቤ ለሻይም፣ ለባስም፣ ለፎቶኮፒም ከማረጋት ሃምሳ ብር ላይ ነበር ለፍቅር የፍቅር
ግብዣዋን በማለዳ "ደፍ" ያረኩባት። ከደስታዋ ብዛት ነብስም አልቀረላት ነበር። ከድር
መልሱን እስኪያዘጋጅልኝ ድረስ እርሷ ብስኩቷን በቀኝ እጇ ፣ ቀኝ እጄን በትንሽዬ ግራ እጇ
ይዛ እኔ ደሞ ተከፍቶ ቆርኪው የተገጠመበትን ሚሪንዳ በግራ እጄ ይዤ ትጠብቃት
ወደነበረችው ሳል ያደከማት ብቻ ሳትሆን ያሰለላት "እፍ ቢሏት እልም" ከምትል እናቷ ጋር
አድርሺያት አጎንብሼ ክብ ቢጫ ፊቷን ስሜ ምሪንዳውን አስጨበጥኳት።
"በይ ቻዎ ፍቅር እንገናኛለን" አልመለሰቺልኝም። ይልቅ በስስት ቁልቁል የምታያት እናቷ
ደጋግማ ደረቅ ሳል ስላ ስታበቃ
"አስቸገረችህ አይደል? እግዚአብሔር ይስጥልኝ!" አለቺኝ ጉርጉድ ያሉት አይኖቿ በደስታ
በርተው። እኔ የምለው ሰው ግን ለምንድነው ከራሱ በላይ የወለደውን ሲወዱለት ደስ
የሚለው??
ከዛ በኋላ ፍቅርን ያገኘኋት ከሶስት ቀን በኋላ ነበር። ዘወትር የምትቆምበት ስፍራ በትንሹ
በተከፈተው በር ስር ቆማ ቢጫና ቡናማ አይኖቿን እያቁለጨለጨች። ፊቷ ላይ የደረቀ እንባ
መስመር ሰርቷል ። እጆቿ አቧራ ልሰዋል። እንደ አዋቂ ጥልቅ ሃሳብ ውስጥ ገብታ
አመልካች ጣቷን አፏ ውስጥ እንደሻጠች መሬት መሬት እያየች ቆማለች። ስላላየቺኝ ቆም
ብዬ
"ፍቅል" አልኳት በራሷ አጠራር። ስታየኝ እምቡጥ ከንፈሯ ፍልቅቅ ብሎ ተከፍቶ ምስር
የሚያካክሉ የወተት ጥርሶቿ አንፀባረቁ። ወደ ኋላ ዞር ብላ ተገላምጣ በግማሽ በተከፈተው
በር ሾልካ ወደ እኔ መጣች። አቅፌ አንስቼ ደጋግሜ ስሚያት
"ዛሬስ ምን እየሰራሽ ነው በር ላይ ?"
"አባዬን እየጠበኩ" ልስልስ ባለ ዝግተኛ ድምፅ መለሰችልኝ። ግራ ተጋብቼ ዝም አልኩ።
በኋላ ግን ከባለሱቁ ከድር እንደሰማሁት አባቷ በመኪና አደጋ ሰበብ በነብስ ማጥፋት
ወንጀል ተፈርዶበት ወህኒ እንዳለ አጫወተኝ። ከታሰረ አንድ አመት ሆኖታል።
"ምን ሆነሽ ነው ያለቀሺው ደሞ?" ፊቷ ላይ የደረቀ እንባዋን በጣቴ እየነካካሁ
እየጠቆምኳት።
"አላጫውትም ብለውኝ"
"እነማን?" ስል ጠየኩ
በትንሽዬ ጣቷ ከማዶ ላይ አሸዋማውን አፈር እየካቡ የሚጫወቱትን ከእርሷ ትንሽ በእድሜ
ከፍ የሚሉ ልጆችን እየጠቆመችኝ
"እነሹ" አስከትላም "ዓይንሽ ያሽፈራል ይላሉ" ብላኝ ለምቦጯን ጣለች። ቅድም እንደ አዋቂ
ያስተከዛት ጉዳይ ይሄ እንደነበር ታወቀኝና ውስጤ በሃዘን ተመሳቀለ።
"ዝም በያቸው! ያንቺ አይነት የሚያምር አይን ስለሌላቸው ነው! ብዬ ሁለቱን አይኖቿን
" ቆይ ልሳምልሽ" ብዬ እያፈራረኩ ደጋግሜ ሳምኩላት።
ደ..........ስ አላት! ጥላው የነበረው ፊቷ ሲሰበሰብ፣ ተክዞ የነበረ ትንሽዬ ልቧ በኩራት
ሲያብጥ ፣ ሁለት ቀለም ያላቸው ያይኖቿ ብሌኖች ሲሰፉ እዛው ሆኜ መስክሪያለሁ። ፍቅር
ታከመች! አይኖቿን የሚወድላት፣ የሚያምሩ ዓይኖች እንዳሏት የነገራት፣ አፈራርቆ የሳመላት
አንድ ሰው አገኘች።
ከዛ በኋላ ለሁለት ወር ያህል እኔና ፍቅር ጔደኛሞች ሆንን። እዛው ሰፈር ካሉት የዘመዶቼ
የልጅ ልጆች ጋር ወስጄ ጔደኛ አደረግኳት። ቀድሜ በነገርኳቸው መሰረት ዓይኖቿን
"ሲያምር!" እያሉ አደነቁላት። ጥቂት ዘግይቶ እኔ ክፍለሃገር ስራ አግኝቼ ስሄድ በቁም ነገር
ፍቅርንና እናቷን ተሰናብቼ ነበር። ፍቅር አለቀሰች። ተመልሼ እንደምጠይቃት ብነግራት፣
ባባብላትም እምቢኝ አለች። እንዴት ትመን? አባቷም ድንገት ሄዶ በዛው ከቀረ ዓመት
አለፈው። ዘወትር ማለዳ አንስቶ ትጠብቀዋለች። ግን አልተመለሰም። እናቷ "ዘመቻ ሄዷል"
ነው ያለቻት። ታስሯል ላለማለት። አሁን ደግሞ እኔን ጔደኛዋን ልታጣ ነው። ፍቅር አልቅሳ
ደክሟት እንቅልፍ እስኪይዛት ጠብቄ ነበር ግንባሯን ስሚያት የወጣሁት። በርግጥ ከነቃች
በኋላ ከእውነቱ ትላተማለች። ከዓመት በኋላ ይመስለኛል እዛ ሰፈር ያሉ ዘመዶቼን ጥየቃ
ስሄድ ባስፈልጋት እርሷም እናቷም አልነበሩም። ከጥቂት ወራት በፊት ሰፈር እንደቀየሩ
ሰማሁ። እዛ ሰፈር በተመላለስኩበት ጥቂት ቀናት ውስጥ ትቆምበት በነበረው ግቢ በር ስር
አይኖቼን ወርወር አደርጋለሁ። ፍቅርን ግን ለብዙ አመታት አላየኋትም ነበር። ይህው ዛሬ
የክትፎ አምሮቴን ልወጣ እርሷም ፍላጎቷ ከአቡወለድ ብስኩት ወደክትፎ አድጎ ልትበላ፣
ካባቷ ጥበቃ ወደ ሰርጔ ቀን ጥበቃ አድጋ ተገናኘን። አጋጣሚው ህልም እየመሰለኝ
"እንዴት ልታውቂኝ ቻልሽ ግን? እንዴት አስታወሺኝ?" አልኳት።
"እንዴት እረሳሀለሁ ጋሼ? ሁለት ቀለም ያላቸው አይኖቼን እንደሚወድልኝ የነገረኝን ሰው
እንዴት ረሳዋለሁ!? ስትነግረኝ እኮ ስስ ትንሿ ልቤ ላይ ነበር ለዘላለም የፃፍከው። አይኖቼን
ስትስምልኝ አይኖቼን መሳሜ ብቻ አልነበረም የተሰማኝ። ነብሴንም ነበር የሳምካት።
በቃላትህ አከምከኝ ። አሁን ሰዎች በአይኖቼ ቀለም ተገርመው ትኩር ብለው ሲያዩኝ አንተ
'ደሞ እንዴት የሚያምሩ ዓይኖች ነው ያሉሽ? እንዳንቺ አይነት የሚያምሩ ዓይኖች በኖሩኝ ።
ዝም በይ ቀንተውብሽ ነው' ያልከኝ ቃላት እዝነህሊናዬ ውስጥ ያስተጋባል። ልዩና የሚያምሩ
ዓይኖች እንዳሉኝ ስለማውቅ ኮራባቸዋለሁ። እድሜ ላንተ! ጋሼ.....ደህና ነህ ግን?"
ጉንጬን እየዳበሰች ጠየቀቺኝ።
*
*
*
እነርሱ ያዘዙት ምሳ ሲመጣ እየተጫወትን አብረን መመገብ ጀመርን ። ስለ አባትና እናቷ
ደህንነት ልጠይቃት አስቤ ጥሩ ያልሆነ ዜና ብሰማ የጨዋታውን ድባብ ሃዘን ያጠላበታል
ብዬ ስለፈራሁ ለግዜው እሱን ትቼ ወደ እጮኛዋ እያየሁ
"እድለኛ ነህ! ይችን የመሰለች ቆንጆ ልጅ ልታገባ ነው!" አልኩት ። ሲስቅ ሚጥሚጣው ትን
ሲለው አይታ ውሃ የያዘውን ብርጭቆ እያቀበለችው እርሷም በተራዋ ስቃ
"ዛሬ እኮ አስቀያሚ የለም ጋሼ?! ልጆቹ ሁሉ ቆንጆዎች ናቸው" አለችኝ። የጎረስኩትን ውጬ
ሳበቃ
"አዎ ቆንጆዎች ናቸ
ው ግን እንዳንቺ ዓይኖች ያሉ ልዩና ውብ አይኖች የላቸውም" አልኳት
እየሳቅኩ
የቆረሰችውን ለምለም እንጀራ በለምለም ረዣዥም ጣቶቿ መካከል እንደያዘች ፍልቅልቅ
ብላ አይኖቿን አይኖቼ ላይ ተክላ በምስጋና እና በመነካት ድምፀት
"ጋ.................,ሼ! " አለቺኝ።
*
*
*
*
"ቆንጆዎቹ ገና አልተወለዱም" ሲል ለፃፈው ደራሲ እባካችሁ ሌላ ፅሁፍ እንዲያስነብበን
እንዲህ ብላችሁ ንገሩልኝ።
ቆንጆዎቹ በርግጥ ተወልደዋል!


ሸጋ ቀን!💚

@wegoch
@wegoch
ወገግታ የስነ ጽሑፍ ወ ሥዕል ምሽት
ሰኞ ጥር 18 በ ሃገር ፍቅር ትያትር ቤት ከ 11:00 ጀምሮ

@wegoch
@getem
ባቡሬ !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ቀጠሮ አለብኝ። ለዛውም የማይቀር ቀጠሮ !
ና ጋብዘኝ...ሳይሆን...ና ልጋብዝህ😃 የሚል አስደሳች ቀጠሮ !
ከሰሚት ተነስቶ ወደ ጦር ሀይሎች የሚጓዘውን ባቡር ትኬት ለመቁረጥ አስቤ በብርማ የግድግዳ መልክና በቀይ የጣርያ ክፈፍ የተሽሞነሞነችው ክፍል አመራሁ።
ከጠባቧ መስኮት ባሻገር አንዲት በአረንጓዴ ሻርፕ ፊቷን በከፊል የተጀቦነች ጠይም ሴት አለች። ቀና ብላ ሳትመለከተኝ.. .ስንት ትኬት? አለችኝ...
አንድ ነው.. ..
ወድያው ትኬቱን በቀኝ እጇ መልሱን በግራ እጇ አፈፍ አድርጋ ...እንካ.. .አለችኝ።
ፍጥነቷ አስገርሞኝ.. .ትንሽ በአንክሮ አየኋትና
"ባቡሯ ትዘገይ ይሆን?" ...ብዬ ገና ጥያቄ ከማከሌ ባለ አንድ ተጎታቿ ባቡር ረዥም ክላክስ ለቃ መቆሟን ተመለከትኩኝ።
ይልቅ ሳታመልጥህ ድረ....
ላፍ አልኩኝ....ባ....አ
...ት.. .. የሚሉትን የሴትየዋን የመጨረሻ ፊደላት በርቀት ነው የሰማሁዋቸው። እንደውም ከችኮላዬ የተነሳ አንድ በነተበ የጃፖኒ ጨርቅ የብብቱን ጭገር የሚያሳይ ሹፌር የሚያሽከረክራት ታክሲ ለትንሽ ጨልፋኝ ነበር... ሹፌሩ በአፉ ጓዳ ውስጥ የቋጠረውን የተፈጨ ጫት ለድፎብኝ እዚህ በማይነገሩ የስድብ ውርጅብኞች ተቀበለኝ።
አልሰማሁትም !
~ቀልቤ ያለው ከባቡሯ ላይ ብቻ ነበር...
ወድያው የቆመችው ባቡር ልትንቀሳቀስ ስትል ዘልዬ ገባሁ... በሩ የግራ እግሬን ተረከዝ እንቅ ሲያደርገኝ ተሳፋሪው እኩል ተንጫጫ ...በሯ መልሶ ሲከፈት ከእገታዬ ተላቀኩኝ።
የአዲስ አበቤ ህዝብ ብዛት እንደ ከዋክብት አለቅጥ የበዛ መሆኑን በደንብ የተረዳሁት ታድያ ይሄኔ ነበር ።
ፊቴን ከባቡሩ መስኮት ስለለጠፍሁኝ በውጭ በኩል ለሚመለከተኝ ሰው መስታወቱ ላይ ፊት የተሳለ 😃 ነበር የሚመስለው ።
ኳስ ተራግጠን መጣን እያሉ የሚጯጯሁት ወጣቶች ዙሪያን ከበውታል ...አንዱ የብብቱ ሌላው የሸራ ጫማው ጥፊ ይደርሰኛል... በግራ በኩል አንዲት ሴት አሳዝኛት ነው መሰል ..."ና እዚህ ጋር ትንሽ ቦታ አለልህ !" ብላ ጋበዘችኝ...በስንት ዱላ ቀረሽ ግፊያ ተሽሎክሉኬ ስሯ ደረስኩ።
"አይዞህ የመጀመርያህ ነው በባቡር ስትሄድ?:"
"ኸረ አይደለም !...ከአንዴም ሁለቴ ሄጃለሁ ...ሰው ግን እንደዚህ አይበዛም ነበር...ጭራሽ ወንበር ሁሉ ይዤ ነበር ስጓዝ የነበረው"
"አንተ አለመኛ ነህ እቴ? ...ባቡር ውስጥ ወንበር አለ እንዴ? ..." ሴትየዋ እንደ አዲስ ተሳፋሪ ዞር አለች 😃
"አንተ እውነትም ወንበር አለ !.".. ለብዙ ደቂቃዎች ያህል የተገረመች መሰለች።
ባቡሯ ተሳፋሪዎች እንስሳ ይዛችሁ እንዳትገቡ ምናምን ከሚለው ዝብዘባዋ ቀጥሎ ባምቢስ ጋር ቆመች...ሌላ የህዝብ ማዕበል ተጨመረ...አንዳንዱ ደግሞ ሲገባም ሲወጣም ትዕግስት የሚባል ነገር አልፈጠረበትም...ደርምሶህ ይገባል...ደረማምሶህ ይወጣል 😊 ...ከዛ ዞር ብሎ "ይቂርታ ቢራዘር" ይልሀል!
እንቅርታም !! ብለህ ብትሰድበው ሁሉ ደስ ይልሀል...ግን ድጋሚ አይኑን እንኳ ላታየው ከምትችለው ሰው ጋር ምን ግብግብ አስጀመረህ? ...ባልሰማ ላሽ ትለዋለህ :)
"ወንድሜ ተራራቅን አይደል ?" ...አለችኝ ከርቀት በሚሰማ ድምፅ...ቅድም ወሬያችንን ካሟሟቅነው ሴት ጋር ቦታ ተራርቀናል...እሷ ሰው ሊውጡ በሚመስሉ ወደል ጎረምሳዎች መሀል ገብታ ወጥ ሆናለች...ባቡሩ ነቅነቅ ባለ ቁጥር ማገሩን አሹሎ በልብስ ውስጥ የሚነቀንቃት ሰው ላይጠፋ እንደማይችል አስቤ አዘንኩላት ...ከኋላዋ የቆመው ጎረምሳ ደግሞ እጁ እንደ ጎልያድ ክንድ የገዘፈ ነው...በሲጃራ የበለዙ ከንፈሮቹን ገልጦ ወደኔ አቅጣጫ እየማተረ ፈገግ ሲል ሰይጣን ሲኦል የመጣ እንግዳውን ሲቀበል የሚያሳየው ፊት መሰለኝ። ከኔ ጀርባ ከቆመው ሌላ እሱን መሰል ጓደኛው ጋር ይነጋገራሉ። ጅላስ በወሬ ተወጥራል... ፈትሺው ምናምን የሚል ቃላትን ይወራወራሉ። ከሚያወሩት የእርድና ቋንቋው ገሚሱ ሳይገባኝ ያልፈኛል።።ባቡራችን ትነጉዳለች.. ..
እነሆ!
የታገሰ ከሚስቱ ይወልዳል.. .እንዲሉ ታድያ እኔም የዛን ህዝብ ግፊያ ተቋቁሜ ጦር ሀይሎች ደረስኩና እፎይ አልኩኝ...ያ ጅብ ፊት ጎረምሳ ሰረቅ አድርጎ አየኝና ለጓደኛው በጆሮው በኩል ተንሾካሹኮ ከኔ ሌላ መንገድ ቀይረው ተጓዙ...ይሄኔ ያ ቀዩ ልጅ የዝንጀሮ ቂጥ ይመስላል ብሎ ጓደኛውን ለማሳቅ እየሞከረ ይሆናል መሰለኝ።
ጥቂት እንደተጓዝኩ ጦር ሀይሎች ተቀምጦ ለድራፍት ግብዣ የሚጠብቀኝን ጓደኛዬን አስቤ ስልክ ልደውልለት እጆቼን ወደ ኪሴ ሰደድኳቸው። አየር ዘግኜ ወጣሁ.. .የኪስ ቦርሳዬም ስልኬም በቦታቸው አልነበሩም።
የዛ ጅብ ፊት ጎረምሳ የለበጣ ሳቅ ፊቴ ላይ ዳግም መጥቶ ተገሰጠ !
ተበላሁ :)

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ኑ ደም በመለገስ በክቡሩ ስጦታ ክቡሩን የሰው ልጅ ሕይወት ከሞት እንታደግ...!

የካቲት 1፣2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በመገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማው አጠገብ!
ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድዎን ይዘው ይመጡ!

ጉራማይሌ የበጎ አድራጎት ድርጅት!!!

@Guramayelie

+251955431015

@GURAMAYLIE
ኑ ደም በመለገስ በክቡሩ ስጦታ ክቡሩን የሰው ልጅ ሕይወት ከሞት እንታደግ...!

የካቲት 1፣2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በመገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማው አጠገብ!
ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድዎን ይዘው ይመጡ!

ጉራማይሌ የበጎ አድራጎት ድርጅት!!!

@Guramayelie

+251955431015

@GURAMAYLIE
Fifty shades of him
'
'
አለሜ የምለው እርሱ "የኔ ጨረቃ " ብሎ ያለኝ ለታ ስሸሻት የኖርኳት የምጠላት
ጨረቃ ፊት እስክቆም ድረስ የአምስተኛ ክፍል ሳይንስ መምህራችን << ፀሃይ
ትልቋ ኮከብ ናት .... ጨረቃ ደግሞ ከእርሷ ብርሃን ትሰበስባለች >> ካሉን ቀን ጀምሮ ብርሃን መስረቋ አናዶኝ ጨረቃን ጠምጄ ያዝኳት ። ስንቴቴ " የዛሬው ብርሃንስ ጤፍ ያስለቅማል " በተባለለት ምሽት ሰማይ ኮርኒስ ላይ የተንጠለጠለች የብርሃን ኳስ ፅልመቱ ላይ የተንሰራፋች ለታ እርሷን
ለመሸሽ ስሮጥ አምጪ የተባልኩትን የታናሽ እህቴን ወተት ንጬ ቅቤ ወጣለት ። እናቴም የተቀበለችኝን የወተት እቃ ከፍታ እያየች << ብራ ጨረቃ እየጠበቀማ የሚያበር ጋኔል ሰፍሮብሻል >> ስትል የምሮጠው ጨረቃ ወለል ስላለች መሰላት እንጂ ከእርሷ እየሸሸሁ እንደሆነ አታውቅም ነበረ ። የኋላ ኋላ የጠመድኳት ጨረቃ መልሳ ጠምዳኝ ነው መሠል የሃምሌ ጭጋግ በጋረደው ምሽት መሃል አግኝቶኝ "ቤት ሄደን ጃኬት ደርቤ ልሸኝሽ " ያለኝን የሰፈሬን ጎረምሳ ተከትዬ ቤቱ ደርሰን ጃኬት ይደርባል ብዬ ስጠብቅ ልብሱን ሁሉ አውልቆ ርቃኑን ወደ ቆምኩበት መጥቶ ወተቴን ተቀብሎኝ ጠረጴዛ ላይ
አስቀምጦ ልብሴን ሲያወላልቅ እንደበግ እየተነዳሁለት የሆነው ሁሉ ሆኖ "
አይዞሽ" እያለኝ አስሬ እንደምንም ለባብሼ ከቤቱ ስንወጣ ቀና ብዬ ሳይ ቅድም የጋረዳትን ጭጋግ ገፍፋ የወጣች ሙሉ ጨረቃ ቁልቁል ስታየኝ አየኋት ። የያዘኝን እጁን መንጭቄ በጉያዬ መሃል ያለውን ህመም ችዬ እየተደነቃቀፍኩ ለመሮጥ
ስንቧቸር በብሩህ ጨረቃ ቀናት የማይነሳሳ ሴትነቴን በደመና ተከልላ ያታለለችኝ ሙሉ ጨረቃ ላስታውሰው እንኳ ለማልሻው ደብዛዛ ሰው ድንግሌን እንደሸለመች እንዳስነጠቀችብኝም እያሰብኩ ነበር ። እና " የኔ ጨረቃ " ያለኝ ቀን ዘመናት በመሃላችን በኩርፊያ ያለፉት እኔና እርሷ ማዶ ለማዶ ፊት ለፊት ተፋጠጥን ። አልጠላኋትም የዛን ቀን አልሸሸኋትም ያን ማታ ብቻ ግን እርሷን ሆንኩላት ፤ እኔንም የሆነች መሰለኝ ። በእኔና በእርሱ መካከል የነበረው የቦታ ርቀት በዘመን ሁሉ የሚሰፈር ይመስለኝ ነበር ። በቃ እርሱን የማቀርብበት ከእርሱ የምገናኝበት ምንም መንገድ የለም
ብዬ ተስፋ ከቆረጥኩ ብሰነብትም አለሜ አፍ አውጥቶ <<አንተያይም ተስፋ
ቁረጪ>> ሲለኝ ቅስሜ ደቅቆ ተሰበረ ።
ገላዬ የናፍቆት ብርድ ያቆራመተው ነው ። በእርሱ መታቀፍ በእርሱ መነካት ብቻ
ይፈልግ ነበር። ጭኔ ላይ ያቆጠቆጡ ጥቃቅን ፀጉራት ሲቆሙ ይታወቀኛል የጡቴ ጫፎች ሲሾሉ ይታወቀኛል ፡ ብሽሽቴን ሲሞቀኝ ይታወቀኛል ፡ ገላዬን የኔ ያልሆነ ያህል ለመቆጣጠር ሲያቅተኝ ። እየሩስዓለሜ ነበር ። ሰርክ እለት ልሳለመው የማልመው ነክቼው ልፈወስ
ዳብሼው ካለ ከሚመጣው ነገር ሁሉ ልነፃበት የምፈልገው ። ዳስሼው ከቅዱስነቱ ቅንጣት ቆንጥሬ ዘመኔን ሁሉ በደጄ የሚፈስ የቅባ መውደዱን ዘይት ነፍሴን እንዲያረሰርስ ፤ ከአላፊ አግዳሚው መሃል ጨርቁን
ጨብጬ ልፈወስ .... ካለሽበት የምመጣበት መንገድ ጠቧል ሲለኝ ለመላከ ገብሬል አባቴ በእለተ ቀኑ
ነግሬው በግራም በቀኝም የለኝ ካላንተ የማስቸግረው ብዬ ከቅፅሩ ተንበርክኬ
የደጁን ጠጠር ዘግኜ ነጠላዬ ጫፍ የቋጠርኩት ቤቴ ስመለስ ጎረቤቴ ለሣምንቱ ሰባት ቀናት ሁለት ጡት ያላቸው ሶስት ጀበናዎች አፈራርቃ የምትካድም ። የፋጤና ከድጃን ቀናት የምታከብር ፡ በአርሲዋ እመቤት ምትምል ባለውቃቢ ደግ ሴት የገብሬል ቡና ካልጠጣሽ ብላ ስትበቅተኝ ። እንደታቦት ቀን እየቆጠረች
ከምታወጣቸው ፍንጀሎቿ በአንዱ ያፈላችውን ቡና አቀብላኝ ...ምን አስተከዘሽ ብትለኝ "የምወደው ሰው የሰው ሃገር ቀረብኝ "ብያት እጆቿን ወደ ላይ ዘርግታ መአት አይነት መለአክ መአት አይነት መላይካ እየጠራች በአማርኛ በኦሮምኛ ተማፅኖዋን ስታንበለብል << በየአፍ መፍቻቸው ይሆን የምትፀልይላቸው?> እያልኩ ። የማግሁትን ቡና ሲኒውን ላቀብላት ከተቀመጥኩበት ስነሳ ነጠላዬ ጫፍ ከተቋጠሩ የገብሬል ጊቢ ጠጠሮች መሃል አንዲቷ ጊርጊራዋ ላይ ድንገት ተፈትታ ብትወድቅ ከእጣን ማጨሻዋ ላይ ሃምራዊ ጢስ ሲንቦለቦል አየሁ ...በሰፈሩ ቀድሞ ያልነበረ ጣዕመ አልባስጥሮስ ጠረን ሸተተኝ ። ይህም
ለመምጣቱ ምልክት ሆኖኝ መላዕክት መላይካዎቹ ጭላንጭል ተስፋ ቢያሳዩኝ
ታላቁ ፀገመ እንዳለው ተስፋ መቀነት ሆነኝ ። አመታት እንደቀናት አልፈው ካለሽበት የምመጣበት መንገዱ ሁሉ ቁልፍ ነው ያለኝ አለሜ ሃገር ቤት ድረስ መጣ ፡ ግን የሌላ ሰው ሆኖ ከሌላ ሰው በፍቅር ከንፎ ያለሁበት ከተማ ውስጥ ተገኘ ። ይህን ሳውቅ ምን ከከፍታ ሆነው ወደ ታች ቢወረውሩት እርሱ እንደሁ እንደ ላባ ነው ተችሏቸውም አይሰብሩት ብዬ የታባልኩለት ልቤ እንክት ብሎ ወደ እልፍ ቅንጣቶች ደቀቀ ። እንባዬ በጉንጬ መም ነድሎ እንደ ጤግሮስ ዥረት ሆነ ። ደውሎ <<ላግኝሽ>> አለኝ ግን ላገኘው አቅም አነሰኝ .... ናፍቆቴ ዘመን ተሻግሮ መጥቶልኝ ከኔ ከተማ ላገኘው ላገኘው ጉልበቴ ከዳኝ ላገኘው ወኔዬ ጠፋ የሰው መሆኑን ስሰማ ። የሚሰሙኝን ስሜቶች ስም ልሰጥ ስጥር ከረምኩኝ ቅናት ነው? ፍቅር ነው? በእርሷና በእርሱ የሚሰማኝ ይህ ነገር ምቀኝነት ነው? እያልኩኝ ። ሌት ተቀን ስብከነከን እህህ ብዬ ከረምኩኝ ።
አንድ ቀን መልክት ደረሰኝ
<< በዚህ ፀባይሽ ሳላገኝሽ ልሄድ ነው።>> <<መች?>> አልኩት መለስኩና <<ዛሬ>> አለኝ......ይሄኔ አንጀቴ ተላወሰ
ጥፋተኝነት ተሰማኝ " ከማንስ ጋር ቢሆን ምን አለ አንዴ እንኳ ባየው " እያልኩኝ
ፀፀት እንደጦስ ዶሮ አርባ ዘጠኝ ጊዜ ሲዞረኝ ቤት ገባሁ በረንዳ ወጣሁ ምጥ
እንደያዛ ድርስ እርጉዝ ስንቆራጠጥ ቆይቼ ድንገት ወደ ላይ ቀና ብል ጨረቃ
ከአናቴ ቆማ እኔን በአንክሮ ስትሰልል .....
ልጅነት እንደ ጧት ጤዛ አላፊ ነው ረጋፊ ወጣትነትም እጢ ነው ክው ያሉ ለታ
ጠፊ ... እርሱን በጠበኩባቸው ዘመናት መሃል የታዘብኩት ፍቅርን ከኖሩት በላይ
የናፈቁት ናቸው የሚያውቁት ።ጊዜ አቃጣሪ ነውና ጉርምስናዬን አስጥሎ ምን ለእርጅና ቢድረኝም እንደ አዲስ "ቀን አንድ" ብዬ ዳግም ብጠብቀው ቅር
አይለኝም ። የስልኬ ሰሌዳ ላይ ሚሴንጀሬን ከፍቼ መፃፍ ጀመርኩ ። << አለሜ በሰላም ግባ ... የሆነ ቀን ግን ናልኝ ለእኔ ብቻ ብለህ እኔ ጋር ብቻ
ናልኝ >>

Note :- ናፍቆት ከፍቅር ይበልጣል ።

@wegoch
@wegoch
@paappii
2024/09/25 19:19:04
Back to Top
HTML Embed Code: