Telegram Web Link
#ዛሬ ራስ ሆቴል እንገናኝ!

# ጦቢያ ግጥም በጃዝ 101ኛው ምሽት በራስ ሆቴል ይቀርባል


እንደምነው ሮብ፤ የሃሙስ ጓደኛ ፤
እንገጥማለን ብለን፤ ሸዋ ገባን እኛ! !!!!
ነገር የመጣኝ ቀን ፤ ነገር እገጥማለሁ ፤
ግጥም የመጣኝ ቀን፤ ግጥም እገጥማለሁ ፤
ያገጣጠመኝ ቀን ግጣም እገጥማለሁ ፤
መግጠም ነው እንግዲህ ፤
ከዚህ ወዲያ ስራ ከወዴት ተገኝቶ ፤
አለም አይደለም ወይ ፤
መግጠም መገጣጠም ቁሞና ተኝቶ ።

@wegoch
@balmbaras
ለጁምኣችን!
💚

*በጎ የዋልክላቸው ሰዎች ሁሉን ዘንግተው ከቁብ ባይቆጥሩህ በሰራኸው መልካም
ተግባር ፈጽሞ አትቆጭ።

*አዕዋፋት በጣፋጭ ቅላጼ ሰርክ አየሩን ሕይወት የሚዘሩበት የሚያመሰግናቸው ሰው
ኖሮ አይደለም። ያም ሆኖ ግን ከመዘመር ቦዝነው አያውቁም።

*ሰዎች ላንተ ያላቸው አመለካከት እየቅል ነው

*እንዲሁ የዓይንህ ቀለም ሳያምረው በክፉ የሚመለከትህ አለ


*ጥሎበት ጥሩ እንደሆንክ የሚያስብ አለ

*ሌላው ደግሞ እጅግ በጣም ድንቅ እንደሆንክ ያስባል

*ጭራሽ የማይመለከትህም አለ

*በትክክለኛው ማንነትህ የሚመለከትህ ብቸኛው ፈጣሪ አላህ (ሱ.ወ) ስላለ ሌላው
ትርፍ ነው።

ከ - አሕላም ሙስተጋነሚ ገጽ

ውብ ጁምኣ!💚

@wegoch
@Nagayta
ለቅዳሜዋ! ለሸጋዬዋ!

በውስጣችን መረጋጋት በሚኖርበት ጊዜ ዓለም በሙሉ ውብ ነው።

ስክን ያለች ቅዳሜ!💚💛

@wegoch
@wegoch
@Nagayta
💋💋 የሚነበብ ከንፈር 💋💋
(ሜሪ ፈለቀ)


ያው ጀመራት እነዚህን ጉልላት የመሰሉ ዓይኖቿን ከንፈሬ ላይ ታንገዋልላቸዋለች። እንኳን ለምን ቢሮዬ እንዳስጠራኋት እኔው ራሴ አሁን እዚህ ቢሮ መሆኔን ብጠየቅ የማስታውስ አይመስለኝም።

"ዶክተር? ዶክተር? ዶክተር?” አሁን የት እንዳለሁ አወቅኩ። ግንሳ እነዚህን ዓይኖቿን ካላሳረፈቻቸው እንዴት ነው ከዚህ ሌላ ማሰብ የምችለው?

"አቤት ህሊና?” ያልኩበት ድምፀት ለምን እንደፈለገችኝ እሷ ልትነግረኝ እንጂ እኔ ያስጠራኋት አይደለም የሚመስለው።

" ለምንድነው ያስጠሩኝ ዶክተር? ችግር አለ?” ለምንድነበር ያስጠራኋት? እህህህህ ዓይኗን ከከንፈሬ ላይ ካልነቀለች ለምን እንደፈለግኳት በምን አውቃለሁ? ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እንደትያትረኛ ተንጎራደድኩ(ተንጎማለልኩ።) እኔ ያየኋቸው ጥቂት የኢትዮጵያ ትያትሮች ላይ ተዋናዩ ታሪኩ ላይ የሚጨምረው ምንም ፋይዳ የሌለውና አስፈላጊነቱ የማይገባኝ መንጎራረድ  መድረኩ ላይ አንድ ሶስቴ ይንጎማለላል። እንደዛዛዛዛ አደረግኩ። እኔ ግን ዓይኗን ሽሽት ነው። ለምን እንደጠራኋት አሁን መጣልኝ። 

ህሊና እኔ በማስተምርበት ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ናት። እንኳን እንደእኔ አይነቱን ዓይንአፋር እኔ ነኝ ያለ ጀግና ወንድ ብርክ የሚያሲዝ ህልም መሰል ውበት አላት። እኔ እሱ አልነበረም ችግሬ። ቆንጆ ትሁን ፉንጋ ከሴቶች ጋር ተከባብሬ የኖርኩ ሰው ነኝ። አይደርሱብኝም። አልደርስባቸውም። የህሊና ጉዳይ የተለየ ነው። በገባሁባቸው አራት ክላሶች ሁሌ ከፊት ነው የምትቀመጠው። እሱም ባልከፋ! እነኚህ አደንዛዥ ዓይኖቿን ከከንፈሬ ላይ ለደቂቃ አትነቅልም። በስህተት መስሎኝ ተከታተልኳት…… ሃሃሃሃ አቃቂያለችኝ እንጂ ሁላ…… የመጀመሪያ ቀን እቤቴ እንደገባሁ ከንፈሬን በመስታወት አየሁት። ሆ! …… ለዓመታት በልበ ሙሉነት ያስተማርኩት ሰውዬ መንተባተብ እጀምራለሁ። ላብ ያጠምቀኝ ይጀምራል።…… አንዱን ቀን ክላሱን ሳልጨርስ አቋርጬ ወጣሁ። ሆሆ!

ምንድነው የምላት? እባክሽ ዓይኖችሽን ከከንፈሬ ላይ ሰብስቢልኝ? ማስተማር ስላቃተኝ ዓይንሽን አሳርፊልኝ? ምን አስበሽ ነው እንደዚህ የምታደርጊው?  ኡፍፍፍፍ……

"ዶክተር?” አለችኝ ጀርባዬን ሰጥቻት ለብዙ ደቂቃ መቆሜ ግራ ገብቷት መሰለኝ። ደሞኮ ድምፅዋ ራሱ የሆነ የፈጣሪ ምህረት የሚመስል ለዛ አለው።

"አቤት! እ…… እ…… የጠራሁሽ…” መንተባተብ ሲያስጠላ! ኸረ ዶክተር ትልቅ ሰው አይደለህ ምን ያንተባትብሃል? ራሴን ገስፃለሁ።

"ዶክተር ከንፈርዎትን ካላየሁ አልረዳዎትም።” ምን አለች? ምን አለች? ምን…… ምን?ጆሮዬ ሲሰማ ስቶት ነው።

"አቤት?” አልኳት ዓይኖቿን ሳልፈራ ተጠግቻት። ሳቅ እንደማለት አለች። መሰለኝ።

"ትንሽ የመስማት ችግር አለብኝ። ሲያወሩ ከንፈሮትን ካላነበብኩ ሁሉንም ቃላት ላልሰማ እችላለሁ። ባጋጣሚ ለሁሉም መምህሮቼ ስናገር  ለርሶ ሳልነግር ቀርቼ ነው።”

የባሰው መጣልህ!! 🤔😀

@wegoch
@wegoch
#ነገ 10:00 ሰዓት ጦቢያ ግጥም በጃዝ 100ኛ ወር ክብረ በዓል ይደረጋል

የት:- ኤሊያና ሆቴል
መግቢያ :- 150 ብር

@wegoch
@Nagayta
ለሰንበታችን!
💚


ጋዜጠኛ : - ካንተ የመሥራት አቅም አንፃር የሠራሁዋቸው ሥራዎች ወይም የፃፍኩዋቸው
መፅሐፍት በቂ ናቸው ብለህ ታምናለህ ?
ጋሽ ስብሐት : - አዎ በቂ ናቸው። በተጨማሪም በየሳምንቱ በጋዜጣ ላይ የማወጣቸው
ፅሁፎች ቢሰበሰቡ ብዙ መፅሐፍት አይወጣቸውም?
ጋዜጠኛ : - ሌላ ምን ሠራህ?
ጋሽ ስብሐት: - ኖርኩ !

* * *
( - አይ ጋሽ ስብሐት እውነቱን ነው ከመኖር የበለጠ ምን ሥራ አለ?! )
* * *
[በአንድ ወቅት አሁን ስሙን ከዘነጋሁት ሬድዮ ጣቢያ ጋር ባደረገው ኢንተርቪው የሰጠው
ምላሽ ነበር]


@wegoch
@wegoch
@Nagayta
ለውብ ቀን!
💚

#ትላንት በዚሁ በቻናላችን ቤተሰቦች የተዘጋጀ Hiking ተዘጋጅቶ ነበር ወዴት..? ካላቹኝ ሰሜን ሸዋ ከደብረብርሃን ወደ ደብረ ሲና በሚወስደው መንገድ የሚኒሊክ መስኮት የምትባል እጅግ እጅግ ውብ ቦታ እዚህ ቻናል ላይ ካሉት ቤተሰቦችና ሌሎች ሆንን ባልሳሳት 125 እንሆናለን ረጅምና ፈታኝ የእግር ጉዞ አድርገን ነበር በጣም የሚገርመው ልክ ቦታው ላይ ስትደርሱ ግን ያን ሁሉ ድካማቹን የሚያስረሳ ተአምር ታያላቹ ...ሀሴት ታደርጋላቹ ፣ ትፈነጥዛላቹ ብቻ የላያቹት ሂዱ ና እዩት እውነት ትወዱታላችሁ !

ትላትና ይሄንን ጉዞ አድርጌ ወደ ቤቴ ከመሸ ስመለስ አንዱ ወዳጅ ምን አለኝ አንተው መፈንጠዝ አበዛህሳ ቢለይኝ ጊዜ......የጫሌው ሼይኽ(ረዐ) ያሉትን ትዝ ቢለኝ ላኩለትና ረፍት ወሰድኩኝ....
*
*
*
እኔ ያየሁትን አይተኸው በነበር
አዳልቀኝ ሳልልህ ታዳልቀኝ ነበር
እንኳን ልለምንህ ትለምነኝ ነበር


ድምቅምቅ ያለ ሳምንት ይሁንልን !💚


@wegoch
@wegoch
@Nagayta
ለውብ ቀን!
💚

እነሆ ውብ አንቀፅ
-------------------------

“አይ ስንታየሁ ! ለሚያደርገው ነገር ሁሉ ልክ የለውም። ሲጠጣ እንደ ዓሣ፣ ሲወድ እንደ
ዻጉሜ ውሻ፣ ሲቸር እንደ ንጉሥ፤ ሲያጣ እንደ ቤተክርስቲያን አይጥ ነው። ለነገ የሚለው
ነገር ከቶ የለውም። የሚያደርገው ነገር ሁሉ ከልክ በላይ መሆን አለበት። ከእርሱ ጋር
እንዲስቁ - ሲስቅ። ከእርሱ ጋር እንዲያለቅሱ ሲያለቅስ - ይፈልጋል። ሕይወትን ካልኖርኸው
እንዴት ልታውቀው ትችላለህ ? የሚል ፈሊጥ አለው። ኃጢአት ነው የሚለው ነገር ያለው
አይመስለኝም። ሕይወት ያለ ኃጢአት አትሰራም፤ ከኃጢአት ባሻገር ምንም የለም። ሕይወት
በራሷ ፍፃሜ ናት ባይ ነው። እና ይኖረዋል። ”

- - -
- በዓሉ ግርማ ፅፎት በየካቲት 1975 ዓም ዕትም እና በኋላም በ"ጭጋግና ጠል"
የአጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ መፅሐፍ ውስጥ ከተካተተው፣ “የፍፃሜ መጀመሪያ”
ከተሰኘው ብቸኛ አጭር ልብ ወለዱ የተቀነጨበ።

@wegoch
@wegoch
@Nagayta
የስነ ፅሁፍ ምሽት በአዳማ f.r.i.e.n.d.s house ቅዳሜ ምሽት ከ12 ሰአት ጀምሮ አዳማ ኮሌጅ ከዮሀና ሆቴል አጠገብ
@getem
@getem
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (“ናካይታ” (Nagayta))
2024/09/25 21:24:56
Back to Top
HTML Embed Code: