Telegram Web Link
ለቅዳሚታችን!
❤️

አምላኬ ሆይ ! ቴሌቪዢን አድርገኝ
====================
አንዲት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርት ተማሪዎቿ አንድ ነገር እንዲፈፅሙ
አዘዘቻቸው። አላህ እንዲለግሳቸው የሚመመኙት ነገር ምን አንደሆነ ሁሉም በነጭ ወረቀት
ላይ ፅፈው እንዲያቀርቡ ጠየቀቻቸው። ስማቸውንም በወረቀቱ ጀርባ ላይ እንዲያሰፍሩ
ጠቆመቻቸው።

ሁሉም ተማሪዎች የታዘዙትን ተገበሩ። ምምህርቷ ወረቀቶቹን በሙሉ ሰብስባ ወደ ቤቷ
አመራች። ከቤቷ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ እያንዳንዱ ተማሪ የፃፈውን ማንበብ ይዛለች።
ትስቃለች ፤ ትገረማለች። የሆነ ወረቀት ላይ ስትደርስ የተፃፈውን ነገር ተመለከተች።
በጣም ተደነቀች። በወረቀቱ ጀርባ ላይ የሰፈረውን ስም ስትመለከት ደግሞ አንጀቷ
ተላወሰ። እንባዋ እንደ ደራሽ ወንዝ በጉንጮቿ ላይ ፈሰሰ። ወረቀቱን በሁለት እጆቿ አጥብቃ
በመያዝ እየተንሰቀሰቀች አለቀሰች። በዚህ ሁኔታ ሳለች ከባለቤቷ ጋር ዓይን ለዓይን
ተገጣጠሙ ።

«ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሺው ?» ... የባለቤቷ ጥያቄ ነበር። ቁጭት ባዘለ ስሜት ተውጣ
«ከተማሪዎቼ መካከል አንዱ ልጅ የፃፈው ፅሁፍ ነው እንዲህ ያስለቀሰኝ» አለችው። «ምን
ስለፃፈ ነው እንዲህ ያስለቀሰሽ ?» አላት። «እስኪ እኔ ከማነብልህ አንተው እራስህ
አንብበው !» ብላ ወረቀቱን ሰጠችው።

ማንበብ ጀመረ። ወረቀቱ ላይ የተከተበው የመጀመሪያው ዐ.ነገር ከላይ በርዕስነት
የተጠቀምኩት ሃሳብ ነበር። የገዛ አይኑን ማመን እያቃተው ማንበቡን ቀጠለ።


«አምላኬ ሆይ ! አንድ ትልቅ ነገር እለምንሃለሁ፣ ግን እምቢ እንዳትለኝ። እንደማንም ብለህ
ዛሬ ምሽት ላይ ቴሌቪዢን አድርገኝ ! እባክህን ዛሬ እንኳ የቴሌቪዢኑን ቦታ እንድተካ
ቴሌቪዢን አድርገኝ ! በእኛ ቤት ውስጥ የተለየ ቦታ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁና ቴሌቪዢን
አድርገኝ ። ቤተሰቦቼ ዙሪያየን እንዲከቡኝ እሻለሁ። ቴሌቪዢን ካደረከኝ የምናገረውን
አፍጥጠው ይመለከታሉ። በትኩረት ያደምጡኛል። ያለምንም ማቋረጥ ይሰሙኛል። ሁሌም
ውሏቸውና አዳራቸው ከእኔ ጋር ይሆናል። አባቴ ከስራ ቦታ ወደ ቤት ሲመለስ ምንም እንኳ
በስራ ጫና አማካኝነት ድካም ቢኖረውም ከእኔ ጋር እንዲሆን ስለምፈልግ እባክህን
ቴሌቪዢን አድርገኝ። እናቴም ትካዜ ሲወርሳትና ስትበሳጭ ከእኔ ጋር እንድትሆን ሰለምፈልግ
እባክህን ቴሌቪዢን አድርገኝ። ተው አምላኬ ቴሌቪዢን አድርገኝ ! ተው እባክህን ተው ! …
እየለመንኩህ ነው። ወንድሞቼ የሚፈልጉትን ነገር ለማየት ከፊቴ እርስ በእርሳቸው ሲከራከሩ
እንድመለከታቸው ተው ቴሌቪዢን አድርገኝ !
ቤተሰቦቼ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገው ወደ ጎን በመጣል ለእኔ ጊዜ እንዲሰጡኝ ስለምሻ
ቴሌቪዢን መሆን እፈልጋለሁ። አምላኬ ሆይ በመጨረሻም ቴሌቪዢን ካደረከኝ ቤተሰቦቼን
እንዳስደስታቸውና እንዳዝናናቸው አቅሙን እንድትለግሰኝ እማፀንሃለሁ። አምላኬ ሆይ !
አንተ ብቻ ቴሌቪዢን አድርገኝ እንጂ የትኛውንም አይነት ቴሌቪዢን ብሆን ግድ
አይሰጠኝም» የሚል ፅሁፍ ወረቀቱ ላይ ሰፍሯል።

«ኦ አምላኬ ሆይ ! ምን አይነት የሚያሳዝን ልጅ ነው እባክሽ ! ምን አይነት ክፉ ወላጆች
ናቸው እያሳደጉት ያለው» አላት መምህርት ባለቤቱን።


ምምህሯም በድጋሜ እንባዋን አነባች። እንደ ናዳ እየተንሸራተተ የሚወርደው የእንባዋ ዘለላ
በረንዳው ላይ እየተንጠበጠበ «እስኪ በወረቀቱ ጀርባ የሰፈረው የተማሪ ስም የማን እንደሆነ
ተመልከተው ?» አለችው።
ስሙን ሲመለከተው በቆመበት ቀረ። ተቸክሎ የቆየ ሃውልት መሰለ ፤ ዞረበት። ከወረቀቱ
ጀርባ ያለው ስም የገዛ ልጃቸው ነበር ።

==================================
ወሰን ባለፈ መልኩ የቴሌቪዢን ስክሪን ላይ ተለጥፈው ልጃቸውን ለሰራተኛ በመስጠት
ባይተዋር የሚያደርጉ ወላጆች ምንኛ ደካሞች ናቸው። የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም
አስፈላጊነታቸው የማይካድ ቢሆንም ፣ አንድ ቤት ውስጥ ያለን የቤተሰብ አባል
እንዳልተፈጠረ ሊያስረሳ የሚችልበት ሁኔታ ካለ ግን ከመጠቀሙ አለመጠቀሙ በላጭ
ነው። ቴሌቪዢን በእኛ ላይ አመለካከቱን በመጫን እንድናደምጠው ያስገድደናል እንጂ
ሃሳባችንን ለማካፈል ከእርሱ ጋር መወያየት አይፈቅድልንም። በቀኝ እጁ አጥንት እየጋጠ
በግራ እጁ ዋትስ አፕ የሚኮረኩር ትውልድ መሃል የሚያድግ ህፃን እጣ ፈንታው ምን ሊሆን
እንደሚችል ማሰቡ በራሱ ያስጨንቃል። ለቻት ጊዜ አጥሮት መፀዳጃ ቤት ውስጥ ሳይቀር
ሞባይል የሚጠቀጥቅ ዜጋ መሃል የሚያድግ ልጅ መፃዒው ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰቡ
ያስፈራል። የተወሰኑ ደቂቃዎችን ብቻ የሚጠይቁ ሃይማኖታዊ ግዴታዎችን ለመፈፀም
በመስጂዶች እና አብያተ ክርስቲያናት ቅጥር ክልል ውስጥ የታደሙ ወጣት አማኒያን
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፥ በስፓኒሽ ላሊጋና በጣሊያን ሴሪዓ ዙሪያ ስፖርታዊ ትንታኔ
ሲሰጡ የሚያደምጥ ህፃን እጣ ፈንታው ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰቡ በራሱ ይረብሻል።
ለአንድ ሰው ትልቁ ካፒታል ልጁ ነው። የአንድ ሃገር ትልቁ ካፒታል ደግሞ የሰው ሃይል ነው።
ጤናማ እና አምራች ዜጋ መፍጠሪያ ምንጩ ደግሞ ቤተሰብ ነው። የቱርክ እና የህንድ
ተከታታይ ድራማዎች ልባቸውን ያቀለጣቸው ወላጆች ልጃቸው እራት መመገቡን እና
አለመመገቡን ለማወቅ እንዳይችሉ አድርጎ ሰልቧቸዋል። ለከት በሌለው መልኩ
የቴሌቪዢን ስክሪን ላይ የሚያፈጥ የወላጅ ዓይን ደግሞ እንኳን ጥሩ ዜጋ ሊያፈራ ይቅር እና
የልጁን የፈት ገፅታ በወጉ መለየት አይችልም።


ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤️

#ምንጭ:-መሀመድ አህመድ

@wegoch
@wegoch
ዲያብሎስ ከሞተ ተጎጂው አንተ ነህ !!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።
ሰላም የቅዳሜ ወግ ተከታታይ ጓዴ ! እንደምን አድረሀል ? :)
ዛሬ አንዲት ሸጋ ወግ ላጫውትህ በሞባይልህ ደረት ገፆች ተከስቻለሁ ።
ወዳጄ ስለ መጥፎ ነገሮች ህላዌ ያለህ ምልከታ ምን ይመስላል? ...ክፉ ሰዎች ቢያልቁ... ጨለማ ነገሮች ቢከሽፉ.. .መጥፎ የህይወት ገጠመኞች ቢሰወሩ ደስተኛ እሆናለሁ ብለህ ታስባለህን ?
መልስህን ከመናገርህ በፊት ወደ ካህሊል ጅብራን ተረክቶች ይዤህ ልንጎድ መሰለኝ...
አንድ ማለዳ ላይ ቄስ ሳማን ወደ ቤተመቅደስ እየተጓዘ ሳለ አንድ ሰው መንገድ ላይ ወድቆ ተመለከተ ። በዚህን ጊዜ ቄሱ ... የታመመውን ግለሰብ በማንሳትና ጥሎ ወደ ጉዳዩ በመሄድ ሀሳቦች ተከፈለ ... ።
ታማሚውን ግለሰብ ቀርቦ እንዳያነሳው ወንበዴዎች ደብድበው በጣሉት ግለሰብ ተጠያቂ ሊሆን እንደሚችል ገመተ ... ጥሎትም እንዳይጓዝ የጌታው ኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝን መሻር መሰለው.. . ታማሚውን በማንሳት ሂደት ውስጥም እሱን በመጠበቅ የሚጉላሉ የቤተ መቅደስ ሰዎች ታዩት...!
ጥቂት ካሰላሰለም በኋላ ጥሎት ለመጓዝ መንገድ ጀመረ። ይሄን ጊዜ ታድያ ዲያቢሎስ ጮሆ ተጣራ ..."ቄስ ሳማን ስለምን ጥለኸኝ ትሄዳለህ? :) " ...(አስገራሚ ጥያቄ! )
ቄሱም ዞር ብሎ ወደ ወደቀው ሰው ሲመለከት ሰይጣን መሆኑን ባወቀ ጊዜ ይበልጥ በፍርሀት ሮጠ ...
"ቄስ ሳማን አትሳሳት !
የእኔ ሞት ማለት ያንተና የፈጣሪህ ሞት ነው።
እኔ ዲያብሎስ ብሞት መስጂዶች...የክርስትያን መቅደሶች ...ህልውና አይኖርም...ያንተን ፀሎት የሚጠባበቁ ምዕመናን አይኖሩም...
እኔ ከሞትኩ ሰዎች ፈጣሪን አያውቁትም...ዛሬ ላይ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች ሁሉ እኔን በመፍራት የተቋቋሙ ናቸው ።
እኔ ብሞት አዛንም ቅዳሴም አይኖሩም። አንተም እንጀራህ ይነካል...ቤተሰቦችህም ይበተናሉ :) "
...
በዚህን ጊዜ ቄስ ሳማን ጥቂት በሀሳብ ከነጎደ በኋላ ...ግራና ቀኙን አመዛዝኖ ወደ ዲያብሎስ ተጠጋ ...የተጎዳ ቁስሉንም በጨርቅ ጠቅልሎ አዝሎ ለህክምና ወሰደው ...።
ወዳጄ ልብ በል !
አንተስ ሰዎች ክፉ ናቸው ብለህ እንዴት ልታጠፋቸው አስብሀል?
በፖለቲካ ሀሳባቸው...በማህበራዊ ህይወታቸው.. .በሴራና በተንኮላቸው ሁሉ አንተን ሊያጠፉ የሚተጉ ሰዎችን በማጥፋት እኔ ተደስቼ እኖራለሁ ብለህ እንዳታስብ ዘንድ ከበላይ የነገርኩህን ጨዋታ አሰላስል....
ብርሀንን ትመለከት ዘንድ ጨለማ የግድ መኖር አለበት ።
ሸጋ ቀዳሚት ተመኘሁልህ 😍

@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (👋ገብርዬ)
ሥዕሎችን በተመጣጣኝ ዋጋ #አሥለው ሥጥታ ያበርክቱ
🎂ለ ልደት🎂
❤️ለፍቅረኛ❤️
👨‍⚖ለሰርግ 👰
🧑‍🎓ለምርቃት👨‍🎓
በ +251934039346
ወይም @cher46 ማዘዝ ይቻላል ።

ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
ይህን እድል ይጠቀሙበት!
#ሥዕል_ብቻ

@seiloch
@seiloch
ምንምነት ውስጥ ምንም ነገር አለ።


ሀሳብ አለ።
… እሚታሰብ እሚንሰለሰል ። ሳትፈልገው ሚፈልግህ…… ሳታልመው
እሚያልምህ…… በአንተ ዙሪያ እየዘወረ እሚዘውረወህ…… ሀሳቡን
ተረድተህ ለመሰደር ብትባዝንም ምንጩንና ፍንጩ የማይገለጥልህ
ግዜ አለ……… ታወጣ ታወርድና ይህን ሀሳብህን ለሚካፈልህ ጓደኛ
ትሻለህ… …ለመረዳት ሀሳብህን ለመካፈል የመጣው ጓድህ " ምን
ገጠመህ ጓዴ? " ይልሀል። የገጠመህ እክል አታውቀውም ግን
ጨንቆሀል……ግን ደብቶሀል…… ግን ያባዝንሀል…… የተምታታ ስሜት
ውስጥህ ሰርፇል። እንዲህ ነው ብለህ ተንፍሰህ ነገሩን ሀሳቡን
ማቅለል ያዳግትሀል።

……ያሳለፍካቸውን ቀናት እየተመለስክ ውሎህን አዳርህን
እያስታወስክ የተገበርካቸውን ትሰልላለህ ። ምንም አታገኝም ወይም
ከስሜቱ ጋር እየታገልክ መንስኤው ይጠፋሀል። ዝም ብሎ ውስጥህ
ይነጫነጫል ንጭንጭህን ተባዕት ወይም እንስት በታገኝ
አግኝተውህ የውስጥህን ስላልተነፈስክ ይከብዳቸዋል።እንዲህ
ይገጥማል ሀቅ ነው ። መንስኤ አለው ወይም ደርሰህ ተደብተሀል።፤

☞ ………ምንም ባልነው ነገር ምንም ያላልነው ነገር ይፈተላል።
ምንም ማለት ባዶ አይደለም ባዶ ያልነውም ምንም አይደለም ማለት
አይደለም። ባዶነትም አንድ ምንነት ነውና።ግን ምን ሆኛለሁ? ምንም
አልሆንኩም አልልም ባዶ ሆኛለሁና።

እናም
☞ ማንኛውም ሀሳብ ሀሳብ ሆኖ… ሀሳብነቱ ገዝፎ ሀሳብን አጨንግፎ
እሱ ሲያንሰራራ… …አንሰራርቶ ሀሳብ ሀሳብነቱን የሚረዳ ሀሳቡ
ደርሶበት ያረፈበት ሰው ላይ ነው።

ደግሞም
ምንም ነገር ውስጥ ምንም ነገር አለ
ምንም ነገር ያለምንም ነገር አይነሳምና።

@wegoch
@wegoch
ክቡራትና ክቡራን ወድ የወግ ብቻ ወዳጆች ለምንሰራው ጥናት እንዲረዳን ማህበራዊ ምልከታችሁን እንድትቸሩኝ ስል ለእናንተ እጠይቃለሁ!
 
 ጥያቄውም:- ''ስለሽመና'' ሙያ የተፃፉ መፅሃፍትን የተሰሩ ዘጋቢ ቪዲዮችን እንዲሁም እርሶ ስለሙያው የሚያውቁትን ከስር በሚገኘው ሊንክ ላይ እንዲያጋሩኝ ስል በትህትና እጠይቃለሁ።

በዚህ ይላኩልኝ @Mykey21
#ዛሬ አለም አቀፍ የራድዮ ቀን ነው ! የሸገሯን መዓዛ አለማመስገን ንፍጉነት ነው! መልካም የስራ ዘመን! ለሸገር ራድዮና ለጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ !


ማሪንጌ ቻ! !!!!!

ኧረ ሸገር ሸገር ፤ ሸገር ባውቶብሱ ፣
የመርካቶ ልጆች ፤
ሸ ከርተፍ እያሉ ፣ ከምኔው ደረሱ ።
ታምር አይደለም ወይ ፤ እንደ ሰማይ መና ፤
ሽበት ክብር ሲሆን ፤ እድሜና ቁመና ።
አስናቀ አስናቀ፤ አስናቀ ቢሉሽ ፤
ኬሬዳሽ በያቸው ፤አይስማ ጆሮሽ ፤
ቼ በይው ፤
ፈረሱን አቤ ነው ብለሽ ።
በደርባባው ዛትሽ ፤ በሁለመናሽ ፤
እንደ እቴጌ ማርዳ ፤ ያምራል ከራማሽ ፤
እድሜ ይቀጥላል ፤ ውብ አንደበትሽ ፤
መአዛ ማር ዘነብ ፤ መኣዛ ጥንቅሽ ።
ማሪንጌ ቻ ፤
ማሪንጌ ቻ ዘመናችን ይመር እንደ ማ'ዛ ብሩ ፤ እንደ አበበ በልቻ ።
ማሪንጌ ቻ! !!!

((( ጃ ኖ )))

መታፈር በከንፈር! !!!!! ያውም ደግሞ ልክ እንደ መኣዛ
ብሩ! !!!!


እናንት የጦቢያ እህቶቼ ሆይ! !!!!ከሴትነት ላይ የሰከነ
እውቀት ሲጨመርበት በዚያ ላይ ያደጉበትን ማህበረሰብ
ለዛና ወዘና ሳይለቁ የሚከወን ጋዜጠኝነት ከህዝባዊ
ሃላፊነት ጋር ተዋህዶ ሲገኝ ግዙፍ ከራማ ይሆንና ላገሩ
ለወንዙ የምትከብዱ እመቤታትና ወይዛዝርት አድርጎ
በጦቢያ ሰማይ ላይ ያነግሳችሃል! !! እንዲህም ያለ ነገር
በዚህች መአዛ ብሩ በምትባል የሸገር ራዲዮ ፊት አውራሪ
፤ ጦቢያዊት ደርባባ ሴት ዘንድ ሲፈጸም አይተናልና ደርባባ
እህትና እናት ያልነሳሃን ያገሬ ሰማይ በረካ ሁንልኝ እንጅ
ሌላ ምን እልሃለሁ! !!!

@Nagayta
@wegoch
@wegoch
ይሄን ሰው ምን ነካው ?
(ሚካኤል አስጨናቂ )
ከእንቅልፌ በነቃሁ ቅፅበት ታናሽ ወንድሜ ከአልጋዬ ግርጌ ቆሞ ውዳሴ ማርያም ሲደግም አየሁት ። አይኔን ባለማመን ደግሜ ፣ ደጋግሜ አሻሸሁት ። ራሱ ታናሽ ወንድሜ ነው ! ያ መጠጥ ከማብዛቱ የተነሳ ዛሬ ምንም አልቀመስሁም አንድ ካሳ ቢራ ብቻ ነው ብሎ የሚሽኮረመመው ፣ ጫት ቅሞ ጉንጩ ውስጥ ሲወጥር የዛች የትግሪኛ ዘፋኟን ሪች መቀመጫ😜 የሚያሳህለው ፣ የሺሻ ጎማ በመጎተት ከኤርታሌ እስለ ሱማሌ የሚሰማ ቱርርርርርር የሚል ድምፅ የሚያወጣው ወንድሜ ነው እየፀለየ ያለው 🙂
የማየው ነገር ህልም እንዳይሆን ተመኘሁ ። ደስ ሲል ደግሞ ህልም አይደለም ! እናቴ በሁኔታው ተገርማ አይኖቿ ሲበሩ ይታወቀኛል ። በሰፈር ሽማግሌ ፣ በንሰሀ አባት ፣ በፖሊስ እና ፌደራል ተሞክሮ ጠባይ ሳይገዛ የኖረው ወንድሜ እነሆ በመጨረሻም በራሱ ጊዜ እንዲህ ለፈጣሪው ተንበረከከ ! አቤት ጠሎት ! አቤት ስግደት ! እጁን እያጣመረ ፣ ከወገቡ ሸብረክ እያለ ሲሰግድ ላየው ዛሬውኑ ጣዲኡ አቡዬን ታልሆንኩ ብሎ የወሰነ ነበር የሚመስለው ።
ደግሞ ከፀሎቱ ብኋላ በላስቲክ አድርጎ ውጭ ካስቀመጣት ፀበል ተጎነጨ ። አቤቱ ማረን ጌታችን አለ ! በስልኩ የቴዎድሮስን መዝሙር ከፈተ !
ያ በማይክል ጃክሰን ዘፈን የቤታችንን ሴራሚክ ያነቃንቅ የነበረው ፣ የሰፈሩን ከለቦች ከራሱ ሸሚዞች በላይ ጠንቅቆ የሚያውቀው ፣ ዲጄ ልሆን ነው ብሎ ላፕቶፕ በጀርባው አዝሎና ጠጉሩን አንጨባሮ ሲንበጫረቅ የኖረው ወንድሜ መዝሙር አዳመጠ ። ደግሞ መዝሙሩን በቅጡ ባያውቀውም በስሜት ነበር የሚዘምረው ።
አይናችን ነሽ ማርያም አንቺን አይንኩብን ! የሚለውን መዝሙር
እናታችን ነሽ ማርያም ባንቺ አይምጡብን ! 🤣🤣እያለ ይዘምራል ። ኽረ ይሄንስ ማን አየበት ? ይሁን ነው የሚያስብለው ! ደግሞ ባንቺ አይምጡብን የሚለው ባንቺ አይምጡብኝ የምትለው የናቲ ማን ሙዚቃ ትውስ እያለችው እንደሆነ እናውቃለን ። ቢሆንም ዋናው ለመዘመር በስሜት መመሰጡ ነው ። ከሀሽሽ ጡዘት ወደ መዝሙር ምሳጤ መግባት እጅጉን አስደማሚ ነገር ነው ።
ጭራሽ ይባስ ብሎ ወንድምዬ እስቲ ተነስ እና እምነት ልቀባህ ብሎ ተመለከተኝ ።
"ማታ ራሴን አሞኛል ብለህ አልነበረምን ?🙂 ና ልቀባህ ትድናለህ ! "
ጆሮዬን አላመንሁትም ። በሌባ ጣቴ ኮረኮርሁት ። የሆነ ቢጫ ኩክ ዘኝዬ ወጣሁ ። ታናሼ ያ “ ጀለስ እስቲ ለውሎ ገንዘብ ቦጭቅ “ የሚለኝ ወንድሜ እምነት ልቀባህ አለኝ ።
ተነስቼ ግንባሬን አቀረብሁለት ። በስመ ስላሴ አንጣረ ገፁን አማትቦ ቀባኝ እና የስራ ሰዓት ደረሰብኝ ብሎ ጥሎን ተፈተለከ ።
ቅፈላ ይል የነበረው ወንድሜ ስራ ሲል ............
እናቴ የምታየውን ባለማመን እንደ ፀሀይ የበራ አይኗ ይበልጡን ቦግ አለ ። እየሱስ ዳግም ሊመጣ ነው አልያም ዓለም አሁኑኑ ልትጠፋ ነው ብላ የሰጋችም ነገር መስለኝ ።
ወድያው ከሰዓታት በኋላ አንዲት ሸጋ መልከ ግቡ ወጣት ቤታችን መጣች !
አመጣጧ ወንድሜን ፈልጋ ነበር ። "ማታ ሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ስላለ ወንድምህ እንዳይቀር ንገረው" አለችኝ ። ዓይኖቿ እንደ ቤተክህነት ጉልላት የተንጎማለሉ ናቸው ። ፈገግታዋ ገዳይ ነው ። 😍
እሺ እነግረዋለሁ !
አመስግናኝ ወጣች ። ዝቅ ብላ አመስግኛለሁ ስትል ከመሬት ላይ ኮብልስቶን ነክሳ ለመመለስ ምንም ያህል አልቀራትም ነበር ። አቤት ውበት ! አቤት ትህትና !
ወንድሜ እሷን አይቶ መሆን አለበት ሀይማኖተኛ ለመሆን የወሰነው ።
ስምሽን ማን ልበለው ?
ሊያ !
ሊያ ! እጅግ ደስ የሚል ስም ።
በድጋሚ አጎንብሳ (ይቅርታ መሬት ልሳ 😀) አመሰገነችኝ ። ጀርባዋን ሰጥታኝ ስትሄድ እስከ መታጠፊያው ድረስ በአይኔ ሸኘኋት ።
አመሻሹ ላይ በጠባቧ የቤታችን በር በኩል አንድ ዘግናኝ ሲጃራ የተቀላቀለበት የአንቡላ ሽታ ሰተት ብሎ ገባ !
አቤት ቅርናት ! አቤት ግማት !
እናቴ የዚህ ሽታ ክፉ ትርታ በልቧ አለባት ። ህይወታችንን አመሳቅሎ እናቴን ተስፋ ያስቆረጣት ይህ አይነቱ ግማት ነው ።
ታናሽ ወንድሜ ጥንብዝ ብሎ ሰክሯል ።
አይ ሰይጣን ! ደግሞ ተመልሶ ሰፈረበት ። እናቴ ተስፋዋ ሲጠልም እና በደስታ ሲፍነከነክ የዋለ ፊቷ ክስም ሲል ይታወቀኛል ።
"አንተ ደደብ አህያ ከበሩ ላይ ዞር በልልኝ አለኝ !"
ያ ሁሉ የጠዋት እንክብካቤ አይኔ እያየ ገደል ገባ ። ውሻ አለኝ ቀጥሎ !
እልሄን ውጬ ዝም አልኩት ።
"ሊያ ! እኔ እንደዛ እያፈቀርኩሽ ሌላ ጓደኛ አለኝ ልትይ አይገባም ነበር !" ልትፈርስ አንድ ሀሙስ የቀራት የቤታችን ግድግዳ በወንድሜ ቡጢ ተነረተች ። የእናቴ ልብ ከግድግዳው እኩል ሲወዛወዝ ተሰማኝ ።
ምስኪን እማዬ !!🙂

@wegoch
@wegoch
@paappii
ና ዘመዴ የሀገርህ ስም መነሻ ከየት እንደመጣ ያነበብነውን እናጋራህ :)

(ሚካኤል አስጨናቂ ነኝ !)

#ኢትኤልንምም አይቶ እንዲህ አለው ...

የእግዚአብሄር ወንዝ አንኤል ከሚመነጭበት ከራሱ ጀምረህ ግዮን ከሚገሰግስበትና ከሚፈስበት ግሼን ምድር ጀምረህ ከሳሌም ምስራቅ ጫፍ ከሚመነጨው አግያን ምንጭ ጀምረህ ባሉት አገሮች ላይ ትከብራለህ ።ዘርህም ለዘለአለም እርስት አድርጎ ምድሪቷን ይወርሳል። ግዮን በሚፈስበት ምድር ላይ በሚገኘውና ስሙ ዮጵ ተብሎ በሚጠራው ብጫ ወርቅ ስለምትከብርና ስለምትበለፅግ ኢትኤል ከምትባለው ይልቅ ስምህ "ኢትዮጵ " ትባላለህ ። ትርጓሜውም ወርቅ የተሰጠህ ማለት ነው። ...(ኢትዮጵም ግዮን የሚያስከብራቸውን ወንዞች የፈለቁበትን ወንዙ የሚፈስበትን ምድር ኢትዮጵያ ተብሎ እንዲጠራ ሰይሞታል)

።።።።።።።።

መራራስ አማን በላይ ብዙ ጥንታዊ መፅሀፍትን በመበርበርና ከግዕዙም ወደ አማርኛ ተርጉመው በማዘጋጀት ታላቅ ባለውለታችን ናቸው ። ሀገር ወደፊት እንድትሄድ ወደ ኋላችንን ዞር ብለን መመርመር እንደሚያስፈልግ በእውቀትም በእምነት መነፅርም ሆነው አስተምረውናል። 

ዛሬ እጅግ ተደመን የምናነባቸው ብዙዎች የአማርኛ ታሪክ መፅሀፍትም መነሻቸው ይኸው የመራራስ አማን ስራዎች ናቸው ። 

መፅሀፈ ሱባኤ ዘበአማን ካልዕ (እየሱስ ክርስቶስ በኢትዮጵያ ሶስት ዓመታትን እንዳሳለፈም ተከትቦልሀል) የቅዳሜ ግብዣዬ ነው። 

ሰናይ ሚሽት 🙏

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew (Mykey))
Coming up Documentary Project #እነእርሱስ #Whataboutthem
ባለቤቴ በለሊት ተነስታ ነጠላዋን አጣፍታ ወደ ቤተስኪያን ጉዞ ልትጀምር ነው ። እንደ ልማዷ "እንቅልፍ የሰማዩን መንግስት የሚያሶርስህ እንዳይመስልህ በል ተነስ!!" የሚለው ንትርኳን ላለመስማት ኮሮና ቫይረስ በቅርቡ የያዘው ገመምተኛ መስዬ ከህይወት መለስ ከሞት ቀነስ ያለ ውሸታም እንቅልፍ ውስጥ ሰጠምኩኝ ።
ነጠላዋን ደግሞ እያጣፋች "የኔ ጌታ አንተ ምን ይሳንሀል ?! አሁን ሳይወድ በግዱ ይሰበሰባታል " ትላለች ። ሶስት ረዘም የሚሉ የጧፍ ዘለላዎችን ደግሞ አፈፍ አድርጋ በጎኗ ሸጎጠች ። ፈገግም እንደማለት ብላለች (የባለቤቴ ሳቅ ሁሉ ችግሮቼን የሚያስረሳኝ ምትሀተኛ ፈገግታ ነው ። እንደውም ከምንም ነገር በላይ በሳቋ ማርካኝ እንዳገባኋት ይሰማኛል ። የእሷን ሳቅ ምድር ላይ የሚወክልልኝ አንዲት ምሳሌ ላጣቅስ ባልችልም የቅዳሜዋ ፀሀይ ግን በትንሹ ልትፎካከራት እንደምትሞክር አውቃለሁ ። እሷም ብትሆን እንደ ስለሺ ስህን ተከታይ ብትሆናት እንጂ የኔን ቀነኒሳ ሳቂ እንደማታስንቃት አውቃለሁ ።
ሳቋ ነፍሴ ነው !!
"ዛሬ ምን ተገኘ ?" ብዙም ነገረ ስራዋ ግልፅ አልሆነልኝም ። ዝም ብዬ በሀሳብ እየተብሰለሰልኩ እንቅልፌን አጣጣምኩኝ ።
ማልዶ ስነሳ "በአስር ሰከንድ ሶስቴ ዱፍ የምትለው ትዕቢተኛ ጀበና ከሰል ማንደጃ ላይ ተጥዳለች ። ፋንዲሻው ጉዝጓዙ ሳሎናችንን አድምቆታል ።
ምንም ሳላስበው ያልተጀመረው ፆሙ ተፈፅሞ ፋሲካ ደረሰ እንዴ ? ብዬ ትንሽ ተብሰለሰልኩ ።
የባላቤቴ እህት ደግሞ አንድ ብርኩማ ላይ በስተጥግ በኩል ተቀምጣ
"እድሜ ለለውጡ መንግስት በይ !! አሁን አንድ ቢራ 30 ብር መግባቷን ሲሰማ ኩም ይላታል "
ኦ ፈጣሪ ! የሰማሁት ድምፅ በህልሜ እንዲሆን ተመኘሁ ። ይሁንና የሰማሁት ድምፅ ፈፅሞ ውሸት አይደለም ።
"እንዴ ይሄን ነገር አምረው እውነት አደረጉት እንዴ ?"
ጓዳ መለስ ብዬ ነስር እንዳስቸገረው ሰው በሁለቱ መዳፎቼ ሁለቱን የሳፋ ጠርዝ ይዤ የምሬን ቆዘምሁ ።
ከደቂቃዎች በኋላ ከየት መጣ ያልተባለ የፍሪጅ ውሀ በአናቴ በኩል ሲንቆረቆር ተሰማኝ ።
"አይዞህ ምናባቱ! ራስህንማ ልትታመም አይገባም ። ቢቀር ቢቀር መጠጣት ቢቀርብህ ነው " ቀና ስል ባለቤቴ በነዛ ሀጫ በረዶ ጥርሶቿ ፈገግታን ተላብሳ እንደ አደይ አበባ ፈክታ ቆማለች ። ለመጀመርያ ጊዜ የሚስቴ ሳቅ ደበረኝ

@wegoch
@wegoch
@paappii

#ሚካኤል አስጨናቂ
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew (Mykey))
◍ Episode Ⅰ Vol Ⅰ ◍
#Whataboutthem #weaving #ሽመና

    #ግለታሪክ

       ቦሻ ቦጋለ እባላለሁ የተወለድኩት በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ጨንቻ ወረዳ ውስጥ ነው። ያደኩት ደግሞ አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ነው። የሽመና ሙያን የተማርኩት ከአባቴ  ነው። ይሄን ሙያ ከ14 አመቴ እስከአሁን እየሰራሁት ነው የምገኘው። አሁን 25 አመቴ ላይ እገኛለሁ። ምንም እንኳን እንደ አብሮ አደጎቼ የተሻለ ገቢ የሚገኝበት የሙያ ዘርፍ ባይሆንም በምሰራው ስራ ደስተኛ ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን!

                                        ይቀጥላል ...
   #The Profile

        My name is Bosha Bogale. I was born in Gamo zone Chencha area in the southern region. I was raised in Addis ababa around Shiro meda. My father was the one who thought me weaving skills. I am twenty five years old now. I have been weaving ever since  I was fourteen. I am happy to have stayed in this proffession! Even if it is not a job sector you gain a lot of money from as my friends, I am happy by the work I do . Thanks God.
                          To be Continued
#hashtags

#እነእርሱስ #Whataboutthem #World #Africa #Ethiopia #Addisababa
@Mykeyonthestreet
2024/09/25 21:19:25
Back to Top
HTML Embed Code: