Telegram Web Link
የክፉዎችን ያክል ዝም ያሉ ደጎች ቢያሴሩ ምድሪቱ መልኳ ምን ይሆን? አራት አምስት
አያቱን ለመቁጠር ድፍረት የሌለው እራስ-ፈር ሁሉ የዘር መስመር ሲያሰምር፣ ሲገነባና
ሲያሴር ይውላል፥ ያድራል።
እራስን በኢኮኖሚና ፖለቲካ ከፍ ማድረግ አንድ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ፣ ዘርን በማንጠርና
በማንዘርዘር ፖለቲካዊ ሸቀጥ ማሻቀጥ በድምር ውጤቱ ኪሳራ ነው።
ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎህን አሳድግ፥ ተደራጅ፣ የጋራ ቋጠሮህን መሰሎችህን ሳብ
ሰብስብበት እንጂ ሌሎችን ለመበተንና ለማራቅ መሳሪያህ አታድርገው። የመጥሎና
መገፋት ትርክት ቁጭት ብትኖችን የመሰብሰብ ሃይሉ አሌ የማይባል ጉልበታም ቢሆንም
ኢትዮጵያን መሰል ዘረ-ቁልፍልፍ ለሆኑ ህዝቦች አዙሪተ-በደሉ ዘመን ተሻጋሪ ነው።
በእኛ ዘመን እንደሆነው ለመጭ ትውልድ መገፋፋትንና ቁርሾን አታውርስ። የመጠላለፍ
ታሪክ ሰሪ የየዘመኑ ሰው የመሆኑንን ያክል የመጠላለፍና የመጠላላት ትርክት አክትሞ ለሰው
ሁሉ የሚበጅ ኢኮኖ-ፖለቲካዊ ስርኣትም የሚበጀው በዘመን ቅብብሎሽ በሚፈጥሩ
አብርሆት በገራላቸው ሰዎች መሆኑንም አትርሳ። ስለሆነም የኢትዮጵያና ህዝቦቿ የፖለቲካ
መጻኢ እድል በእውነትና እውቀት ላይ የተሰመረ መሸጋገሪያ ይሆን ዘንድ ይሄ ትውልድ
አጥፊ ቁርሾና እልኩን ትቶ ስልጡኑን አለም ይመልከት። ሰው ስሜተ-ብዙ ነው። ብዙሃኑ
ከምክንያታዊ ነገ ይልቅ የዛሬ ግንፉል ስሜቱ ሚዛን ያስተዋል።

ሰላም እደሩልኝ💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
አልተፀፀትኩም!!!

አልተፀፀትኩም ግን ልምድ አግኝቼበታለው።በፊት በፊት ገና ቆንጆ ሴት ሳይ request
እልክላቸውና ዝም ሲሉኝ ይከፋኝ ነበር ...ተቀብለው ካዋሩኝ ደሞ ስልክ ይኖርሻል?ብዬ
እጠይቃለው አራዳ ሴቶች ኖ የለኝም facebook የምጠቀመው በላፕቶፕ ነው ይሉኛል ፋራ
ሴቶች ደሞ ምን ያደርግልሀል ይሉኛል።
ያው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወንድ ሀይ ብዬ እልካለው ከዛኛው ሰፈር መልስ
እየተመለሰልኝ ከሆነ ስልኬ ቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ያሰማኛል የዛኔ ደስ ይለኝና ቀጣይ
ወሬዬን እመርጣለው...ያው እናንተ ተማሪ ሰራተኛ ?ነው የምትሉት አይደል እኔ ግን
አይደለም።
የማይታዩ ሴቶች ደሞ ሲያበሽቁኝ ፎቶ ላኪልኝ ማለት አጠያየቁ ግራ ይገባኝና ፎቶ ደመቀን
ታውቂዋለሽ? እላታለው ማነው ደሞ እሱ ካለቺኝ ያው ስታዲየም አካባቢ አትመጣም
ማለት ነው ብዬ ወደ ሌላ ጥያቄ ላልፍ ስል ግን ለምን ጠየከኝ ትለኛለች....ፎቶሽን እሱ
አንስቶ እንዲልክልኝ ነበር እላለው እንደዛ ከምትል ላኪልኝ አትልም? አራዳ ሴት እኮ
ትግደለኝ ቢያንስ ስትገለኝ አሻራ ታጠፋለች ፋራማ አቡክታህ ነው የምትሄደው።ማለት ፈርቼ
እኮ ነው ችግር የለውም እልክልሀለው ግን ለማንም እንዳታሳይ ፕሮሚስ? እኔ ግን
ስንተኛው ሰው እሆን ለማንም እንዳታሳይ ተብዬ የተላከልኝ እላለው በውስጤ።
ፕሮሚስ እገባና ይላክልኛል አንድ ሲላክልኝ ጥጋቤ መከራ ነው እስኪ ደግሞ በሌላኛው
ዳይሜንሽን እላለው ያው እናንተም እንደምታውቁት አንድ ብቻ የሚልከው ሰላቢ ነው
አይደል?ይሄ የመጨረሻ ነው ብላ ሌላ ትልካለች በመሀል ግን አጥፋው እሺ የሚል ትእዛዝ
ይደርሰኛል ድሮስ ፕሮፋይል ላደርገው ነው? የአንዲትን ልጅ ፎቶ ግን ፕሮፋይል አድርጌ
አውቃለው ....እዚህ ጋር አምስት ሴቶች የኔን ነው ብለው ያስባሉ።አሁን እያረጀው ስለሆነ
ወደ ተውበት እየገባው እኮ ነው ጠይቄ የላካቹልኝ አመሰግናለው ያላካቹልኝ አስቀያሚ
ስለሆናቹ ነው ሃሃሃሃ ተውበቱን ረሳሁት እንዴ?....ይሄ ሁሉ የምቸከችከው ለምን ይመስልሀል
ገምታ።
ሸጋ ቀን!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የልጁን ነገር ምን ወሰናችሁ???

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ቤተሰብ ውስጥ ያለ ህፃን እያለቀሰ ያስቸግራል፡፡
ቢያባብሉት፣ እሹሩሩ ቢሉት አሻፈረኝ አለ፡፡ በማባበል እምቢ ሲል ማስፈራራት
ጀመሩ፡፡
“እንግዲህ ዝም ካላልክ ለአያ ጅቦ ልንሰጥህ ነው” አለች እናት፡፡
“ዋ በመስኮት ነው የምወረውርህ!” አለው አባት፡፡
ይህንን ሲሉ ለካ አያ ጅቦ ደጅ ሆኖ ያዳምጥ ኖሯል፡፡ ይጠብቃል … ይጠብቃል
… ይጠብቃል… ልጁ አልተወረወረም፡፡ አሁንም ያዳምጣል፡፡ ተስፋ ሳይቆርጥ
መጠበቁን ቀጠለ፡፡ ምንም ዝር ያለ ነገር የለም፡፡
የልጁ ለቅሶ ግን ቀጥሏል፡፡
አሁንም እናቱ፤
“ዋ! ለአያ ጅቦ ነው አስረክቤህ የምመጣው!!”
አባትም ዳግም፣
“ዛሬ ነግሬሃለሁ ለአያ ጅቦ ነው የምጥልህ” አለው፡፡
ልጁ ማልቀሱን ቀስ በቀስ አቆመ፡፡ አያ ጅቦ ምራቁን እያዝረበረበ፣ ቆበሩን
እየደፈቀ ቀረ፡፡ በመካያውም አንድያውን ጥሎ ለመሄድ፤ “ኧረ የልጁን ነገር
ምን ወሰናችሁ?” ብሎ ጠየቀ፡፡ ቄሱም ዝም፣ ዳዊቱም ዝም፤ ሆነ!
***
አንድ የሀገራችን ዕውቅ ገጣሚ፤ የደርግ ሥርዓት አብቅቶ የኢህአዴግ ሥርዓት
ሲጀምር፤
“ዘመንና ዘመን እየተባረረ
ከምሮ እየናደ፣ ንዶ እየከመረ
ይሄው ጅምሩ አልቆ ማለቂያው ጀመረ” ብሎ ፅፎ ነበር፡፡
ዕውነትም የማያልቅ ዘመን የለም፡፡ አዲስ ሁሉ ያረጃል፡፡ የማይለወጥ
አንዳችም ሥርዓት የለም። የአዲሱ አሸናፊነትም አይቀሬ ነው፡፡ አጠራጣሪው
በየትኛው መንገድ ይለወጣል? የሚለው እንጂ ለውጥ መቼም ቢሆን መቼ
መምጣቱ የማይቀር ሂደት ነው፡፡ ፈረንጆቹ፤
Everything changes
Except the law of change የሚሉት የተፈጥሮ ህግ ነው፡፡
“ከቶም ከለውጥ ህግ በስተቀር የማይለወጥ ነገር የለም” እንደማለት ነው፡፡
እነሆ ለውጥ መምጣቱ ግድ ከሆነ ለለውጥ ዝግጁ መሆን ዋናውና
አስፈላጊው ጉዳይ ነው፡፡ የሀገራችን ሰው አንድ ለውጥ ባገኘ ቁጥር በዚያው
ተወስኖና ያንን ፍፃሜ - ነገር አድርጎ ማሰብ ይቀናዋል፡፡ ሆኖም መሰረታዊ
ችግሩ የጊዜ - ቀመር አለማበጀት (Time - plan አለመኖር) ነው፡፡ መልካም
የጊዜ ግምት ማጣትን የመሰለ ከመርገምት ሁሉ የከፋ መርገምት የለም፡፡
“ጊዜ የስልጣን እጅ ነው” ይለናል፤ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን። ጊዜ
የሚታዘዘው ሰው ብቻ ነው - ዕውነተኛ ባለስልጣን! ለሁሉም፤ ትክክለኛ ምክር
ሰሚ መሆን ታላቅነት ነው፡-
“ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ
እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ …
ምንኛ ታድሏል የሰነፍ አዕምሮ
እንኳን መማር ቀርቶ ፊደል ሳያጠና
ሁሉንም ያወቀ ይመስለዋልና!
አሁን የት ይገኛል ቢፈልጉ ዞሮ
መስማት ከማይፈልግ የባሰ ደንቆሮ”
ይሉናል ገጣሚ ከበደ ሚካኤል፡፡ ካልተደማመጥን ወንዝ አንሻገርም፡፡
ካልተጋገዝን አገር አትንቀሳቀስም፡፡ አሉታዊ ገፅታዎቻችንን ብቻ እየነቀስን
በማጉላት ለውጥ የሚመጣ የሚመስለን በርካቶች ነን፡፡ ሀገራችን ለሶስት ሺህ
ዘመን ያጠራቀመችው በቂ አሉታዊ ነገሮች አሏት፡፡ እነዚህን በማጉላት ምንም
አናተርፍም፡፡ ይኸውም ልዩ ዕውቀት እየመሳሰለን የምንደገግ ብዙ ነን፡፡ ስለ
ሰው ክፉ ክፉውን በመናገር፣ ዘራፍ ማለት የአሸናፊነት ስሜት መፍጠሩ
ዕውነት ነው፡፡ ሆኖም በትክክለኛ መፍትሄ ካልታገዘ ጎጂ ባህል ይሆናል፡፡
ለመፍትሄ ያልተዘጋጀ ህብረተሰብ፣ የአፍራሽነት ሥነ-አዕምሮ ይዞ የሚጓዝ
ስለሆነ ከለውጥ ይልቅ ወግ-አጥባቂነትን ያዘወትራል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ያለው
ማህበረሰብ ከጅምሩም ተራኪ (Story-teller) ህብረተ-ሰብ ነው፡፡
ከተግባራዊነት ይልቅ አፍአዊነት ይቀናዋል፡፡ አፍአዊነቱም በጥናት ላይ
አለመመስረቱ ደግሞ ነገረ - ዓለማችንን የከፋ ያደርገዋል፡፡ ለዚህ ነው የወሬ
አገር ሆነን የቀረነው፡፡
ያለምነውንና የተመኘነውን ዲሞክራሲ እስከምናገኝ ብዙ ዳክረናል፡፡ ብዙ
ፈግተናል፡፡ ልጃቸውን ይወረውሩልኛል ብሎ በር በሩን ሲያይ እንዳመሸው አያ
ጅቦ፤ በመጨረሻው ዘጋግተው እንደሚተኙ እንዘነጋለን፡፡ እንደ ህፃኑ ልጅ
የሚያስቸግረውንም የኢትዮጵያ ህዝብ አባብለው እንደሚያስተኙት ግልፅ
እየሆነ ሲመጣ፤ የእኛ ትርፍ “ኧረ የልጁን ነገር ምን ወሰናችሁ?” ማለት ብቻ
ከሆነ አደጋ ላይ ነን፡፡ ዲሞክራሲ ከራሳችን የሚፈልቅ እንጂ ማንም የሚሰጠን
ምፅዋት ወይም ዳረጎት አይደለም!


ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ


ሽብርቅርቅ ያለ ቀን!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
መንገዱን ያሳጥሩልሀል እኮ...ገብቼ እንደተቀመጥኩ ራሴን ያገኘሁት ከአንዲት ለኔ ቁመት
ትንሽ የቀራት መለሎ አጠገብ ነው።እንዴት አደርሽ? ፀጥ አየሽ ሰላምታ ጥሩ ነገር ነው
ደህና ካልሽ በኋላ አለማናገር ትችያለሽ...ተገላምጣ ደህና አድሪያለው አለቺኝ።እቺ ትንሽ
አይምሮ ቀጣይ ጥያቄ ከየት ታምጣ ከያዝኩት ማስቲካ አንዱን መዝዤ ማስቲካ ልጋብዝሽ?
ፈገግ ብላ በጠዋት ማስቲካ? እንዴ እንቅልፍ ነው እንዴ የጋበዝኩሽ ማስቲካ እኮ
ነው...አመሰግናለው ብላ ወሰደች እኔም አንዱን ጠቅልዬ ስጎርስ ሙሉውን ነው እንዴ
የምታኝከው ?አይ እንደሴቶች ከቦርሳዬ መቀስ አውጥቼ ስድስት ቦታ እቆርጠዋለው.....እንዴ
ሴቶች እንደዛ ያደርጋሉ እንዴ? ያደርጋሉ ግን አንዳንድ ሴቶች ብለሽ ያዠው ስልኬ የአንዲት
ልጅ ምስል ይዞ ብልጭ ብልጭ ይላል እኔ ሳይለንት አደርጋለው አዋራት እንጂ ፍቅረኛህ
ነች? ኧረ አይደለችም እኔ ፍቅረኛ የለኝም።አየህ ወንዶች ስትባሉ ሁላቹም የለኝም ነው
የምትሉት አየሽ እኔ እንዳልኩሽ አንዳንድ ወንዶች ብትይ አሪፍ ነው...እኔ ግን የተሻለች ሳገኝ
ነው የለኝም የምለው ኖርማሊ የለኝም ኖርማሊን ያስገባዋት እንድታምነኝ ነው ሃሃሃ
ተመሳሳይ ጸባይ ነው ያላቹ ብላ ተሟገተቺኝ ግን ነን እንዴ? እኔ አሁን ከአንተ ጋ ተመሳሳይ
ፀባይ ነው ያለኝ? አይመስለኝም ።ለማንኛውም ቁመናሽ ደስ ይላል በተፈጥሮ ነው ወይስ
ተለፍቶበታል? ብዙም አይደለም የተፈጥሮና በምግብ ነው... እዝች ሀገር ላይ መርጠሽ
መብላት መቻልሽ በራሱ ትልቅ ነገር ነው ኖ ለስራዬም እንደዚ መቆየት አስፈላጊ ነው
ሆስተስ ነሽ፣ሞዴል ነሽ፣ማስታወቂያ ነው ምትሰሪው ?ምን አስቸኮለህ እኔ እነግርህ አይደል
...ብራዘር ጃፓን ኤምባሲ ጋር ወራጅ አለ።

💚💛❤️!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
**ህይወት እንደ ገደል ማሚቶ ነው!
አንዲት ትንሽ ልጅ በእናቷ ትናደድባትና " አልወድሽም " ብላ
ትጮሃለች፣ እንዳትገፅፃትም ፈርታ በሩጫ ከቤቷ ወጥታ ርቃ
ትሄዳለች፣ ገደል አፋፍ ላይ ደርሳ አሁንም " አልወድሽም!
አልዎድሽም! " እያለች ትጮሃለች።
የገደል ማሚቶም " አልዎድሽም ! አልወድሽም! " በማለት
አስተጋባ ፣ ከዚህ በፊት የገደል ማሚቶ ድምፅ ሰምታ ባለማወቋ
በሁኔታው እጅግ ትደናገጥና ታድናት ዘንድ ተመልሳ ወደ እናቷ
በመሮጥ በገደሉ ውስጥ " አልዎድሽም! አልዎድሽም !" እያለች
የምትሮጥ መጥፎ ልጅ እንዳለች ትነግራታለቸ።
እናት ነገሩ ስለገባት ልጂቷን ተመልሳ ወደ ገደሉ በመሄድ "
እዎድሻለሁ፣ እዎድሻለሁ!" ብላ እንድትጮህ ነገረቻት፣ ልጂቱም
ተመልሳ በመሄድ እናቷ እንዳለቻት " እዎድሻለሁ! እወድሻለሁ! "
እያለች ስትጮህ የገደል ማሚቶው ያለችውን አስተጋባ ፣ ልጂቷም
አለች ለካ " በህይወት ውስጥ የምታገኘው የሰጠኸውን ነው።"
የሰው ለጅ የዘራውን ያጭዳል፣ አዎ እንክርዳድ የዘራ እንክርዳዱን
ያፍሳል፣ ጥሩ ዘር የዘራ መልካሙን ሁሉ ያፍሳል።
@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa
ማን ምን አለ ? ( ስለ ጥምቀት! ) 😂
😂😂
.
#ዳውድ_ኢብሳ ' ማነው ተጠማቂው ? ማነው ጠማቂው ? '
#ሰራዊት_ፍቅሬ ' እኔ ብቻ አልተጠመኩም . ለመጠመቅ ብለው በደረታቸው እየተሳቡ የዋኙም ነበሩ '
#ቤቲ_Ltv . ' ጥምቀት የማናት ? '
#አብን ' አማራ የጥምቀት ውሀ ነው '
#ጃዋር_መሀመድ ' ጥምቀተ ባህሩን የሰራነው እኛ ነን '
#ቴዲ_አፍሮ ' እወዳችኋለሁ !....ጥምቀት ያሽንፋል '
#ሀጫሉ_ሁንዴሳ ' ተጠመቁ ... አይይ ካላችሁ አባን እጠራባችኋለሁ '
#ኦባንግ_ሜቶ ... ' ጥምቀት ባህር ውስጥ የመለስ ራዕይ እና ብሄር ከሌለ እጠመቃለሁ ብዬ ነበር . ተጠምቄአለሁ . '
#ስዩም_ተሾመ ' ጥምቀት ነፃ ያወጣል '
#ያሬድ_ነጉ ' መንገዱን ዘግተውት እንዳንጠመቅ '
#እየሩስ ። ' ሳራ ቲ። ጥምቀቴን ሰረቀችብኝ '
#ፍቅሬ_ቶሎሳ
ጥምቀት (ቅኔ )
ታቦቱን ሸኝቶ ወደቤት መግባ...ት
በጣም ደስ ይላል ጥምቀት .
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
2011
#በላይ_በቀለ_ወያ ' ጥምቀት ... ካላጠመከኝ በ ብሎክ ሰይፌ '
#ጎሳዬ_ተስፋዬ ። ' ስትጠመቂ እጠመቃለሁ '
#ደፂ። ' ጥምቀትን ለማንበርከክ ሆን ተብሎ ሚሰራ ሴራ ነው '
#አብይ ' ለጥምቀተ ባህር አንድ ጆግ ውሀ ያዋጣ ይመስል ዛሬ ከመሬት ተነስቶ ባህሩ ይደርቃል ይላል . አንተ ትደርቃለህ እንጂ ጥምቀተ ባህር አይደርቅም'
#ግንቦት 7 ' የዜግነት ጥምቀት ነው የሚያስፈልገን '
#አብይ_በድጋሚ ' ካለ ጥምቀት ...ነገሩ እንደሆነ ፍሬ አያፈራ '
#ቴዲ_አፍሮ_በድጋሚ ። " የ ሚኒልክ አምላክ ... የዘርአይደረስ አምላክ በፍቅር ያጥምቃችሁ "
#ስብሀት_ነጋ ። '' ጥምቀ... ቸብ ! ቸብ ! ቸብ

ለማንኛውም እንኳን አደረሳቹ 🙏😌

@paappii
@wegoch

#heny
Zewdalem Tadesse
ማይ ብራዘር ድሮ በሎሚ እየፈነከቱ ቺክ መጥበስ ፋሽን ነበር። በ21 ኛው ክፍለዘመን የማያውቋትን ሴት በሎሚ መፈንከት ግን ፆታዊ ትንኮሳ ነው። ዱባ የሚያህል ሎሚ ተሸክመህ የወጣኸው ፀጉርህን ተላጭተህ ሸቤ መግባት አምሮህ ነው እንዴ? ከግዜው ጋር ወክ አርግ እንጂ ባሻዬ!😂
@wegoch
@wegoch
ባዶ ባዶነት

ሚስት ነች "ትወደኛለህ" ትላለች ባልዋን ኣይን ኣይኑን እያየች
"ኣዎን" ይላል አቶ ባል... የጥያቄውን ወቅታዊ አለመሆን እያብሰለሰለ።
"ምን ያህል" በጉጉት ትጠይቃለች
"ኣይ እሱን እንኳ ኣላውቅም"
ፀጥታ መሃላቸው ይሰፍናል "ህይወትህን እስከመስጠት?" ትጠይቃለች ቆይታ ቆይታ
"አይ... ህይወቴን እንኳ አልሰጥሽም" ታኮርፋለች
እውነት ተናግሮ ከሚያድሩት ያድርገንና የጥያቄያችንን ኣቅም እና ወቅታዊነት
የምንመረምርበት ልቦና ይስጠን እላለሁ።
ጥምቀት እንዴት አለፈ?...
ፍቅረኛዬ ፕሮቴስታንት ነበረች።በኔና የርሷ የፍቅር ኣጭር ታሪክ ውስጥ እንደ ለይላና
መጅኑን ኣይነት ጥዑም ተረክ የለውም፤ አልያም የሄለንን እና ፓሪስን ፍቅር የሚመጥን
ገድል የለውም።ሰው ነን ኣፈታሪክ ስላይደለን ሳቅና ደስታችን ውስጥ የሚሰማው ድምፅ
ሌሎች ጋር ከሚሰማው የሚለይበት እምብዛም ነገር የለውም።
የጂብራኗ የኢሽታርና ክርስቶስ መሃል ጥዑም ልሳን የሆነችው ሴልማ ካራሚን ህመም
ያህል አልታመምንም።ግን እኔ ጨረቃዋ ንፋሱን ሰንጥቃ መጥታ ብርሃንዋ እግሬ ስር
ሲርመሰመስ ከተስፋ በብዙ ሽህ ክንድ መራቄን አብሰለስላለሁ።
እውነት ነው ብርሃን የለበሰ ሰመመናችንን ኖረንዋል።ኣይኖቿ ውስጥ የርሷን ክርስቶስ ልሳን
ህያው ሁኖ እኔ የማምንበትን ፈጣሪ ምህረት ህያው ሁኖ ኣይቸዋለሁ።ግን እንደሴልማ
ብርቱ ኣልነበርኩም ቀን ከሌት ስቅስቅ ብዬ ኣልቅሻለሁ።
"ወንድ ብቻውን ነው ሚያለቅስ" የሚል ሃረግ ላይ ተንጠልጥዬ በምሽቱ ፋና ከራሴ
እያወጋሁ.... ኣይ ወንድ ብቻውን ኣያከቅስም ትዝታው ህመሙ አዘን ትካዜ ኣብረውት ናቸው
ብያለሁ።ኣይ ኣይ ወንድ ብቻውን ኣያለቅስም በእምባው እድሜ ዘመኑን ይገብራል እንጂ ...
ምን ሆነ መሰላችሁ
የቤተ መንግስቱ ግድግዳ ላይ ያለውን ሃረግ እየረገጠ ደርሶ በጨለማ ልዕልቲቱን የፍቅሩን
ልሳን የህይወት ታሪኩ የሆነችውን ሴት ይስማት ጀመር።ህይወትም ሞትም ተናብበው
የሚኖሩባት ኣለም ናት ሴት ማለት እንዲል መፅሃፍ...
ተያዘ ሞት ተፈረደበት
ሞት ፍቅር ኣጠገብ ሲሆን ግርማውን ያጣ የማምሻ ብርሃን ነው፣ በፍቅር ብርሃን
የሚዋጥ.... ፅዋውን ጨርሶ ኣንገቱ ላይ ገመድ ሲገባ የመጨረሻ ትውስታው እሷ
ነበረች።ኣበቦቹ መሃል ያበበች ህያው ኣፀድ
ለካ ንጉሱ ራሱ ነበር .... እሷም ንግስቲቱ።ግን የህያው ስሜት፣ የፍቅር እንጂ የምድር ገዥ
ኣልነበሩምና የሰውና የመሬት ነገስታቶች ሞት ፈረዱበት።
"ስትሄጅ እንደምትረሽኝ ኣውቃለሁ" ኣልኳት
"ስለማትወደኝ ነው እንደዚያ የምትለው" ግን መውደድ ምንድን ነው? ... መውደድ እውነትን
ኣያውቅምን?
"ኣፈቅርሻለሁ ግን እውነታው ከፊትለፊታችን አለኮ።ራሴን ካልሸነገልኩ በቀር የማይታረቅ
እውነታ አለ በኔና ኣንቺ መሃል... ልትሄጂ ነው።ኣዎን ኣፈቅርሻለሁ..."
እውነታው መቼም ኣይቀየርም።እና.... "ተስፋ መቀነን ነው መቼም የሰው ልብ ኣይችለው
የለም" እንዳለው ሰውየው፤ በተስፋና በቀቢፀ ህላዌ መሃል ስዳክር ነበር... ባመሻሽ መሃል
ያለሁ ንጋት ናፋቂ... ግን ንጋት ሲመጣ ምን ኣደርግበታለሁ? ጨለማ ልብ ያለው ስለብርሃን
ማውራት ይቻለዋልን?
ይሄን ሁሉ የምቸከችከው ለምን ይመስልሃል...ገምታ

ሸጊቱ ምሽት💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የአዲስ አበባ ወንድ የመልበሻ ቤት መስታወት ሆኗል። ሴቶቹ በሱ ፊት ላይ አለባበሳቸውን ያያሉ፤የአዲስ አበባ መንገዶች ፣ ካፌዎች ፣ባሮች ፣ ቢሮዎች ፣ሆቴሎች፣የፀሎት ቤቶች ....አለባበስ ማሳያ መድረኮች ሆነዋል።

ወንዱ የጥሞና ጊዜ ተነፍጓል። ሲበላ፣ሲጠጣ፣ሲሰራ፣ሲፀልይ፣ታክሲ ሲጠብቅ ...በሞዴሎች ተከቦ ነው። ህይወቱ የናይት ክለብ ውስጥ እስረኛ ሆናለች። ሲወለድ ሳውና ባዝ የገባ ሲሞት ይወጣል። ኑሮው በላብ መጠበቂያ ስፍራው ሆናለች። አይኑ ሸሽቶ የትም አይደርስም። እድሜ ልኩን መስክ መካከል እንደቆመ ሁሉ በአበባ ተሰላችቷል። ....ትቢያ...ናፍቆታል።

ሴቶች፤የወንዶች አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ሆነዋል። አይኑን ያገለግላሉ፣ልቡን ያገለግላሉ፣ስሜቱን ያገለግላሉ ....የሴቶች የመጨረሻ አማራጭ ...የወንዶች ገበያ .. እንደሚፈለገው ሆኖ መገኘት ነው። ህይወታቸው በወንዶች ህልም የተፈበረከ ነው። ከሰው የሚጠበቀው ከዘንድሮ ሴቶች አይገኝም። ወንድ የሚፈልገውን ግን አያጣም። አይኑ፣ጆሮው፣አፍንጫው፣ምላሱ ... በሴቶች ትጋት ሥር ተጠምዶ ተደናቅፏል። አንዲት ሴት ከአንዲት አበባ ጋር በንፅፅር ቆማለች። የወንድ ቀልብ እንደ ንብ ሲጠመድላት ከማየት ውጪ ሌላ ህልም የላትም። እንግሊዛዊው ደራሲ ዲ.ኤች ላውረንስ ይሄንን ታዝቦ አንዲት የመረረች መጣጥፍ አቅርቦ ነበር "give real her a pattern " ይላል ርእሱ " the real trouble about women is that must always go on trying to adapt themselves to men's theories of women, as they always have done." ብሏል። ( የሴቶች ዋነኛ ችግር ወንዶች ስለሴቶች የሚኖራቸውን ፅንሰ ሃሳብ አሟልተው ለመገኘት ሁልጊዜም መጣራቸው ነው )

የዘንድሮ ሴቶች ሴት የመሆን መብት የላቸውም። ወንድ የሚፈልገውን አይነት ሴት እንጂ። ሴቶች የወንዶችን ህልም ለመተርጎም ህይወታቸውን የሚሰው ጭዳዎች ናቸው። በመሰልጠንም ስም እራሳቸውን ለፆታ ባርነት አጋልጠዋል። ኧረ እንዳውም ከባርነት ወርደው ለአሻንጉሊትነት ተዳርገዋል። ሁኔታውን "living doll" ይለዋል cliff richard የተባለ አቀንቃኝ። ... ህያው አሻንጉሊት ..እንደማለት ነው። "i got myself a sleeping,walking,crying, talking doll" ( እራሴን የምተኛ፣የምትሄድ፣የምታለቅስ፣የምታወራ አሻንጉሊት ሆኜ አገኘሁት ) የዘንድሮ ሴቶች ሰው መሆናቸው የሚረጋገጠው ስለሚተኙ፣ስለሚሄዱ፣ስለሚያለቅሱና ስለሚያወሩ ብቻ ነው። እንደ አበባ ..ንብ መጥራት የህይወት ትርጉማቸው ሆኗል።


(ከዓለማየሁ ገላጋይ "መለያየት ሞት ነው " 2010፤የተቀነጨበ)

ሸጋ ቀን!!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
°•°•
# ንጋት አዲስ ነገሮችን
ይዛልህ እንደመጣች ማመን ቀንህን
የማሳመሪያ ዋና ቁልፍ ነው
# በትናትናው አስከፊ ትዝታ
ውስጥ አትኑር!!

ሸጋ ቀን !!💚💛


@wegoch
@wegoch
@balmbaras
እውነተኛ ታሪክ!!

ተሰብስበን ቁጭ ብለናል የአንዱ ስልክ ይጠራል አያነሳውም....ቢያንስ አንስተህ የሆነ
ነገር በል እለዋለው ተወው ባክህ ይለኛል አሁንም በተደጋጋሚ ግዜ ይጠራል ሳይለንት
ያደርገዋል።ቆይተን ካለንበት ቤት ስንወጣ ደዋይዋ ላዳ ውስጥ ሆና ስሙን ጠርታ ስማ
ሁለተኛ ስሜን እንዳትጠራ እንዳትደውል ስትለው ይሰማኛል. ...ወደ መኪናው ሄጄ
ላረጋጋት ሞከርኩ አንተም ያው ነህ አለቺኝ ከዚህ በፊት አይቻት ማላቃት ልጅ።ላዳውም
ይዟት ሄደ እኔ ወደ ልጁ ተመልሼ ተከተላትና አረጋጋት ስለው ተዋት ኢትዮጵያ ውስጥ
የቫይታሚን እንጂ የሴት እጥረት የለም ብሎ አስቆኛል።ምን ለማለት ነው? እጥረት
ገጠመው መሰለኝ ራሷን አግብቷት አንድ ልጅ ወልዷል።እንኳን ደስ አለህ!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
እኛ ቤት ዶሮ አልታረደም
(በቢትወደድ ተጻፈ)
ክፍል ፩
------------------------------------------------
ገና ሲመጣ ሁሌ የሚያስጨንቀኝ ለወዳጆቼ በተለይ ለፍቅረኛዬ ስጦታ ምን ላዘጋጅ የሚለው ነው።በዘንድሮው ገና ለየት ያለ ስጦታ መስጠት አምሮኛል።ለፍቅረኛዬ በሚያብለጨልጭ ማሸጊያ በትልቅዬ ካርቶን የተጌጠ ዕቃ አይደለም፤ ለፍቅረኛዬ ዶሮ ከ12 እንቁላል ጋር ልሰጣት ነው።ሂሳቡን እንዳታሰሉት፤የኔ እራስ ምታት ብቻ በቂ ነው።ከዶሮው እንቁላሉ በተወደደበት ሀገር 13 ዶሮ ገዛልኝ ትበል።በነገራችን ላይ ዶሮ በጣም እወዳለሁ፤ታርዶ ከተሰራ በኋላ።የምሰጣትን ዶሮ ከፈለገች ከእናቷ ጋር ሁና ሙያዋን ታዳብር አልያም ዶሮውን እና እንቁላሎቹን ሸጣ ህይወቷን ትቀይር።እኔም "ያቺ ዶሮ ሸጣ ህይወቷ የተቀየረው ልጅ ባል" ብባል ደስ ይለኛል።መምጣቱ እንጂ አመጣጡ ብዙም አያሳስብም።ፋሲካ ምስክሬ ነው ያለ ዶሮ በዓል አይደምቅም።ያው እንደነገርኳችሁ ለፍቅረኛዬ ዶሮ ልገዛላት ነው፤በአቅራቢያዬ ወዳለው ገበያ አቀናሁ ግን ዶሮ መግዛቱን ህሊናዬ አልቀበል ቢለኝ "ዶነግ(የዶሮዎች ነፃ አውጪ ግንባር)"ን አቋቁሜ ተመልሻለሁ።ገበያው ላይ ባስተዋልኩት ኢ-ፍትሀዊነት የዶነግን ጽንሰ ሀሳብ ከጥዋቱ 4:00 ሰዓት ጸንሼ 4:15 ላይ ወልጄው አያሌ አባላትን ማፍራት ችያለሁ።አደረጃጀቱንም
ለአቅመ እርድ ያልደረሱ
ከእርድ ያመለጡ እና
ከአቅመ እርድ ያለፉ
በማለት ለሶስት ከፍለነዋል።እኔም እስከ ቀጣዩ ምርጫ የፓርቲው ሰብሳቢ፣ምክትል ሰብሳቢ፣ገንዘብ ያዥ፣የጠቅላይ ጦር አዛዥ፣የውጪ ግንኙነት እና ሌሎች ለጊዜው ስማቸውን ያልጠቀስኳቸው ስልጣኖች ባለቤት ሁኛለሁ።
ከረፋዱ 5:00 ላይ የትጥቅ ትግል ለመጀመር ቅስቀሳ በማደርግበት ወቅት አድማ ለመበተን በሚል ተልካሻ ምክንያት ቁጥራቸው ያልታወቁ ዶሮዎች እስከ እንቁላላቸው በታጣቂዎች ቤት ገብተዋል፤ቁጥራቸው የታወቁት ደግሞ በአባልነት ተመዝግበዋል።አብዛኛዎቹ ዶሮዎች ይሄንን የነጻነት ቀን በተስፋ ሲጠብቁ የነበረ ቢሆንም በነበረባቸው ከፍተኛ የሆነ የስራ እና የስርያ ጫና ሀሳባቸው ከግብ እንዳልደረሰ ነግረውኛል።ይህንን ስሰማ ለሌሎቹ ዶሮዎችም ለመድረስ የአቋም መግለጫችንን በማህበራዊ ድረገጾች እና በተለያዩ TV ጣቢያዎች ከቀኑ 7:00 ላይ ለመልቀቅ ተገደናል።መግለጫው ይህን ይመስላል
1⃣ኛ ዶሮዎች ጥፍጥናቸው ተመስክሮ ሳለ እስከመቼ ከሌሎች እንስሳቶች ባነሰ ዋጋ ይሸጣሉ፤ቢያንስ እኩል እንደሚሆን ዶነግ ቃል ይገባል
2⃣ኛ በሬ፣ፍየል እና በግ ስጋቸው ብቻ እየተሸጠ ስለምን ዶሮዎች እስከ እንቁላላቸው ይቸጣሉ፤ለዚህም ዶሮዎች ልዩ ጥቅም የሚያገኙበትን መንገድ ዶነግ ያመቻቻል።
3⃣ኛ ዶሮዎች ክንፍ እያላቸው በሚደርስባቸው ጫና መብረር ሳይችሉ ቆይተዋል፤ይህም ሞራላዊ እና አካላዊ ጉዳት ስላደረሰባቸው እንደ ቢጫዋ ሄሊኮፖተር የፈለጉበት መብረር እንዲችሉ እናደርጋለን።
4⃣ኛ አንዳንድ ስግብግብ ግለሰቦች የግል ጥቅማቸውን ብቻ በማሰብ 1 አውራ ዶሮን ለ10 እና ከዚያም በላይ ለሆኑ ሴት ዶሮዎች ሲመድቡ ቆይተዋል።ይህም በዶሮዎች መካከል ለዘመናት ሰፍኖ የነበረውን የእኩልነት መንፈስ በመናዱ የአዲስ ጠቅላይ ሚኒስትራችንን 50/50 መርህ በመከተል አንድ አውራ ዶሮን ለአንድ ሴት ዶሮ የሚሆንበትን መንገድ እናመቻቻለን።
.
.
.
ይቀጥላል
@bitweded

@wegoch
@wegoch
💕Under the table💕
It was under the table where we started everything
When you protected me even tho you were a kid
We were hiding from the teachers chasing us
We ran all the block and got inside the class
I can't never cease How you held my hand
And how you told me that we wouldn't be found
For the first time I felt peace by glancing at your eyes
It was surprising cause it is hard to find a person that nice.

Then after that my thoughts was all about you
That moment made me feel like you brought me the moon

We started hanging out
Under the table was our favourite spot
Where we'd talk thousands of things
About school either about our families
Simply you used to be my bliss


One day I was waiting for you sitting under the table
You approached to me (still i don't know if it was a dabble )
But it was so strangely
Looking at me differently
Then You moved your fingers on my face
You pulled back my hair which was looking a mess
Just like that my heart's beating got super intense
Was that moment which assured me that you were my pace
Not too fast I felt that lips of yours drowning on mine
I kissed you back like I was excavating a mine
Damn you! my heart and mind stopped acting fine...

Then eventually we were growing up so fast
Turned out to be big enough not to sit on our spot
Therefore it was on the table where we sat
Like often we were talking , I was upset by my family
Screaming shits out saying i have nobody
And you put your finger on my lips and
Promised you'll always be with me
I looked at your eyes n wondered how I got this much lucky
Your presence in my ride was and still a true blessing..
Two three five Years started to pass
There were millions of miles between us
We were both chasing our dreams
Doing stuffs that our minds needs
And after years of waiting we got back to our town
So to see each other we were genuinely down
But we were grownups no more sitting under the table
We Sat on the chair, our feeling flowing in the room; it wasn't stable
"God even after many years
You were looking so fabulous"
You said that to me
The next thing I saw was you were on your knee
With a ring in ur hands saying, " will you be my wife and my life " (with a look of begging)
I felt the gravity pulling
My breathing slowing
Tears from my eyes running
I shouted "yes , yes , yes I will marry you baby
I will stand by you as you stood for me"
You gave me that toxic kiss n cuddle
Nobody have seen us like that table.
And today writing this
I'm wearing my bridal dress!
🦄
@teku_melanin
@wegoch
አብሮ ለመኖር የሚያስፈልጉ ነገሮች ብሎ የሚዘረዝረው ነገር በራሱ
አድክሞኛል።ቤት,ገንዘብ,መኪና ምናምን ይለኛል ማንም ስለሀሳብ አያወራም ይሄ ሁሉ
ኖሯቸው እየኖሩ ያልሆኑ ሰዎችን ስም ዝርዝር ግን አይነግረኝም...እድሜህ ይባረክ
እንደማለት እድሜህ እንደ ማቱሳላ ይርዘም ብሎ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ አንድ መስመር ላይ
ብቻ ስላለው ሰው ይነግረኛል።እሱ ሺ ግዜ እየካደኝ አንድ ግዜ ብቻ ስለካደው ይሁዳ ሀምሳ
ግዜ ይነግረኛል....ለዛውም ያኛው ተፀፅቷል የኔው ጉድ ግን እንደገና እንዴት
እንደሚያታልለኝ ሂሳብ እየሰራ እንደሆነ ይታወቀኛል...እኔ ላገባት የምፈልገው ኪሴ ውስጥ
ባለው ገንዘብ ብቻ ነው ።ምን አለህ? ስትለኝ አንቺስ ምን አለሽ? የማለት መብቴንስ ማነው
የነፈገኝ ይሄንንስ ለምን አታስረዳትም...እሷኮ ሴት ናት ሃሃሃሃሃ ተጣልተን ስንለያይ
የተጋባነው በእቃችን እንጂ በሀሳባችን ስላልሆነ መጣላታችን አይቀርም. ..የዛኔ ሴት ነኝ
አልካፈልህም ትላለች ወይ?የምጠይቀው እያለኝ የምጠየቀው እንዴት በዛ? እሷም እኮ
ትወድሀለች አትበለኝ ሁሌም ከሷጋ የምናወራው ስለቁሳቁስ ነው።ወሬያችን እንደዛ ከሆነ
ቆይቷል ስለዚህ የኛን መጋባት አታስበው እኔኮ እወደዋለው ግን. ...ግን ካለችህ እኮ ነው
ትተሀት መምጣት የነበረብህ።ኢማን አለው ወይ ብሎ መጠየቅ የት ሰፈር ነው?,ለኔ ያለው
ነገር እንዴት አየኸው ማለትስ የት ነው?።
ስለዚህ አላገባሽም!ግን ማነች?

ሸጋ ጁምኣ!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂💛💛💛💛

አያረጅም ዘመን አልፎበት ቅን ውበቷ በእውነት ክብር የተረጋጋው ሴትነቷ!!!

ባንቺ ውስጥ ያለውን የማይታየውንና ዘላለማዊ ውበትሽን እሱን ነው ምወድልሽ.....በጊዜ ብዛት የማይከየረውን ፣ የማይረግፈውን እሱን ነው ምወደው እሱን ነው ማፈቅረው !!!! ተወዳጅዋ !!!

ሁሌም አንቺን ባሰብኩኝ ቁጥር እነዚህ ነገሮች ከልብ ምቶቻችን ባልተናነሰ እንደ ብሔራዊ መዝሙር ከነብስያችን እስከ ሙሉ አካላችን እንደ ውብ የቁርአን ቃሪ ይደጋግሙታል❤️❤️❤️



ሆድዬ ብዙ አፍቃሪዎች አሉሽ ይሁንና እኔ ደግሞ ብቻዬን አፈቅርሻለሁ !!! ሌሎች በቀረብሻቸው ቁጥር የሚያፈቅሩት ራሳቸውን ነው !!! እኔ ግን ብቸኝነትሽን አፈቅረዋለሁ !! ሌሎች ወንዶች የራሳቸውን ያህል እንኳን እድሜ የሌለውን ዉበትሽን ያያሉ እኔ ግን በጊዜ ርዝመት የማይጠፋና በእድሜ አመሻሽ ላይ ሲያዩት የማይጠፋውንና መስታወት እንደ ማያሳይሽ ያለውን የውበትሽን ማርጀት ሳይሆን ዘላለማዊ ውበትሽን አየዋለሁ ብቻዬኔም በአንቺነትሽ ውስጥ የማይታየውን እሱን


🎂
🎂
🎂🎂
🎂
🎂
🎂
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️


እንኳን ተወለድሽልኝ .....🎂🎂🎂🎂

! እስከተፈቀደልሽ ጊዜ በደስታ ኑሪልኝ....ዋናው የእድሜ
መብዛቱ ማጠሩ አይደለም በኖርንበት እድሜ የሰራነው ነገር ነው....ማቱሳላ 950 አመት
ኖሮ የሚኖርበትን ድንኳን እራሱ የቀየረ አይመስለኝ ...እንደ ነብዩ መሀመድ 63 እንደ
ክርስቶስ 33 አመት ኖረው አለምን ቀይረው የሄዱ አሉና......እናም ያሰብሽው ነገር ሁሉ እሱ
ፈጣሪ ላንተ ይጠቅምሻል ብሎ የሚያስበውን ይስጥሽ..መቼ..?አሁን!!!!!!

አላህ ከሰጠኝ ጥቂት ምርጥ ሰዎች የመጀመሪያውን ደረጃ የምትይዠው አንዱ አንቺ ነሽ😘.....ጥቂቶቹ እነማን ናቸው ብለሽ ደሞ ጠይቂ አሉሽ😁.....ነው...በእድሜሽ ልክ ሻማ ባበራልሽ እጅግ በጣም ደስ ደስ ባለኝ!!ግን ሻማውን የምታጠፊው ኡፍፍፍፍፍ ብለሽ ሳይሆን
የእሳት አደጋ መኪና ጠርቼ መሆኑን ሳሰበው .....ትቼዋለሁኝል ወጪ ማብዛት ነው!!😁😂😂😂



“አንዳንድ ሰዎች ውብ ናቸው!!
በሚመስሉት ሳይሆን በሚናገሩት።
እንዲያው በማንነታቸውም ጭምር፡፡”

የኔዋ አንቺ ነሽ ❤️❤️❤️



ለእኔ ከሚለው በላይ ...ሆድዬ❤️❤️ የእኔ የልቤ ሰው ነሸ
ወዳጅነትን በመልካምነት ብቻ ስትመዝነው ልኬቱ አንቺ ነሽ
፣ ሰው ከራሱ በላይ ለሌላኛው ወዳጁ ጉዳይ በብዙ
ሲደክም አውቃለሁ ግን ሚስትየው❤️ ያንቺ ግን ከእዚህ ሚዛን ያለፈ
ነው በቃ አንድ ሰው እንደዚህ መልካም
የሆነች ሚስት❤️❤️ ካለው የጀመረውን ይጨርሳል የያዘውን
ያሳካል ፣ የወደደውን ያገኛል
የዱንያ ጀነቴ በብዙ የተሰፈረ ፍቅርሽ መልካምነትሽ
ደግነትሽን ማሰብ ደከመኝ ራሴን እንድፈልግ በእውነት
ስለ እውነት እንድቆም የነገረሽኝን ወርቃማ ምክሮች
ዛሬ ላይ ተዘርተዋል....


በሃይል ፍቅርቅር አደርግሻለሁኝ


ሆድዬ አንቺ እኮ ልዩ ነሽ❤️...ዛሬ አንቺ ብቻ ሳይሆን እኔም የተወለድኩበት ቀን ነው....ያንቺ መወለድ ለኔ ደስታ ሰጥቶኛል ያንቺ መወለድ ለኔ እስትፋንስ የመኖር ጉጉት ሰጥቶኛል.....ያንቺ መወለድ ለኔ ህይወትን ጣፋጭ አድርጓልኛል 🎂🎂😍🎂

የኔዋ😘❤️😘 መልካም ሚስት የዱንያ ጀነት ነች !! አንቺ የኔ ጀነት

ሆድዬ"የፈለግሽውን ልሁንልሽ ስትፈልጊ ዛሬ ለሊት ከሰማይ ላይ ሃምሣ ኮኮብ ለቅሜ፣ጠዋት አንድ የብርሃን ጮራ እበጥስና ፣ ከብርሃን ክር በኮከብ ዶቅ ልዩ ያንገት ሀብል እሰራልሻለሁኝ። ጨረቃዋን ሰርቄ መስታወት እንድትሆንሽ እሰጥሻለው። ሰማዩ ባዶውን ይቅር!!! ጨረቃም ላንቺ ብቻ ታብራ !! ላንቺ ያልሆነ ለማን ሊሆን ይችላል ( ያውም በልደትሽ ቀን )

ሆድዬ ሆድዬ ሆድዬ

የመልአክት ምርኩዜ የለሊት መብራቴ
ስራብ እንጀራዬ ስጠማ ወተቴ
ሳዝን መፅናኛዬ ስደክም ጉልበቴ

( ፍቅር እስከ መቃብር እስታየል😊😍 )


ፍቅር የወፎች ዝማሬ እያደመጡ በአበቦች መሀል የመንሸርሸር ጉዳይ አይደለም። ፍቅር የሞራል ፍልሚያ ነው። በመሸነፍ ሚያሸንፋበት ትግል። ጠንካራ ውብ ስብዕና ያላቸው ብቻ ሚጎናፀፉት የመንፈስ ገፀ በረከት !!! እኛ የዚህ በረከት ተቋዳሽ ነን !!! በማን ..? ባንቺ መወለድ ነዋ የኔዋ ሆድዬ❤️❤️❤️አንቺ እኮ በጭንቅላቴ ውስጥ ተወሽቄ ከመኖር ታድገሽ ወደ አስደሳች የህይወት ምዕራፍ ያሸጋገርሽኝ ፍጡር ነሽ .....በመወለድሽ🎂🎂🎂

በመጨረሻም ሆድዬ .....

ጥላሁንን ሙዘቃን አፈቀረ አነገሰችው

ዳቪንቺ ስዕልን አፈቀረ ያለሱ መጠራት አቆመች

ሞዛርት ሙዚቃን አፈቀረ ያለሱ መጠራት አቆመች....ከፍ ከፍ አደረገችው

ሶቅራጠስ ፍልስፍናን ከምንም በላይ አፈቀራት እሷም መልሳ ከማንም በላይ አፈቀረችው


ሆድዬ እኔ አንቺን አፈቀርኩሽ ከፍ ከፍ አልኩኝ....ነገስኩኝ.....ይሄ እንዴት ሆነ በመወለድሽ.....ደስታ ውስጥህ ነች ይባላል አንቺ ውስጤ ነሽ እላለሁ እኔ....ስለዚህም የኔ ደስታ አንቺ እና አንቺ ነሽ እንኳንም ተወለድሽልኝ!!!!!!


አላህ ይቺን ሴት እንዳፈቅራት ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ !! አላህ የዱንያም አላህ ከሷም እንደሷ የሆኑ ልጆችን ስጠኝ ከሷም ሳሊህ ልጅ ስጠኝ የአኺራ ሚስቴ አድርግልኝ !!! አሜን !!!!❤️❤️❤️



የልደትሽ ቀን ነዉ
ስወድሽ ልክ የለኝም…
እኔ ካንቺ ጋር ሆኜ ግማሹ እኔ ተኝቷል
የተኛው እኔ በህልሙ ስላንቺ ብቻ ያልማል
አልቀሰቅሰውም ይተኛ ስላንቺ ማለም ደስ ይላል
ስወድሽ ልክ የለኝም ህልሜን ራሱ አዝዘዋለሁ
ስለሷ ብቻ አልም ሌላውን ተወው እለዋለሁ
ስወድሽ ልክ የለኝም…
ከሳቅ ዓለም ተለይቼ ከግርግር ከቱማታ
ከያንት ያለህ እቁብተኛ ከማያልቀው ሰልፍ ተርታ
ግንባሬን አኮሳትሬ የደበኩትን ፈገግታ
ያስቀመጥኩትን ይመስገን የቆጠብኩትን ሰላምታ
ላንቺ ይሁን ይገባሻል ሌሊት ጠዋት ቀንም ማታ
ስወድሽ ልክ የለኝም…
ሁሉን ነገር ስመለከት ከደስታ ጋር ደስ ሲለኝ
ምድርን በእግሬ እየረገጥኩ አየሩ ላይ በጄ ስዋኝ
ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ…
ከቁርስ ጋር ተጣልቼ ቀዝቃዛ ዉሃ እየጠጣሁ
ስወድሽ ልክ የለኝም ለዚህ ግጥም መዝጊያ አጣሁ
ስወድሽ ቃላት የለኝም ቃላት ደብዛቸው ይጠፋል
ግጥሙ ዝርዉ ይሆናል ዝርው ደግሞ ይገጥማል
እንዳሻው ይሁን ግድ የለም ልቤ ግን አንቺን ይወዳል
የልደትሽ ቀን ነዉ🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂❤️🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂



እጅግ በጣም አፈቅርሻለሁኝ❤️❤️ ይሄን የምለው ሆድዬ...ከዚህ በላይ ቃላት በተጠቀምኩኝ.....ግን ቃላት እንደኛ ስሜት መለጠጥ መስፋት በቻሉ...ለካ ቃላት ለምታፈቅሪው ሰው ልትጠቀሚበት ስትይ ደካሞች ናቸው!!! ብቻ በሃይል አፈቅርሻለሁ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️


ሆድዬ መልካም ልደት !!!!ተወዳጇ🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂
ስኳር ስኳር አለኝ ..
«ዘውድአለም ታደሰ»
ታላቁ፣ ዝነኛው፣ ደጉ፣ ቸሩ፣ ሼህ አላሙዲን ግፈኛው የሳውዲ መንግስት በአሰቃቂ ሁኔታ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ አስሮ በግፍ ሲያሰቃያቸው ቆይቶ እንደለቀቃቸው በሰማሁ ግዜ በደስታ አነባሁ። እርግጠኛ ነኝ ንዋይ ደበበ ራሱ ያን ሁሉ ብር ተቀብሎ እንደኔ አላለቀሰም። አለቃቀሴ "ሐገሬ ከገባሁ ማፊ ሞልን ከመስፍን ባሪያው ቀምቼ ላንተ እሰጥሃለሁ" ያሉኝ እኮ ነው ምመስለው።
ክቡራትና ክቡራን .... እንደምታውቁት እኔ ታማኝ አድናቂያቸው ሼሁ ከታሰሩ ቀን አንስቶ የሳውዲ መንግስትን ሳወግዝ እንደነበር የታወቀ ነው። እንደውም ሳውዲ ባስቸኳይ የማትለቃቸው ከሆነ ሳውዲ ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል የምታገለግለው ያክስቴን ልጅ በማስወጣት ከባድ ማእቀብ ልጥል ዝቼ ነበር። ይኸው ዛሬ ድምፄ ተሰምቶ ታላቁ መካሪዬና ሁለተኛው አባቴ ተለቀቁ። (እዚች ጋር ከባድ እልልታ)😂😂😂
ይህን ታላቅ ተጋድሎ ያደረግሁት ከሳቸው ምንም ፈልጌ አይደለም። ከቤት፣ ከመኪና፣ ከገንዘብና ከተመጣጠነ ምግብ ውጪ ሁሉም ነገር የሞላልኝ ሰው ነኝ። በርግጥ ጋሼ በሳውዲ መንግስት ላይ በግሌ የጣልኩትን ከባድ ማእቀብ ከግንዛቤ አስገብው ለማስታወሻነት ጥቂት ሚሊየኖች ቢለቁብኝ እሳቸውን አክብሬ ልቀበል እችል ይሆናል። ከዚህ ውጪ ግን ቤሳቤስቲ አልፈልግም። ፍቅራቸው ይበቃኛል።
የጎደለኝ በዚች አለም
አንድም ነገር የለም
ደስተኛ ነኝ ሁሌም፣ ባልኖርም ዘላለም
ብሏል ሸዋንዳኝ! አንዳንዴ በዘፋኞቻችን መሃከል ያለ የኑሮ ልዩነት ግርርም ይለኛልኮ ጓዶች!! ሸዋንዳኝ የጎደለኝ ነገር የለም ሲል ፀጋዬ እሸቱ ደግሞ
“ሆዴ ክፉ እዳዬ
መሆኑን አወቅሁት
እህል ውሃ ሲለኝ
ሆዴንም አፈርሁት
የገዛ ገላዬን ሳጣ እየታዘብኩት”.. ብሎ አስለቅሶናል። እንግዲህ ህይወት ለሸዋንዳኝ ድሎት ለፀጋዬ ደግሞ ችሎት እንደሆነችበት እንረዳለን
አብዛኞቹ ዘፈኖቻችን ከምግብና ከሆድ ጋር የተያያዙ ለምን እንደሚሆኑ ግርም ይለኛል። አድናቆታችን ራሱ "ሆዴ" ምናምን ነው። አሁን ባልጠፋ አድናቆት ስንት ነገር አግበስብሶ የያዘውን ሆድ እንደመወዳደሻ መጠቀም ተገቢ ነው? ነው ወይ?
አንዳንዴ ውሃ ሳይጎነጭ ሁለት ኪሎ ስጋ ሲጥ የሚያደርገው ጎረቤቴ ያን የደሃ ጎጆ የሚያህል ቦርጩን እያሻሸ ሚስቱን «ሆዴ» ብሎ ሲጠራት ብስጭት እላለሁ። ደሞ ከሱ ይልቅ ምታናድደኝ ሚስቱ ነች «ሆዴ» ሲላት «ወዬ» ትለዋለች እየሳቀች። ብታይዋትኮ የሆነች ሆዱ ውስጥ ፍራሽ አንጥፋ ሁሉ ሰፋ ብላ ልትተኛ የምትችል ሲምቢሮ እኮ ነች! አሁን የፈረንጅ ሚስት ባሏ «ማይ ስቶማክ» ቢላት ከባድ አምባጓሮ አታነሳም? አታነሳም ወይ?
እና የዘፋኞቻችን ነገር ግርም ይለኛል ጓዶች! የትዝታው ንጉስ መሃሙድ አህመድ ራሱ በምግብ ዙሪያ ያጠነጠነ ዘፈን ያበዛል።
«ከናት ካባትሽ ቤት ጮማ ሰልችቶሻል፣ አትስጊ በኔ ዘንድ ልብ ይቀርብልሻል» የምትል አንድ አንጀት የምትበላ ዘፈን አለችው። ስጠረጥር የተዘፈነላት ሴት ወላጆች ትልቅ ልኳንዳ ቤት አላቸው። በግዜው ደሞ መሃሙድ ያው ምስኪን ዘፋኝ ነው። ድንገት ምላስ ሰምበር ሊበላ አባቷ ስጋ ቤት ሲገባ ሾፋት!! እንደሾፋት ወደዳት!! ከዛ ብእሩን አንስቶ ከላይ ያለችውን ግጥም ፃፈ ... በግዜው አባቷ ዘፈኑን ቢሰሙ ለመሀሙድ እንዲህ ብለው ግጥም የሚፅፉለት ይመስለኛል ...
ሽንጡ ሞልቶ ተርፎ
ጮማው ተትረፍርፎ
ዳቢቱ ቅልጥሙ ፥ ሞልቶ ሳለ ደጄ
ልብ ላብላሽ ያልካት ፥ ድመት ነች ወይ ልጄ?
ስለዘፋኞቻችን ካነሳን አይቀር የዘንድሮ ዘፋኞች ፋሽን ደግሞ ማር ነው!! ማሬ ማሬ የማይል ዘፋኝ የለም። ያኛውም ማር ነው። ይሄም ማር ነው። አረ ማር በዛ ብንል ማን ይስማን? በማር ተጥለቅልቋል ዘፈኑ ሁሉ! ከዚህ ሁሉ ዘፋኝ “ቂቤዬ” ብሎ ሚዘፍን አንድ ዘፋኝ መጥፋቱ በውነቱ ያሳዝናል።
ማር ስል ስኳር ትዝ አለኝ። ስኳር ስል አስቱካ ትዝ አለችኝ! አስቱካ የኔ አስማተኛ በደጉ ዘመን ጠይም ዘለግ ያለ ጎራዴ ታጣቂ የሆነ ሰውዬ ሳመችና «ስኳር ስኳር አለኝ ብቀምሰው ከንፈሩን» ብላ በዚያ ተስረቅራቂ ድምጿ አዜመች!!
ይህን ዘፈን በግዜው የሰማ አጎቴ
«እቺ ሴትዮ ስኳር ስኳር ያላት የሳመችው አባይ ፀሃዬን ነው እንዴ?» ለምን አይለኝም? አረ ሰዉ ነገረኛ ሆኗል!
መቼም እኔ ከጀመርኩ ካልተጋጨሁ አላቆምም። ወደሼሁ ጉዳይ ልመልሳችሁ!!
እህሳ ....እንዴት ነው ሼሁን ምንቀበላቸው? ምን አይነት ዝግጅት እናድርግ? በሚለው ሀሳብ ዙሪያ ለሊቱን ሙሉ ፕሮግራም ሳወጣ አድሬ ሼሁ ከሳውዲ ቀጥታ ጅጅጋ መግባታቸውን ሰማሁ። እንደቅርበታችን እኔን ሳያገኙኝ ጅጅጋ መሄዳቸው ቅር አሰኝቶኛል። ቢሆንም ግድ ግድ የለም አዲሳበባ ሲገቡ ሞቅ ደመቅ ያለ አቀባበል ልናደርግላቸው ይገባል ባይ ነኝ።
እንደኔ እንደኔ ልክ ሼሁን የጫነችው አውሮፕላን መሬት ስትረግጥ ከፕሌኗ እስከ ሸራተን የሚደርስ ሬድ ካርፔት እንዲሁም እንደአሳዬ ደርቤ አይነት ድሆች ይነጠፉላቸው ... አንድ ብርጌድ ጦርም የሰልፍ ስነስርአት ያድርግ። ልክ ጋሼ ከአውሮፕላን ሲወርዱ ታዲያ የኔ ልጅ ሮጣ ሄዳ እቅፍ አበባ ታበርክት ... ጥቂት እንደተራመዱም የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሲከበር ኮባ ለብሶ የሱርማ ባህላዊ ጭፈራ የሚያቀርበው አጎቴ ኮባ ለብሶ ዳሌውን እያወዛወዘ ይጨፍር ... ጥቂት ራመድ ሲሉ ደግሞ መከላከያ ሰራዊታችን አምስት መድፍ ይተኩስ። (አምስቱ ቁጥር ሼሁ የታሰሩበትን አምስት ኮከብ ሆቴል ይወክላል)😳
እዚህ ጋር አደራ ምለው መከላከያ ሰራዊታችን ለምዶበት መድፉን ወደህዝቡ እንዳይተኩስ ጥንቃቄ እንዲደረግ ነው። ኋላ ፈጅተውን ተመጣጣኝ እርምጃ ነው የወሰድነው ምናምን ቢሉ የማን ያለህ ልንል ነው?
ከመድፉ በኋላ እኔ የሳውዲን መንግስት የሚያወግዝ ዘለግ ያለ ግጥም በእንባ ተሞልቼ አነባለሁ። ሼሁ መቼም የኔን ግጥም ሲሰሙ ልባቸው እንደሚነካ የታወቀ ነው። እሳቸው ደግሞ ልባቸው ከተነካ ቼክ የሚመዙት ነገር አለ። ቼኩን ሲመዙ በፍጥነት ሮጣ ብእር እንድታቀብል ደራርቱ ቱሉ በቦታው እንድትገኝ ይደረግ።
በስተመጨረሻም ታከለ ኡማ ፒያሳ ላይ ሳይታዘዝ የሼሁን አጥር ያፈረሰውን የዶዘር ሾፌር ለፍርድ እንደሚያቀርብ ይግለፅ።😜
ሼሁ ከኤርፖርት እንደወጡም ደሞዛቸው ከሶስት ሺ ብር በታች የሆኑ ሰዎች ወደቤታቸው እንዲገቡ ትዛዝ ይተላለፍ።
ስላዳመጣቹኝ አመሰግናለሁ😂
@wegoch
@wegoch
@kaleab_1888
“መንግስትነት ንግስና አይደለም” (ተመስገን )

በጥንት ዘመን ነው፡፡ ሰውየው ቀኑን የሚያሳልፈው መጽሐፍ ሲያነብና
ሲደግም፣ ሲደጉሥ፣ ሲጠርዝና ሲፅፍ ነው፡፡ አስማተኛ፣ መጽሃፍ ገላጭ፣
ኮከብ ቆጣሪ፣ ጋኔል ጠሪ፣ ጠጠር ጣይ፣ ጠንቋይ፣ ደብተራ እያሉ ያወሩበታል፡፡
ነቃ ያሉት ደግሞ ‹ሊቅ› ይሉታል፡፡
የአገሪቱ የበላይ ቧለሟሎችና የእምነት አጋፋሪዎች ሰውየውን አይወዱትም፡፡
ችሎታቸውን የሚያሳንስባቸው ስለመሰላቸው አሴሩበት፡፡ በንጉሱ ዕልፍኝም
ሆነው፡- “ህዝቡ የሚያዳምጠው እሱን ነው፤ ለአልጋህ ያሰጋሃል፡፡” በማለት
አሰማምረው መሰከሩበት፡፡ ንጉሡም እንዲታሰር አዘዘና ተያዘ፡፡ የከተማው ወሬ
ግን ባሰ፡፡ … “ሰይጣን በሱ ተመስሎ እንጂ እሱ አይደለም የታሰረው፣ በዚህ
ሲያገድም፣ በዚያ ሲያልፍ አይተነዋል፣ በዓይጥ ተመስሎ ከእስር ቤቱ እየሾለከ
ይወጣል ወዘተ… ወዘተ ተባለ። ሰውየው ይኸን ሲሰማ በአገሬውና
በሹማምንቱ ጅልነት እየተገረመ ይስቃል፡፡ ዘበኞቹ ደግሞ … “አንድ ነገር
ቢኖረው ነው፣ የታሰረ ሰው ይከፋል፣ ይተክዛል እንጂ እንዴት ይስቃል?” እያሉ
ተሸበሩ፡፡ ነገሩ ሲገን ንጉሡን አሳሰበውና “ስቀሉት!” ብሎ ፈረደበት።
ሊሰቅሉት በወንበሩ ላይ እንዳቆሙት፣ ወታደሩ ገመዱን አንገቱ ላይ
ለማጥለቅ እጁ ተንቀጠቀጠ። ሰውየውም … “አይዞህ! የምሞት
እንዳይመስልህ፤ ነገ እንገናኛለን” አለው፡፡ ወታደሩም የሚወራውን ያውቃልና
ሰይጣን መሆን አለበት ብሎ በመደናገጥ እየጮኸ ፈረጠጠ፡፡ ሌላ ወታደር
ቢመጣም ያው ሆነ።

ራቅ ብሎ ተቀምጦ የነበረው ንጉሥ፤ ግራ እየተጋባ ወደ ሰውየው ቀርቦ …
“ከዕውቀትህ አካፍለኝና የፈለግኸውን ሰጥቼህ ወዳሻህ ትሄዳለህ” አለው፡፡
ሰውየውም … “ድግምት ስላለኝ፣ ሞት አይቀርበኝም፡፡ የተናገርከውን
የምትፈፅም ከሆነ አንተንም እንደ‘ኔ አደርግሃለሁ፡፡” በማለት ተስማማና
እንግዳ የሆኑ ቃላቶችን እንዲያጉተመትም አስጠናው፡፡ ንጉሱም ደስ እያለው
ለተሰበሰበው ህዝብ “ሟች” አለመሆኑን ለማሳየት፣ በሰውየው ምትክ ወንበሩ
ላይ ቆመ፡፡ ሰውየውም ገመዱን አንገቱ ላይ አጥልቆ ሸመቀቀና ወንበሩን
በፍጥነት ከስሩ አሸሸው፡፡ … ከዛስ?

አንዳንድ ሊቃውንት “ገሃነም ማለት ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡ (Hell is other
people)” ይላሉ። አያን ራንድ፡- “ሰብአዊነትን አከብራለሁ፤ ሰዎችን
እወዳለሁ፡፡ ነገር ግን አንድ ሳምንት ከሌሎች ሰዎች ጋር ቢዘጋብኝ አብዳለሁ”
ብላ ነበር፡፡
“እየተመራመርክና እያወቅህ ስትመጣ የህይወትን ምስጢር ትረዳለህ፡፡ … ያ…
ደግሞ ወደ ማታሸንፈው ጦርነት ውስጥ ያስገባሃል፡፡ (“The more you
read, the more you know; the more you know, the more you
understand life. The more you understand life, it puts you in
a war that you cannot win”) በማለት የፃፈልን ደግሞ ጀምስ ሚሽነር
ነው - ‹ዘ ፋየርስ ኦቭ ስፕሪንግ› በሚለው መፅሃፉ፡፡
ታላቁ ሾፐን ሃወርም በበኩሉ ይህንኑ ጉዳይ … “ሰው እያወቀ ሲመጣ በጥልቅ
ያስባል። በማሰቡም የሚያተርፈው መከራን ነው፡፡ (The more distinctly
a man knows-the more intelligent he is, the more pain he
has; the man who is gifted with genius suffers most of all.”)
በማለት ያረጋግጥልናል፡፡
ወዳጄ፡- ዛሬ የጥምቀት በዓል እየተከበረ ነው። መጥምቁ ዮሐንስ … “ከኔ
በኋላ የሚመጣ … እሱ በእሳት ያጠምቃችኋል” ማለቱን ታውቃለህ? …
አትፍራ፡፡ እኔ እንደገባኝ ነዳጅ አርከፍክፎ፣ ክብሪት ጭሮ ያነዳችኋል ማለቱ
ሳይሆን እውነቱን ይነግራችኋል ለማለት ነው፡፡ እኔም ጥቅስ ባበዛብህ
አይግረምህ፡፡ … ጥምቀት ነዋ!! … እንኳን አደረሰህ!!
ወዳጄ፡- ዓለምን የቀየሯት ስልጣኔያችንን የሰጡን ጥቂት ሰዎች ናቸው፡፡
እነሱ፡- በመከራቸው የሚስቁ፣ በራሳቸው የሚጨክኑ፣ ታላቁን ተራራ
እንድንወጣ የሚያግዙን … እነሱ ክቡር ናቸው፡፡ በተመሳቀለ ኑሮ፣ ፖለቲካና
ኢኮኖሚ ውስጥ የማይንገጫገጩ፣ ዓይተው የማያዩ፣ ዐውቀው የማያውቁ
የሚመስሉ፣ እያሉ የሌሉ፣ በሌሉበት ደግሞ ያሉ እነሱ ህያው ናቸው፡፡
በጥቅም የማይደለሉ፣ ለማንም የማያዳሉ፣ ማወቅ ፍዳ የሆነባቸው … እነሱ
ናቸው የለውጥ አባቶች፡፡ እኛ ግን ብዙ ይቀረናል፡፡ … ታላቁ ፀሐፊ ኸርነስት
ሄሚንግዌይ እንዲህ ፅፏል፡-
“If people bring so much courage to the world, the world has
to kill them, to break them. It kills the very good and the very
gentle and the very brave impartially”
ወዳጄ፡- ሰው ለህሊናው ካልኖረ፣ ለስርዓትና ለህግ ካልተገዛ ኋላቀር ይባላል፡፡
ኋላቀርነት አለመሰልጠን ነው፡፡ ባደጉና ራሳቸውን በቻሉ ሐገሮች ባህል ማለት
ስልጣኔ፣ ስልጣኔ ማለትም የዘመናዊነት ባህል ነው። በሌላ አነጋገር
“ዴሞክራሲ” ወይም ራስን በራስ የማስተዳደር ዘይቤ እንደ ማለት ይሆናል፡፡
ስርዓቱ፡- ዜጎች እንደ ‹ዜጋ› ስለሃገር፣ እንደ ግለሰብ ስለ ስራቸው፣ ስለ
ቤተሰባቸውና ስለሌሎች ብዙ ነገሮች በነፃነት የሚያስቡበትና የሚፈልጉትን
የሚሆኑበት ልማድ ነው፡፡ መንግስት ደግሞ የተሻለ ሃሳብና ጉልበት
(energy) ኖሯቸው፣ የበለጠ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ሌሎች
ግለሰቦችና ድርጅቶች እስኪዘጋጁ ድረስ ጎንበስ ቀና ብሎ፣ በቀናነት
በማገልገል ህግና ደንብ የሚያስፈፅም ተቋም ነው፡፡ መንግስትነት ንግስና
አይደለም፡፡
ለዚህ ነው፡- ታላላቅ ሳይንቲስቶች፣ የፈጠራና የጥበብ ሰዎች የሚወለዱት፤
ህዝባቸውንና አገራቸውንም ታላቅ የሚያደርጉት፡፡ ስልጣኔ አያስቀናም ወዳጄ?
***
ወደ ተረታችን እንመለስ፡- በቅዠት የተተበተበው ህዝብና በቅናት የበገኑት
ቧለማሎች፤ ሰውየው በሃሰት እንዲከሰስ ማድረጋቸውን፣ ንጉሱም ስቅላት
እንደፈረደበት፣ ሰውየው ደግሞ የአእምሮውን ኃይል ተጠቅሞ ከሞት ለመዳን
እንደዘየደ ተጨዋውተናል። ንጉሡም ዕውቀቱን ቢያካፍለው የፈለገውን
ሰጥቶት እንደሚሸኘው ቃል በመግባቱ ሰውየው ‹ሞት የሚያርቅ› ድግምት
አስጠንቶት፣ ‹ሟች› አለመሆኑንም ለሚገዛው ህዝብ ለማሳየት፣ በሰውየው
ምትክ ወንበሩ ላይ እንደቆመና ገመዱን እንዳጠለቀ፣ ሸምቀቆውም
እንደጠበቀ፣ አውርተናል፡፡ በዚያው ቅጽበት ሰውየው ንጉሱ የቆመበትን ወንበር
ከስሩ በመሳቡ ንጉሡ ተንጠለጠለ፡፡
አፍታም ሳይቆይ ትንፋሹ ተቋርጦ ሞተ፡፡ ሰውየውም ወንበሩ ላይ ቆመና ጮክ
ብሎ፤ “ከዛሬ ጀምሮ …” በማለት መናገር ሲጀምር አደባባዩን የሞላው ህዝብ
እያጨበጨበ “… ንጉሣችን አንተ ነህ!” በማለት ሰገደ፡፡ ሰውየው ማለት
የፈለገው ግን ሌላ ነበር፡፡ … እስኪ ገምት፡፡😊
ሠላም!!

ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ ( ጥር 11 ቀን 2011 )

ሸጊቱ ምሽት!!!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
2024/09/28 17:22:04
Back to Top
HTML Embed Code: