Telegram Web Link
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

🗣...........ጉዞ ወደሀሳብ

ህሊና
...........................................
ህሊና በተፈጥሮ የሚገኝ ነው በባህል ወይም በሀይማኖት አልያም በትህምርት ደረጃ አማካኝነት የሚሰርፅ??

ህሊና ከቦታ ቦታ ይለያያል?
ትክክለኛ ህሊና የሚያስብል መመዘኛ የጋራ ሚዛን አለ??

በአንድ አካባቢስ ተመሳሳይ የህሊና ጥያቄዎች ይዳብራሉ?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

👇👇👇👇👇👇👇እየተሳተፋቹ

@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
ብቻ. . . .ሰው ሁን!
-
ብቻዬን በምሆንባት አጋጣሚ ትዝብት አላጣም። መንገድ ላይ ብቻዬን ስጓዝ፣ ጠዋት ከእንቅልፌ ነቅቼ እስክነሳ ባለው ሰዓት፣ ማታ ተጋድሜ እንቅልፍ እስኪያሸልበኝ ድረስ፣ መዝሙር ወይም ሌላ ሙዚቃ ሳዳምጥ ወዘተ. . .
በሕይወቴ ስታዘበው የኖርኩት አል-ሐበሽ አዛኝነቱ ለመንግሥተ ሰማይ ቃብድነት፣ እርዳታው ለታይታ፣ ጥየቃው ለውለታ፣ ፈገግታው ለውዳሴ፣ ወዘተ ነው። Altruistic የሆነው ክፍሉ ወይ ተረት ነበር፣ ወይ በወላጆቻችን ጊዜ ቀርቷል። ብቻ በአመዛኙ ደንቆሮ፣ ዥልጥ እና ጨካኝ ነው። ይሄ እሱነቱ ግን ለራሱ አይታየውም። ነጋ ጠባ የሌላውን ጉድፍ ሲያጠራ ይውላል እንጂ የራሱ ምሰሶ ፈፅሞ ልብ አይለውም።
እንደ ሀገር ሁላችንንም የሚመለከት ትዝብት ስጭር ፈጥኖ የሚታየው የተባለው ነገር ሳይሆን ብሔር ነው። ስለራሴም ጭምር ሳይሆን ስለሌላው ብቻ ያወራሁ አድርጎ ይረዳዋል። ልብ በል፣ ከሱ ፈጥኖ ሌላውን «ዘረኛ» የሚል የለም። ነገር ግን ቅንጣት ዘር ከሰው ሁሉ ቀድማ ለሱ ዓይንና አስተሳሰብ ስትገለጥ ነው የምትታዘበው። ነፍፍፍፍ አጋጣሚዎች አሉልህ፣ አይንህን ከፍተህ ብቻ ተመልከት . . .
ሌላው ቀርቶ የዛሬ ዓመት በኃማደ እና ከወላይታ በመጣ ሰው አንድ የፀሎት ቀልድ ስትቀልድ የሳቀ ሰው፣ ዘንድሮ በአብይ እና ከጅማ በመጣ ሰው ቀይረህ እሷኑ ቀልድ ስትነግረው ኡኡ ይልብሃል። ቄሮን በለው ሲል የነበረ ሰው ፋኖ ሲነካ እዬዬውን አትችለውም። ሌባ አሳልፌ አልሰጥም ብሎ ሽንጡን ገትሮ ሲከራከር የነበረው ሰው ስለሌሎች ሌብነት ሲያወራ አፉን ያዝ አያደርገውም። ነፍፍፍ ነገር ታያለህ።
አሁንም ሥልጣን ላይ ያለው (በተለይ በመካከለኛው እና በስረኛው የአመራር ቦታ ላይ) ኢህአዴግ መሆኑን እያወቀ፣ በተለይ ደግሞ በኢህአዴግ ባህል እና መዝገበ ቃላት «እርምጃ» ምን እንደሆነ በደንብ እያወቀ እሱ ወይም «ዘመዶቹ» እንደማይኖሩበት አካባቢ ላይ ሲሆን «መንግሥት ተቅለሰለሰ፣ አልቻለም፣ ቆፍጠን ይበል እንጂ፣ እርምጃ ይውሰድ» ሲል ትሰማዋለህ። ማን የቱ ላይ ይሄንን አስተያየት ሰጠ ብለህ ታዘብ። ኦሮሚያ ላይ ችግር ሲኖር ማን እርምጃ ይወሰድ እንደሚል፣ አማራ ክልል ችግር ሲኖር ማንኛው እርምጃ ይወሰድ ብሎ እንደሚወተውት፣ ትግራይ ውስጥ የሆነ ነገር ሲፈጠር መንግሥትን ተኩስ ብሎ የሚማፀነው ማን እንደሆነ ተመልከት።
መተኮስና መግደል የመንግሥታት አንዱ «ተፈጥሮ» ነው። ሁሉም መንግሥታት ተመጣጣኝና ምክንያታዊ እስከሆነ ድረስ ግድያን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎችን ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በዜጎች ላይ እንዲወስዱ ከዜጎች ጋር ውል ገብተዋልና ይሁን፣ ባትወደውም ትቀበለዋለህ። ነገር ግን አንድ የኔ ቢጤ ተራ ግለሰብ መንግሥትን «ኧረ ግደል» እያለ ሲወተውት ማየት ይዘገንናል፣ ይቀፋል። መንግሥት ይሄንን ውትወታውን የትኛው አካባቢ ላይ ሲደርስ እንደሚሰማና እንደሚወስድ አይታወቅም። እርምጃውን «የኔ» በሚለው አካባቢ ሲወስድ ይሄው ወትዋች ለኡኡታ የሚቀድመው የለም። ለራሱ አይታወቀውም እንጂ በአመዛኙ ሕዝቤ ደንቆሮ፣ ዥልጥ እና ጨካኝ ነው የምልህ ፌስቡክ ላይ የምታየውን ሰው ጨምሮ ነው። ተገቢው ሚዛን ስለሚጎላቸው ለኔ ከዋናው በዳይ አይሻሉም። እጃቸው ላይ መሣሪያው ስለሌለ እና ተጠያቂነት ፈርተው እንጂ «እርምጃውን» በጠሉት ወገን ላይ ራሳቸው የሚወስዱ ታይፖች ናቸው።
እዚህ ጋር ደግሞ እኔ አለሁ። እኔ ደግሞ ብሶታም እንስሳ ነኝ። ቶሎ ይከፋኛል። ሳላስበው ከሰው ብዙ ስጠብቅ ራሴን አገኘዋለሁ። ብዙ የጠበቅኩበት ሰው 8ኛ ክፍል እያለሁ ከነበሩኝ ዶሮዎች ቂጥ ትንሽ ጠበብ ያለ የዕይታ አድማስ ኖሮት አገኛለሁ። እናም የእኩልነት፣ የፍትህ እና የወንድማማችነት ዲስኩር ለማን ነው የማሰማው ብዬ ጠይቃለሁ። በምክንያትና በማስረጃ የማወራቸው በቂ ወዳጆች አፍርቻለሁ፤ ከነሱ ጋር በማገኘው አጋጣሚ አወራለሁ። እከራከራለሁ። እተራረማለሁ። ብስማማም ባልስማማም አልናናቅም። «ሚስ አንድርስታንድ» አልደራረግም። ያንን መርጫለሁ።
ይኸውልህ፣ እዚህ ሰፈር ስትውል የአዕምሮ ጤንነትህን መጠበቅ አለብህ። በዋናነት የምታነባቸውን ሰዎች ምረጥ። የጽሁፋቸው ዓላማ እና ድምዳሜ ላይጥምህ፣ ላያሳምንህ ይችላል። ጊዜህን በንባብ ካባከንክበት አይቀር አፃፃፍ፣ ዳታ፣ ምክንያት ወዘተ አግኝበት። ገልቱ ጽሁፎችን ተከታትለህ አንብበህ ጨጓራህን አትላጥ። መልስ እየሰጠሀቸው ከተገቢው በላይ ዝነኛ ያደረግካቸው ምናምንቴ troll farmers አሉ። እነሱ ሽቀላ ላይ ነበሩ። ንቃ። አንተ በነሱ ተናደህ ሌሎች ሰዎችን አትነጅስ። ደደብ እና ጨካኝ ያልሆኑ፣ ነፍፍፍፍ አሪፍ ፖዘቲቭ ሰዎች አሉ። ተወዳጃቸው። ስልክ ተቀባበል። ተገናኝተህ ማኪያቶ፣ ቢራ ጠጣ። ወዳጅነታቸውን መሬት አውርደው። እድለኛ ከሆንክ ከስጋ ዘመዶችህ የሚቀርቡህና ሀሳብህን የሚረዱህ፣ ምርጥ የዕድሜ ዘመን ወዳጆች ታፈራለህ። ብቻ... ሰው ሁን፣ አይፀፅትህም።
ፈይሳ ቀን!!

@wegoch
@paappii

#gamechu
በፍቅርና በሐይማኖት ስም…….

ለዚህ አጭር ጽሁፍ ሁለት አባባሎችን በአንድ ላይ ልጠቀም እፈልጋለው። እውቁ
የመንፈሳዊ መምህር ዳይላ ላማ፤ ስለፍቅር እና ስለ ሐይማኖት በተለያዩ ግዜያት
የተናገሯቸውን ድንቅ አባባሎች ነው ልጠቀም የሻትኩት።

“ለምትወደው ሰው የሚበርበትን ክንፍ፤ ተመልሶ የሚመጣበትን ስር፤ ካንተ ጋር
የሚቆይበትን ምክንያት ስጠው” ብለዋል። በሌላ ንግግራቸው ደግሞ
ስለሀይማኖት እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፤ “የሀይማኖት አላማ እራስህን
ለመቆጣጠር እንጂ፤ ሌሎችን ለመውቀስ አይደለም”።

ሁለቱን በተለየያ እርስ ላይ የተነገሩ የሚመስሉ አባባሎችን የመረጥኩበት
ምክንያት፤ ሁለቱንም የሚያሳስራቸው ነገር ስላለ ነው፤ ይኸውም ለሌሎች ነጻነትን
መስጠት የሚለው ሀሳብ። ዳይላ ላማ ያለምክንያት እኒህን ጥልቅ ንግግሮች
አልተናገሩም። እንደኔ ነገር መሰነጣጠቅ ለሚወድ ሰው ከውስጣቸው ብዙ
ነገሮች ሊወጡባቸው የሚችሉ ንግግሮች ናቸው።

እዚህ ምድር ላይ በእየለቱ የምናያቸው መጥፎ ክስተቶች በአብዛኛው
የሚተገበሩት በመልካም ነገር ስም ነው። በተለይም ደግሞ በፍቅር እና
በሃይማኖት ስም ብዙ ጥፋቶች ይከሰታሉ። አንዳንዴ ግራ የሚያጋባ ይሆናል፤
በፍቅር ስም እስከግድያ የሚደርሱ ሰዎች አሉ፤ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ
እየተጠቀሙ የሚሳደቡ ሰዎች እጅግ ብዙ ናቸው። እዚህ ላይ እኔ ሌላውን
ለመውቀስ ፈጽሞ አልሞክርም፤ ግን ድርጊቶቻችንን ቆም ብለን ብናስተውል፤
ምክንያታችን በደንብ ይገባን ይሆናል።

ፍቅር እና ሀይማኖት በነጻነት ይተሳሰራሉ፤ ነጻነት ስል ለሌሎች ደስታ ስንል
በመንገዳቸው አለመቆም ማለት ነው። ጸጋዬ ገ/መድህን “ዝም ብለን አብረን
ዝም እንበል” በሚለው ግጥሙ ላይ ሁሌም የሚያስደምመኝ ስንኝ አለ…..አብረን
ዝም እንበል ፤ በተሰኘው ድንቅ ግጥሙ ላይ እንደአዋሽ ውብ ሆኖ የሚፈስ የፍቅር
ታሪክ ይታያል (እርግጥ ነው፤ ስነጽሁፍ ለሁላችንም እንደየ ባህሪያችን እና እንደየ
የህይወት ተሞክሯችን የሚሰጠን ትርጉም ቢለያይም፤ ለኔ የሚሰማኝን እንዲህ
እገልጻለው)።

“ከሰው መንጋ እንገንጠል

ለአንድ አፍታ እንኳን እንገለል

በእፎይታ ጥላ እንጠለል

ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል”

እያለ ገጣሚው የሚወዳትን፤ ከዚህ ከትርምስምሱ አለም እንራቅ እያለ
ያባብላታል። አንድም የአዋሽን ውበት ለማየት ሁለትም ሁለቱ ብቻቸውን በዝምታ
ለመደማመጥ።

“ለማንም ምንም ሳናዋይ ሳንናገር ሳንጋገር

ከአይንሽ፤ ከልብሽ፤ ከልቤ አዋሽ ማዶ እንብረር”- ሲላት፤ ስለፍቅራችን ሌሎችን
ማማከር የለብንም፤ ልብሽ እና ልቤ ከፈቀዱ፤ ሌላ የፍቅራችንን ትክክለኝነት
የሚያረጋግጥ ነገር አያስፈልገንም እያላት ይመስላል። ይቀጥልና

“አጉል ነው ብለን ሳንፈርድ፤ ድንቅም ነው ሳንል ሳንወድ
ዝም ብለን አብረን ብንወርድ” እዚህ ላይ ደግሞ ዳኝነት በፍቅር ውስጥ ቦታ
እንደሌለው ለማመልከት ይመስላል፤ “መጥፎ” ወይም “ጥሩ” ብለን አንድን ነገር
አስቀድመን ከዳኘነው፤ እውነታውን ለማየት እድል አናገኝም። ዋናውና ከዚህ
ጽሁፍ ጋር የተያያዘው ስንኝ ግን የሚከተለው ነው-

“መቼስ አይሆንም ካልሽ ቅሪ፤

ግዴለም አትገደሪ

ልቦናሽ በመተረብሽ ባሳደረብሽ እደሪ ” – የሚለው ውብ ስንኝ


እንግዲህ እንዲህ ያላት፤ ስለአዋሽ ውበት፤ ስለዝምታ ድንቅነት፤ አብረው
ቢያሳልፉ መልካም ስለሚሆነው ጊዜ ካወያያት በኋላ ነው። ለእኔ እዚህ ላይ
ገጣሚው ስለእውነተኛ ፍቅር እያወራ መሆኑን እንድረዳ አድርጎኛል። “ስለምወድሽ
ከእኔ ጋር ወደ አዋሽ መውረድ አለብሽ” አላላትም። “ጨረቃም፤ ሰውም
ሳይመሰክሩብን፤ ኮከባችን ሳትቆጥርብን እኛም ሳንቆጥርባት፤ እባክሽ አዋሽ ማዶ
ሄደን ጀንበር ትጥለቅብን” እያለ ለምኗታል። ሆኖም ግን “ምንም እንኳን ከኔ ጋር
ብትሄጂ ደስ ቢለኝም፤ አይሆንም ካልሽ ቅሪ፤ እኔ ባልኩት ሳይሆን፤ ልቦናሽ
ባሳደረብሽ እደሪ” ሲላት። ፍቅሩ እውነተኛ መሆኑን ለማስመስከር ነጻነቷን
እየሰጣት ይመስለኛል።

እንግዲህ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ይህንን ሁሉ አስቦ ላይሆን ይችላል የጻፈው።
የስነ ጽሁፍ ውበቱ ይህ ነው፤ ለሁላችንም የተለያየ መልክ መያዙ። ከላይ የሰፈረው
የዳይላ ላማ አባባል እና የሎሬቱ ግጥም፤ ለምንወዳቸው ሰዎች ነጻነት
በመስጠት ፍቅራችን በግል ጥቅማችን ሳይበረዝ ንጹህ ሆኖ እንዲቀር ማድረግ
እንደምንችል የሚያስረዱ ናቸው። ቀላል አይደለም፤ እንደ ሀሳብ መልካም
እንደተግባር ደግሞ ከባድ በመሆኑ። ቢሆንም ግን በፍቅር ስም ስህተት እንዳንሰራ
ማሳሰቢያ ሊሆኑን ይችላሉ።

ወደ ሀይማኖትም ስንመለስ ተመሳሳይ ነው። (እኔ የምናገረው እራሴን ወክዬ ነው፤
ምክንያቱም እምነት ግላዊ ስለሆነ). የየትኛውም እምነት ተከታይ ብንሆን፤
የሀይማኖታችን የመጨረሻው ማሰሪያ ፍቅር ነው። እኛ ለፈጣሪያችን ያለን ፍቅር
ብቻም ሳይሆን እኛ ለመላው የፈጣሪ ልጆች ያለን ፍቅር። ለምሳሌ እንደ እናት
ወይም እንደ አባት፤ አንድ ሰው ለእኛ መልካም ሆኖ ለልጆቻችን ጨካኝ ቢሆን ለዛ
ሰው ምን አይነት ስሜት ነው የሚኖረን? ለዚህ ነው፤ ከፈጣሪ ጋር የሚያገናኘን
ድልድይ ለሌሎች ሰዎች በምናደርገው ነገር የሚወሰነው።

“የሀይማኖት አላማ እራስህን ለመቆጣጠር እንጂ፤ ሌሎችን
ለመውቀስ አይደለም” ሲሉ- በእምነት ውስጥ ሌሎችን መዳኘት የእምነታችንን
አላማ እንድንስት ያደርገናል ለማለት ነው።

በፍቅር እና በእምነት ስም ስህተቶች ይበዛሉና፤ የምናደርጋቸውን ነገሮች እውነተኛ
ምክንያት እራሳችንን በግልጽነት እንጠይቅ።

ሸጋ ጁምኣ!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
(በላይ በቀለ ወያ)

ጉድጓድ ውስጥ ያለች አይጥ ሰማዩን የምታየው በጉድጓዱ ቀዳዳ ልክ ነው። ከጉድጓድ ስትወጣ ግን የሰማዩን ግዙፍነት ትመለከታለች። በዘረኝነት ጉድጓድ ውስጥ ፣ በመንጋ ፍረጃ ጉድጓድ ውስጥ ያለ ሰውም ግዙፉን የሰው ልጅ ፣ ግዙፉን ሀገር የሚያዩት ባሉበት የጎሳ ጉድጓድ ጥበት ልክ ነው። ከዚህ ጉድጓድ ሲወጡ ግን ሰው የመሆንን ግዙፍነት ይረዳሉ ።ሀገር የመሆንን ሚስጢር ያውቃሉ። ሌላው ከአይጧም ጉድጓድ የጠበበው ይህ የፌስቡክ ጉድጓድ ነው ። ብዙ ግዜ እንደኔ በዚህ ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች... አንድን ጉዳይ መቶ ሰው ከተንጫጫበት አለም ግልብጥብጥ ያለ ፣ሀገር ምስቅልቅሏ የጠፋ ይመሥለናል። ምክንያቱም ከዚህ ጠባብ ጉድጓድ ወጣ ካላልን የአለምን ግዙፍነት ፣ የሀገርን ትልቅነት ማየት አንችልም። የlike መጠናችን መቶ ሲገባ አክቲቪስት ለመሆን የምናኮበኩብ አለም እኛን እየተከታተለን የሚመሥለን ለምን ይመሥላችኋል? በጉድጓዱ ወጣ ብለን አለም ግዙፍ ተአምር እየሰራ መሆኑን ስላላየን ነው። facebook ላይ 50 ሰው በመንጋ ተደራጅቶ ሲዘልፈን ፣ ሲያድምብን የአለም ህዝብ እየዘለፈን የሚመሥለን ሰማይ ምድሩ የካደን የሚመስለን ለምን ይመሥላችኋል ?ከዚህ ጠባብ አለም ወጣ ብለን የታመነልንን የሚያወድሰንን ግዙፍ አለም መመልከት ስላልቻልን ነው። ከምንም በላይ ደሞ በጠባብ አስተሳሰብ ጉድጓድ ውስጥ ያለ ሰው አለም የምትታየው ብይ አክላ ነው። ከዚህ ጉድጓድ ውስጥ ወጣ ብሎ ካላየ በቀር አለም ግብድዬ መሆኗን አያውቅም። አፋችንን ጠበብ አድርገን አስተሳሰባችንን እናስፋ።
<<ማነህ ልብስ ሰፊ እቺን ሱሪ ዘረኛ አድርግልኝ ማለቴ አጥብብልኝ።😂>>
@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa
ዛሬ በብሄራዊ ትያትር የተከፈተ የስእል ኤግዚቢሽን ነው። ሰአሊው አወቀ ይባላል...እውነት እውነት እላቹሃለው ስምን መላእክት ያወጣዋል...እሱ ጋር በልኩ ተሰፍቶ ልክክ ብሎ ጠልቋአል.....!!

ስእል የጥበብ ቁንጮ ነች!!!!!

ዛሬ እኔ አረጋገጥኩኝ ....እያጋነንኩኝ ከመሰላቹ ምንም እንደውም አላልኩም......ገብታቹ አረጋግጡ እጃቹን በአፍ የሚያሲዝ ጥበብ ተመልክታቹ ትመለሳላቹ!!

መግቢያው በነፃ ነው.......በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር አርት ጋለሪ 14 ቀን የሚቆይ......የምትችሉ ነገ የረፍት ቀን ስለሆነ ከወዳጃቹ ጋር ጎራ በሉና ተደመሙ!!!

ከዚህ በታች በፎቶ እኔጋ ያስቀረዋቸው ስላሉ አንድ ሶስቱን ግርግዳው ላይ እለጥፈዋለው..!!

ሸጋ ሸጊቱ ምሽት ይሁንላቹ!!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የልቦለዴ ጉዳይ!
«ዘውድአለም ታደሠ»
አንድ ልብወለድ ፅፌ ልብወለድ ውስጥ እኩይ ባህሪ አላብሼ የፃፍኩትን ሰውዬ የየትኛው ብሔር ተወላጅ እንደማደርገው ግራ ገባኝ። በዚህ ሰአት የየትኛውንም ብሔር ስም ሰጥተህ ልቦለድ ብትፅፍ ራሱ ብሔረሰቡ ስሎጋን ይዞ ቀኑን ሙሉ ነው ሲያወግዝህ ሚውለው
ስለዚህ ከየትኛውም ብሔረሰብ ጋር ላለመጣላት ልቦለዱን ኡጋንዳ ውስጥ የተፈፀመ ታሪክ አድርጌ ፅፌዋለሁ። የዋና ገፀባህሪው ስም "ኡዙሉጳዮቃ" እኩይ ገፀበህሪ የያዘውን ሰውዬ ደግሞ “ፓሬንጮባጎፓ" የሚል ልሳን የሚመስል ስም ሰጥቻቸዋለሁ
ባሻዬ ባሁን ሰአትኮ ብሔር ብሔረሰቦች ከሚጠምዱህ የሪፐብሊካኑ ጋርዶች እንደጀበና በሰባብሩህ ይቀላል
ለማንኛውም ደና እደሩ። አሁን እንደብሔሬ ሰአት አቆጣጠር አራት ሰአት ስላለፈ ልተኛ😂


@wegoch
@yeyhudaanbesa
@wegoch
እንግዲህ በትንሹ ይሄን ይመስላል......እኔን ገርሞኛል እናንተን ይግረማቹ የሚሉት የመንገድ ላይ ነጋዴዋችን ለዛሬ አፋቸውን ተውሼ

እኔን ገርሞኛልና እናንተም ....ጎብኝታቹ ይግረማቹ....አጃኢብ ነው ...እውነትም አወቀ ቀለሙ...አወቀው ቀለሙን...ቀመመው ጥበቡን....

ሰላም እደሩልኝ !!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/28 19:22:32
Back to Top
HTML Embed Code: