Telegram Web Link
‹‹ የበጋው መብረቅ ሌፍተናት ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ››

ጀግናው ሌፍተናት ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ጥር 21 ቀን 1913 ዓ.ም. በጅባትና ሜጫ አውራጃ በደንቢ ዮብዲ ወረዳ ዮብዶ በሚባል ቦታ ተወለዱ።

ለቤተሰባቸው የመጨረሻ ልጅ ቢሆኑም ከሁሉም ጎበዝና ብርቱ ነበሩና አባታቸው የቤተሰቡ አለቃ አደረጓቸው።
ስማቸውንም ያገኙት ብርቱ መሆናቸውን አባታቸው በማወቃቸው ገና ሳይወለዱ ለወላጅ እናታቸው ‹‹ጥር 21 ቀን ትወልጃለሽ ስሙንም ጃጋማ
ብየዋለሁ›› በማለት ነበር ጃገማ የሚለውን መጠሪያ የሰጧቸው።

“ጃገማ” የሚለው የኦሮምኛ ቃል የአባታቸው የፈረስ ስም ሲሆን፤
የአማርኛ ፍቺው ሀይለኛ ማለት ነው።

ሌፍተናት ጄኔራል ጃገማ እሲኪወለዱ ድረስ የፈረሳቸውን ስም የሚሰጡት ሁነኛ ልጅ ያላገኙት አባታቸው፤ በልጃቸው በጃገማ ይኮሩ ነበር።

ሌተና ጄኔራል ጃገማ ኬሎ፣ በአካባቢው በሚገኘው የቄስ ትምህርት ቤት ፊደል ከቆጠሩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

ጀግናው ሌፍተናት ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ለአገራቸው ነጻነት ሲሉ ከፋሽስት ጥሊያን ጋር ሲፋለሙ የደሙ፣ ዳር ድንበር ለማስከበር የወደቁ፣ ሕይወታቸውን ሙሉ ለወገናቸው ክብር የገበሩና የቆሰሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው።

ፋሽሽት ጣሊያን ኢትዮጵያን በግፍ በወረረበት ዘመን ጀነራል ጀጋማ በ15 ዓመታቸው ሸፈቱ ። በአፍላው የወጣትነት ጊዜያቸው የ3500
አርበኞች አለቃ ነበሩ ።

በምዕራብ ሸዋ የነበረውን የፋሽስት ጦር ሰቅዘው የያዙት ጀግናው ጃጋማ ኬሎ፤ አምስት አመት ሙሉ በጀግንነት
ሲጋደሉ ከማሸነፍ በቀር አንዴም ቢሆን ተማርከውም ሆነ ተሸንፈው አያውቁም ነበር።

በተለያዩ የጦር ውሎዎች ላይ ባደረጉት ተጋድሎ በጠላት ላይ ከፍተኛ ጀብዱን ከመቀዳጀት ባሻገር፤ በርካታ የጥሊያን የጦር አዝማቾችን ማርከው ለጨካኝ ፋሽስቶች የኢትዮጵያውያንን ርህራሔ አሳይተዋል።

የማረኳቸውን በርካታ የጣሊያን ጀኔራሎችም ለእንግሊዝ አስረክበዋል።

ሌፍተናት ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ከሸዋ እስከ ጅማ በመዝመት « ጃጋማን ጥሩት» እየተባሉ በርካታ አስቸጋሪ የፋሽስት ምሽጎችን ሰብረዋል።
ከነደጃዝማች ገረሱ ዱኪ፣ ወይዘሮ ሸዋረገድ ገድሌ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ አርበኞች እስከ መጨረሻው በመምራት ጣሊያንን ቁም
ቁምጥ ነስተው ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርገው አስወጥተውታል።

ከዚህም ባሻገር ሶማሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት የኢትዮጵያን ዳር
ድንበር በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ወደር የማይገኝላቸው የአገር ባለውለታ ናቸው።

ሌፍተናት ጄኔራል ጃገማ ኬሎ
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት የስምንቱ ጠቅላይ ግዛቶች የሰራዊት ኃላፊም ነበሩ።

የበጋው መብረቅ በሚል የሚታወቁት መልከ መልካሙ ሌፍተናት ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ።

እኒህ አርበኛ ከአውሮፕላን ሳይቀር ወድቀው ከሞት ጋር ተጋፍተው ለታምር የተረፉ፤ ሆለታ የጦር ትምህርት ቤትና አሜሪካን አገር ድረስ ተጉዘው ዘመናዊ የጦር ትምህርት የተማሩና በሺዎች የሚቆጠሩ ያገራቸውን ልጆች ያስተማሩ አገር ወዳጅ ጀግና ናቸው።

ስመጥሩ ጀግና ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ ስለአገራቸው ምን እንደሚያስቡ በአንድ ወቅት ተጠይቀው፤ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔን ግጥም በማውሳት.

አገሬ ኢትዮጵያ ውዲቱ ውዲቱ፣
በሶስቱ ቀለማት የተሸለምሽቱ፣
ላንቺ የማይረዳ ካለ በህይወቱ፣
በረከትሽን ይንሳው እስከ እለተ ሞቱ። ነበር ያሉት።

ከሸዋ እስከ ጅማ ዘምተው በማረኩትና ባሸነፉት ጥሊያን ልክ፤ምሽግና የመሳሪያ ግምጃ ቤት ሰብረው ተከታዮቻቸውን ባስታጥቁት ቁጥር
እንዲህ ተብሎ ይገጠምላቸው ነበር. . .
ገዳይ በልጅነቱ፣
ዶቃ ሳይወጣ ባንገቱ፤
ጃጌ ጃጋማቸው፣
እንደገጠመ የሚፈጃቸው፤
አባት እናቱ ከኦሮሞ፣
ግዳዩን አስቆጠረ ከምሮ ከምሮ፤

ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ የማረኩትን ነጭ የጥሊያን ወታደር መቶ ብር ሸጠዋል። ከእሳቸው መቶ ብር የገዛው ደግሞ ጣሊያኑን 5000 ብር
ሽጦታል። ጄኔራል ጃጋማ ፈረንጅ ወይንም ነጭ የሸጡ ጥቁር አፍሪካዊ ጀግና ናቸው ።

የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ከተረጋገጠ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ አፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥታቸውን ዳግም በየዘርፉ
ሲያደራጁ፣ ፍጡነ ረድኤት ሆነው ከተሰለፉት መካከል ጄኔራል ጃገማ አንዱ ነበሩ፡፡

በውትድርናው ዓለም በተለያዩ ክፍለ ጦሮች በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች በመሥራት እስከ ሌተና ጄኔራልነት ደርሰዋል፡፡

በወቅቱ አጠራር ከሐረርጌ ተነጥሎ ራሱን የቻለው የባሌ ጠቅላይ ግዛት፣ እንዲሁም የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ገዢና የግርማዊነታቸው እንደራሴ በመሆን አገልግለዋል፡፡

ከአራት አሠርታት አገራዊ አገልግሎት በኋላ በ1998 ዓ.ም ጡረታ ቢወጡም በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ተግባራት
ውስጥ ከመሳተፍ ወደኋላ አላሉም፡፡

በ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥን ተከትሎ የኢትዮጵያን አንድነት በሚያቀነቅኑ ፓርቲዎች ውስጥ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆኑ ከፍተኛ አመራርነትንም ይዘው ነበር፡፡

ከነዚህም የኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ አባልና ፕሬዚዳንት በመሆን ከ1983-1990 ዓ.ም፣ በኢትዮጵያዊነት ድርጅት ከ1988 ዓ.ም ጀምረው ለበርካታ ዓመታት በምክትል ፕሬዚዳንትነት፣ ከሐምሌ 1987 ዓ.ም. ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ
ኃይለሥላሴ መታሰቢያ ድርጅት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ሠርተዋል፡፡

ከምድር ጦር፣ ከአየር ኃይልና ከባሕር ኃይል የተወጣጡ አንጋፋ መኰንኖች
አማካይነት በ1998 ዓ.ም የተመሠረተው የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ቬተራንስ አሶሴሽን የመጀመርያው ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ሌተና ጄኔራል ጃገማ
ኬሎ ነበሩ፡፡

ጄኔራል ጃገማ ለአገራቸው ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ከንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና ከተለያዩ አገሮች ኒሻንና ሜዳዮችን ተሸልመዋል፡፡

ከነዚህም መካከል የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የአንገት ኒሻን፣ የቅዱስ
ጊዮርጊስ የጦር ሜዳ ጀግና ሜዳይ ባለ ሁለት ዘንባባ፣ የዳግማዊ ምኒልክ ኒሻን ከአገር ውስጥ ሲጠቀሱ፣ ከውጭ አገሮችም ከእንግሊዝ፣ ከዩጎዝላቪያና ከላይቤሪያ የተለያዩ ኒሻኖችን አግኝተዋል፡፡

ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ሕክምና ሲከታተሉ የቆዩት ጄኔራል ጃገማ በተወለዱ በ96 ዓመታቸው ዓርብ መጋቢት 29 ቀን 2009 ዓ.ም አረፉ፣ ሥርዓተ ቀብራቸው በሣልስቱ እሑድ ሚያዝያ 1 ቀን በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በወታደራዊ ሥርዓት ተፈጽሟል፡፡

ለክብራቸውም 21 ጊዜ መድፍ ሲተኮስ አርበኞችና ወጣት ከያንያን ሽለላና ቀረርት ፉከራም አሰምተዋል፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ
ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ ንጉሣውያን ቤተሰብና የቀድሞ ሹማምንት ተገኝተዋል፡፡


ምንጭ፤
፦ ጃገማ ኬሎ ( በፍቅረማርቆስ ደስታ)
፦ ልዩ ልዩ

"ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለኢትዮጵያ ነፃነት ሰማዕታት" ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!


‹‹ የበጋው መብረቅ ሌፍተናት ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ››
አገሬ ኢትዮጵያ ውዲቱ ውዲቱ፣
በሶስቱ ቀለማት የተሸለምሽቱ፣💚
ላንቺ የማይረዳ ካለ በህይወቱ፣💛
በረከትሽን ይንሳው እስከ እለተ ሞቱ።❤️

( የታሪክ ድርሳን ከሚል የቴሌግራም ቻናል የተወሰደ ))


መልካም ልደት!!💚💛


@wegoch
@wegoch
@balmbaras
አንዳንድ ንጉሥ ደሞ እንደ ናቡከደነፆር ህልሜን ከነፍቺው አቀብሉኝ ፣ ንገሩኝ ይላል።
.
አንዳንድ አለቃ ደሞ እንደ በለዓም የሚናገር አህያ ሁንልኝ ይላል። (እንደ ጋሽ አያልቅበት "ብስስ ብስስ" እያለ መጣራት ነውኮ የሚቀረው)
.
አንዳንድ ወዳጅ ደሞ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ አንተ ካልከሰምክ እሱ የሚያብብ አይመስለውም ።
.
አንዳንድ አጫፋሪ ደሞ በተፈቱት ዙሪያ እንደ ደስታ ገብሬ ካልተሽከረከረ ብር ግንባሩ ላይ የሚለጠፍለት አይመስለውም። (አይሻልህም እንደ ራስ ሆቴል በር?)
.
አንዳንድ ግብዝ ደሞ "ደረጃ ወ" ግብር ከፋይ ሆኖ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ካላወጣሁ ይላል።
.
አንዳንድ ዳኛ ደሞ መጻተኛውንና የድሀ አደጉን የመበለቲቱን ፍርድ ሲያጣምም ቆይቶ ወድቆ ያገኘውን ለመውገር ኮብልስቶን ይፈነቅላል።(ኧረ ስራ ላይ ያልዋለ ድንጋይ ፈልግ¡)
.
አንዳንዱ ጎረምሳ ደሞ የምህረት ኢተፋን 'ክበር ንገሥ' መዝሙር በጎርናና ድምፁ ለመዘመር ይሞክራል ።(እሷም ድጋሚ አታወጣውም ያንን ድምፅኮ ፤ እኔ ጆሮዬን ይዣለሁ። ደስ ያለው ግን ይዘምር)
.
አንዳንዱ ዱዝ ደሞ ከስልኩ Screenshot ለመውሰድ የሞባይሉን ስክሪን ይወለውላል።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#tayim tsigereda
ካለፈው የቀጠለ ከየትኛው ?እኔንጃ ብቻ ቀጥዬዋለው ስማ አብረን ሳንሆን ኒካ አስረን እኮ
መቆየት እንችላለን።እቺ ትንሿ እስር ቤት መሆኗ ነው ዋስ ያላት....ዋናው እስር እስኪጀመር
በጣቢያ የምቆይባት አይነት፣ ቆይ ችግርህ ምንድነው ? ችግሬ ቀላል ነው እንደ አባትሽ
መሰረታዊ ችግር የለብኝ...በል እሱን ለቀቅ አድርግ ምን ሆነ ደሞ እሱ? ምን አለው
አላሉም፣ትኖራላቹ ወይ ሳይሉ ያኖርሻል ወይ አላሉም? የምንጋባው ላኖርሽ ነው ልንኖር አየሽ
የምንኖርበት እንጂ የማኖርበት ነገር የለኝም።ይሄ ምን ማለት ነው እኔኮ አንዳንድ ነገርህ
አይገባኝም፣ግራ ታጋባኛለህ...ሁሉም ነገሬ ለኔ ራሱ አይገባኝም እንደ ሜትሮሎጂ በከፊል
ከገባሽ በቂ ነው ግን በገባሽ ልክ እንጂ ባልገባሽ ልክ አትኑሪ።ስማ እድሜዬ እየሄደ ነው
አንተ ግን ታሾፋለህ ለዚም ተጠያቂ እኔ ነኝ? የቀን እና የጨለማን ኡደቶች የማቆም
ስልጣኑስ የኔ ነው? አባትሽ ቤት ያሳለፍሽው ሀያ አምስት አመት እንደ ብክነት ሳይቆጠር
ከኔጋ ያሳለፍሽው ሶስት ወር አንገበገበሽ? አሁን ቁርጡን ማወቅ እፈልጋለው፣በግልፅ
እንድንነጋገር እፈልጋለው....አንድ ሴት እና አንድ አሰልጣኝ ይሄንን አሉህ ማለት መልቀቂያህ
ሊሰጡህ እየተዘጋጁ ነው።ታገባኛለህ? አዎ አገባሻለው መቼ? እሁድ የመቼው እሁድ
የሚመጣው እሁድ? እና ያለፈው እሁድ አገባሻለው? አታሹፍ በአላህ እኔ እውነቴን
ነው።ይኸውልሽ ከፊታችን ካሉት በአንዱ እሁድ አገባሻለው፣እሺ ካላገባኸኝስ ?ሌላ ሰው
ታገቢያለሻ ከዛ እኔን ጊዜዬን በማባከን በሚል በፍታብሄር ትከሺኛለሽ....መቼ ነው ግን ቁም
ነገር የምታወራው? አንተ ታሾፋለህ እኔ ግን ሀሳቤ ሁሉ አንተ ነህ ሀሳቤ ሁሉ አንተ ነህ
ትያለሽ የባለፈውን ሂሳብ ግን አስበሽ ቀሪ ገንዘብሽን ወስደሻል...ይድፋህ እሺ አንዳንዴ
በጥፊ በይው በይው ይለኛል ታውቃለህ?

ሸጋ ቀን💚💛❤️!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
"ፅጉዬ ግን አታምኚኝም አይደል ? ተሻሽያለሁኮ እንደ ድሮው ሐብታም፣ የተማረ፣ ወንዳወንድ መለሎ ምናምን እያልኩ ባል አልመርጥም ትቻለሁ ... አሁን ያመነ፥ የተጠመቀ ፥ የዳነ ፥ የፀሎት ሰው ፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚኖር ፥ ነቀፌታ የሌለበት፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሰራ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ፥ ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥ ልጆቹን በጭምትነት የሚያሳድግ ፥ የቤት አስተዳደር የሚችል ፥ ሌሎች በመልካም የሚመሰክሩለት ፥ ከእኔ በፊት ሴት የማያውቅ ፥ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ በዛ ላይ እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ፤ በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት የበረታ ሌሎችንም እኔንም ሊመክር ሊያስተምር የሚችል ... እናም በቃ መንፈሳዊ የሆነ ... በእውነት ተለውጫለሁ እኔ እንደድሮው ሐብታም ምናምን አልልም ጌታን!"
"የኔ እህት የምትፈልጊው ኤጲስ ቆጶስ ነው? ወይስ ባል?"
# አንዳንድየአዲስአበባነዋሪዎች

@wegoch
@Paappii

#tayim tsigereda
ሙዝ ፣ ብርትኳን ፣ ማንጎ ፣ አናናስ ፣ ፖም .... ወዘተ
የመመገብ ልምዳችሁ ለምን ደካማ ሆነ ? "
ይባላል
በአማርኛ ☞ " ፍራ ፍሬን "
በእንግሊዘኛ " ፍሩት "
ብለው አስጠንቅቀውን ነዋ 😂

@wegoch
@paappii

#lulit tadesse
እራቱን ለቅሶ ቤት ፈልጎ ሚበላው እኮ ነው ደውሎ «እራት በላሽ ማሬ» እያለ ሚያደርቅሽ 😁

@wegoch
@paappii

#yasino
አንዷ የቦሌ ልጅ ሰው ተሰልፎ አይታ አባቷን
"ዳዲ ይሄ ሰልፍ የምንድነው?"
"ለታክሲ ነዋ ልጄ" ይላታል
"ታክሲ ሊገዙ ነው?" 😳😝

@wegoch
@wegoch
@paappii

#natnael ayalew
ስልክ መንትፎ እየሮጠ ለማምለጥ መስጊድ ገብቶ ከሰጋጆች ጋር ተቀላቅሎ ሲሰግድ የሰረቀው ስልክ ሲጠራ ቀውጢ መዝሙር 😳😂

@wegoch
@paappii

#abdu abdel
ቺኳን አቩካዶ ፣ ድንች በዳጣ ፣ ባቄላ እሸት ምናምን ጋብዘሃት ከሸኘሃት ቡኋላ ቤት ስትደርስ የምትልክልህ text
«ምነው ሞዴል አርሷደር ነኝ አልክ?» 😁😂

@wegoch
@paappii

#yasino
ከሰውነት ማንም አያስጥልም !!

ማንም መጀመሪያ ሰው ሆኖ ነው የሚወለደው።

ከብሔሩ በፊት ፣ ከተወለደበት ማኀበረሰብ ሃይማኖት ከመቀበሉ በፊት ፣ ሰው ነው ፣ ማንም "ሰው ነኝ!" ብሎ ሐሳቡን ቢቀይር፣'ማጆሪቲ' ይሆናል።

ግን፣ ሰው መሆንም ነገሩን አያቀለውም። የሰውነት ተፈጥሮ በራሱ አስቸጋሪ ነው። ይሄ ዐቅሙ የተፈጥሮ አካል ነው። ምርጫ ማድረግ የሚችል የሰውን ተፈጥሮ በህግ ማስገዛት የሚከብደው ለዚያ ነው። ማሽን አንድ-ወጥ ሆኖ ተፈጥሮ ለፈጣሪው እንደሚኖር አይደለም የሰው ልጅነት። ይህ የምርጫ ተፈጥሮ በምክንያት ሆነ ያለ ምክኒያት እንዲያምፅ ሊያደርገው ይችላል።

አኹን፣ እዚያ የመኪና መብራቱ ጋ የሚለምኑት ልጆች ማስቲሽ እየተቀባበሉ ያሸትታሉ። ማስቲሽ የተሠራው ለጫማ ማጣበቂያነት ነው። ግን፣በቃ፣መርጠው ያሸትቱታል፤ ይሰክሩበታል። ማስቲሽ ፣ ላስቲክ ለማጣበቅ ካልሆነ፣ለሌላ አገልግሎት ማዋል አይቻልም ! የሚል ሕግ ቢወጣም ፣ ተደብቀው የተከለከለውን ያደርጋሉ፤ በማህበረሰቡ ይገለላሉ። ወይንም ፣ ማኀበረሰብ ስላገለለን፣በሚል ምክንያት ነው እና ፈቃድ እራሳቸውን እየጎዱ ነው። ሰው እራሱን በራ'ሱ ለመጉዳት እንኳን የምርጫ ዐቅም አለው። ብሔር ወይም ቤተሰብ ወይንም ሃይማኖት ስለሌላቸው አይደለም ወጣቶቹ በማስቲሽ ሳንባቸውን የሚያጣብቁት፤ ብሔር ወይንም ሃይማኖት ቢኖራቸውም ከሰውነት አያስጥላቸውም።

ሌላኛው ደግሞ ሲጋራ እያጨሰ ነው።

ከአጨሰ በኃላ ፣ ሳያናፍስ ታክሲ ውስጥ ጥልቅ በማለቱ፣ ተሳፋሪው የአፍጫውን የበላይኛው ከንፈሩ ይደፍን ጀመር። አንድዋ ጠና ያለች ሴት፣"ምነው፣ልጄ፣ሲጋራ መጠጣት ብትተው!?" ምናምን ብላ ምክክር ጀመረች። የሞራል ማማውን ከፍተኛ ስፍራ የተቆጣጠረችበት ቅልጥፍና አሮጊት አያስመስላትም።


እርስዋ ስትመክረው፣ ሰውየው እየተሸማቀቀ ይሰማል---እንዳይተነፍስ ተጠንቅቆ። እንዳይተነፍስ የተጨነቀው የእርሱ ሲጋራ ሽታ ወደ ሴትየዋ አፍንጫ እንዳይገባ ብቻ ሳይሆን ፣ እርስዋ የተቀባችው ቅቤ ሽታው ወደ እርሱ በተለዋጭነት እንዳይመጣበትም ሊሆን ይችላል።

ሰው ምርጫ ያለው ፍጡር ነው። አንዱ ማስቲሽ ያሸታል፤ሌላው ሲጃራ አጭሶ እንዳይሸት ይሸማቀቃል። ሌላው ደሞ ጫማው አለ-እርሱ ፈቃድ መሽተቱ አስጨንቆት ወንበር ሥር እግሩን ይደብቃል።

የአሮጊቷ ምርጫዋ ቅቤ መቀባት ነው፣የሰውየው ደግሞ ሲጃራ ማጨስ። ማኀበረሰቡ ግን፣በተቀባይነት ደረጃ አንዱን ምርጫ የሚደግፉ፣ሌላው ደግሞ የሚነቅፍ ያደርገዋል። የጠላውን ሁሉ ነቅፎ ወደ ሕግ ረቂቅ ለመለወጥ ሙከራ ቢያደርግ ግን ፣ ውጤታማ አይሆንም። የሰውን የምርጫ አቅም ከሰው ተፈጥሮ ውስጥ ለይቶ ማምከን አይችልም።

ለዚህም ነው ፤ አስጨንቆ የሚከለክል ሕግ በድብቅ ሕገ-ወጥ የሚያበረታታ የሚሆነው። ለዚህም ነው ፣ the best law is that which enforces least፣" የሚባለው። የማያስተነፍስ ህግ በድብቅ ሕገ-ወጥነትን የሚያስፋፋ ነው። ምክንያቱም፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮው በምርጫ እንጂ በማስገደድ የሚሠራ ስላልሆነ ነው። አንዳንድ ጊዜ፣የሰው ልጅ የምርጫ ዐቅሙን የሚያመጣው ታሞ በአልጋ ሲወድቅ ብቻ የሚሆንበት ጊዜ አለ። የምርጫዋቹ ድምር፣መምረጥ ወደ ማይችልበት ሱሰኛነት ወይንም በግድ መቀበል ወደ አለበት የሐኪም ትእዛዝ ላይ ይጥለዋል። ምርጫዎቹ ወደ'አልመረጠው ፣ ባይመርጥም ፣ ወደ'ማይቀይረው ፣ ሞት ያደርሱታል።

ግን እንደዚያም ሆኖ፣ሰው ሰውነቱን በብሔሩ ምክንያት ወይንም በሃይማኖቱ ....በሕግ ወይንም በፈሪሃ እግዜአብሄር ምክንያት የሚለውጥ ከመሰለን የእምነት ስህተት ፈፅመናል።

ሰው በተፈጥሮ ፣ "አድርግ!" ተብሎ የታዘዘውን ለማድረግ ሲፈቅድ እንኳን፣የእራሱን አሻራ ጨምሮ የሚያከናውን ፍጡር ነው። ዘይቤ የሚፈጠረውም እንደዛዠዚያ ነው። ጥበብ እና ፈጠራ የዚህ የማፈንገጥ ወይንም የአለመስማማት ምርጫ ተፈጥሮው ዐይነቸኛ ማሳያ ናቸው።

"ሁሉንም ነገር በሕግ ለመቆጣጠር የሚፈልግ ፣ የተሻሻለ ማኀበረሰብ በመፍጠር ፋንታ ፣ ጥፋት እና ዝቅጠትን ማበረታታቱ የማይቀር ነው። ሙሉ በሙሉ ከገጸ -ምድር ለማጥፋት ለማይቻል ነገር ይሁንታ መስጠት የተሻለ ነው፣ምንም እንኳን ነገርየው በራሱ ጎጂ ቢሆንም እንኳን። ከድሎት፣ከቅናት፣ከስግብግብነት፣ከሰካራምነት፣ እና ከመሳሰሉት ባሕሪዎች ስንት ዓይነት ዲያብሎሳዊ ጥፋት ይመነጫል ?.....ግን፣እነዚህን ባህሪዎች በሕግ በረቀቀ አንቀጽ መከላከል አይቻልም። መከላከል እና ማጥፋት ስለማይቻልም በመፍቀድ መታገስ ግድ ነው፤"ይላል ቤኔዲክት ደ ስፔኖዛ ----freedom of thought and speech '

እንግዲህ፣አሮጊት ሲጋራ ያጨሰውን ሰውዬ እንደነተረከችው ፣ እኛም ከተለያዩ ምርጫዎቻችን አንጸር መነታረክ እንችላለን። ሴትየዋጨከ'ተቀባችው ቅቤ ሽታ የቱ ማኅበረሰቡን የበለጠ ይጠቅማል ? የሚል ነው ንትርኩ። ንትርኩ፣ እንደ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሐሳብ ፍጭት፣በመጨረሻያ ላይ ሕግ እንዲጸድቅበት ለማድረግ የታቀደ ሁሉ ሊሆን ይችላል።

ተከናውኖም፣ ሲጋራ ማጨስ ሊታገድ ይችላል። የሲጋራ ፋብሪካ የማምረት ፍላጎቱ ሳይታገድ ፣ አጫሹ ግን ሲጋራ የመለኮስ ምርጫው ሊታገድ ይችላል።ከፈለገ ሲጋራውን በድራፍት እየነከረ ይብላው፣ሊባል ይችላል። ግን ይሄ ዓይነቱ ህግ ፣ ከሲጋራ የባሱ የሚጨሱ ነገሮችን በደድብቅ እንዲስፋፋ ያግዝ ይሆነናልን እንጂ የሰውን የተሳሳተ ምርጫ የማድረግ አቅም፣ ለአንዴ'ና ለመጨረሻ ጊዜ ፣ ገንዞ አይቀብረውም። እንዲያውም፣ አፈና ተፈጸመብኝ በሚል ፣ የሸመቀቀውን የሕግ ልጓም ለመበጠስ ወደ ሌላ አማራጭ ይዞራል። የሰውን ልጅ በሕግ ወጥመድ የተሻለ፣አዎንታዊ ውጤት ያስገኛል።

እንደ'ቤኔዲክት ስፔኖዛ እምነት:- በመንግሥት ሆነ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ሌላ መንግሥትም ሆነ ሌላ የሃይማኖት ተቋም የመፍጠር እንቅስቃሴ የሚጠነሰሰው ፣ ከዚሁ የሕግ መጥበቅ እና የክልከላ መብዛት ጋር በተያያዘ ነው፣ይላል።

ለዚህ፣ነውጨ፣ ተቋማት የበለጠ ሥልጣን እንዲኖራቸው ከፈለጊ፣የበለጠ በሕግ የመፈጠር ፍላጎታቸውን መቀነስ አለባቸው ፣ የተባለው። በተለይ የአንድ ሰው ምርጫ በሌላው ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽዕኖ ገና በሐሳብ ደረጃ ላይ ያለ እና የሚያከራክር በሆነበት ኹኔታ ውስጥ ፣ አንድ ጎኑን ለማስደሰት የሚወጣ ሕግ ብዙ እንቢልታ እና እልኽ የሚፈለፍል መሆኑ አይቀርም።

የምርጫ ነፃነቱ የታፈነ ማኅበረሰብ በሚፈለገው በሚፈለገው'ና በሚደረገው፣በማያስበውና በሚናገረው መካከል የተምታታበት ይሆናል። ምርጫውን በድብቅም ቢሆን ተግባራዊ ይሆናል። የተጫነውን ሕግ እንዲናገር ከ'ሚፈቅድለት አንጻር ይናገራል። እውነት መሆኑን የሚያውቀው ነገር ሲወነጅል ወይንም ማንንም የማይጎዳ ነገር ሲኮንን ይውላል። ይኮንን'ና ከተለያዩ አንጻር የኮነነውን መልሶ ሲያከናውን ይገኛል።

ጠረን የምርጫ ጉዳይ ቢሆንም፣ የሲጋራ ሽታ የማይወድደው በቅቤ ሽታ ይዋጋዋል። በአንድ በተፈጥሮ ላይ ያለ እንቆቅልሽ ነው። ሕግን እንደ ፈጣሪ በሁሉም ጊዜ የሚመለከት እና በሁሉም ስፍራ የሚያስከብር ቢኖር፣ አንድም ሰው ወህኒ ከመውረድ የሚተርፍ ባልኖረ ነበር።

(( ሌሊሳ ግርማ ))

ምንጭ:- ፍትህ መፅሔት ጥር 10 2011

የኔዋ ቅዳሜ!!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የአዲስ አበባ ልጅ ወግ
2

አዲስ አበባ ብሔር የላትም፣ ይሉኛል፣ ሰምቼ ጭጭ እላለሁኝ። ብሔር አላት---'ደፋር " ይባላል። አዲስ አበባ ደግሞ ታላቋ ጋለሞታ ናት። ለደፈራት ኹሉ ቀሚሷን ገልባ ትተባበራለች።'በሕግ አምላክ !' አትልም። ሕግም፣አምላክም ኖሯት አያውቅም። የአዲስ አበባ መተዳደሪያዋ ሕጎች ታክሲ ውስጥ በጥቅስ መልክ ተጽፈው ነው የሚገኙት። "እኔ ላይ የሚጮህ መብት ያለው ስልኬ ብቻ ነው" ይላል አንዱ የደፋር ሕግ። ይሄን ጥቅስ የለጠፈ ታክሲ አላግባብ ጠቅጥቆ ቢጭንኽ፣ለአጭር ጉዞ የረጅም ጉዞ ተመን ቢያስከፍልኽ .....ልትጮህበት አትችልም። ቀጭኑ የደፋር ትእዛዝ ሲተረጐም:- እኔ እንደፈለግሁ ማድረግ እችላለሁ፣ አንተ ግን መጨቃጨቅ እንኳን አልተፈቀደልኽም።

እና አዲስ አበባ የማን ናት ? ጮክ አድርጎ ስለ እራሱ ጥቅም በድምፅ ማጉያ የሚያስብ ደፋር ኹሉ ናት።

ማን ከቀድሞውም አዲሳበባ ውስጥ፣ማን ደግሞ መጤ ነው? የሚለው ጥያቄ ፈጽሞ አያከራክርም። እሱ አይደለም ነጥቡ። ነጥቡ ለማን ነው የተመቸችው ፣ ማንን ደግሞ ያገለገለችው? የሚለው ነው። አዲስ አበባ ላይ የተወለደ ግራ ገብቶት እንጂ ተመችቶት አያውቅም። ምክንያቱ ምንድነው? እኔ አላውቅም። ምናልባት፣በዝግመተ ለውጥ ግምታዊ መላምት እንደሚታሰበው "የተንቀሳቀሰ የበለጠ ይለወጣል፣ባለበት የተቀመጠ እዚያው ዝጎ ይቀራል፣" ይኾን? አላውቅም። ልክ የአውስትራሊያ አቦርጂኖች፣እዚያ በተቀመጡበት፣ነጮቹ በመርከብ መጥተው ሀገራቸውን እንደወረሷቸው፣የአውሮጳ ነጮች፣ዋሻ ውስጥ በነበሩ ጊዜ፣የአፍቃሪቃ ጥቁር ባህር ተሻግሮ ቅኝ ቢገዛቸው ኖሮ፣ምናልባት፣አፍቃሪ ውስጥ የሚታየው የአምባገነን መንግሥታት ታሪክ የምዕራባውያኑ ተሞክሮ ሊኾን በቻለ ነበረ።


በኾነ የዕጣ -ፈንታ አጋጣሚ አዲስ አበባ ውስጥ ተወልጄአለሁኝ። በኾነ የዕጣ -ፈንታ አጋጣሚ የተወለድኩት በመከነው የደርግ ዘመን ነው። ነፍስ ዐውቄ ሙሉ ሰው የኾንኩት ደግሞ ከደርግም በላይ በመከነው የኢሕአዴግ መንግሥት ነው። በአጠቃላይ የባከነው ትውልድ አባል ነኝ። ከ'ባከነው ትውልድ መካከል የብክነቱ ቁስል ለመፈወስ ሀገር ጥሎ የተሰደደው በንጽጽር የተሻለ ኾኗል ብዬ ዐስባለሁኝ። ዐስቤ ሳልጨርስ፣ሀገር ጥሎ ኼዶ፤የተሻለ ኾኖ የመጣው የገበሬ መሬት በብላሽ ከመግዛት እና ከሀገሩ ጋር የማይመጣጠን ምናባዊ ቤት ከመሥራቱ ውጭ ሌላ ምን ተአምር አመጣ? ብዬ እጠይቃለሁኝ። ቁስል ለመፈወስ ኼደው የተመለሱትን ለመኾን ቃዥቶ ፣ ኼዶ ሳይመለስ በ'የባሕሩ ሰጥሞ ቀረ ስንቱን ወይ ኼዶ ሳይኼድ፣ወይ ቀርቶ ሳይነቃ፣በሱስ እና በማይጨው ሕልም ውስጥ ነፍስ እና አካሉ ተነጣጥሎ መከነ!

ከተነሣሁበት ነጥብ አፈነገጥኩኝ መሰለኝ......ደግ አደረግሁኝ!ከሀገራዊ የኅሊና ውል ያፈነገጠ ስንት አለ? ስንት ስለ የኢትዮጵያ ጨዋነት እየሰበከ፣ስንት የብልግና ታሪክ ሠራ! ስንቱ በሕይወት ዘመኑ እና በቀዬው በረሓብ ዘመድ እና በጎረቤት ሲረግፍ ዐይቴ ፣እርሱ በሕይወት ተርፎ ግን በተሞክሮ አዎንታዊ ትምህርት ሳይማር ቀረ፣የተመጣጠነ ምግብ ሳየበላ ያደገ ሰው "የእንብላው"ባህል ተጠቂ መሆን አነበረበትም። በችግር ማደግ ፣እራሱንም እንዳይቸገር፣ሌላም ሲቸገር እንዲገባው፣ያደርጋል እንጂ፣ችጋራም የሚያደርግ ንቃተ-ህሊና መስጠት አልነበረበትም። የችጋራምነትን ባህል ተቀብላ ፣ ተንከባክባ እና እንደ ስለት ልጅ ከእራ'ሷ ልጆች አስበልጣ የምትይዘው ደግሞ ታላቂቷ ጋለሞታ ናት። አዲስ አበባ ፣ እንደረሳሽኝ ብረሳሽ አትፍረጂብኝ ፣ አስተምረሽ ያሳደግሺኝ እንደዚያ ማድረግን ነው።

የተለያዩ የፓለቲካ አመለካከቶች የሚያንጸባርቁ ታክሲዎችን እና በላያቸው የሚለጣጥፏቸው ትርኪ-ምርኪ እስቲከሮች እና ጥቅሶች ዐያለሁ። ኹሉም ከመጡበት አካባቢ ይዘው የመጡት መንፈስ ነው። ኹሉም ቀድሞ የነበረውን ነገር በእራሳቸው ቅርጽ ለመለወጥ የሚፈልጉት ናቸው። ለነገሩ የሚጠበቅ ነው ---occupational hazard ይሉታል ፈረንጆቹ። ጦር ሜዳ የዘመተ ወታደር በታይፈስ እና በታይፎይድ ወይንም በፍቅር ከመሞት ይልቅ፣ በጥይት ወይንም በፈንጂ የመሞቱ አማራጭ ሰፊ ነው። እንደኔ ጸሓፊ የኾነ ሰው በ 'የጸሓፊው ድብታ ' ( writer's block )የመጠቃቱ ዕድል ከሾፌር ወይንም ከልብስ ሰፊ በበለጠ ነው። እንደዚህም በብሔር ፓለቲካ የሚኖር ትውልድም፣ሥራው እና የሚገኘው ጥቅም ከብሔሩ ጋር የጠበቀ ቁርኝት እስካለው ድረስ ፣ የብሔር ባለሙያ መኾኑ አይቀርም። ከሴተኛ -ዐዳሪ ሥራ ጋር የሚገናኝ የሥነ-ልቡና ችግርም ተመሳሳይ ነው፤ብዙ ጊዜ በፍቅር የመውደቅ እና በአንዱም ያለመዝለቅ የሥነ-ልቡና ቀውስ ተጠቂ መኾኗ አይቀርም።

አዲስ አበባ የጋለሞታ ሥነ ልቡና ባይኖራት፣ ጠንኳራ ባህል አጽንታ ፣ማንም ደፋር እንዳይባልግ አደብ ታስይዝ ነበር። በዩኒቨርሲቲዎቿ፣በፍርድ ቤቶቿ ፣ በተለያዩ ተቋማት እና መሥሪያ ቤቶቿ አማካኝነት ያሳደገችው ጽኑ ባህል የላትም። ማንም ፣ ከየት መጥቶ ፣ ምንም ዓይነት ነገር እስከ ልቡ ፍላጎት ቢያረግ ፣ ተው የሚለው የለም።

የጋለሞታ ልጆቿ በደርግ ዘመን (ብሔር ባይኖራቸውም ) በሰፈር ነበር ጎራ ለይተው የሚደባደቡት። ተደባድበው ነፃ ያወጡትን ሰፈር ባይኖርም 'አራድነት' የሚባል የማይረባ ባህል አዳብረው ነበር። አራድነት ዋናው ሕጉ በብልጠት ላይ የተመሠረተ ነው ከ97ዓመተ ምህረት በኃላ ግን ፣ የአራድነት ሕግ በደፋርነት ሕግ ተሽሮ፣ዐዲስ ማንነት የጋለሞታዋን ሥነ -ልቡና ተቆጣጥሮአል።

ወደ'ዚያው የታክሲ ውስጥ ጥቅሳችን እንመለስ።ይሄኛው ደግሞ፣"በደህንነት ካሜራ ውስጥ መሆኖትን አውቀው የተጠየቁትን ለመክፈል ይዘጋጁ፣" ይላል። ደፋሩ የጋለሞታ ከተማ ሕግ-አውጪ የታክሲው አገልግሎት ተመንን ከደህንነት ካሜራ ጋር ያያያዘው ዝም ብሎ አይደለም። ደኀንነትም የሕዝብን ጉዳይ ሳይኾን፣ለእራሱ ጠባብ የብሔር ቡድን የፓለቲካ የበላይነት ሲሠራ እንደነበረው፣አስቀድመን የምናውቀውን፣አኹን ደግም፣ግልጽ ዕወቁለት እየተባለ እየተነገረለት ነው። ታክሲውም የሕዝብን ሳይኾን የእራሱን ፍላጎት አገልጋይ ነው።

የየሥነ ልቡና ዐይነተ ዘርፈ-ብዙ በመኾኑ፣መከታተልም ኾነ መረዳት ያዳግታል። ሥነ-ልቦናውን ወደ ቀላል የሐሳብ አምሳል (ሞዴል) ለመለወጥ ባደረኩት ሙከራ የተረዳሁትን እንደሚከተለው አስቀምጠዋለሁኝ።

በታላቂቷ ጋለሞታ ውስጥ በመሠረቱ ብሔር የለም፤ወይንም፣ቢኖርም፣ብሔር አይደለም ዋነኛው ነገር። በከተማይቱ ውስጥ በእርግጥና በተጨባጭ ያለው ኹለት መደብ ነው።

ከኹለቱ መደቦች አንደኛው በየትኛውም ብሔር ወይንም አስተሳሰብ ወይንም ሃይማኖት ቅርጽ ቢመጣ በመሠረቱ ፣ በየ በዩ መደብ ነው። ይሄ መደብ ከየትም አቅጣጫ ይምጣ፤ወይንም ሳይመጣ፤እዚያው በጋለሞታ ውስጥ ልብስ ውስጥ ይደግ፣ሚናው እና በምድር ላይ የሚኖርበት ምክንያት ለመብላት ነው። ለመብላት የሚያገለግሉትን የተለያዩ ቅርጾችን ይጠቀማል፣መሰላሎችን ያመቻቻል፣የተለያዩ ማርሾችን ይቀያይራል። ኹሌ ተጠቃሚ መሆን እና በጥቂት ልፋት ብዙ ትርፍ ማግኘት ነው ዋነኛ ግቡ። ኹለተኛው መደብ 'ተብዪው' ነው። የተበዪው ቁጥር ከበዪው በብዙ ዕጥፍ ይበልጣል። ተበዪው ህዝብ ነው። "ቢሞት ፣ቢሞት የማያልቅ!"ኹሌ፣እንደ 'ሳላይሰጥ' አጥንት፣አገላብጦ ላየው፣የኾነ የሚበላ ነገር ያገኝበታል። በዪው አበላሉን ያውቅበታል። ተበዪው ደግሞ እየተገላበጠ መበላቱን፣ሲበላ ጸጥ ብሎ ነው፣ሲጠየቅ ይከፍላል፣ተሰለፍ ሲባል ይሰለፋል፣የመብራት ካርድ ሲሞላ፣ባልታወቀ ምክንያት ቆጣሪው ብሩን በእስትሮ ሲጠጣበት፣ትንሽ ከማማረር በቀር፣አልበላም አይልም። በቃ፣ዝን
ተ አለም ለመበላት የተፈጠረ መደብ ነው። "the silent majority "ብለው ይጠሩታል ምሁሮች፤"እናንተ እስተካክላቹ ጥሩት፣እኛ እንበላዋለን፣"ይላል በዪው።

ለመብላት እንዲመች የተለያየ ስም ሲወጣለት ይቀልላል። ልክ የምግብ ሜኑ ላይ እንደሚጠራ የተለያየ የቄንጥ ስም። በተለያየ ቄንጠኛ ስም፣ያው፣ሥጋ ተሽሞንሙኖ ተጠርቶ እንደሚበላው። ለተበዪው፣የተለያየ ሲያወጡለት ለአበላል ይቀልላል።

አንዳንዴ "ደኻ" ብለው ይጠሩታል። ደኻ ብለው ሲጠሩት አንድ የአበላል እስታየል ይፈጥራል። በዪው፣ ድኻ ወዳጅ መስሎ፣በዳኻዊ ሥነ-ልቡና አንደቱ መጀመሪያ በልቶ፣ከዚያ ኪሱን ይደግመዋል። ዝምተኛው ብዙኃን ሲባልም እንደዚያው ነው፤ዘምተኛውን እንዳይናገር አፍኖ የመብያ ዘውግ ይፈጥራል። 'ሰፊው'ን ሕዝብ በሰፊው ለመብላት ለቆረጠ በላተኛ የሚጠቅም መርሐ -ግብር ይከፍታል።

ስለ'ዚህች ከተማ፤እንደ ነዋሪነቴ፣እንደ ተበዪ መደብነቴ ፣ የሚሰማኝ ብዙ ቢኾንም፣ለዛሬ ግን በመጠኑ የተነፈስኩት ይበቃል።


((( ሌሊሳ ግርማ )))💚💛

ምንጭ:- ፍትህ መፅሔት ጥር ቀን18 2011

መልካም የረፍት ቀን!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ምን ማለት እችላለሁ?
-------
መጥፋትማ እሳትም ቢሆን በልቶ ሲጨርስ ይጠፋል። ደግና ደግ ህዝብ ግን የተባይ እሳትን
ንዴት ቀድሞ ያጠፋል።
የአብሮነትና ህብራዊነት፣ የሰውነትና ፍትሃዊነት ሚዛን ልኩ የሚሰፈረው ቀን ሲከፋ
በሚወልደው ውጤት ነው።
ጉዱና መኣቱ የእኔ ሆኖ ሳለ ምን እላለሁ? ማፈር ብቻ። እኛ ኮ የጥርሳችን ንቅሳት ብልጫታ
በወዳቂዎች ገመና የሚገለፍጥ እንጂ ስለጭቅቅታችንና ቁልቁለታችን ለራስ አርምሞ
የሚሆን ራስን ማየትን አያውቅም።
ግንፉልና አንገት አልባ ትውልድ ጆሮው የፊትለፊት ከበሮን ጩኸት እንጂ የልቡን
የማስተዋል ምት በውል አይሰማም። ስለሆነም ሳቁም አያመሽ፣ ለቅሶውም አይቆም።

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
Forwarded from SPACE COMPUTER
በ"በመስተዋት ተጽእኖ " ፓለቲከኞቻችን ቢፈተሹስ?


ቻርሊ ቻፕሊን ዓለም የሚያውቀው በአስቂኝ (የኩምክና) አተዋወኑ ነው። በፊልሞቹ ውስጥ የሚያሳያቸው አካላዊ እንቅስቃሴዎች እና የሚፈፅማቸው በተንኮንል የተሞሉ ድርጊቶች ለሰው ልጅ የሳቅ ምንጭ ሆነው ዘመናትን ተሻግረዋል። በሀገራችን በየ-ሰፈራችን የማሳቅ ችሎታን የተካነ ሰው ሲገኝ፣ቻርሊ ቻፕሊን ተብሎ ይጠራ እንደነበርም አስታውሳለሁ። የቻርሊን ችሎታ በብዕራቸው ያደነቁም:-"ሰውን ለማሳቅ የተፈጠረ ሰው"በማለት ነበር። ነገር ግን፣የቻርሊ ማንነት በወጉ ሲፈተሽ፣ ሰውዬው ከዚህም የላቀ የፍልስፍና ጥበብን የተካነ እንደነበር የሚመሰክሩለት አሉ።ዓለም ግን የሚበልጥባት የማሳቅ ችሎታው ሆነ'ና ለፍልስፍናው ደንታ የሚሰጠው ዐጣ።ቢሆንም፣ለንግግር በተጋበዘባቸው መድረኮችና እና ለቃለመጠይቅ በተገኘባቸው ሚዲያዎች ላይ ቻርሊ ትልቅ ዐሳቢነቱን የሚመሰክርለት ነገር ሳይጥል አያልፍም ነበር። በዓለም ዙሪያ የምትታወቅለት ቀጣይ ንግግሩም ከእነዚሁ መድረኮች በአንዱ የተናገራት ነበረች:-"እውነተኛ እና ምርጡ ጓደኛዬ መስተዋት ነው፤ምክንያቱም፣እኔ ሳለቅስ እሱ በፍጹም አይስቅም።" (በእንግሊዝኛ ትጥመኛለች:-"my true best friend is a mirror ,because it never laughs when i cry.")

ምንም እንኳን ይህ የቻርሊ ንግግር ለሰፊው ሕዝብ ዘመናትን ተሻጋሪ እውነት የያዘ ቢመስልም፣በፓለቲከኞች ዘንድ ግን ተቀባይነቱ እምብዛም ነው። ሮበርት ግሪኔ "the 48 laws of power' በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ "መስታወት"ለፓለቲከኞች"እውነተኛና ምርጥ ጓደኛ" ሳይሆን፤ጠላቶቻቸውን ትጥቅ ማስፈቺያ እና አንበርክኮ ማስወገጂያ መሣሪያ ነው፣" ይለናል። ይህም መሣሪያ "የመስተዋት ተጽእኖ" (The mirror effect ) ተብሎ ይጠራል። ከጥንት ጀምሮ አንዱ ፓለቲከኛ ሌላውን ጥሎ ለማለፍ ሲጠቀም የኖረበት ዘዴ እንደነበርም ግሪኔ አክሎ ይነግረናል። እኔም ይህ ሀሳብ አሸነፈኝ። በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ፣"የመስተዋቱ ተጽእኖ" በሀገራችን ፓለቲከኞች ዘንድ ሲገለጥ የኖረ ዘዴ ሆነብኝ። ለማንኛውም "የመስተዋቱ ተጽእኖ"ምንነት እና አይነቶቹን ከታሪካዊ እውነታዎች ጋር አዛምደን እንቃኝ፤እግረመንገድ ደግሞ እናንተ የሀገራችንን ፓለቲከኞች በምናብ እየሞላቹሁ ተከተሉ።

በመጀመሪያ በዚህ እንስማማለን:-መስተዋት ለእኔ እና ለእናንተ እውነታውን (reality ) የሚያሳይ ቁስ ነው። ነገር ግን፣ስለዚህ ቁስ ያልተረዳነው ወይም የማያስማማን ነገር ደሞ አለ፤ይሄውም የሰው ልጅ አእምሮ መሸንገያ ጥሩ መሥሪያ መሆኑ ነው። ይህን ነው እንግዲህ "የመስተዋቱ ተጽእኖ"የሚሉት። ለጠቢብ ፓለቲከኛ የመስታወቱ ተጽእኖ ኃይል መሣሪያ ነው። መስተዋቱን በተቃዋሚዎቹ ሥነ-ልቡና ላይ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል፤እነርሱን በመስተዋቱ ውስጥ የእራሳቸውን ቅዥት እና ምኞት ተመልክተው በዚያ ሲነሆልሉ እሱ ግን አሳፋሪ ድርጊታቸውን እንዲያስታውሱ የሚያደርገውን ምስል ያስከትላል፤በዚያም የእራሳቸውን ዋጋ እንዲተምኑ እያደረ ትምህርት ይሰጣቸዋል። የመስተዋቱን ተጽእኖ መቋቋም የሚችል ጥቂቱ ብቻ ነው። ብዙዎቹ በመስተዋቱ ውስጥ እራሳቸውን ተመልክተው ሲደሰቱ፤እግረመንገድ፣እየወደቁ እንደሆነ አይረዱም።


ለመሆኑ፣መስተዋት ፊት በትኩረት ስንቆም በእጅጉ እንደምንረበሽ የምናውቅ ስንቶቻች ነን?በእራሳችን የማንነት ነፀብራቅ ላይ እንደማፍጠጥ የሚያስጨንቅስ ምን አለ?ለዚህም ነው፣በመስተዋቱ ፊት ስንቆም የምናየው ማየት የምንፈልገውን ብቻ ነው።በፊታችን ላይ የወጣ አስቀያሚ ነገርን ማየት አንሻም። እንደዚያ ብናደርግ፤ከመስተዋቱ ፊት ዞረን ስንሄድም፣ተከትሎን በመሄድ ሲረብሸን ይውላል። በአንጻሩ፣የመስተዋቱ ተጽእኖን በሰዎች ላይ ፈጥረን እንዲረበሹ፣እንዲያዝኑ፣እንዲበሳጩ፣ብሎም እጃቸውም በሽንፈት እንዲሰጡ እንጠቀምበታለን። ወደ ፓለቲካው የሥልጣን ጨዋታ ሲመጣ ደግሞ አራት አይነት የመስተዋት ተጽእኖዎች እናገኛለን።


የመጀመሪያው #"የማለዘቢያው ተጽእኖ"(The Neutral -izing effect ) ነው።በጥንቱ በግሪክ አፈታሪክ ጎርጎን ሜዶሳ እጅግ አስፈሪ ገጽታ የተላበሰች ፍጡር እንደነበረች ይታመናል። ገላዋ በፀጉር የተሸፈነ ፣ተርገብጋቢ ምላስ፣የሾሉ ጥርሶች፣እና አስፈሪ ገጽታ የተላበሰን እባብ ትመስል ነበር።ሕዝቡም በታላቅ ፍርሐት ይርድላት ነበር።ወደ እርሷ ለአፍታ እንኳን የተመለከተ በድንጋጤ ደርቆ ይቀራል እንጂ አይተርፍም። የግሪክ ሕዝብ በዚህ ዓይነት ጭንቅ ተይዞ በነበረበት ዘመን ግን ከመካከላቸው አንድ ጀግና ተገኘ፤ ፔርሰስ ጀግናው ሕዝቡን ያስጨነቀችውን ሜዶሳን መግደል እችላለሁ አለ። ሕዝቡም ጸለየለት መረቀው'ናም ወጣ።

ፔርሰስ ሰይፋን ስሎ በአንድ እጁ ይዟል፤ በሌላው እጁ ደግሞ መስተዋቱን። ከሜዶሳ ፊት ሳደርስ ከመስተዋቱ ጀርባ እራሱን ጋረደ'ና መልኳን እንድታይበት ከፍ አድርጎ ያዘላት። ሜዶሳ ለመጀመሪያ ጊዜ በመስተዋቱ ውስጥ ፊቷን ተመለከተች። መርበትበት ያዛት፣ድንጋጤው አደረቃት። በዚህ ጊዜ ፔርሰስ ቀልጠፍ ብሎ ሰይፉን መዘዘ'ና ከአንገቷ ጋር አገናኘው። የሜዶሳ ጭንቅላት ከመሬት ተንከባለለ፣ሕዝቡም ከፍርሃት ባርነት ወጣ።

የማለዘቢያ ተጽእኖ ተቃዎሚህን በመስተዋቱ ውስጥ ማንነቱን እንዲያይ በማድረግ ተጽእኖ መፍጠሪያ'ና ማጥፊያው ጥበብ ሲሆን፣ተቃራኒው ደግሞ "ጥላ" ይባላል። ተቃዋሚህ እንዳያይህ ተጠንቀቅ ጥላውን መከተል ነው። ጥላውን ተከትለህ የገባበት እየገባህ ዕቅዱን ትፈትሻለህ፤ፍላጎት እና ልምዱንም እንዲሁም ትረዳለህ። ከዚያም እርሱን ለማንበርከክ ቀላል ነው።

ሁለተኛው ዐይነት ደግም#"የናርሲስ ተጽእኖ " (The Narcissus effect ) ይባላል። በግሪክ አፈታሪክ ናርሲስ ወጣት እና መልካም እጅግ የተዋበ ነበር። ይሁን'ና፣ክፋ ልማድ ደግሞ አለበት። በመንደሩ አቅራቢያ በምትገኝ ሐይቅ ዘወትር ማለዳ እየሄደ በውሃው ውስጥ ከሚመለከተው የእራሱ ምስል ሲጫወት ይውላል። እያደር ከዚህ ምስል ጋር በፍቅር ወደቀ።በአንድ አፍታ ከውሃው ውስጥ ወጥቶ እንዲያቅፈው፣እንዲዳብሰውም ይለምነው ጀመር።አንድ ቀን ናርሲስ ፍቅሩን መቋቋም ከማይችለበት ደረጃ ደረሰ፤በፍቅር የወደቀለትንም ምስል ሊያቅፈው ወደ ጥልቁ ውሃ ዘለለ። በዚያም ፍጻሜው ሆነ።
ፓለቲኛ አንድ ጠንቅቆ ማወቅ ያለበት፣ሰዎች ሁሉ እንደ ናርሲስ ተመሳሳይ ባህሪይ ያላቸው መሆኑን ነው። የሰው ልጅ ከእራሱ ጋር በፍቅር ወድቆ የሚሰቃይ ፍጡር ነው። ስለ'ተሸነፈበት ፍላጎቱ ሲል የማይሆነው ነገር የለም። ይህ ፍላጎቱ ገንዘብ፣ሴት፣ሥልጣን ሊሆን ይችላል። ጠቢብ ፓለቲከኛ ሆይ፣ተቃዎሚህ ፊት የምታቆመው መስተዋት የናርሲስ ተጽእኖ እንዳለበት የሚያረጋግጥለት ይሁን፤በዚህም፤እውነተኛ ፍላግት እና ሕልሙን በቀላሉ ትረዳለህ። ከዚያ በኃላማ፣ከተቃዋሚህ ጀርባ ቆመህ፤የተሸነፈለት ምስሉን እያሳየህ፣በትንሹ ወደ ሐይቁ መገፍተር በቂ ነው፤በቀላሉ ይሰጥማል።
ሦስተኛው #"ግብረገባዊ ተጽእኖ "(The moral effect ) ይባላል። አኹንም፣ጠቢብ ፓለቲከኛ ይህን ያስታውሳል:-"እውነት በደፈናው ትታያለች፤የምትደመጠው ግን አንዳንዴ ብቻ ነው።" በግብረገባዊ ተጽእኖ ተጠቅመህ ሰዎች ፊት የምታቀርበው መስተዋት ዓላማው ተቃዎሚዎችህ በአንተ ወይም በሕዝቡ ላይ ያደረጉትን እንዲያስታውሱ ማድረግ ነው። በዚህም፣ጥፋታቸው እንዲሰማቸው፣እንዲፀፀቱ ታደርጋለህ። ከባህሪያቸው ክፋት የተነሳ፣የፈጸሙትን ክፋ አድራጎት እንዲረዱት'ና እንዲያፍሩበት፣ብሎም እንዲማሩበት ይህን'ግብረገባዊ ተጽእኖ' የተባለ መስተዋት ከፊታቸው ታኖራለህ። ከዚያም፣ከድርጊታቸው መጠን፣አንተም መልሰህ ታደርግባቸዋለህ። ግብገባዊ ተጽእኖ ተቃዋሚዎችህን ለመቅጣት ብቻ ሳይሆን፤እነርሱም ሆኑ ሕዝቡ የአንተን ቅጣት ተገቢነት እንዲያምኑበት የሚያደርግ ኃይል አለው'ና ሞክረው።

የመጨረሺያው # "የመስታወት ተጽእኖ " ዐይነት "የማቀዥት ተጽእኖ " (The hallucinatory effect ) ይባላል። መስተዋት እጅግ አሳሳች መሆኑን አትዘንጋ። በመስተዋቱ ፊት በቆምክ ጊዜ የምታየው መልክህ እና ሰዎች የሚነግሩህ መልክህ የተለያዩ ናቸው። ጠቢብ ፓለቲከኛ በተቃሚዎቹ ፊት መስተዋቱን ሲያቆመው እራሳቸውን እና ዓለምን በውስጡ የሚመለከቱ ይመስላቸዋል፣ነገርግን፣የሚመለከቱትን መስተዋቱን እኮ ነው! መስተዋቱ ከፊታቸው በተነሳ ጊዜ፣በሚያዩት ግራ ይጋባሉ። መስተዋቱ የሚፈጥርባቸው "የማቃዥት ተጽእኖ " የሚባለውም ይሄው ነው። በመስተዋቱ ውስጥ ተቃዎሚህ እንዲመለከተው የምታደርገው ሁሉ የነገሩ፣የቦታው፣የግለሰቡ ማንነት ነጸብራቅ መሆኑን ዘንግቶ፣እውነተኛውን ነገር ይህ ነው ብሎ እንዲቀበለው ማሳመን ነው። በመስተዋቱ ውስጥ የሚመለከተው ቅዥት ፈጥረህበት ስታበቃ፣አንተ በእውነተኛ ማንነቱ ጠልፈህ ትጥለዋለህ።



ደራሲ ሐዲስ ዓለማም'ፍቅር እስከ መቃብር ' ውስጥ እመት ውድነሽ፥ ያናገሩት እውነት ይህኑን "የመስታወቱን ተጽእኖ " ያስታውሱናል። እመት ውድነሽ ከመስተዋቱ ውስጥ ብቅ ካለችው "ሴት"ጋር እንደልባቸው ተጫውተው ሲጨርሱ ደንግጠው ይነቃሉ፤ምናልባት፤ሰው አይቶኝ ይሆን?ብለው ነው። በመጨረሻም እንዲህ አሉ:-"ለካ ሰውን እብድ የሚያሰኘው እብድ የሚያደርገውን ማድረግ አይደለም፤ እብድ የሚያደርገውን ሲያደርጉ መታየቱ ነው።" ጠቢብ ፓለቲከኛ በተቃዋሚ ፊት መስተዋቱን የሚያኖረውም ለዚሁ ነው:-የደበቀውን እብደት በአደባባይ አጋልጦ ፍርድ መስጠት!!!!

#ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ጲላጦስ)💚💛

ምንጭ:- ፍትህ መፅሔት ቁጥር 13 (ጥር 24/05/2011)


ሸጋ ምሽት!!💚💛
@wegoch
@wegoch
@balmbaras
#Art_exhibition
Live music
Fashin show
Salsa dance

February 23
@ marriott excutive apartment

I care fund risinng event

@gebriel_19
@seiloch
@seiloch
ዴዝዴሞና
Written by መሐመድ ኢድሪስ

ከረፋፈደ በኋላ ነበር የትያትር ቤቱ የኋላ ረድፍ ላይ ቦታ ይዞ የተቀመጠው፡፡
የያዘው ክፉ የፍቅር ልክፍት ነው በዚህ ቲያትር ቤት ውስጥ እንዲገኝ
ያደረገው፡፡ ለሼክስፒር የተውኔት ድርሰቶች ፍቅርና ስሜት ኖሮት አያውቅም፡፡
እሱ ፍቅር የያዘው ከገፀባህሪዋ ስም ጋር ሞክሼ ስም ካላት የራሱ ዴዝዴሞና
ጋር ነው፡፡ ክፉ የቅናት ዛር መንፈሱን ከተቆጣጠረው ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል፡፡
እርዳታ ፍለጋ ሃኪም ጋር ሄዶ “ፓራኖያ አለብህ” ተብሏል፡፡ ከወንድ ጋር ያያት
ሴት ሁሉ እስዋ ትመስለዋለች፡፡ ከንግግርዋ፣ ከአዋዋልዋ፣ ከአመሻሽዋ፣
ከአለባበስዋ፣ ከጓደኞችዋ፣ ከቤተሰቦችዋ፣ከትናንት ታሪክዋ ጋር የተገናኘ
የቅናት መንፈስ ተጠናውቶታል። ስልክ ስታወራ በቅናት ልቡ ይመታል፡፡ ትንሽ
ካመሸች ጓደኞቿ ጋር ሁሉ እየደወለ ወይም እየሄደ ሊሰልላት ይሞክራል፡፡
ባልና ሚስት ሳይሆኑ ሌባና ፖሊስ ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ በእንቅልፍ ልብዋ
የሆነ ነገር ብታልጎመጉም፣ በሱ ነገር እየተጨነቀ፣ ፍችውን ለማወቅ ሲባዝን
ያድራል፡፡
ለእሷ ካለው እውር ጭፍን ፍቅር የተነሳ “ኦቴሎ”ን ሊያይ ቲያትር ቤቱ
የመጨረሻ ወንበር ላይ ቢሰየምም፣ መጋረጃው ተገልጦ ቲያትሩ የጀመረው
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ነበር፡፡
ቃሲዮን ሲያይ፣ እጁን ቡጢ ጨበጠ፡፡ ይሄ ነው ሚስቴን ሲዳራ የሚያድረው
እያለ ጥርሱን በቁጣ ያፋጫል፡፡ ኢያጎ ለኦቴሎ በመሰሪ ቋንቋው የዴዝዴሞናን
አለመታመን በጆሮው ሲያንሾካሹክ፣ እሱም ከኦቴሎ ከራሱ በላይ ቁጣው
ገነፈለ፡፡
ወደዚህ ቲያትር ቤት ለመግባት ዋና ምክንያቱ፣ ፍቅረኛው ትላንት በስልክ
ከወንድ ጋር ስትቀጣጠር በመስማቱ ነው፡፡ ሁሉንም ንግግር በትክክል
ባይሰማም “ማዘጋጃ” እና “አስር ሰዓት” የሚሉት ቃላት ግን አላመለጡትም፡፡
ኦቴሎ በኢያጎ ስብከት በቁጣ ሲንጎራደድ፣ ድንገት አይኑ ውስጥ ገባች፡፡ ፊት
ካለው ረድፍ ወንበር ላይ አንድ ጎረምሳ እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ
ተቀምጧል፡፡
እሷ ለመሆንዋ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም ከአመት በፊት
የገዘላትን ሻሽ አንገትዋ ላይ ጣል አድርጋዋለች፡፡ ረጅም ፀጉርዋንም ቢሆን
አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ እንዴት የሚስቱ ፀጉር ይጠፋዋል፡፡ ቢሆንም የማይቀና
ጥሩ ባል ለመሆን በመሞከር፣ ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ቁጥርዋን መታ፡፡
ይጠራል፡፡ ግን አይነሳም፡፡ ሻሹን በደንብ አስተዋለ፡፡ ራሱ ነው፡፡ የሚያያት
ከጀርባዋ ቢሆንም፣ ከት ብላ ስትስቅ፣ ሰውየውም አብሯት ሲስቅ ተመለከተ።
አሁንም ደግሞ ደወለ፡፡ ሶስቴ ከጠራ በኋላ “የደወሉላቸው ደንበኛ ስልክ ጥሪ
እያስተላለፈ ነው” አለች፤ ኦፕሬተርዋ፡፡
እሱ ላይ ስልክ እየዘጋች ከማንም ውርጋጥ ጎረምሳ ጋር ስታስካካ ሊታገስ
አልቻለም፡፡ ሜሴጁን ማዥጎድጎድ ጀመረ፡፡
“አንቺ ውሻ፣ ሸርሙጣ፣ ድሮስ ማን ይፈልግሻል!” አንዱ ነው፡፡
ቲያትሩ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል፡፡ ኦቴሎም የዴዝዴሞና አልፍኝ ለመግባት
እርምጃውን ጀምሯል፡፡
ሁለተኛውን ሜሴጅ ጻፈ፡፡
“በረጅም እንጨት አልነካሽም፡፡ ድሮስ እኔ አላቅሽም ወዘተረፈ …”
ለሃያ ደቂቃ ያህል ስምንት ሜሴጆችን አከታትሎ ቢጽፍም፣ የፍቅረኛው ሜሴጅ
የመጣው ግን ዘጠነኛውን ሊጽፍ ሲያስብ ነበር፡፡
እንዲህ ይላል፡-
“ረስተኸው ይሆናል፡፡ እኔ ግን አልረሳውም። ዛሬ የተገናኘንበት ቀን ነበር፡፡ ልክ
በዛሬው ዕለት፣ ከአራት አመታት በፊት፣ ምሽቱን ወጣ ብለን እንድናሳልፍ
አስቤ ነበር፡፡ ስጦታም አዘጋጅቼልሃለሁ፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ለገዛህልኝ ሻሽ
እሺ ያልኩህ ጊዜ ትዝ ይልሃል፡፡ የኔ ፍቅር፤ የገዛሁልህን ሮሌከስ ሰዓት፣
ማዘጋጃ ቤት አጠገብ ካለው ስዊዝ ሰዓት ቤት ውሰድ፡፡ የኔ ፍቅር ደህና ሁን፡፡
በፍጥነት ተነስቶ እየተንደረደረ፣ ወደ ፊት ወንበሮች አመራ፡፡ ሻሹን እያየ ወደሷ
ቀረበ፤ አጠገብዋ ሲደርስ ፊትዋን በእጁ አዞረው። ዴዝዴሞና አልነበረችም፡፡
ሁለቱ ፍቅረኞች በድንጋጤ ፈጠው እያዩት ነበር፡፡
ኦቴሎ ዴዝዴሞናን ያነቀው በዚያ ቅፅበት ነበር፡፡

ሸጋ ጁምኣ!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
2024/09/28 19:27:47
Back to Top
HTML Embed Code: