Telegram Web Link
" # መስቀሌስ_ለሚሹት_ነው !!"
------------
በወሎና ጎጃም መገናኛ ረዥም ድልድይ፣ አባይ በርሃ ውስጥ ጭርር ባለው ቦታ ከመኪናችን
ወርደን አከባቢውን ስንቃኝ አንድ መነኩሴ አገኘን። መቼስ ምንኩስና ዝምታ ነው፣ ብቸኝነት
ነው፣ ጭርር ባለው ቦታ ሰውነትንና ቃልን መመርመር ነው!! ወቅቱ ክረምት ነው፥ የአባይ
በሙላት ማግሳት ለመነኩሴ የነብስ ምናኔ አደለም የሩህ ጥያቄ ለምትንጠው አለማዊ
ሰውም ሃሴት ይሰጣል።
----------
ወዲያ ወሎ ወዲህ ጎጃም ሆነን ስናይ ወረተኛ ልባችን በማየት ቆዩ አለችን። ዛዲያ በዛ
ግዲም መቆየት መነኩሴ የመሆንን አቅም፣ በዝግታና በርጋታ ሃይማኖትን የመመርመር
ጥናትን፣ ውርውር የማለት የነብስያን ክጃሎት የመክላት መብቃቃትን ሲበዛ ያሻል። የኛ
ነብስ፣ አደለም ዝምታው በሚያስፈራው የአባይ በርሃ ሰው በቃኝ ብላ ልትከትም፣ ከፌስቡክ
ጫጫታ ብትርቅ ባንዴ ህቅ ብላ ትሞታለች!! እኛ ላፍታ ስንነጠል የምንፈራ፣ የውስጣችንን
ጫጫታ በገበያው መሃል የምንፈውስ፣ የጠፋንን የሰረቀን ጋር ሆነን የምንፈልግ ለሁሉም
ነገር ጓድ ፈላጊ ሰነፎች ነን!! ሰው ራሱ ጋር ሰብሰብ ብሎ ዝምምምም ሲል ወደ ውስጥ
ያያል!! ምንኩስና ይሄን እድል ይሰጣል!!
----------
ወደ እሳቸው ስጠጋ ሊባርኩኝ ወደ ኪሳቸው ገብተው መስቀላቸውን አወጡ።
"አባ፣ ያሲን መሃመድ እባላለሁ፥ የማይሳለም ሰላም አይሉዎትንም? ያልተሳለመስ
አይባረክምን?" ስል ጠየቅኳቸው፣
ከመልሳቸው ሳቃቸው ቀደመ፥ ፊታቸው በሳቅ ብርሃን ሞላ። ሰው ሲስቅ ሰውነቱ እንጂ
ሃይማኖቱ አይታይም። ሰው ሲስቅ ማስመሰል አይችልም።
"የለም የለም፥ መስቀሌስ ለሚሹት ነው፥ አንተማ የተባረክ ነህ" እያሉ ወደ ዘረጋሁት እቅፌ
በናፍቆት እንደሳሳ ስጋ ተጠግተው ታቀፉኝ።
"#መስቀሌስ_ለሚሹት_ነው" የሚለው ሃረግ ቢጥፉት መጥሃፍ ነው። ወደ መሬት
ቢያወርዱት ሰላም ነው። መስቀሉን የሚሹ እንደመሻታቸው ይድናሉ፣ ይባረካሉ።
መነኩሴውን የሚሹም ይባረካሉ፣ ይድናሉ። መስቀሉ በመነኩሴው ሰው እጅና ውስጥ
ነውና!! ደሞስ የክርስትና ትልቁ መስቀል በኔ ከተማ አደለምን?
----------
የኛ አይነቱ ባዛኝ፣ አባይና ዝምታውን ለፎቶ እንጂ ለኑሮ አንችለውም። እዛ ልንኖር አደለም
የመነኩሴውን ቡራኬ ልንቀበል ጊዜ አጠረን፣ የሚጮህ የሾፌራችን ክላክስ አስሮጠን።
ሩጫ ነው፣ መድረሻ አልባ ድክ ድክ፥ ኤዲያ!!
በጸሎታቸውና ምልጃቸው እንዲያስቡን አደራ ብለን ተለየናቸው።
------------
ይሄ ትውልድ የመዳኛውን ጥንተ-ስሪቶች በርትቶ ይይዝ ዘንድ ሳንሰለች ትንንሽ
የሚመስሉትን የመተለቂያ መንገዶች አጥብቀን እንጮሃለን።

((( ያሲን መሀመድ )))

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Mufti Hajji Omer Idriss
----------------------------
" አንድነት ማለት አብሮ በመቀማመጥ አይመጣም ። አንድነት እንደዚህ በመሰባሰብም
አይገኝም ። አንድነት በጉርብትናም አይመጣም ጎረቤት ሆኖ እንደተጣላ የሚኖር አለና ።
አንድነት አብሮ በአንድ ቤት በመኖርም የሚመጣ ነገር አይደለም ፡ ባልና ሚስት ሆነው
አይጥና ድመት ሆነው የሚኖሩ ሰወች አሉ ። አንድነት ልባዊ ነው ። አንድነት ልባዊ. ..ልባዊ
ተግባር ነው ስለዚህ ከልባችን አንድ ለመሆን እንትጋ "

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር ኢድሪስ

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ትያትሩ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ህይወት ራሷ በሰራችው መድረክ የscript ወረቀት እየወረወረች እሷ የምትፈልገውን ገፀ ባህርይ እንድንጫወት ስታስገድደን አልቅሰንም ሆነ ስቀን መተወናችን አልቀረም። አንዳንዶቻችን ደግሞ ጭራሽ ትወና ላይ መሆናችንን እንረሳና ሌላ ምስኪን ተዋናይን በተሰጠው ወረቀት ስለነው እናጠፋዋለን። የፊልሙ ዳይሬክተር የሆኑ የመሰላቸው አንዳንድ ተዋናዮች ደግሞ የሚስኪኖችን script እየቀደዱ እነሱ የተበላሸ ትወና ይሰጧቸዋል። በዚህ የተነሳ ህይወት የሰራችውን ታሪክ ተውነን ማሳየት አቅቶን የህይወትም ድራማ ሳይሰራ የኛም ትወና ሳይጨበጨብለት ትያትር ቤቱ ይዘጋል።ትወናችን አለመሳካቱን ያወቅን ጥቂቶች እያዘንን፣ ትወና መሆኑ ገና የገባን ብዙዎችም ነገሩ ሁሉ ግራ ገብቶን፣ ከኛ ትወና አልፈን የሌላውንም ያበላሸን 'ዳይሬክተር' ተብየዎቹ ጥቂቶቻችንም አንገታችን ደፍተን....ከመድረኩ እንወርዳለን። ከዛም.....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
(ከዚህ በኋላ ያለው ታሪክ የ ኮፒ ራይት መብቱ ለትያትሩ ፈጣሪ የተጠበቀ ስለሆነ የዚህ ፅሁፍ ደራሲ ሊከትበው አልተቻለውም።)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
(ኪሩቤል አዳሙ)

@wegoch
@wegoch
ፈገግ

"ከትናንት እስከዛሬ ታምሜ ሆስፒታል ሄጄ አላውቅም:: ለወድፊቱም የኢትዮጵያ እናቶች ይፀልዩልኛል"


@ethio_art
@wegoch
ያቺ ቀን እንደውም
በደንብ ያስታውሳታል...የማሸነፍን ቁንፅል ስሜት የቀመሰባትን ቀን..."መሸለም" የሚሉት ነገር በብልጭልጭ ከተጠቀለለው ምስጢራዊ ሽልማት በላይ ደረት አስነፍቶ በጥርስ የማይገለፅ ውስጥን ብቻ የሚያቀልጥ የንፁህ ደስታ መጎናፀፊያ ሲለብስ ያየባት ቀን...መሸነፍ የሚባለው ነገር አንገትን ቀና አድርጎ የማያስኬድ ከባድ ሰንሰለት መሆኑን ያወቀባት ቀን...እንደውም ያቺ ቀን...ሀያ ሁለተኛ ወጥቶ የተሸለመባት ቀን...
★ ★ ★ ★
ካርድ የሚወስዱበት ቀን ስለሆነ በጠዋቱ ለብሶ ጨርሷል፡፡ምንም እንኳ የትምህርት ነገር የማይሆንለት ከአልጋ ይልቅ ማንበብ እንቅልፍ የሚያመጣበት ስመ ተማሪ ቢሆንም ምን ትምህርት ቀይ ባህር እንደጠለቀ(ከ ሀምሳ በታች አምጥቶ በቀይ እስኪብርቶ እንደተፃፈለት) ለማወቅ ጓጉቷል "እማ ረፈደ እኮ!" አላቸው ከጓዳው በር ላይ ፊታቸውን አቆማጭረው ጣታቸውን ከአፋቸው ሰክተው 'ምንድን ነው የረሳሁት?' የሚል ፊት እያሳዩ የቆሙትን እናቱን፡፡አልመለሱለትም! "አሀ አሀ አሀ" እያሉ ወደ ጓዳ ገብተው ጠዋት መጥታ እንጀራ እንድታስቀምጥላቸው 'አደራ' ላሏቸው ጎረቤታቸው ሶስት እንጀራ እንደ ሳምቡሳ አጥፈው በጨርቅ ፊት ለፊት አስቀመጡላት፡፡የዚህ ግዜ ነው የልጃቸው ቃል እጆሮአቸው የደረሰው፡፡"ቢረፍድስ? አንደኛ እንደወጣ ተማሪ ስትጣደፍ ደሞ...ወገኛ! ካወራህ መች አነሰህ?!" እያሉ ነጠላቸውን አንስተው ቀድመውት ወጡ፡፡ልክ እንደእሱ እንደዚህ ካርድ በሚሰጥበት ቀን ከጎበዝ ተማሪዎች ሌላ የተቀሩት ተማሪዎች ሰላም አይውሉም፡፡"እንዴት ሂሳብ አርባ ታመጣለህ? በየቀኑ ቁማር ተጫውተህ የበላሀቸውን ብዮች ስትቆጥር አይደል እንዴ ምትውለው?"ይሉታል፡፡ሂሳብ እነሱ አይገባቸውም! አስተማሪዎቹም አልገባቸውም! "ቆይ እኔ አበበ የገዛውን ብርቱካን ለማንም አድሎ ስንት እንደቀረው ምን አውቅለታለሁ?ይሄ ልፅደቅ ባይ! እኔ ቆሪጥ አልቀልብ! እንዴት ነው ሀናን የቀዳችው ስንት ሊትር ውሀ መሆኑን የማውቅላት? ይቺ....ልብ ካላቸው በረከት ዛሬ ስንት ብይ አለው ብለው አይጠይቁም?" ይላል ለዛች ትንሽ ጭንቅላቱ የሂሳብን ስህተተኝነት ከአቅሟ በላይ በማስረዳቱ እየረካ፡፡ትምህርት ቤቱ ሲደርስ ከአንድ እስከ ሶስት የወጡት ተማሪዎች እየተሸለሙ ነበር፡፡ቦታ መርጠው ተቀምጠዋል የነሱ ክፍል ሲጠራ ማን እንደሆነ በሀሳቡ እየገመተ ማዳመጥ ጀመረ፡፡ ስምንተኛ ለ ክፍል መጠራት ተጀመረ፡፡ስሙ ተጠራ!ያለበት ክፍል ሌላ በረከት መኖሩን ባያውቅም እንዳለ እርግጠኛ ሆነ...እስኪደገም መጠበቅ ጀመረ..."በረከት ታደሰ" ይላል እላይ የቆመው መድረክ መሪ...ጆሮውን ተጠራጠረ (ድሮምኮ ከሩቅ ሲያዋሩት "እ" ማለት ማብዛቱን አልወደደውም ነበር) "እልልልልልልል! አንቺ መ ብርሀን ፀሎቴን ሰምተሽ እልልልል" አለች እናቱ ግንባር ግንባሩን እየሳመች፡፡ግራ ገባው...'እንዴት አንደኛ ወጣለሁ?' የሚለው በዚህች አጭር የድል ሰዓት ሊመለስ ማይችለውን ጥያቄ ጠየቀ! ('እኔኮ ስሰክር ማደርገውን አላውቅም!' አለች ጦጢት) ወደ መሸለሚያው እንዲሄድ "ሂድ እንጂ?" የሚል የእናቶች ድምፅ አስገደደው፡፡አንዳንድ እናቶች ደግሞ እሱን ተገን አድርገው ልጃቸውን ሲመክሩ ይሰማዋል "ይሄ ኸናንተ ጋር ሆኖ ኳስና ብይ ሲያለፋ የሚውለው ልጅ አይደል? እሱ ተጫውቶ ገብቶ ያጠናል፡፡የተባረከ ልጅ! አንተ ትጋደማለህ...ብለው በኩርኩም ሲደቁሱት እያለፈ ይሰማዋል፡፡የአረማመዱን ምት እንኳ ማስተካከል አቅቶት ይደነቃቀፋል፡፡ሁል ግዜ አርፍዶ ሲመጣ በልምጫቸው ዦጥ የሚያደርጉት ዳይሬክተሩ ሽልማቱን ሲያቀብሉት 'የት ነው ማውቀው?' የሚል ስሜት ይነበብባቸዋል፡፡ሽልማቱን ተቀብሎ ሲወርድ በመደነቅ የሚመለከቱትን ፊቶች ወደዳቸው...ጮክ ብለው በአይናቸው አሸናፊነቱን እየሰበኩት ነበር፡፡ አንደኛ እንደወጣ ራሱን አሳመነው፡፡ ሳያውቀው ጎበዝ መሆኑን አሰበ፡፡ የድል ስሜት ትንሽ ነፍሱን አጨናነቃት፡፡ከዚህ በኀላ ያቺ የክፍላቸው ቆንጆ ልጅ 'አስረዳኝ?' ብላ ቤቱ ድረስ እንደምትመጣ አሰበ፡፡ታዲያ እሱ ምኑ ሞኝ ነው ኮራ ይልባታላ! በስማም!!! እንደዛ አይነት ስሜት ተሰምቶት አያውቅም!፡፡"ይቅርታ!" አለ መድረክ መሪው "ከክፍል ሀላፊው እንደተነገረን የአንደኛና ሀያ ሁለተኛ የወጣው ተማሪ ዉጤት ተቀያይሯል፡፡ተማሪ በረከት ታደሰ የወሰድከውን ሽልማት እንድትመልስ..."ብሎ ክው አደረገው! ሀያ ሁለተኛ? ክፍላቸው ውስጥ ሀያ አራት ተማሪዎች አሉ፡፡ ሁለቱ ተደባድበው ተባረዋል፡፡"ምናለ ትንሽ ሰው እስኪበተን እንኳን የስህተቷን ድሌን ባጣጥም? ሀያ ሁለተኛ ማን ነው የወጣው? እኔ? ኸረ ይደብራል! አሁን አንደኛ አልወጣሁም እንዴ?"ራሱን ጠየቀ፡፡አይረሳውም የተሰማውን ከባድ የድንዝና ስሜት...አይረሳውም የእናቱ የሀፍረት ፊት...አይረሳውም የጓደኞቹ ፌዝ ...ፍፁም አይረሳውም የአሸናፊነትን ጣዕም የቀመሰበት እለት...አይረሳውም የሀናንን ውሀ መጠንና የአበበን ብርትኳን የልግስናውን ትርፍ ማወቅ የፈለገበት ቀን...ያቺ ቀን...ሀያ ሁለተኛ የወጣባት ቀን...እንደውም ያቺ ቀን፡፡

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ትዝብት#1

Yeha Arch students & Xpress presents collaborating with wegoch.


Send us your comments and tzbt @Expressme_bot

@wegoch
@inluvwidart
@yehas
(ከሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም)
ርዕስ፡- መልህቅ
ደራሲ፡- ዘነበ ወላ
የሕትመት ዘመን፡- 2010 ዓ.ም
የትረካ ሥፍራዎች፡ - ምጽዋ ፥ አስመራ ፥ አሰብ ፥ እና አዲስ አበባ
በጨረፍታ
የገጽ ብዛት፡- 448
ዋጋ፡- 150 ብር
ይህ መጽሐፍ ልብ ወለድ ነው እንዳንል ጥናት ላይ እንደተመሰረተ ጽሁፍ
ዋቢ መጻህፍት ታክለውበታል፤ ያውም በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተጻፉ
በርካታ መጻሕፍትና ሌሎችም ምንጮች። በሌላ በኩል እውነተኛ ታሪክ ነው
እንዳንል አቀራረቡ የታሪክ ሳይሆን የልብ ወለድ ድርሰት የአጻጻፍ ዘዴን ነው
የተከተለው፡፡ ታዲያ የድርሰቱ ዓይነት ምንድነው ብለን እንመድበው?
ምናልባት ከደራሲው ዘነበ ወላ ጋር በመስማማት፣ በልብ ወለድ መልክ የቀረበ
እውነተኛ ሁነት ነው ብንል አያስኬድም ይሆን?
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተለመደው የልብ ወለድ አጻጻፍ ዘዴ ወጣ ያሉ ፥ የቤተ
ሙከራ ዓይነት ጽሑፎች ብቅ ብቅ ማለት መጀመራቸውን እንገነዘባለን፡፡ ልብ
ወለዶች ናቸው እንዳንል አጽመ ታሪክ የሌላቸው፤ በውቅር (“ፕሎት”) ወይም
በምክንያትና ውጤት ላይ ያልተመሰረቱ፤ ላይ በላይ እንደ አሸዋ በተከመሩ
ሁነቶች ላይ ብቻ የተገነቡ ጽሑፎች ከአንድም ሁለት በላይ መከሰታቸው
ተስተውሏል፡፡ “መልህቅ” ከእነዚህ አፈንጋጭ መሰል ጽሑፎች አንዱ ይሁን
ወይም አይሁን በእርግጠኝነት ለመናገር ያዳግታል፡፡
ለማንኛውም ይዘቱ በደርግ ዘመን (ሥርዓቱ ተንኮታኩቶ ከመውደቁ ቀደም
ባሉት ሁለት ዓመታት) በአስራ አምስቱ ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ባህር
ኃይል አካባቢ የነበረውን የሕይወት ሁኔታ አጉልቶ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡
በባህር ኃይሉ የነበሩት የጦር መርከቦች ዓይነት፤ የባህረኞቹ (የአዛዦቹና
የታዛዦቹ) የሕይወት ዘይቤ፤ የዕለት ተዕለት የተግባር እንቅስቃሴአቸው፤
የቅኝታቸው ጉዞና መልስ፤ የባህሩ መናወጥና መልሶ መርጋት፤ በተለይ በጉዞ
ላይ የሚደርሱ ፈተናዎች፤ የየዕለቱ ምግብና መጠጥ፤ አልፎ አልፎ
የሚከናወኑት የመዝናኛ ዝግጅቶች፤ የባህረኞች (በተለይም የወጣቶቹ)
የወሲብና የፍቅር ሕይወት፤ የአብዮቱ ዘመን ይፈጥረው የነበረው ፍርሃትና
ጭንቀት፤ አንዳንድ ባህረኞች ሥርዓቱን መሸከም አቅቷቸው ወደ ባዕድ አገር
ለመሰደድ የሚያደርጉት ሙከራ፤ የተፈጥሮ አስደናቂ ክስተቶች፤ በተለይም
የአንዳንድ አሳዎች፥ የየብስ ተንፏቃቂ ነፍሳትና አእዋፍ አስገራሚ የሥጋ
ተራክቦና የሚከተለው የሕይወት ሕልፈት፤ የአሳዎች ዝርያዎች ዓይነትና
ባህርያቸው፤ በአጠቃላይ በባህርና በየብስ የባህረኞችና የሌሎች ፍጡራን
ሕይወት ምን እንደሚመስል ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው -
“መልህቅ”፡፡
ዘነበ ወላ በዚህ መጽሐፉ ከቀድሞዎቹ ሦስት መፅሐፎቹ (ህይወት በባህር
ውስጥ ፥ ማስታወሻ ፥ እና ልጅነት) በበለጠ ደረጃ ጥንካሬ ያሳየው በገለጻ
ኃይሉ ነው ብንል ሞጋች የሚነሳ አይመስለኝም፡፡ ዋቢ እንዲሆን ቀጥሎ
ያለውን እንመልከት፤
“ወደ ራስ ዱሜራ ስንቀዝፍ ቀይ ባህር እንደ ራስ ዳሽን ተራራ ይከመራል፡፡
ጀልባችን ባህሩን በርቅሳው ለማለፍ ትጥራለች፡፡ ባህሩ አፍታም ሳይቆይ
እንደሊማሊሞ ገደል ይናድና ቁልቁል ወደ መቀመቅ ጅው እንላለን፡፡ ከላይ
ውሃ እንለብሳለን፤ ከስር ውሃ መቀመቅ ውስጥ እንሰጥማለን…” (ገጽ 10)
ተጨማሪ ምሳሌ ቢያስፈልግም እነሆ፤
“7,000 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጨው የጀልባዋ ሞተር እንደ አንዳች
ያጓራል፡፡ ማዕበሉን ሰንጥቆ ለማለፍ የጀልባዋ መቅዘፊያዎች እንደ አንዳች
ይሽከረከራሉ፡፡ ባህሩ ተበርግዶ እልም ያለ ገደል ይፈጥራል፡፡ ጀልባዋን ሙሉ
በሙሉ ይውጣትና መልሶ ተጉመጥምጦ እንደተፋት ሁሉ ባህሩ ደረት ላይ
ትገኛለች፡፡ ቀይ ባህር ካለው ጥልቀትና ስፋት አኳያ 118 ቶን የሚከብደው
የጀልባዋ አካል የቡሽን ያህል አትከብደውም፡፡ ከማዶ እንደ ጥቀርሻ የጠቆረ
የባህር አካል ተንደርድሮ መጥቶ ይላተመዋል። እሷም እንደ ሰይፍ ሰንጥቃው
ወደፊት ትመነጨቃለች፡፡ አንዳች ዓይነት የቁጣ፥ የመዓት ድምጽ በድፍን
ባህሩ ላይ ያስተጋባል” (ገጽ 104)
የመጽሐፉ ባለታሪኮች በርካታ ናቸው። በይበልጥ ጎልተው የሚታዩት ግን
ከወንዶቹ መሐከል ያሬድ ሐጎስ፥ ስንታየሁ፥ በብዙ ቦታ ባናየውም ሊረሳ
የማይቻለው ሌናተናንት አሸናፊ ዋቅጅራ (የጀልባ 202 አዛዥ)፤ ከሴቶች
መሐከል ደሞ ገነት አስገዶም፥ ዓወት ግርማይ ፥ እና ኮማሪቷ አበባ አድማሱ
ይገኙባቸዋል፡፡ እነዚህ የመጽሐፉ ባለታሪኮች በገሐዱ ዓለም የነበሩ ይሁኑ
ወይ ደሞ የፈጠራ ገጸ ባህሪያት ይሁኑ አንባቢው ለይቶ ለማወቅ ከቶም
አይቻለውም፡፡ ነገር ግን የፈጠራ ታሪክ ገጸ ባህሪያት ከሆኑ በገሐዱ ዓለም
ሞዴል እንዳላቸው ሊያጠራጥር አይችልም፤ ታሪኩ በእውነተኛ ሁነት ላይ
የተመሰረተ ነው ስለተባለ፡፡
ለመሆኑ የመጽሐፉ ዓላማ ምንድነው? የገጸ ባህርያቱን ስሞች ስናጤን
እያንዳንዳቸው ከየት ብሔረሰብ እንደፈለቁ ይጠቁሙናል፡፡ ከሁለት የተለያዩ
ብሔረሰቦች የተፈጠሩም አሉ። ነገር ግን ሁሉም ለማለት ይቻላል እንደ
ውሁድ ኢትዮጵያውያን ይተያያሉ እንጂ የብሔረሰብ ማንነታቸውን ከቁም ነገር
ሲያስገቡ አናይም፡፡ ትንሽ ያፈነገጠ አመለካከት ያላቸው ቢኖሩ ከሰሜን ጫፍ
በኩል ያሉት ብቻ ናቸው፡፡
በትረካው መጨረሻ አካባቢ ሌፍተናንት አሸናፊ ወደ ሱማሌ ከመኮብለሉ
በፊት የፈጸመው ድርጊት አንባቢውን ግራ ያጋባዋል፡፡ መርከበኞቹ ከመርከቡ
ዘልለው ወርደው ባህር ውስጥ እንዲገቡ ያዝዛቸዋል። እነሱም በዋና
ነፍሳቸውን ለማዳን ሲጥሩ ይታያሉ፡ የሞቱት ሞተው የተቀሩት ይተርፋሉ፡፡ ግን
የሌተናንት አሸናፊ ድርጊት ምን ትርጉም አለው? እነዚህ መርከበኞች በእሱ
ስር ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ በደል ሰርተውበት እንደሆነ የተነገረ ነገር
የለም፡፡ ነገር ግን ለከፋ አደጋ አጋልጧቸው መኮብለሉ ትርጉሙ ምንድን ነው?
ነገሩ እንቆቅልሽ ይሆንብናል፡፡
የእነዚህ መርከበኞች ዕጣ ፈንታ ይህ ብቻ ቢሆን ኖሮ ቢያሳዝንም “መቼስ ምን
ይደረጋል!” ተብሎ ሊታለፍ ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን በዚህ ጦስ ምክንያት
ባልፈጸሙት ወንጀል ተከስሰው ለፍርድ ሲቀርቡ እናያለን፡፡ እነሱ የአዛዣቸው
ሰለባ ከመሆን በስተቀር አንዳችም የፈጸሙት ወንጀል የለም፤ ያሬድ ሀጎስ
ቀደም ብሎ ለመሰደድ ያደረገው ያልተሳካ ሙከራ እንዳለ ሆኖ፣ ታዲያ
ለምንድነው ለፍርድ የቀረቡት? ምክንያቱን ለመረዳት አሁንም ከመጽሐፉ
መጥቀስ ግድ ይላል፤
“የኢትዮጵያ አብዮተኞችም እንዲሁ ራሳቸውን ከወንጀል ለማጽዳት ባለፉት
አስራ አምስት ዓመታት የቀጠለውን የጦስ ፍየል መስዋዕት የማድረግና
ማርከሻውን መፈክር አሰምቶ የማለፍ ልምድ፤ ዛሬ የጦስ ፍየል አራጁ የነገ
ተረኛ እየሆነ ሞትን በቅብብሎሽ አኖሩት፡፡ ይህ የጦስ ፍየል ከምድር ጦር ፥
ከአየር ኃይል ፥ ከባህር ኃይል ፥ ከሲቪሉ ሕብረተሰብ እየታደነ የአብዮታዊያኑን
ጦስና ጥንቡሳስ ይዞ ይገደልና በሟች ሬሳ ላይ መፈክር ይሰማል፡፡ ዛሬም
ያሬድና ጓደኞቹ ባልሰሩት ወንጀል እንደ ወንጀለኛ ታፍነው ደህንነት ቢሮ
በመገኘታቸው የጦስ ፍየል ሊያደርጓቸው መወሰኑ ወለል ብሎ ታየው፡፡” (ገጽ
440)
ስለ አስራ ሰባቱ ዓመታት የጨለማ ዘመን በርካታ ልብ ወለዶችና ኢ - ልብ
ወለድ መጻሕፍት ከዚህ ቀደም ተጽፈዋል፤ የበዓሉ ግርማ “ኦሮማይ”፥
የአማኑኤል ሐዲስ “አስተኳሹ”፥ የባቢሌ ቶላ “የትውልድ
ዕልቂት” (አውግቸው ተረፈ እንደተረጎመው) እና ሌሎችንም ለመጥቀስ
ይቻላል። “መልህቅ” ከእነዚህ አንዱ መሆኑ ነው፡፡ የአብዮቱ ዘመን ታሪክ
በእነዚህ ብቻ ሊወሰን የሚችልም አይደለም፡፡ አሳታሚ በማጣት
በየጠረጴዛው ኪስ ውስጥ ተዘግቶባቸው የሚኖሩ ልብ ወለዶችና ኢ -
ልብወለድ መጻሕፍት እንዳሉ በቀላሉ መገመት ይቻላል፡
፡ ከድርጊቶቹ
አስከፊነት የተነሳ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ወደፊት ከአምሳና መቶ አመታት በኋላም
በታሪካዊ ልብ ወለድ መልክ ሌሎች በርካታ መጻሕፍት እንደሚዘጋጁ
ለመገመት ነቢይ መሆን አያሻውም፡፡

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ወሎ- እስብሪስ! !!!!


ከገጠር የመጣው አጎቴ መሠረተ ትምህርት ቢማርም ንቃቱ ግን ይገርመኛል ።መጠየቅ ፤
ማስተንተን ፤ ያየውን የሰማውን ነገር ፈጥኖ ወደ እሱና ወደሚኖርበት ማህበረሰብ እውነት
አስጠግቶ ፍችና ትርጉም መስጠት ይችልበታል ። ወግ አዋቂ ፤ ቃላት ፈጣሪና ቃል ነጣቂና
ቀልደኛ ነው ። humorous የሚሉት አይነት ሰው ነው ። ከቃል ነጣቂነቱ ገጠመኝ ጀባ
ልበላችሁማ ። ለምሳሌ አንዷ ዘመዳችን የመንግስት ስራ መያዟን ነግሬው ስለነበር ድንገት
መንገድ ላይ ሲያገኛት ባለመስሪያ ቤት ሆነሻል አሉ ሲላት you are employed ለማለት
እንደሆነ ገብቶኛል ። ተቀጠርሽ አሉ ከሚለው ጎርባጣ ቃል ይልቅ የሱ ቃል ሰውኛና ለስላሳ
ሆኖ ተሰማኝ ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ TV እየተመለከትን ሳለ ዘመነኛ ወጣቶች ዘፈን እያቀነቀኑ ከዘፋኙ ሃላ
ሰንሰለት አንገቱ ላይ አንጠልጥሎ ሆሆይ ሃሃሃ ሁሁሁ ሂሂሂሂሂ እያለ እንደ rapper
የሚደነፋውን ልጅ አይቶ ወንድምየ "" ይህ ልጅ በኛ አገር አምቧታሪ ነው የሚባለው"" ሲለኝ
ቃሉ ሂዶ ስክት የሚል /fitting word/ ነበረና በሳቅ ገደለኝ ።
ይከው አጎቴ ባለፈው ሰሞን ወደ ደሴ ብቅ ብሎ ተያይዘን ጭማቂ ቤት ገባን ። አስተናጋጅ
ምን ልታዘዝ ብላ ጠየቀች ። እስብሪስ ጭማቂ ወዲህ በይማ ብሎ አዘዘ ። ጭማቂውን
ልታመጣ ዘወር ስትል አጎቴ እንዲህ ተናገረኝ ""... እስብሪስ ጭማቂና ወሎየ ነገረ ስራቸው
አንድ ነው ። """ ሲል ወጉን ጀመረ ። እኔ ደግሞ ""እንዴት ብሎ??? "" ብየ ጠየቅኩት ።
እሱም መልሱን ቀጠለ ""ወንድሜዋ አድምጠኝማ ፤ እስብሪስ ጭማቂ ባባየ ፤ ዘይቱን ፤
ማንጎ ፤ አቡካዶ ሁሉም ራሳቸውን ችለው ይገቡና ሲቀላቀሉ እኔ ማንጎ ፤ እኔ ዘይቱን ፤ እኔ
ነኝ ባባየ (pappaya ለማለት ነው) እያሉ ራሳቸውን መነጣጠል አይችሉም ፤ እስብሪስ
ሆነዋልና ። ወሎየም እንዲሁ ነው ብሎ ለትውልድ የሚተርፍ ምስጢር ሹክ አለኝ ።
በከተሜኛ Spris የተባለውን ጭማቂ ነው አጎቴ በገጠሬ አንደበቱ እስብሪስ ብሎ የነገረኝ
። ወይ እስብሪስ!!!!
እውነትም ወሎ አማራ ፤ወሎ ኦሮሞ ፤ ወሎ አርጎባ ፤ ወሎ ራያ በ3000 ዘመን ረጅም ታሪክ
ሂደት ውስጥ ተጋብተው ተዋልደው ተዋህደው ""እስብሪስ"" ሆነዋልና በየዘውጉ
ለመነጣጠል መሞከር ከእስብሪስ ውስጥ ዘይቱንን ፤ ማንጎውን ፤ ብርቱካኑን ፤ ነጥሎ
ለማውጣት እንደመሞከር ይቆጠራልና እስብሪሶችን አትነካኩን ለማለት ያህል ነው ። መገን
ወሎ እስብሪሱ!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
""ድምጣችን ይሰማ!!!!"


ይህንን ""ምስኪን የህዝብ አገልጋይ ልጅ አሰሩት አይደል??? """ Unfair ነው........!!!!!
ሰዎቹ ዱቄት አሸክመውት ነበር ጎበዞቹ ደግሞ ዱቄት አደረጉት!!!
ምጽጽጽጽጽጽጽ........ይች ሃገር የሚሰራላትን እኮ አታውቅም!!!!!! "የተሸከመው ኬሻ ግን
ተፈትሾ ይሆን??
ከሾይጣን እንተርፋለን ብለን ተደምረን ነበር ዛሬ ግን ተደበርን አለ አሉ አብዲ ኢሌ... ሰው
ለሰው ድራማ ሲችልበት ቀሽት እኮ ነው!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ቁጭ በሉ መንግስት
ከወጨፎ ኖርዌይ
Aራዶች ከተማችን ውስጥ ስለውስልትና የሚቀልዱት Aንድ ቀልድ Aለ Aዝግሞ በገረድኮ፣
Eስክትመጣ ሚስትኮ' የሚሉት።
ልጅ፣ Aባቱን ለትምህርት ቤት Aንድ የማቀርበው የቤት ስራ Aለብኝ ብትረዳኝ ብሎ
ይጠይቀዋል። Aባትም በደስታ ልጄ ማለት!
ልጅ፣ ፖለቲካ ማለት ምን ማለት ነው?
Aባት፣ ዌል! ቤታችንን Eንደ ምሳሌ Eንውሰድ። Eኔ ለምሳሌ Aባወራ Eንደመሆኔ መጠን
ሰርቼ የማመጣው የወር ደመወዝ Aለ፤ Eኔን Eንደ ቶ፥ ብሌየር ብትወስደኝ Eናትህን
ደግሞ ገንዘቡን ተቀብላ ቤቱን ስለምታስተዳድር Eንደ Eንግሊዙ ገንዘብ ሚንስቴር ጎርደን
ብራውን ቁጠራት፤የAንተን ፍላጎትህን ስለምናሙዋላልህ Aንተን ህዝብ ብለን ልንጠራህ
Eንችላለን፤ የቤት ሰራተኛችንን ደግሞ የሰራተኛው መደብ ብለን ልንጠራት Eንችላላን፤
ትንሹን ወንድምህን ደግሞ የወደፊቱ ተስፋ ስለሆነ የነገው Aገር ተረካቢ Aበባብለን
ልንጠራው Eንችላለን፣ Aሁንገባህ ልጄ? ፖለቲካ ማለት Eንደዚህ ነው፣ ይለዋል።
ልጅ፣ ርግጠኛ ሆኜ መናገር Aልችልም ግን ያልከኝን Eንዲገባኝ ለማድረግ Eሞክራለሁ
ብሎ ምሽቱን ከAባቱ ይለያያል።
በዚያ፥ Eለት ሌሊት ታናሽ ወንድሙ ሽንትና የተፀዳዳው ነገር ስላልተቀየረለት
Eየቆጠቆጠው ምርር ብሎ ሲያለቅስ ታላቅ ወንድሙ ይነቃና Eናትና Aባቱን ለመቀሰቀስ
ወደ መኝታ ቤት ሲገባ Eናት ድብን ያለ Eንቅልፍ ውስጥ ሆና መስማት Eንደማትችል
ያውቃል፣ Aባት ደግሞ ከመኝታ ቤቱ ውስጥ የለም፤ ወደ ሰራተኛዋ መኝታ ቤት
ሲሄድደግሞ በሩ ተዘግቶ ያገኛል፣ በቁልፍ ቀዳዳ ውስጥ Aጮልጎ ሲመለከት ለካስ ወላጅ
Aባትከሰራተኛዋ ጋር ፈንጠዝያ ላይ ነው፣ ልጅ በመጣበት Eግሩ ወደ መኝታ ክፍሉ
በመመለስለሊቱን Eንደምንም ብሎ ያነጋና ጠዋት ቁርስላይ፤ Aባባ፣ Aሁን ፖለቲካ ማለት
ምን Eንደሆነ በደንብ ገባኝ ይለዋል።Aባትም፤ ጎበዝ ልጄ ባንተ ግንዛቤና በራስህ ቃል
Eስቲ ፖለቲካ ምን ማለት Eንደሆነ ተንትነህ ንገረኝ' ይለዋል። ልጅም፤ ` ደህና Aባባ! ቶ፥
ብሌር ሰራተኛውን መደብ በሚዘውርበት ጊዜ፤ ጎርደን ብራውን ደግሞ ድምፁን Aጥፍቶ
በተኛ ጊዜ፤ ህዝብ ደግሞ በAጠቃላይ የተገባለትን ቃልኪዳን ባልተፈፀመለት ጊዜ Eና
የወደፊቱም ተስፋ ደግሞ ጭራሽ ጨቅይቶ Eንዲቀር በሚደረግበት ወቅት ፖለቲካ የሚለው
ቃል ትርጉሙ ምን Eንደሆነ Aሁን ነው የገባኝ' በማለት ለAባቱ Aጠይሞ ይነግረዋል።
@wegoch
@wegoch
@wegoch
“ስንደመር” የኪነ ጥበብ ምሽት
ሐሙስ ይካሄዳል


በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት የሚቀርበው “ስንደመር” የተሰኘ የኪነ ጥበብ ምሽት የፊታችን ሐሙስ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡ በዕለቱ ወግ፣ ዲስኩር፣ መነባንብና ሌሎች የወቅቱን
የአንድነትና የመደመር መንፈስ የሚያንፀባርቁ ኪነ ጥበባዊ ድግሶች እንደሚቀርቡ የምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ምስክር ጌታነው ገልጿል፡፡ አርቲስት ፈቃዱ ከበደ ወግ የሚያቀርብ ሲሆn ዲስኩር ደግሞ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ረ ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ የሙዚቃ ባለሙያውና የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ም/ዋና ዳይሬክተር ሰርፀ ፍሬስብሃት ያቀርባሉ፡፡ በአርቲስት ሽመልስ አበራ ደግሞ “ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” በመሶብ ባህላዊ ባንድ ፉከራና ሽለላ ታጅቦ እንደሚቀርብም ታውቋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ለመታደም 100 ብር የመግቢያ ዋጋ የሚከፈል ሲሆን በአሁን ሰዓት ትኬቶቹ በጃፋር መፅሐፍ መደብር፣ በዮናስ መፅሐፍ መደብር፣ በዓይናለም መፅሐፍት መደብር፣ በሳሚ ካፌና ሬስቶራንት እንዲሁም አራት ኪሎ በሚገኘው ምርፋቅ ካፌና ሬስቶራንት ማግኘት እንደሚቻል ታውቋል፡፡

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
2024/09/30 07:22:26
Back to Top
HTML Embed Code: