Telegram Web Link
ኢስላም ሰላም ነው! !!!!!!!!!!!!!!!!!
ከአንደበታቸው ይቅርታ ፤ ፍቅር ፤ ሰውነት ፤ አንድነት የማይለያቸው አባት ዛሬም
አስደመሙን! !!!!!
አቤት ሙሃባ !!!!!!!!!
!አቤት አንደበት!!!!!!!
!አቤት ርጋታ! !!!!
የሰው ልጅ ሲናገር ወይ ከአፉ ወይ ከነፍሱ ነው ። ከአፉ ሲሆን አይጣፍጥም ። ነፍስን
አይድስም ( አያሸንፍም) ። ከነፍስያው አፍልቆ ሲናገር አጥንትን ያለመልማል ። እኚህ
አባት ሲናገሩ ግን ንግግራቸው ከጥልቁ ነፍስያ የሚፈልቅ ለመሆኑ የኛ ነፍስ ራሷ
ትመሰክራለች ። ሲናገሩም አጥንታችን አብዝቶ ይለመልማል ።የኢትዩጲያ አምላክ ባለ
ሙሃባ አባቶችን አብዛልን! !!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ከአመት አመት ያድርሰን!!!!!!


ሻደይ ማለት በኸምጣጞ ለምለም ማለት ሲሆን ሴቶች
የሚታጠቁት ቅጠል ነዉ፡፡ የሻደይ ታሪካዊ አመጣጥ
ስንመለከት ደግሞ ሀይማኖታዊ ይዘት ያለው ነው፡፡በሰሜን
ወሎ ቆቦ (ሶለል ይባላል)፣ በዋግ ህምራ ሰቆጣ (ሻደይ)
በላስታ ላሊበላ (አሸንድዬ) እየተባለ ይጠራል።፡፡በዋግ
ኽምራ ሀገረ ስብከት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የሻደይ
ምስጋና / ጨዋታ አንዱ ሲሆን ልጃገረዶች በአማረ ልብስ
ደምቀው አሸንድዬ በሚባል ቄጠማ ጉንጉን ወገባቸውን
አስረው የሚያከብሩት ነው። በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ሃማኖታዊ ይዘት አለው። በዓሉ ከነሐሴ 16
ጀምሮ እስከ ነሐሴ 21 ቀን ድረስ ይከበራል።
የሻደይ በዓል ከኦርቶዶክስ ተዋሐዶ እምነት ጋር እየተያያዘ
የመጣ ሲሆን አጀማመሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻ አለው፡፡
ከነዚህም መካከል የአዳም ከገነት መባረር፣ የኖኅ ዘመን
የጥፋት ውኃ፣ ከዘመን መለወጫ፣ ከመጥመቀ መለኮት
ቅዱስ ዮሐንስ አንገት መቆረጥ፣ የእመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም ትንሣኤ (ፍልስታ) እና ከመስፍኑ ዮፍታሔ
ልጅ ታሪክ ጋር በማስተሳሰር የሚያስቀምጡት ሲሆን
በማኅበረስቡ አባቶችና ሊቃውንቱ ዘንድ ጎልቶ
የሚነገረውና የሚተረከው ግን የእመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም ትንሣኤ (ፍልስታ) በዓልን መሠረት
ያደረገ ነው።
አባታችን አዳም በገነት ሳለ ሕግ በመተላለፉ ጸጋ
እግዚአብሔር ርቆት እርቃኑን በሆነ ጊዜ አካሉን ለመሸፈን
ቅጠል መጠቀሙን ለማሰብ ያች አዳምና ሔዋን
ክብራቸውን ተገፈው ከገነት የተባረሩባትን ዕለት በማሰብ
በወቅቱ ያገለደሙትን ቅጠል በምልክትነት በመውሰድ
የሻደይ ቅጠልን በገመድ ላይ ጎንጉነው በወገባቸው
አገልድመው/አስረው/ አዳምና ሔዋን ከገነት
ከመውጣታቸው በፊት ግብረ ሥጋ ግንኙነት ያልጀመሩ
ደናግላን ስለነበሩ ያንን በመከተልና በምሳሌነት በመውሰድ
ያላገቡ የአገው ልጃገረዶች ተሰባስበው ያችን ዕለት
ወይም ቀን በመታሰቢያነት ለመቁጠር ወይም ለመዘከር
የሻደይ ጨዋታን መጫወት ወይም ማክበር እንደጀመሩ
ይናገራሉ።
ከኖኅ ዘመን ታሪክ ጋር ያለው ግንኙነት ደግሞ ከጥፋት
ውኃ በኋላ ውኃው የመጉደሉን ምልክት ርግብ ለኖኅ
የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ በመምጣት በምድር ሰላም
እነደሆነ የምሥራች አብሥራለች። ከዚሁ ጋር በተገናኘ
በዓሉን ያንን ለምለም ቅጠል ወገባቸው ላይ በማሰር
ከጨለማ ወደ ብርሃን ተሸጋገርን ሲሉ ማክበር እንደጀመሩ
ከታሪኩ ጋር አያይዘው ያስቀምጡታል።..
እናቶችና እኅቶች በአደባባይ ወጥተው የድንግል ማርያምን
ሞትን ድል አርጎ መነሣት ትንሣኤዋንና ዕርገቷን እንደ
ነጻነታቸው ቀን ቆጥረው የተለያዩ አልባሳትን በማድረግና
ለበዓሉ ክብር በመስጠት ከበሮ አዘጋጅተው አሸነድዬ
የተባለውን ቄጠማ በወገባቸው ታጥቀው ምስጋና
በማቅረብ በዓሉን ይዘክራሉ፡፡ በዚህም መሠረት የሻደይ
ጨዋታ የፍስልታ በዓል መከበር ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ
እንደተጀመረና በምእመኑ ለረጅም ጊዜ እየተከበረ የኖረ
ሃይማኖታዊ በዓል እንደሆነ ይታመናል፡፡
የሻደይ ልጃገረዶች የቡድን አመሠራረት ደብርን መሠረት
ያደረገ ነው፡፡ የሻደይ ጨዋታ በዓል በሚያከብሩበት ጊዜ
ልጃገረዶች የተለያዩ ባህላዊ አልባሳትን ለብሰው ከበሮ
እና ለምስጋናው የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማሟላት
ተጠራርተው በመጀመሪያ ወደ አጥቢያቸው በመሄድ የቤተ
ክርስቲያኑን ደጁን አልፈው ይዘልቃሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያኑን
ደጅ ከተሳለሙ በኋላ የተለያዩ ጣዕመ ዝማሬ እያሰሙ
ሦስት ጊዜ ይዞሩና ደጃፉን ተሳልመው በቅጥር ግቢው
አመቺ ቦታ ፈልገው ምስጋናቸውን ይጀምራሉ፡፡
ከበሮአቸውን እየመቱ፣ የታቦቱን ስም እየጠሩ በሚያምር
ድምፃቸው፣ ሽብሻቦ፣ ውዝዋዜ፣ ጥልቅ መልእክትን በያዙ
ግጥሞች፣ ለዚህ ያደረሳቸውን አምላክና ታቦት ያወድሳሉ፣
ያሞግሳሉ፣ ያከብራሉ፣ ይለማመናሉ፡፡ ምስጋናው ለዚህ
ዓመት ያደረሳቸውን አምላክ የሚያመስግኑበት እና ቀጣዩ
ዓመትም እንደዚሁ የሰላም፣ የጤና የተድላ እንዲሆን
የሚማጸኑበት፣ ተስፋቸውን የሚገልጹበትና ስለት
የሚሳሉበት በመሆኑ ምስጋናውን ሞቅ፣ ደመቅ አድርገው
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በፍቅር፣ በደስታ፣ በመተሳሰብና
በሰላም ይጫወታሉ፡፡ እያንዳንዱ አባል ለእግዚአብሔርና
ለደብራቸን ታቦት ያልሆነ እያሉ ጉልበታቸውን፣ ችሎታውንና
ልምዳቸውን ሳይቆጥቡ በምስጋናው ይሳተፋሉ።
ከቤተ ክርስቲያን መልስ በአካባቢው ወዳሉት ትልልቅ
አባቶች ዘንድ ሄደው በመዘመር ምርቃን ይቀበላሉ። ከዚያ
መልስ ወደ ተራራማ ስፍራ በመውጣት ክብ ሠርተው
ይዘምራሉ፡፡ ከዝማሬያቸው ውስጥ ግጥሞቹ መንፈሳዊ
ይዘት ያላቸው ግጥሞች ከግለሰባ6 ስሜት ወይም
ከግለሰብ ውዳሴ የራቁ ናቸው፡፡ የቡድን አመሠራረታቸው
ደብርን መሠረት ያደረገ በመሆኑ አንዱ ቡድን ከሌላው
ቡድን የተሻለ መሆኑን ለማሳየት ፣ የደብሩን ኃያልነት፣
ደብራቸውን እንደማያስደፍሩና እንደሚጠብቁ
በምስጋናቸው ይገልጻሉ፡፡

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ዘውግ ጣፋጭ ወግ
ፀሀፊ እና ተራኪ ሙለር

ግብዣችን ነው ተጋበዙልን

@wegoch
@wegoch
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆ርዕስ ~ ፍቅፋቂ
ፀሃፊዋ ~ ሕይወት እምሻው
አቅራቢ(ተራኪ) ~ ሚኪያስ ልየው @Mykey21
🖤ምን ብላቹ እደምትፈርዱት አላውቅም እኔን
🖤አቁስሎኛል🖤

🖤መስከረም 2005 አዲስ ጉዳይ ነገሩን
እንዲህ ያስነብበናል

የ12 ዓመቷ ታዳጊ ዘውትር በእጇ ቅጠላ ቅጠልና የተለያዩ ዕቃዎች ይዛ በዚህ መንገድ
ታልፋለች:: በአካባቢው ወዳለው የቀበና ወንዝ በመውረድ መጫወት ያስደስታታል:: እናቷ ግን አይለቋትም:: ቢሆንም እሳቸውን ተደብቃ መሔዷን አላቋረጠችም:: የአዕምሮ
ህመምተኛ ናት:: ይህቺን ልጅ አይቶ የማያዝንላት ሰው የለም:: ቀይ ቆንጆና የደስደስ ያላት ታዳጊ ናት:: የምታወራውን ነገር አታውቀውም:: እናቷ ዘውትር እያዩዎት ያለቅሱ የነበር ቢሆንም አሁን አሁን የሆነውን በፀጋ ከመቀበል ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው በመገንዘባቸው ዝምታን መርጠዋል

ብዙ ፀበል ሞክረው አልተሳካላቸውም።

ይቺን ህፃን የሚወዳት የዚህ ሰፈር ወጣት አለ ቀበና ሰፈር 24 ዓመቱ ነው:: ዘውትር ከረሜላ ይገ
ዛላታል:: እሷም ትወደዋለች:: ያጫውታታል::ሣን ቲም ይሠጣታል:: ብዙ ጊዜ ከአይኑ እንድትጠፋ አ
አይፈልግም:: አንድ ቀን ከመንገድ ሲመለስ ወንዝ አካባቢ ጫወታ ላይ ሳለች ከረሜላ እንደሚገዛላት
ነግሮ ይዟት ወደ ቤቱ መጣ:: በዚህ ወቅት ግን የለመደችውን ከረሜላ አልገዛላትም:: የገባውን ቃ ል አላከበረም:: ይልቅስ መጥፎ መጥፎ ድርጊት ተፈጠረ::

አልጋው ላይ ካስወጣት በኇላ ልብሶቿን አስወልቆ ደፈራት:: ክብረ ንፅህናዋ ተገሰሰ:: አሟታልና ጮኸች:: ከዚያን በኋላ ግን ከኪሱ ከረሜላ አውጥቶ ሲሰጣት ረሳችው:: ከቤቱ አውጥቶ ወደ ቤቷ ሰደዳት::

ከአንድ ሰዓት በኋላ ቤቱ በሀይል ተደበደበ:: ደነገጠ:: ወጣቶች ናቸው:: አንገቱን ይዘው አወጡት:: ፖሊስ ነበር:: ይዘውት ሄዱ:: የፈፀመውን ድርጊት አመነ:: ታዳጊዋ ቀሚሷ ላይ ደም ስለታየ እናቷ ምን እንደሆነች ጠይቀዋት ይህ ግለሠብ ያደረጋትን ነግራቸው ስለ ነበር ነው ለጎረቤት ሁኔታውን አሳውቀው ፖሊስ ጣቢያ የሄዱት:: ይህ ጨዋ መሳይ ወጣት ለፍትወቱ ጥማት ሲል ህፃን ለዚያውም የአዕምሮ ህመምተኛዋን በመድፈሩ : ይህም በራሱና በማስረጃ በመረጋገጡ ፍርድ ቤት የ12 ዓመት ፅኑ እስራት አከናንቦ ዘብጥያ ልኮታል:: ዕውን የአዕምሮ ህመምተኛው ከህፃኗና ከርሱ ማነው?

🌑ይህን ይመስላል ያስነበበን. . .

🗝 አስራ ሁለት ዓመት ዘና ብሎ የእስር ቤት
እንጀራ በልቶ ይወጣል. . . ጉድ ነው እኮ. . . . . ..

🗝 ይህ ጉዳይ ዛሬም እየሆነ ነው . . .አሁንም
እየተደረገ ነው . . . የዘጠኝ ወር ጨቅላ ደፍሮ
እስር ቤት ጎብኝቶ ይወጣል . . . . . . . እነዚህ
ን ሰዎች ከስራቸው እንቀላቸው . . . ዳግም . .
እዳይበቅሉ እናጥፋቸው . . ለዚህ ደሞ ህጉ
መሻሻል አለበት . . . ከሞት በላይ ይገባቸዋል
ይህ ሀገርን ከመክዳት በላይ ነው . . .. . .

እናንተ በዚሂ ዙርያ ስላለው የህግ መላላት ምን
ትላላቹ ? ? ? እንዴት ነው ዝም ምንለው ? ? ?
እንዴት ነው እነዚህ ሰይጣን እንኳን የፈራቸው
ቆሻሾች የእስርቤት እንጀራ በልተው እየተጋደሙ
ሚኖሩት ? ? ?

💥ይህ በፍፁም አይሆንም !? እራሳችንን ነፃ እና
ውጣ . . ተነሱ አንድም ደፋሪ ኢትዮጵያ ምድር
ላይ እዳይኖር ሆ ብለን እንነሳ. . . . . . . . .

💥እነዚህን ጭራቆች እስር በቂያቸው አይደለም
ብሎ ያመነ @tizta4 ያዋራኝ ! ! ! እና ስራ
እንስራ!!!

💥ሴት ነን ክፋትን ፀብን አንሻም በማንነታችንና
በክብራችን ለመጣ ግን አናፈገፍግም . . . . . .

💥መንግስት ፊት እንቁም የፖሊሲ መሻሻል
እስኪመጣ . . ከያለንበት እንጭው . . . . . .
ይህ የኔም ፣ ያንቺም ፣ ያንተም ፣ የእናንተው ጉዳ
ይ ነው . . . ስለሌላው ይሰማን . . .

🖤 ለሌላው በማዳረስ ሀላፊነቶን
ይወጡ . . . .

🔥 ከሞት በላይ ይገባቸዋል . . . .

እናንተም በዚ ጉዳይ ሀሳባቹን ብታካፍሉኝ እና የበኩላቹን ድርሻ ብትወጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

@tizta4
@wegoch
@wegoch
👆👆👆👆 ሀሳባቹን አስተያየታቹን እያካፈላቹን ላላቹ እጅግ በጣም እናመሰግናለን ግን ደሞ በጣም ያስገረመኝም ፣ ያሳዘነኝም ነገር አለ ሴቶች እየተሳተፋቹ አይደለም ከማንም በላይ ጉዳዩ ሚመለከተው እናንተን ነው...እኔ ላይ ካልደረሰ ምን አገባኝ የሚሉት ፈሊጥ ጥሩ አይመስለኝም ይቆይ እንጂ የሁሉንም ቤት ሟንኳኳቱ ማይቀር ነው......እናም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጉዳዩ ተጠቂ ሴቶች እንደመሆናቸው ብትሳተፉ ሸጋ ነው
👇👇👇👇

@tizta4
@wegoch
@wegoch
ምን አፋሽ?.(ልዑል ሀይሌ)
ከጀግንነቴ የተነሳ በረሮ ገድዬ ሁሉ ፎክር ፎክር!...ሸልል! ሸልል! ይለኛል። ነገር ግን ጀግንነቴን የማውጀውም የማውቀውና የምረዳው እኔ ብቻ ነኝ!!...ዕድሌ ሆኖ ነው መሰለኝ...ስንት ጦር ሜዳ ዘምቼ ስንቱን አንበርክኬ ስንቱን ገድዬ ስመለስ..የገደልኩት ሰው ታሞ እያጣጣረ እንደነበርና በህመም ምክንያት ነው የሞተው ብለው እያወሩ
ጀግንነቴን በከንቱ ሊያልፉት ይዳዳቸዋል። ደስ ሚለው ግን እኔ የራሴን ጀግንነት ላፍታ ዘንግቼ አለማወቄና ራሴን አለመካዴ ነው። ለሰው "አመድ አፋሽ" መሆኔን ባውቀውም እኔ ለእኔ ግን "ወርቅ
አፋሽ!..አልማዝ አፋሽ!..ኒሻን አፋሽ!...ብቻ በአጠቃላይ ጥሩ ጥሩ ነገር ውድ ውድ ነገር አፋሽ!"ነኝ።.....እኔ ለእኔ አለሁ እንጂ የሰው ነገርማ ተዉት....እኔ ጀግንነቴን ላሳይ ጠላትን እጅ እጁን ነስቼ ከጦር ሜዳ ስመለስ ሰው ሁሉ ወንጌል እያነሳ መግደል ጀግንነት መግደል ሳይሆን
ለፍቅር ብሎ መሞት ነው እያለ ምዕራፍ እየጠቀሰ ይነግረኛል። ለነሱ ጊዜ ቢንቢም ገድለው ሰው የሚቀበላቸው የጀግንነት አርማ እያነሳ ነው። ለኔ ጊዜ ጀግንነቴን ላለማወጅ ወንጌል የሚያነሳብኝ ምን ልሁን ብሎ ነው?....(ይስቀጥል?..አይስቀጥል?)

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
i hope u all are doin gr8 out there,so we finally post our 1st poster as Axum,our beautiful ancient city.Plz spread to all arch students to remind them our history and be part of us nd compete.Only if they dare they re creative.

Forward the pic with caption,lets create a chain and knw hw many ppl will be part of us.

Register @SeWa_dear


👇👇👇👇

@inluvwidart
@inluvwidart
መብራት ሃይል የ"ቴሌን" ቅናሽ ሲሰማ የጋበዘን ዘፈን


''እኛ ከሌለን ባዶ እኛ ከሌለን ባዶ''
😂😂😂😂😂😂😂😂

@Wegoch
@Getem
@Mykeypictures
ስልጣኔ ራስን መግለጥ ነው፥ የራስን ትውፊት ዘመን መጣኝ በማድረግ ስልጡን ባህል
መመስረት ነው። ራስን ያልሆነ የተውሶ ባህል ማደሪያ እንጂ መኖሪያ አይሆንም።
ስልጡን ህዝብ የስሪት መደላድሉን አይንድም። የኛን ሳዱላ ልጆች በዚህ ሰኣት እንዲህ
በእንቡጥ አሽንዳ ወገባቸውን ታቅፈው ሶለል ሲሉ ስታያቸው ሩህህ ይላወሳል፥ ውበትና
ደርባባነት ምንጩ የት እንደሆነ ይገባሃል።
ሶለል ሰላምታ ነው፥ ሶለል ዝምድናን ማስቀጠያ ጥላቻን መስበሪያ የህብረተሰብና ቤተሰብ
ማቀራራቢያ ሰንሰል ነው። ሶለል ልትል የወጣች ታድጊ ሳዱላ "ከነ እንትና ቤት አልሄድም"
አትልም፥ "ጸበኞች ነን" አትልም። ወላጆችም "እነ እንትና ቤት አትሄጅም" ሲሉ ትእዛዝ
አይቆርጡም። ሶለል ሰላም ነው።
ሶለል የልጃገረዶች የብቻ ጨዋታና የነጻነት ቀን ነው። በጥባጭና ጎንታይ የሌለብት
በባህላዊ ህግ የተቆነነ የልጃገረዶች ብቻ የሳቅ ቀን ነው።
ይሄን ባህል ማሳደግና ማዘመን የሁሉም ህብረተሰብ ድርሻ ቢሆንም፥ የሙህራኑና
የፖለቲከኛው ሚና ግን ላቅ ያለ ነው። ባህሉ የሚሰራውና የሚንከባከበው ተቋም ይሻል፥
ምርምር ይፈልጋል። ባህል ያድጋል ሲባል ፈሩን ሳይለቆ ትውልድን ሁሉ እንዲመጥን ሆኖ
ይሰራ ዘንድ መሪ ይሻል ማለት ነው።
# ራያ_ቆቦ ሸጋ ጅምር ጀምሯል!! ይበል ያሰኛል!!!!


ሸጋ ጁምኣ!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ከ Black Panter ተቀንጭቦ በአማርኛ የተተሠጎመ 😊😊




😂😂😂😂
ወላጅ አባቷ አቶ አስገዶም አርአያ ትውስ አሏት። ገና ታዳጊ ወጣት እያለች በአንድ ወቅት እንደዋዛ እንዲህ አወጓት። ልጄ ውብ ነሽ ይህ ዉበት ግን ዘላለማዊ አይደለም ።ዘላለም ከአንቺ ጋር ሊኖር የሚችል ነገር ዕውቀት ነው።እሱንም አንብቦ ማስፋት ፣ መኮትኮት ማረም ያሻዋል። አንቺም እንደምታውቂበት ዕምነቴ ነው። በሕይወትሽ የሚከሰቱ ቆንጆ ወዳድ ወንዶች ይኖራሉ። በውበትሽ ተሸንፎ አይንሽ ጥርስሽን እያለ ሊያሞካሽሽ ከሞከረ <<ወራጅ ! በይው !>> ያሏትን አስታውሳ አሁንም ፈገግ አለች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጓደኞቿ መካከል ገነት ባለችበት የውበት ነገር ከተነሳ <<ወራጅ!>> መለያዋ ሆነ።

📝📝 ደራሲ ዘነበ ወላ
📘📘 መልህቅ 189 ገፅ

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
🖤ምን ብላቹ እደምትፈርዱት አላውቅም እኔን
🖤አቁስሎኛል🖤

🖤መስከረም 2005 አዲስ ጉዳይ ነገሩን
እንዲህ ያስነብበናል

የ12 ዓመቷ ታዳጊ ዘውትር በእጇ ቅጠላ ቅጠልና የተለያዩ ዕቃዎች ይዛ በዚህ መንገድ
ታልፋለች:: በአካባቢው ወዳለው የቀበና ወንዝ በመውረድ መጫወት ያስደስታታል:: እናቷ ግን አይለቋትም:: ቢሆንም እሳቸውን ተደብቃ መሔዷን አላቋረጠችም:: የአዕምሮ
ህመምተኛ ናት:: ይህቺን ልጅ አይቶ የማያዝንላት ሰው የለም:: ቀይ ቆንጆና የደስደስ ያላት ታዳጊ ናት:: የምታወራውን ነገር አታውቀውም:: እናቷ ዘውትር እያዩዎት ያለቅሱ የነበር ቢሆንም አሁን አሁን የሆነውን በፀጋ ከመቀበል ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው በመገንዘባቸው ዝምታን መርጠዋል

ብዙ ፀበል ሞክረው አልተሳካላቸውም።

ይቺን ህፃን የሚወዳት የዚህ ሰፈር ወጣት አለ ቀበና ሰፈር 24 ዓመቱ ነው:: ዘውትር ከረሜላ ይገ
ዛላታል:: እሷም ትወደዋለች:: ያጫውታታል::ሣን ቲም ይሠጣታል:: ብዙ ጊዜ ከአይኑ እንድትጠፋ አ
አይፈልግም:: አንድ ቀን ከመንገድ ሲመለስ ወንዝ አካባቢ ጫወታ ላይ ሳለች ከረሜላ እንደሚገዛላት
ነግሮ ይዟት ወደ ቤቱ መጣ:: በዚህ ወቅት ግን የለመደችውን ከረሜላ አልገዛላትም:: የገባውን ቃ ል አላከበረም:: ይልቅስ መጥፎ መጥፎ ድርጊት ተፈጠረ::

አልጋው ላይ ካስወጣት በኇላ ልብሶቿን አስወልቆ ደፈራት:: ክብረ ንፅህናዋ ተገሰሰ:: አሟታልና ጮኸች:: ከዚያን በኋላ ግን ከኪሱ ከረሜላ አውጥቶ ሲሰጣት ረሳችው:: ከቤቱ አውጥቶ ወደ ቤቷ ሰደዳት::

ከአንድ ሰዓት በኋላ ቤቱ በሀይል ተደበደበ:: ደነገጠ:: ወጣቶች ናቸው:: አንገቱን ይዘው አወጡት:: ፖሊስ ነበር:: ይዘውት ሄዱ:: የፈፀመውን ድርጊት አመነ:: ታዳጊዋ ቀሚሷ ላይ ደም ስለታየ እናቷ ምን እንደሆነች ጠይቀዋት ይህ ግለሠብ ያደረጋትን ነግራቸው ስለ ነበር ነው ለጎረቤት ሁኔታውን አሳውቀው ፖሊስ ጣቢያ የሄዱት:: ይህ ጨዋ መሳይ ወጣት ለፍትወቱ ጥማት ሲል ህፃን ለዚያውም የአዕምሮ ህመምተኛዋን በመድፈሩ : ይህም በራሱና በማስረጃ በመረጋገጡ ፍርድ ቤት የ12 ዓመት ፅኑ እስራት አከናንቦ ዘብጥያ ልኮታል:: ዕውን የአዕምሮ ህመምተኛው ከህፃኗና ከርሱ ማነው?

🌑ይህን ይመስላል ያስነበበን. . .

🗝 አስራ ሁለት ዓመት ዘና ብሎ የእስር ቤት
እንጀራ በልቶ ይወጣል. . . ጉድ ነው እኮ. . . . . ..

🗝 ይህ ጉዳይ ዛሬም እየሆነ ነው . . .አሁንም
እየተደረገ ነው . . . የዘጠኝ ወር ጨቅላ ደፍሮ
እስር ቤት ጎብኝቶ ይወጣል . . . . . . . እነዚህ
ን ሰዎች ከስራቸው እንቀላቸው . . . ዳግም . .
እዳይበቅሉ እናጥፋቸው . . ለዚህ ደሞ ህጉ
መሻሻል አለበት . . . ከሞት በላይ ይገባቸዋል
ይህ ሀገርን ከመክዳት በላይ ነው . . .. . .

እናንተ በዚሂ ዙርያ ስላለው የህግ መላላት ምን
ትላላቹ ? ? ? እንዴት ነው ዝም ምንለው ? ? ?
እንዴት ነው እነዚህ ሰይጣን እንኳን የፈራቸው
ቆሻሾች የእስርቤት እንጀራ በልተው እየተጋደሙ
ሚኖሩት ? ? ?

💥ይህ በፍፁም አይሆንም !? እራሳችንን ነፃ እና
ውጣ . . ተነሱ አንድም ደፋሪ ኢትዮጵያ ምድር
ላይ እዳይኖር ሆ ብለን እንነሳ. . . . . . . . .

💥እነዚህን ጭራቆች እስር በቂያቸው አይደለም
ብሎ ያመነ @tizta4 ያዋራኝ ! ! ! እና ስራ
እንስራ!!!

💥ሴት ነን ክፋትን ፀብን አንሻም በማንነታችንና
በክብራችን ለመጣ ግን አናፈገፍግም . . . . . .

💥መንግስት ፊት እንቁም የፖሊሲ መሻሻል
እስኪመጣ . . ከያለንበት እንጭው . . . . . .
ይህ የኔም ፣ ያንቺም ፣ ያንተም ፣ የእናንተው ጉዳ
ይ ነው . . . ስለሌላው ይሰማን . . .

🖤 ለሌላው በማዳረስ ሀላፊነቶን
ይወጡ . . . .

🔥 ከሞት በላይ ይገባቸዋል . . . .

እናንተም በዚ ጉዳይ ሀሳባቹን ብታካፍሉኝ እና የበኩላቹን ድርሻ ብትወጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

@tizta4
@wegoch
@wegoch
ወንዶች የሴት ጠላት አይደሉም ወንድም፣አባትም
ጓደኛም ናቸው . . . .

የሴትም የወንድም ጠላት ሴቶችን
የሚያጠቃ ብቻ ነው. . . .

አላማችን አንድና አንድ ይሁን አንድም ደፋሪ
ደረቱን ነፋቶ የሚራመድበት ዘመን እዲያከትም
መስጠት ያለብንን ነገር ሁላ እንስጥ . . .. .

ህጉ ህግ ይሁንና ደና አርጎ ይቅጣልን . .
ህጉ ይሻሻልልን !!!! ከሞት በላይ ይገባቸዋል!
🦋የሞት ፍርድ አላልኩም . . ከሞት በላይ . .
ይገባቸዋል።

ሁላችንም የመጀመርያው ስራችን ሰዎችን
ለዚህ ዓላማ ማነሳሳት ይሁን. . ይሄ ጉዳይ
የኔም ፣ ያንቺም ፣ ያንተም ፣ የእናንተም ፣ የእነርሱ
ም ጉዳይ ነው . . . ስራችንን ሌላው ላይ ተፅእ
ኖ በመፍጠር እንጀምር . . . .
የመጀመርያ ስራችን ይሄ ነው . . .

ይሄ ነገር ሁላችንንም ስለሚመለከት ለዚ አላማ የተቋቋመ ግሩፑ ስላለ ተቀላቀሉንና የድርሻቹን ተወጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

T
https://www.tg-me.com/joinchat-Fez2QQ3l-ZPm5NQqlHEEWQ

🙏🙏🙏አመሰግናለው

@tizta4
@tizta4
@wegoch
@wegoch
2024/09/30 09:22:15
Back to Top
HTML Embed Code: