Telegram Web Link
“ስንደመር” የኪነ ጥበብ ምሽት ነገ
ይካሄዳል!!!


በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት የሚቀርበው “ስንደመር” የተሰኘ የኪነ ጥበብ ምሽት ነገ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡ በዕለቱ ወግ፣ ዲስኩር፣ መነባንብና ሌሎች የወቅቱን
የአንድነትና የመደመር መንፈስ የሚያንፀባርቁ ኪነ ጥበባዊ ድግሶች እንደሚቀርቡ የምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ምስክር ጌታነው ገልጿል፡፡ አርቲስት ፈቃዱ ከበደ ወግ የሚያቀርብ ሲሆn ዲስኩር ደግሞ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ረ ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ የሙዚቃ ባለሙያውና የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ም/ዋና ዳይሬክተር ሰርፀ ፍሬስብሃት ያቀርባሉ፡፡ በአርቲስት ሽመልስ አበራ ደግሞ “ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” በመሶብ ባህላዊ ባንድ ፉከራና ሽለላ ታጅቦ እንደሚቀርብም ታውቋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ለመታደም 100 ብር የመግቢያ ዋጋ የሚከፈል ሲሆን በአሁን ሰዓት ትኬቶቹ በጃፋር መፅሐፍ መደብር፣ በዮናስ መፅሐፍ መደብር፣ በዓይናለም መፅሐፍት መደብር፣ በሳሚ ካፌና ሬስቶራንት እንዲሁም አራት ኪሎ በሚገኘው ምርፋቅ ካፌና ሬስቶራንት ማግኘት እንደሚቻል ታውቋል፡፡

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
መወሻሸት ይሉሀል!
【ናትናኤል ጌቱ 】
አፍቃሬ ደርጎች ( የደርግ አፍቃሪዎች) የኮለኔል መንግስቱን ጥፋት ለማቃለል የሚያነሱት ሀሳብ የሚገርም ነው ። አንዳ ንዶቹ «ደርግኮ በአደባባይ ነው የሚገድለው» በማለት ይሟገታሉ ። በአደባባይ የተገደሉ ሰዎች ከሳምንት በኋላ ከሞት ይነሳሉ ማለት ነው ? - ሌሎቹ ደግሞ ስለ ደርግ ሲወራ ስለ መለስ የሚያወሩ ናቸው ። ከሰይጣን እና ከሰይጣን ማን ይበልጣል አይነት ሙግት ሊያነሱ ይፈልጋሉ ። እውነቱን ለመናገር ኮለኔሉ ከመለስ ጋር እንኳን የሚወዳደር ሰው አይደለም ። በቀሽም ወታደርና በመሰሪ መሪ መሀል ትልቅ ልዩነት አለ ።
- አንዳንድ ፀሀፊዎች ደግሞ ኮለኔሉ ወደ ዙምባብዌ አለመሸሹን ይልቁንም ሳያስበው ወደዛ እንደተወሰደ ይፅፋሉ ። አልሸሸም ለማለት ነው ። እኔ 'ምለው ሳይፈልግና ሳያስበው ከሆነ የሄደው… ለምን አልተመለሰም? ለምን ተመልሶ መጥቶ እጁን አልሰጠም? … ምክንያቱም እንደሚገደል ያውቃል !! የሸሸውም ሞትን ፍራቻ ነበር ። መሞትና መግደል ብዙ ልዩነት አላቸው ! ስንቱን የጨፈጨፈው ሂትለር ምሽግ ውስጥ ሲኮራመት የነበረው ሞትን ፍራቻ ነው። ምክንያቱም መሞት ያስፈራል ። መግደል ነው የማያስፈራው ! - የደርግ ስርአት ደጋፊዎች በወቅቱ ተጠቃሚ የሆነ ቤተሰብም ነበራቸው ። ባንድ ወቅት ድርቅ ብላ የደርግን መልካምነት ስትሰብከኝ የነበረች ሴት ባሏ ጄኔራል እንደነበር ሹክ ብትለኝ ተገርሜያለሁ ።
ገዳይና ተገዳይ ስሜታቸው ይለያያል !
- ባጠቃላይ ኮለኔሉ ሀገር ውስጥ ቢመጣ ደስ ይለኛል… ወደ ሀገሩ መጥቶ ቅጣቱን ቢቀበልና መቀጣጫ ቢሆን ጥሩ ነው!


@wegoch
@wegoch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
።።።።ልዑል ሀይሌ።።።

ህይወትን በቀለም ግለፃት ብትባል የትኛውን ቀለም ትመርጣለህ?? ህይወትን በፊደል ግለፃት ብትባል የትኛውን ፊደል ትመርጣለህ?? ህይወትን በቁጥር ግለፃት ብትባል የትኛውን ቁጥር ትመርጣለህ??...ህይወት በቀለምም በፊደልም በቁጥርም በምትገልፃት በላይ ባንተ ጉዞ እና እርምጃ ትተረጎማለች ጉዞህ የተቃና ከሆነ ባንተ መዝገበ ቃላት ውስጥ የህይወት ትርጉም አስደሳች
ትሆናለች። ጉዞህ ሁሉ እሾህ የበዛበት ከሆነ ደግሞ ህይወት የስቃይ መንደር መሆኗን በመዝገበ ቃላትህ ውስጥ ታሰፍራለህ። ነገር ግን ምንም እንኳ በእያንዳንዳችን መዝገበ ቃላት ውስጥ ህይወት የተለያየ ትርጉም ቢኖራትም ነገን ለማየት ባለን ጉጉት እና የተሻለ ዕድል እንደሚኖር በማሰብ ትርጉሟን ሚዛናዊ እናደርጋለን!!...ለተሻለ
አጋጣሚ የሚሰጠን ነገ ይጨመርልን ዘንድ ፈጣሪ ፍቃዱ ይሁን አሜን!!

@lula_al_greeko
@getem
@getem
፡፡፡፡ ዳዊት ብርሀኑ ፡፡፡፡
1. እንደምናውቀው ሀገሩን ሁሉ ኮከብ አልባ ባንዲራ እንደ ድንኳን ቢያለብሱ ዘረኝነት እንደዛር ሦስቴ ጮኾ አይወጣም። ታድያ ቆሞ ከማየትና ለዋጋቢስ ሐሳቦች ርካሽ ስድብ ከማስታጠቅ ሌላ ምን ላድርግ you ask? ጥሩ!
.
ዘረኛ ተብዬዎች ስላመኑትና ነው ስላሉት ነገር ሁሉ ከፎቶ እስከ ታሪክ ማስረጃ ሲያቀርቡ፣ ለርካሽ ሐሳቦቻቸው ውድ ምስክር ሲመዙ አንተ "ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!" ፣ "ቅድስት ሀገር -ኢትዮጵያ!" ከማለት ሌላ ወደክርክሩ ምን አመጣህ?
.
አየህ በሐሳብ ጥፊ ግራ ጉንጭህን ሲያጮሉህ ግራ ቆለጣቸውን የሚያፈርጥ የሐሳብ ካልቾ መሰንዘር አለብህ። አልያ ጥፊህን ተቀብለህ፣ ተሳድበህ የምትሄድ ከሆነ ተሸናፊ በመሆንህ ብቻ ችግሩን እንዳፈረጠምከው እወቀው።
.
2. ሰውን ሁሉ እንዳሻው፣ ሞልፋጣ ሐሳቡን የትም እንዲለድፍ መብት የሰጠው አንድ ነገር ቢኖር ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሚሉት በረከተ-መርገም ነው። ግን እውነትም እንዳሻን መናገርና ማሰብ መብት ነው ወይ?
.
አንዳንዴ ሐሳባችን ዘመንና ጊዜያችንን እስኪመስል ድረስ በአደባባይ መናገር መ'ከልከል ያለብን ሰዎች አለን። ለምን?
.
ሁሉም ሐሳቦች እኩል ዋጋ (value) የላቸውም። ለማሰብ የማይደከምባቸው፣ ከአደባባይ የሚሸመጠጡ፣ አግላይና አጥፊ ሐሳቦች ወደጠረጴዛ መጥተው ልንወያይባቸው ይገባል? Sure! ግን ደግሞ ለውይይት ሳይደርሱ፣ ለንግግር ሳናቀርባቸው፣ በሌሎች ሐሳቦች ሳይፈተኑ እንደመመሪያና የኑሮና ፖለቲካ መዘውር ለሕዝብ መድረስ አለባቸው ወይ?
.
ማን ያውቃል ዛሬ አብረን ያላሸናቸው፣ ተሰባስበን ያልፈተንናቸው ሐሳብና ርዕዮቶች የፖለቲካ አልያም የኢኮኖሚ የበላይነት ማግኛ ምክንያቶች የሚሆኑበት ቀን ይመጣ ይሆናል። ያኔ "ምነው በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣናቸው!" ማለት አይቀርም።
.
3. ሰዎች ሐሳባቸው ዋጋቢስና lopsided ነው ብለን እንዳያስቡ ብሎም እንዳይናገሩ ማድረግ አንችልም፤ ብንችልም አናደርግም። የጨዋ ወጉ የሆነው ነገር የሐሳብ ሚዛኑን ወደድድብና የደፋ ሚዛን ስናገኝ ወደምክንያታዊነት ለመመለስ፣ 'ሚዛን የሚደፋ' ሐሳብና ሐቅ ማቅረብ ነው።
.
ለምሳሌ ተ.ቁ 1 ላይ እንደተጠቀሰው "ምንሊክ በጨለንቆ ጦርነት 50,000 ሰው እንደጨፈጨፈ አቶ ዲዮስቶቭስኪ የተባለ ጉምቱ የሩሲያ ጸሐፊ ጽፏል" ብለው በሩሲያኛ የተጻፈ ቡላ ከለር ድርሳን ሲገለጥልህ "ምንሊክ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ አባት ናቸው። ባቡርና ስልክን እዚህ ሀገር ያስገቡት እርሳቸው ናቸው።" ብለህ የምትመልስ ከሆነ may be you should have been dead already!
.
4. ሰሞኑን በአዲስ ጎዳናዎች ላይ "የአርበኞች ግንቦት 7 ጀግኖቻችንን ለመቀበል እንዘጋጅ! (በቅርብ ቀን!)" የሚል ተንጠልጣይ ማስታወቂያ 'የውስጥ አርበኞች' ሰቅለው አየሁ።
.
ወንድሜ አሥር ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ኤርትራ ላይ ተቀምጠህ፣ ፑሽ አፕ እየሠራህ በከረን ቆንጆዎች ስትማልል ከርመህ፣ ለዜና ድምቀት ራሱ የሚሆን አንድ ወታደር ሳትገድል፣ በመቀሌ front ስንጠብቅህ በቦሌ airport ተከስተህ ስታበቃ ጀግና ነኝ አለ እንዴ? አንተ የኖርከው ኑሮ ስም አለው - ቫኬሽን ይባላል።
.
ጃል ኢ-ፍትሐዊነትን መቃወም፣ (ምናልባትም የሞቀ) ቤትህን ትተህ በሰው ሀገር በረሐ መንከራተትህ ለማንም ጀግና ያስብልህ ይሆናል (ያስብልሃልም)። ግን ምን ይደረግ? ቀድሞም የግንቦት ሰባት ድሮም የትጥቅ ትግል (ጦርነት) ደጋፊ አይደለሁም።
.
5. ተ.ቁ. 1 እና 3 ላይ ያልኩህ ጥብስቅ አድርጎ እንዲገባህ የጋሼ አሰፋ ጫቦን "የትዝታ ፈለግ"ን አንብብ።
.
#ሰላም

@tekuye17
@wegoch
Forwarded from SPACE COMPUTER
የግጥም ምሽት

ነገን አናስተምር በሚል መሪ ቃል
ወጣትና አንጋፋ ገጣሚያን ከሞሰብ ባንድ ጋር
ለአመታዊ የትምህርት መሳርያ ገቢ ማሰባሰብያ የተዘጋጀ የጥበብ ፕሮግራም።

በናህሴ 29 ከ 11:00 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል።
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
"መናጢ ያነጠው"
--++++++
የልጆች ድርጊት ወቅትን ይናገራል!! አሁን አሁን ኮንጎ፣ ደቡብ ሱዳን አልያም ኒጀር ያለሁ
አፍሪካዊ ነኝ እንዴ? ማለት ጀምሪያለሁ!!
እነዚህ ልጆች ወደ ዲሞክራሲ በስንት አመታቸው ይደርሱ ይሆን? በሰላማዊ የስልጣን
ርክክብና የምርጫ ሂደት ጨዋታቸውን ሳያደርጉ ልጅነታቸው ይጠነዝል ይሆን? ልጅኮ ከሳለ
አያጠፋም ወገኑ!!
በለቅሶ ፍላጎቱን የሚያሳካ ልጅ ኮ በምክክር የልቡ አይደርስም። በጉልበት ሃሳቡን ማሳመን
የለመደ ልጅ በውይይት አንጀቱ አይርስም!! "የልጅ ነገር" አትበሉ፥ ልጅ የነገሩትንና
የመሩትን፣ ያጫወቱትን ነው!!
------
"የልጅ መናጢ" አትበሉ፥ ይልቁን "መናጢ አናጢ" የልጆችን እሳቤና አእምሯዊ ውቅርና
ህልም እንዲህ ያጣምማል በሉ።

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
"ዕቁብ ልሰበስብ ነው!"
"ስንት ሰው?"
"እኔና አንተ ብቻ! መጀመሪያውን እኔ እበላለሁ... "
"ብድር ነው ዕቁብ?"

በረከት በላይነህ
@wegoch
@wegoch
ገበያ ሲያመች (በዳንኤል ክብረት)

ገበያ ሲያመች የማይሰራ ኢሞራላዊ ስራ የለም ገበያ ሲመች ሀገር ይሸጣል ህሊና ይሸጣል መሬት ይሸጣል ቅርስ ይሸጣል ስም ይሸጣል ባህል ይሸጣል ፍትህ ይሸጣል እናት ይሽጣል አባት ይሸጣል ልጅ ይሸጣል አካል ይሸጣል ሞያ ይሸጣል ሰርተፍኬት ይሸጣል ክህነት ይሸጣል እምነት ይሸጣል ምን የማይሸጥ
ነገር አለ። አንዳንዶች ለመኖር ኅሊናን መሸጥ የሚያዋጣ ከመሰላቸው ከመሸጥ ወደ ኅላ አይሉም። ገበያ ካመቸ
ኅሊናን ይሸጡታል። መመዘኛቸው ትክክል ነው አይደለም ሞራላዊ ነው አይደለም እውነት ነው አይደለም ህጋዊ ነው አይደለም የሚለውን ሳይሆን ያዋጣል ወይስ አያዋጣም የሚለውን ብቻ ነው። እንደዚ አይነት ሰዎች የሚሞቱለት አቋም ሀሳብ ርዮት አለም መስመር እምነት ማንነት ራእይ የለቸውም እንኳንስ ሀሳባቸውን እና አቋማቸውን የሚያዋጣ ሆኖ ካገኙት የትውልድ ቦታቸውን ብሔረሰባቸውን እና ወላጆቻቸውን ጭምር ለመቀየር ዝግጅ ናቸው። ትናት አዋቷቸው ጎጃም ተወልደው እንደሆነ የዛሬውን ገበያ አይተው ጎንደር ሊወለዱ ይችላላሉ። ጎንደር መወለዳቸዉ የረከሰ ከመሰላቸውም ትግራይ ወይንም ወለጋ ከመወለድ ወደ ኅላ አይሉም። እነዚ ሰዎች አማራ ትግሬ የኦሮሞ የወላይታ የሱማሌ ወይንም ጉራጌ የሚሆኑት ከዚያ ማህበረሰብ ስለተወለዱ ወይንም እዚያ ስላደጉ ያለበለዚያም የቋንቋውን ስለሚናገሩ አይደለም።ያዋጣል ወይስ አያዋጣም? ነው መመዘኛው። ገበያ ካመቸ ማንነትም ይሸጣል ።
@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa
ትኩረት ሰረቃ!!!!!!!

ታዋቂና አዋቂ ግለሰብ ላይ አፍቸውን በመክፈት ታዋቂ ለመሆን የሚጣጣሩ ሰዎች
እንደው ተሳክቶላቸው ታዋቂነትን ማትረፍ ቢችሉ እንኳን አዋቂነትን ግን መቼውንም ቢሆን
አያገኟትም! !!!! የመላትም ሱሰኞች!! Attention Seekers!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ከፍ ያለው ስኬት ከፍ ያለ መሰብሰብና ጠለቅ ያለ ዋጋ ይፈልጋል!!!
------
ሰው የመሆን ትግል ድል የሚመጣው ራስን በማሸነፍ ነው። የማሳካትም ይሁን የመውደቅ
የምክንያት ምንጭ በራስ ላይ ድል የመቀዳጀትና ያለመቀዳጀት ጉዳይ ነው። ፈረንጆቹ ነብሰ-
ገዥነት ይሉታል!! ልትተልቅ ስትሻ ነብስህን ግዛ እንደ ማለት!!
ሰውነት ማለት ባንተ ብርሃን የሌላውን ጨለማ የመግፈፍ ትልቀት ነው። ሰው ሁን ማለት
"በነጣ" መዳፍህ እንባ የጋረደውን ያንተን አምሳለ-ፊት መጥረግ ነው። እንዲያ ሲሆን
አጭሩ እንቅልፍህ የሺ ዘመን ያክል ቢሆን ይጣፍጥሃል። መዳፍህን ለሻ ወቅት
የጨለመበት በፍቅር፣ በችሮታና ሰውነት ስትሰጠው አንጀትህ ይረሰርሳል፥ የሰላምህ ብዛቱ
ከሺህ ጥፋትና በደለኝነትህ እድሜህን ያረዝማል።
ሰው ሁን ማለት በጠንካራ ማነቆ አምማጺ የነብስያህን ጥያቄ ድል መንሳትና ወደ ላይኛው
ልእለ-ሰውነት መዳረሻ መንገድህን በመበርታት መያዝ ነው። ጥሩ ሰውነት ምርት ነው። ጥሩ
ምርት ሲባል ጥሩ ዘር፣ ጥሩ ዘሪ፣ ጥሩ አራሽ፣ ጥሩ አዝማሪና ጥሩ ያዥ ይፈልጋል።
ስውነትም እንዲያ ነው፥ እንደ ጥሩ ምርት ብዙ ጉልበት ይጨርሳል፥ አስተዋይነትና ብልሃት
በትልቁ ይከጅላል።
--------
ወደ ትልቁ ሰውነት መቅረብ በእድል አይመጣም! ልፉብኝ ይላል፥ ጣሩብኝ ይላል!! ልእለ-
ሰውነት እራስን ርትእ በሆነ መንገድ በማዳመጥ፣ እራስን በማረቅና ነብስያን በመኮርኮም
የሚመጣ ጣረ-ውጤት ነው!!
--------
ከፍ ያለው ስኬት ከፍ ያለ መሰብሰብና ጠለቅ ያለ ዋጋ ይፈልጋል!!!
----------
ሰው ሁን!!!

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ጌታዋ !!
ይኸ ፅሁፋ ከ 4 አመት በፊት ከተለያዪ ድህረገፆች እና ከተለያዮ ጋዜጠኞች የቃረምኩት
ነው፡፡
ዋና አላማውም
1. ማንም ሠው ለሚሰራው ስራ የገዛ ህሊናው መልስ እንደሚሠጠው
2. ለማንኛውም በግለሠብም ይሁን ለግሩፕ ፍላጎት ብለን ሠውን ያክል ነገር ስንጎዳ
በስተመጨረሻ የሚያመጣብን የአዕምሮ ጫና
3. የስብዕና እና የሞራል እድገት ለሠው ልጅ ያለውን ሚና ከ Kohlberg Moral
development theory አንፃር ያሳየናል የሚል ግምት አለኝ፡፡
.......
"...ሰው ሲራብ፣ ሲቸገር አትዮ፡፡ ካያችሁም ከሌላችሁ ቀንሳችሁም ቢሆን እርዱ፡፡ የህሌና
ቁስል መፈወሻ የለውም ፡፡ ራሳችሁን ከህሌና ቁስለት ታደጉ " ኬቨን ካርተር
‹‹ኬቨን ካርተር›› የተባለ ደቡብ አፍሪቃዊ የፎቶግራፍ ባለሙያ ሱዳን ውስጥ ተከስቶ
በነበረው ርሀብ ከተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ልኡክ ጋር ለደግነት ወደ ደቡብ ሱዳን
ያመራል ፡፡ በአንዷ መከረኛ እለትም ይህቺን ከታች
የምትመለከቷትን ምስል በካሜራው አስቀረ፡፡ ‹‹ርሀብ አድቅቆት የገዛ ራሱን መሸከም
ያቃተው ህፃን ልጅ እና ይህን ገላ ለመግመጥ የቋመጠ ጥንብ አንሳ›› የረሀብን ክፉ ገፅታ
፣የድርቅን አሰቃቂ ሁነት ፣የምስኪኖችን እልቂት ፣ቃላት ሊገልፁ ከሚችሉበት አቅም በላይ
በሆነ መንገድ በድንቅ ካሜራው ለአለም አስቃኘ፡፡ ‹‹ቀጫጫ እጆች እንኳን
ለመሮጥ፣ለመቦረቅ ይቅርና የገዛ አካሉን ለመሸከም ያዳገተው እግር፣ መቆም የከበደው
ገላ እና በርሀብ በሞቱ ሰዎች የደለበ ፈርጣማ አሞራ!!›› *** ይህን ፎቶ ከወራት በኃላ በ
1985 ዓም ለኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ተሸጦ ታተመ፡፡ ምስሉ በመላው አለም ታየ፡፡
ፎቶግራፈሩ፣ክብር እና ዝናን አተረፈ፡፡ ተሸለመ፣ተሞገሰ፡፡ዓለም ስለፎቶግራፈሩ አወራ፡፡
ከዚህ ሽልማት በኃላ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በአንድ አስተዋይ ጋዜጠኛ
የተወረወረች ያልተጠበቀች ጥያቄ ግን የህይወቱን አቅጣጫ እስከወዲያኛው ቀየረችው፤
አመሳቀለችው፡፡ ‹‹ህፃኗ ልጅ እንዴት ሆነች….ታደግካት?!!>> አይኖቹ ፈጠጡ….ላብ
አጠመቀው……… ቃላት ከአንደበቱ ጠፋ!! ………..በምናብ ወደ ደቡብ ሱዳንዋ የርሃብ
መንደር ተሰደደ፡፡ ጠያቂው ግን ድጋሚ በጩኸት ጠየቀ ‹‹ህፃንዋን ልጅ ታደግካት ?? ነው
ፎቶዋን ብቻ ነው ይዘኸው የመጣኸው???›› ካርተር ጋዜጣዊ መግለጫውን አቋርጦ ወጣ፡፡
ከወዳጅ ከዘመድ ሁሉ ተሰወረ፡፡ ከራሱ ጋር ተጣልቶ ለብቻው ውሳኔ አልባ ዶሴ ከፈተ፡፡
በገዳይዋ ፊት ጥሏት የሄደው የጎስቋላ ህፃን ነፍስ ለወራት እንቅልፍ ነሳው፡፡ካርተር ራሱን
ወነጀለ፡፡ የፎቶግራፍ ሽልማቱን ባሸነፈ በሦስት ወሩ በልጅነቱ ሲቦርቅ ባደገባት ‹‹ፓርክሞር››
በተባለች ለምለም ቀዬ በ33 አመቱ እራሱን ገድሎ ተገኘ፡፡ራሱን የሞት ፍርድ ፈረደበት ፡፡
በሞቱ ዋዜማ ላይ ሆኖ ለወዳጅ ዘመዶቹ ባስቀረው ማስታወሻ የሚከተለውን ፀፀት አሰፈረ ፤
"ካለኝ ነገር ቀንሸ አልሰጠሁም፡፡ እኔን ለማኖር ስራየን ብቻ ሰራሁ፡፡ ሚጡ ከርሀብ ጋር
ስትታገል ጥንብ አንሳው በእሷ ጠግቦ ይሆናል፡፡ ሚጡዋ፣የአሞራው እራት ስትሆን፣በሚጡ
ርሀብ እኔ ተሸለምኩ፡፡ይህም እኔን ሚጡ
ወዳለችበት የሞት ጎዳና እንድሄድ ፀፀቱ አስገደደኝ፡፡ደህና ሁኑ ዘመዶቸ፡፡ሰው
ሲራብ፣ሲቸገር አትዮ፡፡ ካያችሁም ከሌላችሁ ቀንሳችሁም ቢሆን እርዱ፡፡ የህሌና ቁስል
መፈወሻ የለውም ፡፡

ጊዜውን የጠበቀ ወርቃማ ብእር !!!
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሰኞን በሳቅና በሳቅ ልናሸንፋት ተነስተናል!!!!!!!


ቀኑ ለሰው ተሰራ እንጅ ሰው ለቀኑ አልተሰራም!!!!!!! እናም
ቀኑ የእኛ ቀን ይሆን ዘንድ ግድ ይለዋል!!!!!!
ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚያው ይሆናልና ሳቅ በሳቅ
በሆነው ሃሳባችን ቀኑን ወደ ሳቅ ጅረት ለመለወጥ
ቆርጠን ተነስተናል!!!!!!
እናም ልክ እንደዚህች ሸጋ ልጅ
ፍልቅልቅ ፣
ድምቅምቅ፣
ፍክትክት፣
ሽብርቅርቅ፣
ፍንድቅድቅ፣ ያለ ሳምንት አንድዬ ይሰጠን ዘንድ ማን

ከልካይ አለው???? ማንም!!!!!!!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
2024/09/30 09:38:20
Back to Top
HTML Embed Code: