Telegram Web Link
የበላይ በቀለ ወያ "ከባሻገር ባሻገር" የወግ መፅሀፍ በቅርብ እንደሚወጣ ግልፅ ነው።
መፅሀፉ ውስጥ ከተመቹኝ ታሪኮች አንዷን በትሬለር መልክ ላስቀነጭባችሁ ወደድኩ !( በላይ ተመስግነሀል! ) ውዶቼ
ፈታ በሉልኝ! !

የማንም አብሿም እየተነሳ "ሐበሻ ምቀኛ" ነው ቢል ኢግኖር ነው የምገጨው። ኢግኖር ባይኖረኝም በመኪና ነው
የምገጨው ። መኪና ባይኖረኝም ግንባር እንዳለኝ አልጠራጠርም ። በቴስታ ነው የምገጨው ። ምክንያቱም ፍቅሬን
ያፀናሁለት ማህበረሰብ ሐበሻ ነው ። ምቀኛ ያስባለውም ሀቀኝነቱ ነው። እንደውም ፈረንጅን ያህል ምቀኛ የለም ።
እስቲ እዚህ ጋር ሐበሻ ምቀኛ የተባለበትን ታሪክ እትዬ "እናና " እንደነገሩኝ ቃል በቃል ላቅርበው።(እትዬ እናና ያገራችን
የተረት እናት ናቸው። እኔ እንኳን እቴት ብዬ ነው የምጠራቸው ) ወደ ታሪኩ ስንመለስ
"እቴት "
"ወየ ጀንፈሌ ። ዛሬ ደሞ ምን ጥያቄ ይዘህ መጣህ? " ይሉኛል።("እቴት" ስላቸው አመጣጤ ለጥያቄ እንደሆነ
የሚለዩበት ጥበባቸው ሁሌ ግርም ይለኛል ። አመጣጤ ለጥያቄ ካልሆነ "እቴት" ስላቸው " ወየ ልጄ " ይሉኛል ። ጥያቄ
ሲኖረኝ ነው "ወየ ጀንፈሌ " የሚሉኝ ። በአንድ አይነት አጠራር ውስጥ ስንት አይነት መልእክት አለ ጎበዝ?
"እቴት "
"ወየ ጀንፈሌ ...."
"ሐበሻ ምቀኛ ነው ይላሉ እውነት ነው?"
"ማነው ያለው? ዝም በላቸው ይሄ የምቀኞች ወሬ ነው "
"የምቀኞች ወሬ ነው?"
"አዎን" ይሉኛል ቆጣ ኮስተር
"ምቀኞች እነማናቸው? "
"ፈረንጆች"
"እንዴት?" እላለሁ የማወቅ ጉጉቴ እንደንስር ከፍ ብሎ
"እንዴት ማለት ጥሩ ። ይኸውልህ በድሮ ጊዜ...." ብለው ሲጀምሩ ጣልቃ ገብቼ ...
"ድሮ መቼ ነው? " እላቸዋለሁ
" ድሮ ከተባለ ቀኑና አመቱ አይታወቅም ። የድሮ ስም የቀን መቁጠሪያ ላይ የለም። በቃ ድሮ ድሮ ነው ጀንፈሎ" ብለውኝ
ታሪካዊ ተረታቸውን ይቀጥሉታል ።
"በድሮ ጊዜ አንድ ፈረንጅ የአንድ ሀበሻን ቤት ተከራይቶ ፍየል ማርባት ይጀምራል ። ይህንን ያየ አከራዩ ሐበሻ ከፍየሎቹ
ጎን ነብር ማርባት ጀመረ ።
"እንዴ ሀበሻው የሚያረባውን ነብር ከየት አመጣ?" አልኳቸው ጣልቃ ገብቼ
"ሂሂሂሂ አይ ጀንፈሎ ይሔኮ የሐበሻ ታሪክ ነው ። ነብሩን ከየት እንዳመጣው ከነገርኩህ ምኑን የሐበሻ ታሪክ ሆነ? አየህ
ሐበሻ ጥንቁቅ ነው ፣ ሚስጥረኛ ነው ። ነብር ሲያረባ እንጂ ነብር ሲያመጣ አያሳይህም ።” እሺ አልኳቸው ታሪኩን
እንዲቀጥሉልኝ
"እናልህ ተከራዩ ፈረንጅ የሐገር ሽማግሌዎችን ሰብስቦ ሀበሻው ነብር ማርባቱን እንዲተው ቢያስለምነው ቢያስመክረው
... "ፍየል ማርባቱን እስካልተወ ድረስ ነብር ማርባቴን አልተውም " አለ። "ምነው?" ቢሉት ፍየሎቹ የጓሮ ጎመኑን
እየጨረሱበት ስላስቸገሩት ፣ ችግሩ ሳይባባስ ለዘለቄታዊ መፍትሔ ነብር ማርባት እንደጀመረ ነግሮ መለሳቸው ። ታዲያ
ሽማግሌዎቹ የአከራዩ መልስ ይዘው ለፈረንጁ ነገሩት ። ድጋሚ መልእክት ሊልካቸው ሲል ሽማግሌዎቹ አሻፈረኝ አሉ።
ራሳችሁ እንደጀመራችሁት ራሳችሁ ጨርሱት" ብለው ተሰናበቱት። ከጊዜ የገነባው ጎመን እየለመለመ ሔደ። በተቃራኒው
የፈረንጁ ፍየሎች ተመናምነው አለቁ ። በዚህ ጊዜ ፈረንጁ ማቄን ጨርቄን ሳይል ቤቱን ለቆ ጠፋ ። ይሔው ፈረንጅ
ሌላ ቦታ ቤት ተከራይቶ በግ ማርባት ሲጀምር ቤቱን ያከራየው ሀበሻ ከጎኑ ተኩላ ማርባት ይጀምራል ። ይሔኔ ፈረንጁ
ቀወሰ ። ጨርቁን ጣለ ። እርቃኑን መንገድ ለመንገድ እየዞረ "ሐበሻ ምቀኛ ነው።" እያለ መለፍለፍ ጀመረ። መቼም እኛ
ፈረንጅ የተናገረው ሁሉ እውነት ይመስለን አይደል? ይኸው እንደደህና ነገር የሚለውን ተቀብለን ከትውልድ ትውልድ
አስተላለፍነው ። እርስ በእርሳችን "ሐበሻ ምቀኛ ነው።" እንባባል ጀመር። እስቲ አሁን ማን ይሙት ነብርና ተኩላ አላምዶ
ማርባት ጥበበኛ እንጂ ምቀኛ ያስብላል ?
"አያስብልም" አልኳቸው የቀረ ታሪክ ካለ እንዲያወጉኝ
"አፌ ቁርጥ ይበልልህ። አየህ ሐበሻ ጥበበኛ እንጂ ምቀኛ አይደለም። ሐበሻ መጀመሪያ እንዳትሰርቅ ፣ እንዳትዋሽ ፣
እንዳታጭበረበር በጨዋነት የምታድግበትን ህግ ያበጅልሀል። ከዛ ህግ ውጪ ሆነህ ስትገኝ ይገስፅሀል ፣
ይኮረኩምሀል ፣ ይቆነጥጥሀል ። በህግ ስላሳደገህ ያላግባብ ሐብት ስታካብት ፣ በአቋራጭ ለመክበር ነገር ስትሸርብ
ይቆጣሀል። ተገቢ አለመሆኑን ይነግርሀል። በአንድ ወር ደሞዝ ሶስት አራት መኪና ስትቀያይር ፣ በየቦታው ህንፃ ስታቆም
"ከየት አመጣህ? " ብሎ ይጠይቅሀል። ግፍህን፣ ዝርፊያህን ፣ ብልግናህን አድበስብሶ ሸፋፍኖ አላሳልፍ ሲልህ " ድሮም
ሐበሻ ምቀኛ ነው" የሚል ስም ይሰጠዋል ። ድሮም ሐበሻ ጥበበኛ ነው ። ዘንድሮም ሐበሻ ሐቀኛ ነው።" እያሉ ስለ
ሐበሻ ሲያወሩልኝ ረጅም ሰአት ቆይተው ወደ ጓዳ ገብተው አቧራ ድሩን ያደራበት ትልቅ ስእል ይዘው ተመለሱ።
ከግርግዳ ላይ ገንጥለውት መሰለኝ ስእሉ ያረፈበት የወረቀቱ ጠርዞች በትናንሽ ቀዳዳዎች ታጥሯል ። ስእሉ ላይ
አንበሳና ሚዳቆ አጠገብ ላጠገብ ሆነው ከአንድ ወንዝ ውሃ ሲጠጡ ይታያል ።እንደውም ወረቀቱን ሲያነቃንቁት
አንበሳውና ሚዳቆዋ እየተሻሹ ፣ እየተላፉ ውሃ የሚጠጡ ይመስላል።
"ደስ የሚል ስዕል ነው!" አልኳቸው ።
"ስዕል አይደለም" አሉኝ ። (እንደመቆጣት አደረጋቸው ልበል?)
"እና ምንድነው?" አልኳቸው። ከስዕልነቱ ውጪ የሚታየኝ ነገር ባይኖርም የሚያወሩኝ ነገር ካለ ብዬ
"ስዕል አይደለም ። ህይወት ነው ። " ብለው በረጅሙ ከተነፈሱ በኋላ
"ለመሆኑ አማሪካን ሐገር ያለውን ልጄን ታውቀዋለህ?" አሉኝ
"ካሳሁንን?"
"እህ"
"እሱማ እንዴት ይጠፋኛል?!"
"በቃ እሱ ነው ይህችን ሚዳቆ እና ይህን አንበሳ አላምዶ ከአንድ ወንዝ እንዲጠጡ ያደረጋቸው። ይህ የምታየው ደሞ
የአባይ ወንዝ ነው። እናልህ አንድ ቀን አራት አማሪካኖች የአባይን መነሻ ለማግኘት ከግብፅ ተነስተው ወንዙን ተከትለው
ወደኢትዮጵያ ሲመጡ ልጄ ካሳሁን አንበሳውንና ሚዳቆዋን ውሃ ሊያጠጣ ወደ ወንዙ ሲወርድ መሐል ላይ ተገጣጠሙ
። ይህን ነገር ከተመለከቱት ፈረንጆች ውስጥ አንደኛው በድንጋጤ ወንዝ ውስጥ ገብቶ የአዞ ምሳ ሆነ። (ሰው እንዴት
ከአውሬ ሸሽቶ ወደ አውሬ ይጠጋል?) አንደኛው ደሞ ከድንጋጤው የተነሳ አንበሳውንና
ሚዳቆዋን ዘሎ በማለፍ አቀበቱን ሲፈረጥጥ የአባይ ወንዝ መነሻ ጋር ሲደርስ ውሃ ጠምቶት ሞተ። "የአባይን ልጅ ውሃ
ጠማው " ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው የዚህን ፈረንጅ አሟሟት የተመለከተ አንድ እረኛ ነው ይባላል ። የተቀሩት
ሁለቱ ፈረንጆች ግን ያዩት ነገር ህልም ይሁን ቅዠት እስኪያረጋግጡ ድረስ ሶስት ቀን ከአራት ለሊት ባሉበት ቦታ
በድንጋጤ ደርቀው ቀሩ ። ታዲያ ይህ ልጄ ነፍስ እስኪዘሩ ጠብቆ ካረጋጋቸው በሁዋላ ወደ ልባቸው ሲመለሱ
ትእንግርት የመሰላቸው ፣ አድርቆ ያስቀራቸው ጉዳይ እውነት ሆኖ አገኙት። የመጡበትን ጉዳይ ረስተውት ለወር ያህል
ጊዜ ልጄ በዋለበት እየዋሉ ባደረበት እያደሩ እየተገረሙ እየተደነቁ ቆዩ። በመጨረሻም ፈረንጆቹ ይህ የምትመለከተውን
ፎቶ እየተዟዟሩ ካነሱ በኋላ ልጄን ይዘውት ወደ አማሪካ ሔዱ ።" አሉኝ። ታሪኩ ባያሳምነኝም ትረካቸው
እንዳይቋረጥብኝ ስለፈለኩ ...
"እንዴ ሚዳቆዋንና አንበሳውን ለማን ትተዋቸው ሔዱ? " አልኳቸው
"ለኔ ነዋ " አሉኝ
"የታሉ ታዲያ?"
"እኚውት " ኮስተር ብለው ወደ ተዘረጋው ፎቶ እየጠቆሙ ።
"ይሔማ ፎቶ ነው?"
"ፎቶ አይደለም ህይወት ነው ስልህ "
"ይሔንንማ አላምንም ። ተረት መሆን አለበት " አልኳቸው ። ተቀያየሩ ። እጃቸው ተንቀጠቀጠ። ግንባታቸው ላይ የደም
ስሮቻቸው ቅርንጫፍ ከነ ግንዱ ተወ
ጣጠረ ። እንዴ እቴት ሌላ ሰው ሆኑ ።
"ምኑ ነው ተረት አንተ? " ብለው በቁጣ አፈጠጡብኝ ።፣ አይናቸው ከምኔው ደም መሰለ። መልስ እስክሰጣቸው
አልታገሱኝም ። ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከቤታቸው ሲያሰናብቱኝ ምን አሉ?
"ሒድ ውጣ ። ድሮም ሐበሻ ምቀኛ ነው። የጎረቤቱ ውብ ታሪክ ተረት ይመስለዋል ።"
ኢግኖር ገጭቻቸው ወጣሁ ።

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
የ ወግ ቤተሰቦች በታላቁ አርቲስት ጋሽ ፍቃዱ ተ/ማርያም ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን😔😔

ነፍስ ይማር !


@wegoch
@wegoch
To change ur life
change ur mind
To change ur mind
change ur blieve
to change ur blieve
change ur "words"

Napolio

@words19
@words19
@words19
📗📒📕📗📒📕📗📒📕📗📒📕📗📒📕
የንባብ ህይወት ኢትዮጵያ

ከሐምሌ 26―30 2010አም ማለትም ከነገ ሀሙስ ጀምሮ ለክረመምት ስንቅ የሚሆነን የተለያዩ ይዘት ያላቸውን መፅሀፋት የምንገበይበት እንዲሁም ደራሲያንን በቅርበት የምናገኝበት ልዩ ኘሮግራም በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል መግቢያ በነፃ <<<---

📗📒📕📗📒📕📗📒📕📗📒📕📗📒📕

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
መጠየቅ ደስ ይለኛል......ዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹ👇👇


እናነባለን ወይንም አንብበናል እንላለን በመፅሐፍት ወይንም ከሕይወት ካገኘነው ምንባብ የተማርነውን ሸጋ እውቀት ስንተገብረው እንስተዋልም...ለምን ይሆን?....ዳይ ተሳተፉ

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
☝️☝️☝️ ለዚህ ጥያቄ ከmember yetesetu መልሶች በጥቂቱ....👇👇

በዝምታ መጮህ!:

አነባለሁ ባልልም በተቻለኝ መጠን አነባለሁ አሁን አሁን ከማነበው ነገር ብዙ ተለውጬበታለሁ ትልቁ ለውጤ ማሰብ ማሰብ ነው ብዙ ነገር እንዳስብ እንድጠይቅ እንድመራመር ለጥያቄዬ መልስ ለማግኝት ደግሞ ደጋግሞ ማሰብ ማንበብ ነው ጥያቄህ ጥሩ አስታውሶኛል ካነብብኩት ነገር ምን አገኝው ብዬ እንድጠይቅ አመሰግናለሁ

Mesay Webet:

Manbeb ewkwt yisetkal keza ewketkn wede tegbar lemelewet gin yaschegral miknyatum simetachin mehal yigebana eminfeligewn aynet sew endanhon yasenakilunal gin be metsehaf yeminebebu tarikoch sew serash silehonu the so called perfect yihonalu malet new en a hiwot ende metshaf kelal adelem

አትናስያ የጌታ ነህ:


በደንብ የሚተገብሩ ሰዋች አሉ ግን እኛ ሰዋች እኮ በህይወታችን የገጠመንን ነገር ነው መፅሐፍ አድርገን ለሌሎች የምናስነብበው ታድያ ይሄን አልተማርንበትም ማለት እንዴት ይቻለናል ምክንያቱም ህይወት አንድ አቅጣጫ የላትም ደሞ የደረሰብንን እና ያነበብነውን ነገር ልንማርበት ካልቻልን የብዙ ነገሮች ተፅዕኖ ያለበት ይመስለኛል ምክንያቱም ጭንቅላታችን የብዙ ችግሮች ማደርያ ከሆነች የአይቻልም መንፈስን ውስጣችን ግንቦን ትገነባለች ያንዬ ያየነውንም የምንሰማውንም የምናነበውንም መተግበር ወይም መማር እንቸገራለን ተረዳሃኝ

Mesi:


May be ymnanbew anbabi nw lmbal slhone yhonal weym dmo ymshafu chbet bdmb saygban slmyalk yhonal 🤔🤔🤔🤔

Tammy:
Mn meseleh wendime balmbars ...yihe guday yante bicha tiyake ayimesilegnim yehulachin new. Endemimesilegn sinaneb kehiyiwet ga eyagenagnen silemananebew yimesilegnal. Sitaneb ke alem ga kagenagnekew mechem aresawm. Bechalinew akim agenagniten binaneb hulem kehiwetachin ga yinoral. Aleza fidelatn yemekuter sira bicha yihonal. ....

Amharic keyboard silelelegn new yikirta


ይሄን ይመስላል ሌሎቻቹም ሃሳባቹን ብታካፍሉን ደስ ይለናል🙏🙏

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ወግ ብቻ
መጠየቅ ደስ ይለኛል......ዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹ👇👇 እናነባለን ወይንም አንብበናል እንላለን በመፅሐፍት ወይንም ከሕይወት ካገኘነው ምንባብ የተማርነውን ሸጋ እውቀት ስንተገብረው እንስተዋልም...ለምን ይሆን?....ዳይ ተሳተፉ @balmbaras @wegoch @wegoch
Tizta 🐣:

እውቀቶች በራሳቸው ያሉ አይደሉም።የዓለምን አቅሞችና አጋጣሚዎችን ለመፍጠር የሚያገለግሉ ናቸው እንጂ።ልታስብ የምትችለው ነገር ሁሉ አስቀድሞ በማይታይ መልኩ ተፈጥሮ እየጠበቀህ ነው።እዲታይ የምትችለው ሀሳብና ስሜቶችህን በምቶደው ነገር ላይ በማድረግ የሰላም ሀይልን መጠቀም ነው።መፅሐፍት ከውጭ የሚያመጡት ነገር ምንም የለም ሁሉም ነገር የሚመጣው ከውስጥ ነው።ያን የተረዳ ሰው ወዳጅ አርጎቸው ያዳምጣቸውና ወደራሱ ያስማማቸዋል

እናም ብዙ ግዜ ማንተገብረው መፅሀፉን ስናነበው ይሰራናል ብለን ነው ግን የተለየ ነገር የለውም ያለንን ነው ሚነግረን ያለንን ተነግሮን
ካልገባን። ከራሳችን ጋር አልተግባባንም ማለት ነው። ስለዚህ ከራስ ጋር እርቅ ያስፈልገናል ማለት ነው።


አመሰግናለው!!!!

Heni Ye Enatu Lij:

Eregt nw metshaf kanbebn behuwala antgberwm gn yehe ye anbabiw cheger sayehon mayanbw sew mebzatu yemselgnal ye miyanb sew 1ngr litgber simoker ke mabrtatat yilk esu lay mekld ena ketsel semoch mawetat selmiknan leza yemslegnal

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Tizta 🐣:

እውቀቶች በራሳቸው ያሉ አይደሉም።የዓለምን አቅሞችና አጋጣሚዎችን ለመፍጠር የሚያገለግሉ ናቸው እንጂ።ልታስብ የምትችለው ነገር ሁሉ አስቀድሞ በማይታይ መልኩ ተፈጥሮ እየጠበቀህ ነው።እዲታይ የምትችለው ሀሳብና ስሜቶችህን በምቶደው ነገር ላይ በማድረግ የሰላም ሀይልን መጠቀም ነው።መፅሐፍት ከውጭ የሚያመጡት ነገር ምንም የለም ሁሉም ነገር የሚመጣው ከውስጥ ነው።ያን የተረዳ ሰው ወዳጅ አርጎቸው ያዳምጣቸውና ወደራሱ ያስማማቸዋል

እናም ብዙ ግዜ ማንተገብረው መፅሀፉን ስናነበው ይሰራናል ብለን ነው ግን የተለየ ነገር የለውም ያለንን ነው ሚነግረን ያለንን ተነግሮን
ካልገባን። ከራሳችን ጋር አልተግባባንም ማለት ነው። ስለዚህ ከራስ ጋር እርቅ ያስፈልገናል ማለት ነው።

ባላምባራስ:
🙏🙏 ሸጋ እይታ ነው ትዝታ.......ግን ደሞ እኔ ውስጥ የሌለ አንቺ ውስጥ አለ አንቺ ውስጥም የሌለ ነገር እኔጋ ይኖራል??


Tizta 🐣:
እሱማ አርግጥ ነው ። ነገር ግን አንተ ውስጥ ያለው እኔን አይሰራኝም ወይም እኔ ውስጥ ያለው
አንተን አይሰራክም። አንተ እስካልፈቀድቅ ወይም እኔ እስካልፈቀድኩ ድረስ ሙሁራኖቹ እንዳሉት እኔ ማለቀውን ሌላው ሚያቀውን ወይም አንተ ማታቀውን ሌላው የሚያቀው 25% አለ።


እናም እኔ ማስበው ያን 25% ነው አንተ ጋር ያለው እኔ ጋር ሲደርስ ውስጤ ብልጥ ቀሆነ ገነገሮች ማሀል ተዓምርን እዳለ አውቄ ሌሎች የሚያውቁትን እኔ ማላውቀውን ሲያሳዩኝ ባልቀበለው እንኳን እቀበለዋለው ለሆነ ቀን አስቀምጠዋለው። ካልሆነ በሆነ ወቅት ወቅቱ እደቀናው ገበሬ እሀሉ በበዛበት ወቅት ወቅቱም ይህ ሚሆን መስሎት ወይ ሳያስበላ ወይ ሳይበላ
አይን አይኑን እዳየው እንሆናለን።

ማለት መፅሀፍት እንደህፃናት ናቸው ፊት ይፈልጋሉ ያለዛ ዶሮ በሌለበት ጥሬ ማባከን ነው

አመሰግናለው!!!!

Heni Ye Enatu Lij:

Eregt nw metshaf kanbebn behuwala antgberwm gn yehe ye anbabiw cheger sayehon mayanbw sew mebzatu yemselgnal ye miyanb sew 1ngr litgber simoker ke mabrtatat yilk esu lay mekld ena ketsel semoch mawetat selmiknan leza yemslegnal

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
"መለስን ከሞት አስነሰዋለሁ"
# ታደለ ጥበቡ

ይሄን የተናገረው እስራኤል ዳንሳ ሐዋሳ ላይ በነበረው አገልግሎት ላይ ነው።እስራኤል ዳንሳ እንዳለው ከሆነ "የ6 አመቱን ሬሳ መለስ ዜናዊን ከሞት የማስነሳት መንፈሳዊ ብቃት ላይ እገኛለሁ።ሰውን ማስነሳት ለኔ አዲስ አይደለም ከዚህ ቀደምም ሁለት የሞቱ ህጻናትን አስነስቻለሁ"ሲል ከሞት የማስነሳት ልምድ እንዳለው በኩራት
ተናግሯል። እስራኤል ዳንሳ ይቀጥልና "ዋናው በጌታ በኢየሱስ ማመን
ነው።የስንፍጭ ቅጣት ታክል እምነት ያለው ሰው የኪሊማንጆርን ተራራ ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት ይቻላል ወይንም አዲስአበባን ወደ ሐዋሳ ሐዋሳን ወደ አዲስአበባ መቀያየር ይቻላል፤ጌታ ኢየሱስም ይሄን ቃል አስተምሯል"ሲል ነው ለታዳሚው የገለጸው።ታዳሚውም
"ይቻላል"በማለት በጭብጨባ አጅቦታል። እስራኤል ዳንሳ እንዳለው ከሆነ "ወ/ሮ አዜብ መስፍን የመለስ
መቃብር እንዲቆፈር ከፈቀደች ካለምንም ክፍያ አስነሳዋለሁ፤ከኔ የሚጠበቀው በጌታ በኢየሱስ ሥም ብቻ መጸለይ ነው"
ብሏል።በርግጠኝነትም ከመቃብሩ እንደ አልዓዛር ተነስቶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር "ይደመራል"ሲል ነው የጌታ የኢየሱስን ስምን እየጠራየተናገረው። አንድ ታዳሚ ይሄ ነገር በወለጋ ቄሌም ወረዳ ተሞክሮ እንደከሸፈና ውርደት እንዳያመጣ ሲጠይቀው "እሱ ሐሰተኛ ነው። ከሐሰተኞች ሰዎች መጠንቀቅ አለባቸው።በኛ ስም የሚነግዱ ብዙ ሐሰተኞች እንደተነሱ እያየን ነው"ሲል መልሶለታል።

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
የ በላይ መልዕክት 😂😂😂
።።።።።።።።።።
እስራኤል ዳንሳ መለስን ካስነሳው እኔ እሱን እገድለዋለሁ። የእስራኤል ዳንሳ ደህንነት ያሰጋኛል 😎😎 ለማንኛውም መለስ ከተነሳ እስራኤል ዳንሳን ገድዬ ወደ አሜሪካን የምሰደድበት ገንዘብ ስለሌለኝ ሀገር ውስጥ ያላችሁ በርከት እያረጋችሁ መፅሐፌን ግዙ።ውጭ ያላችሁ ወዳጆቼ በውስጥ መስመር 30$ ይዛችሁ በመምጣት መፅሐፍ በመውሰድ የህዝብ ልጃችሁን ከመለስ ራዕይ ታደጉት። በቅርቡ በሚኒሶታ እንገናኛለን የራሴ ደህንነት ያሰጋኛል

@wegoch
@wegoch
@lula_al_greeko
ቤት ድግስ ነገር አለ። ሰው ተሰብስቧል። "ወያኔ ሌባ!" ልበል?

ተወሰወስኩ!😂😂
(በረከት)
@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
ዶ/ር አብይ ከመጣ በኋላ እኛ ሰፈር የታዩ ለውጦች

( Natnael Getu)
እንደሚታወቀው ትርፍ ሰአቴን የማሳልፈው በመተኛት ነው ። ለምን?
ምክንያቱም መተኛት ከፍራሽ ውጭ ምንም አይነት ወጪ ስለማያስወጣኝ ። ሁኖም ግን ፍራሼን የገለባ ወይም የላባ ካደረኩት ቶሎ እያለቀ ወጪ ስለሚያስወጣኝ ውስጡን በኮረት እየጠቀጠኩ ያለስጋት አንቀላፋለሁ
ከፍራሼ ተነስቼ ልዝናና ብልስ ግን ኑሮው ይቀመሳል እንዴ? አያርግባችሁና ተስቷችሁ የሆነ ካፌ ሻይ አዛችሁ ብትቀመጡኮ የምትከፍሉት ብር በድሮ ሲመነዘር በራድ ፣ ቀጠፍና ሀያ ሊትር ጀሪካን ውሀ ይገዛል ! በዚያ ላይ የአንድ ወር ሰራተኛ የምትቀጥሩበት ሳንቲም
ሁላ ይተርፋችኋል ። እናላችሁ አልጋ ላይ ተቆልምሜ ነው የምውለው ። የሆነ ጊዜ ግን ሰፈሩ በሰበር ዜና መናወጥ ሲጀምር ምን ተፈጠረ ብዬ ከአልጋዬ ተነሳሁ ። ስወጣ ሰው በደስታ እየተፍለቀለቀ አብይ አብይ ይላል ። "አብይ" የሚባል ፈረንጅ ለሁላችንም ሀያ ሺ ብር በእርዳታ ለቆብን
መስሎኝ አብሬ መጨፈር ጀመርኩ ። ለካ ጉዳዩ ሌላ ነው ። የኛ ሀገር መሪ መሆኑን ስሰማ በአይኔ እንባ ሞላ "ሀገሬ መሪ መጣልሽ!" አልኩ ። መንጌም ሲመጣ እንደዛ ብዬ ነበር ። አምልጭ መጣብሽ ማለቴ ነበር ያኔ አሁን ግን በደስታ ነው እንደዛ ያልኩት ። እናማ ታላቁ የድጋፍ
ሰልፍ ሲደረግ አንዴ ፓርላማ ሳይ አንዴ ነዳጅ ወጣ ሲባል እንቅልፍ አጣሁ ። በቃ ነገሮች ተቀይረዋል ብዬ ሱቅ መድፈር ጀመርኩ ። ዶላር ቀንሷላ! የወር ደሞዜ ሲመጣ እከፍላለሁ ብዬ ከተለያዩ ሱቆች ብዙ ሸቀጥ አመጣሁ ። ኧረ ሻይ ሁላ ልጠጣ ነበር ። ጠዋት ስራ ይረፍድብኛል ብዬ ተውኩት እንጂ ። አብይ ባይመጣ እንደዛ አረግ ነበር? አላደርግም ። ረጅም እድሜና ጤና ለአብይ እያልኩ ብድሬን
ስከምር ከረምኩላችሁና የተፃፈብኝን እዳ ሳይ ያይን ማዝ ታመምኩ ግራ ተጋብቼ ባለሱቆቹን "ከአብይ በፊት በነበረው ዋጋ ነው እንዴ ያሰባችሁት?" ስል ጠየኩ ። "ኧረ ባሁኑ ነው! ያው የቀነሰ ነገር የለምኮ" ብለው መርዶ ነገሩኝ ።
እኔኮ ሰው ሲጨፍር ሳይ በየ ሱቁ የሸቀጥ ዋጋ ቀንሶ መስሎኝ ነበረ!
የጤፍና የማሽላ ዋጋ ወደ ታች ወርዶ ነበረ የመሰለኝ ። በየሱቁ ያለብኝን እዳ ልጄ ለወደፊት ተምሮ ስራ ሲይዝ ይከፍለው እንደሆነ እንጂ በኔ አቅም አይሆንም ! ከተወሰነ ጊዜ በፊት ጉረኛው አጎቴ ከዋሽንግተን ደውሎ "ብር ልላክልህ?" ሲለኝ ደረቴን ነፋ አድርጌ "ተወው አገር ተረጋግቷል" ብዬው ነበርኮ! እሱም ታድያ ለመጀመርያ ጊዜ ተወው ስላልኩት ተገርሞ ነበር ።
እንደፈረደብኝ ወደ አንዲት ባለጠጋ ሴትዮ ሂጄ ለአጎቴ ሚስኮል ታደርግልኝ ዘንድ ተማፀንኳት አጎቴ ግን ደውሎ
"በቀን አንድ ዶላር ለአገሬ ላበረክት ስለሆነ ልልክልህ አልችልም" ብሎ
ተስፋ አስቆረጠኝ ! ባጠቃላይ ዶ/ር አብይ ከመጣ በኋላ እኛ ሰፈር የታዩ ለውጦች እነዚህ
ናቸው:
- አንድ መስሪያ ቤት ውስጥ ተሰቅሎ የነበረው ባለ ኮኮቡ ባንዲራ
በመላጣው ባንዲራ ተተካ! ( የመስሪያ ቤቱ ዘበኛ ግን ደሞዛቸው አልተቀየረም ። ጠዋት ለሽሮ መግዣ ሊበደሩኝ መተው እኔም የለኝም ብያቸው ተሳስቀናል )
- የእኛ ሰፈር ሱቆች የመለስን ፎቶ ገንጥለው የአብይን ለጠፉ ( ሱቆቹ
ውስጥ ያሉ ሸቀጦች ግን ዋጋቸው ያው ነው)
- ብዙ እስረኞች ተፈቱ ( እስረኞቹ ከወጡ በኋላ ግን ዘርፈዋል የሚል ሀሳዊ ክስ የተመሰረተባቸው አንዳንዶች ኑሮ መወደዱን ሲያዩ የምር ዘራፊ ለመሆንና ባንክ ለመዝረፍ አቀዱ )
- ተኩሰው የማያውቁ ወታደሮች ትጥቅ ፈተው ሰፈር መጡ ። ( ሰፈር
ከመጡ በኋላ ደግሞ ስራ ፈቱ ) እኔም ብድሬን እያሰብኩ ድጋሚ አልጋዬን መልቀቅ እንደሌለብኝ ራሴን እያሳሰብኩ ፣ አዳዲስ ኮረቶች በኬሻ ጠቅጥቄ ወደ አልጋዬ አመራሁ

ፖለቲካውን ጨርሰን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ የምናይበት ጊዜ ይናፍቀኛል !

@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from Fitsum Beza Ruby picture
ኢትዩ ግሪን ፌስት ሩጫና ኮንሰርት በአንድ ቶሸርት ጉዞ ወደ ተፈጥሮ ብለን እሩጫ እና ትልቅ የሙዚቃ ድግስ ከፌሽታ ጋር ነሀሴ 13 እና 19 አንድ ቲሸርት በ 300 መቶ ብር ከበርገር ጋር ብዙ መዝናኛዎች ጨምሮ የመጀምሪያ ዙር ቲሸርቶች ሽያጭ ላይ ናቸው ፈጥነው ይግዙ ለበለጠ መረጃ 0921938039
📗📒📕📗📒📕📗📒📕📗📒📕📗📒📕
የንባብ ህይወት ኢትዮጵያ


ከሀምሌ 26 እስከ 30 የነበረው ንባብ ለህይወት የመፅሃፍ ኤግዚቢሽን ነገ ይጠናቀቃል በመሆኑም ያልገዛቹ እንድትገዙ የገዛቹም ደሞ ነገ የ
በመጀመሪያው “ንባብ ለህይወት” የወርቅ ብዕር ተሸላሚ የነበሩት
አምባሳደር ዘውዴ ረታ ሲሆኑ በሁለተኛው ዙር ደራሲ አዳም ረታ፣ በሶስተኛው ደግሞ የአዋቂም ሆነ የህፃናት መፅሐፍትን
በመፃፍና በመተርጎም ለረጅም ዓመታት ያገለገሉት ደራሲና ተርጓሚ አማረ ማሞ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ የዓመቱ የወርቅ ብዕር ተሸላሚ የፊታችን ሰኞ ማለትም ነገ ይሸለማል

ነገ ምሽት ከ11 ሰዓት ጀምሮ የግጥም በጃዝ የተመረጡ ገጣሚያንና ወግ አቅራቢዎች በኢትዮጵያዊነት፣ በአንድነትና
በፍቅር ላይ የሚያጠነጥኑ የጥበብ ስራዎቻቸውን ለታዳሚ ያቀርባሉ፡፡

እና ምን ለማለት ነው ነገ እንገናኘ!!!

እግር መንገዴን አንድ ጥያቄ ጠይቄ ልሰናበተሰ....ሐሙስ ለት ከወዳጄ ጋር መፅሐፍ ለመሸመት ጎራ ብለን ነበር የምንገዛውን መፅሐፍ ከገዛን ቦኋላ ትንሸ አረፍ ለማለት በዛውም ቡና ለመጠጣት ስንሄድ ሁለተኛው አዳራሽ መግቢያ ጋራ ከዚህ በታች post ማረገው ስእል እየተሸጠ አየን እና ሁለት ገዛን ስእሉን ሳየው እጅግ በጣም አስገረመኝ ....ባጭሩ ከዚህ በታች ያለውን ስእል በንስር አይናቹ እዩና ከሃገር ጋር አያይዛቹ የሆነ ነገር በሉኝ👇👇👇👇👇👇👇

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
<< ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል >>
የሚለው ማላዘን አገራችን ላይ አይሰራም!!

አሌክስ አብርሃም በፌስቡክ ገፁ ላይ

በጣም ብዙዎቹን ታዘብኩ እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ! ስለማንበብ ብዙ የሚደሰኩሩ ሰዎች መሰሪ ፣ ዘረኛ ፣መሃይሞች፣ ሃሜተኛ ፣ ለዛ ቢስ ፣ ሃሳበ ቢስ ፣ ፈጠራ ጋር የተጣሉ፣ ሆዳሞች ያውም ለቢራና ድራፍት ሃሳባቸውን የሚቀይሩ ቢመቻቸው እናታቸውን የሚሸጡ ፣ ሰድ ተሳዳቢዎች ፣ ሞራል የለሾች ፣ ተስፋ የቆረጡ ፣ ወሬኞች ፣ እንኳን አንብበው ዓለምን በተለየ መንገድ ሊረዱ በተፈጥሮ የተሰጣቸው ኮመን ሴንስ ስራ ያቆመባቸው ፣ ፈሪዎች፣ ሱሰኞች ፣ ግራ የገባቸው ፣ የማይማሩ የማያስተምሩ፣ ካነበቧት መጽሃፍ ላይ ሃሳብ ወስደው የራሳቸው የሚያስመስሉ ፣ የአዞ እንባ አንቢዎች ፣ የራስ መተማመናቸው አፈር የበላ ፣ ሃላፊነት የማይሰማቸው ፣ ለእውቅና የሚሞቱ፣ጉረኞች፣ምቅኞች ወዘተዎች ናቸው! ቆይ ምንድነው ግን የሚያነቡት
የቱንም ያክል ብታቃጥላቸው እሳት የማይበላቸው ቤተክርስቲያኖችና አማኞች ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው።
አቅም አልባ ነብስህ # ይቆሽሻል ፣ ውትርትር ጉልበትህ #ይዝላል እንጂ #በጥበብና # በእምነት የተሰራን አገር የመንጋህ ጦር አይወጋውም!!
እምነት አልባዎች ስነ-ምግባር የላቸውም፣ እርህራሄና ማስተዋልን የተነጠቁ ሲሆኑ #እራሳቸውን_ባጠፋ ስንፍናና ማይምነታቸው ብስጭት
የጎበዞችንና ምጡቃንን አሻራ በማዳፈን የተለቁ ይመስላቸዋል።
ገዳይ ሆይ ህይወት አይኑርህ፥ዘርህም ይቆረጥ!!

ሸጋ ሸጊቱ ቀን ይሁንላቹ!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
2024/09/30 17:31:53
Back to Top
HTML Embed Code: