Telegram Web Link
📗📒📕📗📒📕📗📒📕📗📒📕📗📒📕
የንባብ ህይወት ኢትዮጵያ


ከሀምሌ 26 እስከ 30 የነበረው ንባብ ለህይወት የመፅሃፍ ኤግዚቢሽን ዛሬ ይጠናቀቃል በመሆኑም ያልገዛቹ እንድትገዙ የገዛቹም ደሞ ዛሬ የ
በመጀመሪያው “ንባብ ለህይወት” የወርቅ ብዕር ተሸላሚ የነበሩት
አምባሳደር ዘውዴ ረታ ሲሆኑ በሁለተኛው ዙር ደራሲ አዳም ረታ፣ በሶስተኛው ደግሞ የአዋቂም ሆነ የህፃናት መፅሐፍትን
በመፃፍና በመተርጎም ለረጅም ዓመታት ያገለገሉት ደራሲና ተርጓሚ አማረ ማሞ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ የዓመቱ የወርቅ ብዕር ተሸላሚ የፊታችን ሰኞ ማለትም ነገ ይሸለማል

ነገ ምሽት ከ11 ሰዓት ጀምሮ የግጥም በጃዝ የተመረጡ ገጣሚያንና ወግ አቅራቢዎች በኢትዮጵያዊነት፣ በአንድነትና
በፍቅር ላይ የሚያጠነጥኑ የጥበብ ስራዎቻቸውን ለታዳሚ ያቀርባሉ፡፡

እና ምን ለማለት ነው ነገ እንገናኘ!!!

እግር መንገዴን አንድ ጥያቄ ጠይቄ ልሰናበተሰ....ሐሙስ ለት ከወዳጄ ጋር መፅሐፍ ለመሸመት ጎራ ብለን ነበር የምንገዛውን መፅሐፍ ከገዛን ቦኋላ ትንሸ አረፍ ለማለት በዛውም ቡና ለመጠጣት ስንሄድ ሁለተኛው አዳራሽ መግቢያ ጋራ ከዚህ በታች post ማረገው ስእል እየተሸጠ አየን እና ሁለት ገዛን ስእሉን ሳየው እጅግ በጣም አስገረመኝ ....ባጭሩ ከዚህ በታች ያለውን ስእል በንስር አይናቹ እዩና ከሃገር ጋር አያይዛቹ የሆነ ነገር በሉኝ👇👇👇👇👇👇👇

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ንባብ ለህይወት ዛሬ እጅግ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል ...እንዳለጌታ ከበደ፣ምዕልቲ ኪሮስ፣ሰለሞን ሳህለ፣ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ፣አንዱዓለም አባተ ( የአፀደ ልጅ ) ስራቸውን አቅርበዋል በተለይ የዶክተር በድሉ ከአዲሱ የግጥም መድብሉ ላይ ነይ ግጥም ዠፈኚ ምትለዋን ጣፋጭ ግጥም አቅርቧል ......እና ትላንት post የተደረገውን ስዕል የሳለው ወንደሰን ስእሉን እንዴት እንደሳለው ሸጋ የሆነ ማብራሪያ ነበር ያቀረበው....


በመጨረሻም "የንባብ ለህይወት " አራተኛዋ የወርቅ ብዕር ተሸላሚ ሰአዳ መሀመድ ሆናለች!!!!!!!


@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Daily motivational messages and qoutes

@words19
@words19

To change ur life
change ur mind
To change ur mind
change ur blieve
to change ur blieve
change ur "words" .

@words19
@words19
85ኛዉ ግጥምን በጃዝ ምሽት ነገ ነሀሴ 2 2010 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ በራስ ሆቴል አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በእለቱ ስራዎቻቸዉን መድረክ ላይ የሚያቀርቡ ገጣሚያን፡ ዋሲሁን በላይ፣ ፍሬዘር አድማሱ፣ ቤተልሔም ኒቆዲሞስ፣ ምዕልቲ ኪሮስ ሲሆኑ ዲስኩር አቅራቢዎች ደግሞ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያምና ዶ/ር አለማየሁ አረዳ ናቸዉ፡፡ ወግ አቅራቢዉ ደግሞ በሀይሉ ገ/እግዚአብሔር ነዉ፡፡


እንደምነው ሮብ፤ የሃሙስ ጓደኛ ፤
እንገጥማለን ብለን፤ ሸዋ ገባን እኛ! !!!!
ነገር የመጣኝ ቀን ፤ ነገር እገጥማለሁ ፤
ግጥም የመጣኝ ቀን፤ ግጥም እገጥማለሁ ፤
ያገጣጠመኝ ቀን ግጣም እገጥማለሁ ፤
መግጠም ነው እንግዲህ ፤
ከዚህ ወዲያ ስራ ከወዴት ተገኝቶ ፤
አለም አይደለም ወይ ፤
መግጠም መገጣጠም ቁሞና ተኝቶ ።

((( ጃ ኖ )))



@balmbaras
@wegoch
@wegoch
መሀል ሸዋ ላይ ነገ ራስ ሆቴል እንገናኝና የሸዋን ቀበሌ መረባ
እንበልበት! !!!

በየወሩ የሚካሄደው ጦቢያ ግጥምን በጃዝ 85 ምሽት

ከቀኑ 12:00 ሰዓት ጀምሮ

እንደተለመደው በራስ ሆቴል ይካሄዳል።

ኑና አብረን መረባ እንበል!

መረባ አትይም ወይ ፤
ከምትወዘወዥ እንዳበደ ጥጃ ፤
መረባ አይደለም ወይ ፤
ጀምበር ሳይዘቀዝቅ የሚያወጣው ሃጃ ።


እንጃ! !!!

(( ጃ ኖ )))

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
❤️❤️❤️ኢትዮጵያዊነት❤️❤️❤️

በአንድ ወቅት የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ጃንሆይን እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል “ለመሆኑ ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? ”
እርሳቸውም ቆፍጠን ባለ አነጋገር “ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ትህትና ነው” አሉት። ❤️❤️
ጋዜጠኛውም ቢሆን የዋዛ አልነበረምና “ይቅርታ ያድርጉልኝ ጃንሆይ ይሄ ሃምብልነስ እና ፕራውድነስ የሚሉት ነገር እርስ በርሱ የሚጣረስ ማንነት አይመስልዎትም?” የሚል ጥያቄ ያስከትላል።
ንጉሱም እንዲህ አሉ “አየህ አንድ በጣም ተራ የምትለው ገበሬ ቤት በእንግድነት ብትሄድ ያለውን አብልቶ፤ እግርህን አጥቦ፤ ያጠበውን እግርህን ስሞ፤ አልጋውን ላንተ ለቆ እርሱ ግን መሬት ላይ ይተኛል። በዚያው ልክ በሚስቱ፣ በርስቱና በሃገሩ ላይ ብትመጣበት ደግሞ በግንባርህ ላይ ጥይት ይቆጥርልሃል፤ ስለዚህ አይጋጭም፤ ነገር ግን ይሄንን ነገር ለመረዳት አንተ ራስህ ኢትዮጵያዊ መሆን አለብህ” ነበር ያሉት።
ኢትዮጵያዊነትን ለመረዳት ኢትዮጵያዊ መሆንን ይጠይቃል፤ ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ነውና!!!❤️❤️❤️❤️

ሸጋ ምሽት!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
85ኛዉ ግጥምን በጃዝ ምሽት እጅግ በጣም ደስ የሚል ምሽት ነበር የገባቹም እንደተደሰታቹ ተስፋ አለኝ በጣም ሰው በዝቶ ስለ ነበር ትንሽ ወንበር ለማግኘት አስቸጋሪ ነበር ይሆን ሸጋ የሆነ የጥበብ ዝግጅት ቆሞ መመልከቱ በራሱ ቢያንስ እንጂ ....መድረኩ ላይ ወደ ነበረው ዝግጅት ስሄድ ፍሬዘር አድማሱ ( ታገቢያለሽ ወይ እና ግሪሳ ) የግጥም ስራዎቹን አቅርቧል ምዕልቲ ኪሮስ ( ፈገግ አለ እሱ እና አዎ ብቻዬን ነኝ ) ዋሲሁን በላይ ( ፒያኖ ላይ የተኛች ሴት እና አንዳንድ ሰው አለ ) የሚለውን ስራው አቅርቧል እኔ ከቀረቡት የግጥም ስራዎች ዋሲሁን በላይ ያቀረባቸው በጣም ወድጄዋለሁ ...... ወግ በማቅረብ ቤቴልሄም ኒቆድስ ( ስምንተኛው ) በሀይሉ ገ/እግዚአብሔር ( አስክሬን አጃቢውና ሹም አጃቢ ) የሚሉ በጣም ሚያስቁ ቁም ነገር ያላቸውን ስራዎቻቸውን አቅርበዋል......ዲስኩር ዶክተር አለማየሁ አረዳ "ስለ መደመር " ሸጋ የሆነ ነገር ብለዋል መደመር ምንድን ነው ? በመጨረሻም ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያምን በህመም ምክንያት እንዳልተገኙ ለዚህም ይቅርታ ጠይቀዋል .....በዚህ ሳምንት ሀገራችን ላይ ለተፈጠረው ነገር እና ለአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያምን የህሊና ፀሎት ተደርጓል።

85ኛው ግጥም በጃዝ በዚህ ሁኔታ ተጠናቋል!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ከታሪክ አለመማር! !!!!!!!


መቼስ የ1960 ትውልድን የፖለቲካ ትርምስ በበርካታ ጸሃፍት ተጽፎ አነበብነው ። ያነበብነው ለጊዜ ማሳለፊያ ከሆነ ከስረናል ባይ ነኝ ። ያ
ትውልድ የማደንቅለት ልዩ መገለጫው ቁርጠኝነቱና ለአላማው የመሰጠቱ ተፈጥሮውን ነው ። ከዚያ ባለፈ ግን ኢህአፓ ፤ መኢሶን ፤
ኢጭአት ፤ ወዝ ሊግ ፤ ሰደድ፤ ተሃህት ፤ወዘተ የቸባሉ የፖለቲካ ቡድኖች የኔን ብቻ ስሙ ፤ ብቸኛ የህዝብ መሲህ እኔ ነኝ ፤ ከኔ ውጭ መዳኛ
የላችሁም ፣ እኔ ብቻ ብቸኛ አመራጫችሁ ነኝ ፤ ከኔ እጅ የወጣ አበቃለት በሚል የእኔ ብቻ ፉከራና ቀረርቶ ከማበጣቸው ባሻገር ሌላውን
የፖለቲካ ቡድን ደግሞ ውግዝ ከመአርዩስ ወንስጥሮስ በሚመስል የውግዘት ናዳ እሱ ጸረ ህዝብ ነው ፤ እንዳትሰሙት ፤ ሊበላችሁ ነው ፤
ሊውጣችሁ ነው ፤ ሊፈጃችሁ ነው አይነት የአያ ጅቦ ማስፈራሪያ በማወጅ ሁሉም ቡድን በስክነትና በመነጋገር የዘመናቸውን የህዝብ
ፍላጎትና ጥያቄ በዲሞክራሲያዊ ስልት መደማመጥና መፍታት ባለመውደዳቸውና ባለመፈለጋቸው ያ ሃገርን የማቅናት አቅም የነበረው
መልከኛ ትውልድ እኔ ብቻ በሚል ልክፍት ተለክፎ ርሱ በረሱ ተራረደ ።ከሃሳብ ውይይትና ከመነጋገር ውዴታ ይልቅ በአፍቅሮተና በአምልኮተ
ፓርቲ እየተገፋፋ ወደመቃብር ወረደ ። የዚያን ትውልድ እኔን ብቻ ስሙኝ ታሪክ ያስከተለውን አስከፊ እልቂት በበርካታ መጽሃፍት ተከትቦ
ያነበብነው አባቶቻችን በተደናቀፉበት ድንጋይ መልሰን እንዳንደናቀፍ ትምህርት ለመውሰድ እንጅ አባቶቻችን በተደናቀፉበት ዲንጋይ መልሰን
እኛም ከተደናቀፍንበት ዲንጋዩቹ እኛና እኛ ብቻ ነን ።
የቀደመው ትውልድ እኔን ብቻ ስሙኝ ፤ ብቸኛ መዳኛችሁ እኔ ነኝ የሚለው ልክፍት አሁን አሁን ወደዚህኛው ትውልድ ተሸጋግሮ የኔን ቡድን
ሃሳብ ብቻ ካልደገፍክ አለቀልህ ፤ ወዩልህ ፤ የእነ እገሌን ቡድን ሃሳብ ከተቀበልክ እንተያያለን ያዘው ፍለጠው የሚለው የድንጋዜና የድንዛዜ
ፉከራ ሲታይ ያ የቀደመው ትውልድ የመደናቀፊያ ድንጋይ እኛኑ ዲንጋይ ሳያደርገን አልቀረም ያሰኛል ።
ያ ትውልድ (That generation)በተደናቀፈበት ""እኔ ብቻ መሲህ!!!! እኔን ብቻ ስሙኝ" " በተባለ ጋንጩር መለከፍ ጉዳቱ ለራስም
ለሃገርም ነውና ብዝሃ ሃሳብን ለማስተናገድ ሆደ ሰፊ መሆን ለምንመኛት ዲሞክራሲያዊት ሃገር ሁነኛ ምሰሶ ነውና ለብዝሃ ሃሳብ ዋጋ
መስጠትን የመሰለ ነገር የለም ለማለት ያህል ነው ። ሻሎም!!!!!

ሸጋ ሸጊቱ ቀን!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሰሞኑን የማያቸው ሁለት ነገሮች ግርርርርም ይሉኛል
ባንዲራ የማስረዘም ፉክክር ይገርመኛል
አንዳንዱ ባንዲራ ከመርዘሙ የተነሳ ፤ተሸንሽኖ፤ ሱሪና ቀሚስ ሆኖ ቢሰፋ አንድ የገጠር መንደር አመት ያለብሳል፤
የጦቢያ ፖለቲካ የተራቀቀ አይደለም፤ ለብር እና ለክብር የሚደረግ ትግል ነው፤ ከላይ ያሉት ጮሌዎች የሚፈልጉትን ያውቃሉ፤ በተራበ ሰው
ስም፤ በተፈናቀለ ሰው ስም፤ነፃነት በጠማው ሰው ስም ፤ በግዜር ስም፤ በናት ሀገር ስም፤ በናት ጎሳ ስም፤ ሀብት ፤ ስልጣንና ዝና
ይሰበስባሉ፤
ከታች ያለው ጎበዝ የኔ ባንዲራ ቁመት ካንተ ባንዲራ ቁመት ይበልጣል፤ በሚል ሀሳብ ተጠምዶ ድርሻውን ሳይጠይቅ፤ ክሬም እድሜውን
ያባክናል ፤ አንድ ቀን ባንኖ ሲነቃ በጁ ምንም የለም፤ ሰው መሆን አይቀርምና ላመፅ ያቆበቁባል፤ ይህን ጊዜ ተጠባባቂው ጮሌ ከሰገነቱ
ወርዶ ለጭፍራነት ይመለምለዋል፤የምድር ወገብ የሚያክል ባንዲራ ያሸክምና በግሩ ፈንጅ ያስጠርገዋል፤
ካርታ በመሳል ሰመመን ጦዘው የሚውሉ አሉላችሁ ደግሞ፤ ድሮ አገር ለመያዝ ያማረው ብዙ ድካም ነበረበት፤ ፈረስ መግዛት ፤ጭፍራ
ማደራጀት፤ ግብር ማብላት፤ መድማት መራብ መጠማት እንቅልፍህን እና ህይወትህን መሰዋት ይጠበቅበት ነበር፤ አሁን አገር ማቅናት አልጋ
ላይ ተንበልብሎ ላፕታፕ ላይ ካርታ ከመሳል አያልፍም፤ እያንዳንዱ ጎራ የሚስለው ካርታ አንድ የሚያስቅ ተመሳሳይነት አለው፤ ወደ አጎራባች
ባህር ወይም ክልል ዘልቆ የሚገባ ሾጠጥ ያለ ነገር አለው፤ያ ሾጣጣ ነገር ያባት አገር ብልት ይሆን? ለማንኛውም ካርታ ስንስል ፤ ጊዜው፤
የመነጋገር፤ የማሽኮርመም፤በፍቅር የመማረክ እንጂ አስገድዶ መድፈር እንዳልሆነ እናስብ፤
የለማ ቡድን የፍቅር የትህትናንና የታታሪነትን ዋጋ ለማሳየት የሚያደርገው ሙከራ የሚደነቅ ነው፤ ግን ሌላው ተምሳሌትነቱን ካልተከተለው
በቀር፤ ለውጥ አይታሰብም፤ አሁን አሁን፤ ተምሳሌትነት አጠገብ ቆሞ ፎቶ መነሳት እንጂ ተምሳሌትነትን መከተል ብዙ አይታይም፤
እዚህ ላይ የቀበጢቱ ታሪክ ትዝ አለኝ፤
አንዲት ከመዘነጥና ሞባይሉዋን እንደ ልጅ ራስ ከመደባበስ ውጭ፤ ስራ በደረሰበት የማትደርስ ቀበጥ ልጅ ነበረች፤ታላቅ ወንድሙዋ እና
እናቱዋ የልጂት ባህርይ አሳሰባቸው፤ እስቲ ስራ እንድትለምድ አንድ ነገር እናድርግ ተባባሉ፤ለምን አርአያ ሆነን አናሳያትም? ያኔ ህሊናዋ
ወቅሱዋት መስራት ትጀምራለች ብለው እቅድ ነደፉ፤
አንድ ማለዳ ላይ፤ ቀበጢት መስታወት ፊት ቆማ ፤ፊትዋን በፓውደር ስትጠበጥብ ፤ እናት አጠገቡዋ ያለውን ወለል መጥረግ ጀመሩ፤ ልጅ
እየሮጠ ደረሰና “ እማየ እኔ እያለሁማ በደካማ ጉልበትሽማ አትጠርጊም” ብሎ መጥረጊያውን ለመቀማት ይታገል ጀመር፤እናት በበኩላቸው
“እኔ እናትህ ክንዴን ሳልንተራስማ አንተ አትጠርግም” ብለው መጥረጊያውን ሰንገው ያዙ፤በዚህ አይነት ሲፋለሙ ቀበጢቱ ፊትዋን
ከመስታውቱ ሳትነቅል እንዲህ ስትል ተሰማች፤
“ሽሽሽሽሽሽስ ! እየረበሻችሁኝ ነው ተራ በተራ ጥረጉ!”

((( በእውቀቱ ስዩም ))

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የቁንጅና ዋጋ
አሸናፊ መለሰ


ለዉበት አልሰግድም የተባለ የግጥም ስብስብ ለማሳተም አስቦ ፣ በግጥሞቹ ላይ አስተያየት እንድሰጠው የቀጠርኩት ወዳጄን ለማግኘት ፣ ከመገናኛ ወደሜክሲኮ እየሄድኩ ነው። ሰዓቱ እኩለ ቀን በመሆኑ ታክሲው ከፀሐይ የተሰጠውን ብቻ ሳይሆን ፣ በግሉ የጠመረብንን ሙቀት በቦታው ላይ አለ ልክ አንሰራፍቶት የታክሲው እልፍኝ ተንቀሳቃሽ ስቶቭ።

ከሹፌሩ ኃሏ ባለው ወንበር ላይ ቀድሜ በመቀመጤ በመስታወቱ በኩል ከሚገባው ጨረር እራሴን ለማዳን ችያለው። በእኔ በኩል አልፈው በቦታው የተቀመጡት አዛውንት ግን በፀሐይዋ ግለት ብርታት ከአንድ ብርቱ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ እንጂ ከአንድ ድሃ ሽማግሌ ግንባር ላይ ሊገኝ በማይችል ወዝ ወርዝተው ፣ ከአንድ ብርቱ የማራቶን አትሌት እንጂ ከአንድ ዕድሜ ጠገብ ቁመና በማይጠበቅ ላብ ተጥለቅልቀው ተቀምጠዋል።


ሃያ ሁለት ማዞሪያ ስንደርስ ሙቀት በሰነጣጠቀው ድካም በጨፈላለቀው ሰላሳ ድምጽ ፣ "ወራጅ አለ !" አሉ፣አዛውንቱ ።

እግሬን እንደሚካኤል አንጄሎ ሥእሎች በአንድ ሰብስቤ እንዳስገባኃቸው።

ትጉው ወያላ ክፍቱን በተተወው በዚያ ትኩስ ምጣድ እኩል ወንበር ላይ የሚቀመጥ ሰለባ ፍለጋ መጣራት ጀመረ.......

"ካዛንቺስ...ፍል ዉሁ...ሜክሲኮ...ብሔራዊ ...ካሳንቺስ......"

የወያላውን የሞት ጥሪ ሰምታ አንዲት ውብ ወጣት ወደታክሲው ደጃፍ ቀረብ አለች።

ከፀጉር እስከጥፍሯ በጥንቃቄ ከተመረጡ አካለው በዕውቀት የተዋቀረች ፣አንገትና ሽንጧ እንዳሻት እንድትዟዟርባቸው ፣እንዳሻት እንትቃኝባቸው ያለሥጋት የተተው ፣ ጡትና መቀመጫዋ በመንቀልቀል እንዳትባዝን ባማረ ጭነት የተሞሉ ፣ በዘረኝነት ውብ አንገቷ እንዳይደፋ ፣ ከዘሮቿ ከሃበሾች መሀል ስትሆንም ባይተዋርነት እንዳይነካካት ፣ ከሁሉም ተቀያይጦና ከቸኮሌት ተሽሎ የተቀመመላት ውብ ሴት ነበረች።


ከእኔ ቀጥሎ ቦታ መኖሩን ስትገነዘብ እንደቀልድ ፈገግ እንደማለት ብላ በእነዚያ አስማተኛ ዓይኖቿ ወደዚያ የፍም ወንበር እንድጠጋ ምልክት ሰጠችኝ።

ወደድንም ጠላንም ዓለም ለቆንጆዎች ታደላለች። ቁንጅናን ውስጣዊም በሉት ውጫዊ ፣ የበላይነቱን ያገኝ ዘንድ ቀዳሚነቱ ይረጋገጥ ዘንድ ቀዳሚነቱ ይረጋገጥ ዘንድ ሁልጊዜም በዕጣ ፈንታ ይደገፈል። ቆንጆ ለተሻለ ነገር በሚደረግ ምርጫ ውሰጥ አስቀድሞ በአዕምሮ ይመረጥ ዘንድ ተፈጥሮ አድሎኦዋን በግልጽ ታሳያለች። ለዚህም ነው፣ የንጉሥ ሚስቶች ሁሉ ወደብ አልባ ቆንጆ የሆኑት።

ለቁንጅና ታላቅነት ፣ ለውበት ከፍታም እነሆ ፉንጋነት የሚባል ማንፀርያ፣መሃይምነት የተባለ ዝቅጠት ተፈጥሮለታል። የውበትን ሃያልነት ማግዘፍ ነው፣ፉንጋዎች ብዙ የሆኑት። ለዚህም፣ ነው ፣ መሃይማን የበረከቱት። በአንፃሩ ደግሞ ቆንጆዎች ጥቂት ናቸው። ሸጋዎች በዕጣና በዕድል እንጂ እንዲሁ አይታዩም።

አሁን ለምሳሌ የዚህችን ሴት ውበት በሌላ ሴት ላይ ለማየት አዲስ አበባን ሁለት ጊዜ ገልብጦ መፈተሽ ያስፈልጋል።


እና ፣ ወደፍሙ ወንበር "ጠጋ በል!" አለችኝ።

ለቁንጅና የማልንበረከክ ፣ ለቆንጆ የማላረግድ ከቶ እኔ ማን ነኝ? ለቁንጅና ዝቅ ማለት የተፈጥሮም ይባል የሰው ልጅ ፣ የውዴታ ግዴታ ነው።

አውሮፓ በብርቱ ክንዱ እያደቀቀ ነገሥታትን በሰይፎቹ ስለት እንዳልነበሩ እያደረገ ዓለምን ለመቆጣጠር ሲገሰግስ የነበረው የሮማው ንጉሥ ጁልየስ ቄሳር "የክሊዮፓትራ አፍንጫ ትንሽ ጎረድ ቢል ኖሮ የዓለም ታሪክ ይቀየር ነበር" እኪባል ድረስ ግብፅ ሲደርስ በተመለከተው በምርኮኛው ንግሥት በክልዮፓትራ ውበት እንዳይሆን አልሆነም? በግብፅ ፒራሚዶች አናት ላይ የሮማውያንን ጦረኝነት የሚናገር ታሪክ ለማስቀመጥ ሄዶ ከሀዲስ አለማየሁ በዛብህና ከዊልያም ሼክስፒር ሮሚዮ የቸሻለውን የፍቅር ገድሉን አልሰራም??

የኛዋስ ጉድ ፣ ዮዲት ጉዲት ብትሆንስ ?! ያን ምስኪን ደብተራ የአምላኩን ፍርሃት አስረስቶ ንዋየቅዱሳኑን ይዘርፍና ያበረክትላት ዘንድ ማን አስገድደው?? ውበቷ አይደለም እንዴ??

በኃላስ ለቅጣት የተቋረጠ ጡቷን በቡቱቶ ሞልታ ታላቁን የጥፋቷን ጦር ታደራጅ ዘንድ ማን ነበር ትልቁ ሃይሏ?? ከጠላቶቿ ስለት ያስተረፈችው ውበቷ አልነበረም? ያ ጦረኛ ቧላስ ቢሆንስ፣ "ወደ ጦርነት ሂድልኝ፣ሄደህ ውበቴን ለማጥፋት ሰይፋቸውን እንዳነሱብኝ ሁሉ ታሪክና ቅርሳቸውን ፣ ሃይማኖትና ኩራታቸውን አጥፋልኝ!" ስትለው "እሺ " ከማለት ውጪ ምን አማራጭ ነበረው!? ምንም !!


ወደመስኮቱ ተጠጋሁ ፣ የጋለው ወንበር መቀመጫዬን ሲጠብሰው ተሰማኝ።

ይሁን ፤ ግዴለም።

ከጥቂት የቅቀላ የፍጅት ጉዞ በኃላ የመቀመጫዬን መጥበስ እያሰብኩ ከመብከንከን ቆንጆዋን ለመጥበስ እንደሚሻል አስቤ፣

በዚህ ፀሀይ ወዴት ነው? አልኳት ውበቷ በፈጠረው የትህትና ፍርሃት ተከብቤ።
አየት አደረገችኝ። ከዚያ ደግሞ በፈጣን ምልከታ ከላይ እስከታች ከገመገመችኝ በኋላ ዘና እንደማለት እያደረጋት ወደትምህርት ቤት ነበር......ግን...ብላ በፊቷ ፈገግታ ላይ ቅጨማ እየጨመረችበት ዝም አለች።

ምነው አልኳት የእኔ ባልሆነ ትህትና።

እንጃ! መማር አይሰለችም? አለችኝ ፈገግታዋ ላይ የነበረውን ቅጨማ በመታከት ቀይራው።

ሣቅ አልኩኝ።

እውነት ግን ከማይረባ ዲግሪ ያማረ ቁመና አይሻልም? እውነት እውነት እንነጋገር ከተባለ በዓለም ታሪክ ውስጥ ቢመዘን ዲግሪ ካስገኛቸው ግለሰባዊ ጥቅሞች ይልቅ ውብ መሆን ያስከፈታቸው የስኬት በሮች መአት ናቸው። በዙዋሎጂ ከሚገኘው ድግሪ ይልቅ ዞማ ፀጉር ስንት ተአምር ሰርቷል ስለ ጂን እያጠኑ እኖራለሁ ብሎ ከመውተርተር ባማረ ጭን መተማመን ያዋጣል።

እና..........


"እና ምን አሰብሽ ??አልኳት ፈገግታዬን ሳላረግብ።

እንጃ ጓደኞቼ ጋር ሄጄ የሆነ ፊልም ነገር ለማየት ወጣ ለማለት አስባለው አለችኝ።

"ልከተልሽ?" አልኳት። ቀልጠፍ ብዬ።

ልትቀላቀል ፈለክ? ይቻላል! እንደመሽኮርመም እያደረጋትተ

መቀላቀል ሳይሆን ማስኮብለል ብችል ደስ ይለኛል አልኩኝ ፊቴን ወደእሷ ጠጋ ድምጼን ዝቅ አድርጌ።

ተሽኮረመመች።

"መሽኮርመም ማለት ግማሽ መስማት በማሀፈለት በውስጤ የከሸፈ ግጥም አነበነብኩ።

ድንገት ስልኬ ጠራ። ያ ጀማሪ ገጣሚ ነው።

አቤት! አልኩት የኔ ባልሆነ ቁጣ።

ምን ነካህ ሰውየው ካፌ አስደግፈኸኝ ትጠፋለህ እንዴ? እዚህ ከደረስኩ'ኮ 25 ደቂቃ አለፈኝ ትህትና ጓደኝነት በሚታዩበት ለስላሳ ድምጽ።

እመጣለሁ! አልኩት ቆጣ እንዳልኩ።

ምነው? ሰላም አይደለህም እን......አላስቸረስኩትም በአውራ ጣቴ የስልኬን ቀይ ጡት ተጫንኩትና ወደሷ ዞር ብዬ ፈገግ አልኩላት አፀፋውንም መለሰችልኝ።

አዉራ ጣቴ የስልኬ ቀይ ጡት እንደተጫነ ጥቂት ቆየ። እናም ስልኬን እንደመንዘር ብሎ እራሱን አጠፋ።

ስልኬን በማጥፋቴ የአንድን ትጉ ኢትዮጵያዊ ገጣሚም ሆነ የኢትዮጵያን የሥነጽሑፍ እድገት በስሱ ቢሆን እንዳዘገየሁት ቢገባኝም ይህ ድርጊቴ ከግጥምም ሆነ ከሥነጹሑፋችን በላይ ለሆነው ውበት ሲባል የተከፈለ መስዋዕትነት በመሆኑ የጥፋተኝነት ስሜት አልተሰማኝም። ደግሞስ ለውበት አልሰግድም ብሎ ለመጽሐፉ ርዕስ የሚሰጠውን ማነኝ ለማለት ነው? ተፈጥፎን የሚጋፋ ከእውነታ የሚቃረን ግጥም ምን ይሠራልናል?


ይህን እያሰብኩ እያለ ድንገት "ወራጅ አለ!!' የሚለውን የዚያችን ውብ ልጅ ውብ ድምፅ ሰማሁ።

ታክሲው ቆመላት።

ከታክሲው ወርዳ ዞሯ በፈገግታ አየችኝ።

ተከተልኳት።


@balmbaras
@wegoch
@wegoch
.....ቢያንስ ከዛሬ ጀምሮ ....

.......እንኳን መንግሥት፣ ሴጣን...ፈጣሪም ቢሆን በቤታችን፣ በልባችን፣ በመንፈሳችን፣ በነፍሳችን ለማዘዝ ፈቃዳችንን ይሻል። ደጃፋችንን ሲቆረቁር ካልከፈትን፣ ወደውስጥም እንዲዘልቅ ካልጋበዝን የመኖሪያ ልዕልና አይደፈርም። እዚያ ያልተገበርነው ነፃነት፣ እዚያ ያላስጠበቅነው መብት ... የት? በጎዳና የማይታሰበውን ሠላማዊ -ሠልፍ ከሣሎን እስከመኝታ ቤት እናካሂድ፤ለገዢዎች የፈራነውን ለልጆቻችንና ለትዳር አጋሮቻችን እንፈክር ቤታችንና ልጆቻችን የመጪው ዘመን እውነታ ማህደር ይሆናሉ ---...ቢያንስ።


......ቢያንስ ከዛሬ ጀምሮ.....


....እነሱ፣ ገዢዎቹ የሚጠላላ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሌት -ተቀን ይለፋሉ። እኛ የሚዋደደውን ማህበረሰብ ለማቆየት ቢያንስ በቤታችን ምን አደረግን? እራሳችንን እንጠይቅ! ሲለያዩ ፣ ያለመለያየት ዕቁብ ጠጣን? ሲነጣጥሉን ያለመነጣጠል ዕድርመሰረትን? ጠላት ሲያደርጉንበጋብቻ ተዛመድን? ሲያቃቅሩን የአነንድነት ፅዋ ማህበር አቋቋምን?.... ወይስ ዓይን-አባት ከብሔራችን አጨን? የጡረታ አባታችንን ከቀያችን ሙጥኝ አልን? ጉድፈቻ ከወንዛችን ፈለግን? ከጎሳችን አጨን? አማጫችንስ? ሸምጋያችንሽርካችንስ....ከጎጣችን? " እጃችሁን ስጡ " ስንባል እግራችንን ጨምረን ማስረከብ ማለት ይሄ ነው።

.....ቢያንስ ከዛሬ ጀምሮ.......

(( ዓለማየሁ ገላጋይ )))

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
.....ቢያንስ ከዛሬ ጀምሮ .......


.....ፓለቲካዊ ክፉ ሥራን ፣ በኢትዮጵያዊ ጨዋ ተግባር እንቃወም። ፋታ ያጣውን አናራውጥ፣ ኑሮ የከበደውን አንጫን ፣ መግቢያ የሌለውን መድረሻ አናሳጣ ፣ ጊዜ የጣለውን አንርገጥ ፣ ከከሰረው አናትርፍ ፣ የወደቀው ላይ " ምሣር " አንሁን .....የዚህ ዘመን ፓለቲካ "እርስ - በእርሱ" ላይ የተመሰረተ ነው። መጣደፍን ሲፈጥሩልን እርስ በእርስ እንረጋገጣለን ፣ ጠላትነትን ሲያቀርቡልን እርስ በእርስ እንባረራለን ፣ እጥረት ሲያመጡልን እርስ በእርስ እንነጣጠቃለን ፣ ጥርጣሬ ሲዘሩብን ጠላትነት እናበቅላለን ፣ " ጃስ " ጥለን እንነካከሳለን ፣ ሲያጋጥሙን እንቧቀሳለን.....


......ቢያንስ ከዛሬ ጀምሮ.....

....ቤታችን ፣ ልባችን ፣ መንፈሳችንና ነፍሳችን ከዚህ ይፅዳ። ነጋዴ ነን? አላግባብ አናትርፍ ፣ አከፋፋይ ነን? ብሔር አንወክል ፣ አርቲስት ነን? ዘር ከዘር የሚከፋፈል ድግስ አናድምቅ ፣ አሰሪ ነን? ሥራን ብቻ ማዕከል እናድርግ ፣ ቤት አከራይ ነን? ለተከራይ እንዘን ፣ ገበሬ ነን? ሰው በቆርቆሮ ቤት አንቀይር ፣ ኮንትራክተር ነን ? ጥራት አንቆነጣጥብ ፣ ጋዜጠኛ ነን? ለሕዝብ ብቻ እንቁም ፣ የሕግ ባለሙያ ነን ? ፓለቲካ አንቀላቅል ፣ የምክር ቤት አባል ነን ? በእንቅልፍ ልብ እጃችንን አናውጣ..........


..... ዛሬ ...ዛሬ.....


.....እውነታው ተገልብጧል። ሌባ ይንጎባለላል ፣ ተዘራፊ ያፍራል። የቀማኛ ልጅ ደረጃ አግኝቷል ፣ በላቡ የሚኖር አባት ያለው መግቢያ አጥቷል። አደባባይ የነውረኞች ሆኗል ፣ ጨዋ መሸሸጊያ ጓዳ አጥቷል። አገሪቱ ከነውር የተገነባ ጎጆ ሆናለች። አድርባይ ጉልላት ፣ አላዋቂ ክፍክፋት ፣ ወሮበላ መርገፍ ፣ አልጠግብ ባይ ደጃፍ ....ሆነዋል።የዚህ ዘመን መሠረት ግን እኛ ነን። እንዴት ?



እንዴትማ .....የመኖር ዋስትና ከማረጋገጥ በላይ የሚከማች ሀብት ሁሉ በማህበረሰብ ዘንድ የተሻሉ ሆኖ የመታየትና የመከበር ፍላጎት ነው። "የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው " ሆነናል የሀብት ጀርባ ማጥናት ትተናል። ለሌባ እንጎናበሳለን ፣ ለቀማኛ ወንበር እንለቃለን ፣ ለዘራፊ እንሽቆጠቆጣለን። ሌብነት እንደማሳለጫ የማቋረጫ መንገድ ብቻ ሆነ።


.....ቢያንስ ከዛሬ ጀምሮ ...

....ሌባን ማቆላመጥ ይቅር ፣ አይናችን ይብላው ፣ ሚስቱ ፊት ይሸማቀቅ ፣ ልጁ ፊት ይሳቀቅ ፣ አማት ደጅ አይድረስ ፣ ከሰው ጋር አይቁረስ .... ቤታችን ፣ ልባችን ፣ መንፈሳችን ፣ ነፍሳችን.... ብሎም አገራችን የሚፀዳዉ እንዲያ ነው። ያልተገባን ባደባባይ ባይቻል በኑሮ በመቃወም

((( ዓለማየሁ ገላጋይ )))

:-መለያየት ሞት ነው (( ገፅ 26 - 27 ))


አበቦቼ ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ ትሁንላቹ!!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ፈላኪው ( አስትሮኖመሩ )


ከወዳጄ ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ሄድን። ለብቻው ተነጥሎ የተቀመጠ አንድ ዐይነ ስውር አሳየኝና " የአገራችን ታላቅ ጠቢብ ሰው ያውልህ " አለኝ።

እኔም ወደ ዐይነ ስውሩ በመሄድ ሰላምታ ካቀረብኩለት በኃላ ተጨዋወትን። ከአፍታ በኃላም " ይህንን ለመጠየቄ ይቅርታ አድርግልኝ - ግን ከመቼ ጀምሮ ነው ብርሃንህን ያጣኽው?" ስል ጠየቅሁት።

" ስወለድ ጀምሮ " መለሰልኝ

" የትኛውን የጥበብ መንገድ ተከተልክ " ጠየቅሁት።

እርሱም " ፈላኪ ነኝ አለኝ። ከዚያም እጁን ደረቱ ላይ ደረቱ ላይ አድርጎ " እነዚህን ሁሉ ፀሐዮች ፣ ጨረቃዎችና ከዋክብት እመለከታለሁ " አለኝ።


((( ካህሊል ጂብራን ))()(

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ መንግስት ስለተመቸን ህዝብ ይቀየርልን 😀😀
ከታሪክ የምንማረው ከታሪክ መማር አለመቻላችንን ነው፡፡" (ሄግል)
ልተኛ ብል እንቅልፌ እንዴት ይምጣ? እንዴትስ እንቅልፍ ይመጣል ያንን ምስል ተመልክቶ? እንደው ሰው መሆን ብቻ በቂ አልነበረምን?
ፈጣሪ አበጃጅቶ የፈጠራትን ነፍስስ ለማጥፋት ስልጣኑን ማን ለሰው ሰጠውና ነው??? ኧረ ወዴት እየሄድን ነው???
ዛሬ በሻሸመኔ የተደረገው ድርጊት እጅግ ያሳፍራል፤ እጅግ ያማል፤ እጅግም ይሰቀጥጣል፡፡ ሰው ካጠፋ ለህግ ማቅረብ ያባት ሆኖ ሳለ
ይሄኛው ግን በምንም መስፈርት ትክክል ያልሆነ ተግባር ነውና ማንም ሰው ነኝ የሚል ሁሉ ሊያወግዘው የሚገባ አስነዋሪ ድርጊት ነውና
ሳይቃጠል በቅጠል መመከርና መዘከር ያለበት አካል ይመከር፣ ይዘከር፡፡ አጥፊዎችም በቶሎ ለፍርድ ይቅረቡ፡፡ ፈጣሪ የወገናችንን ነፍስ
በሰላም ያሳርፍ!
ሰብዓዊነት ይቅደም!
የህግ የበላይነት ይከበር!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ስሟ መአዛ ነው! ወድጃታለሁ! መውደድ ብቻ አይደለም አፍቅሪያታለሁ!
ልነግራት ከወሰንኩ ቀናት ተቆጥረዋል! ዛሬ ጥዋት ፌስቡክ ስገባ ኦንላይን
ተገስጣለች... ነገርኳት! አፈነዳሁት! መልሷን ማየት ስለከበደኝ ገና
እየፃፈችልኝ እያለ ከፌስቡክ ዘልዬ ወጣሁ!
...
ቀኑን ሙሉ ሳስባት ዋልኩኝ! ስበላ... ስጠጣ... ስቀመጥ... ስንቀሳቀስ...
በእያንዳንዷ እርምጃዬ ውስጥ ልረሳት አልቻልኩም!
...
ምሳ ከበላሁ በኋላ ተመልሼ ወደ ፌስቡክ ገባሁ... ፌስቡኬ 1 Message
እንዳለው ያሳያል... ልቤ ድው ድው ማለት ጀመረ... ሜሴጁን ልከፍተው
ጣቶቼን አንቀሳቀስኩ... ግን አቅም አጣሁ... ፌስቡኬን ዘጋሁ!
...
ማሰቤን ቀጠልኩ! ምን ብላኝ ይሆን?!... ላስብበት ብላኝ ይሆን?... የፍቅር
ጥያቄዬን ተቀብላኝ ይሆን?... እራቴን በልቼ ተመልሼ ፌስቡኬን ከፈትኩ!
በፍርሀት በሚንቀጠቀጡ እጆቼ ሜሴጁን ከፈትኩት...
...
የማየውን ማመን አልቻልኩም! ሜሴጁ ቃል በቃል እንዲህ ይላል...
"Tesfaye Bedasa Just joined a messenger..."
መስጅሮ ይጣልህ አቦ የአባቴ አምላክ!
[Dagmawi Dagmawi]

@ethio_art
@wegoch
ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደዉ የሆሄ የስነ ጽሑፉ ዉድድርና ሽልማት ዛሬ ከቀኑ 12 ስዓት ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር ቤት ይካሔዳል፡፡ አዳራሹም ከ11-12 ስዓት ብቻ ክፍት እንደሚሆን ያገኘሁት መረጃ ይገልፃል፡፡ የምትችሉ ሰዎች እንድትታደሙ በሚል ነዉ መረጃዉን ያደረስኳችሁ።

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሰባት ጊዜ ወድቆ ሰባት ጊዜ መነሳት!!!!
በጣም ሊነጋ ሲል በጣም ይጨልማል!!! በጣም ጨለመ ተብሎ መንጋት አይመጣም ብሎ ሌላ የጨለማ ስራ መስራት የተስፋ ቆራጮች
እድል ነው ። እኛ ግን በሃገራችን ላፍታም ያህል ተስፋ አንቆርጥም ። የደረሰብንን ሁሉ ወደ ቁጭትና እልክ ለውጠን የተገኘችውን የተስፋ
ጭላንጭል ጨለማውን ለማንጋት እንጠቀምባታለን እንጅ ሊነጋ ባለው ጨለማ ውስጥ የተሰራውን የጨለማ ተግባር ሊመጣ ካለው ትልቅ
ብርሃን አስበልጠን አንተክዝም! !!! እውነት እልሃለሁ የተከሰቱት ጥቂት የጨለማ ተግባራት ሊመጣ ካለው የብርሃን ጎርፍ አንጻር ሲታዩ
በጽናት ፤ በእልክና በቁጭት የለውጡን ዘመቻ ይበልጥ እንድንጣበቀው የሚገፉ ማንቂያ ደወሎች እንጅ ወደ ሃላ የምንሰበርባቸው ድምጾች
አይደሉምና አሁንም አይናችንና ልባችን ሊመጣ ካለው ግዙፉ ብርሃንና ንጋት ላይ ትክ ብሎ በማየት የጨለማን ሃውልት ሊደረምስ ጉዞዎን
ቀጥሏል ። በዚህ ጥቂት የጨለምተኞች መንደር ውስጥ ልብና ነፍስያቸው ሞልቶ በሚፈስ ርህራሄ የተጠመቁ ሩህሩህና አዛኝኞች
እንደምድር አሸዋ መብዛታቸውን ባሰብን ጊዜ የንጋቱ ወጋገን ከሩቅ እየታየን አሁንም ሃገራችንን በተስፋ አይን እንራባታለን ። ከጨካኝ ልቦች
ይልቅ አልቃሻ ልቦች እንደ ሰማይ ክውክብት በበዙባት ሃገር ጭካኔ ከአፍታ ጀምበር ያለፈ እድሜ የለውም ። ለአፍታ ጀምበር እድሜ ብቻ
ለሚኖረው ጭካኔ ብለን ከትውልድ ትውልድ የሚሻገረውን ግዙፍ የተስፋ ሃውልት የምናፈርስ ጅሎች አይደለንም ። ዛሬም አይናችን
ተስፋችንና ተስፋችን በሆነችው ሃገራችን ላይ እንደተተከለ ነው ።
ሰባት ጊዜ ብንወድቅም ሰባት ጊዜ መነሳት እጣ ፈንታችን ነውና ዳይ ወደፊት ብለናል!!!!
ሻሎም!!!!!

ሸጋ ቀን ይሁንላችሁ!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
2024/09/30 19:36:40
Back to Top
HTML Embed Code: