Telegram Web Link
ኢትዮጵያ ምን ኣይነት ሽማግሌ ያስፈልጋታል?

ሳናውቅ የሰበርናቸው ድልድዮች ብዙ ናቸው፡፡… ይኼ
ድልድይ እግዜር ካደለን ነገ እኛም የምንሄድበት ይሆናል፡፡
የ60ዎቹ ትውልድ አውቆ ይሁን ሳያውቅ ከሰበራቸው
ድልድዮች አንዱ በሽምግልና ሥርዓት ማመን ይመስለኝ
ጀምሯል፡፡ የበቀልንበትን ስር መርሳት፣ ተኮትኩተን
ያደግንበትን ሥርዓት መዘንጋት…
ድልድዩ ተሰብሯል ያልኩት በድልድዩ የሚመላለሱ ሰዎችን
በማጣቴ ነው፡፡ ድልድዩ ስለተሰበረ በሕዝብና በመንግሥት
መካከል ያለው ክፍተት በየጊዜው እየሰፋ ነው፡፡ ጥቂቶቹ
ድልድዩን ተሻግረው ወደዚያኛው ዓለም ለመቀላቀል ሲዘሉ
ይሳካላቸዋል፡፡ ጥቂቶቹ ደግሞ ተሰናክለው ይወድቃሉ፤
ወንዙም ይወስዳቸዋል፡፡ አብዛኞቹ ግን አትድረስብኝ
አልደርስብህም ተባብለው ያሉ ናቸው፡፡ …
በዚህም የተነሳ ብዙ ነገር አጥተናል፡፡ ሕዝቡም
መንግሥቱም ጎድሎበታል፡፡ ወደኋላ ለመቅረታችንም የራሱ
የሆነ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ ምነው ቢሉ ሕዝብ በአንዳች ነገር
ቅያሜ ሲገባው አቤት የሚልበት መድረክ የለውምና፡፡
እናንተ እያላችሁ እንዴት እንዲህ እንሆናለን? ብሎ ብሶቱን
የሚያሳስብበት ምኩራብ የለውም፡፡
ያም ሆኖ ሕዝብም መንግሥትም ሊያውቀው የሚገባ
አንድ እውነት አለ ብዬ አምናለሁ፡፡ እነዚህ ሽማግሌዎች
የሚሰባሰቡበት አንድ ጉባኤ ቢኖር፣ አባላቱ ለሹመትና
ለሽልማት ሳይሆን፣ ወድቆ ለተነሳው ባንዲራ ክብር ሲሉ
እውቀታቸውንና ቀሪ እድሜያቸውን ለመክፈል ዝግጁ
ሆነው ቢገኙ፣ ብዙ ቀዳዳ ይደፈናል፤ ብዙ ጉድለት
ይከደናል፤ ልክ እንደ ሦስተኛ ዐይን ይሆኑልናል፤
በቸልተኝነት ወይም በዝንጋዔ ብዛት ወይም በሥራ
ውጥረት ምክንያት ያላየናቸውን እንድናይ ያደርጉናል፡፡
የማንበብ ባህል ባልተንሰራፋበት፣ የግል ፕሬሶች
በመዋከብ፣ በመታሰርና በመሰደድ እድሜያችንን ፈጀነው
በሚሉበት በአሁኑ ዘመን፣ ሽማግሌዎች በሕዝብና
በመንግሥት መካከል ያለውን ገደል በደለል እንዲሞላ
አድርገው ዐይን ሆነው ያዩናል፤ ያዩልናል፤ ያስተያዩናል፡፡
…በደርግ ዘመን የአብዮት ችቦ ተቀጣጥሎ፣ እራሱንም
ሌሎችንም መፍጀት ሳይጀምር በፊት፣ በአንዳንድ
መኮንኖች … በንጉሡ የስልጣን መዋቅር ውስጥ ከነበሩና
ገለል የተደረጉ ግን አሁንም መለስተኛ ተደማጭነት
ያላቸውን ለማነጋገር ሙከራ አድርገው ነበር፡፡ ከእነዚህ
መካከል አንዱ ደጃዝማች ግርማቸው ተክለሃዋርያት
ናቸው፡፡ ደጃዝማቹ አርአያ በተሰኘ ልቦለድ መጽሐፋቸውና
ቴዎድሮስ ታሪካዊ ድራማ በተሰኘ ተውኔታቸው እውቅና
ያተረፉ ናቸው፤ ትምሕርታቸውን ያጠናቀቁት ፈረንሣይ
አገር ነው ፤ በእርሻና በማስታወቂያ ሚኒስትርነት ማዕረግ
ሲሰሩ ቆይተው፣ በዘውድ አማካሪነት ማገልገል
በጀመሩበት ዘመን ሁለት መኮንኖች ወደ ቤታቸው አመሩ፡፡
ከመኮንኖቹ አንዱ የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፣
ከግራዝማቹ ጋር ስላሳለፉት ቆይታ ምስክርነት ሲሰጡ፣ ‘…
በጥንቃቄ ካዳመጡን በኋላ - የጭን ገረድ ምን እንደሆነ
ታውቃላችሁ? አሉን፤ በአገራችን ባህል ሲያስፈልግ
እንደሚስት፣ ሲያሻም እንደ ሠራተኛ የምታገለግል ናት፤ ያ
ማለት እኔ ነኝ፡፡ አንድ ጊዜ ሚኒስትር ነበርኩ፤ አሁን ደግሞ
ችላ ተብዬ በአማካሪነት አለሁ፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ ሥራ
የለኝም፡፡ የሚያዳምጠኝም የለ፣ ንጉሱንም አልፎ አልፎ
ነው የማገኛቸው - በማለት ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ ረዘም
ያለ ንግግር ካደረጉልን በኋላ - እኔ በአዝጋሚ ለውጥ
እንጂ በአብዮት አላምንም፤ ለእናንተ ለወጣት መኮንኖች
የምሰጣችሁ ምክር፤ በስሜት እንዳትገፋፉና ረጋ እንድትሉ
ነው!’ ማለታቸውን የደም ዕንባ በተሰኘ መጽሐፋቸው
አስፍረዋል፡፡
መኮንኖቹ ምክር ጥየቃና መፍትሔ ፍለጋ ሽማግሌ ዘንድ
ማቅናታቸው ደግ ነው፡፡ የሽማግሌውን ምክር ሰምተው
ለመተግበር የነበራቸው ሞራል ግን የቀዘቀዘ ነበር፤ እናም
ሽማግሌው የፈሩት አልቀረም፡፡ በስሜት ተገፋፍተው
ማንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ እንዲሆን የማይመኘው
ሁሉ ሆነ፡፡ ምክር አቋዳሽ የሆኑት እኚህ ሰውም በዘውዱ
ሥርዓት በነበራቸው ስልጣን ምክንያት ለሰባት ዓመታት
ያህል ታሰሩ፤ ደም ፈሰሰ፤ ያለፍርድ መገደል፣ ማስገደልና
መገዳደል የአብዮቱ መለኪያና መታወቂያ ሆነ፡፡
ቤተክርስቲያኑም ቤተ ሙስሊሙም እራሱን ለማዳን
ይሯሯጥ ገባ፤ ተቋማት በዝምታ ተዋጡ፤ አልበዛም እንዴ
ለማለት አቅም አነሳቸው፤ እና ያ እንዳይደገም የምንለው
ነገር ሁሉ ሆነ …
ሽማግሌ የለንም!

((( እንዳለጌታ ከበደ )))

እናንተስ ምን አይነት ሽማግሌ ያስፈልጋታል ትላላቹ..?

ኢትዮጵያን ከችግር እና ካለመረጋጋት አዙሪት እንዴት
እናውጣት ?

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ታሪክን አንካድ! አጤ ምኒሊክ ጡት አስቆርጠዋል !
( ናትናኤል ጌቱ )


"ምን ግዜም ቢሆን ታሪክን ባንክድና ካለፈው ታሪክ እየተማርን ብንሄድ
መልካም ነው ።
ያለፉትን ነገስታት እንደ መልአክ ለመቁጠር ሲባል ብቻ ይህን
አድርገዋል ያን ግን አላደረጉም እያሉ ማንም የሚያውቀውን ታሪክ
መካድ አግባብ አይደለም! ! "
መሀል ዘማች ደባልቄ እንዳሻው አንቱ የተባሉ የሰፈራችን የእድሜ
ባለጠጋ ናቸው ። ይህን ማንም ያውቃል ። የእድሜያቸው ቁጥር ከሶስት
አሀዝ የበለጠ ብቸኛው አዛውንት ናቸው ። ከዘመነ መሳፍንት ዘመን
በፊት ስንት ሺ አመት ጀምረው እስካሁን በህይወት ያሉ ባለ ብዙ ታሪክ
አዛውንት ናቸው… ማን? መሀል ዘማች ደባልቄ እንዳሻው!
እኔም ታድያ የሚሉትን ለመስማት ጓጉቼ
"እውነት እንደሚባለው አጤ ምኒሊክ ጡት አስቆርጠዋል?" ስል
ጠየኳቸው ።
"እንደተባለው ባይሆንም አጤ ምኒልክ ጡት አስቆርጠዋል! ይህ
የተከናወነና የማይፋቅ ሀቅ ነው!" አሉኝ ቅጭም ብለው። ቀጥለውም
"አየህ አጤ ምኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ አድርገው ለማስተዳደር ሲሉ
በየቦታው እየዞሩ ያስገብሩ ነበር ። አሁን ጡት ተቆርጧል የሚባልበት
አካባቢ ላይም ህዝቡ አልገብርም ብሎ ገጠማቸው ። ተደጋጋሚ
ጦርነት ከተደረገ በኋላ ምኒልክ አሸነፉ ።
ሁኖም ግን አንድ ነገር ጨነቃቸው ። ምኒልክ ህዝብ ከህዝብ
እንዲዋለድና ወታደሮቻቸውም በየቦታው በዘር እንዲተሳሰሩ ፍላጎት
ነበራቸው ። በዚህ ምክንያት የንጉሱ ጭንቀት የገባቸው ወታደሮች
በአካባቢው ወዳሉ ሴቶች ተሰማርተው ጡት ቆረጡ "
"ጡት ቆረጡ? " አልኩ ።
"አዎ ጡት ቆረጡ ። መካድ አያስፈልግም ።" አሉና
"ግን ቆረጡ የሚለው አማርኛ የነበረው ፍቺ እንዳሁኑ አይደለም ።
ቆረጠ ፣ ቆረጡ የሚለው ቃል አዎንታዊ ፍቺ ነበረው ።
ለምሳሌ ለረጅም ግዜ ውሀ ጠምቶት ድንገት ጥሙን ያረካ ሰው '
እሰይ! ጥሜን ቆረጥኩ ' ሊል ይችላል ። ጥሜን ቆረጥኩ ሲልጥሜን
አረካሁ ፣ ጠገብኩ ማለቱ ነው ። በወቅቱ ቆረጥኩ መጥፎ ቃል
አልነበረም ። በዚያ ግዜ አንድ ሰው ተስፋ ቆረጥኩ ካለ ራሱ ተስፋ
አገኘሁ ማለቱ ነበር እና የምኒሊክ ወታደሮች ጡት ቆረጡ ሲባልኮ
ይኸ ምንድን ነውሳ ያሁን ልጆች የምትሉት " ቀና ብለው ካሰቡ በኋላ
"አዎ…ዎርማብ! ዎርማብ አደረጉ ማለታቸው ነው "
መሀል ዘማች ደባልቄ እንዳሻው ለጥቂት ደቂቃ ተከዙና "አይ አማርኛ!
እንደቆረጡሽ ትቆረጫለሽ! " ብለው ተረቱ
"መምሬ አብደላ" ከተሰኘ የልብወለድ መፅሀፍ ተቆርጦ የቀረበ !

ገና ርዕሱን አይተው ሳያነቡ ስድብ የሚኮምቱትንና
ቢያነቡም ባያነቡም የሚሳደቡትን በብሎክ ወገብ ዛላቸውን
እቆርጣለሁ ( አልቦልክም መብታቸው ነው ማለቴኮ ነው )

@wegoch
@wegoch
@wegoch
☝️☝️☝️ ከላይ ያለው ፎቶ ያመራምራል መሰለኝ??? ብዙ ጥያቄዎችም ይወጡታል ?እስቲ ፎቶውን እዩትና የተሰማቹን ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል ለናንተ ምን አይነት ጥያቄ ወይም ሀሳብ ፈጠረባቹ..??

ሸጋ ሸጊቱ ምሽት!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ወግ ብቻ
☝️☝️☝️ ከላይ ያለው ፎቶ ያመራምራል መሰለኝ??? ብዙ ጥያቄዎችም ይወጡታል ?እስቲ ፎቶውን እዩትና የተሰማቹን ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል ለናንተ ምን አይነት ጥያቄ ወይም ሀሳብ ፈጠረባቹ..?? ሸጋ ሸጊቱ ምሽት!!!! @balmbaras @wegoch @wegoch
ከተሰጡ ሀሳቦች እና እይታዎች በጥቂቱ👇👇👇


Yuye G/Hiwot:
ደስተኛ ለመሆን የግድ ከሌሎች የበለጠ ነገር እንዲኖረን መጠበቅ የለብንም ባለን ነገር ደስተኛ መሆን ከምንም በላይ ነው....ምናልባት እኛ የስኬት ጥግ ነው ብለን የምናስበው ቦታ ላይ የደረሱ ሰዎች እንኳን የኛን ያህል ደስተኛ ላይሆኑ ይችላሉና....ስለዚህ አንደኛ ወጥቶ እንደሚያለቃቅሰው ልጅ ከመሆናችን በፊት ባለን ነገር ላይ ደስተኛ ሆነን ለተሻለ ነገር መትጋቱ አዋጭ ነው ባይ ነኝ🙏

Fafi G:
"ከእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል" የሚሉት አበው ይሄንንም አደል። ሲለጥቅ ደሞ...የትኛው ታሪክ ላይ ነበር......ከባለጠጋው ደጅ ላይ ያገኛትን ትርፍራፊ እየበላ በደስታ የሚተኛው እና ባለጠጋው ያን ሁሉ ሀብት ተሸክሞ እንቅልፍ የሚያጣው።ከቅዱሱ መጽሀፍም መሰለኝ።ብቻ በዝንጉእ ህሊናዬ እኒህ ታይተውኛል።

Kenean:
Ene yeteredawet leju andegna biwetam gin be lejitua desta destegna ayedelem😏 bizu giza lejoch laye yeha neger bayetayem👼 neger gin andande sewochi bealem laye enesu becha destegna mehone new mefelegut🧟‍♂ lejitua gin sostegna bitewetam berasua wetate destegna nachi🙋‍♀ andegna bewetaw lije aletenadedechem nethsu na destegna leb new yalate❤️

Willow 🌴:
Yemtadu eyale ye enkbu tentata

Hassen Dawed:
ሰላም ወዳጄ

ባሁን ግዜ የደረስንበትን እውነታ ነው ያስገነዘበኝ
በርግጥም እኛ ያልን ከሌሎች የተሻለ ሁኖ ሳለ በሌሎች ትንሽ ነገር ፊታችን መቅላቱ የተለመደ ባህሪ እየሆነ መቷል

1 ቁጥር የያዘው ቆዝሞ ስለታየኝ ነው

Tizta 🐣:
ምንም ነገር ቢኖርክ ምንም ሀያል ብትሆን
ምንም ነገር ላይ ቃዳሚ ብትሆን። ድሎች ሁሉ ያንተ ቢሆኑ ማጣጣም ካልቻልክበት አሜንን
ማታውቅ ከሆነ ሁልግዜም ቢሆን በስኬት ውስጥ ሀዘንክን ታየዋለክ።

ሌላው ከፎቶው የገባኝ ለመታወቅ ወይም ለክብር ብለህ ስታሸንፍና አምነክበት ለፍላጎትክ ስታሸንፍ ይለያያል።

አንደኛ የወጣው ይመስለኛል ላላመነበት አላማ ነው።
ሶስተኛ የወጣው ይመስለኛል የድሜ ልክ ህልሙ መንገዱን እየጠረገ መሆኑ ታውቆታል።


☝️☝️ በጥቂቱ ይሄን ይመስላል ሀሳባቹን የናንተን እይታዎች ላካፈላቹን በጣም እናመሰግናለን ሌሎቻቹም ፎቶውን የተረዳቹበት መንገድ ብትነግሩን ሸጋ ነው ....🙏🙏🙏


ሸጋ ሸጊቱ ቀን ይሁንላቹ!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
​​ጥቆማ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ይህን ፃፍክ ተብዬ ዛሬ ማታ ክልትው እንደማያረጉኝ ምን ማረጋገጫ
አለኝ?ምንም!ግን እፅፋለሁ። ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ
ላደረጋቸው አንፃራዊ ተግባሮች ላመሰግነው እወዳለሁ። ለወደፊትም አመሠግነዋለሁ። በኔ እምነት ነገሮች የሚዳኙት በአንፃራዊነት ነው። የሰማይን እርቀት የምለካው ለምድር ካለኝ ቅርበት ነው። ሴት የማገባው ወንድ ስለሆንኩ ነው። የምኖረው ለመሞት ነው።
የምሞተው ዘልአለም ለመኖር ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዶክተር አብይ ላሳዩት የምህረት እና የይቅርታ ሀሳብ መቶ ፐርሰንት እስማማለሁ። ምህረት እና ይቅር ባይነት ትልቅነት ስለሆነ። ነገር ግን
ይቅርታ ሲደረግለት ይቅር የማይልን ፣ ምህረት ሲሰጠው የማይምርን ሰው ሰው ስለሆንኩ አልምረውም ። ይቅር አልለውም። እዚህች ጋር በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተች አንድ ግጥም ላንሳ "የገደለን መግደል ፣ እንዳስተውክ አውቃለሁ ይቅር እንዳልለው ፣ እኔ አንተን አይደለሁ ወይ ውረድ ወይ ፍረድ ፣ እጎዳብሀለሁ።" ይላል። ታድያ ዶክተር አብይ እንዲሁም የስልጣኑ ተጋሪዎች የምህረት እና የይቅር እሳቤያቸው ቅዱስ ቢሆንም አለመፍረዳቸው ያረክሳቸዋል። አንድ በንግስና ላይ ያለ ሰው አንድ
ባሪያው ሀገር መሸከም የሚችልን ሰው ከገደለበት ከዚህ በላይ ምን ንቀት አለ። አንድ ሀገር የሚመራን ሰው አንድ ባሪያው የግድያ ሙከራ ካደረገበት ምን አይነት ይቅርታ ነው ሚሰጠው ? አምላክ ሳይሆኑ እንደአምላክ አክት ማድረግ ተገቢ አይደለም። ሰው ነህ ሰዎችህ
እንዳይጎዱ ፍረድ። በመቀጠል የሚሰማኝ ካለ ጥርጣሬዬን ልሰንዝር።
ኢንጅነሩ ከመገደሉ በፊት ዛሬ እና ትናንት በመስቀል አደባባይ ዙሪያ ያሉትን የመንገድ ካሜራዎች በእድሳት ሰበብ ነቅለዋል እየነቀሉም ነው የተባሉትን ተይዘው ቢመረመሩ። ካልጠፋ ቀን ትናንትና ዛሬ ምን አስነቀላቸው?
2 ያው አስክሬኑ ተመርምሮ በመርዝ ነው የሞተው ወይም በልብ ወይም የሰው እጅ በሌለበት በተለያየ ምክንያት ነው ። ሊባል ስለሚችል ፣ ወይም ከተባለ አስክሬኑን የመረመሩት ዶክተሮች ሞቱ ላይ እጃቸው ሊኖርበት ስለሚችል ውጤቱን አምኖ ከመቀበል ይልቅ
መርማሪዎቹ ተይዘው ቢመረመሩ ስል እጠቁማለሁ። በተረፈ ኢትዮጵያ
የድልብ ደነዞች መፈንጫ እንዳትሆን ምኞቴ ነው።

@wegoch
@wegoch
@lula_al_greeko
ላማሰበቅታኒ?
(ዘውዳለም ታደሰ)

በድምፅ አልባ ፀሎት
በእንባ አልባ ለቅሶ
ዳብሶ እንዲያነቃህ
ከእንቅልፍህ ቀስቅሶ
አልማፀን ነገር
“ዝም ብለህ ተቀበል”
ሆኗል የግዜር ነገር!
በገናዬን ጣሉ
ምንጣፌን ጠቅልሉ
የአቤል ደም ጩኸት
ስቦ እስኪያመጣው
ይኸው ..
ከመቅደሱ ወጣሁ!
እንደከንቱ አዝማሪ
ተቀበል ያለኝን ፥ ስቀበለው ኖሬ
ቅኔው ጎመዘዘኝ
ግጥሙ መረረኝ ፥ እንቢ ልበል ዛሬ!

ላማሰበቅታኒ?

@getem
@getem
@lula_al_greeko
(ዳግማዊ)

ቀኑን ሙሉ እንዲሁ ስራዬን መስራት አቅቶኝ ስናውዝ ዋልኩኝ! ምናልባትም በህይወቴ ውስጥ ካጋጠሙኝ መራር የሀዘን ወቅቶች አንዱ ነው!
...
ከጥቂቶች በቀር ሚዲያዎቻችን የኢንጂነሩን ነገር የዜና ማሟያ ከማድረግ በዘለለ ሊያወሩ የፈለጉ አይመስሉም... በኤፌሞቻችን ዳንከኪራ እየተደለቀ ነው!
... መንግስት መርፌ የጠፋበት ያህል እንኳን የደነገጠ አይመስልም! በበረሀ እየተንከራተተ ያገለገላት ሀገሩ ለሞቱ ቀን እንኳን ሰንደቋን ዝቅ ማድረግ አልፈለገችም...
...
አብቅቷል... ከዚህ በኋላ ኢንጅነር ስመኘው የሚባል ሰው ሩጫውን ጨርሷል! በጉባ በረሀ ላይ ከላቡ እያጠቀሰ የፃፈው የጀግና ድርሰት
ብቻ ለዘልአለም እየተነበበ ይኖራል!
...በመጨረሻም የዶክተር አብይ መንግስት "የቀን ጅብ"... "መግደል
መሸነፍ ነው" ምናምን የሚሉትን የቃላት ጨዋታ ትቶ ለኢንጅነሩ ደህንነት አስፈላጊውን ጥበቃና ከለላ ባለማድረጉ የጀግናውን ቤተሰብና የኢትዮጵያን ህዝብ ጎንበስ ብሎ ይቆርታ እንዲጠይቅ እጠይቃለሁ!

ነፍስህ በሰላም ትረፍ አባቴ! ደህና ሁን!!!

@wegoch
@wegoch
ሞት ስትሰማ ብርክ አይያዝህ!!
-------
ስሜታዊነት ጥሩ ነው፥መጥፎ ሚሆነው እኛን ሊያጠፋ
ሲነዳን ብቻ ነው። ሞተብኝ ብለህ ደም ለመመለስ
የምትመርጠው መንገድ አንተኑ ካጠፋ ደምህ ባክኗል
እንጂ ደም አልመለስክም። ሲሞትብህ ከረጋህ ርስት
ጉልት ትቀማለህ። ቀየውን ያንተ ብቻ ታድርጋለህ። ገዳይ
መቅኖ ኖሮት አያውቅም፣ገዳይ አገር ኖሮት አያውቅም።
ሞተብኝ ብለህ ለመግደል አትሩጥ፣ ይልቁን ገዳይህን
ከርስት ጉልቱ ነቅለህ መጣያ መንገድ ፈልግ!! ደም
ስትመልስ ብልጥ ሁን፥ ከእጅህ ሳይሆን ከማስተዋልህ
ቸኩል፣ ከብልጥነትህ ፍጠን። ገዳይ አገር ምድሩን ጥሎ
ብን እንዲል አውጠንጥን።
------
የትልልቆቹ ሃገራት የትልቅነት ታሪክ ብዙ ደም ነው። ሞት
ስትሰማ እንደ ግሪሳ ወፍ ግርርርርር አትበል! እንደ መንጋ
ከብት አትጓጉር!! ለቀስተኛና ፈሪ ድል ኖሮት አያውቅም።
ስለሆነም ከትናንት ስህተት መማርና በስህተታችን መንገድ
ባለመቆየት መታተር እንጂ ዋይታ የለም!!
------
እልፍአእላፍ እኛ ባለንበት አገር ወይኔ አገሬ ፈረሰች ይሉት
መንቦቃቦቅ ከወንድ አይጠበቅም!!
---
እዳው ገብስ ነው!!

((( ያሲን መሀመድ ))

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
For Daily motivational quotes and messages
join👇👇
@Words19
@words19
@Words19
የመረጃ ባህል! !!!!

ጸሃፊው ፤ ""በሬ ወለደ ብሎ ይጽፋል!!!!!""
አንባቢው ፣ ""አዎ ወተቱን ጠጥቻለሁ ብሎ comment
ይሰጣል ።
አለመታደል ነው!!!!

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
ዲያስፖራ!!!!

በ3 ደቂቃ ውስጥ የተሟላ ሃሳብ ያለው ጥያቄ ማቅረብ
ይከብዳል ። የደቂቃዋን ማለቅ እየሰጉ ረብ ያለው ጥያቄ
ለመጠየቅ የቻሉ አይመስልም ። በዚያ ላይ መድረክ
መሪው ሃሳብ አያስጨርስም ። ሰፊ እድል ከሌለ ሰፊ ሃሳብ
ማዳመጥ ያዳግታል!!!!

ሸጋ ምሽት !!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ዲያስቦራ ተዘረረ!!!!


""""...ጉድ በል የቶቢያ ህዝብ!!!!! እነ ይሃደግ ፎሊሲ
ምናምን እያሉ አያደናግሩህ ። አንተ ራስህ ፎሊሲ ነህ ።
ብቻ የኢቶብያ ህዝብ ሆይ! አንተ ብቻ ጭክን ብለህ
ድምጥህን ነይተህ ስጠን። እኛ ይሄ ነው ይሄ ነው ብለን
ቃል የምንገባልህ ነገር የለም! አንተ ብቻ ተኮሮጆው ዘንድ
ድምጥህን ዱልልን ። ካርዷን ተዶልክልነ በሃላ አንተው
ራስህ ነገሩን ታንጠባርቀዋለህ ። እስተዛ ድረስ
ምልክታችን ድስት ነው ሽንኩርቱን እያቁላላህ ጠብቀን! !!!
ወጡን አብረን እንሰራለን ። እኛን ተመረጥከነ የሰራሃውን
ወጥ በማኛ እንጀራ ተኛ ጋር ትበላለህ ።ታልመረጥከነና
ካርዱን የማትዶል ተሆነ ወላሂ ተቀብራችን አትቆምም
እኛም ተቀብረህ አንቆምም ብሎ ፓርቲውን ያስተዋወቀው
ቦተሊከኛ ሰውየ የዛሬውን የዲሲ ጉባኤ ተመልክቶ ምን
ቢል ጥሩ ነው??
@@ እንዲህ ከሆነማ ቀጣይ ምርጫ ላይ ዲያስፖራን
ዘረርናት ማለት ነው !!!!@@


በሞትኩት ትላለች እናቴ!!
USA የከተመው የፖለቲካ ሱፋም ሁላ ሃሳብ የለሽ
ውሽልሽል ነው ለካ?እኝክ ይላል የወሎ ሰው!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ኢትዮጱያዊነት ይባላል የሰፈረብን ጋኔል
ታማኝ በየነ ፤
በኢትዩጲያዊነት ምትሃት የተለከፈ ጀግና!!!!!!!የኔ ጀግና
ነው!!!
ጸረ ዘረኝነት ክትባት ይዞ የሚዞር መዳኒተኛ!!!
ዶክተር አብይ! !!!!!!!
ግፋ ወደፊት! !!!!!!
ያለ ፈተና ውጤት የለም!!!!!!
ጓዴ ትሰማኛለህ!!!! ይኸንን ሰውየ ካለማድነቅ ይልቅ
አድንቆ መሳሳት ይሻለኛል የምልህ ወድጄ
እንዳይመስልህ! !!

@balmbaras
@Wegoch
@wegoch
👼🏻🌞እግዜር በሽታ ይስጣችሁ!!!🌞👼🏻

ርዕሱ ግራ ያጋባል አደል?!አዎ ልክ ናችሁ።ለማለት የፈለኩት "እግዜር በሽታ ይስጣችሁ ነው"ማንበባችሁን አታቁሙ።
ከናንተ ውስጥ በሽታ የሚጠላ አለ? ለምን? እስቲ ቆም በሉና አስቡት! ሰው ያለበሽታ እንዴት መኖር ይችላል?! እኔ ግን በሽታ ጥሩ ነው ባይ ነኝ! ለምን? ጥሩ ጥያቄ ነው።በሽታ ባይኖር ኖሮ ሰው ሁሉ የሚሞተው ያለማስጠንቀቂያ በድንገት ነበር። ስንታመም እኮ ሰውነታችን የሆነ ምልክት እየሰጠን ነው።የሆነ ትክክል ያልሆነ ነገር አለ ማለት ነው።ስለዚህ የጤና ባለሙያ ጋር ሄደን እንታይ እና ማስተካከያ (Diagnosis) ይሰጠናል።በዚህ ምክንያት ዳግም ህይወት ዘርተን መኖር እንቀጥላለን ማለት ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ ግን በማንኛውም ሰዓት ልንሞት እንችል ነበር።ወደ ስራ ስንሄድ፣ወደ ት/ት ስንሄድ፣ወደ ቤ/ክ፣ዘመድ ጥየቃ፣ወደ ቀጠርናት ፍቅረኛችን...ስንሄድ ፈንግል እንደያዛት ዶሮ መንገድ ላይ እንቀር ነበር።"እንደወጣ ቀረ" የሚለው አሳዛኝ ዜናም ለጆሮሯችን ባዳ አይሆንም ነበር።ምግብ ስለሰጠኸኝ፣ጤና ስለሰጠኸኝ፣ልጅ ስለሰጠኸኝ...ብቻ ሳይሆን በሽታ ስለሰጠኸኝም አመሰግንሃለሁ ማለት መቻል አለብን።ምክንያቱም በሽታ የማንቂያ ደወል ነውና።ማር ይስሐቅ የተባሉ በጣም የተከበሩ መምህር በመጽሐፈቸው "ድውይ እና በሽተኛ ስላደረግኸኝ አመሰግንሃለሁ በሉ" ብለው ነበር። ለምን ሲባሉ " ያ ባይሆንማ ምንም ሳልዘጋጅ ንስሐ እንኳን ሳልገባ እሞት ነበር።"ብለዋል።ስለዚህ ስንታመም ተጠቀምን እንጂ አልተጎዳንም።
የበሽታ ሌላውን አዎንታዊ(positive) ጎኑን ደግሞ ላሳያችሁ።አቅምን ያሳውቃል! ሰው በተፈጥሮው የመጣበትን፣ ትናንቱን የመርሳት ችግር አለበት።ትናንት የሚበላው አጥቶ፣የሚለብሰው ቸግሮት በየመንገዱ ሲንከራተት የነበረ ሰው "ጊዜ ጌታ" ነገሮችን ለውጦለት ሁሉም ሲስተካከልለት ከታቹ ያሉትን መርገጥ፣ልቡም ማበጥ ይጀምራል።አንዳንድ ሰው አይታችኋል... በገንዘብ እና በጡንቻው ሁሉንም ነገር ለማድረግ ሲሞክር?! እንደነዚህ አይነት ሰዎች ፈጣሪን ለማስታወስ ጊዜ ይወስድባቸዋል።በጠና የታመሙ እለት ግን የመድኃኒት አይነት ሞክረው፣ሆስፒታል አዳርሰው መፍትሔ ሲያጡ የሚጠቀሟት የመጨረሻ ቃል "ጌታ ሆይ እንደቸርነትህ ማረኝ" የምትል ነች።ስለዚህ እነዚህ ሰዎች አቅማቸውን እንዲያውቁ፣እግዚአብሔርንም እንዲያስታውሱ "በሽታ" አስተዋጽኦ አላበረከተም?!
በሽታ ትእቢተኛውን ዝቅ ያደርገዋል፤እግዚአብሔርን ያሳስባል(ብዙ ሰው ጸበል የሚሄደው ሲታመም አደል?!)፣ የነገሮችን ዋጋ(price) ሳይሆን ክብር(value) ያስመለክተናል፣ጸሎተኛና አመስጋኝ ያደርገናል፤አመስጋኝ ማለት ለተሰጡን በረከቶች (natural gifts) ማመስገን መቻልን ያስታውሰናል።ለምሣሌ፦ የአየርን ጥቅም እና በነፃነት የመተንፈስን ስሜት አስም በሽታ ካለበት ሰው በላይ ማን ሊረዳው ይችላል?!እግራችሁ ምን ያህል እያገለገላችሁ እንደሆነ የምታውቁት ስብራት እና ወለምታ ሲመጣ አደል? የታክሲ ሳንቲም ጠፍቶ ኪ/ሜ በእግር እንዳልተሄደ "መቼ ነው ተሽሎኝ እንደሰው የምራመደው?" ብላችሁ አልተመኛችሁም? በነፃነት የመብላትንና የመጠጣትን እርካታ ጉሮሮው ወይም ጥርሱ ከታመመበት ሰው በላይ ማንም ሊ�ረዳው አይችልም።ፈጣሪ በነጻ የሰጠንን እነዚህን አካላት ጥቅማቸውን የምናስተውለው ስናጣቸው አልያም ሲታመሙብን ነው።
ስጠቀልለው በህመም በበሽታ ስንያዝ ማማረር፣ማዘን፣ተስፋ መቁ�ረጥ ሳይሆን ማድረግ ያለብን ከልባችን እግዚአብሔርን ማመስገን ነው።ለእኛ ከእኛ በላይ እግዚአብሔር ያስባል።የማይጠቅመንን ነገር በፍጹም አይሰጠንም።ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እንዳለው "ስለተሰጠን ነገር ብቻ ሳይሆን ስላልተሰጠንም ነገር እናመስግን።"

@Fafi_G21
@wegoch
@wegoch
ንባብ ለህይወት በአዲስ መልክ ከሐምሌ 26
ጀምሮ ይካሄዳል


በየዓመቱ ክረምት ወቅት ላይ የሚካሄደው
ንባብ ለህይወት የእወቀትና የንባብ ሳምንት
ዘንድሮም የተለዩና አዳዲስ ሃሳቦችን አካቶ
በአዲስ አበባ ኢግዚቪሽን ማዕከል ይካሄዳል።
ላለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት የተካሄደው
ይኸው የንባብና የእውቀት ሳምንት እንዳለፉት
ዝግጅቶች ሁሉ ዘንድሮም የዓመቱ ብዕረኛ
የሚሸለም ሲሆን፤ ከ200 በላይ አሳታሚዎችና
መጽሐፍት አከፋፋዮች ስራዎቻቸውን ለአምስት
ቀናት በሚቆየው ኢግዚቪሽን ላይ ይቀርባሉ።

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ደማቂቱ!!!!!!


ከዚህ ሁሉ የባንዲራ ጋጋታ አሁንም ደምቃ የምትታየው
ያች የአባቶቼ ባንዲራ ናት!!!!! ከሰማይ ቀለም
የተቀዳች ናትና!!!!!
የኔ የጦቢያ አርበኞችና ጀግኖች ፤
እነ ባልቻ አባ ነፍሶ ፤ አብዲሳ አጋ ፤ ሃብተ ጊወርጊስ
ዲነግዴ፤ ጎበና ዳጩ ፤ ጄኔራል ጃገማ ኬሎ
.........ዛሬ እንኳ ከመቃብራቸው ላይ ሆነው
ባንዲራችሁ የትኛዋ ናት ተብለው ቢጠየቁ የትኛዋ
እንደሆነች አሳምረው ያውቋታል!!!!!
የኦሮሞው ባላባትና ባለ ርስት የሆነው የበጋው መብረቅ
ጄኔራል ጃገማ ኬሎ በህይወት ሳለ ደርሸበት ስለዚህች
ባንዲራ ገድል ባይነግረኝና ባይመሠክርልኝ ኖሮ
ይቆጨኝ ነበር!!!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሲጠቃለል!!!!

የዶር አብይና የለማ ጉዞ እጅግ ከተጠበቀው በላይ
ውጤታማ ነበር ። ካልተደሰትንበት ጥቂት ይልቅ
የተደሰትንበት ግዙፍ ነውና የተደሰትንበትን አስበን
በመደመር አቢዩት እጅጉን ተጽናንተናል!!!!

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
2024/09/30 19:21:05
Back to Top
HTML Embed Code: