Telegram Web Link
"ሀ/ማርያም ግን ወርዶም ይሳሳታል?"
"ምን አደረገህ ደሞ?"
"ትዝ ይለኛል!!!"


በሬው
@wegoch
@wegoch
​​ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

ለተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች በቅድሚያ የከበረ ሠላምታዬን እያቀረብኩኝ ላለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያዊነትን በማፈንና ብሄራዊ
ስሜትን በማደብዘዝ አገራችንን ለአደጋ ከዳረገው ስርአት ለመላቀቅና በምትኩ አንድነትን ፥ መተባበርን እና ፍትህን ለማስፈን ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን ለማዳን በተለያየ አቅጣጫ ብዙ እንቅስቃሴዎች በሚካሄድበት በአሁኑ ወቅት፦
በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊነትን እና ይቅር መባባልን ይዘው ብቅ ላሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድና ባልደረቦቻቸው አጭር በሚባል የስልጣን ቆይታቸው ለወሰዶቸው በጎ እርምጃዎች እና ላሳዩን ኢትዮጵያዊ አለኝታነት አጋርነትን ማሳየት እና ከጎናቸው መቆም ጊዜው የሚጠይቀው አስፈላጊ ተግባር መሆኑን ስገልፅ በሚደረጉት የድጋፍ እንቅስቃሴዎች ላይ በሥራ አጋጣሚ በቦታው ባልገኝም በመንፈስ አብሬያችሁ መሆኔን ሳረጋግጥ በታላቅ ኢትዮጵያዊ ስሜት ነው።

ድል ለኢትዮጵያዊነት
ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)


@wegoch
@wegoch
@wegoch
Ethiopia: ኢትዮጵያ በማይመጥኗት እጅ መውደቋ ውርደቷ ነው በዲያቆን ዳንኤል ክብረት
ኢትዮጵያ በማይመጥኗት እጅ መውደቋን ሳይ #በዳንኤል_ክብረት

መጠን 0.5MB

በጣም አስደናቂ እይታ ዳኒ 👏👏👏

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch @wegoch
አንድ ሰው እልፍ ነው!!!!!!!!


አንድ ---ሰው ምንም ነው አትበሉኝ ። አንድ ማህተመ
ጋንዲ አንድ አብርሃም ሊንከን አንድ አልበርት አንስታይን
አንድ መይሳው ካሳ የዘመናቸውን በሽታ ፈውሰው
ያገራቸውን ገመና በክብር ሲሸፍኑ አይቻለሁ ። አንድ
አይነድም ለርጥብ እንጨት እንጅ መጠጥ ያለ እንጨት
አንዱ እልፍ ሺህ ፍም ይወጣዋል ። አንድ ለእናቱ ሺህ
ለጠላቱ ከሆነ አንድ እኮ ሃገር ያክማል!!!!


@Balmbaras
@getem
@getem
የገና ሥጦታ - ዳንኤል ክብረት
የገና ሥጦታ
በዳንኤል_ክብረት

➳ የሚያስፈልገው የብር መጠን 0.28 ሳንቲም በስልክ ዳታ 0.35 በስልክ ፓኬጅ።

መጠን 1 MB

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch
የቀኑ ምርጥ ፎቶ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏


@Wegoch
@Getem
💎💎💎ወዴት እያመራን ነው?💎💎💎

• (የዘመናችን እንቆቅልሽ …)

📗ረጃጅም ህንጻዎች ትናንሽ ትእግስቶች ፤ ሰፋፊ
መንገዶች ጠባብ አመለካከቶች፤ የምናወጣው
ብዙ የሚኖረን ጥቂት፤ ብዙ እንገዛለን ትንሽ
እንደሰታለን፡፡
*
ትላልቅ ቤቶች ትናንሽ ቤተሰቦች፤ የተሻለ ምቾት
ጥቂት ጊዜ፤ ብዙ ድግሪ ትንሽ ማመዛዘን /
ግንዛቤ/፤ ብዙ እውቀት ትንሽ ጥበብ ፤ ብዙ
አዋቂዎች ብዙ ችግሮች ፤ ብዙ መድሃኒት ትንሽ
ጤንነት ፡፡
ብዙ እንጠጣለን ፤ በቸልተኝነት ብዙ እናባክናለን
፤ ትንሽ እንስቃለን ፤ በፍጥነት እንነዳለን ፤ በቶሎ
እንናደዳለን ፤ ብዙ እናመሻለን ደክሞን እንነሳለን
፤ ጥቂት እናነባለን ብዙ ቴሌቪዥን እንመለከታለን
፤ አልፎ አልፎ እንጸልያለን ፡፡
ብዙ እናወራለን ትንሽ እናፈቅራለን ፤ አብዝተን
እንጠላለን ፡፡ ስለ ጥሩ አኗኗር ተምረናል እንዴት
እንዴት እንደሚኖር ግን አልተማርንም ፡፡
*
📒ለህይወት እድሜ ጨምረንለታል ለእድሜ ግን
ህይወት አልጨመርንም፡፡
ስልጣንን ለማገልገል ሳይሆን ሆድ ለመሙላት ፤
ሆድ ተንዘርጥጦ አምሮ ግን ኮሰመነ፡፡
መከባበር በመናናቅ ፤ መተዛዘን በመጠፋፋት ፤
ህሊና በሆድ ተተኩ፡፡
ጨረቃ ላይ ደርሰን ተመለስን ግድግዳ
የሚለየውን አዲስ ጎረቤታችንን መተዋወቅ
አቀበት ሆነብን፡፡
ከምድራችን ውጪ ያለውን ህዋ ተቆጣጠርን ፡፡
በውስጣችን የሚገኘውን ትንሽ ቦታ ግን
አልተቆጣጠርንም ፡፡
ትላልቅ ነገሮቸን እንጂ የተሻሻሉ ነገሮችን
አልሰራንም ፡፡ አካባቢያችንን እያጸዳን ነፍሳችንን
ግን እየበከልን ነው ፤ አቶምን ሰነጠቅን መሰረተ
-ቢስ ጥላቻዎቻችንንና ቅራኔዎቻችንን ግን
አልፈታንም ፡፡
***
📕ብዙ እናነባለን ትንሽ እንለወጣለን ፤ ብዙ
እናቅዳለን ጥቂት እናሳካለን፡፡ መቸኮልን እንጂ
መጠበቅን አልተማርንም ፤ የተሻለ ገቢ እንጂ
ያደገ ስነ-ምግባር የለንም፡፡
ብዙ መረጃ የሚይዝና ብዙ ሥራ ባጭር ጊዜ
የሚያከናውን ኮምፑዩተር ፈጠርን እንጂ
በመካከላችን ግን ብዙ መግባባት አልተፈጠረም
፤ በብዛት ብዙ ሄደናል በጥራት ግን ወደ ኃላ
ተጎትተናል፡፡
ጊዜው እንዲህ ሆነ፡- ሰው በሁለት ገቢ
የሚተዳደርበት ትዳር ግን የሚበተንበት ፤
የተሰነጣጠቁ ቤተሰቦች የሚኖሩባቸው ግን
የተዋቡ መኖሪያዎች ፡፡ ወቅቱ ፈጣን ጉዞ
የሚደረግበት፤ ለአንድ ሌሊት ትዳር
የሚወጣበትና ግብረ -ገብነት ተሽቀንጥሮ
የተጣለበት ዘመን ...
ወዴት ነው እያመራን ያለነው?

📖ምንጭ፡ ወዴት እያመራን ነው? እና ሌሎች
አጫጭር አነቃቂ ታሪኮች 📖
በዶ/ር ተስፋይ ሰለሞን
🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱
@Wegoch
@wegoch
ታሪክ እራሱን ይደግም ይሆን?
ቅዳሜ ዕለት አዲሱን መሪያችንን ለመደገፍ የድጋፍ ሰልፍ ተጠርቷል።እስቲ ወደ ኋላ ተመልሰን ሚያዚያ 30ን ከታሪክ ድርሳናት ላይ እንቀንጭብ
ወቅቱ 1997 ታሪክ ሆኖ ለዛሬ ማወሳው ደግሞ በዛን ወቅት የነበረውን ታላቅ ከስልጣን ሹክቻም ከፍ ያለ የነበረውን ታላቅ ኩነት ነው።

ለሶስት ወራት ከተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ እና ክርክር በኋላ የመጨረሻ ሰልፍ ማድረጊያ ሰዓት ይደርሳል። በ እለተ ቅዳሜ ሚያዚያ 29 ላይ ኢህአዴግ ሰልፍ ይጠራል። መለስ እንደሚያሸንፍ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ አልነበረውም። በ ኔትዎርኪንግ ባወቀራቸው ጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበሮች ሙሉ እምነት ነበረው። በዚህም በመኩራራቱ አለም አቀፍ ታዛቢያንን ሁሉ ጋብዟል። የትኛውም ካድሬ ህዝብ እንዳያስፈራራ እና እንዳያዋክብ ቀጭን ትዕዛዝ ደርሶታል። ሰአቱ የግለት ህዝቡም የሚሆነውን ነገር በንቃት የሚከታተልበት ነበር። ትዝ ይለኛል በህጻንነት አዕምሮዬ በቴሌቪዥን እና በነበርኩበት አከባቢ ሲፈጠሩ የነበሩ ነገሮች ትላንት የሆኑ ይመስል ቁልጭ ብሎ ይታዩኛል። የ ክርክሩን ጡዘት ህዝቡ እንደ ልብ አንጠልጣይ ድራማ ነበር የሚከታተል የነበረው። በምሁራን የተቀናጀው ቅንጅት የ ተማረ ሰው አብሾ የነበረበትን የኢህአዴግ ባለስልጣን በዝረራ ሲያሸንፍ በየክርክሩ ህዝብ ጉድ እያለ መታዘቡን ተያይዞታል በኢህዴግ ትርኪ ምርኪ ዲስኩር የተሰላቸው የኢትዮጵያ ህዝብ የቅንጅት አባላትን እያንዳንዷን ንግግር በደስታ እና በሀሴት ነበር ያጣጥማት የነበረው። ይሄ ሁሉ ጡዘት ወደ ማሳረግያው ቀረበ። ኢህአዴግ በጠራው የሚያዝያ 29 ሰልፍ በጣም የሚገርም ህዝብ ቁጥር ተገኘ። ይሄን የተመለከተው መለስ በራስ መተማመኑ እንደ ሀገራችን ኢኮኖሚ double digit ነበር ያደገው። እንደውም ለወጣው ህዝብ "ይህ ጎርፍ ከምርጫ ባሻገር ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል። ይሄን ህዝብ ይዘን ለምን እናጭበረብራለን?" ብሎ ነበር። ቅንጅት በንጋታው ሚያዚያ 30 ሰልፍ ጠራ። አሁን ተፈርቷል ለኢሀዲግ ያን የሚያህል ህዝብ ወጥቶ እንዴት ቅንጅት የሚወጣለትን ሰው ያገኛል ብሎ ህዝቡ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል። በኢሀዴግ ቤትም ፍርሀት ቢኖርም ግን ለእኛ የወጣውን ያክል ግን አይደርስም የሚል ተዓብዮ የተሞላበት ተስፋ ነበር የሆነው ግን የተገላቢጦሽ ነበር አዲስ አበባ በታሪኳ እንደዛ ቀን ያለ ታላቅ እና በዙ ህዝብ ያስተናገደችበት ሰልፍ የለም ጠጠር መጣያ እስኪጠፋ ድረስ መንገዶች ሁሉ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲያመሩ ግድ የሆነ ይመስል መስቀል አደባባይ ከአፍ እስከ ገደቡ ሞላ። እስከ ሜክሲኮ ያለው መንገድ በሰው ጢም ብሎ መንቀሳቀሻ ሁሉ ታጣ። ከ አንድ ሚሊየን ህዝብ በላይ አዲስአበባን አጥለቀለቃት።
በዛን ወቅት ሁሉን አስገርሞ የነበረው መፈክር እንዲህ ይላል
" ትላንት ለ ቲ-ሸርት ዛሬ ለ ህሊናዬ" ። ገዢው ቡድን ማጥ ውስጥ ገባ የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፋበት ተመርኩዞት የነበረው የትዕቢት ካብ ሲናድ ታወቀው ተስፋው እንደጉም ሲበተን ከዛች ቅጽበት ጀምሮ ምርጫ 97 መጭበርበር ጀመረ። ከዛ ታሪካዊ ሰልፍ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ሰልፍ ለዳቦና ለ ዘይት ሆኖ ቀረ። ከ 13 አመታት በኋላ በመጪው ቅዳሜ ታሪክ እራሱን ይደግም ይሆን???

በጉጉት እየተጠበቀ ነው።
መልካም ከሚሰሩት ጎን መቆም በራሱ መልካምነት ነው

We support our prime minister
(እንቁ ታደለ)
@Wegoch
@ethio_art
"የዕውቀት መለኪያው" የዳንኤል ክብረት ምርጥ ፅሁፍ በሸገር ሼልፍ
✦ የዕውቀት መለኪያ ✦
በዳንኤል_ክብረት

አጅግ ጣፋጭ ወግ 😊

➳ ለማውርድ የሚያስፈልገው የብር መጠን 0.34 ሳንቲም በስልክ ዳታ 0.52 በስልክ ፓኬጅ።

መጠን 1.5 MB

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch
አዋጅ አዋጅ አዋጅ!!


በነገው እለት ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የድጋፍ
ሰልፍ ለማድረግ ወደ መስቀል አደባባይ ለምትወጡ
የአዲስ አበባ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ ባዶ
እጃችሁን እንዳትወጡ ተብላችኋል።
በክረምት ወር በብርድና በቁር እየተመቱ የጎዳናን ህይወት
ለሚጋፈጡ ዜጎቻችን፤ የማትለብሷቸውን፤ ቁም
ሳጥኖቻችሁ ውስጥ ያለ አገልግሎት የተቀመጡ ልብሶችን
በአንድ እጃችሁ ይዛችሁ መውጣት እንዳትረሱ።
ድንገት በእለቱ ቲሸርት ከገዛችሁ ቅያሪውንም መለገስ በጎ
ተግባር ነው። የእለቱን መልዕክት የያዘ ቲሸርት መለገስ
ከፈለጋችሁም እሰየው። ብቻ ለወገኖቻችን መስቀል
አደባባይ ባዶ እጃችሁን እንዳትመጡ።
አስተባባሪዎቹን በእለቱ ለማገዝ በጎ ፍቃደኛ የሆናችሁ
በሚከተሉት ስልኮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን
እንገልጻለን።
0912 65 97 53
0919 26 67 60

@Balmbaras
@Lula_al_greeko
መደመር ስንል???!!!!!!


መደመር ስንል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእለተ ሲመቱ ላይ
ሲናገር አንድነት ማለት አንድ አይነትነት ማለት አይደለም
ሲል ከገለጸው ምንጭ የተቀዳ ግዙፍ እሳቤ ነው ። የሃገር
አንድነት ግንጥል ጌጥ አይደለም ። ሃብሮ የተሸመነ
ማንነት ነው ። ሁሉም የየራሱን እየጠየቀ ከሌላው ጋር
አብሮ የሚጓዝበት ረጅም ጉዞ ነው ። እንደመር የተባለው
በዚህ ሂሳብ ነው ። መደመር ላይ አስደማሪና ተደማሪ
የለም ።ሁሉም ተደማሪ ነው ። እንደመር ማለትና እንዳበል
ማለት ልዩነት አለው ። አልደመርም ማለት መብት ነው ።
ካልተደመርክ ደግም አትቀነስም ። የቅነሳ ጉዳይ
የሚነሳው መጀመሪያውኑ ተደምረህ ኑረህ መደመሩን
ጠልተህ መለየት ስትፈልግ የሚከሰት ነው ። ነገር ግን
ካልተደመርክ መጀመሪያውኑ አልተደመርክምና የቅነሳ
ስሌት በዚህ የለም። ቀድሞ ቤት ከገባው ሰው ቤት ሄደህ
ስትገባ ይኸ ነገር መዳበል ነው ። ባይሆን ራስህ ቤቱን
አብረን እንስራና አብረን እንኑር ማለት ደግሞ መደመር
ነው!!!! ይኼው ነው! !!! የነገው ሰልፋችንም
የመደመር ነው!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
🇪🇹ዘር ሳይኖር ሀገር ነበር 🇪🇹

ይህ የኢትዮጲያ ቻናሎች ድምጽ ነው

🇪🇹ስለሰላም እና አንድነት ፤ ስለ ፍቅር እና መከባበር ፤ስለ መዋደድ እና መተባበር ባጠቃላይ ስለ ኢትዮጲያዊነት እሴት እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹የብሄር ልዩነት ዉበት እንጂ ለመከፋፋል ምክንያት እንዳልሆነ እንመሰክራለን፡፡

🇪🇹የሀይማኖት ልዩነት ለመተሳሰር እና ለመተሳሰብ ምክንያት እንጂ ለጠላት በር መክፈቻ አለመሆኑ እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹የአምላክ ቃል ኪዳን ያለበን ፤ ከ3000 ዓመት በላይ የራሳችን ታሪክ ያለን ፤ የአብሮ መኖር ተምሳሌት የሆነች ሀገር እንዳለን እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹በአባቶቻችን ደም ተቀልሞ የተጻፈ ታሪክ ባለቤት ፤የመሰዋት ሀገር ባለቤት እንደሆንን እንመሰክራለን፡፡

🇪🇹የራሳችን ባህል ወግ እና ስረአት ባለቤት ፤የአክሱም ላሊበላ ፤የሶፍ ኡመር ፤የፋሲል የቴድሮስ ሀገር ፤አባጂፋር እና ከማንም በፊት የነበረው ታላቁ የገዳ ስረአታችን የኛ መገለጫ መሆኑን እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹በሀገራችን የሰላም ጥሪ ፤ፍቅርና መተሳሰብ እያመጣ ላለው ታላቁ መሪያችን ክቡር ዶክተር ጠ/ሚንስተር አብይ አህመድ ጎን መቆማችንን እና በነገው እለት ባለው ሰልፍ ላይ አብሮነታችንን እንመሰክራለን ፡፡

🇪🇹ይቺን የመሰዋእት ሀገር የመረከብ ሀላፊነት የኛ ነው፡፡ የአንድነት መሰረታችን መደመር ነው፡፡

🇪🇹ከምንም በፊት ኢትዮጲያ ፡፡ የኛ አንድነት ለጠላት የማይናድ ተራራ ነው፡፡

🇪🇹እነሆ የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ ፤ኢትዮጲያዊ ነኝ የምትል ከሆነ የሀገርክን ድምጽ አድምጥ ፤ ስለ ሰላም ዘምር ፤የአምላክህን ጥሪ ስማ ፡፡

🇪🇹አብራችሁን በመቆም ኢትዮጲያ ሀገራችንን ለለዉጥ ጎዳና እንውሰዳት ፡፡ ሼር በማድረግ የዜግነት ግዴታዉን ይወጡ፡፡

🇪🇹አምላክ ኢትዮጲያን ይባርክ ፡፡🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዶ/ር ዐቢይ በቦንቡ ፍንዳታ ዙሪያ መግለጫ ሰጠ።
"ደስታችንን ለማጨለም የሞከራችሁ ኃይሎች
አልተሳካላችሁም። ትናንትም አልተሳካላችሁም። ዛሬም
አልተሳካላችሁም። ነገም በፍጹም አይሳካላችሁም።"
...
"የሞቱትን ሁሌም በዚህች የመደመር ቀን እንዘክራቸዋለን።
ለፍቅርና ለአንድነት የተከፈለ መስዋዕትነት ማሳረጊያ ሆነዋልና
አንረሳቸውም። የተጎዱትን እናሳክማለን። ኢትዮጵያ በፍቅር
በአንድነት ትቀጥላለች። እኩዮች ያፍራሉ። በፍቅር ወደፊት
እንሄዳለን።"
(እንቁ ታደለ)
@Ethio_art @wegoch
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዛሬው ሰልፍ ወቅት የቦንቡ ድምጽ ሲሰማ የጠቅላይ ሚንስተሩ ጠባቂዎች ዶክተር አብይን ከበው ሲሄዱ የሚያሳይ ቪድዮ

አምላክ ሆይ እንኳንም ሰቆቃችንን አላበዛህ

@ethio_art
@ethio_art
Mesfin negash
አዲሳባችን! ኩልል ጥርት ያለ ድምጽሽ የእናት ኢትዮጵያን ጋራና ሸንተረር ሞልቶታል። መልእክቱ ግልጽ ነው። ወገናዊነት፣ ሰብአዊነት፣ ፍቅርና ይቅርታ። ይኼው ነው። ይህን መንፈስና ጥሪ መስበር አይችልም። ጉዞው ገና መጀመሩ ነው።
አዲሳባችን፣ ልብ በዪና ስሚኝ።
1፤ እንደተባለው በዛሬው የጥቃት ሙከራ የሞቱ ካሉ በክብር ቅበሪያቸው። በወዱድት ባንዲራ ሸፍነሽ በየእምነታቸው፣ በክብር፣ በፍቅር ሸኚኛቸው። እንደወጡ ቀሩ ሳይሆን በፍቅርና በክብር ተሸኙ አስብዪላቸው። ቋሚን ይግረመው።
2፤ የሟቾቹን ቤተሰቦች አጽናኚ። አጽናኚ። በተለይ ዛሬ ሰልፉን ተካፍላችሁ የነበራችሁ አዲስ አበቤዎች፣ ምናልባትም ሟቾቹ እናንተም ልትሆኑ ትችሉ ነበር። እናንተ ቢሆን ትወዱት የነበረውን ሁሉ ለቤተሰቦቻቸው አድርጉ፤ ሌላው ቢቀር ለቅሶ ድረሱ። አጽናኑ።
3፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ተንከባከቢ። አዲስ አበቤዎች በቀጣዮቹ ቀናት ሆስፒታልም ይሁን በየቤታቸው የተኙትን ጠይቋቸው። አኩሯቸው! አስታሟቸው።
4፤ አዲሳባችን ሆይ! ስለጥቃቱ ፖሊስ ምርመራውን እስከሚጨረስ ድረስ ስለተጠርጣሪዎቹም ሆነ ስለዓላማቸው ከሚፈበረኩ ተረቶች ራስሽን ጠብቂ። የአዲስ አበባ ነዋሪ ሁሉ አዲስ አበባዊ ነው። የትም ይወለድ፣ የትኛውንም ቋንቋ ትወቅ፣ የትኛውንም ሃይማኖት ይከተሉ፣ አዲስ አበቤዎች ራሳቸውን የሚለዩት በጉርብትናቸውና በአብሮ መኖራቸው ነው። አለቀ። የጎጥ በሽታቸውን ሊያጋቡብሽ ከሚራወጡ ድኩማን ራስሽን ጠብቂ፣ አዲሳባችን። "ተጠርጣሪዎቹ እዚህ ከተማ ስለተወለዱ የእንትን ብሔር ናቸው፣ ጥፋቱም የዚያ ብሔር ነው ማለት ነው" የሚሉ በሽተኞችን አትስሚያቸው። "ተስቧችሁን አታጋቡብኝ" በያቸው። ወንጀሉን የፈጸመው ሰው ነዋሪሽ ከሆነ፣ አዲስ አበቤ ነው፤ ከሌላ ክልል ለዚሁ ተልዕኮ መጥቶ ከሆነም አንድ ኢትዮጵያዊ ወንጀለኛ ነው። ይኸው ነው። ግለሰቦቹን አደራጅቶ የሚልከውም ቢሆን ግፋ ቢል አንድ ቡድን ነው፤ ብሔር ሊሆን አይችልም። ወንጀልና ወንጀለኝነት ብሔር የለውም።
5፤ የአዲስ አበባ ከንቲባ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀበሌ መታዊቂያ ላይ የትውልድ ቦታና ዜግነት ብቻ እንዲጻፍ፤ በነዋሪነት መታወቂያ ላይ ብሔርን መጻፍ በሕግ የተከለከለ እንዲሆን በአደባብይ መመሪያ ይስጡልሽ። በፖሊስ የወንጀል ምርመራ ምዝገባም ይሁን በሌላ ሁኔታ፣ በሕግ አስገዳጅ ካልሆነ በቀር፣ ዜጎች አገልግሎት ለማግኘት ብሔራቸውን እንዳይጠየቁ ይደረግ ብለሽ አሳስቢያቸው። ካስፈለገ ፊርማ አሰባስቢ፤ የዛሬው ካልበቃቸው ሌላ ሰልፍ ጥሪላቸው።
6፤ አስታውሺው፤ ጠ/ሚ ዐቢይን እንዲህ በዪው፤ "ኢትዮጵያን እስካከበርክ እጠብቅሃለሁ፤ ግን አንተም ራስህን ጠብቅ፣ አስጠብቅ። ይህን ስታደርግ ደሞ፣ ከሕዝብ በአካልም ይሁን በመንፈስ አለመራቅህን አረጋግጥ!"
7፤ አመስግኚ! ሰልፉን ያስተባበሩትን፤ በዝግጅቱ የተሳተፉትን፣ የታደሙትን፤ ለሰልፉ ጥበቃ ያደረጉትን፤ አደጋ የደረሰባቸውን ለማዳን የተዋከቡትን፤ አደጋው ከሆነ የበለጠ ጉዳት እንዳያደርስ የታገሉትን፤ ሁሉንም አመስግኚቻው።
ወትሮም ቢሆን፣ በጎ በታሰበበት ሁሉ ክፉ መኖሩ የማይቀር ነው። ጥያቄው የትኛው አሸነፈ ነው። ከዚህ አንጻር ሰልፉ የታሰበለትን ዓላማ አሳክቷል። እንዲደርስ የታሰበው አደጋ ምንም ያህል ይሁን፣ አልተሳካም።
ትግሉ ገና መጀመሩ ነው።
[ወዳጆች፣ እነዚህና መሰል መልዕክቶች በስፋት መሰራጨት፣ መነጋገሪያ መሆን እንዳለባቸው ይሰማኛል። ስለዚህ ይህንን መልዕክት በምትፈልጉት መልክ፣ እኔን መጥቀስ ሳያስፈልጋችሁ ብታካፍሉት ደስ ይለኛል።

@wegoch
@wegoch
@audio_poems
ልጆች ሳለን, ከጏደኞቼ (ተፈራና አስቻለው) ጋር
መንገድ ይዘናል:: ተፌ ሳናስበው "ባትጋሩኝ አራት
ብር!" በማለት ተንደርድሮ የተቋጠረ መሃረብ አነሳ::
መሃረቡን ስንፈታው የተጠቀለሉ አራት ብሮች
አገኘን:: ተደስተን: ሻይ ቤት ገብተን እስክንጠግብ
በላንበት :: ወደቤት ስንመለስ ግን የተፌ እናት
"አራት ብሬን ውለድ" በማለት የፊጥኝ አስረው
እንደገረፉትና: የኛንም የዋህነት አስታውሳለሁ::
መሃረቡ ውስጥ አራት ብሮች እንደነበሩ እንዴት
እንዳወቀ ራሳችንን አልጠየቅንም (የልጅ ነገር)::
እናም የዳንኤል ብርሃኔ F-1 ቦምብና የተፌ አራት
ብር ተመሳሰሉብኝ::

@Balmbaras
@getem
@getem
ሰበር ዜና!!
Breaking News
ቦምብ በመወርወር በዶ/ር አብይ ላይ ጉዳት ለማድረስ
የሞከሩት አምስት እብድ መሳይ ሴቶችና አንድ የፖሊስ ልብስ
የለበሰ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ሁሉም የራሳቸው ክልል ያልሆነ
መታወቂያ ይዘው እንደነበር ፖሊስ በሰበር ዜናው አስታውቋል፡፡
አምስቱም ሴቶች መታወቂያው ከ 4 ቀን በፊት መሰጠታቸውን
የገለጹ ሲሆን እያንዳንዳቸው የ300,000 ብር ክፍያ
እንደተደረገላቸውና ስራውን ሲያጠናቅቁ ቀሪ 200,000 ብር
እንደሚሰጣቸው ቃል እንደተገባላቸውም ተናግረዋል፡፡
ግለሰቦቹ ከ 2 ቀን በፊት በ ፒክ አፕ መኪና ከ ተንበይ አዲስ
አበባ መግባታቸውንም ጨምረው የተናገሩ ሲሆን ያዘዛቸውን
ሰው ግን በመልክም በስምም እንደማያቁ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ አዲስ ነገር ሲኖር ለህዝቡ እንደሚገልጹ ኮሚሽነሩ
አስታውቀዋል::

@Ethio_art @wegoch
እውን ለዚህ ሰው መስዋዕትነት ቢከፈልለት ይበዛበት ይሆን

አምላክ ሆይ የተማረም የተባረከም መሪ ስለሰጠህን እናመሰግናለን አንተ ጠብቅልን

@ethio_art @wegoch
ደራሲ ይስማዕክ ወርቁ በህመሙ ምክኒያት ሰልፉ ላይ
መገኘት ባይችልም፣ ቲሸርቱን ለብሶ ይሄንን የድጋፍ ፎቶ
አያይዞልናል!
እግዜር ጨርሶ ይማርህ ወንድማችን

@ethio_art
@wegoch
2024/10/01 07:31:45
Back to Top
HTML Embed Code: