Telegram Web Link
የኖህ መርከብ በኢትዮጲያ - ዳንኤል ክብረት
✦ የኖህ መርከብ ✦
በዳንኤል_ክብረት

አጅግ ግሩም እይታ 😊

➳ ለማውርድ የሚያስፈልገው የብር መጠን 0.55 ሳንቲም በስልክ ዳታ 0.36 በስልክ ፓኬጅ።

መጠን 1.6 MB

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch
"ከቦንቡ መፈንዳት በሁዋላ፣ ቲሸርት አስገዛሁና፣ እንደዚህ
ሆንኩ፡፡ ቦንቡን እበቀል ይመስል፡፡ 'መምህራን አስተምሩ፣
ተማሪዎች አጥኑ... ' ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፡፡
በእውነት እኔ ከዳንኩ በኋላ 'ህብረት በህብረትም' ይላኩኝ፡፡
እልም ካለ ገጠር፡፡ ያለኝን አካፍዬ እመጣለሁ፡፡ ምክንያቱም
የተማረ ሰው፣ ሰው አይገድልምና፡፡"
ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ
@Ethio_art @wegoch
ከሰላማዊ ሰልፍ ሁነቶች የገረሙኝ፦
1. የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር፦ የምሬን ነው፣ በጣም ምርጥ
ነንግግር ነበር። የዶ/ር አብይ ንግግር የማድረግ ብቃት ከቀን
ወደ ቀን በሚገርም ፍጥነት እያደገ ነው። የኃዘኑ ድባብ እንደዚህ
ዓይነት የዕለቱን መልካም ሁነቶች አሁን ቢያደበዝዝብንም ወደ
ፊት የምናነሳው ይሆናል።
2. ከኦሮሚያ የመጡ ፈረሰኞች ቦንቡ ወደፈነዳበት እዚያው
ፈረሳቸው ላይ ሆነው እየፎከሩና እየሸለሉ በታላቅ ቁርጠኝነት
ሲፈጥኑ ሳይ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር።
3. ሕዝቡ የፖሊስን ሚና ተክቶ የተወነበት ሁነት፦ የፍንደታው
ድምፅ እንደተሰማ አጠገቤ ከነበሩ ወጣቶች የተወሰኑት "ወይኔ
አብይ" እያሉ ወደ መድረክ ለመሮጥ ያደረጉት ሙከራ ገራሚ
ነበር። ከሁሉም በላይ ያስደነቀኝ ሕዝቡ በፖሊሱ ላይ እምነት
አለማሳደሩ ነበር፣ ስለዚህም ተጠርጣሪዎችን ከያዘ በኋላ
ለፖሊስ ለማስረከብ ፈቃደኛ አልነበረም። በዚያች ቅፅበት ውስጥ
ፖሊስ ራሱ እጁ ሊኖርበት ይችላል ብሎ መጠርጠር አልናፎም
ተጠርጣሪዎቹን ሊያሸሽብን ብሎ መገመት ምን የሚሉት ብስለት
ነው? በእውነት ወጣቶቻችን ያኮራሉ፣ ስለዚህም አንድ ውሳኔ
ወሰኑ፦ ተጠርጣሪዎቹን ወስዶ በቀጥታ ለአብይ ማስረከብ!
ከነዚህ ወጣቶች ውስጥ አንዱ ወዳጃችን ነበርና ወደ
ቤተ መንግስት ያደረጉትን ጉዞ በስልካችን ላይ እየደወለ Live
ሲያስተላልፍልን ነበር። ዕለቱ ሕዝቡ ለዶ/ር አብይ ያለውን ፍቅር
በተግባር የገለጠበት ሰልፍ ነበር። ጠቅላያችን... የምር
ታድለሃል!
4. በመጨረሻም ከወደድኳቸው ጭፈራዎች ውስጥ
የመጀመሪያው ሕዝቡ ከኤርትራ ጋር የተጀመረው የዕርቅ ድርድር
ተመችቶት፦
ና ና ኢሳያስ..ና ና... እያለ የጨፈረበትና... ምን አለ አብይ ምን
አለ፤ ሀገሬን ለጅብ አልሰጥም አለ...የተሰኙቱ ናቸው።
መልካም እሑድ! ሆስፒታል ላሉ ወገኖቻችንና ሕክምናውን
ሲያካሄዱ ላደሩ ዶክተሮቻችን እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥልን!
(ጌታሁን ሔራሞ)
@Ethio_art @wegoch
​​አብይም እንደ ሳንካራ

ከሰላሳ አመት በፊት የቡርኪናፋሶ ፕሬዘዳንት የነበረው ቶማስ ሳንካራ ወደ ስልጣን የመጣው በህዝብ በሚደገፍ መፈንቅለ መንግስት እንደነበር ይነገርለታል።
ሞገደኛው ሳንካራ ስልጣን ሲይዝ የ33አመት ጎልማሳ ነበር። ስልጣን ላይ የቆየውም ለ አራት አመታት ብቻ ነበር። ይሁን እንጂ በ እነዚህ አራት አመታት የአፍሪካ ምርጡው መሪ ያስባለውን ድርጊቶች መከወን ችሏል። ሃገሪቱን በፈረንሳይ ከሚዘወር መንግስት ነፃ አድርጓል። በቅኝ ገዢዎች የተሰጣትን ስም ቀይሮ ቡርኪናፋሶ The Land of Upright Men ሲል ጠርቷታል። ቅንጡ የባለስልጣን መኪኖችን ሸጦ በርካሽ መኪኖች ከመተካት ጀምሮ በሙሰኞች የተያዙ ድርጅቶችን ለህዝብ ጥቅም እንዲውሉ አድርጓል። የመንግስትን እጅ በእዳ ይጠመዝዛሉ ብሎ ካሰባቸው IMF እና World Bank ሃገሪቱ ገንዘብ እንዳትበደር ወስኖ ነበር። የሌሎች የአፍሪካ ሃገራትም ይህንኑ ፈለግ እንዲከተሉ ይወተውት ነበር።
ቡርኪናፋሶ በሱ የአራት አመታት አገዛዝ በግብርና፣ አካባቢ ጥበቃ፣ የሴቶች መብት፣ የትምህርትና የጤና ሽፋን የደረሰበችን ስኬት ከሱ በሁዋላ አልደገመችውም ይላሉ።

ሳንካራ የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ነበር(አብይ የለበሰውን ቲሸርት ልብ ይሏል)። የአንድነት አራማጅ ነበር። ህዝበኛ (Populist) ነበር። ይሁንና ድራማ በሚመስለው የህይወቱ ፍፃሜ ዛሬም ድረስ ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ በጥይት ተደብድቦ ሞቷል። የቀድሞ ባልደረቦቹ እጅ አለበት የሚሉ አሉ። የፈረንሳይ እጅ አለበት የሚሉ አሉ። ይሁንና ሳንካራ ፈለጉን የተከተለው ባለመገኘቱ የጀመራቸውን ስራዎች የሚጨርስ አልተገኘም። ከበደልም ሁሉ በደል በሆነ መንገድ በሚዲያውም በታሪክ መፅሃፍትም ስሙ ሆን ተብሎ እንዲዘነጋ ተደርጓል ይላሉ።

እነሆ ሰላሳ አመታት አለፉ። ታሪክ ለምስክርነት ያደለን እኛም እንዲህ ጠየቅን። አብይና ሳንካራ ምንና ምን ናቸው? ጊዜ የሚመልሰው እንዳለ ሆኖ ያየነውን የምናውቀውን ብናመሳስል መልሱ ቀላል ነው።
በዘመናችን ማስገደድን ባህሉ ካደረገ ድርጅት ፍቅርን ያስቀደመ፣ የአንድ ዜጋ ህመም የሚያመው ሰው ወጥቶ አየን። ከክፍፍል ባህር የወጣ የአንድነት አቀንቃኝ ተመለከትን። ከግትርነት አጥር ወጥቶ ከሱ በፊት ለተሰራ ጥፋት ይቅርታ የሚጠይቅ ይቅርታም የሚያደርግ መሪ አገኘን። ተስፋም አደረግን።

አዲስ አበባ በስንት አመቷ እውነተኛ ሰልፍ አየች? ከኢሃዴግ አንዱን ይህን ያህል እንወደዋለን ብሎ ማን ገመተ? እኔ ብቻ ነኝ ለአንድ መሪ በተደረገ ድጋፍ ላይ ባለ ኮከቡን ባንዲራ፣ ኮከብ የሌለውን ባንዲራ፣ የኦሮሚያን ባንዲራ ፣ የኦነግን ባንዲራ በአብሮነት ሲውለበለብ በማየቴ የተገረምኩት? ከቤተክህነት እስከ መጅሊስ፣ ከሃብታም እስከ ደሃ፣ ከ ድፍን አዲስ አበቤ እስከተጎራባቹ በኢትዮጲያዊነት ስር ተሰልፎ ማየት አይገርምምን? መደመርስ ከዚህ ሌላ ምንድነው?
(ይህ የድጋፍ ቀን ደሴና ደብረማርቆስም ላይ ተከብሮ ውሏል)
አቢይም ሰልፉ ላይ የማንዴላንና የአፍሪካን ምስል ያጣመረ ቲሸርት ለብሶ በመገኘት የህልሙን ርቀት አሳይቶናል። ኢትዮጲያዊነት ከፍታ ላይ ቆሞ አፍሪካዊነት አሻግሮ ማየት!!
ይሁንና ይህን ሁሉ ባየ አይናችን ቢሳካ ኖሮ የግድያ ሙከራ ተሞክሮ አየን።

በግሌ ከዶክተር አቢይ ጋር ከማልስማማባቸው ሁለት መሰረታዊ ነጥቦች አንዱና ዋነኛው ሁሉም አጥፊ ይቅርታ ይገባዋል ብዬ አለማመኔ ነው። አንዳንድ ጊዜ ከይቅርታም በላይ የህግ የበላይነትና ፍትህ ለሃገር መፅናት ወሳኝ ናቸው። ማን ምን እንደሚያጠፋ እናውቃለን። ማን ከራሱ ጥቅም ውጪ ኢትዮጲያ መልካም ሲገጥማት ማየት እንደማይወድ እናውቃለን። ማን የቦንቡን ፍንዳታ ሊያቀነባብር እንደሚችል እኛም እሱም እናውቃለን። ዶክተር አቢይ ነገ ላይ የሳንካራ እጣ ቢገጥመው አድራጊው ማንም ሳይሆን ዛሬ መቀጣት ሲገባቸው በይቅርታ የታለፉ ሰዎች ናቸው።

አስባለሁ። መደመር መልካም ነው። ነገር ግን ሁሉም ሰው አይደመርም። ኔጋቲቭ ቫልዩ ይዘው የሚመጡትን ስንደምራቸው እንከስራለን። ዛሬ ያየነውም ይህ ነው።

ሳንካራ ይል ነበር። እኔ ብሞትም ሃሳቤ አይሞትም። ዛሬ ግን ስሙም ሃሳቡም የተረሳ ይመስላል። አብይን ይህ እንዳይገጥመው ፍርሃቴ ነው። ያየነውን ጭላንጭል ተስፋ አልጠግብ ባዮች ሲያጠፉት ማየት ፍርሃቴ ነው። የጀመረው ለውጥ እሱ ቢኖርም ባይኖርም መቀጠል ይችል ዘንድ ተቋማዊ መሰረት ይኖረው ዘንድ ግድ ነው። እንኳን ወንጀለኛን ስንቱን ንፁህ ስናስር የኖርን ነንና እነዚህ አጥፊዎች ይቅርታ ሳይገባቸው ከህግ በታች ሲሆኑ ማየትን እመኛለሁ።

ደግሞ ከደረሰብን ሁሉ ያገኘነው ይበልጣል። ከሚደርስብንም የምንሆነው በላጭ ነው።

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!
©Haileleul Aph

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ዶ/ር አብይን እቃወማለሁ! 16k
ናቲ በ ዘሩስ
ዶክተር አብይን እቃወማለሁ 😂
ናትናኤል ጌቱ

አጅግ አስቂኝ ወግ 😊

፨ ናትናኤል ምን ሆኖ ነው 😂
ስሙትና ፈታ በሉ
፨ አቅራቢ ፦ ፈቃዱ ተገኝ ከ ክፈት

መጠን 0.8 MB

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch @wegoch
እውነት ይሆን እንዴ - ዳንኤል ክብረት
እውነት የሆን እንዴ 😳
ዳንኤል ክብረት

አጅግ ግሩም እይታ 😊

፨ አቅራቢ ፦ አንዷለም ከ ሸገር

መጠን 0.9 MB

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch @wegoch
የደራሲ ይስማዕከ ሚስት፣ ”ስቃይና ብሶቴን ስሙኝ” ትላለች
· “ሁለት ልጆቼን የማበላቸው አጥቼ ተቸግሬአለሁ”
· “ህይወቴ በአደጋና በስጋት የተሞላ ነው”
የ27 ዓመቷ ወ/ሮ ፀጋ አንዳርጌ ምህረት፣ የዕውቁ ደራሲ
ይስማዕከ ወርቁ ባለቤት ናት፡፡ በ1998 ዓ.ም መተዋወቃቸውን
የምትናገረው ወ/ሮ ጸጋ፤ ለ12 ዓመታት በትዳር መኖራቸውንና
አንድ ወንድና አንዲት ሴት ልጅ ማፍራታቸውን ትገልጻለች፡፡
ሆኖም የደራሲነት ዝናው እየጨመረ ሲመጣ ውጭ ውጭ ማለት
እንደጀመረ የምታስረዳው የደራሲው የትዳር አጋር፤ አንድ ልጅ
ከወለዱ በኋላ ተለያይተው እንደነበር ትገልጻለች፡፡ ጥንዶቹ
ዳግም የተገናኙት ይስማዕከ የመኪና አደጋ ከደረሰበት በኋላ
መሆኑን ወ/ሮ ጸጋ ተናግራለች፡፡ ሁለተኛ የአብራካቸው ክፋይ
የተወለደችውም በዚህ ጊዜ ነው ትላለች፡፡
ይሁን እንጂ ባላሰብኩት ሰዓት እኔንና ሁለት ህጻናት ልጆቻችንን
ባዶ ሜዳ ላይ ጥሎን በመሰወሩ፤ በአሁን ሰዓት ለልጆቼ ቀለብ
መግዣ አጥቼ የከፋ ችግር ላይ እገኛለሁ ብላለች - አዲስ
አድማስ ዝግጅት ክፍል ድረስ መጥታ ብሶቷን የነገረችን ወ/ሮ
ፀጋ አንዳርጌ፡፡ ደርሶብኛል የምትለው በደል ግን ይሄ ብቻ
አይደለም፤ እስከ ዛሬ መልካም ስሙንና ዝናውን እንዳላጎድፍበት
ብዬ ሲያደርስብኝ የቆየውን ግፍ ደብቄ ቆይቻለሁ የምትለው
የደራሲው ባለቤት፤ ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ጋር
ባደረገችው ቃለ ምልልስ ከዚህ በኋላ የመጣው ይምጣ ብላ
የደረሰባትን ሁሉ አፍረጥርጣ ተናግራለች፡፡ እነሆ ከዚህ በታች
ቀርቧል፡፡
ጉዳዩን ለማጣራት ለደራሲ ይስማዕከ ወርቁ በሞባይል ስልኩ
የፅሑፍ መልዕክት (ቴክስት ሜሴጅ) ልከን “የኮሚቴው ኃላፊ
ሽመልስ አበራ ጆሮ ስለሆነ በእነሱ ፊት አነጋግሪኝ” በማለት
ምላሽ ቢሰጥም በኮሚቴው በኩል ልናገኘው ያደረግነው ሙከራ
ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
ከይስማዕከ ወርቁ ጋር እንዴትና መቼ ተዋወቃችሁ?
ከይስማዕከ ጋር የተዋወቅነው በ1998 ዓ.ም እኔ የአንደኛ
ደረጃ፣ እሱ የሀይስኩል ተማሪ እያለን ነው። የተዋወቅነውም ቤት
ተከራይቶ፣ እኛ ጎረቤቶች ቤት ከገባ በኋላ ነው፡፡ ለአንድ አመት
ብቻ በጓደኝነት ከቆየን በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ አብረን መኖር
ጀመርን። በጥሩ ፍቅር ስንኖር ቆይተን፣ በድርሰቱ እውቅናና
ገንዘብ ማግኘት ሲጀምር፣ በሰው ሲታጀብ፣ ከመጠን በላይ
መጠጣት መስከር፣ እኔንም መደብደብና ማሰቃየት ጀመረ፡፡
ይባስ ብሎ ባመሸበት ማደር፣ ለትዳሩ ታማኝ አለመሆን ጀመረ፡፡
ብዙ ስቃይና ጭቆና ውስጥ ነው የኖርኩት፡፡ ስልክ ማናገር፣
ከጓደኛና ከቤተሰብ ጋር መገናኘት አልችልም ነበር፡፡
ግን እኮ ይስማዕከ በስራው እውቅናና ዝናን ካገኘ ቆይቷል፡፡
በእነዚያ ጊዜያት ጭቆናና በደል ሲያደርስብሽ እንዴት ዝም ብለሽ
ተቀመጥሽ?
እኔ ያገባሁት ለዝና ብዬ አይደለም፤ ገና ተማሪ እያለ ሳይታወቅ
ነው፤ ይወደኝ እውደው ነበር፡፡ ማሰቃየትና መበደል ሲጀምር፣
ብዙ ጊዜ ከቤት እየወጣሁ ቤተሰቤ ዘንድ እሄድ ነበር፡፡ ከዚያ
ሽማግሌ እየላከ ይቅርታ እየጠየቀ፣ መልሶ ይወስደኛል፡፡
ቤተሰቤም፤ “እስኪ ታገሺው፣ ይሻሻል ይሆናል” ብለው
ይልኩኛል፡፡ በዚህ መልኩ አብረን ቆየን፡፡ ሀብትና ንብረትም
አፈራን፡፡ ወንዱን ልጃችንን ወለድን፡፡ እኔም ብዙ ውክልናዎችን
በመውሰድ፣ በመፅሐፎቹ ሥራ፣ በማተሚያ ቤቱ አብሬው እሰራ
ነበር፡፡ በመሀል ብዙ ስቃዮችን፣ ድብደባዎችን ሲያደርስብኝ፣ በቃ
ይሄ ነገር ለህይወቴ ያሰጋኛል በሚል ፍቺ ጠየቅሁኝ፡፡ ጉዳዩ ገና
በፍርድ ቤት እያለ፣ ሀዋሳ ላይ ጠጥቶ ከሌላ ሴት ጋር አምሽቶ
ሲያሽከረክር፣ ያው አገር የሚያውቀው፣ የመኪና አደጋ ደረሰበት፡፡
እኔም ይህን ያህል ጊዜ አብሬው ኖሬያለሁ፤ የልጄ አባት ነው
ብዬ፣ ሁሉን ትቼ እሱን ማስታመም ጀመርኩ፡፡ ይህንንም ወዳጅ
ዘመድ ያውቃል፡፡ ሌሊት ቀን ሳልል አስታመምኩት፣ ዳነ፡፡
ተሻለውና ያንን ረስቼ፣ አብሬው መኖር ጀመርኩ፡፡ እንደገና
ሁለተኛዋ ህፃን ተወለደች፡፡ አሁን ዘጠኝ ወሯ ነው፡፡ ታሞ
ከተሻለው በኋላ፣ እኔ ህፃኗን እርጉዝ ሆኜ፣ መልሶ መደብደብ
ማሰቃየት ጀመረ፡፡ እርጉዝ ሆኜ ሆዴን ረግጦኝ፣ ብዙ እንገላቶኝ፣
ከሞት ተርፌያለሁ፤ የህፃኗ መትረፍ ራሱ ተዓምር ነው፡፡
ከተወለደች በኋላ ያው ስቃዩን ችዬ መኖሬን ቀጠልኩ፡፡ ለልጆቹ
ሥል ነበር ስቃይ የማየው። ከዚያ የፋሲካ በዓል መጋቢት 30
ሊሆን፣ መጋቢት 28 ቀን ፋሲካን ሀዋሳ እናሳልፍ ብሎ ከእነ
ልጆቼ ይዞኝ ሄደ፡፡

ይቀጥላል

አዲስ አድማስ የሰኔ 16 እትም

@ethio_art
@wegoch
Ethiopia kefet MUST WATCH #ወግ_እና_ማስታወሻ ዉሾቹን ተዉ በሏቸዉ
ውሾቹን ተው በሏቸው 😠
ዳንኤል ክብረት

፨ ይድርስ ለ መሪዎቻችን ይድርስ ለአባቶቻችን!!! አጅግ አስተማሪ ወግ

፨ ከአጥንት በላይ የማያስቡ ውሾችንም ተውው የሚል አካል የኑር

፨መጠን 1.3 MB

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch @wegoch
አጋዳይ ሚዛን???????!!!


የወጣቱ ደራሲ ይስምኣከ ወርቁ ህጋዊ ባልተቤት ነኝ
በማለት አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በርካታ ቅሬታ
ያቀረበችው ወይዘሮ ደራሲው በርካታ በደል አድርሶብኛል
ስትል የበደሉንም ዝርዝር አስረድታለች ። ይሁን እንጅ
ደራሲው በአሁኑ ሰአት ነገሮችን አስታውሶና አገናዝቦ
ማመዛዘን በማይችልበት፤ በአንደበቱ መናገርም የተሳነው
ወቅት በመሆኑ ይችው ሴት ያቀረበችው ቅሬታ ደራሲው
ራሱን በአግባቡ መከላከል የማይችልበትን ወቅት ጠብቃ
ያቀረበችው ቅሬታ የመሆኑ ነገር አጠያያቂነቱ እንደተጠበቀ
ሆኖ የደራሲውን ምላሽ ባልሰማንበትና ባላወቅንበት
ምናልባትም ወይዘሮዋ በቃለ ምልልሷ ወቅት
የጠቀሳቻቸው በርካታ 3ኛ ወገን ግለሰቦች ቃል
ባልተሰማበት ሁናቴ ያንድን ወገን አንጀት የሚበላ ትረካ
ብቻ በመስማት ፈጥነን ወደ ፍርድ ማለፋችንና የደራሲውን
ስም በአንድ ጊዜ አፈር ድሜ ማብላታችን ፍትሃዊ ነው
ብየ አላምንም ። አበው ሲተርቱ አጋጥመህ ስማ እንዲሉ
አጋጥመን ለመስማት እድልና ጊዜ መስጠት ሳይሻል
አይቀርም ። ሚዛኑን ለማወቅ ተገቢው ጊዜ አሁን
አይደለምና በአጋዳይ ሚዛን ለፍርድ ባንቸኩል መልካም
ሳይሆን አይቀርም ።
እኔ ለሱ ወይም ለሷ እየወገንኩ አይደለም ። ታሪኩ
እውነት ነው ወይም ሃሰት ነው እያልኩም አይደለም ።
ሃቁን አላወቅኩምና ። ይልቁንስ ያንድን ወገን ድምጽ ብቻ
ሰምተን በፍጥነት መፍረድና ጠርዝ መያዝ ስር የሰደደ
ባህላችን እየሆነ ሃገር እስከማፍረስ እየደረሰ ነውና
አጋጥሞ ዙሪያ ገባውን አድምጦ መፍረድ ምትክ የለሽ
የፍርድ ሚዛን ነው ለማለት መከጀሌ ነው እንዲህ መጻፌ

ሻሎም!!!!

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
የህዝብ ብሶት የወለደው የጀግናው ጠቅላያችን አብይ ወላጅ
አባት ጋሽ አህመድ አሊ አኚህ ናቸው!..እስቲ ክብር
እስጣቸው!..ክብር ይገባዎታል አባባ

@ethio_art
@wegoch
ፌስዳቢ written by danielkibret -reader eyob yonas
ፌስዳቢ በሀገራችን አዲስ ጎሳ
እየተፈጠረ ነው 🙈😁
ዳንኤል ክብረት

፨ከሰርቆ አደሮች ስብሰባ የተወሰደ
፨መጠን 1.9 MB
፨አቅራቢ ፦ ኢዮብ ዮናስ

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch @wegoch
የዞረው ጎዳና


በጠማማ መንገድ ጉዞ የጀመረ
ሲወድቅ ሲነሳ ባለበት አደረ።
መንገዱስ ከራቀ የህልሜ መድረሻ
አንቺንና መጠጥ ሃዘኔን ማስረሻ።
____
ይህ ፅሁፍ የአልኮል መጥጥ ማስታወቂያዎችን የሚነካካ
ነው። ማንኛውንም ግለሰብ ወይም የትኛውምንም አይነት
አምራች ድርጅት አይመለከትም። በአንዲት ነፍስ
የሚብሰከሰክ ግለሰባዊ ትዝብት ነው። ሃሳቡ ቢስማማህ
አንተም ውስጥ የሚብሰለሰል ነገር ስለነበረ ቢሆን እንጂ
አዲስ ተዓምር ፈጥሬልህ አይደለም፤ ሃሳቡ ቢጎረብጥህ
አላማዬ አንተን ማስደሰት አይደለምና ሃሳቤን አክብረህ
ማስታወቂያህንም፣ ጨብሲህንም የመቀጠልና
የማስቀጠል ምርጫው ያንተ ነው።


“ሸገር ላይ አብቦ ሸገር ላይ ያፈራ
የጥንት የማለዳው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ
አብሮ እየዘመነ ከዘመኑ ጋራ
አራዳን ያሞቀ አራዳን ያደራ


ዘላለም ጥም ቆራጭ ዘላለም ፍሰሀ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ የነፍስ እህል ውሃ
ወዳጅነት ጠብቆ ጨዋታ እንዲደራ
ይንቆርቆር ይቀዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ!”


ይህ የማንቆለጳጰሻ ግጥም በጥላሁን ገሠሠ “የጥንቱ ትዝ
አለኝ” ዜማ ታጅቦና በአንባቢው አስገምጋሚ ድምፅ
ግርማ ሞገስ ተላብሶ በሸገር ኤፍ ኤም ሲቀርብ ለጆሮ
ደስ ይላል። ደስ ማሰኘትና ለመጠጥ ማነሳሳት
የማስታወቂያው አላማ በመሆኑ በዚህ በኩል
ተሳክቶለታል። ፋብሪካው ለዚህ ሙገሳ የተጠየቀውን
ቢከፍልም አይቆጨው፤ ለአርቲስቱም ለድርጅቱም የገቢ
ምንጭ ሆኗልና ይቅናቸው።


በግጥሙ ውስጥ ከተካተቱት የማስዋቢዋ ቃላት ጋር ግን
በግሌ ፀበኛ ነኝ። ‘ዘላለም ጥም ቆራጭ’… ‘ዘላለም
ፍሰሃ’… ‘የነፍስ እህል ውሃ’… ‘ወዳጅነት አጥባቂ’…
ምናምን የሚሏቸውን የውዳሴ ቃላት በሰማኋቸው ቁጥር
ግርም ይሉኛል። ገንዘብ ስለተከፈለና እድሉ ስለተገኘ ብቻ
የሚንፎለፎል ቅጥፈት አይጥመኝም። ቢራ በየትኛው
ስሌት ዘላለማዊ ጥም ሊቆርጥ እንደቻለ አልገባኝም።
ዝንታለም ፍሰሃ ሊለግስ ይቅርና በብዙ መከራዎች
ተቀነጣጥሳ ያጠረች እድሜን የባሰ የሚያሳጥርም ይሄው
ልኩ የማይታወቀው አልኮል ነው። የነፍስ እህል ውሃነቱም
ጠግቦ ላላደረ አንጀት የሰማይ ያህል ሩቅ ነው፤ ጠግቦ
ላደረው ግን ምን እንደሆነ አላውቅም።


“ስማ ይሄ እኮ ማስታወቂያ ነው!… ማሻሻጫ እንጂ ሃቅ
አይደለም!… ጅል ነህ እንዴ?!… ምን ታካብዳለህ?…
ክባዳም!” አይነት ሰልጠን ያለ ቡጢ ከሰለጠኑት አካባቢ
የሚሰነዘር ከሆነም ይህችን ጣል አድርገን እንቀጥላለን …


ዘላለም ጥም ቆራጭ ከሆነማ አርኪ
ለዝንታለም ሃሴት ከተሰኘ ምልኪ
የነፍስ እህል ውሃው በወግ ተበጥብጦ
በብልቃጥ በሲኒ ተደርጎ በጡጦ
ልልጆች ለህፃናት ይመረት አደራ
ታላቋን ኢትዮጵያ በቶሎ እንድንሰራ።

ቺርስ
በጊዮርጊስ


በርግጥ የአልኮል መጠጦችን በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣
በተለያዩ የህትመት ውጤቶች እንዲሁም በእስፖንሰር
መልክ ማስተዋወቅ በጭራሽ አይገባም የሚል ደረቅ
አቋም የለኝም። መንግሥትስ ለምን በህግ ‘ፈፅሞ
እንዲከለከል’ አያደርግም?! የምል ወገኛም አይደለሁም፤
አይተዋወቅ ብዬም እየተነሳሁ አይደለም። በህግ የተከለለ
የማስተዋወቅ ስርዓት ይኑረው (ወይም ህጉ ካለ በብርቱ
ይተግበር) ነው መነሻዬ። አዎ በነጋ በጠባ ቢራ ቢራ
አይበሉብን!.. ጎዳናዎቻችንን ሁሉ በቢራ አይሙሉብን!…
ኧረ በዛ!… ኧረ ለከት ይኑረው!… ነው የኔ ሃሳብ። እኛ’ኮ
ባይተዋወቅም በመጠጣት አንታማም!… ኑሯችን ለስካር
ሩቅ አይደለም!… እንኳን አይዞህ ጠጣ ተብለን እንዲሁም
ጠጪዎች ነን… ለዚህ እንኳን ብቁ ነን!…


የኛ አርቲስቶች፣ የኛ አስተዋዋቂዎች፣ የኛ ጋዜጠኞች፣ እና
ሌሎች የሚመለከታቸው ባለሙያዎች አልኮልን
የሚያስተዋውቁበትን መንገድ ልብ ብሎ ላስተዋለው
ያስተዛዝባል ብቻ ሳይሆን ያሳስባልም። በተለይ ይሄን
ማስታወቂያ እየሰሙ የሚያድጉ ልጆችስ ብሎ ማሰብ
ለሞከረ የኔ ብጤ ክባዳም አንገት ያስደፋል።


‘የነፍስ እህል ውሃ ነው’… ‘የዘላለም ፍሰሃ ይሰጥሃል’…
‘ጨዋታህ ያለ ቢራ አይደራም’… ‘ወዳጅነትህ ያለ መጠጥ
አይቀጥልም!’… እያልክ ላሳደግከው ልጅህ ኋላ ላይ
ደግሞ ‘መጠጥ ይጎዳሃል’… ‘ጤናህን ያዛባብሃል’…
‘ከወዳጅ ያጣላሃል’… ምናምን ብትለው “አባዬ ደግሞ
ታሾፋለህ እንዴ?!… አንተ አይደለህ እንዴ ለህዝቡ ስታውጅ
የነበረው?!” ብሎ እንደሚያፌዝብህ ለማሰብ ጥልቅ
ተመራማሪ መሆን የሚሻ አይመስለኝም። ያው እንዳላገጥን
እንለቅ ካልሆነ በቀር…


አብዛኞቹ አርቲስቶች በግጥም፣ በዜማና በሙዚቃ ቅንብር
ሲያንቆለጳጵሱት፤ በተለያየ የምስል ዲዛይን
ሲያስሽሞነሙኑትና ሲያሞጋግሱት ስራዬ ብሎ ላያቸው
አስካሪ መጠጥ የሚያስተዋውቁ ሳይሆን ብርቱ የነፍስ
አድን መድሃኒት ሊያድሉ የሚሰናዱ ነው የሚመስሉት።
አብዛኞቹ ነገረ ስራቸው ቅጥ ያጣ፣ የሚከፈላቸውን ገንዘብ
እንጂ የሚሉትን ነገር ለሽራፊ ሰከንድ እንኳ ያሰቡበት
የማይመስሉ ናቸው። በርግጥ ሁሉም ብሎ በአንድ ላይ
መጨፍለቅ አግባብ አይደለም (እዚህ ውስጥ ያልተካተቱ
አርቲስቶች ይቅር ይበሉኝ) በአብዛኛው ለአይናችን አሊያም
ለጆሯችን የከበዱት አርቲስቶቻችን (ትልልቆቹም
መጤዎቹም) ግን ቢያንስ የአንድ ቢራ አስተዋዋቂ
መሆናቸው የአደባባይ ሃቅ ነው።


በነጠላ ዜማም ይሁን በነጠላ ፊልም ትንሽ ዝና ከተፍ
ካለች ጥቁር መነፅርና ቢራ መለያቸው እየሆነች ነው። ኧረ
ጎበዝ እየተሳሰብን እንጂ!… በጥቁሩ መነፅር ስታዩት ሌላ
ነገር ወይም ሌላ ሃገር እየመሰላችሁ ይሆን እንዴ?!…
እስቲ ከጥቁሩ መነፅር ውጡና ጎዳናዎቻችሁን…
ህዝባችሁን እዩት… በሃላፊነት ጠጡ ከማለታችሁ በፊት
በሃላፊነት ታስተዋውቁ ዘንድ ትለመናላችሁ።


“አውዳመት ሲደገስ ጎረቤት ሲጠራ
ወዳጅ ለመጋበዝ ገበታ ሲሰራ
እንዲሞቅ እንዲደምቅ ጨዋታ እንዲደራ
ይንቆርቆር ይቀዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ


ደስ ብሎ እንዲውል ያውዳመቱ ቆሌ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ አብሮ ይኑር ሁሌ
ወዳጅነት ጠብቆ ፍቅር እንዲደራ
ቅዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ያዘቦት ያውዳመት የሁል ጊዜ ቢራ።”


ያዝ እንግዲህ!… ቢራ ከሌለህ አውዳመት የለም!…
ወዳጅነት የለም!… ጎረቤት የለም!… መሰባሰብ የለም!…
መተሳሰብ የለም!… ፍቅር ብሎ ነገር የለም!… ይልሃል!…
በል እንግዲህ ጠጣና አውዳመትህን አድምቅ!…
ወዳጅነትህንም ቀጥል… ቢራህም ሁሌም አብሮህ ይኑር
ይልሃል!…


እኔም ልጨምርልህ… ከቢራህ የተለየህ እለት ድህነትህና
ድንቁርናህ ፍንትው ብሎ ይታይሃልና በድህነትህ
እንዳታፍር በኋላቀርነትህም እንዳታዝን ለከት የሌለው
አጠጣጥ ጠጣ!… ጠጥተህ ድህነትህን እርሳ!… ይሄንንማ
መፅሐፉም ብሎኛል ካልክም መብትህ ነው…
መፅሐፉንም… ማስታወቂያውንም… እኔንም “እምቢኝ!”
ያልክ ቀን ግን ወዳጅነት እንዴት እንደሚጠብቅና ድህነት
እንዴት እንደሚፋቅ ሊከሰትልህ ጀምሯል ማለት ነው። ያኔ
እናወጋለን!… ላሁኑ ግን ይህችን ሚጢጢዬ ግጥም
እያላመጥክ ቀጥል …


‘አባቱ ደንዳና ብርቱ ጌሾ ወቃጭ፤
እናቱ ታታሪ ብቅል አብቃይ ቀያጭ፤
ኮበሌ ልጃቸው ሆነላቸው በጥባጭ፤
በል ዝም ብለህ ጨልጥ ያገር ሰው ተቀማጭ።’


ላሁኑ ሰላም
ትዝብቱ ግን ይቀጥላል
አብዲ ሰዒድ

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
የንጉሥ ሰለሞን ፍርድ አስደናቂ ታሪክ - በዲያቆን ዳንኤል ክብረት | King Solomon | Deacon…
የንጉሥ ሰለሞን ፍርድ
ዳንኤል ክብረት

፨ ኑ ሀግሬን እናዋልዳት እና ሌሎችም
፨ አጅግ ጡም ወግ ተጋበዙልኝ
፨ አስደናቂ ታሪክ የያዝች
፨ አደራ ስሙልኝ
፨ መጠን 2.4 MB

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch @wegoch
ነጭ ጅብ!!!!


ሁሉም ድግስ ላይ አሳላፊ ሆኖ የማደሽደሽ በሽታ በስነ
ልቡና ሳይንስ መጠሪያ የሌለው ቢሆንም እኔ ግን
የበሽታውን መጠሪያ ""ድግሶማኒያ "" ብየዋለሁ ።
በድግሶማኒያ የስነ ልቡና በሽታ የተጠቃ ሰው ብቻ የትም
ቦታ ድግስ ይኑር እንጅ ቁርሱን ከገዳይ ዳስ፤ ምሳውን
ከሟች ድንኳን ስር ተቀምጦ ይበላል ። ድግሱን እንጅ
ደጋሹን የማያስብ ሆድ የተሸከመ ሰው ከጅብ እኩል ነው

አንዳንዱ ግን አይቀፈውም እንዴ??? ስሙንና ፎቶውን
ከጸጋየ ገብረመድህን / ወይ ደግሞ ከበድሉ ዋቅጅራ /
ወይ ደግሞ ከምስራቅ ተረፈ ጎን እኩል አሰልፎ " ያገሬ
ሰው ነቅታችሁ ጠብቁን፤ እኛ የጦቢያ ባለቅኔዎች "
በቅርብ ቀን በእንትና ከተማ በጥበብ መንደር እንገለጣለን
ብሎ ሲያውጅ አፉን እሬት እሬት አይለውም? ?? ይህች
""እኛ "" የተሰኘችው የመናጆ ቋንቋ እኮ አሻሮ ይዞ ወደ
ቆሎ መጠጊያ ኮፋዳ ናት ። ወዳጄ ቤተመንግስት ብቻ
ሳይሆን የኪነጥበብ መንደር ውስጥ በክብር የተደገሰውን
የጥበብ ድግስ ከነ ጭቂቂታቸው ለመዋጥ የሚሰለፍ
የቀን ጭብ እየመጣ ስለሆነ በራችሁን ዝጉ ። ድግስ
በታየበት ደጀ ሰላም በሙሉ ከሊቃውንቱ / ከጠቢባን ጎን
እኩል ሱክ ሱክ እያሉ ማውደልደል ሊቅነትን ሳይሆን
ቅልውጥናን ያስለምዳልና ማነህ እንደ ባልንጀሮችህ
በወዝህና በጥረትህ እንጅ ከሊቃውንት / ከጠቢባን እኩል
""እኛ" እያልክ ሊቃውንቱን /ጠቢቡን ወደ ራስህ ዝቅታ
አታውርድብን! !! ከነ ክብሩ ጦም ያደረ ከጠቢብ እኩል
ነውና ጦም ማደርን ተማር። ለካንስ
ውብ የሆነው ኪነ ጥበብ ትል እንደበላው እሸት (የጉድ
እሸት)) ምንም ሆኖ አደባባይ ላይ ሲሰጣ ማየት
ያማል!!!!!

እኝክ ይላል የወሎ ሰው!!!!

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch

ሸጋ ሸጊቱ ጁምኣ!!!!!
የፌስቡክ እንቅስቃሴአችንን ብናቆም ይሻለናል!
---
ምክንያት: እየተደማመጥን ስላልሆነ
----
ይህንን የጻፈው: አፈንዲ ሙተቂ
-----
እኔ የምለው? ታሪክን አታውቁትም ማለት ነው?
ታላላቆቻችሁን አትጠይቁም ማለት ነው? ይገርማል።
እስቲ አንድ ነገር ላስታውሳችሁ። የሩዋንዳው ጭፍጨፋ
እንዴት ነበር የተጀመረው? ረሳችሁት ማለት ነው?
የዘመኑ የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጁቪኔል ሀቢየሪማና
እኤአ ሚያዚያ 6/1994 ከቡሩንዲው አቻቸው ጋር
የሚጓዙበት አውሮፕላን በኪጋሊ ከተማ ባለው የአየር
ማረፊያ ለማረፍ ሲቃረብ ከምድር በተተኮሰ ጥይት
(መትረየስ) ተመታ። ሁለቱ ፕሬዚዳንቶችም ተገደሉ።
በዚህም የተነሳ በስልጣን ጉዳይ ለዘመናት በጥርጣሬ
በሚተያዩትና ሁቱ እና ቱትሲ በሚባሉት የሀገሪቱ ታላላቅ
ጎሳዎች መካከል ከባድ ጦርነት ተቀሰቀሰ። የሰው ልጅ
እንደ ከብት መተራረድ ጀመረ። እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ
በሁለት ወር ውስጥ ብቻ 800 ሺህ ሰው ተጨፈጨፈ።
(ጭፍጨፋው በዚህ ፍጥነት የተካሄደው በመታወቂያ
ወረቀት ላይ የጎሳ ስም ተለይቶ ይጻፍ ስለነበረ ነው)።
በኋላ ላይ ነገሩ ሲጣራ አውሮፕላኑ የተመታው የሩዋንዳ
አርበኞች ግንባር በተኮሰው መሳሪያ መሆኑ ታወቀ።
እንግዲህ የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር በዚህ ዘዴ ህዝቡን
አስጨርሶና አጨራርሶ ነው ስልጣን የያዘው።
----
ትናንትና (ሰኔ 16/2010) ለኛ የታሰበው ይህ ነበር። ክቡር
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢገደሉ ኖሮ የሚጠብቀን አደጋ ይኸው
ነው። ለዚህ ደግሞ የማጅራት መቺው ስርዓት በቂ የሆነ
የጥላቻና የበቀል ዘር በመላው ሀገሪቱ ዘርቷል።
በመታወቂያ ላይ ብሄርን ለይቶ መጻፍ፣ ሰውን በብሄር
እየለዩ ከትውልድ ስፍራው ማፈናቀል፣ ብሄርና ጎሳ እየለዩ
ከስራ ማባረር፣ ብሄርን ከብሄር ጋር ማጋጨት፣ ለጥቂት
ብሄሮች ብቻ የልዩ መብት ተጠቃሚነት መስጠት፣
በሀይማኖት ለይቶ ማጥቃት፣ በተለያዩ ሀይማኖት
ተከታዮች መካከል ጥላቻን መዝራት፣ ቤተ እምነቶችን
እያፈረሱ በሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች ማሳበብ ወዘተ
በሰፊው ይካሄዱ ነበር።
በሰለጠነው ሀገር የሚሠሩ የኢንተሌጀንስ መሥሪያ ቤቶች
የየሀገራቱን ጸጥታና ደህንነት ነው የሚያስከብሩት።
የሀገራችን የኢንተሊጀንስ መሥሪያ ቤት ግን ጥላቻንና
ሁከትን ሲዘራ ነበር የቆየው። ክፋቱ ደግሞ የስርዓቱን
መሠሪነት አውቀን በመንቃት ፈንታ ሁላችንም ስሜትን
እየተከተልን ጎል የምንገባለት መሆኑ ነው።
እስቲ አስቡት! የትናንትናው ጥቃት ዒላማውን ቢመታ
የሀገራችን መፃኢ እድል ምን ይሆን ነበር? እኔ እንጃ!!
የኢትዮጰያ ህዝብ ሃይማኖተኛ በመሆኑ እንደ ሩዋንዳው
ዓይነት የከፋ አደጋ ላይከሰት ይችላል። ነገር ግን ሁከትና
ግርግር ተፈጥሮ ማጅራት መቺዎቹ የተመኙት ነገር
ሊሰምርላቸው ይችል ነበር። ይኸውም ህዝቡ
የተጎናፀፋቸውን ድሎች መንጠቅና የቀድሞውን የአፈና
አገዛዝ መመለስ ነው።
----
ጓዶች!
ብዙዎቻችሁ ከትናንት ጀምሮ ስለ ፖሊሶቹ መኪና
እየጻፋችሁ ነው። በኛ በኩልስ የሚጠበቅብንን አድርገናል?
በጭራሽ! ጥንቃቄ በጣም ይጎድለናል። እጅግ በጣም!
ከፍተኛ መዝረክረክ ታይቶብናል። እስቲ ባለፉት ጥቂት
ቀናት ያየናቸውን እንከልስ!
1 ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ እና አቶ ጀዋር
መሀመድ የስርዓቱን መሰሪነት በመጠቃቀስ ጥንቃቄ
እንድናደርግ እየደጋገሙ ሲመክሩን ነበር። ምክራቸውን
በበቂ ሁኔታ ተግባራዊ አድርገናልን? አላደረግንም።
2. በወያኔ ስርዓት ሰውን ደብድቦ ማሰቃየት በዚህ ሳምንት
የተጀመረ ይመስል ከሀዋሳ የተቀዳውን ቪዲዮ በዚህ
ወሳኝ ወቅት በሶሻል ሚዲያው ላይ ማሽከርከር ምን
ይባላል? የሰልፉ ቀን እስኪያልፍ ድረስ መታገስ
አይቻልምን? በፌስቡክ ላይ በቆየሁበት ዘመን በመቶ
የሚቆጠሩ ተመሳሳይ ቪዲዮዎች ደርሰውኛል። ጊዜውንና
ወቅቱን ያልጠበቀ ከሆነ ሼር አላደርገውም። ብዙዎች ግን
የሰልፉ ቀን እስኪያልፍ በመጠበቅ ፈንታ እየደጋገሙ
ቪዲዮውን ወደኔ ኢንቦክስ ይልኩታል (ቲሽ! በዘበዛ!
ብሽቅ! ትልቅ የምትሉት ሰው ሁሉ ነው እንዲህ
የሚያደርገው)።
አዎን! ቪዲዮው በአዋሳ ተቀድቷል። ነገር ግን በዚህ ሰዓት
ከማጅራት መቺዎቹ ቤት የተለቀቀ ለመሆኑ
አልተጠራጠርኩም። ስለ ፍትሕ መናገር ተገቢ ነው። ነገር
ግን ሀገር እንዳይበጠበጥ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
"አጥፍተውን ሊጠፉ የተነሱ የቀን ጅቦችን እንከላከል"
የተባለው ለዚሁ ነው።
3. ሰልፉ ቦታ ስትሄዱ ከክብር ትሪቡኑ ራቅ ብላችሁ ቁሙ
ተብላችሁ ነበር። ሰልፈኞቹ የሚቆሙበት ስፍራ ከክብር
ትሪቡኑ (ከመድረኩ) ቢያንስ ሽጉጥ ተተኩሶ ጉዳት
ማድረስ የማይችልበት ርቀት ያህል ሊኖረው ይገባ ነበር።
ነገር ግን ተግባራዊ አልተደረገም። የህንዶቹ ኢንዲራ
ጋንዲና ራጂቭ ጋንዲ (እናትና ልጅ)፣ የፓኪስታኗ ቤናዚር
ቡቶ፣ የኮንጎው ፓትሪስ ሉሙምባ የሞቱበት ሁኔታ ተረስቷል
ማለት ነው።
ውጥረት ባለበት ሀገር መሪው በአደባባይ ስብሰባ ላይ
ከተገኘ ተመሳሳይ ነገር መከሰቱ የሚጠበቅ ነው
(በነገራችን ላይ በኋላ ላይ በወጣው ቪዲዮ እንዳየነው
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረገው ጥበቃ በጣም የሳሳ
ነው። ፈጣሪ በጥበቡ አትርፎናል እንጂ ትልቅ ጥፋት
ተደግሶልን እንደነበረ በቀላሉ መረዳት ይቻላል)።
4. "ሶሻል ሚዲያውን ስትጠቀሙ የብሄርን ስም
እየጠቀሳችሁ ማንንም አትዝለፉ" የሚለው ምክርም
እየተሰራበት አይደለም። ፓርቲና ህዝብን መለየት፣ ፓርቲና
ቋንቋን መለየት፣ ግለሰብንና ህዝብን መለየት የሚሉት
መርሆዎች በትክክል እየተሰሩበት አይደለም። በዚህ
ሳቢያም የተወሳሰበውን ችግራችንና ፈተናችንን ማቃለል
አስቸጋሪ እየሆነብን ነው።
-----
ወዳጆች
ማንኛችንም በፌስቡክ በምንለጣጥፈው ነገር
እየተከፈለንና የተለየ ጥቅም እያገኘንበት አይደለም።
በአንፃሩ ብዙ ነገር እየሰዋንበት ነው እዚህ ላይ
የምናድረው (በየጊዜው የሞት ዛቻ ጭምር ሲሰነዘርብን
እንዳለየን ሆነን ነው የምናልፈው፣ የግል ስራችንንም
መዝጋት ሲኖርብን እንዘጋለን)።
እኛን እዚህ ያሰባሰበን ሀገራችንና ህዝባችን ነፃነትን
በማያውቁ ጨካኝ ገዥዎች እጅ መውደቃቸው ነው።
ገዥዎቻችን የዘረጉት የማጅራት መቺ ስርዓት
ከሚወድቅበት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል። ስለዚህ
ተባብረንና ተደማምጠን የመከራውን ቀን በጋራ ትግል
ልናልፈው ይገባል።
ካልተደማመጠን የቀን ጅብ ብቻ ሳይሆን የቀን ቀበሮ፣
የቀን ተኩላ፣ የቀን ዘንዶ፣ የቀን ድራጎን፣ የቀን እፉኝት
እስከ ቤታችን ድረስ ገብተው እየዘነጣጠሉ ይበሉናል።
ስለዚህ እንደማመጥ! እንተባበር! እንደመር! አንድ እንሁን!!
ይህንን ስርዓት በጋራ አሽቀንጥረነው ልጆቻችን በነፃነት፣
በእኩልነትና ከዘረኝነት በፀዳ መንፈስ እንዲያድጉ እድል
እንፍጠርላቸው።
------
ድል ለሰፊው ህዝብ!
Injifannoon Ummata Bal'aaf!
ዓወት ንሓፋሽ!
Victory to the Mass!
አል-ዒዘቱ ሊ-ሻዕብ

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የዓለም ፀሐይ ዓለም . . .

ዓለም ፀሐይ ወዳጆ . . .


አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆን የማያውቅ የጥበብ
ቤተሰብ ይኖራል ብዬ አልገምትም… ከኖረም ከቲያትሩም፣
ከትወናውም፣ ከዘፈኑም፣ ከግጥሙም ዓለም ራሱን
ያራቀ… በስሚ ስሚ ወሬ እንኳን በኪነ ጥበብ ዘርፍ
ነፍሱን ያላፀደቀ መሆን አለበት… ዓለም ፀሐይ ዘርፈ ብዙ
የሆነች የጥበብ ፈርጥ ናት!… የተውኔት ጸሐፊ፣ የቲያትር
አዘጋጅ፣ ተዋናይ፣ ገጣሚ ከመሆኗም በተጨማሪ
የኢትዮጵያ ሕጻናት ቲያትር መስራች እንዱሁም በውጭው
ዓለም በተለይም በአሜሪካ ኢትዮጵያዊ የጥበብ ስራዎች
ከኢትዮጵያዊያን ልቦች እንዳይጠፉ በብርቱ የምትንቀሳቀስ
የጥበብ አድባር ናት!… ጣይቱ የጥበብ ማእከልን
ይጠቅሷል…


የሷን የጥበብ ስራዎች በሙሉ ልዘረዝር አልተነሳሁም!…
ሁሉም በየመስኩ እንደመልካቸው ለየብቻ ሊዘርዘሩና
ሙያዊ ትንተና ሊሰጥባቸው የሚችሉ ናቸው… ስለ ትያትር
ስራዎቿ ለብቻ… በመጽሃፍና በሲዲ ስላሳተመቻቸው
ግጥሞቿ ለብቻ… ለበርካታ ዘፋኞች ስለሰጠቻቸው የዘፈን
ግጥሞች ለብቻ.. እያልን ከጥበብ ባሕሯ ልንጨልፍ
ይቻለናል!… እናም ይህ ጽሁፍ ትኩረት የሚያደርገው
የዘፈን ግጥሞቿ ላይ ብቻ መሆኑን መግለጹ
ያስፈልገኛል…


አብዛኞቻችን ብዙውን ጊዜ ትኩረት የምንሰጠው ለዘፋኞች
እንጂ ለግጥምና ዜማ ደራሲዎችም ሆነ ለአቀናባሪዎች
አይደለም… በእርግጥ ዘፈን የድምጽ ስራ በመሆኑ ዘፋኙን
ማወደስና ማክበር የተገባ ነው… አንድ ሙዚቃ ሙሉእ
ሆኖ ቀልብን እንዲገዛ የሁሉም አስተዋጽኦ የየራሱ ዋጋ
እንዳለው መዘንጋቱ ግን የጥበብን ውህደት እንደመዘንጋት
ይቆጠራል… ዜማ ያለ ግጥም… ግጥምም ያለ ዜማ…
ሁለቱም ያለ ጥሩ ቅንብር ለመንፈስ እርካታን የሚለግስ
ዘፈን ሊሰጡን አይቻላቸውም… ሶስትም አንድም
እንደማለት ነው… የማይነጣጠሉ!… ዓለም ፀሐይ
የምትታወቀው ውስጥ ዘልቀው በሚገቡ ግጥሞቿ ነው…
እናም ግጥም ላይ ብቻ ትኩረት አደርጋለሁ…


ከወራት በፊት ስለ ዘፈን ግጥሞቿ አወራኋት… ባጋጣሚ
ውይይታችንን የቀረጽኩበት ድምጽ መቅጃ ከጄ ወጣ…
በሲዲ አሊያም በሌላ መሰል ነገር አልገለበጥኩትም
ነበርና ተበሳጨሁ… በድጋሚ ላውራሽ ማለቱ ደግሞ እሷን
ማድከም እንደሆነ ተሰማኝ… እፍረትም ሸንቆጥ አደረገኝ…
እናም መልሼ እስካገኘው መጠባበቅ ግድ ሆነብኝና
እስካሁን ቆየሁ… መቼም ቅር እንደማትሰኝብኝ እምነቴ
ነው… ከራሷ የሰማሁትን ለማጠናቀር ስለፈለግኩ እንጂ
በተባራሪ የሰማኋቸውን እንዲሁም ካሴቶች ላይ ያየኋቸውን
ለቃቅሞ መጻፍ እንደሚቻለኝ ዘንግቼው አይደለም…
ጊዜዋን ሰውታ ስለ ስራዎቿ ስላዋየችኝ እጅግ
እያመሰገንኩ ከራሷ አንደበት የሰማሁትን በራሴ መንገድ
ለመነካካት እሞክራለሁ…. እጅግ ከባድ ቢሆንም…


ከ400 በላይ የዘፈን ግጥሞች . .

.
ስለ ሙሉ የዘፈን ግጥሞቿ በዚህ ጽሁፍ ለመዘርዘር
መሞከር የማይታሰብ ነው… ምን ያህል ግጥሞች ለምን
ያህል ዘፋኞች እንደሰጠች በእርግጠኝነት ለመናገር
ይቸግራታል… “የማታ እንጀራ” የተሰኘው የግጥም
መጽሐፏ ሲመረቅ በድምጽ ባለሙያዎችና በጓደኞቿ
ትብብር የተዘጋጀ ‘ሰርፕራይዝ’ አይነት ስጦታ
ተበረከተላት… ስጦታው ሲታይ እስካሁን የሰራቻቸውን
የዘፈን ስራዎች ያሰባሰቡ ሲዲዎች ነበሩ… በደስታና
በአግራሞት መሃል ሆና አመስግና ተቀበለቻቸው… በኋላም
ከ400 በላይ የዘፈን ግጥሞች ለ47 ዘፋኞች እንደሰጠች
ተረዳች… ተገረመችም… ተደሰተችም… አመሰገነችም…


ምንም እንኳ ወዳጆቿ የቻሉትን ያህል ለማሰባሰብ
ቢሞክሩም ሙሉ ነው ለማለት ግን አይቻልም…
ምክኒያቱም በካሴት የመቀረጽ እድል ያላገኙ በድሮው
ጊዜ በቲያትር ቤቱ የባሕል ክፍል ይዘፈኑ የነበሩ ዘፈኖችን
ማካተት አልተቻለምና ነው… እንደ ምሳሌም የነ ጠለላ
ከበደን፣ የነ ፀሐይ እንዳለን፣ የነ መልካሙ ተበጀን በካሴት
ያልታተሙ ዘፈኖች መጠቃቀስ ይቻላል….


የሷን ግጥም ያልዘፈነ ዝነኛ ድምጻዊ ማግኘት ይከብዳል
ከክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ ጀምሮ እነ ማሕሙድ
አህመድ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ ፀሐዬ
ዮሐንስ፣ ሻምበል በላይነህ፣ ዳዊት መለሰ፣ ኅይልዬ ታደሰ፣
ግርማ ተፈራ፣ ብዙአየሁ ደምሴ፣ ሰጠኝ አጣናው
እንዲሁም ከሴቶች አስናቀች ወርቁ፣ አስቴር አወቀ፣ ኩኩ
ሰብስቤ፣ በዛወርቅ አስፋው፣ አቦነሽ አድነው፣ ሂሩት በቀለ፣
ፋንትሽ በቀለ፣ አሰፉ ደባልቄ እያልን ከብዙ በጥቂቱ
መጠቃቀስ ይቻለናል… የቻልኩትን ያህል በቀጣይ
ለመነካካት እንደምሞክር ቃል እየገባሁ ላሁኑ ሙሉቀን
መለሰ ላይ ብቻ ትኩረት አደርጋለሁ…

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሙሉቀን በተነሳ ቁጥር የዘፈኖቹን ግጥሞች ውበትና
ጥልቀት… የተሸከሙትን መልእክትና ቁምነገር ያለማንሳት
አይቻልም!… ዘመናችንን ሙሉ ካጣጣምናቸው
ከአብዛኛዎቹ ድንቅ ግጥሞች ጀርባ ደግሞ ዓለም ፀሐይ
አለች… ሙሉቀን በአብዛኛው የእሷን ግጥሞች ሲጫወት
ነው የኖረው… “ሌቦ ነይ” ከሚለው የመጀመሪያ የካሴት
ስራው ጀምሮ ዘፈን እስካቆመበት ጊዜ ድረስ የዓለም
ፀሐይን ግጥሞች አዚሟቸዋል… ባጋጣሚ ሙሉቀንን
ብታገኘውና “እንትን የሚለው ዘፈንህ ግጥሙን ማን ነው
የጻፈው?” ብትለው ድንገት የሰጠውን ገጣሚ ቢዘነጋው
አልያም በጊዜያዊነት ግር ቢለው በርግጠኝነት “ያው
ዓለም ፀሐይ ትሆናለች” ብሎ ነው የሚመልስልህ….


ሙሉቀን እጅግ ውብ የሆኑ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቹን
ለኢትዮጵያ ሙዚቃ አበርክቶ ዓለማዊውን ዘፈን
የተሰናበተና መንፈሳዊውን ዓለም የተቀላቀለ ብርቅዬ
አርቲስት ነው… የቋንቋው ውበት… የአዘፋፈኑ ለዛ…
የሚጫወታቸው ግጥሞችና ዜማዎች… ቅንብሮቹ… ብቻ
በሁሉም የተዋጣለትና የተለየ ቦታ መቀመጥ የቻለ
ድምጻዊ ነው… ዓለም ፀሐይ ራሷ ምንም እንኳ ስራዎቿን
የተጫወቱላትን ዘፋኞች በሙሉ እንደየመልካቸው
ብትወዳቸውም… ብታከብራቸውም… ብታደንቃቸውም…
ለሙሉቀን ያላት ስሜት ግን ይለያል….


ሙሉቀን ቋንቋ አዋቂ ነው… ቋንቋን የማሳመር ተክኖ
አለው… ዜማ መርማሪ ነው… አንድን ዘፈን የሚሰራው
ብዙ ተጨንቆና ተጠቦ… ብዙ ዜማዎችን አጥንቶና
መርምሮ… ብዙ ጊዜ ወስዶ… ከነፍሲያው ጋር አዋህዶ
ነው… ጥድፍ ጥድፍ ያለ ጥናት አይወድም!… የተዋከበ
ቀረጻም አይዋጥለትም!… ያልመሰለውን ቅንብር
አይቀበለም!… በወቅቱ የነጋዴዎችን ተጽእኖ ተጋፍጦ
ለጥበቡና ለስሜቱ ያደረ በሳል አርቲስት ነው!… በዚህም
የኢትዮጵያ ሙዚቃ በቅንብር ረገድ እንዲያድግ የበኩሉን
አስተዋጽኦ አድርጓል… እነ ሙላቱ አስታጥቄን የመሳሰሉ
ሊቅ አቀናባሪዎች ስራዎቹን ተግተው እንዲያቀናብሩለት
ድርሻውን ተወጥቷል… በክፍያም ረገድ በዘመኑ ለዘፋኞች
የሚከፈለው ክፍያ ከፍ እንዲል ፈር የቀደደ ነው…


ዓለም ፀሐይን የሚያበሳጫት አንድ ችግር ግን ነበረበት…
ግጥሞቿ ውስጥ የባህል፣ የህዝብ፣ አሊያም ገጣሚያቸው
በውል የማይታወቁ ስንኞችን እያመጣ ይጨምራል…
አንዳንድ ዘፈኖቹ ላይ ግማሹ ግጥም የሷ ይሆንና ግማሹ
የሌላ ይሆናል… ይህን ስራውን አትወድለትም!…
“እንደዚህ አታድርግ ግጥሞቹን እንዳሻሽላቸው ከፈለግክ
እራሴው ላሻሽላቸው እንጂ የሌላን አምጥተህ ስራዎቼ
ውስጥ አትጨምርብኝ!” ብትለውም እሱ ከወደደና
ካመነበት ያደርገዋል… ካሴቱ ከወጣ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ
ከፊቷ ይሸሻል… “እስቲ ጥይቋት… ምን አለች?…
ተቆጣች?…” እያለ ይጠይቃል… በኋላም ስራው
ይቀጥላል… እንዲህ አይነቶቹን ዘፈኖች በሙሉ ልብ የኔ
ናቸው ለማለት አትደፍርም… ይህ ግን ባንዳንዶቹ ስራዎቿ
እንጂ በሁሉም ላይ አይደለም…



በአብዛኛው ሙዚቃ አፍቃሪ እጅግ የሚወደዱት እነ
“ገላዬዋ”… “ሰውነቷ”… “ወይ እዳዬ”… “አልዘገየሽም
ወይ”… “ቁመትሽ ሎጋ ነው”… “መውደዴን ወደድኩት”…
“ቁረጥልኝ ሆዴ” እና ሌሎች በርካታ ስራዎቹ የሷ
ግጥሞች ናቸው… ጥቂት ስንኞችን ልቆነጣጥርና ለዛሬ
ላብቃ…



1) ♪♪ ገላዬዋ ♪♪
♪♪ ገላዬዋ ነይ ነይ
ገላዬዋ ነይ ነይ
ሰው በገላው ውበት ይናፈቅ የለም ወይ♪♪


♪♪ ያይን ሽፋሽቷን ቅንድቧን አድንቁ
ጣቷን አስተውሉ ስትተዋወቁ
ዓይኗን ተመልከቱት እኔው ፈቅጃለሁ
ከኔው ጋር እያለ ሲዋሽ ይዤዋለሁ ♪♪


♪♪ አንገቷን አድንቁ መቃ ነው ብላችሁ
አካባቢ ሲቃኝ ታገኙታላችሁ
ቁጣ ግልምጫውን እችላለሁ ያለ
ጡቷን ቢመለከት ከልካይ አንድም የለ ♪♪


♪♪ ጥርሷን አሳስቁት ዝምታን አያውቅም
ፈገግታ በሷ ዘንድ ብዙ አያስጨንቅም
ዳሌ አቀማመጡን እዩት ለናሙና
እግሯን አትንኩብኝ መምጫዋ ነውና♪♪


♪♪ ገላዬዋ ነይ ነይ
ገላዬዋ ነይ ነይ ♪♪


2) ♪♪ ቁመትሽ ሎጋ ነው ♪♪


♪♪ ቁመትሽ ሎጋ ነው ሰንደቅ ያሰቅላል
የሰላም የፍቅር ምልክት ያሳያል ♪♪


♪♪ አሸን ክታብ ድሪ አልቦ ለቋ* ቀርቶ
ሽመል ሰውንተሽ ይታያል አብርቶ
ድሪውን ጠልሰሙን ገላሽ ባያደርግም
የፍኝ እኩሌታ ውበትሽን አይነፍግም ♪♪


♪♪ ለምድና ጎፈሬ ምን ይሆነኝ ብለሽ
ጌጤ መድመቂያዬ እራስ ወርቄ አንቺ ነሽ
የኔ በትረ ሙሴ መጥፎሽን አልወድም
ጠምበለል ነሽ ሎጋ ይህንን አልክድም ♪♪


♪♪ ቁመትሽ ሎጋ ነው ሰንደቅ ያሰቅላል
የሰላም የፍቅር ምልክት ያሳያል ♪♪


3) ♪♪ መውደዴን ወደድኩት ♪♪


♪♪ አንቺን መሳይ ቆንጆ ለኔ የሰጠኝን
መውደዴን ወደድኩት ያንቺ ያረገኝን
የኔ ያረገሽን መውደዴን ወደድኩት
ሳስብ ሳሰላስል ቆየሁ ከወሰንኩት ♪♪


♪♪ ሃር ከመሰለው ከጸጉርሽ ጀምሮ
እንከን የሌለብሽ ውብ ነሽ በተፈጥሮ
ትኩስ የፈነዳው ጽጌሬዳ ከንፈር
እስኪ አፍ ያውጣና ውብትሽን ይናገር ♪♪


♪♪ የሐረር መንደሪን የመስከረም አደይ
የሞጆ ብርትኳን የነሐሴ እንጉዳይ
ከንፈርሽ እንጆሪ ቀይ ጽጌሬዳ
ወፍ ጭጭጭ ሳይል ማልዶ የፈነዳ ♪♪


♪♪ አንቺን መሳይ ቆንጆ ለኔ የሰጠኝን
መውደዴን ወደድኩት ያንቺ ያረገኝን
የኔ ያረገሽን መውደዴን ወደድኩት
ሳስብ ሳሰላስል ቆየሁ ከወሰንኩት ♪♪


. . . በመጨረሻም እስቲ እናንተም የምታውቁትን
ስራዎቿን ጻፍ ጻፍ አድርጉልኝ… ከዓለም ፀሐይ ጋር
ያወጋነው ብዙ ነው… በቀጣይ ደግሞ ከሌላ ብርቅዬ
ድምጻዊ ጋር ይዣት እመለሳለሁ… ረጅም እድሜ ላንቺ
ዓለም ፀሐይ… ሰላም ለሁላችን!!!


ክብር ለጥበበኞች!
አብዲ ሰዒድ
2005 E.C

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
አብይ ና ቴዎድሮስ …..ለባለራእዮች የማትመቸ አገር፡(በለዘብተኛ ቋ.ተ
አንዲ ማኛ)



በዚያን ዘመንም አገሪቷ በጎጥ የተከፋፈለች ነበረች፡፡መሳፍንቱ ሁላ በየጎራው የራሱን አስተዳደር መስርቶ አገር በሺ ብጥስጣሽ መንግስታት ተካፋፍላ በታሪክ እስከ የመን ድረስ ግዛት እንደነበራት የተነገረላት ታላቋ ኢትዮጲያ አይሆኑ ሆና ባለችበት ወቅት" ካሳ" የሚባል ከቆመበት መሬት የትና የት አሻግሮ ማየት የሚችል ባለ ታላቅ ራእይ ደቦል አንበሳ ቋራ ላይ ተነሳ፡፡….. ከመቶ ሰባ ምናምን አመታት በኋላ ኢትዮጲያ ዳግም እንደዘመነ መሳፍንት ዘመን በጎጥ ተከፋፍላ የመበጣጠስ አደጋ ውስጥ ወደቀች፡፡ ፈጣሪም የቃልኪዳኗን ሀገር ፈጽሞ አልረሳትም ነበረና አብይ አህመድ የሚባል ገራም እና ባለ ትልቅ ራእይ ከጅማ አስነሳ፡፡….. ካሳም ሆነ አብይ ማንም ሳይገምታቸው ራእያቸውን በሆዳቸው ይዘው የፊተኛው በፋሲል ቤተመንግስት የኋላኛው በሚኒሊክ ቤተመንግስት ሰተት ብለው ገቡ፡፡
ካሳም "ቴዎድሮስ" የሚለው ስም ኢትዮጲያን የሚታደግ የንጉስ ስም ለመሆኑ ትንቢት ነበረውና ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ተብሎ በኢትዮጲያ ምድር ነገሰ፡፡ ነገር ግን ገና ካሳ ከነገሰበት ቀን ጀምሮ ጥቅማቸው የተነካባቸው መሳፍንቶች በየቦታው ማመጽ ቀጠሉ፡፡….በሰሜን የትግራዩ ደጃች ውቤ ዘመድ የነበረው ደጃዝማች ንጉሴ ፡ በጎጃም
ደጃች ተድላ ጓሉ..እነ ብሩ ሃይሉ…የደጃች ክንፉ ልጅ ..ልጅ ጋረድ የሸዋው የልኡል ሳህለስላሴ አመጽ ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስን በዘመቻና እና በጦርነት ባክኖ እና ተዋክቦ እንዲቀር አደረጉት፡ አንዱን አመጽ አብርዶ ከብዙ ድካም በኋላ ከመናገሻው ሲደርስ ሌላኛው አመጽ ፈንድቶ ይጠብቀው ነበር..….ያንዱን እሳት ሲያበርድ ሌላኛው
ይለኮሳል…ግና ምንም እንኳን እጅግ ፈታኝ ቢሆንም ቴዲ የኢትዮጲያን
አንድነት በሰይፍ ሃይል አምጥቶላት እንደነበር ሁሉም ይስማማል፡፡.. አብይ ስልጣን ከያዘ በኋላ በተመሳሳይ ሁኔታ በየቦታው አመጽ ይበረታበት ይዟል….ሁኔታው የተለያየ ቢመስልም በይዘት ግን ያው ነው ፡፡እነ ደጃች ተድላ ጓሉ በነ አብዲ ኢሌ ተተክተዋል…እነ ሹም ጎበዜ በነ አህመድ ናስር ተቀይረዋል..እነ ብሩ ሃይሉ በእነ ሽፈራው
ሽጉጤ እነ ልጅ ጋረድ በነ ሲራጅ ፈጌሳና ደሴ ዳልኬ እነ ደጃች ንጉሴ በእነ አባይ ጸሃዬ ቢቀየሩም አሁንም በተቃራራቢ የታሪክ ሽክርክሪት ውስጥ መሆናችን አይካድም፡፡ ….በቴክኖሎጂ እርዳታ ሰውየው ከቦታ ወደቦታ እየዞረ ወደ ዋና ከተማው ስለሚመለስ እንጂ በአገሪቷ ሆነ ተብሎ በተቀነባበሩ አመጾች እዚህም እዛም የሚሎኮሱ እሳቶችን ለማጥፋት እንደባጀ ነው፡፡ የሚገርመው ደግሞ ቴዎድሮስ ስልጣን ከያዘ በኋላ ባሉት የመጀመሪያ ሁለት አመታት ማለትም ከ1855-1857 (እ.ኤ.አ).. ብቻ 17 ግዜ
የግድያ ሙከራ የተደረገበት ሲሆን አብይ ስልጣን ከያዘ ገና በ3 ወሩ የመጀመሪያው የግድያ ሙከራ በአደባባይ ተፈጽሞበታል….የወደፊቱን
ባናውቅም እቺ አገር ባለራእይ አይበርክትልሽ ተብላ የተረገመች
ይመስላል፡፡ ግርም የሚለኝ ብርሃኑ ዘሪሁን በጻፈው "የታንጉት ሚስጥር" በሚለው ታሪክ ቀመስ ልብወለድ ላይ አጼ ቴዎድሮስ ለታንጉት እንዲህ ሲሏት
ይነበባል…"አሁን ደግሞ እኛ የታላቋን ኢትዮጲያ ዝናዋን ለመመለስ ስንፈልግ ጠላት ሊያደክማት የሚሰራውን ይሰራል…ይኸ ተንኮል ያልገባው የእኛ ሰውም ተነሱ ጋር አብሮ ሊያፈርስ ይቆፍራታል፡፡ ሌላው ደግ ይኸው የዘመነ መሳፍንት ጨምላቃ የቀድሞ ኑሮውን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥሮት ያ ለምን ተነካብኝ ብሎ በዚህም በዚያም ይዶልታል…"… (ገጽ 67) አብይ በተመሳሳይ ይህንን ነገር በተደጋጋሚ ሲናገር ይደመጣል……."ስልጣን ይዞ የቆየው ክፍል አገሪቷን ከፍላ የማትጨርሰው የብድር ማጥ ውሥጥ ዘፍቋት ሲያበቃ ጭራሽ በፍቅር የያዝከውን እንደያዝክ ተደመር ቢባል የሌብነቱን የኑሮ ዘመን እንደኑሮ ቆጥሮ ተደመር ቢባል አሻፈረኝ ብሎ በዚህም በዚያም ይዶልታል…" ቃል በቃል ባይሆንም አጼ ቴዎድሮስ አጋሰስ የሚሏቸውን አብይ ደግሞ የቀን ጅቦች በማለት የሚጠሯቸውን የቀደምት ባለስልጣናት በተመሳሳይ ሃሳብ ያማርሯቸዋል፡፡

በሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም የቀን ከጠዋቱ 3፡00 ላይ አብይም ሆነ ሰፊው ህዝብ ጠላቶቹ የደገሱለትን ሳያውቅ በመስቀል አደባባይ ተገኝቷል…እኔም በዚህ የህዝብ የፍቅርና የአንድነት ማእበል ውስጠ
ሆኜ …..በአእምሮዬ ውስጥ በለሆሳስ ሳዳምጥ የነበረው ይሄንን የቴዲን ግዜ አይሽሬ ዘፈን ነበር . "….ዝግባ ሚያሳክለን አንድ ፍቅር አጥተን … ዝግባ ሚያሳክለን አንድነትን አጥተን ከፊት የነበርነው ከሰው ኋላ ቀርተን …….. አናሳዝንም ወይ …… እርርር………..
ጎንደርና ጎጃም ወሎና ትግራይ … ኦሮሞና ተጉለት ሆነን አንድ ላይ"
ጉራጌና ሀረር …..ዶርዜ ወላይታ … ቤኒሻንጉል ሶማሌ አፋር አሳይታ
ግመሌን ላጠጣት እንደ አፋር ተጉዤ…… ግመሌ ላጠጣት ቀይባህር ተጉዤ
አንድ ገመድ አጣሁ……. ልመልሳት ይዤ
የአንዲት እናት ልጆች መሆናችን አውቀን…. ጎሳና ሃይማኖት ሳይነጣጥለን
ምን ይሳነን ነበር ብንተባበር…..እርርር
እያልኩ በአይኔ እምባ ሞልቶ ሊፈስ ጫፍ በደረሰበት ሰአት መንፈሴ ሙሉ በሙሉ ፍቅር በተሞላበት ቅጽበት የፍንዳታ ድምጽ ተሰማ፡፡ ከመቅጽበት ነገሮች እንዳልሆኑ መሆን ጀመሩ…….ፍንዳታው በተሰማ የመጀመሪያው ቅጽበት ነገሩን ርችት እና መሰል ከክፋት ነጻ ከሆኑ
የፍንዳታ ድምጾች ጋር ባያይዘውም …ወዲያው ነበር ከመድረኩ አካባቢ
ከማየው ግርግር ምን እየተካሄደ እንደነበር የገባኝ…..ይህ ይመጣል
ብሎ ያልጠረጠረው አብይ ብድግ ብሎ ቆመ፡፡ድምጹን ወደሰማበት አቅጣጫ ዞሮ ሲቆም አየሁት….የተቃጣበት ነገር ይገባዋል… እህህህ ና…ና….. ሲል …ና…..ና ደርሶ ላያስጥለው ለምዬ ባይደርስለትም…. ተዋከበና………. ና…..ና….. ተዋከበና ወዲህ ዞር ቢል ሰው የለምና ወዲያ ዞር ቢል ለማ የለምና……………..ይቀጥላል፡፡

(መታሰቢያነቱ ትንናት በሙሉ ጤንነት ወደ አገራቸው ለተመለሱት
የተከበሩ አቦ ለማ መገርሳ ይሁንልኝ፡፡)
ይመቻችሁ፡፡


@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/10/01 09:21:33
Back to Top
HTML Embed Code: