Telegram Web Link
አብደላ የሚሉት ጀብራሬ
"አገሪቱኮ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ሰባት የችግር አለንጋዎች
ያረፉባት ናት! ምንድን ነው ሰው ሁሉ በየመፅሀፉ ስለ ስድስት ስልሳ
ስድስት ሲደሰኩር የሚውለው? " ብሎ ነበር ። አገሪቱ ያለው እማዬን
ይሁን አይሁን እንጃ! ብቻ ባለፈው ስሰማው ግርም ብሎኛል ።
የአለንጋው ቁጥር ስላስገረመኝ አልረሳሁትም ።
6667 ( ባንድ ወቅት የሆኑ ቄስ ክርስቶስ ተገርፏል ካሉኝ ግርፋት
በአንድ ይበልጣል!! )
እንኳንም የመጀመሪያው ምርጫዬን… ፖለቲካል ሳይንስ አደረኩ!
ስመረቅ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር እሆናለሁ! !
ባድመንና አሰብን ከአገሪቱ ካርታ ጋር አንድ አደርጋቸዋለሁ ። (የአገሪቱ
ካርታ የትኛው ነው የሚል ካለ…እዚያ ከእኛ ቤት ግድግዳ ከአባዬ ፎቶ
ጎን እማዬ የሰቀለችውን ካርታ ይመልከት!)


@wegoch
@wegoch
የጠቅል አሽከር - ዳንኤል ክብረት Daniel Kibret | Sheger Shelf on Sheger FM…
የጠቅል አሽክር 😉
በዳንኤል ክብረት

አቅራቢ፦ አንዷለም ተሰፋዬ
ሳይዝ 0.7 Mb

የጠቀል አሽከሮች 😊 ሰላም ነው

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch
ከወንዶች ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
ውድ ሚስቴ እንደምታውቂው የአለም ዋንጫ ዛሬ ሊጀመር ነው ስለዚህ ይህን የአቋም መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል
1 ወሩን መሉ ሪሞቱ በእጄ ይሆናል
2 በቃ ሚጀምር ቃል መጠቀም ክልክል ነው ቃና ቲቪ ትዝ እንዳይልሽ
3 በዚ ወር ልደት ክርስትና ሰርግ ሞት ቢኖር እንደማልሰማ እና እንደማልሳተፍ ለሚውለዱትም ለሚሞቱም ንገርልኝ
4 ጨዋታ እያየሁ ማውራት አይፈቀድም ወይ እረፍት ላይ ወይም ጨዋታው ሲያልቅ መጠበቅ ይኖርብሻል
5 ቲቪው ባለበት 20 ሜትር ውስጥ ማለፍም ሆነ ማቋረጥ ክልክል ነው
6 አስጠሊታ ጥያቄ መጠየቅሽን እንድታቆሚ ልክ ይሄ ጨዋታ ቸልሲ ከ እንግሊዝ ነው እንዴ አይነት
7 ሮናልዶ የብራዚሉና ሮናልዶ የፖርቱጋሉ ምንም ዝምድና እንደሌላቸውና ታንዛንያና ኤርትራ ለአለም ዋንጫ እንዳላለፉ ቀድሜ ላሳውቅሽ
8 በዚ ሁሉ ክልከላ ውስጥ የተፈቀደልሽ 1 ነገር ዶር አብይ እያወራ ከሆነ ቻናል የመቀየር መብት አለሽ
9 እኛ ስንኖር ባል ስንቆይ አባት ስንሞት የ አርሰናል ደጋፊ እንሆናለን
10 በዚ ወር የሚረገዝ ልጅ ስሙን የማውጣት መብት ላንቺ ይሰጥሻል ስለማይረገዝ
የማእከላዊ ኮሚቴ የቦርድ ሊቀመንበር ሩሲያ!

@wegoch
@wegoch
@ageregna
🙏እንኳን ለ1439ኛው የኢድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ።

ኢድ ሙባረክ ለ ሙስሊም ኢትዮጵያኖች ።
💚💛❤️
💚ግጥም ብቻ💚
💛ስዕል ብቻ 💛
❤️ወግ ብቻ❤️

@getem @seiloch @wegoch
በውቀቱ ስዩም
.
.
አቶ መለስ ዜናዊ በተሰዋ ሰሞን ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ
በጠና*ታመው ኮማ ውስጥ ገብተው ነበር:: ከሁለት ወር በሁዋላ
ከኮማ ነቅተው ሲንሸራሸሩ አገር ምድሩ በመለስ ፖስተር ተሞልቶ
ያያሉ:: ይሄኔ ምን አሉ?
.
.
"ይሄ ሰውየ አልበም አወጣ እንዴ?"

@wegoch
@wegoch
በቲቪ የሚፈውስ ፣ ህዝብ ፊት የሚያስለፈልፍ ፣ በስልክ አጋንንትን
የሚያስወጣ ፓስተር እንዳለ አይታችኋል …
አሁን ደግሞ ሜሴንጀር ላይ በቻት የሚፈውስ ታምረኛ መጥቷል!
አፈዋወሱን ይከታተሉ ፦
ፓስተር: ሀይ
አማኝ፡ እሪሪው ፕሮፋይል ፒክህ አቃጠለኝ
ፓስተር: የት ነው የያዝከው ?
አማኝ: በየኮሜንቱ ሲንቀለቀል በሴት ፎቶ
ተደግሜ ነው
ፓስተር: እሺ አሁን የእኔን አካውንት ሶስቴ ሼርና ላይክ አድርገህ ውጣ!
አማኝ: ኡኡኡኡ እወጣለሁ እወጣለሁ

ፓስተር ፡ ሀይ
ተጠቃሚ ፡ ?
ፓስተር ፡ ስንት ናችሁ
ተጠቃሚ ፡ ??
ፓስተር ፡ ሰይጣን በጌታ ስም ውጣ!
ተጠቃሚ ፡ what?
ፓስተር ፡ ሶስቴ ጮኸህ ውጣ !
ተጠቃሚ ፡ yikrta silke amaregna ayanebim


@wegoch
@wegoch
11ኛው ሰአት እየደረሰ ይመስላል! ነገሮች ሁሉ ጥሩ አይመስሉም! 17 አመት ታግለናል የሚሉት ወንበዴዎች ይሄን ብርቅዬ ሰው ስጋ እንዳየ አሞራ ሰልቅጠው ሊበሉት አሰፍስፈዋል! በእድሜ ጃጅተው እንኳን ትዕቢት የለቀቃቸው አይመስሉም...
...
በሀገሩ አንድነት የማይደራደረው ህዝብ እንደ ነብር እየታዘባችሁ ነው... ዶክተሩ እየዘረጋው ባለው ስርአት ላይ እንኳን ጥቃት ልታደርሱ ይቅርና
ፀጉሩ ላይ ያረፈችን ዝንብ ካላሱ ፈቃድ ከነካችሁ ፀባችሁ ከእሱ ጋር
ሳይሆን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ነው!
...
ቀልድም ገደብ አለው! በየቦታው የብሔር ግጭት እየቆሰቆሳችሁ ስልጣናችሁን መመለስ አትችሉም! ኒሻን እየሸለመ የዘረፋችሁትን አርፋችሁ ብሉ እያለ የሸኛችሁን ሰው ለመንካት ካሰባችሁ የራሳችሁን መቃብር እየቆፈራችሁ ነው! በመጨረሻም ከጥንት ጀምሮ ወዳጆቹን እያከበረ ጠላቶቹን ከአፈር እየደባለቀ የኖረው ጨዋው የኢትዮጵያ ህዝብ ከመቼውም ግዜ በላይ አንድነቱን አጠናክሮ አካባቢውን በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ አደራ እላለሁኝ!

(ዳግማዊ ))
@wegoch
@wegoch
By Abel
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አብይ መኪናውን እያሽከረከረ ፣ ልክ ብሄራዊ ጀርባ ሲደርስ መኪናዋን ያቆማታል፣ ከዛን ልዕሉ ምናው አብይ ይለዋል? በብላክ ከባንክ ይቀንሳል ፣ ዶላር ስንት እንደሆነ ልጠይቅ ነው? 😀


አብይ ምናው ራስህ ሹፌር ሆንክ ይለዋል? አብይ ምን አለ፣ እና 3 ቢሊዮን ያመጣ ሰው እንዴት አምኜ ለሹፌር ልስጥ? 😁

@wegoch
@wegoch
ተደናጊረ! !!!!


አቶ ባል ሁል ጊዜ ማታ ማታ ወደ ቤቱ ሲገባ ሚስቱን
በጥፊና በእርግጫ እያዳፋ ሲያንገላታት ከርሞ ድንገት
አንድ ቀን ቅይር ብሎ ወደ ቤቱ ሲገባ ወሮ ሚስትን
እቅፍቅፍ አድርጎ የኔ ማር I love you more than i
can say! !!!!!!!!!!!! እያለ ሳም አድርጎ እግርሽን
ካላጠብኩኝ ብሎ ቢግደረደር ሚስት ሆየ ""ተደናጊረ !!!"""
የሚለውን ዘፈን ከማቀንቀን የምትመለስ አይመስለኝም ።
ከመለስ ግዛት ወደ አብይ ግዛት መሸገጋገር እንደማለት
ያህል ነው! !!

@Balmbaras
@wegoch

(( ሸጊቱ ቅዳሜ ))
Bewketu Seyoum and Daniel Kibret Wazana Kum Neger በአንድ መድረክ ላይ ያቀረቡት…
በዳንኤል ክብረት (ድጋሚ)
በዕውቀት ስዩም

@Zerusoutlying

@wegoch @wegoch
የመሪዎችን ፎቶ የሚሸጠው ልጅ ለአምስተኛ ግዜ፣ የመለስን ፎቶ አለክ ብዬ ስጠይቀው ?

ልጁ ፦ እንዴ የለም እያልኩህ ለምንድነው ደጋግመክ የምጠይቀኝ?

እኔ፦ የለም ስትለኝ ደስ ይለኛል ☺️☺️

@wegoch
@wegoch
ልጁ ሙሉጌታ! !!!!!!


አይሸከሸክም በርበሬ በጎታ ፤
አባትየው ጃርመን ልጁ ሙሉጌታ ።
ይህች ግጥም በሙሉጌታ ርህራሄና እዝነት ልቡ
የረሰረሰው ወሎየው የጮሬ ሶደማ ገበሬ ለሙሉጌታ
የሰጠው ሽልማት ናት ።
ሙሉጌታና ግጥም ተዋህዶ ናቸው ። ለአያ ሙሌ ግጥም
መክተብ ኦኮስጅኝ እንደመሳብ ያህል ነው።
እስትንፋሱ ነው ። መኖሩና መቆሙ በሱ ነው ።
ወልዲያ ጨው ሪጋ መንደር ቅኔ ስትሞሸር እኛም ልጆች
ሆነን ኩማንዳ ጠባ ላይ ድጉስን በልተናል ። ያኔ
የሙሉጌታን ጉርሻ አግኝተን በነበር የዛሬው የጥበብ
ረሃባችን ይጠግግ ነበር ።
ሙሉጌታ ተስፋየ የኔ ሼክስፔር ነው ። የኔ ካህሊል ጅብራን
እሱ ነው ፤ የኔ መንዙመኛ ነው ፤ የኔ ባለቅኔ ፤ የኔ መራቂ
፤ የኔ አበጋር እሱ ነው ። ዋሪዳው ጎርፍ ሆኖ ሰማይ ላይ
ሲረብ የመደዱን ምንጭ እየተለመ ጣፍጭ ቅኔ ማፍለቅ
ነው የሱ ዱንያ ። ፍቅር ያወፈፈው ፤ እዝነት ያጎበጠው ፤
መስጠት የዳሰው ፤ ሰው መሆን ያሸነፈው የሰውነት ወልይ
ነው! !!! በቃ ወልይ ነው! !!! አበጀሁ!!!!!

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
የድብርት መዳኒት የታዘዘለት ልጅ ምን አለ?

መዋጥ ደበረኝ 😳

@wegoch
@wegoch
ያለኝ ቦታ ውስን ነው !!!
**************
ቺኳ በጠዋት ደውላ
"ምን ሆነህ ነው ማታ ስደውል ስልክ ማታነሳው ?
Missed Call ስታይ እንኳን አትደውልም ?" አለችኝ ገና
ስልኩን ከማንሳቴ የጩኸት እና የንዴት በሚመስል ድምፅ
ሰላምታ እንኳን ሳንለዋወጥ...
"ማሬ የዓለም ዋንጫ እያየው ነበር ለዛ ነው እረፍ ላይ
ልደውልልሽ አስቤ ነበር መሽቷል ብዬ ነው" አልኩ
በተቅለሰለሰ ድምፅ...
ፍቅሬ እኔ ላይ ከሰከንዶች በላይ ተናዳ እና ተበሳጭታ
እንደማትቆይ አውቃለው.... ትወደኛለች (እኔ ዚዳን ፣
ዴልፔሮ ፣ ዞላን የምወደውን ያህል)
ታፈቅረኛለች (እኔ እግር ኳስን በተለይ ሴሪ አ
እንደማፈቅረው)
ትናፍቀኛለች (እነየ ጣሊያን የምትሳተፍበት የዓለም ዋንጫ
እንደናፈቀኝ)
አሁን ድምፄን እንደሰማች ንዴቷ ቀዝቅዟል "ጁዬ ስልክ
ሳታነሳ ስትቀር ይደብረኛል... አውቃለው ኳስ
እንደምትወድ... የኔ ዓለም ዋንጫ ግን አንተ ነህ አንተን
መመልከት ነው ምፈልገው" አለችኝ ፍቅር ፍቅር በሚሉ
ማራኪ ቃላቶች......
አሁን በሆዴ እንዲ ማለት ጀመርኩ
ለሷ ዓለም ዋንጫዋ ከሆንኩ የተሳታፊውን ቁጥር ከ 1
ወደ 32 ከፍ ማድረግ አለብኝ ማለት ነው 31 ክፍት ቦታ
አለኝ
*
በሉ ቆንጆ ቆንጆ ቺኮች inbox መጥታችሁ መጋተት
ጀምሩ ያለኝ ቦታ ውስን ነው😜😜😜

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
እኔ በሞትኩ በማግስቱ - ዳንኤል ክብረት
እኔ በሞትኩ በማግስቱ
በዳንኤል ክብረት

አቅራቢ፦ አንዷለም ተሰፋዬ
መጠን 1.6 Mm

የሁለት ሃውልቶች ወግ እና ሌሎችም
ከሚለው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch @wegoch
PM Dr. Abiy ahmed today on parlama

<<ለረጅም ዓመታት ሲያስርና ሲገርፍ የለመደ አካል አሁን ያለውን ለውጥና መሻሻል ሕገ መንግስቱን እንደ መጣስ ሊቆጥረው ይችላል፡፡>> ጠሚ ዓቢይ
.
<<አሰብን ስንሰጥ ሕዝብን መቼ አወያይተናል። ለአሰብም የሞተው
የኢትዮጵያ ልጅ ነው።>> ጠሚ ዓቢይ
.
<<ከዚህ በኃላ የሥራ አስፈጣሚ ስብስባ በየሠዓቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይገለጣል። ከዚህ በኃላ ከኢትዮጵያ ሕዝብ በድብቅ የሚደረግ የፖለቲካ ውይይት አይኖርም። በግርድፉ እንለቃለን፤ አብረን እናብሳላለን።>> ጠሚ ዓቢይ
.
<<ሽብር ማለት አላግባብ የስልጣን ዘመንን ለማራዘም ሲባል የሚወሰድ እርምጃንም ያጠቃልላል። ዜጎችን ጨለማ ቤት ማሰር እና ማሰቃዬት ሽብር ነው። እስካሁን አሸባሪው መንግስት ነበር።>> ጠሚ ዓቢይ
.
<<እኛ እስር ቤት ብንገባ ግን ለኢትዮጵያ ለውጥ የለውም። ልጅ ኢያሱ ሲወርዱ ጃንሆይ አድርገውታል፣ ጃን ሆይ ሲወርዱ መንግስቱ አድርጎታል። በየዘመኑ ሆኗል፤ አልጠቀመንም። መቆም አለበት በይቅርታ፤ ሰው ጭንቅላቱ መቀየር አለበት። ለዘላለም እንደማይኖር
አውቆ በህግና በህግ ብቻ መግዛት ፣ ማስተዳደር እና መቀየር መቻል
አለበት። ይህ ሲባል እነ ግንቦት 7፣ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ በዚሁ አጋጣሚ ጊዜው ያለፈበት ፋሽን ነው፤ ውጊያ አቁማችሁ ኑ አይጠቅምም። ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እኔን ገድሎ ወይም አስገድሎ ስልጣን መያዝ፣ እኔ እሳቸውን ገድዬ ወይም አስገድዬ ስልጣን ላይ መቆየት። ሁለቱም ጊዜ ያለፈበት አሮጌ ፋሽን ነው። ለኢትዮጵያ ጥይት ማባከን ምንም አያስፈልግም።>> ጠሚ ዓቢይ
.
<<የትግራይን ሕዝብ ከጥቂት ሆዳሞች ጋር አብረን ደምረን ልናሳድድ አይገባም።>

@wegoch
@wegoch
📙ውድ የዚህ ቻነል ተከታዮች እንዴት ናችሁ? እንደሚታወቀው ቻነሎቻችን እስከዛሬ ድረስ በተቻላቸው መጠን የተመረጡ:
ግጥሞችን (@getem)እና
ወጎችን (@wegoch) ፣ሲያቀርቡላችሁ ቆይተዋል የህ እንዳለ ሆኖ በቀርብ ቀን ደሞ አድማሳቸውን ሰፋ አድርገው የተወደዱና የተመረጡ ግጥሞችን እና ወጎችን ከ ሚኪ pictures (@mykeypictures) ጋር በመተባበር በከፍተኛ ጥራት በፎቶ ይዘዉላችሁ ሊቀርቡ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

ከግጥም ብቻ እና ወግ ብቻ
(@lula_al_greeko)

Mykey ምስሎች
(@mykey21)
2024/10/01 09:19:43
Back to Top
HTML Embed Code: