Telegram Web Link
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew (Mykey))
Episode Ⅰ Vol Ⅱ
#Whataboutthem #weaving #ሽመና

#ፍሬሀሳብ
.

የሽመና ሙያ ጥንታዊ ሙያ ነው! እኛ ከአባቶቻችን ተምረን ለዚህ አድርሰነዋል እዚህ ሙያ ላይ አስቸጋሪ ነገር ብዬ የማስበው እና እኔንም ሆነ የስራ ባልደረቦቼን ደጋግሞ ተስፋ የሚያስቆርጠን ነገር ማህበረሰቡ  ትኩረቱን ለነጋዴ እና ለዲዛይነሮች ብቻ መስጠቱ ነው! እኛ የምንሸምናቸውን  ልብሶች ለምትወዷቸው ፣ ለምታከብሯቸው ፣ ለተለየ ቀናቹ እየለበሳቹ ለኛ ግን ለልብሶቹ የምትሰጧቸውን ትንሽ ክብር እንኳን አትሰጡንም...ለምን? እኛ  ከሸመናቸው (ከሰራናቸው)  ልብሶች አንሰን ነው? እውነት ፈጣሪውን ሳያከብሩ የተፈጠረውን ማክበር ልክነት ነው..?
ይቀጥላል....
.
.
.
#Thecore
.

The traditional weaving profession is an ancient one! We have learnt it from our fathers and they from their forefathers. What makes the job difficult and at times make you hopeless is that the society gives more value to designers and vendors!  you love and value the garments we produce. you wear them on special days but you don't give us as much respect as what we produce. why? are we less than what we make?

To be Continued
.
.

#እነእርሱስ #Whataboutthem #World #Africa #Ethiopia #Addisababa #Mykey
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew (Mykey))
Episode Ⅰ Vol Ⅲ
#Whataboutthem #weaving #ሽመና

#Theconclusion

አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሽመና ሙያ ተደብቆ ነው ያለው ብዬ አምናለሁ፥ ለኛም ተገቢውን ነገር እየተደረገ ነው ብዬ አላስብም ፤ ማህበረሰብም ሆነ መንግስት በዚህ በኩል ችላ ብሎናል  ከእኛ ላይ ገዝተው ለሚያተርፉት ነጋዴዎች የተመቻቸ ነገር ይደረጋል ። እንደ መፍትሄ ብዬ የማስቀምጠው ነገር ማህበረሰብም ሆነ መንግስትም ለሙያው ተገቢውን እውቅና ቢሰጥና ለምንሰራው ስራ ተገቢውን ክፍያ ብናገኝ  የሽመና ሙያን አሁን ካለበት ሁኔታ ማዘመን እኛንም ደግሞ ከሞራል እና ከኢኮኖሚ አንፃር ከፍ ወደአለ ደረጃ የሚያሸጋግረን መፍትሄ ነው ብዬ አስባለሁ።

-አለቀ-
.
.
.
.
I believe currently the profession of weaving is is hidden. I also don't believe that the right things are done for us . The government and the society is reluctant towards us. More opportunities are provided for vendors who put our products on the market and profit from them. What I suggest as a solution is that the government and the society gives recognition the profession deserves.I believe its a way that can create modernized ways of production, boost morale for us raise our status economicaly and this is our history!

-The End-
.
.
.


#እነእርሱስ #Whataboutthem #World #Africa #Ethiopia
#እነርሱስ!

ከራስህ በላይ ለሌሎች ማሰብ የዕድሜ ሳይሆን የሰውነት መገለጫ ነው!!!

እዚህ ሀገር የሚሰሩ እጆችን የማክበር ፣ እውቅና ክብር የመስጠት ችግር አለብን ብዬ አስባለሁኝ ለዛም ይመስለኛል ብዙ የእጅ ስራ ውጤቶቻችን ከዘመኑ ጋር ማደግ ያልቻሉት እንደ ጅማሯቸው ማለቴ ነው.....ከነዚህ ውስጥ አንዱ የሽመና ሙያ አንዱ ነው በተከታታይ ለ3 ቀን ሲቀርብ የነበረው በዚሁ ስራ ላይ የሚገኘው የቦሻ ታሪክ የአብዛኛውን የሸማኔውዎች ታሪክ ነው እነዚህ ጥበበኞች የሚገባቸውን ክብር አላገኙም ፣ የሚገባቸው እውቅናም እየተሰጣቸውም አይደለም የሚሰሩትን ጥበብ እንኳን ዋጋ የሚያወጣላቸው ደላላና ነጋዴው ነው......በነሱ ጥበብ በነሱ ልፋት እየከበረም ፣ እየታወቀም ያለው ሌላ ነው ( ዲዛይነሩ ፣ ደላላው ፣ ነጋዴው ) እኛም እነሱን ከማክበር ይልቅ አግልለናቸዋል ስም ሰተናቸዋል ...ለሀዘናችንም ሆነ ለደስታችን የምንለብሳቸው የነሱ የእጅ ስራዎችን ነው ልብሶቻቸውን እየደመቁበት #እነርሱን መጠየፍ ግን ተገቢ ነው...? ቦሻ በታሪኩ ውስጥ እንደነገረን ፈጣሪውን ሳያከብሩ ተፈጣሪውን ማክበር ልክነት ነው...? እኔ በግሌ አይመስለኝም !!!

#በመጨረሻ እናንተ በዚህ ስራ ላይ የተሰማችሁን በተሰራው የፎቶግራፍና የፅሁፍ ዶክመንተሪ የተሰማችሁን አስተያየት ብትሰዱልን ለእኛም ብርታት ይሆነናል🙏🙏🙏

👇👇

@Mykey21
@Mykey21
@Mykey21
እርቅና ይቅርታ ለምን? ከማን ጋር?
(መላኩ አላምረው)
...
‹‹አጥብቀን የምንሻ - ከአምላክ ምህረቱን
ይቅር ካልተባባልን - አናየውም ፊቱን››
.
አንዴ ፍቀዱልኝማ..... ስለ እርቅና ይቅርታ ልሰብካችሁ ነው፡፡
(በዚያውም ሰባኪነት የሚያዋጣኝ ከሆነ ጠቁሙኝማ ያው
ሰባኪነት በነጻ የሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት ሳይሆን የትልቅ
እንጀራ ምንጭ እየሆነም አይደል )
ዕድሜና ጊዜ በፈቀደልኝ መጠን ካነበብኋቸው መጻሕፍትም ሆነ
እንዲሁ በእእምሮዬ መርምሬ የተረዳሁት ቁም ነገር ቢኖር... ሰው
እርቅንና ይቅርታን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አምኖ ሊቀበለውና
ሊተገብረው ይገባል፡፡ ምክንያቱም በምንም መመዘኛ እርቅና ይቅርታ
ጥቅሙ ለራስ ነውና፡፡ እርቅና ይቅርታን የማይቀበልና የማይተገብር
ሰው ሰላማዊ ኑሮን ገንዘቡ አያደርጋትም፡፡
ሰው መታረቅ ያለበት እርቅ የነፍስ መድኅን የአእምሮም ነፃነት ስለሆነ
ነው። ጥላቻ ነፍዝን ያቆስላል። አእምሮን ያቆሽሻል። ሰው መታረቅ
ያለበት እርቅ የሰላምና የመረጋጋት ምንጭ ስለሆነ ነው።
ሰው ይቅር መባባል ያለበት የትኛውንም የጥፋትና የበደል ዓይነት
ነው። ለጥፋትና በደል ደረጃ አውጥተን ይህንን ይቅር እንበል...
ይህኛው ግን ይቅር ሊሉት ይከብዳል አንበል። በደል በደል ነው።
ይብዛም ይነስም በእርቅና ይቅርታ ካልተወገደ በሽታ ነውና ሰብዓዊ
ጤንነትን ያዛባል። "ይቅርታ አይገባውም" የምንለው የበደል ዓይነትና
መጠን ሊኖር አይገባም። እንደዚያ ካልን እኛም በየግላችን ይቅር
ሊባል የማይገባ ጥፋት ሊኖርብንና ያለ ምህረት ልንኖር ነው ማለት
ነው።
ሰው እርቅን መፈጸም ያለበት መተማመንን ለመመለስ እንጅ
ለይስሙላ አይደለም። ሰው በደሉን አምኖ ይቅርታ ከጠየቀ በኋላ
የቀድሞ ጥፋቱ ለነገ ሕይወቱ ተጠያቂ ሊያደርገው አይገባም። ያንንማ
ጥፋት መሆኑን አምኖና ይቅርታ ጠይቆበት ጥሎት መጥቷል። ሰው
መታረቅ ያለበት አንድነትን ለማምጣት ነው። እርቅና ይቅርታ
የአንድነትና የመረጋጋት ምሥጢሮች ናቸው። የነፍስና የሥጋ አንድነት፣
የሐሳብና የተግባር መመሳሰል፣ የእርስ በርስ መግባባትና
መተማመን... በጥል ይጠፋሉ - በእርቅና ይቅርታም ይመለሳሉ።
ሰው ይቅር መባባል ያለበት አምላኩን ለማስደሰትና ውለታ መላሽነቱን
ለማሳየት ነው። ሰው እንኳንስ እርስ በርሱ ከፈጣሪው ጋርም እንኳን
በየሰዓቱ ይጣላል። ፈጣሪው ግን በደሉን ሳይቆጥርበት ይቅር
ይለዋል። ሰው ጥፋቱን አምኖና ከልቡ ተጸጽቶ "በድያለሁ፣ ይቅር
በለኝ አምላኬ" ባለበት ቅጽበት መረጋጋትን የማግኘቱ ምሥጢር
የአምላክ ይቅር ባይነት ነው። ታዲያ በየቀኑ ይቅር የሚለውን አምላክ
ውለታ በምን ይመልሰው? ሌላውን ይቅር በማለት ብቻ። ይቅር
የማይሉ ይቅርታን መጠየቅ እንደምን ይችላሉ?
ይቅር ባይነት አምላክን የምንመስልበት ምሥጢር ነው፡፡ ሰው ይቅር
ማለት ያለበት የበደሉትን ነው። የበደላቸውንማ ግዴታው ነው። ሰው
እልምላኩን የሚመስለው የበደሉትን ይቅር ሲል ብቻ ነው። የበደለማ
ይቅርታን ይጠይቃል እንጅ ይቅርታ አድራጊ አይደለም።
...
በእርቅና ይቅርታ ላይ ጥናት ያደረጉ ጸሐፍት አንድ ሰው ከ4 ነገሮች
ጋር እርቅ መፈጸም እንዳለበት ያትታሉ፡፡
1ኛ. ከራሱ ጋር፡-
ሰው ከምንም በፊት መታረቅ ያለበት ከራሱ ጋር ነው። ከራሱ ጋር
ያልታረቀ ከሌላው ጋር እንዴት ሊታረቅ ይችላል? ከራሱ ጋር እርቅ
የፈጸመ ሰው ከሰውም ከአምላኩም ከተፈጥሮም ጋር ለመታረቅ
አይከብደውም። ከሕሊናው ጋር ሲሟገት የሚኖር እርሱ ከራሱ ጋር
እርቅ ያልፈጸመና ከልቡ ሐሳብ ጋር ስምምነት የሌለው የራሱ ጠላት
ነው፡፡
2ኛ. ከሌላው ጋር፡-
ከራሱ ጋር እርቅና ይቅርታ የፈጠረ ሰው ከሌላውም ጋር ይስማማል፡፡
ምክንያቱም ጣዕሙን ቀምሶታልና፡፡ በእርቅና ስምምነት የሚገኘውን
ሰላም አይቷልና፡፡ ከራሱም ከሰውም ጋር የሚታረቅና የሚስማማ
እርሱ የተባረከ ነው፡፡ ኑሮውም ሰላምና ደስታ ይሞላበታል፡፡ ሰውን
ይቅር የማይል እርሱ ለራሱም ሰላም የማያስብ ነው፡፡ ሌላውን አሳዝኖ
መደሰት የማይታሰብ ነው፡፡
3ኛ. ከአምላኩ ጋር፡-
ሰው ከአምላኩ ጋር ለመታረቅ አስቀድሞ ከራሱና ከወንድሙ ጋር
መታረቅ አለበት፡፡ ከራሱ ጋር ያልተስማማና ወንድሙንም የበደለ ሰው
የአምላክን ይቅርታ በትጋት ቢፈልግም አያገኛትም፡፡ ሁለቱን እርቆች
ቀድሞ የፈጸመ ግን በዚያው ቅጽበት ከአምላኩ ጋር ይታረቃል፡፡
ወንድሙን ይቅር ለሚል ለእርሱ አምላኩ ከእርሱ ጋር ነው፡፡ ሰዎችን
በሚወድበት መጠን ፈጣሪው ይወደዋል፡፡ ሰው ከአምላኩ ጋር
የሚኖረው እርቅና ይቅርታ ከራሱም ሆነ ከወንድሙ ጋር በሚያደርገው
እርቅና ይቅርታ ይወሰናል፡፡ ከራስ ጋር ሳይታረቁና ወንድምን ይቅር
ሳይሉ ከአምላክ ዘንድ ምህረትን መጠበቅ በራሱ ግብዝነት ነው፡፡
4ኛ. ከተፈጥሮ ጋር፡-
የሰው ልጅ ምንም እንኳን እርስ በርሱ ቢስማማና ከአምላክ ጋር ነው
የምኖረው ብሎ ቢያምን.... ከተፈጥሮ ጋርም ስምምነት ካልፈጠረ
በቀር ምድራዊ ሰላሙ ምሉዕ አይሆንም፡፡ አካባቢውን በክሎ ንጹህ
አየርን መመኘት የዋህነት ነው፡፡ አትክልትና ዛፎችንም አጥፍቶ
አረንጓዴና ለዓይን ማራኪ ምድርን መመኘት እብደት ነው፡፡ ከተፈጥሮ
ጋር ለመታረቅ ሰው ለተፈጥሮ መስጠት ያለበትን መስጠት ግድ ነው፡፡
ከተፈጥሮ በመቀበል ላይ ብቻ የተመሠረተ የዓለም ጉዞ ወደ ጥፋት
እንጅ ወደ ልማት ሊመጣ አይችልምና፡፡

@wegoch
@wegoch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“ እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል ። ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል ።

ከሰማሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም ። ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ ።

ልብህን ከከፈትክላቸው የየድርሻቸውን ጠርበው ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።

እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው። 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው' ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ ።

እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል ። እንደ እኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል ። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ። የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ። "


" ጠበኛ እውነቶች " ከተሰኘው የሜሪ ፈለቀ መጽሐፍ የተቀነጨበ ::

@wegoch
@wegoch
@paappii
ትዳርን ከነ ብጉሩ
አንድ፡ ‹‹ወሲብ በአርባዎቹ››
-------------------
ጥር የሰርግ ወር አይደለ? የትዳር መጀመሪያ…? ያንን ይዤ ትዳርን ሀ ብለው ለሚጀምሩም፣ ትንሽ ለዘለቅንበትም፣ ገና ዳር ዳር ለሚሉም ቁምነገር አይጠፋውም ብዬ ‹‹ትዳርን ከነብጉሩ›› የሚገልፁ እውነተኛ ታሪኮችን ፍለጋ ባለትዳሮችን ማነጋገር ጀምሬ ነበር፡፡ አሁንም ከዜሮ እስከ አርባ አመታት የትዳር ልምድ ያላቸውን ባለትዳሮች እያነጋገርኩ ነው…ስለ ፍቅር፣ ስለ ጠብ፣ ስለ ልጆች፣ ስለ የእርጎ ዝምብ ዘመድ፣ ስለ መማገጥ፣ ስለ ወሲብ...እንዲያው ስለሁሉም ነገር በፍፁም ግልፅነት ብዙ ተጫውተናል… ብዙ እንጫወታለን…አንድ ቅርጽ ሰጥቼው እስካቀርብለችሁ ዛሬ ለቅምሻ 20 አመታትን በሞቀ ትዳር ከቆየ አባወራ ጋር ያደረግኩትን ጨዋታ ቅንጫቢ እነሆ….ጌዲዮን ይባላል ስሙ….አርባዎቹ መጨረሻ፣ ሃምሳዎቹ መባቻ ላይ የሚገኝ ጎልማሳ ነው… በደራ ጨዋታችን መሃል እንዲህ ብዬ ጠየቅኩት፤ ‹‹ለመሆኑ…ከሃያ አመት በኋላም…አንተና ሚስትህ አሁንም ፍቅር ትሰራላችሁ?›› ‹‹ህእ…አታምኚኝም! እንደተጋባን…ከዚያም ልጆች ከወለድን በኋላ ራሱ በሳምንት አራት አምስቴ ሴክስ እናደርግ ነበር….አራት አምስቴ! አንዳንዴ ጠዋትና ማታ ሁሉ እናደርግ ነበር…›› አለና ፈገግ ብሎ ዝም አለ፡፡ ‹‹እሺ…አሁንስ ከሃያ አመታት በሁዋላ?›› ብዬ ጠየቅኩት.. ‹‹ ያው ሁሉም ትዳር ውስጥ እድሜ ሲጨምር…ልጆች ሲኖሩ…ጊዜው ሲሄድ ሴክስ ይቀንሳል አይደል?›› ብሎ አሁንም ዝም አለ፡፡ ራሴን በመስማማት ከነቀነቅኩ ቀሪውን እንደሚነግረኝ በመገመት፣ ሃሳቡም እውነት ስለሆነ እንደዚያ አደረግሁ፡፡ ራሴን በስምምነት ነቀነቅኩ፡፡ ‹‹የእኛ ግን ትንሽ ይለያል….አሁን… አሁን እንግዲህ ሁለታችንም አርባዎቹን ላፍ
አድርገን ልንጨርስ ነው… እውነቱን ንገረኝ ካልሽኝ…ዛሬ ዛሬ ሴክስ ከምናደርግ ድንጋይ ብንፈልጥ የሚሻለን ይመስለኛል…ሁለታችንም ለሴክስ የሚሆን እንጥፍጣፊ ፍላጎትም፣ ጉልበትም የለንም…ጭራሽ ትተናል….ኮምፕሊትሊ ነው ያቆምነው….ሃኪም ጋር ሁሉ ልንሄድ አስበን ነበር…የሆነ…ኮታችንን
በመጀመሪያዎቹ አስር አመታት ተስገብግበን ተጠቅመን የጨረስን ሁሉ ነበር የሚመስለው….ግን ድንገት አይደለም ያቆምነው…መጀመሪያ ሰሞን እንዲያው ደባል እንዳንሆን በመፍራት ይመስለኛል ተነጋግረን ቢያንስ ለአመት በአል ለአመት በአል ማድረግ ጀምረን ነበር…ከዚያ ግን በአመት ውስጥ ያሉት አመት በአሎች ራሱ በዙብን…አስቢው…ሌላውን ትተሸ ዶሮ የሚታረድበትን እንኳን
ብትቆጥሪ አዲስ አመት…ገና….ፋሲካ.. ስትዩ በአመት ሶስት አራቴ ማድረግ
አለብን….ደከመን…ምን እንደሆንን አናውቅም ግን ገና ስናስበው ሁሉ ትክት
ይለናል….እንዋደዳለን….እንግባባለን…እንነጋገራለን…የፍቅር ችግር የለብንም…
ተቃቅፈን ነው የምንተኛው…ልክ እንደ ድሮው…..›› አለና አሁንም፣ ለሶስተኛ ጊዜ
በድንገት ዝም አለ… ‹‹እ…ታዲያ ምን አደረጋችሁ….በቃ አቆማችሁ አቆማችሁ?›› አልኩት፡፡
‹‹አይ…ነግሬሻለሁ…ትዳራችን ምሳሌ የሚሆን ነው….በግልጽ ተነጋገርን እና
በአንድ ሃሳብ ተስማማን…››
‹‹በምን?›› ‹‹ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ የማያከብረው ለእኛ ግን ተስማሚ የሆነ በአል መርጠን በዚያ ቀን ሴክስ ለማድረግ ተስማማን….›› ሆ! እነዚህ ደግሞ ልዩ ናቸው ብዬ አሰብኩና፣ ‹‹ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ የማያከበረው በአል›› ሲል የቱን በአል ማለቱ ነው ብዬ በማሰብ ጉጉቴ ጨመሮ፣ በፍጥነት… ‹‹ምን በአል ነው..ማለቴ በምን በአል ቀን ነው ሴክስ የምታደርጉት?›› ብዬ ጠየቅኩት፡፡ አላስጠበቀኝም፡፡ ፈጠን ብሎ፤ ‹‹ጳጉሜ 6 ስትሆን!›› አለና ፈገግ አለ፡፡ በሃይል ሳቅኩ፡፡ ‹ሳቂ አንቺ ምናለብሽ!….ትንሽ ጊዜ ስጪው አንቺም ትደርሺበታለሽ…›› አለ አብሮኝ እየሳቀ፡፡
የበለጠ ሳቅኩ፡፡ ‹‹አንቺ እሱ ይገርምሻል….›› አለ ሳቁን ገታ አድርጎ፡፡ ‹‹ሌላም አለ?›› አልኩ እኔም መሳቅ ለማቆም እየታገልኩ ‹‹ያቺም ቀን በየአራት አመቱ ስትመጣ ከማድረጋችን በፊት ምን እንደምንል
ታውቂያለሽ?›› ‹‹ምን ትላላችሁ?››
‹‹ወይ ጉድ እስቲ አሁን ከምኔው አራት አመት ሞላ? ጊዜው ይከንፋል ልጄ!..››

@wegoch
@wegoch
@paappii
Hiking to Dinbaro
📅 March 1,2020
📍 Dinbaro(debre sina)

departure Spot - Piassa, tayitu hotel

Departure Time - 6:00 A.M

Price - 350 ETB

🎉🎊Package 🎋🎊

- Tourist level Bus
- Snack , Lunch
Bottled water
photograph by professional photographers

Brought to you by Sunset Hiking Team
for more join the
🔸channel @sunsethiking
🔹the group @sunsethike
🔻📷 @sunsetphotography

🎫 tickets available at
@useryise
@Paappii
@thomaskagnew
@Chere_daregot
Forwarded from 1MSW Temu
3ኛ ዙር የአንድ ወር ተግባራዊ የህይወት መምሪያ ስልጠና ከሰርተፊኬት ጋር

ከ70 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ላይ ለውጥ ያመጡበት ስልጠና።

-ሳይኮሎጂን መረዳት
-የህይወት አላማ /life purpose
-የስሜት ብልህነት
-ፍርሀት ድብርትና ጭንቀት
-ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም እና ሌሎችንም ያካተተ ስልጠና

የስልጠና ሰአቶች፡
ቅዳሜ 3-4:30 ወይም
ቅዳሜ 10-11:30 ወይም
እሁድ 10-11:30

500ብር ብቻ

አድራሻ፡ ቅዱስ ኡራኤል ቤ/ያን አጠገብ ሸገር ህንፃ 2ኛ ፎቅ #201

ለበለጠ መረጃ 0946333951

@Psychoet @temuabiy
#### ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ####
(በፈረስ ስማቸው አባ ነፍሶ)
በአገምጃ ሶዶ(ወሊሶ) በሚባል ቦታ በነሀሴ ወር ፲፰፻፶፬ ዓ.ም ተወለዱ። የዓድዋው ጦርነት ሥመ ጥር ጀግናው ባልቻ አባ ነፍሶ ፋሽስት ጣልያን ኢትዮጵያ በድጋሚ ስትወር ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋራ ፀብ ስለነበራቸው ባልቻ ከጣልያን ጎን ይሰለፋሉ ብለው ጣልያኖች አሰቡ። ደጃዝማች ባልቻ በንጉሱ ላይ ቅሪታ ቢኖራቸውም በአገር ጉዳይ ላይ ሌላ ድርድር መግባት አልፈለጉም ስለሆነም ጦራቸውን ማሰባሰብ ጀመሩ እናም ከነ ደጃዝማች ኃይለማርያም ማሞ፣ አበበ አረጋይ፣ በላይ ዘለቀና አቡነ ጴጥሮስ ጋራ ስለ ጦርነቱ የሚስጥር ደብዳቤ መለዋወጥ ጀመሩ። ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ አምስት ሺ ጦራቸውን ይዘው በ፸፱ ዓመታቸው ከትውልድ መንደራቸው ከአገምጃ ሶዶ ተነስተው አዲስ አበባ ደረሱ ከዛም ረጲ ተራራ ላይ ሆነው መድፋቸውን ጠምደው የሌሎችን አርበኞች መልዕክት ይጠባበቁ ጀመር።ሺ የባልቻ ሰላይ የነበሩት በባንዳ ተይዘው ሲገደሉ ጣሊያን በአውሮፕላን ሆኖ የደጃዝማች ባልቻ ጦርን እየተከተለ በጣም ብዙ ሰው ፈጀባቸው። በህይወት ዘመናቸው ጣልያንን ሁለት ጊዜ የተዋጉት ብዙ ወታደር የነበራቸው ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ ብቻቸውን ቀሩ። ባልቻ ሁለት ወንድሞች ነበሯቸው ፊታውራሪ ገብረ መድህን እና ፊታውራሪ ሳህለሚካሄል ሁለቱም በጦርነት ተማርከውና ተገለዋል። በዚህም ጊዜ ደጃች ባልቻ እንዲህ አሉ ጦር መጣ ይላሉ እኔ ምን ቸገረኝ እናቴም ልጅ የላት ለእኔም ወንድም የለኝ። ደጃዝማች ባልቻ በልጅነታቸው ከጦርነት ላይ ተማርከው በአፄ ምኒልክ ቤት ያደጉ ታማኝ የጦር መኮንን የነበሩ...ከዓድዋ ጦርነት ፊት በጅሮንድ ተብለው የንብረት ኃላፊ ነበሩ። ኋላ በዓድዋ ጦርነት ላይ ፊታውራሪ ገበየሁ በጦርነት ላይ በጀግንነት ሲያልፉ መድፈኛነቱን ተክተው በመቀሌ እና በዓድዋ ጦርነት በጀግንነት ተዋግተዋል። ሰውነታቸውም ቀጭን ሆኖ ሳል መድፉን ሲያገላብጡ እንዲህ ተብሎላቸዋል....

ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ
እንደ ደጋ ገብስ እንዲያ ኮስሶ
ያስቆረጥማል ጠላቱን ኮሶ
የዳኘው ጀግና ባልቻ አባ ነፍሶ።

በጦርነቱም ከጠላት በተተኮሰ ጥይት ጆሯቸው በመቆረጡ ባለቅኔው እንዲህ አሞገሳቸው
ማን እንዳተ አርጎታል የእርሳሱን ጉትቻ
የዳኘው አሽከር አባ ነፍሶ ባልቻ።
የጠላት ጦር ደጃዝማች ባልቻ ወደሚኖርበት እስከ ጉራጌ ድረስ በመዝለቅ በእሳቸው ላይ ዘመተባቸው ህዝቡም ከዳቸው ወታደሮቹም ለህይወታቸው ሲሉ ሸሿቸው ደጃዝማች ባልቻ እና ሁለቱ አሽከሮቻቸው ከእሳቸው ጋራ ሦስት ሰው ብቻ ቀረ ብዛት ያለው የጣልያን ጦር ከበባቸው ወዴትም መሄድ አልቻሉም ። በመጨረሻም እጅህን ስጥ መሳሪያህን ጣል ብሎ ጣልያኑ ሲያዛቸው ደጃዝማች ባልቻ እኔ እጄን የምሰጥ ሰው አይደለሁም ትጥቄን አልፈታም ብለው ነጩን ጣልያን ገድለው በራሳቸው ጥይት የራሳቸውን ህይወት አጠፉ። እጃቸውን እንኳን ለጠላት ሳይሰጡ በራሳቸው ሽጉጥ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም ተሰው።

@wegoch
@wegoch
2024/09/25 19:27:49
Back to Top
HTML Embed Code: