Telegram Web Link
👆👆👆👆


አድምጧት አጭር፣አስተማሪና አዝናኝ ወግ!!

ምንጭ
ደራሲ :-አሌክስ አብርሀም
ከ "ዙቤይዳ" መጽሐፍ
ገጽ 201 የተወሰደ
ርዕስ:- "እግር በእግር"
ተራኪ :- ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
(@San2w)
ሚያዚያ 2011 WOLDIYA UNIVERSTY

@wegoch
@wegoch
ሦስት ሙሉ ጥሪ ጨርሶ በአራተኛው በሰላም ሊሆን እንደማይችል ገምቼ ነበር
ስልኩን ያነሳሁት። 'ስልኬንም ማንሳት ደበረሽ?' ሲለኝ ተናደድኩበት። ደብሮኝ ሳይሆን ፡ ልትደውል የሚያስችልህ ፡ የቀረህ ነገር እንደሌለ ስለማውቅ ነው ማንሳቱን ያልመረጥኩት። አሁንም ተደጋጋሚ ሲሆንብኝ የሰላም ስላልመሰለኝ ነው። መጀመርያ ግን ሰላምታ አይቀድምም? ። ገርሞኛል ድፍን 60 ቀናት ተቆጥረዋል ሳንደዋወልም ላንገናኝ ከተስማማንም። "በዚህ ፍጥነት እንዲህ ትረሺኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም" አለኝ። ድፍረቱ! 'ተውኩህ እንጂ አልረሳውህም'
"ያው ነው ፣ ጭራሽ ነው ያቆምሽው፣ መደወሉንም ፣ መልዕክት መላኩንም።
ጉድሽን ልየው ብዬ ነበር ዝም ያልኩሽ" አለኝ። ስልክ ማውራት የማይመች ሁኔታ ውስጥ ስለነበርኩኝ ፡ ይቅርታ ጠይቄው መልሼ እንደምደውልለት ነግሬው ስልኩን ዘጋሁት። ገርሞኛል ፣ ምን ነበር የጠበቀው? ተስማምተን አልነበር እንዴ የተለያየነው? ሀሳቡ ከርሱ አልነበር የመጣው? ከሁለት ወራት በፊት የሆነው እንዲህ ነበር ... ሰሞኑን እየሆንን ያለነው ነገር ምንድነው? ብዬ ጠየኩት። መክሰስ በልተን አስተናጋጁ እቃዎቹን ካነሳልን በኋላ "እንዳትለምጂኝ እያደረኩ ነው " ሲለኝ ለአፉ እንኳን አልከበደውም! በሰዓቱ ድንጋጤ ብቻ አልነበርም የተሰማኝ ፣ በተቀመጠበት ትቼው መሄድ
ፈልጌኣለሁ ፣ ግን ደሞ ፈራሁ ። መለየትን እፈራለሁ ፣ ተላምዶ መለያየትን ፣ ጨለማን በህይወቴ በጣም ከምፈራቸው ነገሮች ቁጥሩ አንድ ነው። ማጣትን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ፡ ለዓይን ምንም እንደማይታይ ዓይነት እፈራዋለሁ።
ዓይኔን እያየ "እንዳትለምጂኝ" ሲለኝ በፈጠረብኝ የመደናገር ስሜት ብድግ ብዬ ብሄድ ተመኝቼ ሁላ ነበር። ግን ድጋሚ ባላገኘውስ ብዬ ፈራሁ ፣ አጎንብሶ ስልኩ ላይ አፍጥጧል። አየዋለሁ ፡ በየመሃሉ ከስልኩ በሚያየው ነገር ይመስላል ፈገግ ይላል መች ነው እንደዚህ የሆነው? ሴትነቴ እሱን አለማስደሰት የጀመረው መች ነበር? ከሁለት ሳምንት በፊት "ካንቺ ጋር ስሆን የማገኘውን ደስታ እስከዛሬ የትም
አግኝቼው አላውቅም" አላለኝም ነበር? ጆሮዬ ነው የፈጠረው፡ ወይስ ብሎኝ
ነበር? ድንገት መደንገጤንም ፡ ንዴቴንም ዋጥ አደረኩና 'ዎክ እናድርግ የኔ ፍቅር ?' አልኩት ልምምጥ በሚመስል ቅላፄ "ውይ ደክሞኛል ዛሬ ፣ ታክሲ ያዥና ሂጂ" ሲለኝ በድንገት እምባዬ ከየት መጣ? ጉንጮቼን አልፎ በአንገቴ በኩል አድርጎ እየወረደ መሆኑን እንዴት አላስተዋልኩትም? አሁንም ስልኩ ላይ እንዳቀረቀረ ነው። ፍቅሬን ምን ነካው? ባለፈው ፡ የጥር ሚካኤል ዕለት አልነበር ፡ ከጥምቀት መልስ ቤታቸው ሄደን እናቱን እየተፍለቀለቀ '' ወደፊት የማገባት ሚስቴ እሷ ናት'' ብሎ ያስተዋወቀኝ? እናቱ ከግንባሬ እስከ አንገቴ አገላብጠው ስመውኝ አልነበር? እሺ በጣም በቅርብ አልነበር እንዴ ከውጭ ከመጣው ወንድሙ ጋር ለ 3 ቀናት ደብረዘይት ሄደን አሪፍ ጊዜ አሳልፈን የመጣነው? ፍቅሬ የት ሄደ? ሰሞኑን በስልክ ጭቅጭቅ ስላበዛን ነበር ዛሬ የተገናኘነው። መታገስ አለብኝ ፣ ንዴቴን መቆጣጠር ፣ ተረጋግቼ ማዋራት አለብኝ። ውሃ ልጠጣ? ወይስ አየር በደንብ እየሳብኩ ላስወጣና ራሴን ላረጋጋ? ምን ነበር ራስን ለማረጋጋት የሚደረገው? ብድግ አልኩና መታጠብያ ቤት ሄጄ ራሴን አረጋግቼ ተመለስኩ። የሰሞኑ ሁኔታህ ምንም አላማረኝም የኔ ፍቅር ፣ ምንድነው የሆንከው? ልታሳውቀኝ የምትፈልገው ነገር እንዳለ ስለነገርከኝ ነበር የመጣሁት። ግን ደሞ
ለማውራት ፈቃደኛም አይደለህም ፡ ምንድነው የሆንከው? ብዬ ጠየኩት።
ምን ሆኜ ነው የምለማመጠው? ትዕግስት ነው ወይስ ፍራቻ እንዲህ
የሚያደርገኝ? ቀና አለና ከአንገቱ ተመለከተኝ። ዓይኔን ግን ይሸሻል "ይሄን ስልሽ አዝናለሁ ምንም የምነግርሽ ምክንያት የለኝም ። ግን ግንኙነታችን እዚሁ ላይ ቢያበቃ ደስተኛ ነው ምሆነው" አለኝ። ሆዴን ለምን ቆረጠኝ? ምንድነው የተበጠሰው ከውስጤ? ለደቂቃዎች ያህል ምንም አልመለስኩለትም : ዝምታዬ ያስፈራው ይመስል በየመሀሉ እየሰረቀ ያየኛል።
ከብዙ ዝምታ በኋላ፡ አንተን የሚያስደስትህን ነገር እኔም አደርጋለሁ።
ምክንያትህን እንድትነግረኝም አላስጨንቅህም። ሀሳብህን አከብራለሁ። በነበረን ጊዜም በጣም ደስተኛ ነበርኩ ፡አመሰግናለሁ የኔ ፍቅር። ብዬ ከንፈሩን በስሱ ስሜው ደህና እንዲያድር ተመኝቼለት ነበር በተቀመጠበት ትቼው ወደ ቤቴ የገባሁት። መሰናበቻ ነበር!
ረጅም መንገድ በእግሬ ተጉዣለሁ ፣ ካለፈው ህይወቴ እንደተማርኩ የገባኝ የዛን ምሽት ነበር። በማግስቱ ጧት ለአለቃዬ እንዳመመኝ እና ስራ እንደማልገባ መልዕክት በስልኩ ትቼለት ስልኬን አጠፋሁና ለሁለት ቀናት ከቤቴ ሳልወጣ ከራሴ ጋር ሆንኩኝ። በ 3ኛ ቀኔ በጧት ተነስቼ ቁርሴን በአግባቡ ተመግቤ ቆንጆ ሆኜ ወደ ስራ ገባሁ። ብርታት አገኘሁ፣ ነገ የተሻለ አዲስ ቀን እንደሆነ አምኜ ወደ ስራዬ ተመልሻለሁ። ፍፁም ሰላማዊ ሆኜ መኖር ጀምሬአለሁ። እና ዛሬ በምን ትዝ ብዬው ምን ፈልጎ ነበር የደወለው? እኛ እንደዚህ ነን። በቃ የምንሸዋወድ ሰዎች ነን። የውስጣችንን ስሜት ፣ ዕውነት የሆነውን ስሜታችንን ማዳመጥና መኖር የምንሸሽ ፣ በትንሽ ክፍተት ደስታችንን የምናጣ . . . ስንቶቻችን ተላልፈናል? እኔ ግን...መልሼም አልደውልለትም።ቢደውልም የሚቀየር ነገር አይኖርም። እኔና እሱ የአብሮነትን መንገዳችንን ስተናል። ምናልባትም የፍቅሬን መጠን መፈተኛ መንገድ መስሎት ይሆን? ቢሆንም ግን ስህተት ሰርተናል፡ በቃ ተላልፈናል ...


@wegoch
@wegoch
@paappii

By ጠርሲዳ ከበደ
በአንድ ዘመን ላይ ኖረውልን ቢሆን ኖሮ ማንም አይደርስብን!

👉 መከላከያ ሚኒስቴር
አሉላ አባ ነጋ 👊

👉 የቴክኒዮሎጂ ሚኒስቴር
አፄ ምንይልክ 👌

👉 የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
አፄ ሐይለስላሴ 🙏

👉 አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን
ዋና -አቶ መለስ ዜናዊ
ምክትል -ታማኝ

👉 የመንግስት ቃልአቀባይ
ዶር ብርሃኑ ነጋ

👉 የፌዴራል ፖሊስ ዋና አዛዥ
ኦቦ አብዲሳ አጋ

👉 የሁሉም ልዮ ሃይሎች ዋና አዛዥ
በላይ ዘለቀ
ምክትል -ዋለልኝ

👉 ትምህርት ሚኒስቴር
ሼኽ በክሪ ሰበሎ
ምክትል - ነጋድራስ እሸቴ

👉 ኤኮኖሚ ምኒስቴር
አትሌት ሃይሌገብረስላሴ
ሼኽ አሊ አል አሙዲን

👉 ውሃ እና ፍሳሽ የበላይ ሃላፊ
ጌታቸው አሰፋ 😊

👉 ማዕድን ሚኒስቴር
መለስ ዜናዊ

👉 የሰላም ሚኒስትር
ሃይለማርያም ደስ አለኝ 😃

👉 ሕዝብ ግንኙነት ሚኒስቴር
ዋና - ለማ መገርሳ
ራስ አሊ (ወሎ )
ምክትል -(የጅማው) አባጅፋር

👉 ሰብሳቢ- ክቡር ነጋሶ ጊዳዳ

👉 ፀሃፊ-አይተ እቁባይ በርሄ

👉 ማስታወቂያ ሚኒስቴር
ጃዋር መሃመድ
ደሳለኝ ጫኔ

👉 የሶማሊያ እና ጎረቤት ሃገሮች ጉዳይ አማካሪ
ኦቦ ዳውድ ኢብሳ

👉 የከተማ ፕላን
አፄ ፋሲል

👉 የየሰሜን ዋልታ ጫፍ አምባሳደር
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

👉 ጠቅላይ ሚኒስቴር
አብይ አህመድ

👉 ፕሬዝደንት
መንግስቱ ሃይለማርያም 💪

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Abeba birhanu
"አንድ ግጥም አንድ ወግ" በልዑል ሀይሌ እና አዱኛ አስራት

አይጠራጠሩ ይወዱታል!!

https://m.youtube.com/watch?v=uQeOUPsKI2k&itct=CBgQpDAYACITCJ343--S2uECFdHywQodEskBPlIk4Yqg4YqV4Yu1IOGMjeGMpeGInSDhiqDhipXhi7Ug4YuI4YyN&hl=en&gl=US&client=mv-google

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
#የድሮ_ጓዴ
አቅራቢ :ትንቢት ዳንኤል
ደርሰት ፦ትንቢት ዳንኤል

@wegoch
@wegoch
ግጥም ብቻ
ሰልችቶናል! (ከአጠገቤ ለተቀመጠችዋ የተፃፈ)
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ከአሰልቺው መንገድ... እንደ ቢንቢ ጆሮህ ስር እየተከተለ ጥዝዝዝዝዝዝዝዝዝ እያለ የሚመታህ የሰሞኑ ፀሀይ... እረፍት ቢስ ሀሳብ እና ረጅም የህይወት ጉዞ ለመገላገል ወደ ቤት እየሮጥኩ ነው፡፡ ግድግዳ እና ጣራ ከሚባል ከሀሳቤ ጭንቀት ሊያድነኝ ወደማይችል ውሸት እሮጣለሁ፡፡ ጭንቅላቴ አካባቢ የሆነ ጭምቅ የሚያደርግ ስሜት ይሰማኛል... ህመም ብርቅ ባልሆነበት አለም ውስጥ ቢጨምቀኝ ቢጠምቀኝ ለዚህች አለም ህመም ጩኸት አላዋጣም! የሆነ ራሴንም እያመመኝ ነው... እኔንጃ አልገረመኝም! ይመመኛ! አስራ ስንት ሺህ ግዜኛ ነው ራሴን ያመመኝ? ሌሎቹን ምን ሆንኩ? ምንም! ለዚህች አለም ጩኸት እና 'እህህህህ' የሚል የህመም ድምፅ አላዋጣም! ሰልችቶኛል!

አንዳች ከባድ ሸክም ከጀርባዬ አዝያለሁ... ለሰው ይታያል ወይስ እኔ እየመሰለኝ ነው? ምን እንደሆነ እንጃ... ልነካው እጄን ወደ ጀርባዬ ስሰድ ጣቶቼ ምንም አይነኩም... በቃ ተሸክሜው ዞራለሁ... ስተኛ ተሸክሜ ፣ ስቀመጥ ተሸክሜ ፣ ቸርች ስሄድ ተሸክሜ ፣ ስመለስ ተሸክሜ ፣ በመሰላቸት የሆነ ሌላ ሰው የፈነቀለውን ክብ ድንጋይ ጠልዛለሁ፡፡ ምን ሆናለሁ?
ወደ ቤቴ የሚወስደኝ ታክሲ ጋር ስደርስ ሰልፍ አለ፡፡ ስሰለፍ ተሸክሜ... ሰልፍ ሰልችቶኛል... ምንም ሰልችቶኛል፡፡ ጩህ ጩህ አለኝ! አይይይ! ለዚህች ብጥብጥ አለም ጩኸት አላዋጣም፡፡ ሰልፉ ረጅም ነው... ሄጄ ከሰልፉ ፊት ለፊት ቆምኩ (ከሰው ጋር መጨቃጨቅ አልሰለቸኝ ይሆን?) ዝም ብዬ ቆምኩ! መኪና መጣ... እንደ መብቴ ገባሁ፡፡ ማሸነፌ ይሆን? ሳሸንፍ ተሸክሜ ይሆን?

አንድ ወጣት መጥታ አጠገቤ ተቀመጠች፡፡ አላየሁዋትም... መቁለጭለጭ ሰልችቶኛል... የማያውቁትን ለማወቅ መጣር ሰልችቶኛል፡፡
መሄድ ጀመርን... በመስኮቱ ልታምር ስንዝር የሚቀራትን ጨረቃ እያየሁ ነው፡፡ የሆነ ሰዓት ላይ ዞሬ ሳያት እያለቀሰች ነው... ቆንጆ ናት... ሳያት አፈረች... ማፈሯ እንባዋን አልያዘውም ከደገፈችበት እጇ ስር አንድ ዘለላ እንባ መስመር እየሳለ ወረደ፡፡ ዞርኩ... በአይኔ ሽንፈቷን ልሰብካት አልፈለኩም... ከማልቀስ በላይ ሲያለቅሱ መታየት ያስለቅሳል፡፡ መስኮቱን ከፈትኩላት... ንፋሱ እንባዋን እንዲያደርቀው አስቤ ነው? ማልቀሷ በምን ይታወቃል? እንባዋን ካደረቅኩባት... ሀዘኑን በእንባው መጠን በሚለካ ህዝብ እና ባህል መሀል እየኖሩ የሰው እንባ ማድረቄ ያስጠይቀኝ ይሆን? ምናልባት ለዚህች ስግብግብ አለም እንባ እያዋጣች ይሆን?
እኔንጃ! አለማወቄን ይሆን የተሸከምኩት?

ምን ሆና ይሆን? ምን ልበላት ብዬ አሰብኩ...ምናልባት ከእጮኛዋ ጋር ተጣልታ? በዚህ ፀብ ዘመን አለመጣላት እኮ ነው የሚከብደው፡፡ ወይ ዘመድ ሞቶባት? ወይ የአክስቷ ልጅ ሰድባት... ወይ አክስቷ? ጓደኛዋን ከሌላ ሴት ጋር አይታው? ምናልባት እሷ ያላወቀቻቸው አራት ሌሎች ሴቶች ይኖሩታል... እሱን ብታውቅ የበለጠ ታለቅሳለች? ነው ወይስ እንደ እኔ ሁሉ ስልችት ብሏት ነው?
እንደ ፈላስፋው ኒቼ ከእግዜር ትግል ገጥማ ደክሟት ነው?
"a peace is a buffer zone between two wars" እንዳለው ሆና ይሆን? ከሆነችስ ጦርነቷ ወይስ ሰላሟ የሚያስለቅሳት?
እንጃ! አለማወቅን ብቻ ነው ለአለም የማዋጣው፡፡ መውረጃዬ ደረሰ... እጇን ያዝኳት... በዚህ በሀዘኗ ሰዓት ባለ ውለታዋ ለመሆን እየሞከርኩ ነው? እኔንጃ! ሰልችቷታል ከተደገፈችበት ቀስስ ብላ ዞረች፡፡
አፌ ላይ ያለውን አወራሁ "ምን እንደሆንሽ አላውቅም! ሰው እያየሽ አታልቅሺ፡፡ አይዞሽ!" በሆነ አይነት አስተያየት እያየችኝ ነው... ሸክሜ ታይቷት ይሆን እንደዚህ ምታየኝ?

"ወራጅ" አልኩ ክንዷን ለቅቄ... ሰው ፊት ስለ እምባዋ አውርቼ አሳፈርኳት? እንጃ!
ወረድኩ... ከኀላዬ ወረደች... ቀስስ ብላ መራመድ ጀመረች... ቆሜ አየሁዋት፡፡ ተሻገረች... ውስጤ ሂድ አፅናናት ይለኛል... ነው ወይስ ሌላ ፍላጎት አለኝ? አየኀት... ቀስስ ብላ ትሄዳለች፡፡ እሷም ሸክሟ ከብዷት ይሆን?
ለዚህች ልጅ የኔ ቃል ምኗ ነው? ዞሬ ሄድኩ...
አሰብኳት... አሳዘነችኝ... ከእህት የቀረበች መሰለችኝ... የሴት እምባ ይከብደኛል የሚፈስ የሀዘን አሎሎ...
ሄድኩ... ራቅሁ.... ቀስ ብሎ ከአንዱ አይኔ ስስ እምባ ተንከባለለ
ለዚህች ልጅ የኔ የምፅዋት እምባ ምኗ ነው?
ሰልችቶኛል...
(በረከት ታደሰ)

@wegoch
@wegoch
<<ኤርትራ ውስጥ ብትወለድና እትብትህ እዛ ቢቀበር እትብትህን የበላው ምስጥ ግን አፋር ላለመድረሱ እርግጠኛ አትሁን። ጋምቤላ ተወለድ እትብትህን ጋምቤላ ውስጥ የበላው ምስጥ ግን አፋር ላለመድረሱ እርግጠኛ አትሁን። ለምን ከምስጡ ለመሻል አትሻም ? ለምን ትጠባለህ?.......ሰፊ አገር እያለህ ለምን ጠባብ ክልል አገርህ እንዲሆን ትመኛለህ?.....አህያ እንኳ ጋጣው ሲጠበው ይራገጣል። አትጥበብ። የማያሳፍርህ ነገር ቢኖር በኢትዮጵያነትህ ማመንህ ብቻ ነው በቃ። >>

<>ዴርቶጋዳ <>
©ይስማዕክ ወርቁ

@wegoch
@wegoch
@Bebra48
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቀንዲል ዲጂታል መፅሔት.pdf
6 MB
ቀንዲል ዲጂታል መፅሔት

#አዝናኝ #አስተማሪ #ወቅታዊ #ሀገርኛ መፅሔት

ቅፅ 1 - ቁጥር 3

💵ፓኬጅ ከገዙ 70 ሳንቲም ብቻ💵

@KendilM
@KendilM
"ማሰብ፣መናገር፣ማድረግ" እነዚህ ሶስት አብይ አሳቦችን አፅኖት ሰጥተን እንመልከት የሰው ልጅ የሚፈጠረው ፣በሕይወቱ ዘመኑ ፅድቅም ሆነ ሀፅያት የሚሰራው በነዚህ ሶስት ነገሮችነው፡፡ 1 እንዴት የሰው ልጅ ይፈጠራል? እልፍ አመት ተጉዘን ቁዱስ ቁርሃን እና መፀሀፍ ቅዱስ ገልጠን ብንመለከት ይሄን የጥያቄያችንን መልስ እናገቻለን ግን ቀላል በሆነ መንገድ ለመመለስ ያህል "ሁለት ጥንዶች አብረው በአንድ ጎጆ በፍቅር ይኖራሉ፡፡ በነዚህ ጥንዶች መካክል ጊዜውን ጠብቆ የሚመጣ የቀጣይ ሕይወታቸውን ያማረ ፣ተድላ የሆነ ምኞታቸውን ላምባ የሚያሳይ ልጅ የመውለድ አሳብ በአይምሮአቸው ይቀረፃል፡፡ ይህ አሳባቸውን እውን ለማድረግ በመነጋገር ይፈታል ከዛ የአሰቡት፣ የተነጋገሩት ሁሉ በሁለቱም ዘንድ ተቀባይነት ካገቸ ወደ ተግባር ይገባሉ፡፡ ከዛ ከዘጠኝ ወር በኦላ የሰዉ ልጅ ይፈጠራል 2እንዴት የሰው ልጅ ሀፅያት ይሰራል? "ሰው ሆነን ስንፈጠር ፣ወደ ዚህ ስንቀላቀል ከፍት ፣ተንኮልን ይዘን የተፈጠረ ማንም ሰው የለም፡፡ ጊዜ እድሜን፣ ማንነትን፣ አሰተሳስብን፣ እውቀትን፣ ደረጃን.... ብዙ ነገር ቀያራ ነው፡፡ በምንኖርበት፣ በምንሰራበት፣ በምንማርበት ቦታ ከእኛ ቅንፁል ደረጃ ከፍ ያለ ጓደኛ ይኖረናል፡፡ ለዛ ሰው በውሰጣችን የሚሰማን ሰሜት ይኖራል፡፡ እንዴት በለጠን? ፣ከእኔበምንተሽሎነው? እያልን ሌትም በማህልትም የተቃረነ አሳብ በውሰጣች ገብቶ እንብከነከናለን፡፡ ሰሚ አገቸንም አላገቸንም ለብዙ ጊዜ በውሰጣችን የሚመላለሰውን አሳብ ለምናውቃቸው ናለሚያውቁን ሰለዛሰው እያነሳን እናወራለን፡፡ ከዛ የዛ ሰውን እድገት ለማደናቀፍ የውሸት መረብ በማዘጋጀት ከሰራው፣ ከትምሕርቱ፣ ከማሀበራዊሕይወቱ እንቅፍት እንዲገጥመው እንጥራለን፡፡ ጥረታችን እውን ሲሆን የዛ ሰው ሕይወት መና ሲሆን እኛ እንደሰታለን ሕልማችንም እልባት ያገኛል፡፡ 3እንዴትየሰው ልጅ ፅድቅ ይሰራል? "የመልካምነት ዋጋዋ ትንሽ ናት፡፡ ግን ቱርፍቱ ብዙነው፡፡ የምናሰበው አላማ ፍሬውን ማግቸት ባንችልም በሌላ ሰው ዘንድ ማየት ስንችል ለእኛም ተስፍ ይሰጠናል እና ልንደሰት ይገባል፡፡ ብዙ ሰዋች በአዮት፣ በሰሙት ነገር ተነሰተው ለሰዋች አድናቆት ይሰጣሉ፡፡ መልካም ነገር መናገር ደግሞ የመልካምነት አሰተሳሰብ ውጤትነው፡፡ ብዙ ሰዋች ለሰው ያላችውን ከብር ለመግለፅ ለዛሰው የሰራእድልበመፍጠር፣ የትምሕርትእድል በማመቻቸት ፣ሽልማት ፣እውቅና፣እርዳታ በመሰጠት መልካምነትን ያደርጋሉ" በሕወታችን ውሰጥ በሚጠቅሙሞ በማይጠቅሙም አሳቦች ተዘፍቀናል እንከርዳዱን ከንፁሁ እህል ለመለየት ደግሞ የሰው ልጅ የጊዜ እሰረኛ ነው ፡፡ትናንት መጥፎ ያልከው ዛሬመልካምነው ፣ዛሬ መልካም ነው ያልከው ነገ መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ለሁሉም ነገርመልካምነት ይሻላል፡፡

5/8/2011 የተፃፈ
ከአሸናፊፍቃዱ/1050/

@wegoch
@wegoch
@wegoch
..........................................
ያመለጠው ዶሮ እና አመላለጡ(ልዑል ሀይሌ)
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አመለጠ!!...እውነቴን ነው አመለጠ!!...ለስንት ነገር ያሰብኩት ዶሮ
ለስንት ነገር ሳያስበኝ ከእጄ አፈትልኮ አመለጠ!!...እኔም በድንጋጤ
በመንገዱ ስታልፍ ከነበረች ባልቴት በእጇ ይዛው የነበረችውን
መዘፍዘፊያ ነጥቄ ዶሮዬን ባሯሩጠውም በቅያሱ በኩል ታጥፎ
አመለጠኝ። ...ፍጥነቱ ሲገርም ይሄማ የኡሴን ቦልት እጅ አለበት እንጂ
ሰው (ማለቴ ዶሮ) እንደዚህ አይሮጥም። ወይም ልክ እንደተሸጠ
ከገዢው አምልጦ እንዲመለስ ሻጮቹ አለማምደው ተልዕኮ
ሰጥተውታል እንጂማ ሰው (ማለቴ ዶሮ) እንደዚህ አይሮጥም።
ከዶሮው ማምለጥ በኋላ ቆም ብዬ ዙሪያ ገባውን ስቃኘው ከኋላዬ
ሁለት ቆመጥ(አጭር ዱላ) የያዙ ፖሊሶች መቆማቸውን አየሁና
"በዚህ ነው!...በዚህ ነው ያመለጠው!!..ኧረ ድረሱበት..." ብዬ ገና
ብሶቴን ከመጀመሬ አንደኛው ቆመጥ(ማለቴ ፖሊስ)..ጀርባዬን
ሲነርተው 'ከዶሮው ጋር ተመሳሰልኩበት ይሆን?' ብዬ የተገነጠለውን
(ማለቴ የተመታውን አካሌን) ማሻሸት ጀመርኩ።
"ባንተ ቤት አምልጠህ ሞተሃል...ከኔ እንኳን አንተ አንድ ወመኔ ንፋስ
ውስጥ የምትንገላታ አንዲት ስንጥር ልታመልጥ አይቻላትም!.." አለኝ
ከቁመቱ በላይ እየነጠረ እኔም ከድንጋጤዬ ለመውጣት እየታገልኩ
'ምነው ይሄ ሰውዬ አክቲቪስት ነኝ አለ!!..'(አልኩኝ በውስጤ)..."ኧረ
ዶሮዬ እየራቀች ነው እባክህን በዚህ ሞራልህ በቁጥጥር ስር
አውልልኝ ...እውነት ከደረስክባት እና ከያዝካት ከአንቀፅ 39 በኋላ
(ማለቴ ከግንጠላው በኋላ) እግሯንና አንገቷን..." ብዬ ሳልጨርሰው
ሁለቱ ፖሊሶች እየተከታተሉ በንፋስ ፍጥነት ከአጠገቤ ሲርቁ ሳስተውል
ክው ብዬ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ "በቃ ጆሮ ቀረ ማለት ነው?...አሁን
የዶሮ አንገትና እግሯ ምን ያደርግላቸዋል?...ዘንድሮኮ ከማዳመጥ
መሮጥ እየቀደመ ተቸገርን...ወይ ሳላስበው አንገቷ ላይ ጩባ
አድርጋለች ብያቸው ይሆን እንዴ?...ከተገንጣይ ላይ ለመካፈል
እንደዚህ መሮጥ አግባብ ነው?..ኦ ኦ!..ሳላስበው ቡተሊካን ነካካሁ
መሠለኝ...የኔ ጥያቄ የዶሮዬ ማምለጥ ነው እኔ እንደሌሎቹ ዶሮዬን
አስታክኬ ቡተሊካ አላወራም የስንት ዘመን መጠጫዬን
አጠራቅሜ..ስንት ዕቁብ ዕድሩን አዳርሼ የገዛሁት ዶሮዬ የሚገኝ ከሆነ
ግን ፓርቲ ባቋቁምም አይቆጨኝም። እንደውም ላቋቁም ይሆን
እንዴ?...የ.ዶ.ብ.ፓ.(የጠፋችው ዶሮዬ ብትገኝልኝ ፓርቲ)...12
ብልቶቹ ክልሎችን እና አዲሱን የዶሮ ማደሪያ ሽቦ... የሚወክል ሆኖ
(አይ የኔ ነገር አፈርኩ እኮ!...እንዴት ግን ሐበሻ ለራሱ አንድ ብልት
ወስዶ ዶሮን ብልት በብልት አደረገው?..አሁን ፈረሰኛ እንዴት ብልት
ሊሆን ይችላል?...ኦ..ኦ..እንደውም ይህቺን ጥያቄ በፓርቲዎች ስብሰባ
ላይ አንስቼ ጉድ ካላስባልኩ ምናለ በሉኝ..ተከታይ እንደሆነ
አላጣ...ስንቱ ማንን እንደሚከተል ጠፍቶት ሲያዛጋ አይደል
የሚውለው?)...ወይኔ ዶሮዬ ግን የት ደርሶ ይሆን?...ኧረ መኪና
እንዳይገጭብኝ ሌላውስ ሌላ ነው። ለነገሩ እንደዛ ከሆነስ ከቴሌቪዥን
ጣቢያዎች በአንዱ በዜና ሳላየው አላመሽም..'በዛሬው ዕለት 600 ብር
የተገዛ ዶሮ ሊያመልጥ ሲሞክር በመኪና ተገጭቶ ሆስፒታል ገብቶ
የሕክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል::'..ብሎ አንዱ ሲዘግብ
አላጣውም። ..ወይ አፋልጉኝ ልለጥፍ ይሆን?..እንዲህ ብዬ ልፃፈው?
'ተፈላጊ:-አንድ መልከ መልካም ነጭ እና ጥቁር ዶሮ...አካባቢውን ዞር
ዞር ብዬ ንፋስ ልውሰድ በሚል ተልካሻ ሰበብ ከገዢው መደብ(ማለቴ
ከገዢው እጅ) አፈትልኮ ከአካባቢው ተሠውሯል። ይሄንን ዶሮ አግኝቶ
ለባለቤቱ ላስረከበ ወገን ፈረሰኛው ጊዮርጊስ ውለታውን ይክፈለው።
ፈላጊ ባለጡሩምባው....''አይ ዶሮዬ ምነው የበላህ ሰውዬ አልጮህ
አለ?''...ለነገሩ ይሄንን የመሰለ ለበግ ሩብ ጉዳይ የሆነ ዶሮ ሰልቅጦ
እንደምን ይጮሃል?...እህህ...እስቲ ተዉኝ!!...ከራሴ ጋር አስፓልት
ዳር ቆሜ እንዲህ ስወዛገብ ..አንዲት ባልቴት መጥታ በእጄ የያዝኩትን
መዘፍዘፊያ ነጥቃኝ "ሌባ!!..ሰርተህ አትበላም?..ትልቅ ሰው
አይደለህ?..." ብላ በጩኸት ከገባሁበት ሐሳብ ስታናትበኝ
እያገላበጥኩ አያት ጀመር የአወራሯ ፍጥነት ከጠፋው ዶሮዬ ጋር
ተመሳስሎብኝ...ምናልባት ተቀይራ ብትሆንስ ይኸው ሴትዮዋ
እንደማያት ብልት በብልት ነች 12 ይሙላ አይሙላ እርግጠኛ
ባልሆንም...አይቼ ሳልጨርሳት ቂን ቂን እያለች እየለፈለፈች ዶሮዬን
ወደገዛሁበት አቅጣጫ ስትሄድ ተከትያት መሄድ ጀመርኩ...ጉዷን
ልየው ብዬ!!...ስትሄድ ስከተላት የሚለው የጋሽ ጥላሁን ገሠሠ ዘፈን
እንዳጋጣሚ ከአንድ ቡቲክ ሲያጅበኝ ምናልባት ግምቴ ትክክል ሊሆን
እንደሚችል እያሠብኩ ...መዘፍዘፊያዋን..ማለቴ ሴትዮዋን ወደ ዶሮ
እስክትቀየር በጉጉት እየተጠባበቅኩ እየተራመድኩ ነው። ዘንድሮ
ሁሉም እንደ እስስት በሚቀያየርበት ጊዜ ይህቺ ሴትዮ ወደ ዶሮነት
ብትቀየር ምኑ ያስገርማል?..ሴትዮዋ አንድ የዕንቁላል ሻጭ ጋር ዋጋ
ስትደራደር ሳይ ይበልጥ ጥርጣሬዬን ጨመረችው። እንዴት ይሄንን ሁሉ
ዕቃ ዘልላ ዕንቁላል ልትጠይቅ ቻለች?..ዕንቁላሉን እያገላበጠች
ስትፈትሽ ሳይ ለምን እንደሆነ እንጃ.. ልጇን ከገበያ እየፈለገች እንደሆነ
ተሰማኝ...አገላብጣ ካየች በኋላ አላገኘችውም መሰለኝ ጉዞዋን
ስትቀጥል እኔም መጨረሻዋን ልይ ብዬ ተከተልኳት...ሴትዮዋ አየሩን
በመዘፍዘፊያው እየቀዘፈች ከአንድ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ስትገባ ጠጋ
ብዬ ማማተር ጀመርኩ..ከሴትዮዋ ፊት ለፊት ያየሁትን ነገር ግን ማመን
አልቻልኩም። ቁርጥ የጠፋውን ዶሮዬን የሚመስል ዶሮ አንድ እግሩ
ላይ ካሰርኩለት ከቤት ይዤ ከወጣሁት ቀይ ማሠሪያ ገመድ ሳይ
በድንጋጤ የማደርገው ጠፋኝ..የኔ ነው ብዬ ሐገር ምድሩን በአንድ
እግር ስለማቆም አሰብኩ ነገር ግን ታርጋ የለው ነገር በምናባቴ የኔ
መሆኑን ማሳመን እችላለሁ?.. ያ ዶሮዬ አይን ዓይኑን ትክ ብዬ ሳየው
እንዳጋጣሚ ሲጮህ ተስረቅራቂው ድምፁም የኔ ዶሮ መሆኑን
አረጋገጠልኝ። ሆኖም እንዴት እንዴት ብዬ የኔ የጠፋው ዶሮ እንደሆነ
ላሳምናቸው?...ወይ ስም የለው..ወይ መታወቂያ የለው...ወይ ብሄር
የለው ነገር...እንደጨነቀኝ እዛው ተገትሬ ፊት ለፊቴ የሚካሄደውን
ትንግርት እያየሁ ከቆየው በኋላ ቤት የሚጠብቀኝ ጭቅጭቅ በሃሳቤ
ውልብ ብሎ ሲያልፍ አንዳች ኃይል ገፍቶኝ ሱቁ ውስጥ ተገኘሁ።..ያቺ
መዘፍዘፊያዋ የኔን መግባት ስታይ በአሽሙር መሸርደድ ጀመረች..."አይ
እቴ!...ምነው ጥላ በዛብኝ...ይህቺን መዘፍዘፊያ ገዛች ተብሎ
ሲ.አይ.ኤ. ይመደብብኝ?..አዪ ዕድሌ...ዕድሌ ነው.." ...እኔም
የምናገረው ጠፍቶብኝ ዓይኔን ከዶሮዬ ሳልነቅል "እዚህ ሱቅ ካርድ
ይኖራል?"ስል...የመዘፍዘፊያዋ ድምፅ ድጋሜ አስተጋባብኝ "ወይ
ጉድ?!..ዶሮ በየት ሐገር ነው ካርድ የሚጠየቀው?..."...ሳላስበው
አንድ ቃል አሟልጮኝ ወጣ..."ይሄ ዶሮኮ..." ብዬ ከመጀመሬ ከሱቁ
ጓዳ ውስጥ አዲሷ ፍቅረኛዬ ስትወጣ ሳይ ሐሳቤን በእንጥልጥል
ተውኩት...መዘፍዘፊያዋም ከአፌ ያመለጠውን ቃል እስክቋጨው
እንደሚጠባበቅ በሚያሳብቅ ሁኔታ ስትገላምጠኝ
ብመለከትም...በፍቅረኛዬ ውብ ፈገግታ ተረትቼ አረፍተ ነገሩን መቋጫ
ሳላበጅለት ቀረሁ....አዲሷ ፍቅረኛዬም በአይኗ ጥቅሻ እንደማላውቃት
እንድሆን አሳወቀቺኝ(ስለቤተሠቦቿ ወግ አጥባቂነት ደጋግማ
ስለነገረቺኝ እኔም ወዲያው ነበር ምልክቷን የተረዳሁት)..."እ...ካርድ
ይኖራል?"..."አለ...ግን ባለመቶ ብቻ ነው...ልስጥህ?.." ስትለኝ
የሞት ሞቴን "አ...አዎ ስጪኝ" አልኳትና የሷንና የቤተሰቦቿን ማጅራት
መቺነት እየረገምኩ ከሱቁ ወጣሁ...እንግዲህ አንዳንዴ እንዲህ ነው።
ስጦታ መስጠት እንደማልወድ የገለፅኩላት ፍቅረኛዋ እኔ ብቻ
የማውቀው 700ብር ለሷና ለቤተሰቦቿ ሰጠሁኝ ግን ዕድሌ ሆነና
ተነጥቄ እንዳበረክት ተገደድኩ!!...እንኳን አደረሠሽ ውዴ!!..እንኳን
አደረሠሽ ውዴ!!...እንኳን አደረሠሽ ውዴ!!...እያልኩኝ የዶሮውን ገበያ
አቋርጬ ወደ ቤቴ ተመለስኩ...አይጣል...የአንዳንድ ቀን አዋዋል..!!

@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (👋ገብረዬ)
እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡

በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡
በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡
መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡

ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡
መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡

ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡
በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡

ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤ ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!

ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@getem
@wegoch
ለመከራ የፈጠረኝ! Re
«ዘውድአለም ታደሠ»
ኮንዶሚኒየም መኖር ችግር ነው! ሁሉም ዶሮና በጉን በሩ ላይ አስሮ ብሎካችንን ኤልፎራ አስመስሏታል። እኔም ትናንት ሚስቴ በግ ካልገዛህ እያለች ስትነተርከኝ ጥቂት ብር ይዤ በግ ልገዛ ብወጣ አንድ ቀውላላ በግ ነጋዴ ሁለት ፊታቸው ላይ ከባድ ድብርት የሚታይባቸውን ከሲታ በጎች ይዞ ቆሞ አገኘሁና ጠጋ ብዬ
«ልትሸጣቸው ነው?» አልኩት
«እና ሐገር ላስጎበኛቸው ነው ካገሬ ይዣቸው የወጣሁት?» አለኝ
«እንደው ኩነኔ አይሆንም እነዚህን መግደል?» ስለው ፈጠን ብሎ
«አንቀህ ነው እንዴ ምትገድላቸው?» አለኝ
«አይ ያው በቢላም ቢሆን ...» ብዬ ሳልጨርስ
«ወንድሜ ካሳዘኑህ ውሰድና በጉዲፈቻ አሳድጋቸው» አለኝ
«እሺ ስንት ነች እቺ?» አልኩት ወደአንዷ እየጠቆምኩ
«በግ ታውቃለህ ማለት ነው። በጣም አስተዋይ በግ ነች እሷ» ብሎ ጀርባዋን መታ መታ ሲያደርጋት ወደጎን ፍንግል አለችና አቧራዋን አራግፋ ተነሳች።
«እኔ አስተውሎቷ ምን ይሰራልኛል ላስተምራት አይደለም እኮ ምወስዳት» ስለው
«ሁለት ሺ ብር ክፈል» አለኝ
«ሁለት ሺ ብርማ አታወጣም»
«በርግጥ ላታወጣ ትችላለች ነገር ግን እኔ ሁለት ሺ ብር ነው የሚያስፈልገኝ»
«ቀንስና ልውሰድልህ» አልኩት
«አይ ወዳጄ በጓን ግን አይተሃታል? ውስጠ ወይራ እኮ ነች። መፍዘዟን አትይ። በዚያ ላይ በእንክብካቤ ነው ያደለብኳት»
«ጭራሽ ደልባ ነው እንዲህ የከሳችው?»
«አዎና! በርግጥ እኔ ስብእናዋ ላይ ነው የሰራሁት። በጥሩ ስነምግባር ነው ያሳደግኋት» አለኝ ቆፍጠን ብሎ። ሳቄን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ
«አንድ ሺ ብር ትሸጥልኛለ ...?» ብዬ ሳልጨርስ
«ውሰዳት!» አለኝ በደስታ ተሞልቶ።
ምነው ዝም ባልኩ ብዬ በይሉኝታ አንድ ሺ ብር ሰጥቼው በጓን ይዤ ልሄድ ስል መራመድ አቅቷት በቀስታ ስታዘግም
«ቃሬዛ ቢኖርኮ ደግ ነበር» አለኝ ሰውዬው በጉን በሃዘን እየሸኘ።
ተበሳጭቼ ዝም ብዬው ስሄድ
«ወንድሜ እንደው ለነፍስ ትሆንሃለች መጀመሪያ የህክምና እርዳታ አርግላት» አለኝ
መንገድ ላይ በጓን ያየ ሁሉ ከንፈሩን እየመጠጠ ያልፋል። አንዳንዱ እኔን እያየ አንገቱን በሃዘን ይነቀንቃል። በግ ላርድ ሳይሆን እንደአብርሃም ልጄን ልሰዋ ይዤ እየሄድኩ ነው ያስመሰሉት። ሽምቅቅ እንዳልኩ ቤት ደረስኩ። ሚስቴ በጓን እንዳየቻት
«ምንድነው ይዘህብኝ የመጣኸው?» ብላ ጮኸች። በጩኸቷ ከኔ ይልቅ የደነገጠችው በጓ ነች። አይኗን አስለምልማ መሬት ወደቀች! የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ላደርግላት ሞከርኩ። አልነቃ ስትለኝ በአፌ ትንፋሽ ልሰጣት ሳጎነብስ ሚስቴ
«በዚህ አፍህ እኔ ከንፈር ጋር ድርሽ እንደማትል እወቀው!» ስትለኝ ቀና ብዬ መጨረሻዋን ማየት ጀመርኩ ..
ውይይ! አረፈች! በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነው የገጠመኝ ጎበዝ።
ለሚስቴ «ያ ሙታን አስነሳለሁ ሚለው ነብይ ጋር ይዘናት እንሂድ ይሆን?» ስላት
«እሱ አክስቱ ሞታ ክፍለሐገር ሄዷል» አለችኝ። እሺ ምን ተሻለኝ ጓዶቼ?
«ቆይ ግን ...የግድ ስጋዋን ለመብላት እኛ ልንገድላት ይገባል እንዴ? ያው ሞት ሞት ነው። በቢላም ሞተች በድንጋጤ ያው መሞቷ አይቀርም!» ስል ሚስቴ ሶስት ግዜ አማትባ «በል አውጥተህ ጣል» አለች።
እኔ ግን ተስፋ አልቆረጥኩም! እቺን በግ እኮ ስጋዋን ፈልጌ ሳይሆን እንደበግ እንድትተውን ነው የገዛኋት። አክተር ደሞ አይሞትም
ኦህህህህህ! ተመስገን!
ነቅታለች ጎዶች «እልልልል ...» (አሉ እትዬ ዘርፌ የቤት እቃ (ማማሰያ ሳይቀር) እየሰረቀ ያሰለቻቸው ልጃቸው ሲታሰር)
እንዲህ ነው እንጂ በግ! ዝም ብሎ መሞት አለንዴ? እኛ ሳንፈቅድላትማ አትሞታትም! አልኩ ለሚስቴ (አንዳንዴኮ እንደ አፍሪካ መሪዎች ሚያደርገኝ ነገር አለ)
ሚስቴ መንቃቷን ስታይ «በል ቶሎ እረድልኝ» ብላ የአሉላ አባነጋን ሻሞላ የሚያህል ቢላ ይዛ መጣች።
«አሁን ለዚች በግ ይሄን የሚያህል ቢላ መጠቀም ተመጣጣኝ እርምጃ ነው ብለሽ ታስቢያለሽ?» አልኳት
«ወሬውን ተወውና ሳትሞት እረዳት» የሚል ቀጭን ትዛዝ ሰጠችኝ! ሻሞላውን ተቀብዬ ወደበጓ ስጠጋ አይኗን ከፈት አርጋ ቢላውን አየት አረገችና እንደሰው እንባዋ ባይኗ ሞልቶ ፀጥ አለችላችሁ! በቃ ሞተች!
ብቻ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው የገጠመን ወገን! ከሚስቴ ጋር ያደርኩትን አዳር አዳር አትበሉት። ለሊት ላይ ጠጋ ብዬ እያቀፍኩ
«አይዞን እኛ ጤና የሚቀጥለው ፋሲካ ምን የመሰለ ሙክት ነው ምናርደው» ስላት እንደአለቃ ገብርሃና ገፍትራ ከግድግዳ ጋር አጋጨችኝ!
ኤጭ አሁንስ መረረኝ! ጌታ ሆይ ትመጣለህ ወይስ እኔ ልምጣ?

@wegoch
@wegoch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5.pdf
3.2 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5

💰 ፓኬጅ ከገዙ በ 0.70 ብር ብቻ 💰
አንዳንድ ቀን
(ቡሩክ ካሳሁን)

እረፋዱ ላይ ኢንተርኔት ካፌ ገብቼ ፌስቡኬን ስፈሰቡክ ቆየውና ከፍዬ ተነስቼ ከወጣው፡፡ በኋላ ቅር ቀልቤን ስለቀፈፈኝ ተመልሼ ወደ ኢንተርኔት ካፌው ስገባ፤ ለካ አካውንቴን ሎግ አውት አላረኩትም ነበር፤ አንዱ ነውረኛ በእኔ አካውንት ገብቶ የመንግስት ባለስልጣናትና ሹማምንት ተሰብስበው የተነሱት ፎቶ ላይ ‹አስመሳይ ሌቦች› ብሎ ሊኮምት ሲል እጅ ከፊደል ያዝኩት፡፡ ከዛም በድንጋጤ
‹ኡኡኡኡ ብዬ ሳልጮህ በህግ አምላክ የጀመርከውን ነገር አቁም፤ በህግ፣ ለውጥ አደናቃፊ ነው ብዬ አሲዝሀለው› ስላልኩት ፈርቶ ለቀቀልኝ፤ እኔም ሎግ አውት እያረኩኝ ‹‹በራስህ አካውንት እንዲደረግ ማትፈልገውን በሰው አካውንት አታድርግ ነው፡፡› ሚለው መፅሃፈ ማርክ ዙከርበርግ ከመነሻው እስከ መድረሻው› ብዬ ገስጬው ወጣሁ፡፡ እስኪ አንድ ጊዜ የማርክ ወዳጅ አሜን ይበል እዚጋ!!! ፡-)
ከኢንተርኔት ካፌው ወጣሁና መንገድ እንደጀመርኩ ዝናብ ጀመረ፡፡ ተሯሩጬ አንድ ካፌ ገባሁ፡፡ ካፌው ውስጥ በጣም ብዙ ሰዎች ስለነበሩና የመቀመጫ እጥረት ስለነበረ አንድ ጠረቤዛ ላይ ለመጠቀም ሳይሆን ከበረከቱ ለመሳተፍ በሚመስል ሁኔታ በጣም ብዙ ሰዎች ተሰበሰብን፡፡ ሁሉም የየግሉን ይሰራል፤ ስማርት ፎን የያዙ ከስልካቸውጋ ሲያወሩ፤ ስማርት ፐርሰን የያዙ ደግሞ እርስ በእርስ ያወራሉ፡፡ ከሁለት ጓደኛሞች ጎን የነበረ አንድ ወጣት ስልኩን እየተጠቀመ ሁለቱ ጓደኛሞች እያወሩ በድንገት ተበሳጭቶ ስልኩን መጠቀም ያቆምና ‹ጀለሴ ወይ ዣንጥላ ይዤ ልቁም እንዴ አበሰበሺኝ እኮ፤ ካፊያ ፈርቼ ብገባ ዶፍ ለቀቅሺብኝ› አላቸው ሁለቱ ጓደኛሞች አፍጥጠው ‹ምነው?!› ብለው ጠየቁት
‹ስታወራ እኮ ሀምሌን ሆነክብኝ! እየተፋህብኝ ነው፡፡› መለሰላቸው ወደአንዱ እየተመለከተ
ጠብ ሊነሳ እንደሆነ ቀልቤ ስለነገረኝ ጠቡ ደግሞ ወደ ብሄር ግጭት ማደጉ ስለማይቀር “ዝናብ በስንት ጣዕሙ” ብዬ ካፌውን ጥዬ ወጣሁ፡፡ ዝናቡም አቁሟል፡፡ ወደ ሰፈር ለመመለስ ታክሲ ለመያዝ ስራመድ አንድ ሸምገል ያሉ ሰውዬ አየሁኝ፡፡ የ8ኛ ክፍል ሂሳብ መምህሬን አስታወሱኝ፤ የ8ኛ ክፍል መምህሬ አሁን አሁን ሳስባቸው በጣም ያስቁኛል፤ ያኔ ግን ያበሳጩኝ ነበር፡፡ ሰፈራችን ባለው በ“መማር ምን ሊበጀኝ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት” እኔ፣ ዱባለ እና ገጀረው አብረን ተምረናል፡፡ ከዱባለጋ አንድ ክፍል የሆንኩት ደግሞ (ዳዊት እንዳይመስልህ ወንድሜ 7ኛ ክፍልን ነው 3 ጊዜ ሀትሪክ የሰራው) ቢሆንም ከገጀራው ጋር ግን አንድ ክፍል የሆነው ዘግየት ብሎ ትምህርት ስለጀመረ ነው፡፡ ገጀራው የሰፈራችን ልጅ ባይሆን ኖሮ “መምህር ነው” ብለው ያስያዙንን ሁለት ልጆች እኔና ዱባለ ደፍረን አስይዘን ባልበላናቸው ነበር፡፡ ገጀራው እድሜው በጣም ትልቅ ነው፤ እኛ ብቻ ሳንሆን አስተማሪዎቹም ይፈሩታል፡፡ እኚ ሂሳብ መምህራችን እንኳን እኔን፣ ዱባለን እና መሰሎቻችንን ውሀ ቀጠነ ብለው ቤተ-እግዚሀር እንደ ገባ ውሻ ሲያንከለክሉን ሳሮንንና ገጀራውን ግን ያከብሯቸው ነበር፡፡(እዚጋ እንዳትሸወዱ ሳሮን የገጀራው እህት ወይም የስጋ ዝምድና ኖሯት አደለም ሂሳብ መምህራችን ሚያከብሯት፤ ይልቁንም የክፍላችን ቆንጆ ስለሆነችና አስተምረው ሲጨርሱ ከሷ ጎን ተቀምጠው ማውራት ስለሚወዱ ነው፡፡) ሂሳብ መምህራችን አንድ ጥያቄ ለተማሪው ይወረውሩና ተሸቀዳድመው እኔ ላይ ያፈጣሉ
‹አጅሬው እስኪ ተነስ! ይሄ ምንድን ነው?› ያፈጡባኛል መቼም ይጠይቁኛል አይባልም በዚ አኳኳን
እኔም ብድግ ብዬ ለመልሱ ሚቀራረብ መልስ ስሰጥ
‹ጨርሰዋ ደደብ!!!› ይሉኝና ወደ ዱባለ ዞር ብለው ‹ተነስ አንተኛው!› ይሉታል
ዱባለም ተነስቶ ፀጉሩን ያፍተለትላል
‹ተናገር እንጂ ምን ይለጉምሀል! አለምዘላለምህን ማትሻሻል 7ኛ ክፍልን ሀትሪክ ሰርተክ 8ኛ ደረስክ ይኸው እዚህም ቁጭ ብለህ ቂጥህን ከመደፍጠጥ የዘለለ ምንም አትሰራም፤ ቁጭበል ዶማ!› ይሉና ከዱባለ ኋላ ገጀራው አለ፤ ወደሱ ገና ማየት ሲጀምሩ.. ሳይጠይቁት ‹አላውቀውም!› ብሎ በልበ ሙሉነት ይመልስላቸዋል፡፡
‹ጎሽ! እንደዚ ነው ሚባለው፡፡ ካላወክ አላውቅም አትልም አንት ደደብ!!!› መልሰው ዱባለ ላይ ያፈጣሉ፡፡ ዱባለ አንገቱን ሰብሮ ፀጉሩን ያፍተለትላል፡፡ ‹እስኪ ሳሮን ሞክሪ› ብለው ወደሷ ይዞራሉ፡፡ (ለወትሮው እንደምታረገው በጣም የከበዳትን በአይኗ ስትነግራቸው እራሳቸው ይመልሳሉ፤ የቀለላትን ግን ተነስታ ትሞክራለች፡፡) ሳሮን በቄንጥ ተነሳችና እኔ የተናገሩኩትን ቃል በቃል ስትናገር (የኮፒ ራይት መብትኮ እዚ ሀገር አይሰራም ብዬክ ነበር አልኩት ለበድሉ ጠጋ ብዬ) ገና ሳትጨርሰው ከአፏ ተቀብለው እራሳቸው አሟሉትና ‹ጎበዝ ልጅ! እዚ ከድንጋይ ጋር ተቀምጠሸ ግንበኛ አስመሰሉሽ› ብለው እሷን ለማሞገስ እኛን ይሰድባሉ፡፡
አይ ሂሳብ መምህሬ ብዙ ታሪክ ሰርተዋል እኮ አልተፃፈላቸውም እንጂ፡፡ የታክሲ የመጨረሻውን ሰልፍ ለማግኘት ስራመድ ተባራሪ ታክሲ አግኝቼ ገባሁ፡፡ ሂሳብ ስሰጠው ለሰልፉ ጫፍ ስጓዝ አንድ ፌርማታ እንደመጣሁና ተጨማሪ ብር ከሀምሳ እንደሚያስከፈለኝ በታላቅ ማመነጫጨቅ ወያላው አበሰረኝ፡፡

@wegoch
@wegoch
ማንም ከኢትዮጵያዊነት ማማ ሊያወርደኝ አይችልም!
(ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)
ለእኔ ቋንቋዬ የሀሳብ መግለጫ፣ ባህሌ የአኗኗሬ መንገድ ብቻ ነው፡፡
እናቴ ጉራጌ ናት – ክስታኔ፡፡ አባቴና አባቱ ክስታንኛ አቀላጥፈው የሚናገሩትን ያህል ኦሮምኛም ይናገራሉ፡፡ በድሉ – ዋቅጅራ – ደበላ – ወልደጊዮርጊስ – ካሳ እያለ የሚዘልቀው የአባቴ ወገን መጠሪያ ሌሎችን የሚያስጨንቃቸውን፣ ግራ የሚያጋባቸውን ያህል እኔን
አስጨንቆኝ አያውቅም፤ ግራም አያጋባኝም፡፡ የማያስጨንቀኝ እነሱን ስለምጠየፍ አይደለም፡፡ የማያስጨንቀኝ በማኛቸውም ማንነት ማንነቴን መበየን፣ ስለማልፈልግ ነው፡፡
እናቴ ኬርአለም ክስታኔ ናት፤ አባቴና አያቴ የኦሮሞና የጉራጌ ድብልቅ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ወልደጊዮርጊስና ካሳ ትግሬ ወይም አማራ ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ፡፡ እኔ ውስጥ ያለው ግን ከነዚህ ሰዎች ጎሳ በላይ ነው፡፡ እኔ ውስጥ በደም ከዝርያዎቼ ከተቀበልኩት ይልቅ፣ ካደግኩበት የኦሮሞ ማህበረሰብ ከልጅነት እስከ ጉርምስና የቀሰምኩት ይበልጣል፡፡
በወጣትነቴ ባሌ ለሦስት አመታት፣ ጎንደርና ጎጃም ለአሥር አመታት ስኖር ማንነታቸውን አትመውብኛል፡፡ ባህር ተሻግሬም አውሮፓ ላይ ያን ያህል ኖሬያለሁ፡፡ ታዲያ እንዴት ነው የእኔን ማንነት በእናትና አባቴ ጎሳ (ምንም ይሁን ምን) የሚገለጸው?
አዎ የክስታኝና ቋንቋን አፌን ፈትቼበታለሁ፤ እርግጥ ነው በጉራጌና በኦሮሞ ባህል ከልደት እስከ ጉርምስና ጥሪት ቋጥሬበታለሁ፤ አንድም ቀን ግን እራሴን ጉራጌ ወይም ኦሮሞ ብዬው አላውቅም፡፡
ላለፉት ሃያ አምስት አመታት ማንነትን በጎሳ የመበየን ፖለቲካ ተንሰራፍቶ እንኳን ጎሳዬን የማንነቴ መበየኛ አድርጌው፣ ወይን ሆኖ ተሰምቶኝ አላውቅም፡፡ ለዚህ ነው ጉራጌ ወይም ኦሮሞ መሆን አለመሆኔ የማያስጨንቀኝ፡፡
እኔ ከዚያ የበለጠ ሳልሸራረፍ የሚገልጠኝ ማንነት አለኝ –
# ኢትዮጵያዊነት

@wegoch
@wegoch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/28 09:32:55
Back to Top
HTML Embed Code: