Telegram Web Link
"መሄድ መምጣቱን ዕብደት በሚመስል መልኩ በጣም ዕወደው ነበር" ትለኛለች ግርምቴ በጣም እንዳደምጣት አድርጎኛል። ዓይኔን ከአይኖቿ መንቀል አልፈልግም።እንድታወራኝ ፣ እንዳላቋርጣት ፣ እያዳመጥኩሽ ነው ፣ታሪክሽን ወድጄዋለሁ እያልኳት እንደሆነ እንዲገባት። "ታውቂያለሽ ይሄ የተለየ ባህሪዬ ሳይሆን አይቀርም። ማንም ሰው እንዲህ እያለ ሲያወራ ሰምቼው አላውቅም። ለነገሩ እኔ ብዙ ሰው አልቀርብም። ሁሌ አብሮኝ ሲሆን ይሰለቸኛል። ደሞ ትንሽ ራቅ ሲለኝ እጅጉን ይናፍቀኛል። ድፍን ሰባት ዓመታትን በዚህ ሁኔታ አሳልፈናል። ሁለት ዓመት ለትምህርት ማሌዢያ ቆይቼ ስመጣ ፡ ቤቱ ምንም አልተቀየረም። ሁሉም ዕቃዎች እንዳሉ ናቸው። ቦታቸው እንኳን አልተለዋወጠም። እንዴት ሴት አትመጣም እዚህ ቤት? እላለሁ በውስጤ።አውቃለኋ ፡ ሴት የሚያመጣ ቢሆን የቤቱን ጠረን መለየት እችላለሁ።" "ስሚኝማ እኔኮ ለሁለት ዓመታት ከሱ ተለይቼ ትምህርት ላይ በነበርኩ ጊዜ ከአንድም ሁለት ወንድ አውቃለሁ። በእርግጥ ኢትዮጵያ እያለሁ ቢሄድም ቢመጣም ምንም ነገር መሀል ላይ አይገባም ። ማንም ወንድ እንዲገባ ዕድል ሰጥቼው አላውቅም። አንዳንዴ...እኔ ከዚህ ልጅ የምፈልገው ምንድነው? ስል ራሴን እጠይቃለሁ። ምላሼ ምን እንደሆነ ተረድቼው ግን ኣላውቅም። ተጋብተን ልጆች እንድንወልድ እንስማማና ድንገት የሚሰለቸኝ ነገር ይኖራል። የሚገርምሽ
...ኣንዳንዴ ዕብደት መሳይ ስሜት ይሰማኛል። እንዲሄድ እመኛለሁ ፡እንዲናፍቀኝ ፣ ሌላ ሴት ይዞ እንድቀና እመኛለሁ። እሱ ግን በጭራሽ አያደርገውም ነበር! " "ከ 3 ዓመት በፊት ምን ሆነ መሰለሽ? ቤት አሟላን ፡ ልንጋባ ፣ ልጆች ልንወልድ ፣ ቤተሰብ ልንመሰርት ሃሃሃ(ረጅም ሳቅ) ከዛ ብድግ ብዬ ስልክ አለማንሳት ፡ እሱን አለማግኘት ምናምን ሆነ ስራዬ ለ 4 ወራት ያህል። አልገርምም? ከዛ በ 4ኛ ወሬ ቀጥ ብዬ አንድ ሰኞ ቀን ማታ ቤቱ ሄድኩኝ። ቁልፍ ስላለኝ ቤት ባይኖርም ከፍቼ ገብቼ ጠብቀዋለሁ ብዬ።ስገባ አልጋ ላይ ጋደም ብሎ መፅሀፍ እያነበበ አገኘሁት። በምን ፍጥነት እንደሆነ አላውቅም ብድግ ብሎ ስንተቃቀፍ። ለረጅም ሰዓት ተቃቅፈን ቆየን፡ አልተቀመጥንም ተያይዘን ወጣን ፡ ራት በላን ፡ ከተማዋን ስናካልላት ሊነጋ ሲል ቤታችን ገብተን ተኛን። እንደዚህ ያሉ ሰዎች ገጥመውሽ ያውቃሉ?" አለችኝና ዓይኔን ተመለከተች። ጭንቅላቴን ብቻ በማወዛወዝ ገጥመውኝ እንደማያውቁ መለስኩላት። በቃላት ቢሆን ምላሼ፡ እንደማቋርጣት ስለተሰማኝ ቃል ማውጣት አልፈለኩም። "እኛ ብቻ የሆን ይመስለኛል የምር። እና እንደዛ ሆነን አድረን በማግስቱ ስራ ቀርተን ቤት ዋልን። ከዛ ለ 3ሳምንታት በጥሩ መዋደድ ከቆየን በኋላ ነበር ሁለተኛ ዲግሪዬን ልሰራ ከሀገር የወጣሁት። ስመለስ ሁሉም ነገር በቦታው ነበር። እዛ እያለሁም በየመሀሉ እንደዋወል ነበር፡ በፅሁፍ መልዕክቶች እናወራ ነበር ምናምን። ትምህርቴን ጨርሼ ከመጣሁ 6 ወራት ገደማ ሆኖኛል። በቀደም ቅዳሜ ዕለት እንደልማዴ ከ 2 ወራት ምናምን የመኮራረፍ ስሜት በኋላ፡እቤቱ ስሄድ ገና ከመግቢያው ጀምሮ አዲስ ነገር አየሁ። በሩ ላይ የእግር መርግጫ ወይም የቆሻሻ ጫማ መጥረጊያ የሚመስል ትንሽዬ ምንጣፍ ነገር ተነጥፏል። አለወትሮው የቤቱ ጠረን ሰው ሰው ይሸታል። ማለቴ እም . . . ብቻ ሰው ያለበት ቤት ይመስላል። አለ አይደል ህይወት ያለው ፣ደስ የሚል ምግብ የሚበስልበት ፣ቡና የሚፈላበት ቤት፣ ጧት ላይ ቆንጆ ቁርስ የሚበላበት፣ እራት ሰዓት በሚያማምሩ ዕቃዎች የተሞላ የምግብ ጠረጴዛ ያለው የሚመስል፡ ሳቅ የሚደምቅበት ፡ክረምት የሚሞቅበት ፣ማታ የምትናፍቂው ዓይነት ጠረን ያለው ቤት መሰለኝ። ልግባ ልመለስ በሚል ማመንታት ውስጥ ሆኜ ፡ ይሄ ቤትማ የሚኩ አይሆንም አልኩ ለአፌ። ልቤ ግን የሆነ ያወቀው ነገር አለ። ልቤን ማመን አልፈለኩም። በር ላይ እንደቆምኩ ሰው ቢያየኝ ምን ይለኛል ብዬ ደንገጥ አልኩና ፡ እግሬ የሆነ ሸክም እየመሰለኝ ዓይነት ነገር ጎ~ተ~ት አድርጌው ተጉዤ በሩን እንደማንኳኳት አደረኩኝ። የምታምር ፣ ከቆንጆ፣ ዘናጭ ከሆነች ሴት፣ የምትወደድ ዓይነት ፣በስራ ቦታ ፣በቤተሰቦቿ ፣ በጓደኞቿ የምትከበር ፣ታድለሽ ምናምን የምትባል
ዓይነት ሴት ድምፅ "ማነው?" ስትል ተሰማኝ። ያን የመሰለ ድምፅ አልጠላሁትም መሰለሽ? ቀጥ ብዬ ገባሁ ቤቱ ተለውጧል። ቀና ስል ግድግዳው ላይ ሚኪን የሚመስል ወንድ ፊት ለፊት ከቆመችው ሴት ጋር በትልቁ ፎቶግራፋቸው አለ። እንግዳ እንዳልሆንኩባት ታስታውቃለች። ፊቷ ጠይም ፡ ሞላ ያለ፡ ዓይኖቿ የሚያምሩ ፡ ሙሉ ፈገግታ የሚታይባት ሴት ነች። ምን ያስቃታል? አልኩኝ በልቤ። የሚኪ የወንድሙ ሚስት መሆን አለባት። አይገርምም ሚኪ እሱን የሚመስል ወንድም አለው ማለት ነው? ቤቱን የቀየረው ብቻዬን ከሆንኩ ይሄ ትልቅ ቤት
ምን ያደርግልኛል እናንተ ኑሩበት ብሏቸው ሰጥቷቸው ሌላ አነሰ ያለ ቤት ተከራይቶ ነው ማለት ነው? እያልኩ ሳስብ "ፀጊ ደህና ነሽ"? አለችኝ በማርያም ምን ሆኜ እንደደነገጥኩ አትጠይቂኝ.." ሚኪ ቤት የለም ለስራ ወደ ክፍለሀገር ወጥቷል።ትላንት ነው የሄደው" አለችኝ።
አፌ የሆነ ነገር ለመናገር ተከፍቶ አንደበቴ ግን ተይዞ እንደነበር አስታውሳለሁ። አዎ አፌን ከፍቼ ነበር። ከትንሽ ዝምታ በኋላ ደፍሬ ጠየኳት። ከ 2 ኣመት በፊት ይሰራበት የነበረ መስሪያ ቤት ውስጥ ፡የስራ ባልደረባው የነበረች ሴት እንደሆነች ፡እኔን በዝና እና በፎቶዬ በጣም ታውቀኝ እንደነበር ዓይነት ነገር ፡ከሚኩ ጋር የፍቅር ግንኙነት በጀመሩ በ3ኛው ሳምንት ምክር ቤት ተፈራርመው ጋብቻ እንደመሰረቱ ፣አሁን የ 1 ወር ከ15 ቀን ነብሰ ጡር እንደሆነች ነገረችኝ"
። ከዛ በዝምታ ለብዙ ደቂቃ እንደተቀመጥኩ የገባኝ በማግስቱ ጧት ላይ ነበር። በምን ዓይነት ሀኔታ ውስጥ ፣ እንዴት ባለ ስሜት እና በምን ትራንስፖርት
እንደሄድኩ እንኳን ሳላውቅ ራሴን ጧት አልጋ ላይ አግኝቼዋለሁ። ከፍቶኝ ይሁን ፣
ባዶነት ስሜት ተሰምቶኝ ፣ፀፅቶኝ ፣ቁጭት ውስጤ ገብቶ በውል እንኳን
አላውቀውም ምን እንደዛ እንዳደረገኝ።
ቀሽም ሴት ነኝ አይደል? ዕቅድ ፣ተስፋ የሌለኝ ፣ህይወት ትርጉሟ የተዛባችብኝ? አለችኝና እጇ ላይ የነበረውን በብርጭቆ የተቀዳውን አልኮል መጠጥ በአንድ ትንፋሽ ጨርሳ ብርጭቆውን እንደያዘችው ቀና አለች። ዓይኖቻችን ሲገጣጠሙ እያዳመጥኳት እንደሆነ ስታውቅ "እና ሚኩ ጥፋተኛ
ነው? እሺ እኔስ አፍ አለኝ? ለምን ብዬ የመጠየቅ? ቤት ውስጥ ያለችውስ ሚስቱ ምን ጥፋት አለባት? ቆይ እንዳገባ ሲያውቅ ለምን ቤቱን አልቀየረም? ይሄንን ሁሉ ጊዜ አብረን ስንሆን በመሀከላችን ሁለታችንንም የሚያውቅ ሰው የለም ማለት ነው? እንዴት አልሰማሁም ማግባቱን?" እያለች ራሷንም እኔንም ትጠይቃለች። አጎነበስኩ ግራ ገብቶኝ ፡ የምላት ፣የምመልስላት ፡መልስ ማገኝ ይመስል ወደ መሬት ዝቅ ብዬ አያለሁ። እንደዚህ ሆና አላውቃትም። ለነገሮች ሁሉ ቸልተኛ እንደሆነች ነበር የማውቀው። የሚሆነው ይሆናል ካልሆነም ይቀራል የምትል ዓይነት ሴት። ከስራ ስወጣ እንደምትፈልገኝ ነግራኝ ነበር የተገናኘነው። ፀፀት ያንገበገበው ስሜት ዓይኗ ውስጥ አይባታለሁ። አይዞሽ ፣በርቺ ፣ጠንከር በይ ፡ያልፋል ፡ ሁሉም ሰው የሚያጋጥመው ነው ምናምን የሚባሉት ማፅናኛዎች ይጠቅሟታል? ያስፈልጋታል? ቦታቸው ናቸው? ራሷን እየቀጣች እንደሆነ ይሰማኛል ምን ግዜ የታክሲ ደንበኛዋን እንደጠራች አላየኋትም ብድግ ብላ በአግባቡ ሳትሰናበተኝ እያየኋት ሄዳ ገባች...ሌላ መተላለፍ!

@getem
@getem
@paappii

#Tersid kebede
#እንድቅትዮን
ዕንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው በገነት መናፈሻ
#ማክሰኞ ሚያዚያ 29 2011ዓ.ም.
አመሻሹ 11:30
መግቢያ ዋጋ 50 ብር

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ስራ እና የስራ ልምድ
(ቡሩክ ካሳሁን)

በሀገራችን እየተበራከተ ለመጣው የስራ አጥ ቁጥር ማሻቀብ ምንም እንኳን ብዙ ምክንያት ቢኖሩትም ለእኔ ግን በዋናነት የሚታየኝ ስራ በሌለባት ሀገር ውስጥ የስራ ልምድ ማፈላለጉ ይመስለኛል፡፡ አስቡት እስኪ ስራ በሌለባት ሀገር “የስራ ልምድ” እየጠየቁ “ስራ” መከልከል፤ የማያልቅ አዙሪት ውስጥ መግባት ነው፡፡ “ስራ የሌለኝ የስራ ልምድ ስለሌለኝ ነው፡፡ የስራ ልምድ የሌለኝ ስራ ስለሌለኝ ነው፡፡” የሚል አዙሪት ውስጥ መዘፈቅ፡፡ አንድ ግዜ ጓደኛዬ ዱባለ በ“የስራ ልምድ” እና በ“ስራ” ጠኔ ሲመታ ከዚህ ችግር ለማምለጥ የተጠቀመው ስራ አገኝበታለው ብሎ ባሰበው ሙያ ሀሰተኛ “የትምህርት ማስረጃ” እና “የስራ ልምድ” በማጋጀት ወደ ሰርቶ አደር ማህበረሰብ ራሱን መቀላቀል ነበር፡፡ ያም ቢሆን ቀላል አልሆነለትም፡፡ የውበት ባለሙያ እንደሆነና በዛም ልምድ እዳለው አድርጎ ያዘጋጀው ዱባለ ከተማችን ላይ አለ የተባለ የውበት ሳሎን ሊቀጠር ተወዳደረ፡፡ ልምዱና ማስረጃዎቹ ጥሩ ተደርገው ስለተሰሩ በቀዳሚነት ከተወዳዳሪዎቹ ተመርጦ ለተግባር ፈተና ተቀጠረ፡፡ ይህን ጊዜ ታዲያ ዱባለ ‹‹ለካ አዳሜ እንደዚ ነው ስራ የያዘው፡፡ ስራ የማይዙት ልምድ የሌላቸው ሳይሆኑ የዋሆች ናቸው፡፡›› አለ፡፡
በዱባለ እድል ጠማማነት ብተማመንም እንደዚ ይከፋበታል ብዬ ግን አስቤ አላውቅም፡፡ የተወዳደረበት የስራ መደብ የፌሻል (የፊት ውበት) ስራ ረዳት ባለሙያ ለመሆን ነበር፡፡ ነገር ግን የስራ እድሜው ከተግባር ፈተና አልዘለለም፡፡ ለፈተና በሄደ ሰዓት የተከሰተውን እንደሚከተለው አድርጎ አጫወተኝ…
‹‹ ሚገርም እኮ ነው! እኔ ሴቶች ይመጣሉ ብዬ ለዛውም ሀብታሞች ፊታቸው የጠራ፣ የበራ እንዲሁ የውበት ሳሎን ለመግባት እንጂ መሰራት ማያስፈልጋቸው ቆነጃጅት ስጠብቅ ወዳጄ የመጣው መንግስቱ ሀ/ማርያምን የመሰለ ሰውዬ፡፡ በመጀመሪያ ‹ይቅርታ ብርጭቆ ወረቀት ጨርሰናል› ብዬ አግባብቼ ልመልሰው ሞክሬ ነበር፡፡ ጭራሽ ፊቱን አኮሳትሮ የስራዬን ክብደት በአጭሩ አስረዳኝ፡፡ ዋናዋ የፌሻል ስራ ባለሙያዋ መጣችና ሰውየውን ፊቱን ለመስራት የሚደረገውን ቅድመ ዝግጅት እንዳደርግለትና የቆዳውን አይነት (ስኪን ታይፕ) ለይቼ እንድጠብቃት ነግራኝ ሄደች፡፡ ወንበር ላይ አስቀምጬ ፎጣ ካለበስኩት በኋላ ትኩር ብዬ የፊቱን ቆዳ እሷ እስክትመጣ ድረስ ስመለከት ቆየሁ፡፡ ጓንት አድርጋ ስትመጣ እሷም እንደ እኔ የሰውየው ፊት ከብዷት (ቀፏት ከማለት ይሻላል) ጓንት አድርጋ የመጣች መስሎኝ ነበር ለካ ደንብ ነው፡፡ ካጠገቤ ቆማ ቅባቶችን እያወጣች
‹የቆዳውን አይነት ለየኸው?› ብላ ጠየቀችኝ
‹አዎ ለይቼዋለው የሰው ቆዳ አይነት ነው›› መለስኩላት
ሰውየው አፈጠጠብኝ!
‹ምን?!› ብላ መልሳ ጠየቀችኝ፡፡ ባታምነኝ ነው ብዬ ‹አገላብጠሸ እዪው ሲታይ አይመስልም እንጂ የሰው ቆዳ ነው፡፡ ምን አስዋሸኝ ዘመዴ አይደል› አልኳት፡፡
‹ቀስ ብለህ ጋውኑን አውልቅና ከዚህ ውጣ!› አለችኝ አይኗን እያጉረጠረጠች
‹እና አንቺን ለማስደሰት የአዞ ቆዳ ነው ልበልሽ? ገፈሽ አትሸጪው ምን ያረግልሻል አይነቱ? አርፈሽ ሚሰራውን ሰርተሽ ብርሽን አትቀበዪም?›
‹ጥበቃ ሳልጠራ ውጣ!› አንባረቀችብኝ፡፡ እኔም በኋላ ፖሊስጋ ወስዳኝ ከነማስረጃዬ መቀመቅ እንዳልወርድ ላጥ ላጥ ብዬ ወጣሁአ ››
.
.
.
@wegoch
@wegoch
@burukassahunC
ኢትዮጵያ እግር ኳስ¿¡ ወይስ ኳስ ራስ?!
(ቡሩክ ካሳሁን)

ከማልወዳቸውም ከማልጠላቸውም ነገሮች አንዱ እግር ኳስ ነው፡፡ እኔ በህይወቴ በእግር ኳስ ያለ አንድ ቀን ተበሳጭቼም ይሁን አዝኜ አላውቅም፡፡ አንድ ጊዜ ትዝ ይለኛል ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ አልፋ ከማን ጋር ተጋጥማ ይሁን አላውቀውም (ሳስበው ግን ከማድሪድጋ ይመስለኛል) ተጠበጠበች አልኳቹ ተጠበጠበች! (ሀገራችንን ሲጠበጥቡ ኸረ መላ በሉ እያልኳቹ ሰሚ አጥቼ ይኸው ዳኛዎቻችን መጠብጠብ ጀመሩ)፡፡ እና ያው የሀገር ጉዳይ ነበር ጨጓራዬ ሲነድ አደረ ሲነድ፡፡ ( እኔኮ መሸነፉን ይሸነፉ ግዴለም፤ ሰው 50 ብር ሊያሲዝ ይችላል ብለው ገምተው ቢጫወቱ ምናለበት፡፡ ይኸው እስከዛሬ በዛች 50 ብር ምክንያት ጨጓራዬ ይነዳል፤ ደግሞኮ ከእስፖርት ፌዴሬሽንጋ ነበር ያስያዝኩት።)
እግር ኳስን አጥብቄ ባልወድም የሚወዱ ሰዎችን መብት አልጋፋም፡፡(አንዳንዶች ግን ኳስ ከመውደድም አልፈው የሚወልዱ ሁላ ይመስላቸዋል፡፡) ነገር ግን አንድ ሰው ኳስን እንደ ኳስ እንጂ ኳስ ራስ ሆኖ ሲደግፍም ሆነ ሲጫወት ማየት አልወድም፡፡ (አልወድማ ደስ አይለኝም፡፡) እነዚ ኳስ ራሶች ተጫዋች ከሆኑ ልክ ሲናደዱ በዳኛውና በኳሱ መካከል ያለው ልዩነት ይጠፋባቸውና በቃ ዳኛውን እያጣጠፉ ወደ ጎል ይለጉታል፡፡ እዚጋ ግን ዳኛዎቹ ብዙ ጊዜ ያስቸግራሉ፤ ሚሮጡት ነገር አለ፡፡ ምን አለበት እስኪ ኳስ ሆነው ሃላፊነታቸውን ቢወጡ፡፡ ደግሞ አንዳንዱ ተጫዋች ህግ አያከብርም ወስዶ ዳኛውን በቦክስ፣ በጡጫ ያጣድፈዋል ይሄ እኮ ‹ማኖ› እኮ ነው፡፡ ፋራ ነው እንዴ፡፡ ልክ ግን እንደዚ ‹ማኖ› ሲነካ ያው ፌደራሎች እንደዳኛ ያገለግላሉ (ኢትዮጵያም አይደል ያለነው) እየሮጠ አንዱ ፌደራል ይመጣና ዳኛውን በቦክስ ሚነድሉትን ገለል ካደረገ በኋላ ለተቃራኒ ቡድን ቅጣት ምት እንዲመቱ ዳኛውን አመቻችቶላቸው ይሄዳላ፡፡ ዘጠና ደቂቃዋ እስክታልቅ የበረታ ዳኛ እየሮጠም እየተጎተተም ተጫዋቾቹን የማዳከም ስልት ይጠቀማል፡፡ (እዚጋ ደግሞ ለእድለ ቢስ ዳኛ በደከመ ተጫዋች ሌላ ተቀያሪ ገብቶ ያበጥረዋል፤ በጣም እድለቢስ ሲሆን ደግሞ ተቀያሪ ተጫዋች ባይኖር እንኳን የቡድን መሪው ገብቶ ያገላብጠዋል፡፡) እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የጎድን አጥንት ያለው ዳኛ ማግኘት ከባድ ነው፡፡
ደጋፊ ደግሞ ኳስ ራስ ሲሆን የሚከተሉት ምልክቶች ይታይበታል፡፡ ሚደግፈው ቡድን ሲያሸንፍ፤ ተንደርድሮ ድራፍት ቤት ይገባና ሂሳብ በኔ ነው ይላል እዛኮ ልጁ ሂሳብ ደብተር ጨርሶ ግዛልኝ ካለው ወር አልፎታል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ጥግብ ብሎ ይሰክርና አስፋልት መንገድ ዘግቶ አንቡላንስ አሳልፈኝ ሲለው ቀስ በል እስኪ ወተት ጥደሀል ይለዋል (እንደነዚ አይነቶቹ ላይ ፌደራሎቻችን የፈላ ወተት ቢደፉባቸው የወተት መግዣ ቦንድ እገዛለው)፡፡ የኳስ እራሶች ችግር ግን ጎለቶ ሚወጣው የተሸነፉ እለት ነው፡፡ ከሜዳ ውስጥ ይጀምራሉ፡፡ ገና ጨዋታው እየተኪያሄደ እንደሚሸነፉ ቆሌያቸው ሲነግራቸው ‹ዋ.ዋ.ዋ…› ይሉታል ዳኛውን በህብረት፡፡ ያን ጊዜ ዳኛው ስልክ ደውሎ ቤተሰብ ይሰናበታል፤ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አልጋ ያሲዝና ብሞት እንኳን የጀግና ሞት ልሙት ብሎ ጨዋታውን ያስጨርሳል፡፡ መጨረሻ ላይ እነዚ ኳስ ራሶች በመጀመሪያ ዳኛውን ከተጫዋቾች የተረፈ የጎድን አጥንት ካለው ጎኑን እየዳበሱ አረጋግጠው እየረገጡ ይሰብሩለታል (ደግነቱ ሳያረጋግጡ አይረግጡም :-) ) ከዛ በወንበር ከባላጋራቸው ደጋፊጋ ይከሳከሳሉ፡፡ በቸርነቱና በምህረቱ ተርፎ ወደቤቱ የተመለሰ ደጋፊ ደግሞ ‹ነገ ስራ ገቢ ስለሆንኩ ስትራፖ እንዳይዘኝ› ብሎ ሚስቱን የዳኛውን ጽዋ ያቃምሳታል፡፡ ታዲያ እኔ እንዴት አርጌ ኳስ ራሶችን ልውደድ!?፡፡ (እነዚ ኳስ ራሶች ግን ተጫዋችም ሆነ ደጋፊ caseአቸው ይሄ በጫማ ጥፊ ሰይጣን በሚያወጣው ፓስተር ቢታይ ሚበጅ ይመስለኛል። እሾህን በእሾህ ነው ዘመዴ።)
ለዳኞች ለወደፊት ምክር
የትኛውንም አይነት የኢትዮጰያ ጨዋታ ከማጫወታቹ በፊት ‹ለህይወቴ ያሰጋኛል› ብላቹ ፖሊስ ጣቢያ አመልክቱ፡፡ ከፌደራል ፖሊሶች የመስታወት ጋሻ ብትዋሱ 30 ፐርሰንት የመትረፍ እድላችሁን ታሰፋላቹ፡፡ በተለይ ስማቸው ላይ ‹ወ› ያለበት ቡድን ስታጫውቱ ከመወሰናቹ በፊት የቡድን መሪውን አማክሩ (ማምሺያም እድሜ ነው)፡፡ ደግሞ ፀብ ሲነሳ ስትሮጡ ለፍጥነት እንዲረዳቹ ታኬታችሁን አውልቃቹ በእጃቹ ይዛቹ ፈትለክ በሉ (ከፊት ሚመጣም ካለ በታኬታው ድው)፡፡ከዚ ሁላ ጥረት በኋላ ግን ከነዚ ኳስ ራስ እጆች ላይ ከወደቃቹ አጉል ቦታ እንዳይመቷቹ ጥቅልል ብላቹ በፊታቹ ተኙ፡፡ በቃ ምንም ማድረግ አይቻልም ኢትዮጵያም አይደል ያለነው!?!!።

ሚያዚያ 2010 ዓ.ም

ቡሩክ ካሳሁን ቴሌግራም ቻናል @burukassahunC

@wegoch
@wegoch
‹‹ግን.... ባይሆንስ?››
----------------------------------------------

ቴድ ቶክ ማየት በጣም ደስ ይለኝ የለ? ከምሳ ሰአቴ ቀንሼ ነው የማየው…አፌን በምግብ፣ አእምሮዬን ደግሞ በጥሩ የቴድ ቶክ ተናጋሪዎች ታሪክ ስሞላ ፍስሃ
ይሰመኛል፡፡ በሁለት በኩል መመገብ ነዋ ዛሬ ያየሁት የዳያንን ነው፡፡ ዳያን ቮን ፈርነስተንበርግ (ስሟ መርዘሙ፣ ደግሞ
ማስቸገሩ).. ዳያን እጅግ ስመጥር የፋሽን ዲዛይነር ናት፡፡ አለም ላይ አሉ
ከሚባሉት አንዷ፡፡ ዳያን ንግግሯ መጀመሪያ አካባቢ ናዚ ጀርመን አይሁዶችን እያደነ በሚገድልበት
ጊዜ ወጣት ስለነበረችው አይሁዳዊ እናቷ ታወጋናለች፡፡ እንደሌሎቹ አይሁዳዊያን በጀርመኖች ለሞት የታጨችው እናቷ መልካም ነገር ገጥሟት ጀርመንኛ ትንሽ ትንሽ የምትናገር ጠና ያለች ሴት መዋወቋ ሕይወቷን ሊያርፍላት እንደሚችል ተስፋ አደረገችና ተጣበቀችባት፡፡ ከእሷ አልለይ አለች፡፡ በሄደችበት ሁሉ ትከተላት ጀመር፡፡ በመጨረሻም ለማይቀረው ፍርድ እስረኞቹ ሁሉ ተሰበሰቡና አንድ የጀርመን ወታደር በተራ እየተቀበለ ‹‹አንቺ በግራ፣ አንቺ በቀኝ›› እያለ እንዲሰለፉ ሲደረግ፣ ተስፋ ያደረገችባት ሴት ‹‹አንቺ በቀኝ ተሰለፊ›› ተባለች፡፡ ያቺ ጀመርንኛ ታተርፈኛለች ብላ ያመነችው የዳያን እናትም የወታደሩን ትእዛዝ ሳትጠብቅ ከሴቲቱ ላለመለየት ቶሎ ብላ በቀኝ ተሰለፈች፡፡ ወታደሩ ምንም አላላትም፡፡ ተዋት፡፡ ምን ያደርጋል! እስካሁን ድረስ ብዙ እስረኛ በተባለው መስመር ሲሰለፍና ይሄ ሁሉ ሲከናወን ከፍ ባለ ቦታ ላይ ቁጭ ብሎ በዝምታ
የሚቃኘው የወታደሮቹ ሃላፊ ግን ወዲያውኑ የዳያን እናት ጋር መጥቶ በያዘው ጅራፍ ገረፋትና በግራ በኩል እንድትሰለፍ ገፈተራት፡፡ እያንገሸገሻት በስተግራ ተሰለፈች፣ ውስጧ በከፍተኛ ጥላቻ ተሞልቶ ቀና ብላ አየችው፡፡ ‹‹ለምን እንዲህ ያደርጋል? ቢተወኝ ምናለ….?››ብላ እጅግ ተማርራ ቀና ብላ አየችው፡፡ እስከዚያች ቅፅበት በብዙ ስቃይ ብታልፍም ከፈለገችው ሰልፍ አውጥቶ ወደፈራችው ሰልፍ የገፈተራትን ሰው ግን ከማንም በላይ አጥብቃ ጠልታው ቀና ብላ አየችው፡፡
ከዚያ የሆነው ግን ይሄ ነው፡፡ እንዲህ እስክትንገሸገሽ የጠላችው ሰው ነው
ሕይወቷን ያተረፈው፡፡ ለምን? በቀኝ በኩል የተሰለፉት ሰዎች በጋዝ ታፍነው ሊገደሉ የተመረጡና በኋላም ያለቁ ነበሩ፡፡ ዳያን ይሄን ታሪክ ለምን ነገረችን? አልፍ አልፎ ሁላችንም እንደ ዳያን እናት ባይከፋም የመረጥነው መንገድ ስለተዘጋብን ዓለም ክንብል ብላ የተደፋችብን፣ እጅግ ከባድ ነገር የደረሰብን ይመስለናል፡፡…ግን ባይሆንስ? ተገፍትረን የያዝነው መንገድ መርጠነው ካጣነው መንገድ የተሻለ ቢሆንስ?

@wegoch
@wegoch
@paappii


#hiwot emishaw
ስብሰባው
=======+++++=====
አንዱ አብዮታዊ ፈጣሪን ከሰይጣን ጋር ሊያስታርቅ እቅድ አዘጋጅርና ሽማግሌዎችን መርጦ ውይይት እያደረገ ነው። (መግለጫ መስጠቱ ነው)

ሰብሳቢው:- የስብሰባው አጀንዳ ሰይጣንን ከፈጣሪ ጋር እንዴት ማስታረቅ አለበን የሚል ነው። እንደምታውቁት የሰይጣንን ቦታ መላእኩ ከተረከበ በሁዋላ ሰይጣን እንቅልፉን አልተኛም። እንደምታዩት እርስ በእርሳችን ጠብ ጭቅጭቅ ንትርክ ሁኗል ተግባራችን። ስለዚህ እሄን ነገር ሰላም ለማድረግ ሰይጣን ከፈጣሪ ጋር መታረቅ አለበት። በዚህ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ እንድትሰጡበት እንፈልጋለን '' ሲል ስልኩን መነካካት ጀመረ
*
ሽማግሌ ተመረጠ (ሉካን ቡዱን መሆኑ ነው)
****
ሰይጣን እንቅልፉን ተኝቶ አገኙት
***
ሠው:- ሰይጣን የተመቸህ ትመስላለህ ?
ሰይጣን:- እድሜ ለናንተ ሰላሜን ሰጣችሁኛል ዛሬ ምን እግር ጣላችሁ?
ሠው:- ፈቃድህ ከሆነ አንተን ከእግዚአብሄር ጋር ለማስታረቅ አስበን ነበር
ሰይጣን:- አይሆንም! አትልፉ! ከናንተ ጋር የታረቅኩት ይበቃል። እሱ እኮ ካንዴ ሁለት ጊዜ ከስልጣኔ አስለቅቆኛል። እንደምታዩኝ እንቅልፋም አድርጎኛል። ስሜን ስልጣኔን እና ማንነቴን ቀይሮ አንኮታኩቶኛል። እና እንዴት እታረቀዋለሁ?
ሰው:- ደግሞ ከየትኛው ስራህ ነው ያስለቀቀህ ?ለሚካኤል ከሰጠው ውጭ
ሰይጣን:-አዎ! ለዘመናት ብቻየን ስፈነጥዝበት የነበረውን ዝሙትና ተንኮል ንትርክና ጭቅጭቅ ውሸትንና ክህደት አብዝቶ ለሚሰራው ሰው ለተባለው ፍጡር አሳልፎ ሰጠብኝ። ሰዎች በኔ ስም እየተጠሩ እርስ በእርሳቸው ይናከሳሉ። እኔ ለመስራት የሚከብደኝን ሀጢያት እናንተ እንደጽድቅ ትቆጥሩታላችሁ። እኔ እስካሁን ሰው አልገደልኩም። እናንተ ግን ሰውን አርዳችሁ ትበሉ ጀመር: እኔ እስካሁን ከሴት ጋር አልተኛሁም ለናንተ ግን ዝሙት ስራችሁ ነው ሰዎች ሰይጣን አሳሳተኝ ትሉኛላችሁ እኔ ግን እንኳን ላሳስታቸው በስራችሁ ታስቀኑኛላችሁ:: እግዚያብሔር እኔን የሚያሸንፈኝ በቃሉ ነው: ሀይሉ ያንበረክከኛል: እኔ የእግዚብሄርን ወንበር የደፈርኩት በወቅቱ ከኔ በላይ ስላልነበር ነው: እናንተ ግን ካለቃችሁ በላይ አለቃ መሆን ያምራቹሃል: ከባሏ በላይ የቤቱ አባወራ ትሆናላችሁ: ከሻጩ በላይ ትርፋማ ትሆናላችሁ: ካረ'ባው ይልቅ ወተት ትጠግባላችሁ: ጠዋት ማታ ስርቆት: ሌት ተቀን ዝሙት: ሰርክ ጭቅጭቅ: ነጋ ጠባ ጦርነትና ሀሜት!! ያንተ ያለህ እኔ የማላውቀውን ሀጢያት ሁሉ አሳያችሁኝ እኮ
ሠው:-እና አንተ እያሳሳትክን እኮ ነው
ሰይጣን:- በቀር ለሀሜትማ ምን ተይዞላቹሀል: እኔ አመንዝሩ ስረቁ ቀሙ ተጋደሉ ተጣሉ ብዬ አማልኳቹህ? ካለአመነዘራችሁ ብልታቹሁን እቆርጣለሁ: ካልሰረቃችሁ እጃችሁን እሰብራለሁ አልኳቹሁ? ካላማቹህና ካልገደላችሁ ዘራችሁን አጠፈዋለሁ አልኳቹሁ? በነጻ የሚጠጣውን ጸበል ንቃችሁ በብር የሚገዛውን አልኮል የምትጋቱ እናንተ! ሚስታችሁን ህጻን እያስታቀፋቹህ የምትሴስኑ እናንተ! የሠራን የምትቀሙ የሠረቀን የምትሸልሙ: የቀማን ጀግና የገደለን ታጋይ እያላችሁ ስላንድነት የታገለውን በፍላጻ የምትቆራርጡ እናንተ! ከከቅቤ ላይ ሙዝ ከእንጀራ ላይ ሳጋቱራ ጨምራቹሁ የምትሸጡ እናንተ! ከወደቀ እንጨት ላይ ምሳር ይበዛበታል ሁኖ ነገሩ ጥፋታችሁን ሁሉ በኔ ስታላኩ የማይሰቀጥጣቹሁ እናንተ! ደግሞ እኔሳ ስልጣኔን ተቀምቼ አርፌ በተኛሁ ምን አረኩ?
ሰው:- እሹ አሁን ወቄስታውን ተወውና የመጣነው ከእግዚአብሄር ጋር ልናስታርቅህ ነው
ሰይጣን:- (ከትከት ብሎ ስቆ) 'ልናስታርቅህ ነው' ነው ያላችሁ? ትገርማላቹሁ እኮ! መታረቅን እንጂ ማስታረቅንማ ትወዱት የለ! አስታራቂማ እንደምድር አሽዋ በዝቶ የለ! የጠፋው እኮ የሚታረቀው ነው! ከሲኦል ይልቅ የሚያስፈራችሁ እኮ ይቅርታ ነው! ይቅርታ የሚባለው ነገር አይደለም ተግባሩ ስሙ በራሱ ያንቀጠቅጣቹሃል! እናንተ እርስ በእርሳቹሁ ሳትታረቁ ሰው ለማስታረቅ ጉባዬ ትጠራላችሁ! በስድብና በቂም ልባቹህ ተሞልቶ ጸጉራቹህ ስለሸበተ ብቻ እናስታርቅ ትላላችሁ! ለመሆኑ እስካሁን ከወጡት ሙዚቃ ስለእርቅ የተዘፈነ አለ? ''እያየህ በለው: ገዳይ ና ገዳይ ና: ነይ ማታ ማታ: ልቡን ልበለው: አምጡት ምንሽሬን' የሚለውን ከመሥማት ውጭ ስለእርቅ አድምጠን እናውቃለን? ሰው ከገዛ ህሊናው ጋር ተጣልቶ ያስታራቂ ያለህ እያለ እየጮህ እናንተ ከዚህ እኔን ትረብሻላቹሁ' ሲል ትቷቸው ሄደ
=====
ሰብሳቢው:- ሰይጣንን አገኛችኛችሁት?
ሽማግሎች:- አግኝተነው ነበር ነገር ግን ሰድቦ ሰደደን
ሰብሳቢው:- ባይሆን አስማት አላስተማራችሁም?
''እየተከዘ''

Mezin worku

@wegoch
@wegoch
ስብሰባው
=======+++++=====
አንዱ አብዮታዊ ፈጣሪን ከሰይጣን ጋር ሊያስታርቅ እቅድ አዘጋጅርና ሽማግሌዎችን መርጦ ውይይት እያደረገ ነው። (መግለጫ መስጠቱ ነው)

ሰብሳቢው:- የስብሰባው አጀንዳ ሰይጣንን ከፈጣሪ ጋር እንዴት ማስታረቅ አለበን የሚል ነው። እንደምታውቁት የሰይጣንን ቦታ መላእኩ ከተረከበ በሁዋላ ሰይጣን እንቅልፉን አልተኛም። እንደምታዩት እርስ በእርሳችን ጠብ ጭቅጭቅ ንትርክ ሁኗል ተግባራችን። ስለዚህ እሄን ነገር ሰላም ለማድረግ ሰይጣን ከፈጣሪ ጋር መታረቅ አለበት። በዚህ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ እንድትሰጡበት እንፈልጋለን '' ሲል ስልኩን መነካካት ጀመረ
*
ሽማግሌ ተመረጠ (ሉካን ቡዱን መሆኑ ነው)
****
ሰይጣን እንቅልፉን ተኝቶ አገኙት
***
ሠው:- ሰይጣን የተመቸህ ትመስላለህ ?
ሰይጣን:- እድሜ ለናንተ ሰላሜን ሰጣችሁኛል ዛሬ ምን እግር ጣላችሁ?
ሠው:- ፈቃድህ ከሆነ አንተን ከእግዚአብሄር ጋር ለማስታረቅ አስበን ነበር
ሰይጣን:- አይሆንም! አትልፉ! ከናንተ ጋር የታረቅኩት ይበቃል። እሱ እኮ ካንዴ ሁለት ጊዜ ከስልጣኔ አስለቅቆኛል። እንደምታዩኝ እንቅልፋም አድርጎኛል። ስሜን ስልጣኔን እና ማንነቴን ቀይሮ አንኮታኩቶኛል። እና እንዴት እታረቀዋለሁ?
ሰው:- ደግሞ ከየትኛው ስራህ ነው ያስለቀቀህ ?ለሚካኤል ከሰጠው ውጭ
ሰይጣን:-አዎ! ለዘመናት ብቻየን ስፈነጥዝበት የነበረውን ዝሙትና ተንኮል ንትርክና ጭቅጭቅ ውሸትንና ክህደት አብዝቶ ለሚሰራው ሰው ለተባለው ፍጡር አሳልፎ ሰጠብኝ። ሰዎች በኔ ስም እየተጠሩ እርስ በእርሳቸው ይናከሳሉ። እኔ ለመስራት የሚከብደኝን ሀጢያት እናንተ እንደጽድቅ ትቆጥሩታላችሁ። እኔ እስካሁን ሰው አልገደልኩም። እናንተ ግን ሰውን አርዳችሁ ትበሉ ጀመር: እኔ እስካሁን ከሴት ጋር አልተኛሁም ለናንተ ግን ዝሙት ስራችሁ ነው ሰዎች ሰይጣን አሳሳተኝ ትሉኛላችሁ እኔ ግን እንኳን ላሳስታቸው በስራችሁ ታስቀኑኛላችሁ:: እግዚያብሔር እኔን የሚያሸንፈኝ በቃሉ ነው: ሀይሉ ያንበረክከኛል: እኔ የእግዚብሄርን ወንበር የደፈርኩት በወቅቱ ከኔ በላይ ስላልነበር ነው: እናንተ ግን ካለቃችሁ በላይ አለቃ መሆን ያምራቹሃል: ከባሏ በላይ የቤቱ አባወራ ትሆናላችሁ: ከሻጩ በላይ ትርፋማ ትሆናላችሁ: ካረ'ባው ይልቅ ወተት ትጠግባላችሁ: ጠዋት ማታ ስርቆት: ሌት ተቀን ዝሙት: ሰርክ ጭቅጭቅ: ነጋ ጠባ ጦርነትና ሀሜት!! ያንተ ያለህ እኔ የማላውቀውን ሀጢያት ሁሉ አሳያችሁኝ እኮ
ሠው:-እና አንተ እያሳሳትክን እኮ ነው
ሰይጣን:- በቀር ለሀሜትማ ምን ተይዞላቹሀል: እኔ አመንዝሩ ስረቁ ቀሙ ተጋደሉ ተጣሉ ብዬ አማልኳቹህ? ካለአመነዘራችሁ ብልታቹሁን እቆርጣለሁ: ካልሰረቃችሁ እጃችሁን እሰብራለሁ አልኳቹሁ? ካላማቹህና ካልገደላችሁ ዘራችሁን አጠፈዋለሁ አልኳቹሁ? በነጻ የሚጠጣውን ጸበል ንቃችሁ በብር የሚገዛውን አልኮል የምትጋቱ እናንተ! ሚስታችሁን ህጻን እያስታቀፋቹህ የምትሴስኑ እናንተ! የሠራን የምትቀሙ የሠረቀን የምትሸልሙ: የቀማን ጀግና የገደለን ታጋይ እያላችሁ ስላንድነት የታገለውን በፍላጻ የምትቆራርጡ እናንተ! ከከቅቤ ላይ ሙዝ ከእንጀራ ላይ ሳጋቱራ ጨምራቹሁ የምትሸጡ እናንተ! ከወደቀ እንጨት ላይ ምሳር ይበዛበታል ሁኖ ነገሩ ጥፋታችሁን ሁሉ በኔ ስታላኩ የማይሰቀጥጣቹሁ እናንተ! ደግሞ እኔሳ ስልጣኔን ተቀምቼ አርፌ በተኛሁ ምን አረኩ?
ሰው:- እሹ አሁን ወቄስታውን ተወውና የመጣነው ከእግዚአብሄር ጋር ልናስታርቅህ ነው
ሰይጣን:- (ከትከት ብሎ ስቆ) 'ልናስታርቅህ ነው' ነው ያላችሁ? ትገርማላቹሁ እኮ! መታረቅን እንጂ ማስታረቅንማ ትወዱት የለ! አስታራቂማ እንደምድር አሽዋ በዝቶ የለ! የጠፋው እኮ የሚታረቀው ነው! ከሲኦል ይልቅ የሚያስፈራችሁ እኮ ይቅርታ ነው! ይቅርታ የሚባለው ነገር አይደለም ተግባሩ ስሙ በራሱ ያንቀጠቅጣቹሃል! እናንተ እርስ በእርሳቹሁ ሳትታረቁ ሰው ለማስታረቅ ጉባዬ ትጠራላችሁ! በስድብና በቂም ልባቹህ ተሞልቶ ጸጉራቹህ ስለሸበተ ብቻ እናስታርቅ ትላላችሁ! ለመሆኑ እስካሁን ከወጡት ሙዚቃ ስለእርቅ የተዘፈነ አለ? ''እያየህ በለው: ገዳይ ና ገዳይ ና: ነይ ማታ ማታ: ልቡን ልበለው: አምጡት ምንሽሬን' የሚለውን ከመሥማት ውጭ ስለእርቅ አድምጠን እናውቃለን? ሰው ከገዛ ህሊናው ጋር ተጣልቶ ያስታራቂ ያለህ እያለ እየጮህ እናንተ ከዚህ እኔን ትረብሻላቹሁ' ሲል ትቷቸው ሄደ
=====
ሰብሳቢው:- ሰይጣንን አገኛችኛችሁት?
ሽማግሎች:- አግኝተነው ነበር ነገር ግን ሰድቦ ሰደደን
ሰብሳቢው:- ባይሆን አስማት አላስተማራችሁም?
''እየተከዘ''

Mezin worku

@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
ወረፋ
(ቡሩክ ካሳሁን)
አናሳዝንም ወይ? ኸረረረረረ
የቴዲ ዘፈን መስሎህ ለእስክታ እንዳትነሳ ጎበዝ፡፡ ይህ የታክሲ ናፋቂ ህዝብ ድምፅ ነው፡፡ ከሜክሲኮ ወደ አራት ኪሎ ለማቅናት ያኔ ሙሴ እስራኤሎችን ለማሻገር ያሰለፈውን ሰልፍ የሚያስንቅ የታክሲ ሰልፍ ተሰልፈናል፡፡ እንደው አንድ አፈ ቀላጤ ሰው ‹እስኪ 1፣ 1 ብር› እያለ እዛ የተሰለፈውን እየዞረ ቢጠይቅ እኔ ነኝ ያለ ቅጥቅጥ ይገዛ ነበር ዳሩ ምን ያደርጋል ቀጥቃጣ ብቻ ነው የተሰበሰበው፡፡ በዚህ ጊዜ ወዳጄ፣ ተራ አስከባሪ ማወቅ አንድ ትልቅ ባለስልጣን ከማወቅ አይተናነስም፡፡ ተራ አስከባሪዎችም ጊዜ የሰጠው ቅል ሆነው የተከበሩ ሰዎችን ሚስት ስልጣንን ተገን በማድረግ (ያቺም ስልጣን ሆና ማለት ነው) ፆታዊ ጥቅም ያሳድዳሉ፡፡ እኔ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ተራ አስከባሪ መሆን ተመኘው፤ ቀናሁ ;-) ፡፡ እዛ የተሰለፈች ሴት ሁላ ለተራ አስከባሪው ደማቅ ፈገግታ ታሳያለች፡፡ እነ እገሌ እቺን ሰልፍ እየቀረፁ ይመስለኛል በእንትን ፊልም ሰልፍ አገር ሲጨናነቅ ምናምን የሚሉት፡፡
ሰልፉ ላይ ከታክሲ ይልቅ አዳዲስና አሮጌ ሃሳቦች ቶሎ ቶሎ ይመጣሉ፡፡ ‹ቃና ይዘጋ› እያለ አንዱ ከጓደኛው ጋር ሲያወራ ከፊቱ የተሰለፈ ባለ ጥቁር ፂም ጎረምሳ ‹ ምነው ብራዘር የከሰረ የፊልም ደራሲ ወይ ዳይሬክትር ዘመድ አለክ እንዴ ወይስ ኢ.ቢ.ኤስ ነው ምትሰራው?› ብሎ መለሰለት
‹ ትውሉዱ እኮ እየተበላሸ ነው ባህሉንና ወጉን እየረሳ ነው ቃና መዘጋት አለበት›
‹እና ታዲያ ትውልዱን ወደ ባህሉና ወጉ ምትመልሰው ምርጫ ቢስ በማድረግ ነው እንዴ? ከቻልክ አስተምረህና አስረድተህ እንጂ አስገድደህ ነው እንዴ? ደግሞስ የትኛው የሀገራችን ፊልም ነው ለወጉና ለባህሉ ሲጨነቅ ያየከው? እቺ እቺ ማምታቻ ናት፤ ባይሆን ሰዉ ፊልምን ማጣጣምና መገምገም ጀመረ፤ ገበያችንን ዘጋው በለኝ በግልፅ› እየተባባሉ ሲጨቃጨቁ ‹ኸረ ወንድሞቼ የቸገረን ታክሲ ነው የኢትዮጲያ የፊልም ደረጃ አንድ እርምጃ ወደፊት ወደኋላ ስትሉ አደናቅፎት እንዳይከሰከስ› በመሀል ሰላላ ድምጽ ተወረወረች፤
በድንገት ተራ አስከባሪው አንዲት ቆንጆ ልጅ ስልክ ቁጥሯን ተቀብሎ መጀመሪያ ሰልፍ ሲወስዳት
‹በህግ አምላክ ወደሰልፏ መልሳት› አሉ ከራሰ በራነት የተረፈ ፀጉራቸው ፈትል ጥጥ የመሰለ ሰውዬ
ተራ አስከባሪው ልጅቱን እርጉዝ ናት ብሎ ደረቀ… ሰውየውም ‹እንኳን እርግዝና የረባ ቦርጭ የላትም ባይሆን ዛሬ ማታ ታረግዝ እንደሆን ንገረን› አሉ የፊታቸው ደምስር እንደተገተረ
ተራ አስከባሪውም ‹ዉ…ይ ፋዘርዬ በሁለትሺ አስርም እንደዚ ኖት አልተለወጡም?¡› አፌዘ
‹ኸረ ፌደራል ይዘዝብህ ሌላ ምንም አልልህም› ሰልፈኛው ፈገግ አለ፡፡
.
አንድ ነጭ ሚኒባስ ያንን ሰልፈኛ ሊታደግ ከተፍ አለ፡፡ ዲጄው(ወያላው) ሰልፉን ሲያይ ልቡን አወረው፤ ‹አምስት አምስት ብር ይመቻችኋል?› አለ ወደሰልፈኛው እየተመለከተ
‹አዎ ይመቸናል 2ብር ከሀያ አምስት መልስ ምትሰጠን ከሆነ› የሆኑ አሮጊት መለሱለት
‹ጥሩ ይቀልዳሉ ቃና ላይ እርሶ ኖት እንዴ 300ሺ ብር ያሸነፉት? 5 ብር ሚመቸው ይግባ› ወያላው ተናዶ መለሰላቸው
ሰልፉ ያታከተው ተሯሩጦ ገባ፡፡ እንደምንም እኔም ትርፍ ሆኜ ገባሁ፡፡ ወያላው ሂሳብ መሰብሰብ ሲጀምር ታምረኛ እኮ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ባዘቦቱ ዝርዝር የለኝም ሚል ሁላ ሁለት ከሰባ አምስት፣ ሁለት ከሰባ አምስት እያወጣ ለወያላው ይሰጥ ጀመር፡፡ ጦርነት ተነሳ አምስት ብር ነው ያልኳቹ አምስት ብር አምጡ ወያላው ደነፋ፡፡ ‹እሺ አትልማ› ሚል ድምጽ ከኋላ ተወረወረ ዞር ብዬ ሳይ ቅድም 2ብር ከሀያ አምስት ከመለስክልን ያሉት ሴትዮ ናቸው፡፡
‹ካፌ እና ሬስቶራንት ገብተህ 5 ብርና 10 ብር ቲፕ ሰጥተህ ትወጣለህ ታክሲ ላይ ግን ለ25 ሳንቲም መልስ ትንገበገባለህ› ወያለው በንዴት መለሰ ከኋላ ኪሱም ‹እቺም እንጀራ ሆና ሚጥሚጣ በዛባት› የሚል ጥቅስ አውጥቶ መኪናው ላይ አንጠለጠለ፡፡ 4ኪሎ ደርሰን መውረድ ስንጀምር የቅድሟ ሴትዮ ‹ይኸውልህ ልጄ ጊዜ ሰጠኝ ተብሎ አይመፃደቅም እራሱ ጊዜ ይጥላልና› ሲሉት ለወያላው
‹ኸረ ስራዬን ልስራበት በሰላም ግቢ› ለትልቋ ሴትዮ መለሰላቸው
አውርዶን እንደጨረሰም መኪናውን ወደ ሜክሲኮ አዙሮ ሱዳን ድረስ በሚሰማ ‹ሜክሲኮ ሜክሲኮ› እያለ ጮኸ ግን ተሳፋሪ አላገኘም፡፡


ጥቅምት 2010 ዓ.ም
ቡሩክ ካሳሁን ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል
@burukassahunc


@wegoch
@wegoch
//ሕይወት እንደ ተረት/// (1)
(ጆኒ ፀጋዬ)

..ህይወት እንደ እመት ቦቦሊና አሮጊት ናት፡፡ ግን ሁሌም ጨርቅ
አስጥሎ ለማሣበድ የሚያስችል አንዳች መላ አታጣም.. ይላል፤
አሌክሲስ ዞርባ፤ የካዛንታኪስ ገፀ ባህርይ፡፡ ከእነዚህ መላዎችዋ
አንዱ አዲስ ዓመት ነው፡፡ ህይወት ሰርክ አዲስ ናት፡፡ በመደጋገሟ
ኃይሏ አይቀንስም፡፡ ሁሌም ልባችንን እንደ ሰቀለች ታኖረናለች፡፡
ህይወት ሰማያዊ፤ በደም በሥጋ ትተርከናለች፡፡ የሰው ልጅ መሬታዊ፤
በቃል፣ በዜማ፣ በቀለም፣ በኪነ ቅርፅ ኮርጆ ይተርካታል፡፡ አንዳንዴም
በትረካው እርሷን ለማስናቅ ይዳዳናል፡፡
ህይወት፤ ሁሌም ቢነበቡ ከማይሰለቹ ..ታላላቅ ተረቶች.. አንዷ ነች፡፡
እንደ ኤዞፕ ወይም እንደ ተራኪዋ - የአላዲን? ልጃገረድ ባለ ጥበበኛ
እጅ ስትገባ፤ ተደጋግማ ብትነገርም ሁሌም እንደ አዲስ የምንሰማት
ውብ ..ተረት.. ናት፡፡ ህይወትን ..ተረት.. በሚያደርግ ጠቢብ ትርጉም
ታገኛለች፡፡ ትከብራለች፡፡ህይወት ..ተረት.. ከመሆንዋ በፊት ትርጉም
የለሽ ናት - ዝብርቅርቅ የዕብድ ቃል፡፡ ወደ ትረካ ስትመጣ ትርጉም
ትይዛለች፡፡ የሰው ልጅ ህይወት ከእንስሳት እድር ወጥቶ ማዕረግ
የሚያገኘው በትረካ ነው፡፡ በቦታ እና በጊዜ ተበታትኖ የነበረ ህይወት
ትርጉም በሚሰጥ መንገድ ትቀመራለች፡፡ ምርጥ ታሪክ ትሆናለች፡፡
ህንዳዊቷ የልቦለድ ደራሲ አሩንዳቲ ሮይ በአንድ ጽሁፍዋ ..ምርጥ
ታሪክ ማለት፤ ትናንት ሰምተናቸው፤ ዛሬም ደግመን ለመስማት
የምንፈልጋቸው ናቸው፡፡ ከየትኛውም የታሪኩ አንጓ ብትጀምሩ
ይመቻችኋል፡፡ ምርጥ ታሪኮች፤ ያልታሰበ ወይም ያልተገመተ -
አስደንጋጭ? አጨራረስ የመከተል ጮሌነት ያላቸው አይደሉም፡፡
እንደምንኖርበት ቤት ወይም እንደ ወዳጅ ጠረን የምታውቃቸው እንጂ
አዲስ አይደሉም፡፡
..ታሪኩ እንዴት እንደሚጠናቀቅ እናውቃለን፡፡ ግን እንደማናውቅ
ዓይነት ጆሮአችንን ከፍተን፤ ልባችንን ሰጥተን ታሪኩን ለመስማት
ዝግጁ ነን፡፡ ነገሩ፤ አንድ ቀን እንደምንሞት ስናውቅ፤ ሞት የሌለብን
ሆነን መኖር ነው፡፡ በታላላቅ ታሪኮች ውስጥ ማን እንደሚሞት፣ ማን
እንደሚኖር፣ ማን አፍቃሪውን እንደሚያገኝ ማን እንደማያገኝ
ታውቃላችሁ፡፡ ግን እንደገና እንዲነገራችሁ፤ እንደገና እንድታውቁት
ትፈልጋላችሁ፡፡ ይኸ ነው የምርጥ ታሪኮች ምትሃት፣ አስማት፣
እንቆቀቅልሽ.. ትላለች ሮይ፡፡
ህይወትም እንዲህ ዓይነት ድንቅ ታሪክ ናት፡፡ በአዲስ ዓመት መንፈስ
አሙቃ፤ በተደጋጋሚ ባየነው አስማቷ አፍዝዛ፤ አሮጌውን አዲስ አድርጋ
አሳይታ ልታሰክረን ትመጣለች፡፡ ሽርጉድ ታሰኘናለች፡፡
በህፃናቱ አንደበት፤ እያዜመች ከፊታችን ቆማለች፡፡ ይኸው አሁን፤
..አበባዬ ሆይ ለምለም፤ ባልንጀሮቼ ለምለም.. እያለች፤ እንደ ገና
ልባችንን ታሞቀው ይዛለች፡፡
..ህይወት እንደ እመት ቦቦሊና አሮጊት ብትሆንም፤ ... ሺህ ጊዜ
ከአልጋ ተጋድማ፤ ሺህ ጊዜ በድንጋሌ -ሀሳብ - እይታ? ከመደብዋ
ትነሳለች፡፡ ዳግም ትወለዳለች፡፡ ምትሃት ነች፡፡
..ለምን? እንዴት?.. የሚል ጥያቄ በማንሳት ለዛዋን፣ ጣዕሟን
ማበላሸት ትርፍ የለውም፡፡ ይልቅስ በተስፋ ዝናብ ያጨለጨለ ምናብ
አድላ፤ በአዲስ ዓመት እንደገና ልትሞሽረን ከመጣችው ምትሃተኛ
ህይወት ጋር መተቃቀፍ ነው፡፡ እኔ ስታቀፋት እንዲህ ሆነ፤
..ከየት መጣሁ ሳልል ከአንድ ሥፍራ ዱብ አልኩ፡፡ በመደነቅ ፈንታ
የሚያሳስበኝ ክፉ ነፋስ ዱብ አለ፡፡ ህይወት ድግግሞሽ መሆኗን
የሚያስታውሱኝ ትናንሽ ቀበሮዎችን ታሰሩ፡፡ የፅጌ መስኩን
የሚያማስኑ ቀበሮዎች ታገሱ፡፡ በዘላለም ሜዳ እና ሰማይ፤ በጊዜ
ማሣ ዳር ከበቀለች እና ፍፃሜው በማይታወቅ ህዋ ውስጥ ብቻዋን
ካለች ዛፍ ላይ ከሰራችው ጎጆ እንቁላልዋን ታቅፋ የተቀመጠች ርግብ
ሆኜ ነቃሁ፡፡ እኔው ራሴ፤ ከእንቆቅልሽ እንቁላል ውስጥ ክሌውን ሰብሬ
እንደ ጫጩት ብቅ ስል እራሴን አየሁት፡፡
ይኸን ተዓምር ለማወደስ ፈለግኩት፡፡ ከሰው ዕድሜ የላቀ ዕድሜ
ያለው ..ቋንቋ.. ለመንኩ፡፡ የተወሰደ ልሳኔ እንዲመለስልኝ ጠየቅኩ፡፡
በኃያሉ አምላክ ዙፋን ፊት ቆሜ ውዳሴውን እንዳወርድ ይፈቀድልኝ
ዘንድ ማለድሁ፡፡ የተዘረጋ እጄ ሳይታጠፍ፤ ምስጋና የተራበ ልቤ
ዘመረ፡፡ የምስጢር ወይንጠጅ ተጎነጨሁ፡፡ ታላቁን ውቂያኖስ
የምትውጥ አንዲት ጠብታ ከፍቅር ላምፋ ላይ እንደ ጤዛ ጠብ ስትል
አየሁ፡፡
ድንገት ደግሞ፤ ኃይለኛ ውሽንፍር የቀላቀለ የጥርጣሬ ወጀብ ተነሳ፡፡
ወጀቡም የነፋስ ድንኳኔን ካስማ ሊነቅለው ታገለ፡፡ ያኔ ልቤ በእምነት
ጀልባ ተሳፈረች፡፡ ይኸው በፍቅር አምባ፤ የተስፋ ድንኳን ተተክሏል፡፡
ልቤም ወደዚያው እየቀዘፈች ስትሄድ ተመለከትኳት፡፡ አራቱም
አቅጣጫዎች ጠቀሱኝ፡፡ አዜብ፣ መስእ፣ ሊባ እና ባህር ጠሩኝ፡፡ የዕፀ
በለስ ማዕበል ተነሳ፡፡ ጀልባዋን ሊውጣት አገሳ፡፡ የትዕቢት ባህር
ፎገላ፡፡
ያኔ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈረሱን እየጋለበ መጣ፡፡ በእረፍት ውሃ ዳርቻ
ለመቀመጥ የሚታገለውን መሬታዊ ፍጡር ሊታደገው በነጩ ፈረሱ
ጋለበ፡፡ የትዕቢት ባህር ፀጥ አለች፡፡ የእፀ በለስ እሣት ተዳፈነች፡፡
የክፋት አፍንጫ ተፎነነች፡፡ ጀንበር ገብታ እስክትወጣ ድረስ ህይወት
ሰልፍ ሆኖ ቆየ፡፡
ቀንም ሆነ፤ ማታም ሆነ፤ ሁለተኛ ቀን፡፡ የማለዳ ፀሐይ ስትወጣ፤
የፍቅርን ሰረገላ የሚስቡት ነጫጭ ፈረሶች እየተቅበጠበጡ መጡ፡፡
የሌቱ የሀሳብ ዝርፊያ ተገታ፡፡ ፈረሶቹ በማለዳው ጮራ
እያብለጨለጩ ይታዩኛል፡፡ ክፉዎች ሊነኩት በማይችሉት የፍቅር
ልጓም፤ እየኮለኮለ የሚጋልበው አምባላይ ፈረስ መጣ፡፡ ..የወይኑን
ተክል ከቀበሮዎቹ ጠብቁ፡፡ የወይኑን ማሣ እንዳያማስኑት ትጉ..
የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ ነቃ አልኩ፡፡ ግን ስለሆነው ነገር ከማወቄ በፊት
ሁሉም ነገር ፀጥ አለ፡፡ ከሩቅ ስፍራ እንደሚመጣ ነፋስ እየተውጀበጀበ
ከጆሮ የገባው፤ በልስላሴው እያዘናጋ ኪሶቼን በረበራቸው፤
ካህን የነፍሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ፤ የሚል ዜማ ነው፡፡
ሃሌ - ሃሌ ሉያ፤ ፀባኦት - ኤልሻዳይ፤ ሃሌሉያ፤ ዛሬ ህይወት ታሪክ
መሆን አልፈለገችም፡፡
ከተራራው ጀርባ፤ ከወንዙ ባሻገር
የተጨዋወትነው፤ ብዙ ምስጢር ነበር..
እያለ ያዜመው ማን ነበር? ህይወት የሮማንቲካዊ ቅርጽ የያዘ ተረክ
ስትሆን እንዲህ ነው፡፡
የፈረሰው የእውን እና የህልም ዓለም ግድግዳ እንደ ገና ቆመ፡፡
ህይወት እንዲህ ትዘፍናለች፡፡ እንዲህ ትተረካለች፡፡ ህይወት እንዲህ
በቀለም ተስላለች፡፡ ነገ በሌላ ካንቫስ ሌላ፣ በሌላ ሰዓሊ እጅ በአዲስ
ቀለም እንደ አዲስ ዘመን በልምላሜ አጊጣ ታድሳ ትመጣለች፡፡
ህይወት ትንግርት ናት፡፡ እንኑራት፡፡ አበባዬ ሆይ ለምለም፡፡
ጨፍር ጎበዝ ደንስ ጎበዝ
ህይወት የምትፈቷት እንቆቅልሽ አይደለችም፡፡
በድንቅ ተጥለቅልቃችሁ የምትኖሯት ተዓምር ነች፡፡ በፍርሃት እና
በፍቅር የምንዘምራት የሞት እና የትንሣዔ መዝሙር ናት፡፡ አሁን
ባግዳድ ልውሰዳችሁ፡፡ ተረት ልንገራችሁ፡፡ የሃማሉን ቁጥብ እና
የሦስቱ የባግዳድ ወይዛዝርት ታሪክ የዘመን መለወጫ ስጦታዬ ነው፡፡
ከዘመናት በአንዱ ዘመን፤ ባግዳድ ውስጥ ሚስት ሳያገባ በላጤነት
ብቻውን የሚኖር ቁጥብ የሚሉት ሐማል ነበር፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን
በጎዳናው ዳር ቦዝኖ፤ ቅርጫቱንም ደገፍ ብሎ እንደ ቆመ አንዲት
ወይዘሮ መጣች፡፡ በወርቅ የተጠለፈና የወርቅ ጉንጉን ጥለት ያለው
ሙሉ ሐር ቀሚስ እንደለበሰች ከፊቱ ቆመች፡፡ ጫማዋ ወርቅ፤
ፀጉሯም በወርቅ የተጌጠ ነው፡፡ ዓይነ ርግብ ያደረገች ይህች ሴት፤
ብርሃን የሚረጩ ጥቋቁር ዓይኖች ያሏት ናት፡፡



ይቀጥላል

@wegoch
@wegoch
📌 ሳይክ-ኢንፎ

የምክርና የንግግር ህክምና (Counseling and Therapy) በ Online Chat ፣ በ Video Call ወይም በ Phone Call በማንኛውም ሰዓት እና ቦታ ላይ ሆነው በነፃ ማግኘት ይችላሉ ። 100% ሚስጥሮት ተጠብቆ የሚፈልጉትን እርዳታ አሁን ያግኙ !
//ህይወት እንደ ተረት // (2)
(ጆኒ ፀጋዬ)

እይታዋ ቅዝዝ ልስልስ
ያለው፤ ፍጹም የተዋበችው ያቺ ሴት እንደ ሙዚቃ በአማረ ድምፅ
..ቅርጫትህን ይዘህ ተከተለኝ.. አለችው፡

ሐማሉ ቁጥብ ፍፁም ተደንቆ እና የሚሰማውንም ማመን አቅቶት፤
..ያአላህ! እንዴት ያለች የተባረከችና ዕድላም የሆነች ቀን ነች.. አለ፡፡
ያንን ብሎ ቅርጫቱን አፈፍ አድርጎ ከትከሻው ጣለ፡፡ከአንድ ቤት ደርሳ
እስከ ቆመች ድረስ ተከተላት፡፡ በዚያም በሩን አንኳኳች፡፡ የናዛሪው
ሽማግሌ ፈጥነው ብቅ አሉ፡፡ የወርቅ ሳንቲም ተቀበሉ፡፡ በእሱም እንደ
ወይራ ዘይት ኩልል ያለ የወይንጠጅ አምጥተው ሰጥዋት፡፡ እርሷም
ቀስ አድርጋ ከቅርጫቱ ውስጥ አስቀመጠችው፡፡ ..አንሳና ተከተለኝ..
አለችው፤ ሐማሉን ቁጥብ፡፡ ..ሰው ያሰኘውን ሁሉ የሚያገኝበት አላህ
የባረከው ቀን ይሄ ነው.. እያለ ቅርጫቱን ተሸከመ፡፡ አሁንም ከአንድ
የአትክልት መሸጫ ሱቅ በር ደርሰው እስኪቆሙ ተከተላት፡፡ በዚያም
የሻሚ አፕል፣ የኦስማን ኩንች፣ የአማን ኪሽኒት፣ የአባይ ወንዝ
ያበቀለው ዱባ፣ የግብፅ ሎሚ፣ የሱልጣኒ ብርቱካን እና ትርንጎ
ገዛች፡፡ ከቅርጫቱም አኖረች፡፡ ደግሞ መልካም ማዕዛ ያላቸው የአደስ
ፍሬዎች፤ ሽታው የሚያውድ የአልፓይን ሐረግ፣ የደማስቆ ኔኑፋረስ እና
ከሞሜላ፣ እንደ ደም ቀይ የሆነ ፅጌሬዳ፣ የቫዮሌት፣ የኢግላንታይን፣
የፈካ የሮማን እና የአደይ አበባዎች በቅርጫቱ ተጨመረ፡፡ ከዚያም
..በል አንሳ.. አለችው፡፡ አንስቶ ተከተላት፡፡TN> እልፍ ብሎ ደግሞ
ከሉካንዳ ቤቱ ቆመች፡፡ ..አምስት ኪሎ ሥጋ ቁረጥልኝ.. አለች፡፡
ከፈለች፡፡ በሙዝ ቅጠል ጠቅልሎ ሰጣት፡፡ ከቅርጫቱ ጨመረች፡፡
አሁንም ..በል አንሳ.. አለች፡፡ ሃማሉ ተሸከመ፡፡ ተከተላት፡፡ደግሞ
ከአንዱ ግሮሰሪ ቆመች፡፡ ከዚያም ደረቅ ፍራፍሬዎችን ገዛች፡፡
ለውዙን፣ ዘቢቡን ጨመረች፡፡ ከምግብ በኋላ የሚቀርቡ ጣፋጭ
ተከታዮችንም አከለች፡፡ ..ሐማል አንሳ ተከተለኝ.. አለች፡፡ ቅርጫቱን
አነሳ፡፡ ተሸከመ፡፡ ተከተላት፡፡
ከጣፋጭ መሸጫ ሱቅ ገብታ፤ ዝርግ የሸክላ ሰሃን ገዝታ፤ እንደ ዝባድ
ያሉ ለዓይን እና ለአፍንጫ የጣመ ጠረን ያላቸው መዋቢያ ዕቃዎችን
በሰሃኑ አስቀምጣ፤ ከቅርጫቱ ጨመረች፡፡ ..ሃማል አንሳ.. አለች
ቀጠለች... ቀጠለች...በዚህ ጊዜ፤ በፍፁም ደስታ የተጥለቀለቀው
ሐማል፤ ..ይሄን ሁሉ ዕቃ እንደምትገዢ አስቀድመሽ ብትነግሪኝ ፈረሴን
ወይም ግመሌን ይዤ እመጣ ነበር.. አላት፡፡ እሷም ፈገግ አለችና
..ወሬውን ተወው፤ በልማ እንሂድ አይዞህ፤ ኢንሻ አላህ፤ ጠቀም ያለ
አስብ ታገኛለህ.. አለችው፤ ማጅራቱን በእጇ መታ እያደረገች፡፡
ደግሞ ከሽቱ መሸጫ ሱቅ ገባች፡፡ የፅጌሬዳ፣ የብርቱካን፣ የአደይ፣
የቫዮሌት፣ አበቦች መዐዛ ያላቸውን ፈሳሾች ገዛች፡፡ አንድ የሽቱ
ማርከፍከፊያ ጠርሙስም ገዛች፡፡ እጣኖችን፣ ሰንደሎችን ገዛች፡፡
በእስክንድሪያ የተሰሩ ሻማዎችን ሸመተች፡፡ ከዚያም በቅርጫቱ
ጨምራ ..አንሳና ተከተለኝ.. አለች፡፡ ሄዳ ከአንድ ሰፊ ግቢ ቆመች፡፡
በግቢው የሚታየው ቤት እጅግ ያማረና አምዶቹ ሞገስ የሰጡት ቤት
ነው፡፡ ባለ ሁለት ተካፋች የሆነው እና ከጥቁር እንጨት የተሰራው
የቤቱ በር ላይ ቀይ የወርቅ ቅጠል ተለብጦ ይታያል፡፡ ከበሩ እንደ
ደረሰች ዓይነ እርግቧን ወደ ጎን አደረገች፡፡ እናም በቀስታ አንኳኳች፡፡
ሐማሉ ከኋላዋ እንደ ቆመ፤ ስለ እመቤቲቱ ቁንጅና፣ ተወዳጅነት እና
የደስደስ በስተቀር ሌላ የሚያስበው አልነበረውም፡፡ በሩ ተከፈተ፡፡
ጉድ ነው፡፡ በሩን የከፈተችው ረዘም መለል ያለች ወጣት ናት፡፡
የቁንጅና አብነት የምትሆን፤ የአዕምሮ ብሩህነትን የታደለች ፍጹም
ግርማ ሞገስ ያላት ወጣት ናት፡፡ ግንባሯ እንደ ነጭ አበባ ሆኖ
ጉንጮቿ እንደ ቀይ ፅጌሬዳ የቀሉ ናቸው፡፡ ብሩህነትን የተላበሱት
ዓይኖቿ እንደ ጊደር ወይም እንደ ሜዳ ፍየል ስክት ያሉ ናቸው፡፡
ቅንድቦቿ የአዲስ ጨረቃ ቅርፅ የያዙ ናቸው፡፡ አፏ የጠቢቡ ሰለሞንን
ቀለበት የመሰለ ሲሆን ከንፈሮችዋ ፍም ናቸው፡፡ ጥርሷም በክር
ተለክቶ የተደረደረ ሉል ይመስላል፡፡ አቤት አንገ አንገትዋ እንደ ሚዳቋ
አንገት መለል ያለ ነው፡፡ ጡቶቿ ሞላ ያለ ሮማን ይመስላሉ፡፡
ስትራመድ፤ ሰውነቷ በለበሰችው ቀሚስ ውስጥ እንደ ፀጉር ጉንጉን
ይሽመለመላል፡፡ እምብርቷ፤ አንድ ብልቃጥ የወይራ ዘይት ይይዛል፡፡
በጥቅሉ የምድር ባለቅኒያት ሁሉ በቅኔያቸው ያወደሷት ሴት
ትመስላለች፡፡ ቁጥብ፤ በዚህች ሴት እልፍኝ ገብቶ በሚያየው እና
በሚሰማው ነገር ሁሉ እየተደመመ ቆየ፡፡ ከወይዛዝርቱ ጋር ተላመደ፡፡
ተፈቀደ፡፡ እናም ግጥም በወይንጠጅ እየተጎነጨ ጥያቄ
አቀረበ፡፡ ..በአላህ ብቻችሁን ናችሁ፡፡ እኔ በዚሁ ብቆይ ምን
ይመስላችኋል?.. ብሎ ጠየቀ፡፡ ጥያቄውን ከመቀበላቸው በፊት
ከሦስቱ ሴቶች አንዷ ጥያቄ አቀረበች፡፡ ጥያቄውም ..ምንም ነገር
ብታይ አንድም ጥያቄ ላታነሳ ማሃላ ታደርጋለህ?.. አለችው፡፡ ሐማሉ
ቁጥብ ..እምላለሁ.. አለ፡፡ ከመሃላው በኋላ ..ወዲያ ሂድና እዚያ
ከበሩ ላይ የተፃፈውን ነገር አንብብ.. አሉት፡፡ በወርቅ ፊደል ከበሩ
የተፃፈው ቃልም እንዲህ የሚል ነው፡፡ ..የማይኮነስረውን ነገር
የሚያወራ ሰው፤ የማያስደስተውን ነገር ይሰማል.. ተረቱ ይቀጥላል፡፡
ህይወት የምንፈታት እንቆቅልሽ ሳትሆን የምንኖራት ትንግርት እንደ
ሆነች ስንቀበል የማይኮነስረንን አናወራም የማንወደውንም
አንሰማም፡፡ ከፍ ሲል ቀንጨብ ያደረኩት የሪቻርድ በርተን ተረት
ይቀጥላል፡፡ ተረቱም የኛ ህይወት ነው፡፡ ህይወት እንደ ቁጥብ
እመቤት ነች፡፡ እኛም ሐማሎቿ ነን፡፡ እመቤት ህይወት፤ መጪውን
ዘመን እንደ ቁጥብ በሸክሟ፣ በስጦታዋ፣ በፀጋዋ አምበሽብሻ ታሳድረን ።

(ጆኒ ፀጋዬ)

@wegoch
@wegoch
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት

#አዝናኝ #አስተማሪ #ወቅታዊ #ሀገርኛ መፅሔት👇👇

#ቅፅ 1 - #ቁጥር 4

@KendelM
@KendelM
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቅንድል Digital መፅሔት.pdf
4.3 MB
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት

#በአዲስ እና በአማረ አቀራረብ‼️

ቅፅ 1 - ቁጥር 4

💵ፓኬጅ ከገዙ 50 ሳንቲም ብቻ💵

@KendelM
@KendelM
ቆዳ እና ባለቆዳ(ልዑል ሀይሌ)

በሬው እግር እግሬን እያየ ይጮሃል "እምቧ!!..." እኔም የሱ እንደዛ ማፍጠጥ እየገረመኝ እግሮቼን እንደ አዲስ እመለከታቸው ጀመር። "ምናባቱ አይቶ ነው ይሄ በሬ እንዲህ እያፈጠጠ የሚጮኸው?" እላለሁ አንዳችም አዲስ ነገር ከእግሮቼ ሳጣ ....ነገር ግን በሬው
ጩኸቱን ቀጥሏል "እምቧ!!..." ምን አይቶ ይሆን ይሄ ከብት እንዲህ የሚጮኸው?..." እያልኩ እየተነጫነጭኩ እርምጃዬን ስጀምር በሬውም እየተከተለኝ ሲጮህ ሳይ ተገርሜ እኔም እግር እግሩን አየው ጀመር። ሁለታችንም እግር እግራችንን እየተያየን ከቆየን በኋላ የበሬው እረኛ ደርሶ ሲቆም እኔም የእፎይታ ትንፋሼን እየለቀቅኩ "ምን ሆኖ ነው ባክህ እግር እግሬን እያየ የሚጮኸው?...ምነው ሊጠርግልኝ
አስመሠለውሳ..." ስለው በሬው የታሰረበትን ገመድ አጥብቆ እየያዘ "አመሉ ነው...ማለቴ ከቆዳ የተሰራ ነገር ሲያጋጥመው ሳያስወልቅ አይተውም። እርሶም ቆዳ ጫማዎትን ቢያወልቁት ከዚያ በኋላ ፊቱን አዙሮ ይሄዳል" ሲለኝ የተጫማሁትን አንበሣ ጫማ እያየሁ "አይ ዕድሌ የአያ ጎበዜ እንዳይበቃኝ አንተም ትቀናብኝ?!..ስንት ዕድር ዕቁቡን
በኩራት እየተራመድኩ ያቋረጥኩበትን ስንቱን ምቀኛ ዓይኑን ያቀላሁበትን ጫማ የኔ ነው አልክ?!..እንግዲህ አንተንስ ምን ገዶኝ አወልቅልሃለሁ...እንኳን ጫማዬ እግሬም የኔ አይደለ!!...ተውሸውም አይደል የዚህችን ዓለም ግሳንግስ እጓዝበት ዘንድ የሆነው?...ይሁና!!"
ብዬ ጫማዬን አውልቄ ወደሱ ሳስጠጋለት እረኛው እንዳለው ፊቱን አዙሮ ሄደ። ...እውነት ነው ያስጮሃል ቆዳህን ሌላው እንደጫማ እየረገጠው ሲሄድ ያማል!!...ነገህን በሌሎች ላይ ስታይ ካልነቃህ ዕጣ ፈንታህን እያበላሸኸው እንደሆነ አትጠራጠር
.
.
...(ይቀጥላል)

15-09-11
አሶሳ ኢትዮጵያ


@wegoch
@wegoch
የጋሽ እርገጤ ልጅ ባረገዘች ማግስት
(ቡሩክ ካሳሁን)
ጋሽ እርገጤ ከተኙበት በ11፡30 በሚስታቸው ወይዘሮ የሻሽ ወርቅ አማካኝነት ከእንቅልፋቸው ተቀስቅሰው ወደ ሳሎን እንዲመጡ ተደረጉ፡፡ ጋሽ እርገጤ ብስጩ እና ቁጡ ሰው ቢሆንም ወደ ሳሎን ሲያመሩ ግን በጣም ደንግጠዋል፡፡ ጋቢያቸውን አገልድመው ሳሎን ሲደርሱ ሶስት ሱፍ የለበሱ ሽማግልዎች ከፊታቸው ቆመው አገኟቸው፡፡ ይበልጥ ደነገጡ አፋቸው እየተሳሰረ ‹ምነው ምን ተፈጠረ?› ሲሉ ሶስቱን አዛውንት ጠየቋቸው፡፡ ሆኖም ግን መልስ አላገኙም ጋሽ እርገጤም እግራቸውን ብርክ ብርክ ይላቸው ስለጀመር ከሶፋው ላይ ተቀምጠው ‹እሺ ተቀመጡና እንነጋገር› አሏቸው፡፡ ሶስቱ አዛውንትም ‹የመጣንበትን ሳንናገር አንቀመጥም› ብለው መለሱ፡፡ ጋሽ እርገጤ ትግስታቸው ሞለቶ ሞለቶ ፀጉራቸው ጋር የደረሰ ይመስላል፡፡ ወይዘሮ የሻሽ ወርቅም በሳሎኑና በመኝታ ቤቱ መሀል ቆመው ‹አንቺ ታውቂያለሽ› እያሉ ወደሰማይ ያንጋጥጣሉ፡፡ ጋሽ እርገጤም ‹ታዲያ ምን ይሁን ትሉኛላቸው አመጣጣቹ እንደ መርዶ ነጋሪ በለሊት፤ አኳኳናቹ ልጅህን ለትዳር ስጠን አይነት፤ እንዴት ነው ነገሩ?› ቁጣ ቀላቅለው መናገር ጀመሩ፡፡
.
ከሶስቱ ሽማግሌዎች አንድኛው እየፈሩና እየተቡ ‹እእ እኛ የመጣነው እእ ልጆት ኤደን…› መጨረስ ተሳናቸው ከኪሳቸው መሀረባቸውን አውጥተው ግንባራቸው ላይ የተቸፈቸፈውን ላብ ይጠርጉ ጀመር፡፡ ‹እኮ ልጄ ኤደን ምን ሆነች?› ጋሽ እርገጤ ጠየቁ
ከሽማግሌዎቹ በእድሜ አነስ ሚሉት ‹እንዴ እኛ አላስረገዝናት የምን መርበትበት ነው፡፡ ያስረገዛት እዛ ተንጋሎ እንቅልፉን ይደቃል እኛ በምን ሀጥያታችን እንሽማቀቅ› ለራሳቸው ብለው ልባቸውን አጀገኑና ‹ልጆት ኤደን አርግዛለች› ነገሩን አፈረጡት፡፡ ነገሩን ሲያፈርጡት ጋሽ እርገጤ አይናቸው ፈጦ ነበር፤ ሁለቱ ሽማግሌዎች መሬት መሬት እያዩ መሬትን ሲያሽኮረምሙ ነበር፤ ወ/ሮ የሻሽ ወርቅ በሁለት እጃቸው ጆሯቸውን ደፍነው ነበር፡፡
.
ጋሽ እርገጤ ለረጅም ሰዓት አይናቸውን ካፈጠጡ በኋላ ‹ወይኔ እርገጤ› ብለው አንባረቁ፡፡ ሶስተኛ ጎረቤት ያለ ህፃን ልጅ በድምፃቸው ባኖ ማልቀስ ጀመረ፡፡ ሁሉም ተጨንቀዋል፡፡ ማነው ያስረገዛት? እገላለው ብለው የድሮ ጠብመንጃቸውን ሊያመጡ ሲነሱ ሚስታቸው ተንደርድረው እግራቸው ላይ ወደቁ ሽማግሌዎቹም ይለምኗቸው ጀመር፡፡
‹ኸረ ግዴሎትም ይረጋጉ፤ ቁጭ ብለን አውርተን መፍትሄ እናመጣለን፤ መቀጣትም ካለበት በህግ እንዲቀጣ እናደርጋለን እንጂ መንግስት ባለበት ሀገር ደም መፋሰሱን ምን አመጣው?› ከሽማግሌዎቹ አንዱ ሊያረጋጋቸው ሞከረ
‹መንግስት በኔ ልጅ ምን አገባው? ያገባኛል ካለም መንግስትን እራሱ አስረግዤ ነው ማሳየው› ለያዥ ለገላጋይ አቃቱ፡፡
.
እንደምንም ተለምነውም ተሸንግለውም ከተረጋጉ በኋላ በወጉ መሰረት ለጋብቻ እንዲበቁ ሽማግሌዎቹ ጥያቄ አቀረቡ፡፡
ጋሽ እርገጤም ‹ስለየትኛው ወግ ነው ምታወሩት? ከጣልያን ነው እንዴ የመጣችሁት እናንት ሰዎች? ጭራሽኮ ግራ እያጋባችሁኝ ነው፡፡ ቆይ ከሰርጉ በፊት ያረገዘችው ጥሎሽ መሆኑ ነው? እኔ አይኔ እያየ ይሄ ወሮበላ ልጄን አያገባትም› አሉ፡፡
በዕድሜ ትንሹ ሽማግሌ ‹በቃ አይኖትን ጨፍነው ልጆቹ ይጋባሉ› ለማለት ቃጣቸው ነገር ግን እሳት ላይ ቤንዚን አርከፍክፈው ነገሩን የብሔር ፀብ ላለማስመሰል ብለው ተዉት፡፡ ጋሽ እርገጤ ቢለመኑ ቢሰሩ ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ አሉ፡፡
‹ታዲያ ምን ቢሆን ይሻላል› አሉ እስካሁን ዝም ብለው የነበሩት ሽማግሌ
‹ቀልድ…ቀልድ ቢሆን ይሻላል› ጋሽ እርገጤ ፈጠን ብለው መለሱ::
.
.
.


ጥቅምት 2010 ዓ.ም

ቡሩክ ካሳሁን ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል👇
@burukassahunc


@wegoch
@wegoch
Forwarded from አንድነት ይሻላል ፨ ፍቅር ያሸንፋል
የእውነተኛ ፍቅር ትርጉም የገባው ሰው እንኳን ብሔር ቆጥሮ ሰውን ከሰው ለይቶ ሊጎዳ ይቅርና እንስሳት ላይ እንኳን አይጨክንም።
ያኔ በኛ ጊዜ
(ቡሩክ ካሳሁን)
እንደ ዛሬ ፈታና ማይሰረቅበትና ጃዋር ማይፈነጭበት ያኔ የኛ የትምህርት ጊዜ ዋነኛ የፈተና ፀር ገጀራው ነበር፡፡ አስረኛ ክፍል እያለን ገጀራው ለፈተና ጊዜ ሚያወጣው አሰላለፍ ሞሪኖን ሚያስንቅ አሰላለፍ ነው፡፡ እሱ ካወጣው የፈተና አቀማመጥ ማንም ወለም ዘለም አይልም፡፡ (ምን ያደርጋል ማትሪክ ላይ መንግስት በራሱ አሰላለፍ አስቀመጠንና ተበላ እንጂ፡፡) ለሁላችንም የምንቀመጥበትን ቦታ ከነምናልባት አስተማሪ ‹ተነስ› ቢለን ምናቀርበው ምክንያት ይነግረናል፡፡
አሁን ለምሳሌ መስኮት ዳር ላስቀመጠው ልጅ አስተማሪ መጥቶ ከቦታህ ልቀይር ቢለው ከልጁ ሚጠበቀው ገጀራው እንዳለው ‹ ብዙ ብርሀን ከሌለ አይነበበኝም› ማለት ብቻ ነው ከዛ በኋላ ገጀራው ጣልቃ ገብቶ ‹ታዲያ ማይታይህ ከሆነ እዛው ተቀመጣ› ብሎ ውሳኔ ያስተላልፋል፡፡
ገጀራው በጣም ብልጥ ነው፡፡ ራሱን ከክፍላችን ጎበዝ ተማሪ ኋላ ያስቀምጣል፡፡ እኔና ዱባለን የሰፈሩ ልጆች ስለሆንን ያው የጎሳ ፖለቲካ አደል ሀገሪቱን በ4ቱም አቅጣጫ ሚያዋስናት?¡ ከእሱ አቅራቢያ ያደርገንና ለሱ ከተላኩት መልሶች ርዝራዡ ይደርሰናል፡፡ ሳሮን በዚ ጊዜ ከገጀራው ጋር እጅና ጓንት አይገልፀውም ምናልባት ስጋና አጥንት ከገለፀው ትሆናለች፡፡ ሁል ጊዜ ሳሮንን ከጀርባው ነው ሚያስቀምጣት፡፡ አንድ ጊዜ ትዝ ይለኛል ዱባለ ከገጀራው ትይዩ ተቀምጦ መልስ ስጠኝ ብሎ እንባ ቀረሽ ልመና ሲለምነው ፅፎ ካዘጋጀ በኋላ ዞሮ ለሳሮን ሳትጠይቀው ሰጣት፡፡ የዱባለ ሀሞት ሲፈስ ፊቱ ላይ ይነበብ ነበር፡፡እጁን ሁላ አውጥቶ ቢናገር ምንኛ አንጀቱን ባራሰ ነበር፡፡ ምን ያረጋል ገጀራው ነዋ፡፡ ገጀራው ለፈተና ሰሞን ፂሙን አለቅጥ ያሳድጋል፤ አንገቱ ላይ ስካርፕ ጣል ያረጋል፡፡ ባጭሩ የዘመኑን ገጣሚዎች ይመስላል፡፡ ታዲያ እንዲ ሆኖ ከሩቅ ላየው ባንክ ሊዘርፍ እንጂ ፈተና ሊፈተን ሚመጣ አይመስልም፡፡ እሳት የለበለበው ብርጭቆ ወረቀት የመሰለ ፊቱ እንኳንስ ተቆጥቶና ተኮሳትሮ ፈገግታው ራሱ ቀልብ ይገፋል፡፡ የፊቱ ጥቅም የሚገባህ በፈተና ሰዓት ነው፡፡ በፈተና ሰዓት ፈታኛችን እኔና ሌሎች ተማሪዎች ላይ አራስ ነብር ሆኖ ለመተንፈስ ራሱ ሲያሳቅቀን ይቆይና ገጀራው ጋር ሲደርስ ግን የትዳር ጥያቄ የቀረበላት ልጃገረድ ይሆናል፡፡ በሙሉ አይኑ ገጀራውን አያየውም፤ አይኑን ይሰብራል፣ ያስለመልማል፡፡ ያኔ ገጀራው ጋቢናውን ተማምኖ ካፅናፍ እስከ አፅናፍ ፈታ ብሎ ይኮርጃል፡፡ አስተማሪው በጣም ሲመረው ገጀራው አጠገብ ይሄድና ስለ ኑሮ፣ ኳስ፣ ንግድ ይቀባጥራል፡፡ በአጭሩ አንድ ያልታወቀ ጋዜጣን ይመስለኛል፡፡ በዚህ ሰዓት ገጀራው ፈተናውን ሰርቶ ካልጨረሰ ‹ይቅርታ እየሰራው ነው ሀሳቤን እየሰረቅከኝ ነው› ብሎ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ አስተማሪውን ወደ ጥጉ ይመልሰዋል፡፡ በአጭሩ ገጀራው ማለት የፈተና ሰዓት ባልቻ አባ ነፍሶ ማለት ነው፤ ድል ሳያረግ አይመለስም፡፡
ያን ሁሉ ጀብዱ የሰራ ሰው ታዲያ ምን ያደርጋል በ11ኛው ሰዓት መንግስት ጉድ አደረገው፡፡ ማትሪክ በምንፈተንበት ሰዓት የክፍላችን ጎበዝ ልጅ ክፍል ሞልቶ ተቆርጦ ሌላ ክፍል ገባ፤ ገጀራውን ውሀ በላው፡፡ ፈታኙ ገጀራውን እንደልቡ እንዲፈነጭ ቢፈቅድለትም ‹መልስ ካልተሰጠ ምርጫ ምን ያደርጋል?› አደል ኤፍሬም ስዩምስ ያለው፡፡ አንድ ሙሉ ክፍል ተዟዙሮ ኮርጆ አንድ ሙሉክፍል አይነት ስህተት ከፍንጥርጣሪ መልስ ፈተናው ላይ አሰፈረ፡፡ ገጀራው በአስደማሚ ውጤት በዝረራ 10ኛ ክፍል አቋረጠ፡፡ የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ተስፋ ማንሰራራት የጀመረው ያኔ ይመስለኛል፡፡

መስከረም 2010 ዓ.ም

ቡሩክ ካሳሁን ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል 👇
@burukassahunc


@wegoch
@wegoch
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6 እነሆ ወቅታዊ ጉዳዮችን እና መዝናኛን አካቶ ለንባብ በቅቷል።
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6.pdf
4.3 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6

💰 ፓኬጅ ከገዙ በብር 1.20 ብቻ 💰
2024/09/28 07:25:05
Back to Top
HTML Embed Code: