Telegram Web Link
# ኦሮማራ_ከፖለቲካ በላይ ነው!!
-------
ጭርርርር ሲል ገበያ የለም!! ሰላም ሲሆን ኮንትሮባንድ የለም! ፍቅርና አንድነት ሲመጣ
አቅመ-ቢሶችና አጋሰሶች በፖለቲካ ስልጣን ታከው፣ በባለስልጣን ወንበር ተጋርደው ሽቅብ
ወደ ላይ በሃብት አይመነደጉም!!
ብዙ ህዝብ በአንድ መቆም ሲጀምር ጥቂቶች የመጋረድና የመሸፈን ፍርሃት በቁማቸው
ያቀልጣቸዋል። ስለሆነም ብዙሃን እንዳይጠጋጉ፣ እንዲባሉና ትርምስምስ እንዲሉ ጥቂቶች
አይናቸው ርግብ ሳይል ቁመው ይውላሉ፣ ቁመው ያድራሉ።
ብዙዎች በተፈጥሯቸው የጥቂቶችን ያከል አይጠጋጉም፥ ክፉ ጥቂቶች ይሄን ተፈጥሯዊ
ክፍተት በስሌት ይጠቀሙበታል። ልዩነቱን በማስፋት የብዙዎችን እድል ያመክናሉ።
ይበላሉ!!
አማራና ኦሮሞ ትሥራቸው ደም፥ ታሪክና ባህል ሆኖ ሳለ ተጽፎ የተቀመጠላቸውና
የተነገራቸው ክፉ ትርክት የጋራ የሚባል ነገር የሌላቸው ምስራቅና ምእራብ
አስመስሏቸዋል!! !አንድ ነን" ሲሉ "እሳትና ጭድ አደላችሁን" የሚሉ ምንዱባን አንገታቸውን
እንዲያስደፏቸው ሆኗል። "አንድ ነን" ሲሉ ከምላሳቸው እስከልባቸው ያለው የመተማመን
መንገድ ስሉጥና እሙን አጭር እንዳይሆን ሆኗል።
ኦሮሞና አማራ ከዛፍ ቅርንጫፍና ስር በላይ ናቸው። ውህደታቸው የስጋና ነብስ እንጂ
ሲያጥቡት የሚጠራ የስጋና ደም አደለም። ሰሜንና ምእራብ ሸዋ፥ ወሎ፣ ጎጃምና ሃረር፣
ጅማና ኤሊባቡር ላይ ሁለቱ ህዝቦች ውህደታቸው ከመገመድ በላይ ነው።
ሁለቱ ህዝቦች በጋራ ሲቆሙ ጥቂት ክፉዎች የክፋት ስለታቸው መክተቻ አፎት ያጣባቸዋል።
የክፋት ጭቅቅታቸው ማጣፊያ ያጥረዋል። ስለሆነም ሳይታክቱ የሁለቱን ህዝቦች ቀዳዳ
ይሰፋሉ፥ ቁስል ይነካካሉ፣ ብሶት ያከፋሉ። የዚህ ውህደት ጣጣ የማይሰማቸው ጫፎች
በዛም በዚህም ይወጥራሉ። ጅግጅጋንና ሃዋሳን ያለየ በዚህ ጨዋታ ጠንክሮ ይሰለጥናልና!!
ልብ ያለው ልብ ይበል፣ ትንንሽ ልዩነቶችን በማጦዝ ትልቁን ህዝብ ዳግም ለማንኮታኮት
ጅማታቸው እስኪበጠስ የሚመናተሉ ክፉ ነብሶች ከበውናል። ይሄን ሴራ ደፍቆ መጭዋን
አገር መስራት የትውልዱን ሁሉ ጣጣና መከራ እድሜ ያሳጥራል!!!!!!



ድንግል ሳቅ!!!!!!!


አጥንት የሚያለመልም፣ ነፍስያን የሚያረሰርስ ድንግል
( geniune) ሳቅ!!!!!! እንደ ሉባንጃ ጭስ፣ እንደ አሽኩቲ
መአዛ፣ እንደ አርቲ ጠረን፣ እንደ ጠጀ ሳር ሽታ፣ ቀናችሁን
ከዳር እስከ ዳር ያውደው ዘንድ ተመኜሁላችሁ!!!!!


ሽብርቅርቅ፣
ድምቅምቅ፣
ፍልቅልቅ ያለ፣ በሳቅና በደስታ የተሞሸረ፣ የፍቅር ቀን
ጀባ!!!!!!!



@balmbaras
@wegoch
@wegoch


ምግብ፣ ልብስ፣ መጠለያ የሌለው ህዝብ እንዴት ዘረኛ ሊሆን ይችላል? ኑሮ ሶስት ለባዶ የሚመራን ህዝቦች ማለት እኮ እኛ ነን:: እየራበን፥ ቀዳዳ ሱሪ ለብሰን፥መፀዳጃ ቤት በሌለው ጣራው በሚያፈስ ቤት የምንኖር! ግን ዘረኞች! በሌሎች ሀገራት ሰዎች የበሉትን ምግብ ለማቃጠል ሲሮጡ ይውላሉ:: እኛ የዕለት ጉርስ ፍለጋ ስንሮጥ እንዉላለን:: ማታ ቤታችን ገብተን ጦማችንን ዜና እንሰማለን ከዛም እየራበንም ቢሆን የኛ ብሄር ከሌሎች እንዴት እንደሚበልጥ እያሰላሰልን እንተኛለን:: ልጆቻችንን ማብላት እና ማልበስ አቅቶን ከት/ቤት ይቀራሉ በየቤታችን ግን ብሄርተኝነትን እናስተምራቸዋለን:: ከአዲስ አበባ ብዙም ሳንርቅ በ21ኛው ክ/ዘመን ወገባቸው እስኪጎብጥ እንጨት የሚሸከሙ እናቶች ማየት የተለመደ ነው:: ጧሪ ያጡ አባቶች
አደባባይ ወጥተው ላለመለመን ኢትዮጵያዊ ክብራቸው ይዟቸው ቤታቸውን ዘግተው በረሀብ ይሰቃያሉ:: ወጣቱ ደግሞ በዚህ በኩል ከተማ መሀል ከትሞ ፥ አንዱ ግብዝ ምስኪን ወንድሙ ብልት ላይ ውሀ በኮዳ ያንጠለጥላል ሌላው ደሞ ያንተን ቋንቋ መስማት አልሻም ብሎ በየመድረኩ የውሀ ኮዳ
ይወረውራል:: እስከ መች እንዲህ እንቀጥላለን? ወጣቱ፣ አዛውንቱ፣ ህፃናት ሳይቀሩ ፖለቲከኛ ሆንን እኮ:: ሁሉ መንገድ ቀያሽ እንዴት ይሆናል? ምሁራን ዕውቀታቸውን እና እድሜያቸውን ለፖለቲካ ትግል ከገበሩ መች ነው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትግል አድርገን የነቃ እና ጠግቦ የሚያድር ማህበረሰብ የምንፈጥረው? ኧረ ጎበዝ ለልጆቻችን የተሻለ ነገ እንፍጠር::

(ግሩም ሰይድ)

@lula_al_greeko
@getem
@getem
ዘሀራን ቡዳ በላት...ክፍል አንድ
( በ Natnael Getu )

በዝምታዋ የምትታወቀው ቆንጅየዋ ጎረቤታችን ዘሀራ እሪሪሪሪው ብላ ጮኸች! ግቢውን ድብልቅልቅ አደረገችው..ኡኡ አለች! እንኳንስ ኡኡታና ከኡኡታም የዘሀራን ኡኡታ ቀርቶ ፈስ ማዳነቅ የሚወደው የሰፈር ሰው ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ወደ ግቢው ተንጋጋ ። አክስቷ እትዬ አሰለፈች ባለቤታቸውን ተከትለው ዘሀራ ወደምትኖርባት
ትንሽዬ ሰርቢስ ከቤታቸው ትልቅ ደረጃ በቀሚሳቸው ውስጥ እንደ ኖህ
መርከብ እየተንሳፈፉ ወረዱ ። ዘሀራን ሲወዷት ከነፍሳቸው ነው ... ለነገሩ ዘሀራን የማይወድ ማን አለ ? እኔ ራሱ የእሪታዋን ድምጽ እንደሰማሁ ነበር በብርሀን ቅፅበት ወደ ሰርቢሷ የበረርኩት ።
እንደደረስኩ ከሰርቢሷ ውሀ ልክ ዝቅ ብሎ ያለው ሰፊ ቦታ በተከራዮችና ከ ግቢው ውጭ በመጡ በርካታ ሰዎች ጭንቅንቅ ብሎ ጠበቀኝ፥ ከምኔው እንደከበቧት ፈጣሪ ይወቅ ! እንደምንም እየተጋፋሁ ወደ መሀል ስገባ... ዘሀራ በግራና በቀኝ በኩል ተይዛ የባጥ የቆጡን
እየቀባጠረች ነው ። እትዬ አሰለፈች ፊታቸው ሀዘን ተላብሶ እንባ እየተናነቃቸው ያጉረመርማሉ
" ወይኔ ልጄን ! ...ወይኔ ልጄን..! ድሮም መፍዘዝና መተከዝ ስትጀምር ፈርቼ ነበር..ምነው ፈጣሪዬዋ መኣቱን አወረድክብኝ? " አሉ እያዘኑ "እስቲ ተረጋጉ...እንደው ማዘን ምን ይፈይዳል ?" አለ ጣሰው ወ/ሮ አሰለፈችን ከወደ አንገታቸው ለማፅናናት በሚመስል መልኩ ሊያቅፍ እየሞከረ ጋሽ ተሾመ የአሰለፈች ባለቤት ..የጣሰውን እጅ እየመነጨቁና እየገፉ "ወይድ አንተ ደግሞ...ተረጋጉ ይላልዴ?..ቡዳ በላት እንጂ ውሻ ነከሳት የተባለ መሠለህዴ? " አሉና ኩም አደረጉት ። ጣሰው ቂጡን ውሻ ነክሶት ለሁለት ሳምንት ቤቱ ውስጥ ሲማቅቅ ነበር ! እኔ ነገሩ ግር ብሎኝ አይኔን በቀጥታ ወደ ዘሀራ ስወረዉር
ደነገጥኩ...ዘሀራ አስፈራችኝ። አይኗ ፍጥጥ ብሎ የግንባሯ ጅማት
ተወጣጥሯል ። ዘሀራ ከክፍለ ሀገር የመጣችው ለትምህርት ነበር ። አክስቷ እትየ አሰለፈች "ተማሪ ሰርቢስ ይወዳል..ቤት ውስጥ ከሆነ አያጠናም"
ብለው ከሰባቱ ሰርቢሶች ውስጥ ጫፍ ላይ ያለችዋን ሰርቢስ ሰጧት ። ሰርቢሷ እኔን ወደ ቤቴ በሚወስደኝ መንገድ ፊት ለፊት ስትሆን ወደ ቤቴ በገባሁ ቁጥር የሰፈሩ ቤቶች ተጠጋግተው መሠራታቸውን እያመሠገንኩ አይኔን አሾልኬ አያታለሁ.. ከፈገግታ ውጭ ድምጿ አይሰማም። ቀይና ክብ ፊት አላት...ብዙ ጊዜ ስታየኝ ፈገግ ትልና ከሁለት የተከፈለ ብርቱካን ትመስላለች ..ብዙ ነገሯ ደስ ይለኛል ። ዝምታዋም ጭምር...አሁን ግን ዝምታዋ ተሰብሮ እንደ ጉድ እየለፈለፈች ነው ። ..መንደርተኛውም አብሯት በቡዳ የተበላ ይመስል ይንጫጫል ። ከዛም ከዚም ንግግር ይሰማል "ግንባሯን ለምን በጋለ ብረ አንተኩሳትም?" አለች ...የሰፈሩ የቅናት ዛር ያጥወለወላት ብርቱካን ። እሷ የማትቀናበት ነገር የለም።
የምትቀናበት ነገር ብታጣ ..ሰዎች ሁሉ የሚቀኑበት ምክንያት አላቸው እኔ ግን
የለኝም ብላ ትቀናለች ። "አሁን አንቺ ለእሷ አዝነሽ ነው? ቅናታም !..ፊቷን ለማበላሸት ነውጂ " አለ አሉላ ጠጆ ....ብርቱካንን እየገላመጠ ።"እሷስ ቀንታ ነው ሆኖም ግን....ጠባሳው የሚወጣው የበላው ሰው ላይ ነው" አለ ግርማ ዛፍ ቆራጩ! " እንደዛማ ከሆነ ጥሩ ነው...ግን ብረት ማጋል ጊዜ ስለሚወስድ ለምን በኤሌትሪክ አናንዘረዝራትም ? " ጸጋ..የመብራት ሀይሉ ሰራተኛ ነው ይሄን ያለው..ትልቅ ሀሳብ እንዳመነጨ ሰው ጭንቅላቱን በኩራት ነቀነቀ ። " ምጽ! ስለየትኛው መብራት ነው የምታወራው? ...የሚጎዳው የበላት
ከሆነ ..በሲሊንደር ልናጋያት..ወይም ከፎቅ ልንወርውራት እንችላለን" ይሄን ደግሞ ሩቅያ ቀውሷ ነች ያለችው ። ከሳዑዲ ከተመለሠች በኃላ
እንደመቀወስ አድርጓታል ። አባቷ ኑር ሁሴን ጤናዋን ለመመለስ ስንት ጣሩ ...አልተሳካም እንጂ! "ምንድን ነህ ተናገር ቡዳ ነህ?" ይላል መኮነን። መኮነን ሰፈሩ ውስጥ በሌብነት የሚጠረጠር ሰው ነው ። ከአንድም በተደጋጋሚ ጊዜ ሌባ ነው እየተባለ ተወርቶበታል ። ከዘሀራ ፊት ቁሞ ማንን ነው ተናገር የሚለው
ብዬ ግራ ገብቶኝ ነበር ። መኮነን የዘሀራን አውራ ጣት ጥብቅ አድርጎ ይዞ ይጠይቃል ። ዘሀራ ጎርነን ባለ የወንድ ድምፅ ትመልሳለች ።
" ቡዳ ነህ አይለህም ? "
" አዎ...ቡዳ ነኝ" ዘሀራ ወፈር ባለ ድምፅ ። ማለቴ ሲታይ ዘሀራ ናት የምታወራው ...ግን የበላት ሰው ነው የሚናገረው ይላሉ ። ግራ የሚያጋባ ነገር ነው ።" ማን ነህ? ከየት ነው ያገኘሃት..? " " አለባቸው ነኝ...ኣ...ኣለባቸው "
የሰፈራችን ቅብጥብጧ ሰአዳ በቀጭን ተስረቅራቂ ድምጿ " አለባቸው ማን..አለባቸው ሉሌ ነህ? " ...ሰፈርተኛው ገረመማት ። አለባቸው ሉሌ ሠፈራችን ውስጥ የታወቀ ሀብታም ነጋዴ ነው ። " ..ስራህ ምንድን ነው?...ስልክ ቁጥርህን ንገረኝ " አለች ቀጥላ ...ግማሹ ሰው በሳቅ ፍርስ አለ ።... " ምን ያስቃችሇል...የማውቀው ከሆነ ብዬ ነው" አለች ።
" ይቺን ከውካዋ አፏን አዘጉልኝ " አሉ አቶ ተሾመ ። መኮነን ቡዳውን ማናገሩን ቀጥሏል ።
" ዬት ነው ያገኘሃት..ተናገር?."..አውራ ጣቷን ጫን ብሎ በሚያስፈራራ
ሁኔታ እያያት ። " ተማሪዬ ናት...ተማሪዬ ናት !...ልትማር ስትመጣ ነው ያገኘሁዋት "
እግዚኦ አለ ሰዉ ።
እስካሁን ምንም ያላሉት እትዬ ብርጣሉ አፋቸውን በጨርቅ ሸፈን
አድርገው..."አለባቸው ዳምጤ...ያ ከውካዋ መምህር....ሰፈሩስ እዚሁ ከኛ ሰፈር ትንሽ አይደልዴ ፈንጠር የሚለው?...እሱማ ስንቱን የበላው ታዋቂ ቡዳ ነውኮ...ቀድሞ ከሚያስተርምበት ት/ቤትም የዲኔክተሩን ልጅ በልቶ ነው የተባረረው ሲሉ ሰምቻለው" ጉድ.. ጉድ! ተባለ ሰፈርተኛው ለዘሃራ ከንፈሩን መጠጠላት።
ይቀጥላል…

@gebriel_19
@wegoch
@wegoch
🔴🔴 #ሼር_ሼር_ሼር 🔴🔴

❗️ ❗️ #አስቸኳይ_የእርዳታ_ጥሪ ❗️❗️

🔴 ወገንን ለመርዳት ግዴታ የቡና ደጋፊ መሆን የለብንም ✔️
🔴 ሰው መሆን በቂ ነው !!!!

ወጣት #ሀያት_ኑሩ_ሁሴን የ18 አመት ወጣት እና #የኢትዮጵያ_ቡና ደጋፊ ስትሆን በደረሰባት የ ኩላሊት ህመም በሽታ ምክንያት ሁለቱም ኩላሊቶቿ መስራት እንዳቆሙ በ ህክምና ተረጋግጧል ።

#ቅዱስ_ጳውሉስ_ሆስፒታል በሳምንት 3 ጊዜ ዲያሊሲስ (የኩላሊት እጥበት) ይደረግላታል እሱም የምታወጣው ገንዘብ ከ 2250 ብር በላይ ነው ። ይህንንም ብሩም ከባድ ስለሆነ ጔደኞቿ በየቀኑ ትኬት 200 ብር እየሸጡላት ነው እሱም ከተሳካ ይሸጣል ።

እስከ አሁን ድረስ ዲያሊሲስ (የኩላሊት እጥበት) ላይ የቆየች ቢሆንም 7 ወር አልፏታል ግዴታ ንቅለ ተከላ መደረግ አለበት ይህንንም ለማድረግ ገና ፕሮሰስ ላይ ነች ።

ነገር ግን ንቅለ ተከላው ከተደረገ በኋላ የማይቋረጥ መድኃኒት መውሰድ አለባት ታድያ ይህንን ወጪ የሚሸፍን አቅም ስለሌላት በ አቅራቢያዋ ወደ ምንገኘው ወደ እኛ እህት ወንድሞቿ እጇን ለመዘርጋት ግዳጅ ሆኖባታል ።

እናም የእግር ኳስ ቤተሰቦች ስንት እህትና ወንድሞቻችን ወገኖቻችን እርዳታ እየፈለጉ ሰው ሳይደርስላቸው ህይወታቸው አልፏል የዚህችንም ህይወት እንታደገው ዘንድ ሁላችንም የ እህታችን እርዳታ ያስፈልጋታል በፍጥነት ሁላችንም የ እህታችንን ህይወት እንታደግ ።

አድራሻ ☞ #አውቶቢስ_ተራ ወረድ ብሎ ዜድ ዋይ ህንፃ ገባ ብሎ መካነ ሰላም ፊት ለፊት #አያት_ኑር_ሁሴን

ስልክ ቁጥር የ እናቷ -- 0911948682 #ሰአዳ

✔️ የባንክ ቁጥር #ኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ
➡️ 1000230747648 #ሰአዳ_እንድሪስ

#ሼር_በማድረግ_ሀላፊነታችንን_እንወጣ 🙏🙏🙏
ዘሀራን ቡዳ በላት
ክፍል ሁለት


(በ ናትናኤል ጌቱ)

👇👇👇
@wegoch
@wegoch
ዘሀራን ቡዳ በላት ...ክፍል 2
( በ ናትናኤል ጌቱ )
...
ዘሀራን አሁንም ግራ እንደተጋባሁ እያየሇት ነው ። ሁሉ ነገሯ ባንዴ ቅይርይር ብሏል ..ለስላሳው የፊቷ ቆዳ አስፈሪ ገጽታ ተላብሷል። ቅጥነቷ ብዙ ምግብ እንደማትመገብ ያሳብቃል... ግን
ገዘፈችብኝ..የሆነ የሚያስፈራ መግዘፍ ...ሂጃቧ ተገልጦ ለስላሳ ጸጉሯ በጨረፍታ ይታያል.. አንገቷ ላይ ያለው ሀብል አቧራ ቅሟል ። አስታውሳለሁ ይሄን ሀብል ለመጀመሪያ ጊዜ የመጣችም ቀን ለብሳው ነበር። እትዬ ብርጣሉ ስለ አለባቸው ዝነኛ ቡዳነት እንደተናገሩ ሠፈርተኛውም አብሮ 'አለባቸው ዳምጤ' የሚል ስም እያነሳ እያጉረመረመ ነው ። አሁን ማን ይሙት አለባቸው ዳምጤ የቡዳ ስም ይመስላል? ሳላስበው ከዚህ በፊት ያገኘሇቸውን አለባቸው የተባሉ ሰዎች አንድ ባንድ ለማስታወስ ሞከርኩ ። ለካ እስከዛሬ አለባቸው በሚል ስም የማውቀው አንድ ሰው ብቻ ነው !
..አለባቸው መኩሪያው : ከአንደኛ ክፍል እስከ አምስተኛ ክፍል ድረስ አብሮኝ የተማረ የሰፈሬ ልጅ ነበር ። አስታውሳለሁ እጅግ በጣም ንፍጣም ነበር ። እግዜር ሞኝነት እና ንፍጥን እንደሱ በገፍ የቸረው ማንንም አላየሁም ! የሁላችንም ወላጆች ግቢው ውስጥ ይሰሩ ስለነበር በእረፍት ሰአት እየጠሩ የሆነ ነገር ያደርጉልናል ። ለምሳሌ የእኔ እናት ሁሌ ትጠራኝና አሳምቡሳ ትገዛልኛለች ። የአቡሻ እናት ከጠራችው ቀሚሷን ዳብሳ መቀነቷ ስር የቋጠረቻትን ሳንቲም አውጥታ ቦንቦሊኖ ትገዛለታለች። የአለባቸው እናት ግን ሁሌ ካስጠራችው በቀሚሷ ንፍጡን ትጠርግለታለች።..ከሁላችንም የበለጠ ደስተኛ ይሆናል ። እየሳቀ ይመለሳል ..ወዲያው ንፍጡ ይመጣዋል..በልብሱ ይጠርጋል..ልብሱን
በንፍጥ በጣም አጨቅይቶት..ንፍጥ የመጥረግ አቅሙ ሲቀንስ ..ከእኛ ተገንጥሎ ወደ እናቱ እየሮጠ ይሄድና
"እማዬ ተመልከቺ...አፍንጫዬንኮ በድጋሚ አላበኝ " ይላታል። "አልቦህ
አይደለም ንፍጥህ መጥቶ ነው " ትለውና ትጠርግለታለች ። እናቱ ከሰዎች ጋር እያወራች " ስራሽ ምንድን ነው? " ከተባለች .. " የጽዳት ሰራተኛ ነኝ " ትልና እሱን የጎሪጥ ታየዋለች!..ሁሌ .ጠዋት ጠዋት ወደ ት/ቤት እንድንሄድ ልጠራው ስሄድ ቁርሱን ዳቦ በሻይ እየበላ
አገኘዋለሁ...ዳቦውን በሻይ እያማገ ይበላል ከማለት በንፍጡ ያምገዋል ማለት ይቀላል ። አንድ ጊዜ የሰፈር ልጆች በአካባቢያችን ካለው ወንዝ ዋና ለመዋኘት አብረን ወረድን...ጥቂት እየተንቧቸን እንደተጫወትን አለባቸው ወደ መሀል ገብቶ ሰመጠ..ተጯጯህን! አንዲት ወጣት ሴት ከነ ልብሷ ዘላ
ገብታ አወጣችው..ሲወጣ አለባቸው ተዘግቶ ነበር.. መተንፈስ የለ
ምን የለ..ጸጥ! ልጅቷ በአፉና በአፍንጫው አየር እየላከች ደረቱን እየተጫነች ከእንቅልፈ ውሀው አነቃችው..በአፉ ውሀ ቡልቅ ቡልቅ እያለ ወጣ.. እናቱ ታዲያ ተጠርታ እንደመጣች እየተዋከበች.."ልጄ እንዴት ነው?"
አለቻት ለልጅቱ። ልጅቷ ፈገግ እያለች.. "ጨው ጨው ይላል " አለቻትና ሁላችንም ሳቅን ። እና ታዲያ እሱ ቡዳ ነበር? እኔንጃ እኔ እሱ ዳቦ ሲበላ እንጂ ሰው ሲበላ አላውቅም። ሰፈርተኛው መንጫጫቱን አላቆመም..ዘሀራን የበላትን ቡዳ በራሷ
በዘሀራ አማካኝነት መኮነን ቃለ መጠይቅ እያደረገለት ነው ። ቅልብልቧ ሰኣዳ እና ቅናታሟ ብርቱካን አንዳንዴ በመኮነን ጥያቄ መሀል ይገባሉ ። ድንገት አንድ ሰው ተሽሎክሉኮ መጥቶ ትከሻዬን ነካ ሲያደርገኝ ወደ ሇላ ዞርኩ...ፕሮፌሰር አካሌ ናቸው። ፕሮፌሰር አካሌ እዛው ግቢ ውስጥ መሀል ላይ ያለቺዋን ሰርቢስ ተከራይተው የሚኖሩ መላጣ ሰው ናቸው ። መላጣ ብቻ ሳይሆኑ
ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጥንታዊ መነሻ መሆኗን የሚያትት ትልቅ መጽሀፍ አሳትመው የተሸለሙ ሰው ናቸው ። እንደ ፕሮፌሰር አካሌ መጽሀፍ ከሆነ... በምድር የሚገሰግሱ መኪናዎች ፥ በአየር ላይ ' ሚገለባበጡ የጦር ጀቶች እና የህክምና ጥበቦች ከሀገራችን በተሰረቁ ጥንታዊ የብራና መጽሀፍት ሚስጥር የተሰሩ ናቸው ። ፕሮፌሰር አካሌ ዘመን አመጣሽ ስልጣኔ የተባለውን
የፈጠራ ውጤት በሙሉ አባቶች ቀድመው ያሰቡት ነው ብለው በዝርዝር የጠቀሱ ሲሆን..እስካሁን ዝርዝራቸው ውስጥ የሌለው ኮንደም ብቻ ነው ።
"ይሄ ቡዳ ግን እንዴት ይመስልሀል?" አሉኝ "እኔንጃ ግራ የሚያጋባ ነው" አልኩ ...የእውነቴን ነው! ከፊት ለፊቴ ዘሀራ በሰዎች ተከባ እየጮኸች ነው..የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሰው በልቷት ነው ብሎ ማመን አይከብድም?... "እኔ ግን አንድ ነገር እያሰብኩ ነው?" አሉኝ ፕሮፌሰር አካሌ መነጸራቸውን ከፍና ዝቅ እያደረጉ.. "ምን?" አልኩ
"እንደምታየው ዘሀራን ሲያናግሯት የሚመልሰው የበላት ሰውየ ነው "
"እና" አልኩ ምን ለማለት እንደፈለጉ በውስጤ እየገመትኩ
" ያው እንደምታውቀው ነጮች የእኛን ቀደምት ባህላዊ ስልጣኔ ንቀን ስንጥለው እነሱ ወደ ዘመናዊ እየቀየሩ መልሰው ለእኛ እየሸጡልን ነው
"
"አዎ ከእርሶ መጽሀፍ ላይ አንብቤአለሁ" አልኩ
" አየህ አሁን ይሄ አለባቸው የተባለው ቡዳ በዘሀራ አማካኝነት በቦታ ከራቀው ሰው ጋር መነጋገር ..ጥያቄ ሲጠየቅም መልስ መስጠት ችሏል ".
አሉኝና ዘሀራን ትክ ብለው አይተው ማስታወሻቸው ላይ የሆነ ነገር ሞንጨር ሞንጨር እያደረጉ " እንግዲህ መቸም ፈረንጅ የስልክ ቴክኖሎጂን የመፍጠር ሀሳብ የመጣለት በቡዳ የተበላች ኢትዮጵያዊት ሴት አይቶ እንደሆነ እሙን
አይደለም ? አየህ አባቶች ትልቅ ነበሩ..ምናልባት ይሄን የቡዳ መንፈስ ለስለላ ቴክኖሎጂ ሲሉ ፈልስፈውት ይሆናል ። በድሮ ጊዜ የሀገራችን ሰዎች
ጠላትን እንደ አሁኑ ሲመጡ በመከላከል ሳይሆን እየሄዱ በማጥቃት ነበር የሚያጠፉት። ብዙ ጊዜ ውጊያቸው ረጅም ጉዞ ስለሚጠይቅ ከሰራዊቱ ቀድሞ የሚገሰግስ አንድ ሰላይ ይልካሉ ...አየህ..ይህ ቀድሞ የተላከው ሰላይ እስኪመለስ ድረስ ረጅም ጊዜ ስለሚፈጅ. ..አስቀድመው ከሰራዊቱ ውስጥ አንዱን ከሰላዩ ጋር የሚያገናኝ የቡዳ መንፈስ ይተክሉበታል...ምናልባትም ያኔ ሰው በቡዳ ሲበላ ኤንዳሁኑ 'ስምህ ማን ነው ተናገር' አይባል ይሆናል ምናልባትም
ያኔ የነበሩት ጥያቄዎች እንዲህ ይሆናሉ -ማሽላ ሀያ ሶስት ( ማሽላ ሀያ ሶስት ለስለላ የተላከው ወታደር የሚስጥር ስም መሆኑ ነው )..ይሰማል? ...አዎ ይሰማል!....ተራራው ላይ ምን ያህል የጠላት ጦር አለ?...ጌታዬ ዘመናዊ ጎራዴና አዳዲስ ጩቤዎችን የታጠቁ ወደ መቶ የሚቆጠሩ ወታደሮች ይታያሉ ...' ይባል ይሆናል ያኔ!..አሁን ለምን ዝምብሎ
መበላላት ተጀመረ ያልኸኝ እንደሆነ..ያኔ መንፈሱን ለጥሩ ነገር ተጠቅመው ሲመልሱት አንዳንዶች ግን ለምቀኝነትና ሰውን ለማስለፍለፍ አዋሉት ። ፈረንጅ ግን ይህን አይቶ ስልክ ሰራ...አባቶች የተኛ ሰውና ቡዳ የለከፈውን ሰው የሚቆጣጠሩት በአውራ ጣት
ነበር...አሁን ደግሞ ፈረንጅ ስልኩን በመክፈቻና በመዝጊያ ይቆጣጠረዋል ፣ የሞባይል ስልክ ባውራ ጣት አይደል የሚነካው? " ፕሮፌሰር ማስታወሻቸው ላይ ትልቅ ነገር እንዳገኘ ሰው በተመስጦ
ከሞነጫጨሩ በኃላ ቀስ ብለው በመጡበት እየተሽሎከለኩ ወደ
ሰርቢሳቸው ሄዱ ። እኒህ ፕሮፌሰር ግራ እንዳጋቡኝ ነው ..እስቲ አሁን ስልክና ቡዳን ምን አገናኘው? የግድ ሁሉንም ነገር ድሮ ኢትዮጵያ ሰርታዋለች እያሉ መከራከር ጥሩ ነው? ፕሮፌሰሩ ወደ ሰርቢሳቸው እንደገቡ ቀስ በቀስ ዘሀራን የከበቧት ሰዎች እየተበተኑና ወደ ቤታቸው እየገቡ ከዘሀራና ከቤቱ ባለቤቶች( ወ/ሮ አሰለፈች እና ጋሽ ተሾመ) በስተቀር እኔ ቀረሁ.....

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
ወደ ቤቴ ከመሄዴ በፊት ጋሼ ተሾመ ትካሻቸው ላይ አስደግፈዋት ወደ ሰርቢሷ የምትገባውን ዘሀራን ለማየት አይኔንላኩ...ቅድም አቧራ ቅሞ ያየሁት ...ሀብሏ የለም..በፍጥነት ወደ ኃላ ተመለስኩ...መኮነን እጁን ኪሱ
ውስጥ ከቶ ወደ ግራ ሲታጠፍ አየሁት...
.
.
.
ይቀጥላል

@Lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
📙“ኢትዮጵያ” ማለት በአይሮግሊፊክ አትኦፕቢያ “የበላይኛው የእውነት አገር” ማለት ነው፡፡
📙“ሳባ” ማለት “የመንፈስ ልጅ” ማለት ነው፡፡
📙“ጋላ” ማለት ለቧልት እንደሚባለው “ሃይማኖት የሌለው” ማለት ሳሆን ካራ “የእግዚአብሔር ፀሐይ ፋና” እንደማለት ነው፡፡
📙“ዐማራ” ማለት በሻዕቢያ ቧልት እንደተባለው “ወፈፌ” ወይም
📙“ፉዞ” ማለት ሳይሆን “ዓም ሀራ” ወይም “የካም ሰራዊት ፀሐይ”
እንደማለት ነው፡፡
📙“ሃማ ሴን” “የካምን ወገን ዝርያ” እንደማለት ነው፡፡
📙“አጋሜ” ማለት በቧልት እንደሚባለው “ለማኝ” ወይም “ቆሻሻ” ማለት ሳይሆን “አጋ ሃሜ” “ታላቅ የካም ወገን” እንደማለት ነው፡፡
📙“እግዚአብሔር” ማለት “እግ-ዘ-አብሔር” “ታላቁ የምድር አባት” ማለት መሆኑን፣ “ጋዳ” ማለት “ካ አዳ” “የእግዚአብሄር ሥርዓት” ማለት ነው ፡፡
ፀጋዬ ገ/መድህን


ምንጭ፡- ጢቢያ መፅሄት ቅጽ 5፣ ቁጥር 11፣ 1990
@gebriel_19
@wegoch
@wegoch
መልመጃ 3 - ባዶ ቦታውን ሙሉ
ቀጣሪ: እኛ የፈለግነው ሳይንስ አስተማሪ ነበር። አንተ የተማርከው ሙዚቃ ነው።
ተቀጣሪ: ምን ችግር አለው? እየተማርኩ አስተምራለሁ።
ቀጥሪ፡ ከዚህ በፊት የት ነበር ያስተማርከው?
ተቀጣሪ፡ ---------------

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
<<እየውልህ ልጄ፣ ስለ ሰው ደግ ነገር መስማት ጤና ይሰጣል፡፡ እድሜንም ያስረዝማል፡፡
ስለ ሰው ክፉ ነገር መስማት ግን በሽታ ያመጣል፤ እድሜንም ያሳጥራል፡፡ ስለ ጠላትህ
እንኳን ክፉ ክፉውን መስማት አንተኑ ነው የሚጎዳው፡፡ ቀደምቶቻችን እንኳን ስለ ሰው ስለ
ሸይጣን እንኳ ክፉ መስማት አይጠቅምም ይሉ ነበር፡፡ ሸይጣን አንድ ጊዜ ሸይጥኗል፡፡
አይጠቀምም አይጎዳም፡፡ አንተ ግን የእርሱን ክፉ በመስማትህ ያምሃል፡፡ ዛሬ ደስ ያለኝ ስለ
ሰው ጥሩ በሚነገርበት ቦታ ስለጠራኸኝ ነው፡፡ ስለ ሰው ደግ ደጉን መናገርና መስማት
የሚጠቅመው ሰሚውን ነው፡፡ ሰው ሁሉ ይራራቃል እንጂ አንድ ሥጋ ነው፡፡ ያኛው ሰው
ሲያመው አንተንም ያምሃል፡፡ ጣትህ ወይም ዓይንህ ማለትኮ ነው፡፡ ስለዚያኛው ሰው ክፉ
መስማት ማለት ስለራስህ አንድ አካል ክፉ መስማት ማለት ነው፡፡ እስኪ ተመልከት ልጄ፡፡
አንድ ሰው መጥቶ እግርህ መጥፎ ጠረን አለው ቢልህ ቀኑን በሙሉ ጤነኛ ሆነህ
አትውልም፡፡ ስለ ወንድምህ ክፉ መስማትም እንዲሁ ነው>>
የምንወዳቸው ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ፤ ሳያቸው እንዲሁ ግምባራቸው ላይ
አብርሆታቸው ይታየኛል።


@balmbaras
@wegoch
@wegoch
እንደሰው እንተያይ
አንድ አስረኛ ክፍል እያለሁ ጓደኛዬ የነበረ ልጅ የም (ለጅማ ቅርብ ነው) የሚኖሩ አስገራሚ
አያት ነበሩት፡፡ ከነገረኝ ታሪኮች መሃል አንዱን አልረሳም፡፡ የአያቱን እርሻ የዝንጀሮ መንጋ
እየበላ ያስቸግረዋል፡፡ ዝንጀሮዎቹ በጣም ከመዳፈራቸው የተነሳ ትንሽ ልጅና ሴት ሁሉ
አይፈሩም ነበር፡፡ በዚህ የተማረሩት አያቱ አንድ መላ ፈጠሩ፡፡ እንደምንም ብለው
ከዝንጀሮዎቹ መሃል አንዱን ያዙት፡፡ ከዛም ቀይ ቀለም ቀቡትና ለቀቁት፡፡ የተለቀቀው ዝንጀሮ
ወደዘመዶቹ ሲሄድ ዘመዶቹ "የምን ቀይ ፍጥረት ነው የመጣብን" እያሉ ሲሸሹ፣ የተቀባው
ዝንጀሮ ደግሞ "ዘመዶቼ ሸሹኝ" እያለ ሲከተል እየተሳደዱ ከአካባቢው ርቀው ሄዱና በዛው
ጠፉ፡፡
____________
ይሄ ነገር በሰው ቢሆን ብላችሁ አስቡት፡፡ ቀይ ተቀብቶ የሚመጣ ጓደኛችሁን ከሩቅ ብታዩ
በመጀመሪያ "ምን አይነት ፍጡር ነው?" ትሉ ይሆናል እንደዝንጀሮዎቹ፡፡ መሸሽም
ሊያምራችሁ ይችላል እንደ ልባችሁ ሁኔታ፡፡ ግን ጓደኛችሁ "እረ እገሌ ነኝ፡፡ ችግር ደርሶብኝ
ነው" ብሎ ጮክ ብሎ ማውራት ቢጀምር ቆም ብላችሁ መስማታችሁ አይቀርም፡፡ ከዛም
ወደ መነጋገር፣ መግባባትና መረዳዳት ትሸጋገራላችሁ፡፡ ሰውን ከሌሎች እንስሳት አንድ
የሚለየው ሃሳብን መግለጽ ነው፡፡ ውጪው ሌላ ቀለም ስለተቀባ አትሸሹትም፡፡ ሰውን
በሙሉ የሚገልጸው አመለካከቱ፣ ውስጡ ሲጨመር ነው፡፡
ሌሎች እንስሳት ለዚህ አልታደሉም፡፡ አንድ ዶሮ ጫጩቷን ጭልፊት ሲመጣ መሮጥ
ካላሳየች ነገ ጫጩቷ የለችም፡፡ ተምራ የተረፈች ጫጩት ደግሞ ነገ ልጅዋን ከጭልፊት
ልጅ ስለመሸሽ ታስተምራለች፡፡ ሰው በእንዲህ አይነት primal instinct አይደለም መኖር
ያለበት፡፡ ሰው ከመለስ ዜናዊ ስላልተስማማ ከሰምሃል መለስ መሸሽ የለበትም፡፡ የልጅ
አስተሳሰብ ከአባት ይለይ ይሆን አንድ ይሆን ተነጋግሮ መለየት አለበት፡፡ ዉጪን ብቻ እያዩ
መቧደን የሰው አይደለም፡፡
ሰው ከተወለደበት ቦታ ወጥቶ ተዘዋዉሮ ነግዶ ተለዋውጦ ይኖራል እንጂ በሽንቱ አስምሮ
"ከዚህ አትለፍብኝ እኔም አላልፍም" አይልም፡፡ በዚህም ልውውጥ መሃል አመለካከቱም
አብሮ ይቀየራል፡፡ ከኢትዮጲያ ወደ አሜሪካ ብመጣ ኖሮ ምናልባት አሜሪካ ተራማጅ ሃገር
ትመስለኝ ይሆናል፡፡ በማሃል ኔዘርላንድስ እያለሁ በደንብ የተለጠጠ ተራማጅ አስተሳሰብ
ጋር ስለተላመድኩ የአሜሪካ ፓለቲካ በጣም ወግ አጥብቂ ይኖንብኛል ባብዛኛው፡፡ እናም
አይደለም የብሄር የሰው አመለካከትም ቋሚ የለም፡፡ ጠላት ነው የምትለውን ሰው
ተነጋግረህ ወዳጅ ማድረግ ትችላለህ፡፡ ቀበሮና በግ ግን በታምራቱ ወይ ሰው አላምዷቸው
ካልሆነ ወዳጅ አይሆኑም፡፡ እነሱም ቢሆኑ ሰው አብሮ ካሳደጋቸው ወዳጅ ሊሆኑ ግን
ይችላሉ፡፡ እና ሰው እንዴት አርጎ ነው "ከዚህ ዘር የሆነ ጠላቴ ነው፤ ከዚህ ደግሞ ወዳጄ
ነው" የሚለው?
እናም ራሳችሁም ተቀብታችሁ ይሁን ቀብተው ለቀዋችሁ በቀለም መደራጀት የምትፈልጉ
ስለ ብሄር ፓለቲካ ያለኝ አመለካከት ይህን ይመስላል ማለት ነው፡፡ እንደዣ ኖ!
ይህ አስተሳሰብ አካባቢ ለማልማት እና ለተመሳሳይ ጉዳዮች መደራጀትን አይከለክለኝም፡፡
በተመቸኝ ቋንቋ መናገርና ያማረኝን ባህል መከተልንም አይከለክለኝም፡፡ ለምሳሌ አካባቢዬ
ብዙ ወላይትኛ ተናጋሪ ስለማያጋጥመኝ youtube ላይ ሁሉ ሄጄ ሰማለሁ፡፡ የሚያውቅ ሰው
ሲያጋጥመኝ እንዳልረሳ በዛ ማውራት መርጣለሁ፡፡ ሲዳምኛም ትንሽ ለምጄ ያልቀጠልኩት
ይቆጨኛል፡፡ ወላይትኛም ሆነ አማርኛም ወይም እንግሊዘኛ እንደ አስፈላጊነቱ
የምጠቀምበት እንጂ የቱም የመላእክት ቋንቋ መስሎ አይታየኝም፡፡ ግን ደግሞ እያንዳንዱ
ቋንቋ የራሱ ስሜትና ድባብ አለው፡፡ ሌላም ሰው ያደገበትን ቋንቋ ባይረሳ ጥሩ ይመስለኛል
ብቻ እኔን በማልሰማው አይማኝ እንጂ ፡፡ ችግር የሚሆንብኝ አንድ ሰው በዘሩ ብቻ
የተነሳ ወዳጄ ወይም ጠላቴ ይሆናል የሚለውን አመለካከትና በዘር ተደራጅቶ ፓለቲካዊ
ፉክክር ማድረግ ነው፡፡ ላደግክበት ለኖርክበት አካባቢ ማሰብ ችግር ያለው አይመስለኝም፡፡
መቼስ መጀመሪያ የማስበው ለራሴ ነው፡፡ ከዛም ለቤተሰቤና ለማውቀው ዘመዴ፡፡
ከማላውቀው አንድም ቀን ካላየሁት ዘመዴ ግን አብሮኝ ያደገ ጓደኛዬ ይቀድማል፡፡
ሲቀጥልም ለኖርኩበት አካባቢ አስባለሁ፡፡ ሃዋሳ እንደመኖሬ ለሃዋሳ አስባለሁ፡፡ አብሮኝ
የተማረ ጎጃሜም እኩል ያስባል ስለ ሃዋሳ፡፡ ወላይታ ትንሽ ልጅ ሆኜ በመኖሬም ስለዛ
አካባቢ ይገደኛል፡፡ ወላይታ ሶዶ ረጅም ጊዜ የኖሩ አያቶቻቸው ጉራጌ የሆኑ ሰዎች ደግሞ ከኔ
በላይ ባለቤት እንደሆኑ አስባለሁ፡፡ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመማሬ ስለ አርባምንጭ
ይገደኛል፡፡ ስለሳሪስም ስለ ሳርቤትም በኖርኩበት በወደድኩት ያህል እንደዛው፡yከብዙ
ኢትዮጲያዊ ጋር የምጋራትም ኢትዮጲያም እንደዚሁ፡፡ እነዚህ ሁሉ ዘር ቆጥሬ
የምድረስባቸው ሳይሆን ስለኖርኩ ከህብረተሰቡ ጋር የተጋራሁት ትዝታና ወዳጅነት ስላለኝ
ነው፡፡ ጎንደር ያደጉ ልጆችም ስለጎንደር ባያስቡ ነው የሚገርመኝ፡፡ ጅጅጋም ባሌም
መቀሌም ያደጉ ልጆችም እንደዛው፡፡

((( ተመስገን ማርቆስ ))


ሸጋ ሸጊቱ ጁምኣ!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Forwarded from SPACE COMPUTER
/ ሲመት/ ምርጥ የአማርኛ ፊልም

🍿
በአይነቱ እና በይዘቱ ለየት ያለ ታሪክን ወደ #18ኛው_ክፍለ_ዘመን ተመልሶ በተለየ እና በ አዲስ አቀራረብ የዞ የመጣ ምርጥ አማሪኛ ፊልም በሁሉም ሲኒማ ቤቶች በመታየት ላይ ነው ።
#ቴውድሮስ ይመጣል ሁሉም ሰዉ ልያየዉ የሚገባ ድንቅ ፊልም 🎭

@tebeb_mereja
እንዳሰብነው ባይሆን እንኳን እንዳሰበልን አኑሮናል ከዘመን ዘመን
አድርሶናል መጪውንም እሱ ፈጣሪ አብሮን ይሁን😍🙇🏾‍♂
እነዚህ የጳግሜ ቀናት የይቅርታ እና የምስጋና ቀናት ናቸው ስለሆነም
ሳላውቅ በስህተት❤️
💙አውቄ በእልህ💔
አስቀይሜ
አሳዝኜ
አስከፍቼ
💜ከሆነ ከጉልበቴ
በርከክ ብዬ💓
💞
💞
💞
💞ታ ጠይቃለው💞
🖤በችግሬ በሃዘኔ ስከፋ ተከፋታችሁ💘 ሳዝን አዝናችሁ
💖በደስታዬ ተደስታችሁ ሃሳቤን በመካፈል መፍትሄ ለሰጣችሁኝ
💚ስሜታዊ ሆኜም
💜መታገስን ላስተማራችሁኝ💜💗
💖💕💞በዙሪያዬ
❤️💖💗💓ያላችሁ
💜💙❤️ሁሉ
💝
💝
💝
💝
💝
💝
💝
💝 መልካም አዲስ አመት💚💛❤️

እውነት ስቃይ ላይ ያለችበት ዘመን ላይ ነወ፡፡ ከእውነትና ከሀቅ ይልቅ ቅጥፈትና ሸፍጥ የገነኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

እውነት የማታ ማታ ግንባሯ መች ይታጠፋል
እውነት የማታማታ ክንዷመች ይዘነጠፋል
የማታ ማታማ ምላስ'ንኳ ቢቀጠፍ
መልሕቅ የጣለ ሐቅ አይነጥፍ
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

ይላል ሙሉጌታ ተስፋዬ፡ ' እውነት ' እንደገና ጉልበት የምታገኝበት ፣ ቅጥፈትና ሸፍጥ የሚያስፎክሩበት ሳይሆን አንገት የሚያስደፉበት ዘመን ይሁንልን:: ከእውነት በስተቀር ምንም አማራጭ የለምና::!!!!!!!!!!💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
*ሰሞኑን ከፌስቡክ መንደር ከታዘብኩት ትንሽ ልበል##


ሃሳብን በነጻነት መግለጽ መብት ሆኖ ሳለ ግን ሁሉ ነገር ላይ እንደ አዋቂ መናገር ተገቢ አይደለም። አሁን እዚህ መንደር ላይ የበረከቱት ሰፈር እንኳን የተጣላ ጎረቤት አስታርቀው የማያውቁ ግን ሃገር ሊያሸማግሉ አቧራ ሚያስነሱ፥ አንዳንዶቹ ደግሞ ተገቢው እውቀት ሳይኖራቸው ለሁነቶች የፖለቲካዊ ትንታኔ የሚሰጡ ጥቂት አይደሉም ልክ ደግሞ የፈስቡክ ንፋስ ማርሽ ሲቀይር ተገልብጠው ከCIA የመጡ ወንጀል መርማሪ የሆኑ እስኪመስላቸው ድረስ የወንጀል ምርመራ ሪፓርት የሚሰጡ ሰዎች ናቸው። እኛ ኢትዮጵያውያን ልንማር የሚገባው ትልቅ ነገር አለ እሱም የማናውቀው ነገር ላይ አለመቀባጠር ነው። አላውቅም ማንን ገደለ? የህክምና ሙያ ወይም እውቀት የሌለው ሰው የታመመን ሰው ሊያክም ቢሞክር እንደሚገለው ልክ እንደዛው ያለ እውቀት ወይም ያለ ሙያዊ ክህሎት የሚደረጉ ንግግሮች ሃገራችንን ይገላሉ። የኢትዮጵያን የተሃድሶ ጉዞ በማዘግየት የአንበሳውን ድርሻ የያዘው ያለ እውቀት የሆነ እርምጃ ነው። የባለሞያውን ስራ ለባለሞያ እንተወው።

እናም በመጨረሻ የኢትዮጵያን ትንሳዔ እንደሚናፍቅ ሰው ይሄን መልእክት አስተላልፋለው በማላውቀው ጉዳይ ላይ ላልናገር ግን በማውቀው እና አቅሙ ባለኝ ጉዳይ ዙርያ በኢትዮጵያ ትንሳኤ ላይ የራሴን አሻራ ላስቀምጥ ቃል እገባለው። ጥሪየንም ለእናንተ አስተላልፋለው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!


እንደምን ከርመሻል ፤
አንች ጦቢያ ሚሉሽ በሽተኛይቱ ፤
እኔን የሚገርመኝ
ያልታከመው ሁሉ፤
በሽተኛው ሁሉ ፤ ላክምሽ ማለቱ።

ተፃፈ በሳሙኤል ግጥም በጃኖ

@getem
@getem @gebriel_19

#ዝምታለኢትዮጵያ
#ዝምታዬንለኢትዮጵያ
#SilenceForEthiopia
#MySilenceForEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለ ፈገግታ የአዲስ አመት ስጦታ ከ ወግ ብቻ 😂😂😂😂😜😜

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
Forwarded from Mykey (MikiyasLiyew(Mykey))
Ethiopia's Top Priority

Patriotic Ginbot 7 Movment for Unity and Dmocracy

Sun September 9

#Streetofaddis
Addisababa,Ethiopia

@Mykeypictures
#Mykeyምስሎች
 
2024/09/30 07:34:06
Back to Top
HTML Embed Code: