Telegram Web Link
ለሁለተኛው ጊዜ በተዘጋጀው ሆሄ የስነ ጽሑፍ ሽልማት በግጥም "የማለዳ ድባብ " በዕውቀቱ ስዩም አሸናፊ ሲሆን በረጅም ልብወለድ "በፍቅር ሥም" ዓለማየሁ ገላጋይ አሸናፊ ሆነዋል!!

እንኳን ደስ አላቹ!!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
In girlish shop
አዲስ አና ምርጡ online shop
ልብስ,መዋቢያ እቃ, ሽቶ,ጫማ ለመግዛት መርካቶ እየሄዱ ደክመዋልስለ ጤናዎ አጠባበቅስ የሚላቹ ነገር አለ
👇👇👇👇👇👇
@shopi_nova
@shopi_nova
@shopi_nova
በሀሳብ መንገድ ላይ
Written by ተመስገን


“ቦታ የሚጠበው አዕምሮህ ሲጠብ ነው”
“My house is small,
No mansion for a millionaire,
But there is room for a friend,
And room for love,
And that is all what I care”
እያንዳንዱ ህይወት ያለው ፍጡር፤ የየራሱን ‹አሁን› የሚከውንበት ጊዜና ጥግ አለው፡፡ … ንጉሡ በወርቅ ዙፋን ላይ ሊቀመጥ
ይችላል፡፡ … ምስኪን ደግሞ ብርኩማው ላይ፡፡ … ወይም ጎዳና ጥግ። … ሁለቱም ግን ተቀምጠዋል፡፡ … ቢቆሙም፣
ቢቀመጡም፣ ቢላፉም በየራሳቸው ቦታ ሆነው ነው፡፡ … ቦታ ቢቀያየሩም ለውጥ የለውም፡፡ … አውሮፓ ወይም አሜሪካ ብትሄድ
ወይ እነሱ ወዲህ ቢመጡ አንተ የቆምክበት ቦታ፣ የምትተኛበት ጥግ፣ የምትራመድበት መንገድ ያንተ ብቻ ነው። …. ዞር ብለህ
መንገድ ብትለቅ፣ ከመቀመጫህ ተነስተህ ሌላውን ብታስቀምጥም የራስህ ቦታ አለልህ፡፡ … አየር ላይ አትንሳፈፍም፡፡
በጠባብ ጎዳና ላይ ሺ ሰዎች ሲተረማመሱ እያቸው፡፡ … አውቶብስና ታክሲ ውስጥም ጭምር። አይተዋወቁም ግን ይግባባሉ፡፡
ተጋፍተውና ተጣበው ይተላለፋሉ፡፡ ግን አይገፈታተሩም፣ አይጣሉም፡፡ … ሁሉም በራሱ መንገድ ወደ ራሱ ጉዳይ ይጣደፋል፡፡ …
በጎ የመሆን ፈቃድና መተሳሰብ ካለ፣ ትንሽ ቦታ ለብዙ ሰዎች ትበቃለች። … ፍቅር፣ መተሳሰብና በጎነት የሃሳብ ልቀት ነው፡፡
ሌሎችን ሰዎች የተረዳኸው፣ ለሌሎች ሰዎች ያሰብከው ወይም ሌሎችን ሰዎች የምትወደው በሃሳብህ ነው፡፡ ይህም ማለት
ለሌሎች ሰዎች ቦታ የምትሰጠው አእምሮህ ውስጥ በመሆኑ ነው፡፡ አእምሮ ደግሞ ወሰን የለውም፡፡ አንተ ከፈለግህ ለቢሊዮንና
ቢሊዮን ሰዎች የሚሆን ቦታ አለው፡፡
ወዳጄ፡- ቦታ የሚጠበው አእምሮህ ሲጠብ ነው። አእምሮህ ከጠበበ ቦታ አይበቃህም፡፡ ትልቁ ግቢ ያንስሃል፤ ትልቁ መንገድ
ይጠብሃል፡፡ ግቢውን ታጥረዋለህ፣ መንገዱን ትዘጋዋለህ፡፡ … ማንም ድርሽ እንዲልብህ አትፈልግም፡፡ … የሌሎችን ቦታም
ትገዛለህ ወይ ትቀማለህ፡፡ በቦታ ትጣላለህ፣ በድንበር ትካሰሳለህ። … አንዳንዴም ትጋደላለህ። … ደውሉ ሲደወል፣ ተራህ ደርሶ
ስትሞት ግን ሌላው ላይ ትደረባለህ፡፡ … እንደ ዕቃ! … ወይ ሳርና ዛፍ ይበቅልብሃል፣ ቤት ይሰራብሃል፣ ወይ መንገድ
ይወጣብሃል፡፡ … ራስህ ቦታ ትሆናለህ!!
***
“ሁለት መላዕክቶች ናቸው፡፡ … ታላቅና ታናሽ። በሰው ተመስለው ይዘዋወራሉ፡፡ ሲጓዙ ውለው መሸባቸው፡፡ በቅርብ ወዳዩት
ግቢም ተጠጉ።” እያለ የሚተርክልን የማናውቀው ሰው ነው፡፡ … ግቢው ትልቅና ያማረ ነው፡፡ መሃል ላይ ብዙ ክፍሎች ያሉት
ትልቅ ቤት አለ፡፡
“ምን ትፈልጋላችሁ?” በማለት ጠየቃቸው ባለቤቱ።
“ሩቅ መንገደኞች ነን፣ መሸብን ደክሞናል፤ ማደሪያ እየለመንን ነው” አሉ፡፡ ባለቤቱም ሲያቅማማ ከቆየ በኋላ ከአገልጋዮቹ አንዱን
ጠራ፡፡ ከቤቱ ስር ያለውን ጋጣ እንዲሳያቸውና እንዲተኙ አዘዘ፡፡ እንግዶቹም እጅ ነስተው ሄዱ። ሲነጋጋም አመስግነው
መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡ … እንደገና መሸ፡፡ ማደሪያ ሲፈልጉ አንዲት ደሳሳ ጎጆ በአካባቢው ተመለከቱና ወደዚያ አቀኑ፡፡ ቀርበውም፤
“የመሸብን መንገደኞች ነን” በማለት ጮክ ብለው ተናገሩ፡፡ ባለቤቱም ወጥቶ …
“ቤት ለእንግዳ ነው፡፡ እባካችሁ ግቡ” አላቸውና አስገባቸው፡፡ የገበሬው ሚስት ታማ መደብ ላይ ተኝታለች፣ አጠገቧ ደግሞ
ላማቸው ታስራለች። እንግዶቹ የጎጆዋን ጥበት ሲያውቁ አፈገፈጉ። ባለቤቱ ግን መውጫውን ይዞ … “በጭለማ አትሄዱም”
በማለት ከለከላቸው፡፡ ባለቤቱም እያቃሰተች፤ “እባካችሁ ደስ እንዲለን ይሁን” ብላ ለመነቻቸው፡፡ … ጥግ ላይ አረፍ አሉ፡፡
ወተትና ቤት ያፈራው እህል ቀርቦ ደስ እያላቸው ተመገቡ። ሲጫወቱና ሲስቁ አምሽተው በያሉበት ድብን ያለ እንቅልፍ
ወሰዳቸው፡፡
በማግስቱ ረፋድ ላይ ከመኝታቸው ሲነሱ፣ ገበሬውና ሚስቱ እያለቀሱ ነበር፡፡ ላማቸው ሞታ ነበር ያደረችው፡፡ እንግዶቹም
አፅናንተዋቸው መንገዳቸውን ጀመሩ፡፡ … ትንሽ እንደተጓዙም …
“እንዲህ ዓይነት ጭካኔ ሊዋጥልኝ አይችልም!!” አለች፡፡ … ትንሿ መልዓክ እየተበሳጨች፡፡
“አንዳንድ ጊዜ ነገሮች እንደምናያቸውና እንደምናስባቸው ላይሆኑ ይችላሉ” አላት ትልቅየው፡፡
“በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ እንዴት ሊኖሩ ነው?”
“ህይወት ረቂቅና በተዓምራት የተሞላ ነው። በጥልቅ ለማይመረምረው ችግር ነው፡፡ የተዛባ ፍርድ እንዲሰጥ ሊያደርገውም
ይችላል፡፡”
“እንዴት? … ምን ማለት ፈልገህ ነው?”
“ምክንያቱም ሁላችን ሁሉም ነገር ላይ ዕኩል ዕውቀት የለንም፤ ሊኖረንም አይችልም፡፡ ዕኩል ካላወቅን ደግሞ እኩል መረዳት
አንችልም፡፡ ዕኩል ካልተረዳን ዕኩል ትዕግሥት አይኖረንም፡፡ ዕኩል መታገሥ ካልቻልን ደግሞ ብዙዎቻችን ስሜታዊ ነን ማለት
ነው፡፡ ለዚህ ነው ፍርድ የሚዛባው፡፡ … ለመሆኑ እንዲህ የተቆጣሽው ምን ነክቶሽ ነው?”
“እንዴት አልቆጣም? … ከትናንት ወዲያ ያደርንበት ግቢ ባለቤት ጥሩ ሰው አልነበረም፡፡ ብዙ ባዶ ክፍሎች እያሉ፣ ብዙ የሚበላ
ነገር ሞልቶ ሳለ ጋጣ ውስጥ፣ ጦማችንን አሳደረን፡፡ … አንተ ግን ምንም አልተሰማህም፡፡ ትናንት ማታ ደግሞ እነዚያ ምስኪኖች
በፍቅር ተቀብለው፣ ያላቸውን አብልተው፣ መኝታቸውን አጣበን ማደራችን አንሶ ወተቷን እየሸጡ የሚተዳደሩባት አንዲት ላማቸው
በድንገት ስትሞት እያየህ ዝም ማለትህ ነዋ ያበሳጨኝ፡፡”
“አየሽ ነገሮች ሁልጊዜ እንደሚታዩትና ሌሎች እንደሚያስቧቸው አይደሉም … ያልኩሽ ለዚህ ነበር፡፡”
“ማለት?”
“የመጀመሪያው ግቢ ባለቤት ገብጋባና ክፉ ነው፡፡ ወርቅና ገንዘቡን የቀበረው እኛ ያደርንበት ጋጣ ውስጥ ነበር፡፡ ከአሁን በኋላ ግን
አያገኘውም። … ድህነትን እንዲያውቅ፣ እንግዳ እንዲያከብርና እንዲወድ ሆኗል። … ገበሬውና ሚስቱ ግን ደግና ትሁት ሰዎች
ናቸው፡፡ ሌሊት አንቺ ተኝተሽ መልዓከ ሞት መጥቶ ነበር፡፡ … የገበሬውን ሚስት ለመውሰድ፡፡ … ከለከልኩት። በሷ ፈንታ ላማቸውን
ሰጥቼው ሄደ፡፡ አሁን የገበሬው ሚስት ድና ተነስታለች፡፡ ወደፊት ብዙ ላሞች ይኖራቸዋል” አለ፡፡ … ትንሿ መልዓክ በጣም ደስ
አላት፡፡
“እውነትም ነገሮች ሲመረመሩ እንደሚታዩትና እንደሚታሰቡት አይደሉም” አለች፡፡
ወዳጄ፡- “There is no mathimathical certainity in life” … ሲባል ምን ማለት ይመስልሃል? … ለሌሎች ሰዎች የሚሆን
ቦታ አዕምሮህ ውስጥ አለ? ወይስ የለም?….

ሠላም!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
እስከ ቀራኒዩ! !!!!

ጉዳዩ የሃገር ትንሳኤ ነው ። በመሃከል ይሁዳ በክህደት ተነሳብን ብለን የቀራኒዩ
ጉዟችንን አናቆምም ። እስከቀራኒዩ ድረስ የሚገጥመንን ፈተና ፤ መከራ ፤ ስቃይና
ግርፋት እየፈራንና እየሰጋን ወደፊት በአሻጋሪ የሚታየንን ትንሳኤን መቋመጥ የህልም
እንጀራ ነው የሚሆነው!!! ትንሳኤን አብዝተን ፈልገናልና እስከቀራኒዩ ድረስ የተዘጋጀልንን
ህማማት ለመቀበል የመንፈስ ጽናታችን በሰባት እጥፍ ይታተም ዘንድ ጊዜው አሁን ነው


@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የግብጽ ሽንኩርት ናፍቆት!!!!!!!


ሙሴ የነጻነት መሪ ነው ። ህዝቡን ከግብጽ ይዞት ወጣ ። ከአምላኩ ጋር ሆኖ ቀይ
ባህርን አሻገረው ። ምድረ በዳው ላይ መከራና ፈተና በዛ ። ሰነፉ ህዝብ ለዚህ ለዚህማ
ፈርኦን ምን በደለነ??? ወደ መጣንበት ወደ ግብጽ መልሰን ብሎ ጮኸበት ። አየህ
ወዳጄ ፤ ነጻነቱን ያለ ዋጋና መስዋእትነት መጨበጥ የወደደ ሰው መከራ በመጣ ጊዜ
እንደገና ባርነቱን ይናፍቃል ። እንደገና የግብጽን ሽንኩርት ይናፍቃል ። ለዚህ ለዚህማ
ወያኔ ምን አለኝ የሚል እንዲህ አይነቱ ምስኪን ነፍስያው ራሷ በፈርኦን ሽንኩርት
የተሰራች ሽንኩርት ነገር ነው ። ሽንኩርታ ሽንኩርት ነገር!!!!!

ሸጋ ምሽት!!!

@balmbaras
@getem
@getem
Forwarded from JONNY ARTs🎨 (Johns24 (ጊዜ አስታወሰው))
ለ ወገን ደራሽ ወገን ነው አብሮነታችንን እናሳያቸው፡፡ የሞቱትንም ፈጣሪ በገነት ያሳርፍልን አሜን፡፡

፡እባካቹ ሼር አርጉት
፡እንርዳቸው ከጎናቸው መሆናችንን በመርዳትና በማሰብ በመፀለይ አለንላቹ እንበላቸው
በዚ የባንክ #አካውንት በመደገፍ እንርዳቸው

ፈጣሪ ከ ሁሉም ነገር ይጠብቀን አሜን፡፡
ለውጥን እየፈለገ ራሱን ለመለወጥ ያልተዘጋጀ ሰው ብሽቅ ነው! !!!! አሁን በደንብ
እየተባሸቅን ይመስለኛል ። ለማናቸውም እንደ ሰው አስበን እንደሰው እንኑር!!!!
የሚሻለውና ደጉ ነገር ይኸ ይመስለኛል ። እንደ አውሬ ለመሆን አንድ ቀን ጀምበር
ሳይበቃን አይቀርም! !! ሰከን! !! ሰከን!!!! አሁንም ሰከን!!!!

ሰላም እደሩልኝ አበቦቼ!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ነሀሴ 12 የሚከበረውን የደጉ ንጉሳችንን የእምዬ ምኒልክን 174ኛ የልደት በዓል አስመልክቶ ተከታታይ ጽሁፍ እናቀርባለን

@wegoch @kinchebchabi
@ethio_art
“ንፋስ ያነሳው ጥላ” - የግብዝነታችን ወረንጦ!
Written by ደረጀ በላይነህ


በየዓመቱ ከሚታተሙ የግጥም መጻሕፍት ውስጥ ጥቂቱ፣ እጅግ ጥቂቱ የዘውጉን መስፈርት አሟልተው፣ የጥበቡን ውበት
ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡ ሙሉ ለሙሉ ምሉዕነት ተጎናፅፈዋል ባይባልም በቋንቋ ገለፃ፣ በሃሳብና በምት፣ ወዘተ አንዱ ከአንዱ
ይለያያሉ፡፡ በልዩነታቸው ውስጥ ያለው ምትሀትና ሙዚቃ፣ የሃሳብ ጡዘትና ትዕይንት በየፈርጁ፣ ሊማርኩን ይችላሉ፡፡
እንደ ተርታው አንባቢ፣ በመጀመሪያ ንባብ የምንስማማባቸው የራሳችን ምርጦች ቢኖሩም መሰላል ዘርግተን ወደ መመዘኛዎቹ
ስንሄድ የምንሰጠው አስተያየት ይለያያል፡፡ ግጥም የሁሉም፣ በሁሉም ደረጃ የሚነበብና የሚዳኝ ስለሆነ፣ ሰው ለራሱ፣ የራሱንም
መምረጥ መብት አለው፡፡ ውበትና ቅርፅ የሚያዩ እንዳሉ ሁሉ፣ የሀሳቡን ስብከት ብቻ የሚያደምጡ (message hunters)
ጥቂት አይደሉም፡፡
ወዲህ መለስ ስንል ግን ለምርጫ የተወሰኑ አላባውያንን ማየት ግድ ይለናል፡፡ በተለይ ማዕከላዊ ሀሳቡን ለማጎልበት ከግራና
ከቀኝ ገጣሚው የሚጠቀማቸውን ስልቶችና ሌሎች ፈርጦች፡፡
ዛሬ የገጣሚ ብርሃነሥላሴ ከበደ፤ “ንፋስ ያነሳው ጥላ” የግጥም መድበልን ይዤው ብቅ ያልኩትም፣ ከአላባውያኑ የተወሰኑትን
ተጠቅሞ፣ በሀሳብና በቅርፅ የተሻለ ቀለም አለው ብዬ ስላመንኩ ነው፡፡ ምናልባትም ይህ ወጣት ገጣሚ ይበልጥ ካነበበና
የሕይወት ልምዱን መልዕክቶች ካደመጠ፣ የተሻለና ሀገር የሚያጣፍጥ ሰው ይወጣዋል ብዬ በመገመትም ነው፡፡
እስቲ ከሰሞነኛ ሀሳቦቻችን ጋር የምትጣጣመውን ግጥም አጥቅሼ ልጀምር፡-
“ለ‘ኛ”
መቻቻል ትርጉሙ፡-
አበው ሲተርቱ
“ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል..”
እንደሚሉ፣
ሰርክ እየተናጩ
እየተቋሰሉ፣
ተዛዝሎ መኖር ነው
ሳይነጣጠሉ፡፡
የሚያምም ነገር ነው፡፡ አጋም አጠገብ ያለ ቁልቋል ሁሌ እንዳለቀሰ ነው፡፡ እንደተነጨ፣ ነጭ ደም እንደደማ ነው፡፡ ግን “አብሮ
መኖር አይታክተውም” የሚል ሀሳብ ያንጸባርቃል፡፡ ወደ መሬት ስናወርደው፤ አንዱ ብቻ ሁሌ አልቃሽ ከሆነ ግፍ ስለሚሆን አብሮ
መዝለቁ ከባድ ነው፡፡ ግን ቦታ እየተለዋወጡ፣ አንዱ አንዱን እየታገሰ ከኖረ መልዕክቱ ጥሩ ነው፡፡ ንቡር ጠቃሽ ዘይቤ ተጠቅሞ፣
“ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል” የሚለውን አባባል ማምጣቱ የግጥሙን ኃይል ከፍ ያደርገዋል፡፡
ለሁለቱ ተክሎች አጥር ማበጀት አይቻልም፤ አይጠቅምም፣ አያድንም፤ ፍቅር ግን ሊያስተዛዝላቸው አቅም አያጣም፡፡
ገጣሚው ሁለንተናዊነት ላይ ያተኮሩ ግጥሞችም አሉት፡፡ ለመላው የሰው ልጆች ልዕልና የሚሞግቱ፣ ሥዕሉን የሚያስቀምጡ፣
በሂስ የሚሸነቁጡ፣ የሰብዕናን ልክ፣ የክብርን መለኪያ፣ የማንነትን ቁመና ሊያሳዩ የተደረደሩ ስንኞች በጌጥ ተቀምጠዋል፡-
“በነጋዴው ዓለም”
ሸቀጥ ዋጋው ንሮ
ከላይ መቀመጡ፣
የሰውነት ተመን
እያደር መዝቀጡ፣
በገበያ ሕግነት
ይኖራል ያለ እክል፣
ሰው የራሱን ዋጋ
እስከሚያስተካክል፡፡
ይህ ግጥም መላውን የሰው ልጅ ያቀፈ ነው፡፡ በተለይ በዚህ ዘመን፤ ገንዘብና ሀብት ዘውድ ደፍቶ፣ የሰው ልጅ ማቅ ለብሶ፣
ዐመድ ነስንሶ እያለቀሰና እያላዘነ ሊኖር የተገደደበት ደረጃ ደርሷል፡፡ የመኪና አደጋ ሲደርስ እንኳ “ሰው ተረፈ?” ከማለት ይልቅ
ውዱን ዕቃ መትረፉን የምንጠይቅበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡
ግና የዚህ ሁሉ ምንጭ፣ የጥበብ ሁሉ ምንጭ ራሱ ሰው ነው፡፡ በራሱ እምነት ከፈጣሪ አገኘሁ ይበልም አይበልም፣ መሳሪያው
ግን ራሱ ሰው ነው፡፡ ይሁንና ዋጋው ዘቅጧል፡፡ ገጣሚው ይህንን ሀሳብ ነው በሙዚቃ ጣዕም፣ በቃላትና ፍቺ አበልፅጎ፣
ለአንባቢው እርካታን ለማምጣት የፃፈው፡፡ የሙግቱን ጡንቻ፣ የሰቀቀኑን ዜማና ትኩሳት ሊያወርሰን አቅም ፈጥሮ መጥቷል፡፡
የገጣሚው ጭብጦች፤ ታሪክን ትውልድንና ማኅበራዊ ህይወትን ያጣቀሱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ከጥቅሉ የሰው ልጅ አጥር ወጣ
ብሎ ሀገራዊ የታሪክ እርሻዎቻችንና ፍሬያቸውን እየጎበኘ፣ ከታሪክ ድርሳናት መነሻ ዛሬ የቆምንበትን መሬትና ሀቅ ያሳያል። የነገም
አድማስ ወለል ብሎ እንዲታየን መቆሚያ ቦታ ሰጥቶናል፡፡ “ቅብብል” የምትለው ግጥሙ፣ ያለፍናቸውን መቆሚያ ቦታ ሰጥቶናል፡፡
ያለፍናቸውን ዘመናት ፎቶግራፎች ከፊታችን አምጥታ ታቆማለች፡፡ ዐይኖቻችንን ከፍተን እንድናይ፡-
ከባዕድ ሰማይ ስር
ጉም እንደጨለፈ፣
የነሌኒን ምርኮ
ያ ትውልድ አለፈ፡፡
አወይ ምስኪን ቧጋች
ሕልሙን የተቀማ፣
ራዕይ መሳይ ቅዠት
ደጋግሞ እየሰማ፤
መልስ አልባ ጥያቄ
ከንቱ እየጠየቀ፣
ይኼኛውም ያልፋል
ከራሱ እንደራቀ፡፡
ይህ ትርክት ዛሬ እንደ ጎርፍ በፈሰሱት መጽሐፍት የተነበበ ሀቅ ነው፡፡ ከባዕድ ምድር የመጣው የሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም
አምልኮ፣ የዚህን ትውልድ ልብ ነጥቀው፣ ደሙን እንዲሰጥ፣ በፍቅር አክንፈውት እንደነበር ሁሉም በየራሱ ማዕዘን ፅፎታል፡፡ የራሱ
ህልም የበቀለበት ምድር ራዕዩን ሙሉ ለሙሉ አስቀምጦ፣ ሲባትት፣ ሲመኝና ሲፋለም ባክኖ የቀረ ትውልድ አለ፡፡ የዚያ ትውልድ
ጥያቄ ደግሞ በዛሬው ትውልድ ላይ የወደቀ ጥላ ሆኖ፣ ወደ ኋላ እያየ፣ ወደፊት ማየትና መራመድ ሲሳነው፣ ራሱን ሳያይ፣
እርሱም በሀገሩ ሰዎች ህልም ውስጥ ሰምጦ ይቀራል እያለን ነው፡፡
እውነትም አልባነንንም ይሆን? ብለን ውስጣችንን መበርበር፣ ራሳችንን መፈለግና ጀንበራችን ሳትጠልቅ ከህልማችን ጋር
መግጠም የኛ ፈንታ ነው፡፡ ገጣሚው ግን እንደ ጣፋጭ ሽሮፕ መድኃኒቱን ሰጥቶናል። እየጣፈጠ ሊፈውሰን፡፡ ከዚሁ ሀሳብ ጋር
የተያያዘ የዘመናችንን ሥዕል ያሳየበት ግጥም አለ፡፡
“ውጭና ውስጣችን”
በየቤተ እምነቱ ያሞቅነው እልልታ፣
በየኳሱ ሜዳ ያቀለጥነው ሆታ፤
በየመሥሪያ ቤቱ የካድሬ ስብሰባ፣
በስሜት ተውጠን ያሞቅን ጭብጨባ፣
ወደየቤታችን አብሮን ስላልገባ፣
በደስታ ናፍቆት ጎጇችን ኮሰሰ፣
ውጭና ውስጣችን እንደተለያየ፣
ወደምንም ጅረት ዕድሜያችን ፈሰሰ፡፡
“እምነት” ብለን የያዝነው የውሸትና የግብዝነት ሜዳ ነው፡፡ በየኳሱ ሜዳ፣ የጨፈርነው የውስጥ ጩኸታችንን ለመሸሽ ነው፡፡
በየካድሬው ስብሰባ እጃችን እስኪቃጠል ያጨበጨብነው ልባችን ሞቆት አይደለም፤ ውስጣችን በርዶታል፤ ስለዚህ ቤታችን
ስንገባ እንደሚንሿሿ ፀናፅል ነን፡፡ ባዶ ሙዚቃ፣ ኦና ቃላት! … ልብ የማይነካ ቃል!
በግብዝነት እየኖርን ስለሆነ እግራችን መሬት አልረገጠም፡፡ የነገ አቅጣጫችንን አናውቅም፤ ንፋስ እያንገላታን ነው፡፡ ስለዚህ
ዕድሜያችን ውስጥ ምንም ፋይዳ ያለው ነገር አልተቀመጠም፡፡ ለታሪክ ኮረጆ ያቀበልነው ነገር የለም፡፡ ዝም ብለን ያለ አቅጣጫ
ፈስሰናል፡፡ በጥቅሉ የግብዝነታችንን ኪሳራ ተንትኖ አሳይቶናል፡፡ እንደ ሀገር በየትኛውም በኩል አልተሳካልንም፡፡
ራሳችንን ዋሽተን፣ ራሳችንን ከራሳችን ውስጥ አጥተነዋል፡፡ ጩኸታችን ግን ከአድማስ ያስተጋባል። የመጽሐፍ ቅዱሱ መሊ ልጆች
ልክ እንደ ጨዋ ካህን የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው እንደተዋረዱት፣ በውሸታችን ዕድሜያችንን ገድለናል! ሕይወታችን ሳይሆን
ሞታችን እያለቀሰ ነው፡፡ እንባችንን- ቃላችንን- ቀድሟል!!
ገጣሚው ብርሃነሥላሴ ከበደ፤ ብዙ ግጥሞቹ ማኅበራዊ ሂስ ናቸው፡፡ አፍረን ወይም እንዳናፍር፣ በየኮረጆዋችን ደብቀን
በግብዝነት የተውናቸውን ሀቆች ፈንቅሎ እያወጣ ከደጃችን ደርድሯቸዋል፡፡ ብንወድ ልንቀበለው፣ ባንወድ የውስጣችንን ሀፍረት
ቅመን ባደባባይ ያንኑ ሻሽ የመሰለ ንጣታችንን አጣፍተን፣ ዕድፍ ጉድፋችንን መልሰን ሳጥን ልንቆልፍበት እንችላለን፡፡ ሕሊናችን
ግን ያላምጠው ዘንድ አጣፍጦ አስቀምጦታል፡፡
“ለምዶበት”ን እንያት፡-
የስጋ አምሮት ያዋለለው
በተሰጠው ያልጠገበ፣
የሰው ዳቦ ሰረቀና
ሊበላ ሲል አማተበ፡፡
አያዎን ተመልክተን፣ የራሳች
ንን ገፆች ሥናነብብ፣ ሳቃችን ይሁን እንባችን ማፈትለኩ አይቀርም- እንደየ ትርጓሜያችን፡፡ “ንፋስ
ያነሳው ጥላ” የተሰኘው መጽሐፍ አዳዲስና የተለዩ አተያዮችን ይዟል፡፡ ጣዕም ባለው ዜማ፣ በጥሩ አሰነኛኘት፣ አንባቢን
የሚማርኩ ግጥሞችን አካትቷል፡፡ ችግሮቹ ብዙ አይደሉም፡፡ አልፎ አልፎ የተለመዱ ነገሮችን በተለመደ መንገድ አቅርቧል። እንደ
“መጽሐፍና ሰው” እንደ”ማንዴላ” ዐይነቶች፡፡
በተረፈ፣ ወጣቱ ገጣሚ፣ በተለይ አተያዩና አሰነኛኘቱ ሸጋ ነው፡፡ የኖርንበትን ሕይወት አሳይቶናል፡፡ “The meaning of a poem
is the experience which it expresses nothingless” እንዲል የስነ ግጥም ፕሮፌሰሩ፡፡ ይሁንና የመጽሐፉ ሽፋን
የግጥሙን ውበት የሚያዩ አንባቢዎችን እንደሚገፋበት እገምታለሁ፡፡ ጥንቃቄ የጎደለው፣ ወይም የገጣሚው ስዕል የማጣጣም
አቅም ያነሰ ይመስለኛል፡፡

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ከራስ ጋር እንደመሟገት አድካሚ ፣ እራስን እንደመደለል አሰልቺ ነገር የለም፡፡ ያልሆኑትን << ነኝ >> ብሎ ፣ ሌሎችን ማሳመን ይቻላል፡፡ በተለይ እንደ እኛ በይሉኝታና በመምሰል የተቀየደ ማህበረሰብ << ነኝ >> ያልከውን ፣ << ነህ >> ይልሀል ፤ እንዳልሆንክ እያወቀም ቢሆን፡፡ ይህን ይሁንታ ከእራስ ነብስ ማግኘት ግን ከባድ ነው - << ነኝ >> ስትለው ፣ <<አይደለህም >> ይልሀል ፤ ስትነግረው አይሰማህም፡፡ የእራስ ምስል ከውጭ - ከላይ - ገፅ ላይ የሚቀባ አይደለም ፤ የነፍስክን አስኳል ንድፍ ነው - ነፍስህ የሚስለው - ከውስጥ ፡፡ የውስጥ የማንነትህ ያልሆነውን ንድፍ በምላስህ ገጽህን ብትቀባው አህያን በቅባት እንደማውዛት ነው፡፡ የአህያ የነፍስ ልክፍት ከአመድ ነውና ወዟ እድሜ የለውም፡፡

ራስህን ሁን ነብስያህን አድምጥ/ጪ!!!!

ሸጋ ሸጊቱ ቀን!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
DAILY WORDS

@words19
@words19

To change ur life
change ur mind
To change ur mind
change ur blieve
to change ur blieve
change ur "words" .

@words19
@words19
ሰላም ክቡራት እና ከቡራን አባሎቻችን በዚህ ሳምንት በተከታታይ የአፄ ምኒልክን 174ኛ የልደት አስመልክቶ የዳግማዊ ምኒልክን ታሪክ እናወሳለን

ልጅ ምኒልክ በ1836 ነው ነው የተወለዱት ይህ ማለትም ከ174 ዓመታት በፊት ነበር ይህቺን ምድር የተቀላቀሉት፡፡ የአፄ ልብነድንግል ልጅ ከሆኑት አፄ ያዕቆብ 13ኛ የዘር ሀረግ ይመደባሉ፡፡ አያታችዉ ሣህለስላሴ የየሸዋዉን ንጉስ ሀይለመለኮትን ይወልዳሉ፡፡ ሐይለመለኮት ወ/ሮ እጅጋዉን አገብተዉ ልጀ ምኒልክን ይወልዳሉ፡፡
ልጅ ምኒልክ ነሀሴ 12 ቀን 1836 አንጎላላ ኪዳነምህረት ነው የተወለዱት የመጀመሪያ የልጅነት ጊዜያቸወን በአንኮበር እና ደብረብርሀን እየተዘዋወሩ ካሳለፉ በኋላ ዐፄ ቴዎድሮስ ሸዋ ሲመጡ ይዘዋቸዉ ወደ ጎንደር ሄዱ እዛም እንደልጅም እንደአማችም (አማቸነታቸው የአፄ ቴዎድሮስን ልጅ አልጣሽን በማገባታቸዉ ነበር) ሆነዉ በአፄ ቴዎድሮስ ቤት በቧለሟልነት አደሩ፡፡ በመጨሻዉ የንገስና ዘመናቸዉ(1856-60) አጼ ቴዎደሮስ ለያዥ ለገናዥ አሰኪያሰቸገሩ ደረሰ ደርዝ የለቀቀ ቁጠኝነት እና ማንንም ያለማመን ይሰተዋልባቸዉ እንደነበር ታሪክ ያሰረዳል በዚህም ወቀት በአፄ ቴዎድሮሰ ዙሪያ የተኮለኮሉት የሸዋ እና የበጌምድር መኳንንት ምኒልክም ላይ በእኚህ ቁጠኛ ንጉስ ሰበብ ጉዳት እንዳይደርስ ሰጋት ነበረባቸዉ ይህን ተከተሎም ምኒልክን ለማስመለጥ ሴራ መጎነጎን ተጀመረ፡፡ሆነም ቀረም ወደኋላ ለምኒልክም ቢሆን የመጋዙ (ቃሉ ሚነበበው ጠበቆ ሲሆን ትርጓሜዉም በግርድፉ በንጉስ ጥብቅ ቁጥጥር ውሰጥ መዋል ወይም መዉደቅ የሚል አዉድ አለዉ) ነገር አልቅረላቸዉም ነበር፡፡
🎢🎢🎢ከአፄ ቴዎደሮሰ ቤት የማምለጣቸዉ ነገር

ለማምለጥ ካገዟቸዉ ነገሮቸ መካከል የግዞቱ መላላት እንደሆነ የታሪክ ጸሀፍት ያሰረዳሉ በተጨማሪም ከጎናቸዉ የነበሩት የሸዋ ና የበጌምድር ባላባቶች ብሎም የምኒልክ ዘመዶች (ለአብነት ያከል አቶ ገርማሜ ወልደሀዋሪያት፤አቶ ሀብተሰላሴ ደሰታ፤ አቶ ናደዉ፤አቶ ወልደገብርኤል እንዲሁም የምኒልክ እናት ወይዘሮ እጅግአየዉ) ቁልፍ ቦታ እንደነበራቸዉ ታሪክ ያወሳል ይህንንም ሲያወጡና ሲያወርዱ ከምኒልክ ሚሰት አልጣሽ ቴዎደሮስም ጭምር ደብቀዋቸዉ እንደነበር ይነገራል፡፡
ለዚህም ጉዳይ ምቹ ጊዜ ሲጠብቁ ቆይተዉ ሰኔ 24 1857 ማታዉኑ ታላቅ ድግስ ተሰናዳና የጥበቃ ሹማምንቱንና ወታደሮቹን በመጠጥ ካሰከሯቸዎ በኋላ ጥልቅ እንቅልፍ ዉስጥ ሲገቡ ጎልማሳውን ምኒልክን ይዘዉ ከመቅደላ በአሊ በር በኩል አምልጠዉ ወረሂመኑ ገቡ፡፡
የምኒልክን ማምለጥ አፄ ቴዎድሮስ ሲሰሙ “ለምን አልጣሽን ትቷት ሔደ አሉ ይባላል”:: ይኽዉም ከምኒልክ ማምልጥ የልጃቸዉ የአልጣሽ አብሮ አለመሄድ የቆጫቸዉ ይመስላል፡፡ ምኒልክን ተቀብለዉ የሸኟቸዉ የወሎ መኳንንት ናችዉ ሲባል ስለሰሙ አፄ ቴዎደሮስ በብሰጭት ገደል እያስገፉ አስገድለዋቸዋል፡፡

በዚህ ወቅት የነበረዉነ ኩነት በዛን ወቅት የአይን ምስክር የነበሩት አለቃ ወልደማሪያም ሲገለፁት እንዲህ ይላሉ
“የሸዋን ሰዉ እናትዎን (ምኒልክን ማለታቸዉ ነዉ የአክብሮት አገላለጽ ነዉ) ይዘዉ ወጡ፡፡ ሲነጋ ኩተማ በሚባል ፈረሳቸዉ አፄ ቴዎደሮስ ወደ እስር መንደር መጡ (በአሁን አገላለጽ ወይኒ ቤት) በጣም ተናደዉ ስለነበር እሰርኛዉን ሁሉ አዉጡ ብለዉ አዘዙ ዘመዶቻቸዉንም ጭምር እጅ እና እገራቸዉን በማሰቅረጥ ወደ ገደል አሰወረወሩ“
ምኒልክም ብዙ ዋጋ ተከፍሎላቸዉ ወደአባታቸዉ ሀገር ወደ ሸዋ ገቡ
ይቀጥላል አምላክ እድሜና ጤናዉን ከቸረን
አከባሪያቸሁ ወግ ነኝ @wegeee

@wegoch @kinchebchabi
@ethio_art
።። " ስንደመር " ታላቅ የኪነ ጥበብ ምሽት ።።።

ነሀሴ 18 /12 / 2010 በብሔራዊ ቲያትር አዳራሽ

ፕሮግራሙ የሚጀምረው 11 ሰዓት ከ 00 ነው

★★ ገጣሚያን ★★
★ ኤፍሬም ስዩም
★ ነብይ መኮንን
★ ምስራቅ ተረፈ

★★ ወግ አቅራቢ ★★
★ ፍቃዱ ከበደ

★★★ ዲስኩር ★★★

★ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ
* ረ/ፕሮፌሰር አበባው አያሌው
* የሙዚቃ ባለሙያው ሠርጸ ፍሬስብሐት

★ ሙሐዘ ጥበብ ዳንኤል ክብረት ★

★★★ መነባንብ ★★★

★★★ አርቲስት ሽመልስ አበራ (ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት)★★★
#መሶብ የባህል ሙዚቃ ቡድን
ፉከራ ሽለላ
ትኬቶቹን በሚከተሉት ቦታዎች ያገኙታል
* ጃፋር መጽሐፍት መደብር
* ዮናስ መጽሐፍት መደብር(ራስ ሆቴል ግቢ)
* አይናለም መጽሐፍት መደብር
* ሳሚ ካፌና ሬስቶራንት
*ምርፋቅ ካፌ እና ሬስቶራንት(አራት ኪሎ)

የመግቢያ ዋጋ 100 ብር ብቻ

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ክፍል ሁለት

ምኒልክ ሽዋ ከገቡ በኋላ የነበረው ኩናቴ ምን ይመስል ነበር?👇

እንደታሰበው ግን ምኒልክ ወደ ሸዋ ለመግባት አልተመቻቸውም ነበር ነገሩም አልጋ በአልጋ ከመሆን ይልቅ ቀጋ ከቀጋ ሚለው የበለጠ ይገልፀዋል፡፡ የሸዋው ንጉስ የነበሩት በዛብህ
"ምኒልክ ከአጤ ቴዎድሮስ ጋር ውል አለው፡፡ ውሉም እኛን አሳልፎ ለቴዎድሮስ መስጠት ነው፡፡ ...." በማለት አዋጅ አስነግሮ ለጦርነት እንዲዘጋጁ አደረገ፡፡

ቢሆንም ምንሊክ ሸዋ እንደደረሱ ደጃች ወልዴ እና አቶ ሀብተየስ ሳይዋጉ በሩን ለቀው ወደ ደፍራታ ሸሹ፡፡ የምኒልክ ሰራዊትም እየበዛ ሄደ..
የምኒልክን ወደ መሀል መግባት የሰሙት አቶ በዛብህ ከምኒልክ ጋር ጦር ለመግጠም ጋዲሎ ከተባለው ቦታ ተሰለፉ በዚህን ጊዜ አንዲት ሴት

"ማነው ብላችሁ ነው
ጋሻው መወልወሉ
ማነው ብላችሁ ነው
ጦራችሁ መሳሉ
ማነው ብላችሁ ነው
ካራችሁ መሳሉ
የጌታችሁ ልጅ ነው
አረ በስመዐብ በሉ" በማለት ገጠመች


ውጊያው ጋዲሎ ላይ ነሐሴ ፲፮ ቀን ተፋፍሞ
ሳለ ከአቶ በዛብህ ጋር ተሠልፈው የነበሩት
የ ሸዋ መኳንንት “በጌታችን በኃይለ መለኮት
ልጅ ላይ አንተኩስም” ብለው ወደምኒልክ
ዞሩ። አቶ በዛብህም ሸሽተው አፍቀራ ገቡ፤
ድሉም የምኒልክ ሆኖ ምሥራቅ ምስራቁን
ተጉዘው በድል አድራጊነት አባቶቻቸው ከተማ
አንኮበር ገቡ። ንጉሥ ምኒልክም በ አንኮበር
ጥቂት ወራት ከተቀመጡ በኋላ ወደ ደብረ
ብርሃን ወርደው አዲሱን ከተማቸውን ልቼ ን
እያሠሩ ተቀመጡ።
በጦርነቱም ምኒልክ ድል አደረጉ፡፡
.....ቀጣዩ ስራቸው የሆነውም ግዛታቸውን ማስፋፋት ሆነ፡ ከመጀመሪያው ጀምረው አብዛኛው ስራቸው ነገሮችን በሰላም መጨረስ በሸዋ አከባቢ ለተከፈሉት የኦሮሞ ባላባቶች
"ያሳደጋችሁኝ ልጃችሁ አብረን ያደግን ባልንጀራችሁ ነኝና በአባቴ አልጋ ከተቀመጥሁ በፍቅር ተገዙልኝ" እያሉ መልዕክተኛ ይልኩ ጀመር፡፡
በዚህም መሰረት
አርሲ:-__አንገዛም ብለው በማስቸገሩ ምኒልክ በ1874 ዘምተው ነበር፡፡
ወለጋ:-__ ባላባቱ ኩምሳ በሰላም ገበሩ
ከፋን ወላይታንም ማስገበር ጀመሩ፡፡
ምኒልክ ከነበሯቸው ጠባይ ዋነኛው የዲፕሎማሲ ዘዴ ስለነበረ ከባላባቱ ጋር ተዋግተው ዋናውን ባለባት ሲማርኩ በቦታው መልሰው ሚሾሙት ያንኑ የድሮውን ባላባት ሲሆን ካልሆነው የበላባቱን ልጅ ያለዚያም ህዝቡን እየሰበሰቡ የመረጠው ይሾሙ ነበር፡፡

እድሜ እና ጤና ከቸረን--
.. ይቀጥላል......

@wegoch @kinchebchabi
@ethio_art
ከመፅሐፍት የተወሰዱ አጫጭርና አስተማሪ ፅሑፎችን ለማግኘት ይቀላቀሉ።
👇👇👇👇👇
@ethio_deraseyane
@ethio_deraseyane
@ethio_deraseyane
@ethio_deraseyane
ያውም ሰልጥኜ! !!!!


የኔ ሃገር ሰው ቋንቋው የነጻነት ነው ። ከልጅነቴ ጀምሮ
ከገጠር የሚመጡት የቆላ ዘመዶቼ ነጻነት የሞላበትን
ንግግራቸውን የሙዚቃ ያህል ማድመጥ ያስደስተኝ ነበር ።
ዘመዶቼ ወደኛ ከተሜዎች ሊጠይቁን ሲመጡ ያን ሸጋ
ቋንቋ ይዘውት ይመጣሉ ። ንግግራቸው ጥበብና ውበት
የታከለበት ነው ። እንደወረደው ንግግራቸው ለኔ ብዙ ስንቅ
ሆኖኛል ። በየጊዜው የቆላ ሃገር ወግና ጨዋታ በሰማሁ
ጊዜ እኒያ ገራገርና ጨዋታ አዋቂ ዘመዶቼ ይታወሱኛል ።
እነሆ ጨዋታ! !!
አንዱ የቆላ ሰው ወደ ፍርድ ቤት ጉዳይ ኖሮት በቀጠሮ
ቀን መጥቶ ስም ጥሪ እየጠበቀ ሳለ ድንገት ስሙ
ይጠራል ፤
ጠሪ ፤ መንገሻ ዳርጌ
ተጠሪ ፤ ሄ ( ቆለኛ አቤት ለማለት ሄ ነው የሚለው ።)
ዳኛ ፤ ይኸ ፍርድ ቤት ነው ። ከእርሻው የለመድከውን ሄይ
ይባላል እንዴ? ??
መንገሻ ሲመልስ ፤ ጌታዬ ያውም ዛሬ ሰልጥኜ ነው እንጅ
ስትጠሩኝ ምን ሁንሃል ነበር መልሴ ።
እውነትም ምን ሁነሃል? ???

ሸጋ ሸጊቱ ጁምኣ ይሁንላቹ!!!!!!

@balmbaras
@getem
@getem
👆👆👆👆
አዲስ ከወጣው ከ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ "የወይራ ስር ጸሎት" ነይ ግጥም ዝፈኚ እና እንዴት ! ያውም አድዋን!? ሚሉት ግጥሞች ቀልቤን ስለሳቡት ለምን አላካፍላቸውም በማለት በራሴ ድምፅ አቅርቤያለሁ

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
2024/09/30 17:20:16
Back to Top
HTML Embed Code: