Telegram Web Link
ለህዝብ ያልታወቀ ከህዝብ የራቀ በዳንኤል ክብረት 16k
On ዘሩ
ለህዝብ ያልታወቀ ከህዝብ የራቀ
ዳንኤል ክብረት

°° ማስገደድ እና ማዘዝ ስልጣን እንጂ
አቅምን እያመለከቱም °°

፨ መጠን 1.1 MB

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch @wegoch
የአፋልጉኝ ማስታወቂያ

የመለስን ራዕይ ያያችሁ

@ethio_art
@wegoch
የስታዲየሙን ክብ የሞላው ባንዲራ

ዛሬ ነበር ባህርዳርስ መገኘት

@wegoch
@ethio_art
Forwarded from AHMEDIN
የታዋቂ ና የአዳዲስ ፀሀፊያንን የፅሁፍ ስራወችን በድምፅ በሚማርክ አቀራረብ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇



@gtmbemesenko
Christiano Ronaldo's lesson...

When he received one of his awards recently, Ronaldo dedicated it to a certain ... *Alberto Fantrau.* Then said: *"Yes I am a great footballer and all my success is thanks to my friend Alberto"*
People looked at each other and said, "Who is this Mr. Fantrau?"

Then Ronaldo went on: *"We played together in a youth team. When Sporting of Lisbon recruiters came to observe us, they told us that the striker who scored the most goals will be recruited into the sports academy.*

*That day we won 3-0. I scored the first goal and then Albert scored the 2nd with the head. And then the 3rd goal was the one that impressed everyone.* *Alberto started from the wing, then found himself face to face with the keeper, dribbled the goalkeeper and all he had to do was push the ball into the empty goal. In the meantime I was running to his side. And instead of shooting into the empty goal, Alberto decided to pass the ball to me and I scored.* *This is how I find myself at the Sporting Lisbon Academy. After the game I went to him, and asked him "why did you do that?" And he replied, "Because I know that you are better than I"*

Curious to know more, the journalists began to investigate and were able to meet this Alberto Fantrau to ask him if the story told by Ronaldo is true, and he confirmed it, adding that his career as a footballer ended after this match as it was the only opportunity to become professional and since that time he has remained unemployed.

*However, journalists, observing his luxurious house and his Mercedes parked in the garage asked Alberto "but being unemployed how could you have such a house and car and living so luxuriously? You seem rather comfortable physically " Alberto's answer: "All that? .. is Ronaldo*

Moral of this story:
Let us ask ourselves the following question: How many of us have ever done something like Ronaldo and Alberto? On the contrary, many of us show the opposite of this story showing selfishness and ingratitude to their mates.

Friends! Let's help each other so that we are proud of the success of our brothers /sisters /friends /relatives
And when we help a person succeed, the latter must never forget those who contributed to this success in his life.
And above all, we should never forget the Karma and that God is watchimg!

Never leave ur roots, however tall u get...


@wegoch
@wegoch
Andualem Tesfaye - A Daniel Kibret story Andualem Tesgaye presents…
° ያልሰማህው ነገር
ዳንኤል ክብረት

፨ ✦ ግሩም እይታ ✦
፨ አቅራቢ አንዷለም ተስፋዬ
፨ መጠን 0.7 MB

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch @wegoch
ሁሉም በሽተኛ ሁሉም ራሴን ባይ 16k
ኤፍሬም እንዳለ @Zerusoutlying
ሁሉም በሽተኛ ሁሉም ራሴን ባይ
ኤፍሬም እንዳለ

፨✦ ድንቅ ወግ ✦
፨ መጠን 1.2 MB

አዘጋጅ @Zerusoutlying
@wegoch @wegoch @wegoch
ጠቅላይ ሚንስትርዬ 16k
በጣም አስቂኝ መጣጥፍ On ዘሩ
ጠቅላይ ሚንስትርዩ 😊

#የአመተቱ_አስቂኝ_ወግ

፨ መጠን 2 MB
፨ ለጠቅላይ ሚንስተሩ ከ አድናቂዎት
የተፃፈ አጅግ አስቂኝ መጣጥፍ።

አዘጋጅ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
✦✦ @Zerusoutlying ✦✦
@wegoch @wegoch @wegoch
​​አንድነትን ከ “ቦ ም ብ” እንማር!!


እስቲ አንድ ጊዜ ከታች ያለውን ምስል በትኩረት ተመልከቱት ጓዶች ! ቦንብ ነው! ቦንብ ምንድን ነው? ዊክፒዲያ ቦንብ? << በቅጽበት በውስጡ በሚፈጠር ኢነርጅ በዙሪያው ባለው አካባቢ ላይ ጭስ፣ ጨረር፣ ከፍተኛ ሙቀት፣ ተቀጣጣይ ነገር ወይም ተፈነጣጣሪ ጠጣር ነገሮች በመርጭት ውድመት የሚያስከትል የጦር መሳሪያ ሲል ይተነትነዋል!! እኔ ግን ከቅዳሜ ጀምሮ ሰለቦንብ ሳሰብ የተለየ ሃሳብ በለጭ አለብኝ ! እንድናገር ይፈቀድልኝ ? አመሰግናልሁ!

ቦ ን ብ በተለይም ምስሉን ከታች የምተመለከቱት ቦንብ የሞት ሳይሆነ የኢትዮጲያ ምሳሌ ይመስለኛል! ተመልከቱት አሰራሩን የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች ተገጣጥመውና ተያይዘው የፈጠሩት አስፈሪ መሳሪያ ነው ! ብረቶቹ የራሳቸው ጠንካሬና ቅርጽ ቀለምና ማንነት(ምንነት) አላችው! ይሁንና በራሳቸው የብረት ቁራጭ በጋራ ግን ማንንም የሚያርዱ ፣ ዝም ቢሉ ጥላትን ሰርዓት የሚያስይዙ ቢፈነዱ መሬት ይሚያርዱ በበጎም በክፉም ክንዳቸው የበረታ እምቅ ሃይል!!

ለምሳሌ አንድ ክፉ ሰው አንዷን የብረት ቁራጭ ብቻ ይዞ መስቀል አደባባይ ቢሄድና <<ይሄን ህዝብ በዚች የብረት ቁራጭ ጭጭ አደርገዋለሁ ዘራፍ>> ቢል ህዝቡን በፍንዳታ ሳይሆን በሳቅ ይገድለዋል! ቦንቡን ይዞ ዘራፍ ቢልስ ? ባይልም እንደው ይዞ ቢገኝ? ማንም ሊስቅ እና ሊያላገጥ አይችልም ! ብረቶቹ ብረት በቻ አይደሉማ!! እንደዛ ነው የአንድነት ሃይል !!!

ጓዶች ቦንብ ዝም ብሎ የማይፈነዳው በውስጡ ለፍንዳታ በቂ የሆነ ኬሚካል ሰለሌለ አይደለም !! እነዚህን የብረት ቁረጥራጮች እንዲህ በአንድ ላይ ያቆማችው ቦንቡ ውስጥ ያለው ኬሚካል በሰላም ሰለተቀመጠ ነው! ሰላሙ ከላይ በምታዩት ቀለበት የሰላም ቃልኪዳን ታሰሯል! ቀለበቱ ሰላም እስከሆነ ድረስ ቀለበቱን ማንም ነቅሎ እስካልወረወረው ድረስ ፣ቀለበቱን ደሙ በጥላች የፈላ ወይም የቀለበቱ መነቀል ምን እንደሚያስከትል ያልገባው እሰካልነቀለው ድረስ ቦንቡ ውስጥ ምንም አይነት አፍራሽ ሪአክሽን አይኖርም፣ እሳት አይጫርም ፣አንድነቱን ይሚበታትን ሃይል ከውስጥ ወደውጭ አይገፋም!! ብረቶቹም ጠላት እንደፈራቸው ወዳጅም እንደታመነባቸው ቦንብ እንደሆኑ ይቆያሉ!!

አገርም እንዲሁ ነው! በተለያዩ ህዝቦች አንድነት ተመስርተን የምንታፈር የምንፈራ ሉዓላዊ አገር ሉዓላዊ ህዝቦች ነን!! የፍቅር ቃልኪዳናችን እንደቦንቡ ቀለበት ሁሉ ፍቅራችን ነው ፣መከባበራችን ነው! እኩልነት ነው! ያልተበታተነው የምንበታተንበት ምክንያት በውስጣችን ሰላልነበረ ዓይደለም ! የአንድነት ቀለበታችን በውጭም በውስጥም ሃይል ሰላልተነቀለ የሚበታትነን የዘር ፣የሐይማኖት እና ወዘተ ኬሚካል ሪአክት እንዲያደርግ ሰላልፈቀድንለት ነበር!! አያችሁ ቦንብ በህጻን እጅ ከገባ ቀለበቱን መጫዋቻ መስሎት ሊነቅለው ይችላል ለዛ ነው ሰልጣንም የበሰለ ሰው ይሚሻው!! ቦምብ በጀብደኛ እጅ ከገባ በጀብዱ ቀለበቱን ነቅሎ ጠፋት ይሆናል ! ለዛ ነው ስልጣን ለጀብደኛ ሊሰጥ የማይገባው ! ሰልጣን ማለት ይችን ቀለበት በከፊለም ሆነ በሙሉ ሳይነቀል ውስጥ ያለው በሁኔታዎች የተፈጠረው አጥፊ ሰው ሰራሽ ልዩነት ወደፍጹም አንድነት እንዲመጣ ለሚተጋ መሪ ቀለበቱን አደራ ብሎ ውክልና መስጠት ነው!!

ይህ ቀለበት በመናናቅ በራስ ወዳድነት በማን አለብኘነትንና ስግብግብነት የተነቀለ ቀን ውስጣችን ጥላቻ ሪአክት ያደርጋል ! ጥላቻ ደግሞ ማንንም አንድ አያደርግም !! የጥላቻ ሃይል ፍንዳታ የሚፈጥር ኔጌቲቭ ኢነርጅ ነው! ባለፈው ቅዳሜ የፈነዳውን ቦንብ ዛሬ ላይ ማንም እንደማይፈራው ሁሉ እንደአገር ከተበታተንን ከተለያየን በኋላ ማንም አይፈራንም አያከብረንም እንኳን ለሌላ ለራሳችን እንስ ያልን <<ነበር>> እንሆናለን! አንዴ የፈነዳን ቦንብ ማንም አይፈራውምና!!


አሌክስ አብርሃም
@wegoch @wegoch
ሰላም ክቡራት እና ክቡራን አባሎቻችን ዛሬ ለሀያ ዓመታት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ተገንብቶ የነበረውን የጥላቻ እና የጥል ግድግዳ ለማፍረስ በጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አህመድ የሚመራ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ባለስልጣናትን ያነገበ አይሮፕላን ወደ አስመራ እየነጎደ ነው

አስመራ ኢትዮጵያንን ለመቀበል ከወትሮው በተለየ ሸብ ረብ ብላ ዝግጅቷን አጠናቃለች ከተማዋም በሁለቱ ሀገራት ባንዲራ እንዳሸበረቀች ላየ ቀን መጥቶ ከሁለት ባንዲራ ወደ አንድ ምንቀየርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ብሎ ተስፋ ቢሰንቅ እውነት አለው


የዛሬውን ታሪካዊ ኩነት በቀጥታ ከዚ ቻነል የትም ሳይሄዱ ይከታተሉ ዘንድ እጋብዛለው

አክባሪያችሁ ወግ ነኝ
እስኪ ተዋደዱ ይያያዝ እጃችሁ
ካለበለዚያማ
በምን ያስታውቃል እኛን መውደዳችሁ

እንዲል ብላቴናው

ሸጋ ቆይታ
@wegoch
@ethio_art
‹‹ሚያው››

አብረን ያየን ሰው ሁሉ ‹‹አፈስሽ አፈስሽ›› እያለ ያወራል።

ቆንጆ፣ ሎጋ፣ ረጋ ያለ እና ዝምተኛ ነው። የወንድ ልጅ አማላይነት የተሰራው ከእነዚህ ተንኮለኛ ንጥረ ነገሮች አይደል?

በፍቅር መውደቅ ከገደል እንደመውደቅ ያማል?
በፍቅር መያዝ እንደ ተስቦ ያማቅቃል?

አዎ። ቢሆንም እያመመኝ እወደዋለሁ። እየማቀቅኩ አፈቅረዋለሁ።

እኔ እወደዋለሁ።

እሱ ግን እንደሁሉም ሰው በግብረስጋ ሳይሆን ከመላእክት ተዳቅሎ እንደተፈጠረ ይለጠጥብኛል። ይንበላጠጥብኛል።
ቢሆንም ስሜቴ ለእርሱ ባሪያ ነው። ሲያወድሰኝ ብቻ የማብብ- ሲኮንነኝ የምጠወልግ ፣ ሲመለከተኝ የማምር- ፊቱን ሲያዞርብኝ የማስቀይም እስከሚመስለኝ ድረስ እወደዋለሁ።

ይሄን አውቃለሁ። ፍቅሬ አቅብጦታል። መውደዴ አቀማጥሎታል።

ብዙ ጊዜ ደህና ስንጫወት እንውልና በድንገት ያኮርፈኛል። ይኮፈሳል። አይኔን ማየት ይጠላል። ያን ጊዜ ሁሉ ነገር ይዞርብኛል። ሳቄ ይከስማል። የልቤ ቡረቃ በሃዘን አታሞ ይተካል።

ይገርመኛል። በስሜቴ ላይ እንዲህ እንዲሰለጥን ከመፍቀዴ በፊት…እሱን ከማግኘቴ በፊት በምን ነበር የምስቀው? በምንስ ነበር የምደሰተው?

‹‹ምን ሆንክብኝ›› እለዋለሁ ልክ እንደዚያ ሲሰራው።

‹‹ምንም አልሆንኩም…ተይኝ ላንብብበት›› ለዚህች ለዚህች ጊዜ ተዘጋጅታ የምትቀመጥ፣ መዥረጥ አድርጎ የሚያወጣት መደበኛ እና የዘወትር መልሱ ናት።

– ኤሊ..
– እ… (ከልቡ ሳይሆን)
– ሻይ በጦስኝ ላፍላልህ?

(ሻይ በጦስኝ ስለሚወድ)

– አልፈልግም
– ፍሬንድስን ልክፈትልህ?
(ፍሬንድስን አይቶ ስለማይጠግብ)
– አላሰኘኝም
– ቶሎ ሃያ ሁለት ሄጄ የፀሃይን ሽሮ ይዤልህ ልምጣ?
(ከትግሬ ሽሮ ሌላ በአለም ላይ ደህና ምግብ ያለ ስለማይመስለው)
– አልራበኝም…
– እሺ ምንድነው ምትፈልገው?
– ተይኝ ላንብብበት…

ይሄኔ ነው የአዳም ረታን አንዱን መፅሃፍ አውጥቶ ጥሎኝ የሚሄደው። ይሄኔ ነው የራሱን ክብ አለም ፈጥሮ አፈናጥሮ የሚያስወጣኝ። ያን ጊዜ ማውራት መቀጠሌ ለሬሳ መድሃኒት ከመስጠት እንደማይለይ ስለማውቅ ጥዬው ለመሄድ እሰናዳለሁ።

መፅሃፉ ላይ ተተክሎ አንዴ የለዘዘ ፈገግታ ሲያሳይ፣ አንዴ ጮህ ብሎ ሲስቅ፣ ከዚያ እንደማልቀስ ሲሰራው በእሱ ስሜት ላይ በሰለጠነው ብቸኛው ሰው አዳም ረታ እቀናለሁ። አንዳንዴም የምወደውን ልጅ ስለነጠቀኝ እያልጎመጎምኩ በልቤ እረግመዋለሁ። ‹‹ብእርህ ይንጠፍ..እጅህን ቁርጥማት ይዘዝበት›› አይነት ነገር።

‹‹ልሄድ ነው ቻው›› እለዋለሁ ጫማዬን አጥልቄ ስጨርስ።

– እሺ..ቻው… ይለኛል ቦግ ቦግ ያሉ አይኖቹን ከመፅሀፉ ሳይለይ። ስሜቱን ከአዳም ረታ ገፀ ባህሪያት ሳያላቅቅ።

ያን ጊዜ ከእንባዬ እየታገልኩ ወደ ቤቴ!

ስምንት ወር አብረን ስንወጣ- ስንገባ – ስንተኛ ስንነሳ- ብረት አሎሎ ልቡን አልፈታልኝም። ስለአለፈ ሕይወቱ አይነግረኝም። ስለወደፊቱ አያወራኝም። ከቤተሰብ- ጓደኛ አያስተዋውቀኝም።

እየቆየ የትርፍ ሰአት ስራው መሆኔ ሲገለፅልኝ ጨምቷ ልጅ ላብድ ደረስኩ። ተዉኩት ስል እያገረሸ በሚያስቸግረኝ አስቀያሚ ፍቅሩ ብሸነፍም ቁርጤን ማወቅ እንዳብኝ አመንኩ።

አንዱን ቅዳሜ ስገሰግስ ቤቱ ደረስኩ። ከሰአት 9 ሰአት ቢሆንም አብዝቶ የሚለብሰውን እህቱ ከካናዳ የላከችለትን ፒጃማ አድርጎ ሶፋው ላይ ተጋድሞ ያነባል። ማንን? ያንን በየአመቱ መፅሃፍ የሚያመርተውን አዳም ረታ።

– ስማ ኤልያስ …እኔ እንደዚህ መቀጠል አልችልም…ማውራት አለብን… አልኩ ቦርሳዬን አንዱ ሶፋ ላይ ወርውሬ አጠገቡ እየተቀመጥኩ።
– እ…. ? አለኝ መፅሀፉን ሳይዘጋ ቀና ብሎ እያየኝ..
– አመልህ ሊገባኝ አልቻለም…እኔ እወድሃለሁ…ግን ማትወደኝ ከሆነ…ማለቴ ልብህን ማትሰጠኝ ከሆነ…

ሳልጨርስ አቋረጠኝ።

– ምንድነው ምትፈልጊው? ተናዶም በማይለወጠው እርጋታና ግዴለሽነቱ ጠየቀኝ
(መፅሃፉን ዘጋ። ጉዳዩ ሲሪየስ ነው!)

– እኔ?
– አዎ አንቺ…ምንድነው ምትፈለጊው?
ምንድነው የምፈልገው? እንዴትስ ብዬ ነው የምጠይቀው…?

ከአንጀቱ- እንዲህ በትኩረት እያየኝ ይጠይቀኛል ብዬ አስቤ ስለማላውቅ እያሰብኩ ያንን ውብ ፊቱን አየሁት።

ጢሙ እንደምወደው አድጓል። ጠጉሩ ጨብረር ብሏል። መከረኛ ፒጃማው እጅጌ እና አንገቱ ጋር መንችኳል።

ዝም ብሎ ያየኛል። ብዙ ጊዜ ይሄን ያህል ጊዜ ሰጥቶ አያየኝም። አንሶላ መሃል ገብተን ወንድና ሴት- ድርና ማግ ስንሆን እንኳን ሳያስበው አይኖቹን በአይኖቼ ስይዘው አይኖቹ ላይ ትኩረትና ፍቅር አላይም። አንዳንዴ እንደውም ውስጤ መቆየት የሰለቸው…እሙሙዬ ውስጥ ዘልአለም የከረመ ያህል የታከተው የሚመስል ነገር አይኖቹ ላይ አነባለሁ።

እንዲህ አይቶኝ አያውቅም።

በማውራት ይሄን ያልተለመደ ክስተት ላቋርጥና ላበላሽ ስላልፈለግኩ ካለሁበት ሶፋ እየተሳብኩ ተጠጋሁት። ማየቱን ቀጥሏል። ደርሼ አንገቴን አንገቱ ውስጥ ቀብሬ በጥልቀት አሸተትኩት። ጦስኝ ጦስኝ ይላል።

ልቤ እንደሰም ሲቀልጥ፣ መንፈሴ በስሜት ማእበል ሲታመስ እንኳን የማወራው የማስበው ነገር ከአንጎሌ ሲተን…

– እህስ….ምንድነው የምትፈልጊው? አለኝ ከአንገቱ ውስጥ በእጁ ጎትቶ እያወጣኝ…
– ምንም…
– ምንም አትፈልጊም?
– ኤሊ…እንድትወደኝ…እንድትወደኝ ነው የምፈልገው…ያ ይከብዳል? ወደ አንገቱ ስር ተመልሼ ልወሸቅ ስል አሁንም መልሶ አወጣኝና በእነዚያ አሸባሪ አይኖቹ እያየየኝ
– መች ጠላሁሽ… ?አለኝ።

– እንደማትጠላኝ አውቃለሁ..ግን አንድ ቀን እወድሻለሁ ብለኸኝ አታውቅም…እ…ከመሬት ተነስተህ ታኮርፈኛለህ…ታበሻቅጠኛለህ…

– ምንድነው የምትፈልጊው? በስርአት ቁጭ ብለን ይሄን ነገር እንቋጨው…አለኝ ለስብሰባ እንደተቀመጠ ሰው መፅሃፉን እንደተከፈተ ሶፋው ላይ አስቀምጦ፣ እጆቹን አጣምሮ።

ቀና ብዬ ተቀመጥኩ።

– ልብህን…ልብህን ነው የምፈልገው…

እጆቹን አመሳቀለና ሳቀ።
ተበሳጨሁ።
– ያስቃል?
– ሃሃ…አዎ..እዚህ መፅሃፍ ላይ ያለው…አንዱ የአዳም ካራክተር ምን አለ መሰለሽ… ልቤን ለሴት ከምሰጥ ለጎረቤት ድመት ብሰጥ ይሻለኛል…

ዝም ብዬ አየሁት።

– ምን ታይኛለሽ..ካንጀቴ እኮ ነው…እውነቱን ነው…
አሁንም ዝም ብዬ አየሁት

– ጨረስን? ወደ መፅሃፌ ልመለስ?
– እየቀለድክ አይመስለኝም…አልኩ በተቀመጥኩበት እየተቁነጠነጥኩ
– አይደለም አልኩሽ እኮ…
– የአንድ ደራሲ ተረት ተረት እያነበብክ የእኛን ሕይወት ማበላሸት አለብህ?
– አዳም ስለማይገባሽ አልፈርድብሽም….
– እሱን ተወው..ዝባዝንኬ አይገባኝም…ድመት ምናምን…ሰውየው የሚያወራውን አያውቀውም…ግን አንተ ምነው ለልብህ እንደዚህ ሳሳህ? ልብህን ሰጥተኸው የጎዳህ ሰው ነበር እንዴ…እየተቁለጨለጭኩ ተጠየቅኩት

ዝም ብሎ ሲያየኝ ቆየና…
– ለምን ጦስኝ ሻይ አታፈይልኝም? ጠዋት የጠጣሁ ነኝ አለኝ መፅሃፉን እያነሳ…
– ለምን አትመልስልኝም…ለምንድነው እንደዚህ ፍቅርን የምትፈራው?
– በናትሽ ሻዩን…እያዛጋኝ ነው….

የምናብ ደጁ ሊዘጋብኝ ነው። ለዛሬ ከዚህ በላይ ሊያናግረኝ አልፈቀደም።
ለሻዩ ወደ ኩሽና መንገድ ጀመርኩና መለስ ብዬ አየሁት
-ኤሊ…
– እ….? (ከልቡ ሳይሆን)
– ልቤን ለሴት ከምሰጥ ለድመት ብሰጥ ይሻለኛል ነው ያልከኝ አይደል..?
– እ…አዎ…

የኩሽና መንገዴን ቀጠልኩ።

ሻይ ጀበናውን በውሃ ሞልቼ ምድጃው ላይ ጣድኩ።
ጦስኙን አዘጋጀሁ።

የእሱን ልብ እንዳገኝ ሰውነቱ ቀርቶብኝ ምነው ለአንዲት ቀን ድመት ባደረገኝ።
የማፈቅረው ልጅ መልሶ እንዲያፈቅረኝ ምነው ለአንድ ሌት ሚያው ባስባለኝ።

ሚያው….


ሕይወት እምሻው

@wegoch
@wegoch
@wegoch
​​እናት +251-912-176-635 ወይዘሮ ሙሉ አብርሃ

ታማሚ +251-920-667-623 አማኑኤል ፍቃደ
0173072831300 ሙሉ አብርሃ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

+14692315220 ዳግማዊት ውጪ ላላችሁ ኢትዮጵያዊያን

መርዳት እንኳን ባንችል ሼር በማረግና ደዉሎ እግዜአብሄር ይማርክ ማለት ትልቅ ነገር ነው
የኤርትራ ህልም! (ክፍል አንድ)
ጸሓፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
----------
ኤርትራ ዛሬ ራሷን የቻለች ሀገር ናት፡፡ ትናንት ግን የኛው
አካል ነበረች፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሤ ብልጥ የሆኑ
መስሎአቸው ለሁላችንም አስፈላጊ የነበረውን የፌዴሬሽን
ፎርሙላ ሰረዙትና ህዝቡን አስቀየሙት፡፡ ደርግ ደግሞ
የራሳችንን ህዝብ እንደ ባዕድ እየቆጠረ በመትረየስ
አጨደው፡፡ በታንክ ደመሰሰው፡፡ በዚህም የተነሳ ወጣቱ
“አደይ ኤሪቲሪያ”ን እየዘመረ ወደ ባርካና ሳህል ነጎደ፡፡
ራሱን አደራጅቶ ጀብሃና ሻዕቢያ ሆኖ መጣ፡፡ ውጤቱም
1983 ላይ ታየ፡፡
የደርግና የኃይለ ሥላሤ ያደረጓቸው ነገሮች ሲገርሙን
በጣም ግራ የሚያጋባው ሶስተኛው መንግሥታችን መጣ፡፡
ይህ የኛ መንግሥት “የተበላሸውን ሁሉ አስተካክለን
አብረን መኖር እንችላለን” ብሎ መከራከር ሲገባው
ጭራሹኑ “ኤርትራ ካልተገነጠለች ኢትዮጵያ ሰላም
አታገኝም” ባይ ሆኖ ተገኘ፡፡ ክፍለ ሀገሩ ወደዚያ ከሄደ
በኋላም መንግሥቱ ከሚከተለው ግልጽነት የጎደለው
አሰራር የተነሳ በ1990 ዓ.ል. ሺዎችን ያረገፈ ግዙፍ
ጦርነት ተቀሰቀሰ፡፡ ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ህዝቦች
ተጋደሉ፡፡ እነሆ ዛሬም ድረስ ነገሩ ሳይለይለት በጨለማ
ውስጥ ነው ያለነው፡፡
እኛ ግን ተስፋ አንቆርጥም! በአያያዝ ጉድለት የተለየንን
ወገናችንን መመለስ እንፈልጋለን፡፡ ህዝቡ ለጊዜው
ሪፈረንደም አድርጎ ነጻነቱን ማወጁን ብንደግፍለትም አንድ
ቀን ተቀራርበን በጋራ ስለመስራት እንወያይ ይሆናል ብለን
እናልማለን፡፡ የኛ ልጆች ደግሞ በኮንፌዴሬሽን ስለመስራት
ያስቡ ይሆናል፡፡ የልጅ ልጆቻችን በፈቃደኝነት ስለመዋሃድ
ያስቡ ይሆናል፡፡ በዚያን ጊዜም አሁን የምንመኘው
በአንድነት ውብ የመሆን ሚስጢራችን ይመለስልናል ብለን
እናልማለን፡፡ ምን ይታወቃል?
ወገኖቼ ደጉን ነው የተመኘሁት፡፡ በቅን ልቦና በርትተን
ከጸለይንና ከኛ የሚጠበቀውን ካደረግን ሁሉንም
የሚችለው ፈጣሪ ህልማችንን እውነት ያደርግልናል ብለን
ተስፋ እናደርጋለን፡፡
-------
ምን እንደጣለብኝ እንጃ! ያንን ምድር እጅግ ሲበዛ
እወደዋለሁ፡፡ እኔ ለተወለድኩበትና አብዛኛውን ዘመኔን
ለጨረስኩበት የምስራቅ ኢትዮጵያ ክልል ጎረቤት
ከሆነችው ሶማሊያ ይልቅ በ1600 ኪ.ሜ. የምትርቀው
አስመራ ናት የምትናፍቀኝ፡፡ ስለሶማሊያ የተጻፈ መጽሐፍ
ማንበብ ብዙም አይማርከኝም፡፡ ስለ ኤርትራ የተጻፈ
መጽሐፍ ካጋጠመኝ ግን ሳላየው አላልፍም (ይህ ግን
ሶማሊያን ከመጥላት እንደማይቆጠርብኝ ተስፋ
አደርጋለሁ)፡፡
ታዲያ በርካቶቻችሁም እንደኔው ትመስሉኛላችሁ፡፡ ለምሳሌ
ከ1970ዎቹ ጀምሮ ሲታተም የቆየው የቤኒ አምሩን
ወጣት የሚያሳየው ፖስተር ዛሬም ድረስ ከኛ ጋር ተሳስሮ
ነው ያለው፡፡ አሁንም ድረስ በበርካታ ስፍራዎች ተለጥፎ
አይቼዋለሁ፡፡ በፌስቡክም እርሱን እንደ ፕሮፋይል ፒክቸር
የሚጠቀም ኢትዮጵያዊ ሞልቷል፡፡ በሌላ በኩል የኤርትራን
ሙዚቃ የሚያዳምጡ ሰዎች በሽ ናቸው፡፡ ደራሲ መሐመድ
ሳልማን መቐለ ሄዶ ያየው ነገር ቢያስገርመው “በኤርትራ
ሙዚቃ የምትጨፍር ከተማ” የሚል አስደናቂ ወግ ጽፎ
እውነቱን አስረድቶናል፡፡ መንግሥታት ቢጣሉ እንኳ ህዝቦች
ምንጊዜም እንደሚነፋፈቁ ከዚህ በላይ የሚያስረዳ ዋቢ
ያለ አይመስለኝም፡፡
--------
ማርታ ሀይሉን አስታወሳችኋት? አዎን! ማርታን “ብራ…
ነው… ብራ ነው”፤ “አዘዞ”፤ “ሎጋ ..ና እናውጋ” በተሰኙት
ዘፈኖቿ እናውቃታለን፡፡ ከማርታ ዘፈኖች ዘወትር ቀልቤን
ይገዛ የነበረው ግን የትግርኛ ዜማዋ ነው፡፡ አዝማቹ
እንዲህ ይመስለኛል፡፡
ካብ አስመራ ድንገት ርእዮ
ምጽዋ ገባሁ ልበይ ሕብዮ
እንተርጉመው እንዴ?… ግድ የለም ማርታ ራሷ እንዲህ
እያለች በአማርኛ ተርጉማዋለች፡፡
“ከአስመራ ድንገት አይቼው
ምጽዋ ገባሁ ልቤን ሰጥቼው”፡፡
አዎን! ትናንት የኛ ናት ስንላት ለነበረችው ኤርትራ ነው
እንዲህ የዘመርንላት፡፡ ዛሬም ብንዘምርላት እንከበራለን
እንጂ አንወቀስም፡፡ ምክንያቱም በመንግሥት ደረጃ ነው
የተለያየነው፡፡ ሁለት ፓስፖርት እንዲኖረን ነው
የተደረግነው፡፡ ሁለታችንም ግን አንድ ህዝቦች ነን፡፡
በደምም ሆነ በባህል በጣም የተዋሃድን የአንድ መሬት
ብቃዮች ነን፡፡ ሁለታችንም የተዋብን የሴምና የኩሽ
ህዝቦች ውቅር ነን፡፡ እንደኛ የሚያምር ህዝብ በትኛውም
ዓለም የለም፡፡ የጀበና ቡና፣ ዶሮ ወጥ፣ ድፎ ዳቦ፣ የስጋ
ፍትፍት፣ አምባሻ፣ ወዘተ…. ሁለታችን ዘንድ ብቻ ነው
ያለው፡፡
-----
በርግጥ እላችኋለሁ፡፡ በምንባብና በወሬ እንጂ በአካል
የማላውቃት ኤርትራ ትናፍቀኛለች! ያ በታሪክ ምዕራፎች
“ምድሪ ባህረ ነጋሽ” እየተባለ ሲጠራ የኖረው ጀግና
መሬትና ህዝብ ይናፍቀኛል፡፡ ያ የሰሜኑ በረኛ እያልን
እንመካበት የነበረው ህዝባችን ይናፍቃል፡፡
እውነትም ኤርትራ ! የዳማት ታሪክ ውቅር! የመጠራ
አብያተ መንግሥታት ከርስ! የሀውልቲ ፍርስራሾች ቀብር!
የአዱሊስና የዙላ ወደቦች መዘክር! የሱዋኪምና የዳህላክ
ሱልጣኖች ደብር!
ኤርትራ የአብረሃ ደቦጭ ሀገር! የሞገሥ አስገዶም ሀገር!
የዘርዓይ ደረስ ሀገር! የሎሬንዞ ታዕዛዝ ሀገር! የደጃች
ሀረጎት ሀገር! በአይበገሬ ጀግንነታቸው ድፍን አፍሪቃን
ያኮሩ አርበኞች የበቀሉበት ምድር!
ኤርትራ የበረከት መንግሥተ አብ ሀገር! የአብረሃም
አፈወርቂ ሀገር! የአሕመድ ሼኽ ሀገር! የሄለን መለስ
ሀገር! የየማነ ባሪያው ሀገር! የሄለን ጳውሎስ ሀገር!
በስርቅርቅ ድምጻቸው የሰውን ልብ እየሰረሰሩ የመግባት
ሀይል ያላቸው የጥበብ ከዋክብት የወጡበት መንደር!
ኤርትራ የፊያሜታ ጊላይ ሀገር! የስዕላይ በራኺ ሀገር!
የኦቦይ ተኽሌ ሀገር! የተክላይ ዘድንግል ሀገር! የሆቴል
ፓራዲዞ ሀገር! የዕቁባይ ሲላ ሀገር! የምንወደው
ደራሲያችን በዓሉ ግርማ በ“ኦሮማይ” መጽሐፉ እንደ
ፊልም ግልጥልጥ አድርጎ እየተረከልን ዝንተ-ዓለም
እንድንወዳት ያደረገን የቀይ ኮከብ ትዝታ ወመዘክር!
ኤርትራ የፊዮሪ ሀገር! የሳባ ሀገር! የማርቲና ሀገር!
የብርኽቲ ሀገር! ፊያሜታ ጊላይን የመሳሰሉ “ሽኮሪናዎች”ን
ያበቀለች ውብ የውቦች እመቤት!
-----
ኤርትራን ስንጠራ በቅድሚያ ወደ አዕምሮአችን
የምትመጣው አስመራ ናት፡፡ የአስመራ ናፍቆት ይገድላል፡፡
አስመሪና፣ አስመሪቲ፣ አቲ ጽብቕቲ!…
ውይ ስታምር! “ቀሽቲ” እኮ ናት፡፡ ያኔ በልጅ አዕምሮአችን
በዘምባባ ጥላዋ ተሸክፋ በፖስትካርድ ስትቀርብልን “የኛ
ውቢት” እያልን እንመጻደቅባት ነበር፡፡ እንቆቅልሽ
ስንጫወትና መልሱ ጠፍቶን “ሀገር ስጠኝ” ስንባል እርሷን
ለመስጠት እንሰስት ነበር፡፡ ጠያቂውም የዋዘ ስላልሆነ
“አስመራ” ካላልነው ለጠየቀን ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ
አይነግረንም ነበር፡፡ ከማናውቃቸው “ዋሽንግተንና” ሮማ
አስመራ ነበር የምትበልጥብን፡፡ በትምህርት ቤት
መዝሙራችንም እንዲህ እንል ነበር፡፡
ኦኬ ኦኬ ኦኬ ስራ
ሰላም ሰላም ወደ አስመራ
አዲስ አስተማሪ ከጃፓን የመጣ
ማስተማሩን ትቶ በቦክስ የሚማታ
አናግረኝና አናግርሃለሁ
በአሜሪካ ሽጉጥ አዳፍንሃለሁ፡፡
ግጥሙ “አንታራም” የሚሉት የህጻናት ጨዋታ ዓይነት
ነው፡፡ ነገር ግን አስመራ ከልባችን እንዳትጠፋ አድርጓል፡፡
ዛሬም በልባችን ነግሳለች አስመሪና!
----
አስመሪና! እንተይ ሽኮሪና! ሰሜናይት ጽብቕቲ! በዓሉ
ግርማ ላንቺ ክብር የጻፈው ትዝ ይልሻል? እስቲ
እናስታውሰው!
አስመሪና አስመራዬ
ካብ ሐንቲ ንግሥቲ ይበልፅ መልክእኪ
አማአድዬ ክርእየኪ ከሎኹ ኽአ
አብ ኢደይ ዘሎ ነገር ይወድቕ፡፡
------
ጸጸራት፤ ፎርቶ፣ ሐዝሐዝ፣ አርበእተ አስመራ፣
እምባጋሊያኖ፣ ኮምቢሽታቶ፣ አዲጓእዳድ፣ ቃኘው፣
ማይተመናይ፣ ሰምበላይ፣ ጎዳይፍ፣ ገጀረት፣ ወዘተ…
በጽሑፍ የማውቃቸው የአስመራ
ሰፈሮች ናቸው፡፡ አንድ
ቀን በሆነልኝና ባየኋቸው እያልኩ አልማሁ፡፡ እነዚህ
አስገራሚ የአስመሪና ሰፈሮች ብዙ ባለታሪኮችን
አብቅለዋል፡፡ ብዙዎች ገድላቸው እየተደጋገመ
ሲነገርላቸው እሰማለሁ፤ አነባለሁ፡፡ ለኛ ቅርብ የነበረ
አንድ ውድ ልጅ እየተረሳ በመሆኑ ግን አዝኛለሁ፡፡
አማኑኤል እያሱ ይባላል! አስታወሳችሁት አይደል? አዎን!
አማኑኤል በኛ ዕድሜ ዘመን ኢትዮጵያ ዋንጫ መብላት
እንደምትችል ያስመሰከረው የታላቁ የ1980 የእግር ኳስ
ቡድናችን ቋሚ ተሰላፊ ነበረ፡፡ የማሊያ ቁጥሩ 2
ይመስለኛል፡፡ አማኑኤል የያኔው ቡድናችን ባደረጋቸው
ሁሉም ጨዋታዎች ተሰልፏል፡፡ ቡድኑ ዋንጫውን ሲበላም
ከጓደኞቹ ጋር ቤተመንግሥት ድረስ ተጋብዞ ተሸልሟል፡፡
አማኑኤልን ያስገኘው ከዚያ ዘመን ዝነኛ ቡድኖቻችን
መካከል አንዱ የነበረው የኤርትራ ጫማ ቡድን ነው፡፡ ይህ
ቡድን የኤርትራ አንደኛ ዲቪዚዮን ዋንጫን በተደጋጋሚ
ያሸነፈ ነው፡፡
አማኑኤል እያሱ በኢትዮጵያ ትቅደም አንደኛ ደረጃ
ዋንጫም ለኤርትራ ክፍለ ሀገር ምርጥ ቡድንም ተሰልፎ
ተጫውቷል፡፡ ባልሳሳት የ1981 የኢትዮጵያ ዋንጫን
ያሸነፈው እነ አማኑኤል የነበሩበት የኤርትራ ክፍለ ሀገር
ቡድን ነው፡፡ የአማኑኤል እያሱን ወሬ ለመጨረሻ ጊዜ
ያነበብኩት በ1988 ለወዳጅነት ጨዋታ አዲስ አበባ
መምጣቱን በማስመልከት በርካታ የግል ጋዜጦች ቃለ-
መጠይቅ ባደረጉለት ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ ወዲህ በምን ሁኔታ
ላይ እንዳለ መረጃው የለኝም፡፡ እስቲ የአስመራ ልጆች
ወሬው ካላችሁ ስለአማኑኤል እያሱ አንድ ነገር በሉን፡፡
-----
ወደ ምዕራብ ኤርትራ ተሻግረናል! ባርካና ጋሽ የሚባሉት
የኤርትራ ቆላዎች እዚህ ነው ያሉት፡፡ አቆርዳት፣ ተሰነይ፣
አሊጊደር፣ ባሬንቱ የተሰኙት ከተሞችም በቆላው ውስጥ
ተዘርግተዋል፡፡ ኩናማ፣ ናራ እና ቤጃ የተሰኙት ብሄረሰቦች
እዚህ ነው የሚኖሩት፡፡ የአካባቢው ዋነኛው ህዝብ ግን
ለኛ በጣም ቅርብ ሆኖ ዓመታትን ያስቆጠረውን ሳቂታውን
የቤኒ አምር ወጣት ያስገኘው የትግረ ህዝብ ነው፡፡
የትግረ ህዝብ በውስጡ በርካታ ጎሳዎች አሉት፡፡ ከሁሉም
የሚበረክተው ግን የቤኒአምር ጎሳ ነው፡፡ ህዝቡ
የሚነጋገርበት የትግረ ቋንቋ ከሴማዊ ቤተሰብ ነው
የሚመደበው፡፡ ለዚህ ቋንቋ በጣም የሚቀርበው በደጋው
ኤርትራና በኛዋ የትግራይ ክልል የሚነገረው ትግርኛ ነው፡፡
እነዚህ ሁለት ቋንቋዎች ከጥንታዊው የግዕዝ ቋንቋ ነው
የተወለዱት፡፡ የትግረ ቋንቋ ከኤርትራ ሌላ በሱዳንም
(ከሰላ አካባቢ) በስፋት ይነገራል፡፡
ትግረና ትግርኛ በጣም ከመመሳሰላቸው የተነሳ እንግዳ
ለሆነ ሰው አንድ ዓይነት ቋንቋዎች ሊመስሉት ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም ለትግርኛ ተናጋሪዎች የትግረ ቋንቋን
መልመድ በጣም ቀላል ነው ይባላል፡፡ የትግረ ተናጋሪም
ትግርኛን በቶሎ መልመድ ይቀለዋል፡፡ በመሆኑም በዛሬዋ
ኤርትራ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝብ ሁለቱንም
ቋንቋዎች መናገር ይችላል፡፡
ምዕራባዊው ቆላ ኤርትራዊያን በጣም የሚያደንቋቸውን
እንደ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ፣ ሙሐመድ ኢድሪስ እና
ኢድሪስ ገላውዴዎስን ያፈራ መሬት ነው፡፡ በዚህ ሰሞኑን
ልቤን ያሸፈተው የትግረ ልጅ ግን “አሕመድ ሼክ” ነው፡፡
አሕመድ ሼክን አወቃችሁት አይደል? አዎን! “ባቡሬይ”፣
“ኢላ ሰርጎ” ወዘተ.. እያለ በማይጠገበው የትግረ ምት
የሚያዜመው ተወዳጅ ድምጻዊ ነው፡፡ አንድ ኤርትራዊ
ወዳጃችን “ኤላ ሰርጎ”ን ሲፈታልን `ከጀርባው ፌሎሶፊ
አለው” ነው ያለኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
የትግረ ሴት ለምትወደው አንድ ሰው (ለባሏ) እንጂ
ለማንም ጸጉሯን አትገልጠውም፡፡ ስለዚህ ጉብሊቷን ልጅ
የወደደው አሕመድ ሼክ በተዋቡ ግጥሞች እያወደሳት
ዘፈነላትና ፍቅሩ ልቧ ውስጥ ዘልቆ መግባቱን ለማረጋገጥ
ጸጉሯን ማየት ጀመረ፡፡ እርሷም ግጥሞቹን ከሰማችለት
በኋላ ጸጉሯን ገልጣ አሳየችው፡፡ ድል አድራጊው ወዲ
ሼክም ይዟት በረረ፡፡ ኤላ ሰርጎ! ኤላ ሰርጎ” እያለ ነጎደ!
------
ሰሜን ኤርትራ!
ተወዳጇ የከረን ከተማ እዚህ ነው ያለችው! የሀረርጌዋ
የድሬ ዳዋ ከተማ መንትያ እህት የምትመስለው ውቢቷ
የሰሜን ፈርጥ! በቪዲዮ አይቻት ውበቷን አደነቅኩላት!
አበቦቹ! ቤቶቹ! መንገዶቹ ሁሉም ውብ ናቸው፡፡ ከትግራይ
የተገኘው ዝነኛው ብርሃነ ሃይለ አንድ ላይ በነበርነት ዘመን
ለከረኗ ጉብል እንዲህ ብሎላታል፡፡
ሸው በሊ ብለነይ ብለነይ
ዝለሊ ብለነይ ብለነይ
አሊሊ ብለነይ ብለነይ
አቲ ጓል ከረነይ ብለነይ
አዎን! ቢለን ከከረን ከተማ ጋር ስሙ የሚጠቀስ ብሄረሰብ
ነው፡፡ ቋንቋው ከኛው የአገው ቋንቋ ጋር አንድ ዐይነት
ነው፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይ ነው አንባቢ ሊመራመር
የሚገባው፡፡ በወሎና በጎጃም የሚኖረው አገው ምን
ሊያደርግ እዚያ ሄደ?… መቼ ነው እዚያ የሄደው?…
መላምት ከመዘብዘብ በስተቀር ማንም ሰው ይህንን
እንቆቅልሽ በሚያመረቃ ሁኔታ ሊፈታው አልቻለም፡፡
ኤርትራና እኛ አንድ ነን የሚያሰኘኝ እንዲህ ዓይነት
ተጨባጭ ማስረጃ ስላለን ነው፡፡
ቢለን ውብ ባህል ያለው ህዝብ ነው፡፡ በዚህ ህዝብ ባህል
መሰረት ሴቶቹ ካገቡ በኋላ ጸጉራቸውን መሰተር ግድ
ነው፡፡ ህዝቡ የቢለን ቋንቋ ተናጋሪ ቢሆንም የትግረ
ቋንቋንም ይጠቀማል፡፡ ትግርኛም በስፋት ይነገራል፡፡
እጅግ ታዋቂ የሆነው የቢለን ተወላጅ “ዑመር እዛዝ”
ነው፡፡ የጀብሃ ጦር ከመፍረክረኩ በፊት የሁለተኛው ዞን
አዛዥ እንደነበረ ከዚህ በፊት ጽፌ ነበር፡፡
ከከረን ሽቅብ ወደ ሰሜን ስናመራ ታሪካዊቷ አፋቤት
አለች፡፡ ጄኔራል ታሪኩ አይኔ የሚመራው ናደው እዝ እዚህ
ነበር የሰፈረው፡፡ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ዋና አምባም ይህ
ነበር፡፡ ከአፋቤት ወደ ሰሜን ስንበር ንዳዳማውና
አስቸጋሪው የሳህል መሬት አለ፡፡ በዓሉ ግርማ
እንደተረከልን ከሆነ ሳህል ማለት እሳት ነው፡፡ ነገር ግን
ሰዎች ይኖሩበታል፡፡ ከብቶች ይሰማሩበታል፡፡ ተክልም
ይበቅልበታል፡፡ እዚህ አካባቢ በብዛት የሚኖረው ህዝብ
“ረሺዳ” ይባላል (አንዳንዶች “ራሻይዳ” ይሉታል፤ ስህተት
ነው፤ ትክክለኛው አጠራር “ረሺዳ” ነው)፡፡
የ“ረሺዳ” ህዝብ ከሌላው የኤርትራ ህዝብ የሚለይበት
በርካታ ነገሮች አሉት፡፡ ለምሳሌ ይህ ህዝብ ከሳዑዲ
ዐረቢያ ተነስቶ ወደ ኤርትራ የገባው በቅርብ ዘመን
(በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ) ነው፡፡ በዚያ ወቅት
የአሁኗ ሳዑዲ ዐረቢያ አልነበረችም፡፡ ሀገሩ ሁሉ በጎሳዎች
የተከፋፈለ በረሃማ ምድር ነበር፡፡ ከነዚህ ጎሳዎች አንዱ
አል-ረሺድ ይባላል፡፡ ይህ የአል-ረሺድ ህዝብ የአካባቢው
የበላይ እንዲሆን በኦቶማን ቱርክ ተወሰነ፡፡ አብዛኛው
ህዝብም ለነርሱ አደረ፡፡ “አል-ሱዑድ” የሚባለው ቤተሰብ
ግን “አሻፈረኝ” አለ፡፡ “ራሴ በረሃውን ጠቅልዬ መግዛት
ስችል ለምን በአል-ረሺድ ጎሳ የበላይነት አድራለሁ”
በማለት አንገራገረ፡፡ በሁለቱ መካከል ጠብ ተነሳ፡፡
በመጀመሪያው ላይ የአል-ረሺድ ጎሳ አሸነፈ፡፡ አል-
ሱዑዲዎች ወደ ኢራቅ ሸሹ፡፡
ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን የአል-ሱዑድ ቤተሰብ
በእንግሊዞች ደጋፊነት ራሱን አጠናክሮ መጣ፡፡ በአል-
ረሺድ ጎሳ ላይም ድልን ተቀዳጀ፡፡ በዚህም የተነሳ
የዐረቢያ በረሃ ለአል-ረሺድ ጎሳ አባላት ሲኦል ሆነ፡፡
ረሺዳዎች እየተያዙ በጅምላ ታረዱ፡፡ ንብረታቸው ተዘረፈ፡፡
በፊት ይረዳቸው የነበረው የቱርኮች መንግሥት በራሱ
ችግር በመወጠሩ ምንም ሊያደርግላቸው አልቻለም፡፡
በመሆኑም ከእልቂቱ ለመዳን ሲሉ ባህር እያቋረጡ ወደ
አፍሪቃ ምድር ተሰደዱ፡፡ በሱዳንና በኤርትራ መኖሪያቸውን
ቀለሱ፡፡
እንግዲህ ረሺዳዎች ከዘር ማጥፋት ወንጀል ለመሸሽ ወደ
ኤርትራ የመጡ ተፈናቃዮች ናቸው ማለት ነው፡፡ በኤርትራ
ውስጥ ንጹህ የዐረብ ዝሪያ የሚባሉት እነርሱ ናቸው፡፡
የአፍ
መፍቻ ቋንቋቸውም ዐረብኛ ነው፡፡ በረሺዳ ባህል
መሰረት ለአካለ መጠን የደረሰች ማንኛዋም ሴት ፊቷንም
ሆነ ጸጉሯን መሸፈን ግዴታዋ ነው፡፡ በዓሉ ግርማ
በኦሮማይ ውስጥ ሲተርክልን “ማንኛውም የረሺዳ ባል
የሚስቱን ፊት ገልጦ የሚያይበትን ሰው አይፈልግም”
በማለት የተናገረውም የባህላቸው አንድ አካል ነው፡፡
-----------------
(ይቀጥላል)

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch
.. የኤርትራ ህልም! (ክፍል ሁለት)
ፀሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
----
የኢትኖግራፊ ሽርሽራችን በኤርትራ ምድር ቀጥሏል፡፡ አሁን
ወደ ምዕራብ ኤርትራ ተሻግረናል! ባርካና ጋሽ የሚባሉት
ቆላማ አውራጃዎች እዚህ ነው ያሉት፡፡ አቆርዳት፣ ተሰነይ፣
አሊጊደር፣ ኡምሐጀር፣ ባሬንቱ የተሰኙት ከተሞች በቆላው
ምድር ውስጥ ተዘርግተዋል፡፡ ኩናማ፣ ናራ እና ቤጃ
የሚባሉት ብሄረሰቦች እዚህ ነው የሚኖሩት፡፡ የአካባቢው
ዋነኛው ህዝብ ግን ለኛ በጣም ቅርብ የሆነውን ሳቂታውን
የቤኒ አምር ወጣት ያስገኘው የትግረ ህዝብ ነው፡፡
የትግረ ህዝብ በውስጡ በርካታ ጎሳዎች አሉት፡፡ ከሁሉም
የሚበረክተው ግን የቤኒ አምር ጎሳ ነው፡፡ ህዝቡ
የሚነጋገርበት የትግረ ቋንቋ ከሴማዊ ቤተሰብ ነው
የሚመደበው፡፡ ለዚህ ቋንቋ በጣም የሚቀርበው በደጋው
ኤርትራና በኛዋ የትግራይ ክልል የሚነገረው ትግርኛ ነው፡፡
እነዚህ ሁለት ቋንቋዎች ከጥንታዊው የግዕዝ ቋንቋ ነው
የተወለዱት፡፡ ይህንን ቋንቋ ከ35 በመቶ የማያንሰው
የኤርትራ ህዝብ ይናገረዋል፡፡ የትግረ ቋንቋ ከኤርትራ ሌላ
በሱዳንም (ከሰላ አካባቢ) በስፋት ይነገራል፡፡
ትግረና ትግርኛ በጣም ከመመሳሰላቸው የተነሳ እንግዳ
ለሆነ ሰው አንድ ዓይነት ቋንቋዎች ሊመስሉት ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም ለትግርኛ ተናጋሪዎች የትግረ ቋንቋን
መልመድ በጣም ቀላል ነው ይባላል፡፡ የትግረ ተናጋሪም
ትግርኛን በቶሎ መልመድ ይቀለዋል፡፡ በመሆኑም
ከጠቅላላው የኤርትራ ህዝብ 50% የሚሆነው ሁለቱንም
ቋንቋዎች መናገር ይችላል (ይህ ቁጥር ትግርኛ ብቻ
የሚናገሩትን፣ ወይንም “ትግረ” ብቻ የሚናገሩትን
አይጨምሩም)፡፡
ምዕራባዊው ቆላ ኤርትራዊያን በጣም የሚያደንቋቸውን
እንደ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ፣ ሙሐመድ ኢድሪስ እና
ኢድሪስ ገላውዴዎስን ያፈራ መሬት ነው፡፡ በዚህ ሰሞን
ልቤን ያሸፈተው የትግረ ልጅ ግን “አሕመድ ሼክ” ነው፡፡
አሕመድ ሼክን አወቃችሁት አይደል? አዎን! “ባቡሬይ”፣
“ኢላ ሰርጎ” ወዘተ.. እያለ በማይጠገበው የትግረ ምት
የሚያዜመው ተወዳጅ ድምጻዊ ነው፡፡ አንድ ኤርትራዊ
ወዳጃችን “ኤላ ሰርጎ”ን ሲፈታልን `ከጀርባው ፌሎሶፊ
አለው” ነው ያለኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
የትግረ ሴት ለምትወደው አንድ ሰው (ለባሏ) እንጂ
ለማንም ጸጉሯን አትገልጠውም፡፡ ስለዚህ ጉብሊቷን ልጅ
የወደደው አሕመድ ሼክ በተዋቡ ግጥሞች እያወደሳት
ዘፈነላትና ፍቅሩ ልቧ ውስጥ ዘልቆ መግባቱን ለማረጋገጥ
ጸጉሯን ማየት ጀመረ፡፡ እርሷም ግጥሞቹን ከሰማችለት
በኋላ ጸጉሯን ገልጣ አሳየችው፡፡ ድል አድራጊው ወዲ
ሼክም ይዟት በረረ፡፡ “ኤላ ሰርጎ! ኤላ ሰርጎ” እያለ ነጎደ!
------
ሰሜን ኤርትራ!
ተወዳጇ የከረን ከተማ እዚህ ነው ያለችው! የሀረርጌዋ
የድሬ ዳዋ ከተማ መንትያ እህት የምትመስለው ውቢቷ
የሰሜን ፈርጥ! በቪዲዮ አይቻት ውበቷን አደነቅኩላት!
አበቦቹ! ቤቶቹ! መንገዶቹ ሁሉም ውብ ናቸው፡፡ ከትግራይ
የተገኘው ዝነኛው ብርሃነ ሃይለ አንድ ላይ በነበርነበት
ዘመን ለከረኗ ጉብል እንዲህ ብሎላታል፡፡
ሸው በሊ ብለነይ ብለነይ
ዝለሊ ብለነይ ብለነይ
አሊሊ ብለነይ ብለነይ
አቲ ጓል ከረነይ ብለነይ
አዎን! ቢለን ከከረን ከተማ ጋር ስሙ የሚጠቀስ ብሄረሰብ
ነው፡፡ ቋንቋው ከኛው የአገው ቋንቋ ጋር አንድ ዐይነት
ነው፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይ ነው አንባቢ ሊመራመር
የሚገባው፡፡ በወሎና በጎጃም የሚኖረው አገው ምን
ሊያደርግ እዚያ ሄደ?… መቼ ነው እዚያ የሄደው?…
መላምት ከመዘብዘብ በስተቀር ማንም ሰው ይህንን
እንቆቅልሽ በሚያመረቃ ሁኔታ ሊፈታው አልቻለም፡፡
ኤርትራና እኛ አንድ ነን የሚያሰኘኝ እንዲህ ዓይነት
ተጨባጭ ማስረጃ ስላለን ነው፡፡
ቢለን ውብ ባህል ያለው ህዝብ ነው፡፡ በዚህ ህዝብ ባህል
መሰረት ሴቶቹ ካገቡ በኋላ ጸጉራቸውን መሰተር ግድ
ነው፡፡ ህዝቡ የቢለን ቋንቋ ተናጋሪ ቢሆንም የትግረ
ቋንቋንም ይጠቀማል፡፡ ትግርኛም በስፋት ይነገራል፡፡
በጣም ታዋቂ የሆነው የቢለን ተወላጅ “ዑመር እዛዝ”
ነው፡፡ የጀብሃ ጦር ከመፍረክረኩ በፊት የሁለተኛው ዞን
አዛዥ እንደነበረ ከዚህ በፊት ጽፌ ነበር፡፡
ከከረን ሽቅብ ወደ ሰሜን ስናመራ ታሪካዊቷ አፋቤት
አለች፡፡ ጄኔራል ታሪኩ አይኔ የሚመራው ናደው እዝ እዚህ
ነበር የሰፈረው፡፡ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ዋና አምባም ይህ
ነበር፡፡ ከአፋቤት ወደ ሰሜን ስንበር ንዳዳማውና
አስቸጋሪው የሳህል መሬት አለ፡፡ በሰህል እምብርት ላይ
የኤርትራ ገንዘብ መጠሪያ ለመሆን የበቃችሁ “ናቅፋ”
አለች፡፡ በዓሉ ግርማ እንደተረከልን ከሆነ ሳህል ማለት
እሳት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ይኖሩበታል፡፡ ከብቶች
ይሰማሩበታል፡፡ ተክልም ይበቅልበታል፡፡ እዚህ አካባቢ
በብዛት የሚኖረው ህዝብ “ረሺዳ” ይባላል (አንዳንዶች
“ራሻይዳ” ይሉታል፤ ስህተት ነው፤ ትክክለኛው አጠራር
“ረሺዳ” ነው)፡፡
የ“ረሺዳ” ህዝብ ከሌላው የኤርትራ ህዝብ የሚለይበት
በርካታ ነገሮች አሉት፡፡ ለምሳሌ ይህ ህዝብ ከሳዑዲ
ዐረቢያ ተነስቶ ወደ ኤርትራ የገባው በቅርብ ዘመን
(በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ) ነው፡፡ በዚያ ወቅት
የአሁኗ ሳዑዲ ዐረቢያ አልነበረችም፡፡ ሀገሩ ሁሉ በጎሳዎች
የተከፋፈለ በረሃማ ምድር ነበር፡፡ ከነዚህ ጎሳዎች አንዱ
አል-ረሺድ ይባላል፡፡ ይህ የአል-ረሺድ ህዝብ የአካባቢው
የበላይ እንዲሆን በኦቶማን ቱርክ ተወሰነ፡፡ አብዛኛው
ህዝብም ለነርሱ አደረ፡፡ “አል-ሱዑድ” የሚባለው ቤተሰብ
ግን “አሻፈረኝ” አለ፡፡ “ራሴ በረሃውን ጠቅልዬ መግዛት
ስችል ለምን በአል-ረሺድ ጎሳ የበላይነት አድራለሁ”
በማለት አንገራገረ፡፡ በሁለቱ መካከል ጠብ ተነሳ፡፡
በመጀመሪያው ላይ የአል-ረሺድ ጎሳ አሸነፈ፡፡ አል-
ሱዑዲዎች ወደ ኢራቅ ሸሹ፡፡
ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን የአል-ሱዑድ ቤተሰብ
በእንግሊዞች ደጋፊነት ራሱን አጠናክሮ መጣ፡፡ በአል-
ረሺድ ጎሳ ላይም ድልን ተቀዳጀ፡፡ በዚህም የተነሳ
የዐረቢያ በረሃ ለአል-ረሺድ ጎሳ አባላት ሲኦል ሆነ፡፡
ረሺዳዎች እየተያዙ በጅምላ ታረዱ፡፡ ንብረታቸው ተዘረፈ፡፡
በፊት ይረዳቸው የነበረው የቱርኮች መንግሥት በራሱ
ችግር በመወጠሩ ምንም ሊያደርግላቸው አልቻለም፡፡
በመሆኑም ከእልቂቱ ለመዳን ሲሉ ባህር እያቋረጡ ወደ
አፍሪቃ ምድር ተሰደዱ፡፡ በሱዳንና በኤርትራ መኖሪያቸውን
ቀለሱ፡፡
እንግዲህ ረሺዳዎች ከዘር ማጥፋት ወንጀል ለመሸሽ ወደ
ኤርትራ የመጡ ተፈናቃዮች ናቸው ማለት ነው፡፡ በኤርትራ
ውስጥ ንጹህ የዐረብ ዝሪያ የሚባሉት እነርሱ ናቸው፡፡
የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውም ዐረብኛ ነው፡፡ በዚህ ህዝብ
ባህል መሰረት ለአካለ መጠን የደረሰች ማንኛዋም ሴት
ፊቷንም ሆነ ጸጉሯን መሸፈን ግዴታዋ ነው፡፡ በዓሉ ግርማ
በኦሮማይ ውስጥ ሲተርክልን “ማንኛውም የረሺዳ ባል
የሚስቱን ፊት ገልጦ የሚያይበትን ሰው አይፈልግም”
በማለት የተናገረውም የባህላቸው አንድ አካል ነው፡፡
-------
አሁን ወደ ምስራቅ ኤርትራ ተሻግረናል፡፡ ብርኽቲ
የሆነችው ምጽዋ እዚህ ነው ያለችው፡፡ ብርሃነ ሃይለ “ሸው
በሊ ብለነይ” የተሰኘውን ዘፈን ሲቀጥል ምጽዋን እንዲህ
ይላታል፡፡
“አብ ዋሊድ ማሳዋ
ኩለ ሊየን ሒልዋ”
ትርጉሙን በትክክል ባላውቀውም “የምጽዋ ልጆች ሁሉም
ጣፋጭ ናቸው” የሚል መልዕክት እንዳዘለ ይገባኛል፡፡
የምጽዋ ልጆች ቆንጆ ናቸው ተብሎ እየተደጋገመ
ተነግሮላቸዋል፡፡ ከወደብ ከተማ የተገኙ በመሆናቸው
ዓለም አቀፍ ስልጣኔና ልዩ ልዩ ባህሎች ነበርሱ ላይ
ሲነፍስ ይታያል፡፡
ምጽዋ በጣም ውብ ናት፡፡ በተለይም ኪነ-ህንጻዋ ብዙ
ተብሎለታል፡፡ ከዑስማናዊያን ቱርኮች ዘመን ጀምሮ ብዙ
ገዥዎች ሲፈራረቁባት የነበረች መሆኗ በከተማዋ
የሚታየውን ኪነ-ህንጻ እንዳሳመረው
ምሁራን ያስረዳሉ፡፡
ኤርትራዊያን ምጽዋን ይወዷታል፡፡ እኛም እንወዳታለን፡፡
ነገር ግን ወደዚያ ለመድረስ የሚሻ ሰው እንደ እሳት
የሚፋጀውን ሙቀቷን መቻል አለበት-ከተማዋ በዓለም ላይ
ከፍተኛ ሙቀት ካላቸው ስፍራቸው አንዷ ናትና፡፡ የዚህች
ከተማ ህዝብ ኑሮውን ከአየር ጸባዩ ጋር እንዲጣጣም
አድርጎ ቀይሶታል፡፡ በመሆኑም አብዛኛው የንግድ
እንቅስቃሴ የሚከናወነው ከምሽት እስከ እኩለ ሌሊት
ባለው ጊዜ ነው፡፡ ታዲያ ከተማዋ ለዘወትር እንደጋለች
አትቀርም፡፡ በዓመት ሁለት ጊዜ ሙቀቱ ጋብ ይልና
ጤናማው አየር ይነፍስባታል፡፡ ይህም ከጥር-የካቲት
ባለው ጊዜ እና በሀምሌ ወር ነው፡፡ በነዚህ ወራት
ከተማዋን የሚጎበኘው ቱሪስት በጣም ይጨምራል፡፡
በቀድሞው ዘመን ቀዳማዊ ኃይለሥላሤም ከተማዋን
ለመጎብኘት የሚመጡት በነዚህ ወራት ነው (እርሳቸው
ያሰሩት ቤተ-መንግሥት እስከ አሁን ድረስ አለ)፡፡
ምጽዋ በወደብነት አገልግሎት መስጠት የጀመረችበት
ዘመን በትክክል አይታወቅም፡፡ የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት
ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው ከተማ ቀመስ ሰፈራ
ነበር፡፡ ይሁንና እስከ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ እንደ
ወደብ ሲያገለግሉ የነበሩት ከምጽዋ አጠገብ የነበሩት
ጥንታዊያኑ “ዙላ” እና “አዱሊስ” ነበሩ፡፡ የምጽዋ
ተፈላጊነት ጉልህ ሆኖ የተከሰተው የባህር መደቡ በ1508
በዑሥማናዊያን ቱርኮች (Ottoman Turks) በተያዘበት
ወቅት ነው፡፡ ከቱርኮቹ በማስከተልም ግብጾችና የኢጣሊያ
ወራሪዎች ተፈራርቀውባታል፡፡
ኢትዮጵያና ኤርትራ በፌዴሬሽን ከተዋሃዱ በኋላ ምጽዋ
ከፍተኛ እመርታ ማሳየት ጀምራ ነበር፡፡ ከ1970ዎቹ
መግቢያ ጀምሮ ግን የጦርነት ቀጣና ሆነች፡፡ የሻዕቢያ
ሀይሎችና የኢትዮጵያ ሰራዊት ከፍተኛ እልቂት
የተፈጸመባቸውን ጦርነቶች አካሂደውባታል፡፡ በተለይም
በ1982 (እ.ኤ.አ. 1990) በተካሄደው ጦርነት ከሁለቱም
ወገን በአስር ሺህ የሚቆጠር ሰራዊት መርገፉን ሁኔታውን
በቅርበት የተከታተሉ ወገኖችና የዐይን ምስክሮች ገልጸዋል
(የሀምሳ አለቃ ታደሰ ቴሌ ሳልባኖን “አይ ምጽዋ”
አስታውሱት)፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል
መንግሥቱ ኃይለማሪያምም “ለከፍተኛ ሽንፈትና ኪሳራ
የዳረገን ውድቀት ያጋጠመን በምጽዋ ነው” በማለት
ተናግረዋል፡፡
የድሮው ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሻዕቢያ) የአሁኑ
“ህዝባዊ ግንባር ንዴሞክራሲን ንፍትሒን” (ህግዴፍ)
ምጽዋን የተቆጣጠረበትን ዘመቻ “ኦፕሬሽን ፈንቅል”
በማለት ይጠራዋል፡፡ ምጽዋ የተያዘችበት ዕለትም (የካቲት
20) በየዓመቱ ይከበራል፡፡ በርካታ ህዝብ ወደ ምጽዋ
ከሚጎርፉባቸው ዕለታት መካከልም አንዱ ይህ “የኦፕሬሽን
ፈንቅል” መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን ነው፡፡
ምጽዋ የብዙ ህዝቦች መኖሪያ ናት፡፡ ዋነኞቹ ነዋሪዎች
ግን የአሳውርታ፣ ሳሆ፤ እና አፋር ብሄረሰቦች ተወላጆች
ናቸው፡፡ በከተማዋ በዋናነት የሚነገረው ቋንቋ ዐረብኛ
ነው፡፡ የሻዕቢያ መስራች ተብሎ የሚታወቀው ዑስማን
ሳልህ ሳቤ የተወለደው በምጽዋ አጠገብ ካለችው ሂርጊጎ
የተባለች አነስተኛ መንደር ነው፡፡ ኢብራሂም አፋ፣ ረመዳን
መሐመድ ኑር እና ዓሊ ሰዒድ አብደላን የመሳሰሉት
የህግሓኤ (ሻዕቢያ) እውቅ ኮማንደሮችም የምጽዋ ልጆች
ናቸው፡፡
ከምጽዋ ወደብ ዝቅ ብሎ ጥንታዊቷ የአዱሊስ ወደብ
ትገኛለች፡፡ ይህች የወደብ ከተማ ከክርስቶስ ልደት በፊት
ጀምሮ የተጓዦች መግቢያና መውጪያ ነበረች፡፡ የጥንቱ
ሮማዊያንና ግሪኮችም በደንብ ያውቋታል፡፡ አጼ ካሌብ
ወደ ደቡብ ዐረቢያ ሲዘምት ወታደሮቹን በመርከብ
ያስጫነው ከዚህች የወደብ ከተማ ነው፡፡ በሀገራቸው
ከፍተኛ በደል ያጋጠማቸው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
ተከታዮች ከጥቃቱ ለመሸሽ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ
በአዱሊስ በኩል ነበር ያለፉት፡፡ ሌላም ብዙ ታሪክ
ተስተናግዶአል-በአዱሊስ፡፡
---------
ከምጽዋ ወደ መሀል ኤርትራ ለመጓዝ መንገዱን ስንጀምር
በቅድሚያ የምናገኘው የሳሆ ህዝብን ነው፡፡ ይህ ህዝብ
በስተደቡብ በኩል ከሚጎራበተው የአፋር ህዝብ ጋር
ተመሳሳይ የሆነ የኢኮኖሚ መሰረት አለው፡፡ ሁለቱም
በከብት እርባታ ነው የሚተዳደሩት፡፡ ሁለቱም ኩሻዊ ቋንቋ
ነው የሚናገሩት፡፡ በአለባበስ ግን ሳሆን ከአፋር በቀላሉ
መለየት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የሳሆ ተወላጅ የሆነ ሰው
አፋሮች የሚታጠቁትን “ጊሌ” የሚባለውን ረጅም ቢላዋ
አይታጠቅም፡፡ የሳሆ ሰው የሚያሸርጠው ሽርጥም ከአፋር
ሽርጥ ረዘም ይላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሳሆ ብዙ ጊዜ
ከእጁ ጦር አያጣም፡፡ ታዲያ የሳሆ ቋንቋ በትግራይ ክልል
ጉሎ መኸዳ ወረዳ የሚኖረው የኢሮብ ህዝብ ከሚናገረው
ቋንቋ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢሮብና ሳሆ የሚለያዩት
በሚከተሉት እምነትና በኢኮኖሚ መሰረታቸው ነው፡፡ ሳሆ
ሙሉ በሙሉ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው፡፡ ኢሮብ ግን
በአብዛኛው ክርስቲያን ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የሚበዙትም
ካቶሊኮች ናቸው፡፡ በሌላም በኩል የኢሮብ ህዝብ አራሽ
ገበሬ ይበዛዋል፡፡ ከላይ እንደተገለጸው የሳሆ ህዝብ
በከብት እርባታ ነው የሚተዳደረው፡፡
ሳሆን ስናልፍ ደግሞ ትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ በስፋት
የሚኖርባቸውን የአከለ ጉዛይ፣ ሰራዬ እና ሐማሴን
አውራጃዎችን እናገኛቸዋለን፡፡ በኤርትራ ውስጥ ካሉት
ብሄረሰቦች መካከል ብዙ ቁጥር ያለው (50 %
የሚሆነው) ይህ ትግርኛ ተናጋሪ ህዝብ ነው፡፡ ይህ ህዝብ
በባህሉም ሆነ በቋንቋው ከኛው የትግራይ ህዝብ ጋር
ይመሳሰላል፡፡ ህዝቡ በአብዛኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ
እምነት ተከታይ መሆኑም ከትግራይ ህዝብ ጋር
ያመሳስለዋል፡፡ ይሁንና ቋንቋው ባለፉት በርካታ ዘመናት
ከጣሊያንኛ፣ ከዐረብኛ እና ከትግረ ቋንቋዎች ጋር
በመወራረሱ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚነገረው ትግርኛ
የተለየ ዘዬ ሊሆን በቅቷል፡፡
አጅግ በርካታ የሆኑ የኤርትራ ከተሞች ያሉት በዚህ ክልል
ነው፡፡ ጊንዳዕ፣ ሐሙሲት፣ ሰገነይቲ፣ ደቀምሐረ፣ መንደፈራ
(አዲ ዑግሪ)፣ አዲኳላ፣ ሰንዓፈ፣ ደባሩዋ ወዘተ… እዚህ
ነው የሚገኙት፡፡ በመሀከላቸው ደግሞ አስመራ ጉብ ብላ
ትታያለች፡፡ ከከተሞቹ መካከል የሚበዙት በጣሊያን ዘመን
የተቆረቆሩ ናቸው፡፡ በሰራዬና በአከለ ጉዛይ አውራጃ
ውስጥ ግን የጥንቱ የአክሱም ዘመነ መንግሥት ታዋቂ
ከተሞች የነበሩትን እንደ “ሀውልቲ” እና “መጠራ”
የመሳሰሉ መንደሮችን ማግኘት ይቻላል፡፡ በነዚህ ከተሞች
ፍርስራሽ ስር ገና ያልተነካ ድልብ የአርኪዮሎጂ ሀብት
አለ፡፡ ወደፊት ቆፈረን የምናወጣቸውን ማቴሪያሎች
የህዝቦቻችንን አንድነት የሚመሰክሩ ቋሚ ቅርሶች አድርገን
ልጆቻችንን እናስተምራለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
-------
ኤርትራን በኢትኖግራፊ ጉዞ እንዲህ ቃኝተናታል፡፡ ነገር ግን
በዚሁ አናበቃም፡፡ ወደፊትም በተሻለ ዝግጅት ተመልሰን
እንዘይራታለን፡፡ ለአሁኑ በዚሁ ይብቃን!!
ሰላም!!
-----
አፈንዲ ሙተቂ
ነሐሴ 30/2006
------

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
You Alone Are Good Enough

I don't deal with change well. Actually, I would rather stay in the same place, with the same people for the rest of my life. Kind of in my own bubble. But life just doesn't work that way. I don't like to be pushed out of my comfort zone. It scares me to even fathom trying new things. But when I finally do, I find this new sense of identity and direction every time. It's a feeling I can't describe.

Before I lost my grandpa to cancer I had the perfect family, perfect childhood. We went on vacations, had big family dinners, parties and always spent the weekends doing things as a family. I guess you could say I was naive and oblivious to what was set to happen, which would change the course of my life, entirely. I don't think any 10 year old can ever understand what battling a terminal illness is like.

I was still playing with stuffed animals and barbies, holding onto my favorite red blanket any where I went.
I had that security that a lot of other kids didn't have. My parents were happily married, had respectable jobs, we lived in a comfortable, modest huge house and I had lots of toys and friends. I was in paradise.

That brief point in my life is now, only remembered through the dust-stained photo albums. Fast forward to four years later, in some ways I ache for the comfort and security I had before.
I never had to worry if we could afford to pay the bills, food on the table or a place to sleep, people and servants tending to my needs every step of the way. That luxury was given to me.

Until it wasn't anymore.

My family struggled Emotionally, and physically. But we did it together. That's what kept me strong.
The day my grandpa died we stopped living too it seems. His funeral was grand and We were uncertain what was to come. I had to mature and be resilient without a choice.

Since then I have always built walls around the people in my life in order to protect myself. It was my main coping mechanism when my grandpa was receiving treatment and continued after he died.

I've been so used to others walking in and out of my life. They all leave to find other people who suit them better or just get tired of me be so protective of myself. I struggle with anxiety. Every little thing is like a mountainous journey. I procrastinate and worry about everything. I have always been afraid of people. Because it's not easy grieving and feeling like you're always alone.

So I shut myself out even when I don't mean to. I can't control when I'm about to break down or just snap. I want so badly to feel controlled. To feel like I can cope and organize how I feel.

I can only find serendipity in music. I am a different person when I do music. That's what keeps me going.

I thrive on the memories of the relationship I had with my grandpa to keep me going. So even when I lose and gain friends I know that there is that constant that I will have for the rest of my life. And though I am fearful of where I go and what happens, I know that deep down the world is a beautiful place. Despite tragedy, loss and change.

Because this is how I grow, through every little victory. Because every day I look up to the sky and know that my grandpa and me are out there floating among the clouds. There is hope and possibility in every moment and every challenge I may face.

We are built to fail. But we are built to overcome. No one can help us find our identity, only we can. Who we are is a multitude of misadventures, fails and plenty of heart break and loss.

As much I yearn for friends that I once had, that are now a distant memory& the life I used to have with the most important person in my life, I know that my life ahead of me is going to be better. I have experienced alot more in twenty years than some people experience in their lifetime& that's what makes me who I am. I have a lot to give to the world & that's what I'm going to do.

Everyone has a story. Big or small. Everything matters. Who you are is so important to this world, I hope you never lose it.

Source... britannica

@wegoch
@wegoch
ልጅነቴን አፋልጉኝ

ማደግ በመሰለኝ ረግረግ ውስጥ የጠፋች
ልጅነቴን አፋልጉኝ – ማወቅ በመሰለኝ ጥልቅ
ውስጥ የተደበቀች ልጅነቴን አፋልጉኝ –
ከድቅድቅ ጽልመት ውስጥ የዘነጋሁዋትን
እውነት አፋልጉኝ…
~
ዕድሜ የሥጋ ኑረት መስፈሪያ እንጂ የውዷ
ሕይወት መግለጫ አይደለም… ሕይወቴ
ልጅነቴ ነው… ዕድሜ ደግሞ የልጅነቴን
ንጽሕና የነጠቀኝ ቀበኛ…
~
ልጅ እያለሁ ፍርድ አልነበረኝም… ከልክነትና
ስህተት ጋር ፈጽሞ አንተዋወቅም ነበር…
ከመሆን ጋር በጥልቅ ትስስር ውስጥ ነበርኩ…
ልክነትና ስህተት ማደጌ ውስጥ ያጎነቆለ አጥር
ነው… ከኑረት ወንዝነት ጋር ከመፍሰሴ
አናጥበው በልክና ስህተት ኩሬ ውስጥ ያቆሩኝ
‘ያደጉ ሰዎች’ ናቸው… በልጅነቴ ሙቀት
ውስጥ የነበረኝን ስክነት ትልቅ መሆን አለብህ
በሚል ኩሸት የነጠቁኝ ትልልቅ ሰዎች ናቸው…
ልክነትና ስህተትን በማላውቅበት ዘመን ከሁሉ
ጋር እንደ አንድ እኖር ነበር… አድጌ መስመር
ሳበጅ ግጭት ውስጥ ገባሁ… ‘ልክ
አይደለህም – ልክ ነህ’ ውዝግብ ገነባሁ…
መስፈርቴ ግን ከግል ተሞክሮዬ የተጨለፈ
አልነበረም… ከሌሎች ግንዛቤ የተቀዳ እንጂ…
እናም አድግ ብዬ ከራሴ ተፋታሁ… ልጅነቴን
አፋልጉኝ…
~
ልጅ ሳለሁ ሚዛን አልነበረኝም … በጎ መጥፎ
ብዬ አላውቅም… የደስታዬ ጅረት የሆነን
ከመቀበል እንጂ ሁነቱን ከመመዘን ፈልቆ
አያውቅም… ይሄ መጥፎ ያኛው በጎ ነው ያሉኝ
ታላላቆቼ ናቸው… በበጎነትና መጥፎነት ሚዛን
ትላልቆች ሁሉ እንደማይስማሙ ያወቅሁት
አድጌ ነው… ልጅነቴን አፋልጉኝ…
~
ልጅ ሳለሁ ደረጃ አልነበረኝም… ከፍታና ዝቅታ
የኑረቴ አካል አልነበሩም… ጌታና ሎሌ፣ አለቃና
ምንዝር፣ ዲታና ምስኪን፣ አዋቂና ማይም
አላውቅም ነበር… ‘በማደግ እውቀት’ ነው
ደረጃዎቼ የተሰሩት… ከልጅነቴ ፍራሽ ላይ ነው
የማደጌ ቅራቅንቦዎች የበቀሉት… ልጅነቴን
አፋልጉኝ…
ልጅ እያለሁ ስለ ጊዜ አላውቅም ነበር…
የትናንት ጸጸትና የነገ ስጋት ውሎ አዳሬን
አያውቁትም… ደስታዬ ከቅጽበታት ምንጭ
የሚቀዳ ነበር… በእኔ ውስጥ እዚህና አሁን
መኖር እንጂ ፔንዱለማዊ መባከን
አልነበረም… አስቤ አላውቅም ነበር… ሃሳብ
የሚባለውን መርዝ የረጩብኝ ከልጅነቴ ያፋቱኝ
ታላቆቼ ናቸው… ፈጽሞ ተጨንቄ አላውቅም
ነበር… የሰርክ እንቦቃቅላዊ ሳቄ የከሰመው
ታላላቆቼ የጭንቀት አዚም ካደረጉብኝ በኋላ
ነው… የማግኘት ተብሰልስሎት ስጋዬን
ጨርሶት አያውቅም… የማጣት ስጋት ልቤን
ሰቅዞኝ አያውቅም… የኔ የምለው አልነበረም…
የእነእከሌ ነገርም ታስቦኝ አያውቅም… ሁሉ
የሁሉአዊው ነውና እንዳፈተተኝ ስጠቀመው
ኖሬያለሁ… ልጅነቴን አፋልጉኝ…
~
ልጅ ሳለሁ ድንበር አልነበረኝም… ከዚህ
ወዲያ – ከዚያ መለስ ብዬ አላውቅም…
ቤተሰብ.. ቀዬ.. ሰፈር.. ሃገር.. ወገን..
ብሔር.. ሐይማኖት.. የሚባሉ ክፍልፋዮችን
አላውቅም ነበር… ሰው ብቻ ነበርኩ… የስጋ
መገለጥ በጎበኘኝ ጊዜ ከዚህ ውጭ
አንዳችም ልክና ልኬት አልነበረኝም…
ቤተሰቦቼ ‘የእኛ ልጅ ነህ’ ከማለታቸው በፊት
የእኔ የምለው ቤተሰብ አላውቅም ነበር…
ሰፈሩ ‘የእኛ ሰፈር ልጅ’ እስኪለኝ ድረስ
ሰፈርተኝነት ጎብኝቶኝ አያውቅም ነበር… ስም
እስኪሰጡኝ ስም አልባ ነበርኩ… የሆነው ሁሉ
ከፍቃድና ፍላጎቴ ውጭ ሆነ… ብሔር ሰጡኝ…
ሃገር ሰጡኝ… ‘ከዚህ ውጭ ውልፊት ብትል’
ብለው ግድግዳ አበጁልኝ… ከእስከ-አልባው
ሕዋ አባልነቴ ሰረዙኝ… አንዱንም ፈልጌው
አልሆንኩም… ፈልገው ያልሆኑትን ነው
አስገድደው ያሆኑኝ… ልጅነቴን አፋልጉኝ…
~
ልጅነቴ ውስጥ ያልተነካካ ውበት ነበር…
ድንግል ውበት… ‘ውበት ማለት ይህ ነው’
እስኪሉኝ ከሁለንታ ውስጥ ውብ ያልሆነ
ስለመኖሩ አስቤ አላውቅም ነበር… ዓይኖቼ
ያረፉበትም ሆነ ምናቤ የደረሰበት ሁሉ ውብ
ነበር…
~
ልጅነቴ ነፃነት ነበረች… ማደግ እስራት
ሆኖብኛል… ሃፍረት፣ መሸማቀቅና ይሉኝታን
የገመደብኝ እስራት… ከአስተሳሰብ ባርነትና
ከአዕምሮ እስርቤት ያልወጡ እነርሱ ግና
‘ከወህኒ ስትገባ ብቻ ነው ነፃነት ሚጎድለው’
ይሉኛል…
~
ልጅነቴ ውስጥ ፍቅር ብቻ ነበር… ከፍልቅልቅ
ሳቅ ውስጥ የምሰማውን የደስታ ሙዚቃ
ሽርደዳን ቀላቅዬ እንድሰማበት ያሰለጠኑኝ
እነርሱ ናቸው… ከሌሎች ርህራሄ ጥግ አዛኝ
ልብን ሳይሆን ተንኮል እንድፈልግ ያሰሉኝ
እነርሱ ናቸው… ከአብሮ ማዕዴ ጥርጣሬን፣
ከጉርብትናዬ ቂምን፣ ከባልንጀራዬም ሴራን
እንዳሻትት የገፋፉኝ እነርሱ ናቸው…
አለመግባባቴን በጠብ – ኩርፊያዬንም
በግጭት እንድትረጉም ያጸኑኝ እነርሱ ናቸው…
የልጅነቴ ቀበኞች!!… ልጅነቴን አፋልጉኝ…
————————————————
ውዴ ሆይ…
______________________________
በኩርፊያችን ማግስት ጀርባ ለመስጠት
ከፈጠነው አዋቂነት ይልቅ በንጹህ ልብ
የሚፈላለገውን የልጅነት ድምጽ ሰምተን
እንታረቅ!!…

((( በ ደምስ ሰይፉ )))

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
2024/10/01 07:14:08
Back to Top
HTML Embed Code: