Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ዱሃዝባጉና ቀበሌ ቲክቫህ አባላት ስለትላንት ለሊቱ ክስተትና ስላሉበት ሁኔት ተከታዩን ብለዋል ፦

- ማህበረሰቡ ሁሌም ቢሆን እንደታደነ ፣ ደህንነቱን እንዳጣ ፣ እንደተረበሸ፣ እቃውን እንደጫነ ፣ እንደሞተ ነው ያለው ፤ ይሄ እጅግ ያሳዝናል።

- ትለንት ለሊት በተፈጠረው ክስተት ከ12 በላይ ሰዎች ናቸው የሞቱት ፤ በፍፁም በሰላም መኖር አልተቻለም።

- ሰላም ወዳለበት መጥተን ስንሰፍር ሰላም ነው ፣ ህግ አለ ፣ ችግር አይፈጠርም እያሉ ይመልሱናል ፤ ስንመለስ ደግሞ መኖር አንችልም።

- ከዞኑ፣ ከወረዳው ምንም መፍትሄ ማግኘት አልቻልንም። ሰው እየተገደለ እንኳን ምን ሰምታችሁ ነው ? እየተባልን ነው የምንጠየቀው ፤ እንዴት ሰው እየተገደለ እያየን እንኑር።

- መንግስት አመራሩን ሊፈትሽ ይገባል ፣ ችግር ሲፈጠር አይደርሱልንም ፤ ሰላም ነው ይላሉ ፤ ችግር ከተፈጠረ በኃላ ነው የሚደርሱት፤ ይሄ በጣም ተደጋግሟል።

- አሁን ውስን ማህበረሰብ ነው ያለው ፣ ግማሹ ወደ ጫካ ተበታትኗል፤ እኛ ለደህንነታችን ጥሩ የሆነ ቦታ መሄድ ነው የምንፈልገው።

- ለገፅታ ግንባታ ሲባል ሰዎች ለደህንነታቸው ጥሩ ወደሆነ ቦታ መሄድ እንፈልጋለን ሲሉ እንዳይሄዱ ይከለከላሉ፣ እንዴት ነው ሰው ሲገደል እያየን የምንኖረው ?

- ዛሬ ክልሉ በሰጠው መረጃ ላይ እምነት የለንም፣ በገለልተኛ ወገን ሊጣራ ይገባል። ይሁን ቢባል እንኳን እንዴት 3 ሰው መሳሪያ ለቀማው ከ10 በላይ ሰው ይገደላል ? ምንም የማያውቁ ህፃናትን ጨምሮ ?

- ወረዳና ዞኖች ሰላም ነው ፣ ስጋት የለም እያሉ የሚያስውቁ እየመሰለን ነው ፤ መንግስት እራሱ ውስጡን ይፈትሽ፤ ምንም በሰላም መኖር አልተቻለም።

- አሁንም ቢሆን የዜጎች ደህንነት ይጠብቅ፤ እራሱ መንግስት ውስጡን ይገምግም።

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጋሹ ዱጋዝ ፥ በማንዱራ ወረዳ ድኋንዝ ባጉና ቀበሌ ትናንት ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ 'በግለሰቦች መካከል' በተፈጠረ ግጭት የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል ሲሉ አሳውቀዋል።

3 ሰዎች የአንድን ግለሰብ መሳሪያ ነጥቀው በመሰወራቸው ምክንያት በአካባቢው የሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ሃላፊው አስታውቀዋል።

በቀበሌው ውስጥ ነዋሪ የሆነ እና መሳሪያ የተነጠቀበት ግለሰብ ቤተሰቦች በፈጸሙት ድርጊት ነው የሰዎች ህይወት እንዳለፈ የገለፁት ፤ አጥፊዎችን በህግ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ አቶ ጋሹ ተናግረዋል።

መሳሪያ ነጥቀው የተሰወሩ ግለሰቦች ጨምሮ ሌሎች እስካሁን ያልተያዙ ግለሰቦችን ወደ ህግ ለማቅረብ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የፌደራል ፖሊስ እና የክልሉ የጸጥታ አካላት እየሰሩ እንደሆነ ኃላፊ አስታውቀዋል።

አቶ ጋሹ ዱጋዝ ፥ ለሊት የተከሰተው ድርጊት በግለሰቦች መካከል የተፈጠረ ቢሆንም እንኳን ከጀርባ ተልዕኮ ያላቸው ሃይሎች መኖር ፤ አለመኖራቸውን ለማጣራት ምርመራ እየተደረገ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ባንግላዲሽ አስገድዶ ደፋሪዎችን በሞት ልትቀጣ ነው!

በባንግላዴሽ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ከፍተኛ የወሲብ ጥቃትን አስመልክቶ ለቀናት የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።

ይህ የህዝብ ተቃውሞ ተከትሎ ሀገሪቱ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጻሚዎች ላይ የሞት ቅጣትን ልታስተላልፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የባንግላዴሽ ፕሬዝዳንት አብዱል ሐሚድ ለዚህ ጉዳይ ህግ እና ደንቡን እንደሚወጣ መናገራቸውን የህግ ሚኒስትሩ አኒሱል ሀክ አሳውቀዋል ፡፡

በባንግላዴሽ ባለፈው ሳምንት በአንዲት ሴት ላይ በጭካኔ የተፈጸመ የቡድን ጥቃት በምስል በማህበራዊ ሚዲያ በሰፊው ከተሰራጨ በኋላ ቁጣ መቀስቀሱ ተጠቅሷል፡፡

ባለፈው አመት ወደ 5 ሺህ 400 ያህል አስገድዶ መድፈር ወንጀሎች መመዝገባቸውን ከBBC የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ባሌሮቤ

ትላንት በባሌ ሮቤ ቁጥራቸው ውስን የሆኑ ወጣቶች የታሰሩ ፖለቲከኞች (አቶ ጃዋር መሀመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ሃምዛ ቦረና... ሌሎችም) ይፈቱ በሚል ሰልፍ በሚያደርጉበት ወቅት ከመንግስት የፀጥታ ኃይል በተተኮሰ ጥይት 'አወል አብዱሮ' የተባለ ወጣት መገደሉን የባሌ ሮቤ ቲክቫህ አባላት አረጋግጠዋል።

የወጣቱ አወል የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት መፈፀሙን አዲስ ስታንዳደርድ ድረገፅ አስነብቧል ፤ ከዚህ በተጨማሪ ትላንት የታሰሩ እና የተጎዱ ወጣቶች ስለመኖራቸው ከድረገፁ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

PHOTO : ADDIS STANDARD
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በኦሮሚያ ክልል የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ጥቅምት 16 ትምህርት ይጀምራሉ!

የኦሮሚያ ክልል የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ በሰጡት መግለጫ በክልሉ ከጥቅምት 16 ጀምሮ ተማሪዎች በሦስት ዙር ተከፍለው ትምህርት እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ፦

ዙር 1 - ጥቅምት 16 የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩ ይሆናል፣

ዙር 2 - ጥቅምት 30/2013 ዓ/ም የዞን በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩ ይሆናል።

ዙር 3 - ልዩ ዞኖች እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞች ትምህርት ይጀምራሉ።

በኦሮሚያ ክልል ከ33 ሺ በላይ አዳዲስ መማሪያ ክፍሎች መገንባታቸውን ያስታወሱት አቶ አዲሱ አረጋ በዚህ ዓመት ከ11.5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር መታቀዱን ገልጸዋል፡፡ (OBN)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#4_ቀናት_ቀሩ !

ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲስ የመቀየር ስራ ከብር 100 ሺህ እስከ ብር 1.5 ሚሊዮን ለመቀየር ዛሬን ጨምሮ 4 ቀናት ብቻ ቀርቷል።

ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኃላ ባንኮች የተጠቀሰው ገንዘብ መጠን ይዞ የሚመጣ ተጠቃሚ አያስተናግዱም። በቀሩት ውስን ቀናት በአቅራቢያቹ ባለ ባንክ ገንዘባችሁን እድትቀይሩ ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ እያደረሰ ያለው ጉዳት ከባድ በመሆኑ ሕብረተሰቡ የሚችለውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠየቀች።

ቤተክርስቲያኗ አርሶ አደሩ በባሕላዊ መንገድ ፣ መንግስትም ባለው አቅም ሁሉ አንበጣውን ለመከላከል እያደረጉት ያለውን ጥረት መላው ሕዝብ በገንዘቡ ፣ በእውቀቱ እና በጉልበቱ እንዲያግዝ ጥሪ አስተላልፋለች።

ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችም የአንበጣ መንጋውን ለማጥፋት የመድሃኒት ፣ የባለሙያ እና የመድሃኒት መርጫ አውሮፕላን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቃለች። (ENA/ኢዜአ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ጥቅምት 2/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሶማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት የላብራቶሪ ምርመራ አልተደረገም። ትላንት 10 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 60 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 659 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 93 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 349 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 16 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1132 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 201 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 2,763 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 399 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBOT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ከዳንጉር ወረዳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ፦

"ዛሬ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ቀበሌ የታጠቁ ሃይሎች ጥቃት ሊያደርሱ ነበር ፤ የሰላም አስከበሪዎች ቀድሞ ኢንፎርሜሽን በመስማታቸው ጥቃቱ ከሽፏል።

የጉብላክ ማህበረሰብ በድጋሜ ለጥቃት ሙከራ የመዳረጉ ፣ ደህንነቱም አደጋ ላይ የመውደቁ ምክንያት የወረዳው አስተዳደሮች ችልተኝነት ነው።

ምክንያቱም ማህበረሰቡ ያረሰውን ማጨድ ትቶ መፍትሄ እንዲሠጠው ቢጠይቅና ንብረቴ ይቅር ሰላም ወዳለባቸው አከባቢዎች ሊሂድ ትራንስፖርት ይፈቀ ቢልም ፤ እዛው ሁኑ ተብለን ስጋት ላይ ነን። መንግስት ካለ መፍትሄ ይፈልግልን"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION😷

"በዓለም አቀፍ ደረጃ በየ10-15 ሰከንዶች ውስጥ በኮቪድ-19 ሳቢያ አዲስ ሞት ይመዘገባል፡፡ እያንዳንዱ ሕይወት ውድ ነው። እባካችሁ ፣ እባካችሁ እንጠንቀቅ!" - ዶክተር ሊያ ታደሰ (የጤና ሚኒስትር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ባለፉት 24 ሰዓት የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 841 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,997 የላብራቶሪ ምርመራ 841 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 588 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 85,136 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,301 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 38,904 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ማስጠንቀቂያ

"የቡሬ ከተማና አካባቢው በሙሉ በአሁኑ ሰዓት መንግስት ብር ኖት መቀየሩ ይታወቃል።

ይህን ብር አመሳስለው የሚሰሩ ህገወጦች በከተማችን ይዘው እየተዘዋወሩ ሲሆን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦችም ተይዘው በህግ ጥላ ስር ይገኛሉ።

በመሆኑም ሁሉም ሰው መጠንቀቅ ይገባዋል። የአዲሱ ብር ምልክቶች ለማወቅ ከላይ ያለውን ምስል ይመልከቱ!" - ቡሬ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

ከአስራ አንድ ቀናት በፊት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከበሽታው ስለማገገማቸው ተገልጿል።

ከትናንት በስቲያ የግል ዶክተራቸው ዶናልድ ትራምፕ ኮሮናን ወደሰው እንደማያስተላልፉ የተናገሩ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ደግሞ በተከታታይ በተደረገላቸው ምርመራ ነፃ ሆነው ተገኝተዋል ብለዋል።

ዶክተራቸው ፥ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ በየትኞቹ ቀናት ምርመራ እንደተደረገላቸው ከመናገር መቆጠባቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በቻይና በአንድ ከተማ 9 ሚሊዮን ሰዎችን ኮቪድ-19 ልትመረምር እየተዘጋጀች ነው !

በምስራቋ የቻይና Qingdao ከተማ እሁድ 9 ሰዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ መገኘቱትን ተከትሎ 9,000,000 የከተማው ነዋሪዎች እንደሚመረመሩ ተገልጿል።

በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ዘጠኙም ሰዎች ከውጭ ሀገር የሚገቡ የኮቪድ-19 ታጋላጮችን ከሚያክም አንድ ሆስፒታል ጋር ግንኙነት የነበራቸው መሆኑን የጤና ሚኒስቴሩን ጠቅሶ ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

ለበረሀ የአንበጣ መንጋ መከላከል ስራ የሚሆኑ ሁለት አውሮፕላኖች መግባታቸውና ሶስተኛው ዛሬ ኮምቦልቻ እንደሚገባ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ይህ ያሳወቁት ትላንት በምስራቅ ሀረርጌ እና በድሬዳዋ በመገኘት በበረሃ አንበጣ የተጠቁ አከባቢዎች ከጎበኙ በኃላ በትዊተር ገፃቸው ባሰራጩት መልዕክት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በትግራይ ክልል ያጋጠመውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ባለሃብቶች፣ የግል እና የመንግስት ተቋማት በርካታ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ልማት ማህበር (TDA) gofundme በመክፈት በኢንተርኔት ባደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ዳይስፖራዎች ባደረጉት የገንዘብ ድጋፍ እስከ ዛሬ ጥዋት ድረስ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገልጿል።

በትግራይ ክልል ከነሃሴ ወር ጀምሮ በተከሰተው የአንበጣ መንጋ እስካሁን 20 ሄክታር የሚሆን ሰብል በትግራይ ደቡባዊና ደቡብ ምስራቃዊ ዞን መውደሙን ከትግራይ ቴሌቪዥን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ለ7ኛ ጊዜ የተካሄደው የሶማሌ ክልል ፓርቲዎች ስብሰባ !

የሶማሌ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስብሰባ ለ7ኛ ጊዜ ከትላንት በስቲያ በጅግጅጋ ተካሂዷል።

በስብሰባው ገዥው ፓርቲ ጨምሮ 5 በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፈዋል።

ፓርቲዎቹ በክልላዊ ጉዳዮች ፣ በመጪው ሀገራዊ ምርጫ እና የክልሉን ህዝብ አንድነት እና ሰላም በማስጠበቅ ዙሪያ ተወያይተዋል። (SRTV)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#EAF

ዛሬ ጥቅምት 03/2013 በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡካን ቡድን አሸኛኘት ይደረግለታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/21 12:24:45
Back to Top
HTML Embed Code: