Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ጥቅምት 1/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 104 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 39 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1,154 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 99 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ99ኙ መካከል 64 ከምዕ/ጎጃም ዞን ፣ 16 ከባህር ዳር ከተማ ይገኙበታል።

#DireDawa

በድሬዳዋ 142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 47 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 468 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 19 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 471 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 169 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 3,913 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 365 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#Harari

በሐረሪ ባለፉት 24 ሰዓት 120 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 53 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 645 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 50 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 184 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 18 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

@tikvahethiopiaBOT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

በድሬዳዋ የተከሰተ አንበጣ መንጋ በ10 ሺህ ሄክታር ሰብል እና ግጦሽ ሳር ላይ ጉዳት ማድረሱን የአስተዳደሩ የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ለኢዜአ አስታውቋል።

መነሻውን ከሶማሌ ላንድ ያደረገ የአንበጣ መንጋ ከመስከረም 21 ቀን 2013 ዓም ጀምሮ ነው በድሬዳዋ በ22 ገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው።

በ4 ሺህ ሄክታር ማሳ ላይ የሚገኝ የበቆሎና ማሽላ ሰብል ላይ ጉዳት አድርሷል፤ በተጨማሪ 6 ሺህ ሄክታር የግጦሽ ሳር ሙሉ ለሙሉ አውድሟል።

በተወሰኑ ቦታዎች ላይ በደረሰ የአተር ሰብል፣ በቲማቲምና ፍራፍሬ ተክሎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

አንበጣ መንጋውን በባህላዊ መንገድ ጭስ በማጨስ እና ድምፅ በማሰማት እና በኬሚካል ርጭት ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም ከአቅም በላይ መሆኑን ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የኬሚካል መርጫ አውሮፕላኖች ጥገና ላይ መሆናቸው ችግሩን ያባባሰው መሆኑን ተገልጿል። (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#አስቸኳይ_መልዕክት !

በሓፀቦ አከባቢ የአንበጣ መንጋ እየታየ ስለሆን በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ቦታው በመገኘት የአርሶ አደሩ የመከላከል ስራ እንድትቀላቀሉ ተጠይቋል - (AXUM UNIVERSITY)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,383 የላብራቶሪ ምርመራ 866 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 633 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 84,295 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,287 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 38,316 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

በአርሜኒያ እና አዛርባጃን መካከል ተደርጎ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ከአንድ ቀን በላይ መዝለቅ አልቻለም።

አዛርባጃን በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀችው የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ከአንድ ቀን በኋላ ለዛሬ እሁድ አጥቢያ የአርሜኒያ ኃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት 7 ሰዎች ተገድለዋል።

ጥቃቱ የተሰነዘረው በአዛርባጃንዋ የጋንጃ ከተማ የመኖርያ መንደሮች ላይ ነው ተብሏል።

በጥቃቱ ከተገደሉት ውጭ ህጻናትን ጨምሮ ሌሎች 33 ሰዎች መቁሰላቸውን የአዛርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ነገር ግን የአርሜኒያ ኃይሎች ውንጀላውን አጣጥለው ይልቁኑ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ የአዛርባጃን ኃይሎችን ተጠያቂ ማድረጋቸው የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል።

በሩስያ አደራዳሪነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ተደርጎ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ለሁለት ሳምንት የሚቆይ እንደነበር የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል። (DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የቀወት ወረዳ ወጣቶች እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች የአንበጣ መንጋ መከላከል ስራ በውድቅት ጨለማ እየተጋፈጡት ይገኛሉ።

በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ በቀበሌዎች በመስፈሩና እያደረሰ ያለው የሰብል ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ለነገ ተብሎ የሚታለፍ ባለመሆኑ በባህላዊ ዘዴ የኬሚካል ርጭት ስራ እየተሰራ ይገኛል።

አንበጣ መንጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የፀጥታ አካላት የአንበጣ መንጋውን የመከላከል ስራን እየሰሩ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ግብዣ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ !

የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ።

በጉብኝቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኡስማን ሳሌህና የፕሬዜዳንቱ አማካሪያ የማነ ገብረአብም ተካተዋል።

#YemanGMeskel
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ZamZamBank

ዘምዘም ባንክ ለዓመታት ሲያደርግ የነበረው ዝግጅት አጠናቆ ዛሬ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ/ም በይፋ ሥራውን ሊጀምር እንደሆነ ሪፖርተር አስነብቧል።

ባንኩ በኢትዮጵያ 'ከወለድ ነፃ ባንክ' አገልግሎት በመስኮት ደረጃ እንዲሰጥ ምክንያት በመሆን የሚጠቀስ እና የመጀመርያው ከወለድ ነፃ ባንክ ለመሆን ሲንቀሳቀስ የቆየ ባንክ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጅማ ገቡ!

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጅማ ሲደርሱ በዚያው የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል እንዳደረጉላቸው etv ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ኮሮና ቫይረስ የገንዘብ ኖቶች ላይ ፣ የስልክ ስክሪኖች ላይ እና በማይዝጉ ብረቶች ላይ ለ28 ቀናት ሳይሞት ቆይቶ በሽታ ሊያስተላለፍ እንደሚችል ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ።

የአውስትራሊያ ብሔራዊ ሳይንስ ኤጀንሲ ይፋ ያደረገው ጥናት ሳርስ-ኮቭ-2 የሚል ሳይሳዊ መጠሪያ ያለው ኮሮናቫይረስ ከተገመተው በላይ ለረዥም ጊዜ በቁሶች ላይ እንደሚኖር ያረጋገጠ ነው።

ኮሮናቫይረስ በብዛት የሚተላለፈው ሰዎች ሲያስሉ ፣ ሲያስነጥሱ ወይም ሲነጋገሩ እንደሆነ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህ አዲሱ የተመራማሪዎች ግኝት ቫይረሱ ከቁሶች ወደ ሰዎች የሚተላለፍበት መጠንም ከተገመተው በላይ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

ምንጭ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ የሰዎች ህይወት አለፈ!

በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ዱሃዝባጉና ቀበሌ መነሻው የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የክልሉ መንግስት ፤ ለሰዎች ሞት መንስኤ የሆነው የግለሰቦች ግጭት ነው ብሏል።

በዱሃዝባጉና ቀበሌ አንድ ግለሰብ የሠው መሳሪያ ለመንጠቅ ሙከራ ባደረገበት ወቅት ፣ ባለ መሳሪያው ራሱን ለመከላከል ባደረገው ጥረት መሳሪያ ሊነጥቀው የመጣውን በስለት መሳሪያ የመቁሰል ጉዳት አድርሶበታል ተብሏል።

ይህን ተከትሎ ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ ቤተሰብ በበቀል ስሜት ተነሳስተው ባደረሱት ጥቃት የንጹኃን ዜጎች ሕይወት እንዳለፈ ተገልጿል።

የክልሉ መንግስት ምን ያህል ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ አልገለፀም።

ጥቃት አድራሾቹ ግለሰቦች በቁጥጥር የዋሉ ሲሆን ፣ የክልሉ እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ችግሩ እንዳይሠፋ ለማድረግ በጋራ እየሠሩ ናቸው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#INVEA

ኢማግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከዛሬ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለውጭ አገር ዜጎች በOnline ላይ ቪዛ የማራዘም እና ግዜያዊ መኖሪያ ፍቃድ የማደስና አዲስ የመጠየቅ አገልግሎት ጀምሯል።

በዚህ አድራሻ መሰረት online ላይ መገልገል እንደምትችሉ INVEA አሳውቋል ፦ https://www.evisa.gov.et/

በተጨማሪ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ እድሳት እና ጥያቄ መደበኛ አገልግሎት ከዛሬ ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም ጀምሯል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለetv በሰጡት ማብራሪያ ከተናገሩት ፦

- በመንግስት እና በግል ባንኮች የብር ቅያሪ ከተጀመረ ወዲህ ባለፉት 26 ቀናት ውስጥ 920 ሺ ገደማ አዳዲስ አካውንቶች ተከፍተዋል።

- አዲስ በተከፈቱት አካውንቶች 31 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል። የመቀየሪያው የጊዜ ገደብ እስከሚጠናቀቅ በርካታ ባንክ የማይጠቀሙ ሰዎች አካውንት እንደሚከፍቱ እና ከባንክ ዉጭ የሚገኝ ገንዘብ ወደባንክ እንደሚመጣ ይጠበቃል።

- ከ100 ሺህ - 1.5 ሚሊዮን ብር ለመቀየር ከተሰጠው የ 1 ወር ጊዜ ውስጥ የቀረው 4 ቀን ብቻ በመሆኑ የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ በእጁ ላይ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ ይሁን ድርጅት በነዚህ ጥቂት ቀናት ገንዘቡን ሊቀይር ይገባዋል።

- የብር ቅያሪው በመላው ሀገሪቱ በአብዛኛው በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል። በአንድ አንድ ቦታዎች ሀሰተኛ የብር ኖቶች ገበያ ላይ እየታዩ ነው።

- ሀሰተኛ የብር ኖቶች በገበያው ላይ መሰራጨት ኢኮኖሚውን ስለሚጎዳ የጸጥታ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ፤ ህብረተሰቡም ይህን ለመከላከል የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

- ከተለያዩ የውጭ ሀገራት የኢትዮጵያ ብር አለን በኤምባሲ በኩል እንቀይር የሚል በርካታ ጥያቄ እየቀረበ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ወደ ውጭ የሚወጣ ሰው ይዞ እንዲወጣ ከሚፈቀደው የብር መጠን በላይ በ ውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ብር ምንም አይሰራም ፤ ይህን አንቀይርም። በተለየ ሁኔታ ሊታዩ የሚችሉ ሊኖሩ ይችላሉ።

- ገንዘብ ላይ ምንም አይነት ጽሁፍ መጻፍ እንዲሁም የተለያየ ምልክት ማድረግ በህግ የተከለከለ ነው ለዚህም መመሪያ ተዘጋጅቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/21 14:41:44
Back to Top
HTML Embed Code: