Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የትምህርት ሚኒስቴር ለክልሎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ስርጭት እያካሄደ ነው፡፡ የስርጭቱ ቁጥራዊ መረጃ ከላይ ቀርቧል! #MoE

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ችሎት!

አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

አቶ ልደቱ ፍርድ ቤት የቀረቡት በኦሮሚያ ክልል አቃቤ ህግ የተመሰረተባቸውን "ህገወጥ የጦር መሳርያ መያዝ" ከስ ምስክሮች ለመስማት ነበር።

አቃቤ ህግ ግን ምስክሮችን ማቅረብ ያልቻለ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቢሾፍቱ ወረዳ ፖሊስ ምስክሮቹን አስገድዶ እንዲያቀርብለት ትዕዛዝ ይጻፍልኝ በማለት ጠይቋል፡፡

በዚህም ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 5/2013 ቀጠሮ ሰጥቷል።

(አል ዓይን)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#GERD

ዛሬ ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በጋር በመሆን የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በጉብኝቱ ወቅት ግድቡ በዘንድሮ ዓመት አሁን ከያዘው በ3 እጥፍ የሚበልጥ ውሀ እንደሚይዝ ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በዚህ ዓመት ኃይል ማመንጨት የሚጀምሩ ተርባይኖች ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ተርባይኖቹ ለስድስት (6) ወራት ሙከራ ካደረጉ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ኃይል ወደ ማመንጨት ይገባሉ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው የግድቡ ግንባታ ሂደት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውን አሳውቀዋል።

በህዳሴ ግድቡ ግንባታ ላይ ለተሳተፉ እና አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ምስጋና ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#AtoAhmedShide

ዛሬ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ በ2013 በጀት ዓመት የ3 ወራት እቅድ አፈፃፀም ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ አህመድ ሽዴ ፥ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር የጀመረውን ስራ ለጊዜው መቋረጡን አሳውቀዋል።

ትግራይ ክልል ለሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በከተሞች ለሚገኙ ዜጎች የበጀት ድጋፍ ለማድረግ ጥረት በመደረግ ላይ ነው ብለዋል።

ለመንግስት የስራ ሀላፊዎች አ/አ ሲኤምሲ አካባቢ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን በጨረታ በመሸጥ እስከ አንድ ቢሊዮን ብር ለማግኘት መታቀዱን ገልፀዋል።

በ2013 ዓ/ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 80.8 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል - (etv)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

ትምህርት ሚኒስቴር ሃዋሳ ኢንዲስትሪ ፓርክ የተመረቱ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛዎችን ከስር ከስር እርክክብ በማድረግ ለሁሉም ክልሎች እንዲሰራጩ በማድረግ ላይ ነው።

የደቡብ ክልል የመጀመሪያውን ዙር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ስርጭት ዛሬ ተረክቧል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ክልሎች የተረከቡትን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎች በየትምህርት ቤቱ የማከፋፈል ስራውን እንደሚሰሩ ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በ1 ወር ማውጣት በሚቻለው የገንዘብ መጠን ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ አንስቷል።

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የወጣው መመሪያ ግለሰቦች በወር ከ 1 ሚሊየን ብር በላይ እንዳያወጡ ይከለክላል፡፡

ድርጅቶች ደግሞ በ1 ወር ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እንዳያወጡ ተከልክሎ እንደነበር የሚታወስ ነው። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ!

ምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ አማኑኤል ከተማና ደጋሰኝን ታዳጊ ከተማ መስከረም 28 እና ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም ወደ ገቢያ ሊሰራጭ የነበረ 24 ሺ 8 መቶ ባለ መቶ የሀሰተኛ የብር ኖት በህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ዛሬ ገልጿል፡፡

ፖሊስ በድርጊቱ ተሳትፈዋል ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ከማቻክል ወረዳ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ኮማንደር አምሳል ሰውነት ከብር ኖት ቅያሬው ጋር ተያይዞ በወረዳው ውስጥ የሀሰተኛ የብር ኖት እየተሰራጨ ስለሆነ ህብረተሰቡ ግብይት በሚፈጽምበት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርግና አጠራጣሪ ነገሮችን ሲያይ ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#WNM

የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የዎላይታ ሕዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ የደረሰበት ደረጃ የዎላይታ ዞን አስተዳደር ለሕዝቡ ግልፅ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ !

ከዎብን መግለጫ የተወሰደ ፦

" ... አዲሱ የወላይታ ዞን አመራር ወደ ሥልጣን ሲመጣ የዎላይታ ሕዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠው በቁርጠኝነት የሚሠራ መሆኑን ገልፆ ነበር።

ይሁን እንጅ ዛሬ ለሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ ከማስገኘት አኳያ ሂደቱ የደረሰበት ደረጃ በየጊዜው ለሕዝቡ ግልፅ እየተደረገ ባለመሆኑ ሕዝባችንን ጉዳዩ በተያዘበት ሁኔታና እና በአመራሩ ህዝባዊነት ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲያድርበት አድርጓል፡፡

በመሆኑም ጉዳዩን ይዞ የሚገኘው የዎላይታ አስተዳደር እና የዞኑ ምክር ቤት እጅግ አንገብጋቢ የሆነው የዎላይታ የሕዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጥ ዎብን አጥብቆ ይጠይቃል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
PIIS1473309920307647.pdf
1.3 MB
ጥናት ፦

በኮቪድ-19 ታሞ የሚያውቅ ሰው ቫይረሱ በድጋሚ ሊይዘው እንደሚችል አዲስ የወጣ ጥናት አመለከተ።

ትናንት ላንሴት መጽሄት ላይ የወጣው ጥናት ዩናይትድ ስቴትስ ኔቫዳ ግዛት ውስጥ አንድ የሃያ አምስት ዓመት ወጣት ሚያዝያ ወር ውስጥ ኮሮናቫይረስ ይዞት እንደገና ሰኔ ወር ላይ እንደያዘው አመልክቷል።

በሁለተኛው በጽኑ ታሞ ሆስፒታል መግባቱና ተጨማሪ ኦክሲጂን የሚያስፈልገው ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር ጥናቱ አክሏል።

በዓለም 2 ጊዜ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ሰዎች እስካሁና አምስት ብቻ ሲሆኑ የዩናያትድ ስቴትሱ የመጀመሪያ መሆኗ ታውቋል። (VOA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,344 የላብራቶሪ ምርመራ 582 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 403 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 85,718 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,305 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 39,307 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

ዛሬ ለገጣፎ በሚገኘው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ሆቴል በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡካን ቡድን ሽኝት ተደርጎለታል።

በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ ተገኝተው ነበር።

ፕሬዝዳንቷ አትሌቶቻችን በሰልጠና ያገኙትን ልምድ በቡድን ስራ እንዲያሳዩ አደራ ካሉ በኋላ በድል እንዲመለሱ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች እና አሰልጣኞች ጥሩ ልምምድ አድርገው ለውድድር መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ EAF
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
* ማስተካከያ

ግለሰቦች እና ኩባንያዎች ከባንክ እንዲያወጡ የፈቀደውን ወርሃዊ የጥሬ ገንዘብ ጣሪያ አለማንሳቱን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። ብሄራዊ ባንክ ግለሰቦች ሆነ ኩባንያዎች የሚያወጡት ወርሃዊ የጥሬ ገንዘብ ጣሪያ ተነስቷል የሚለው መረጃ ትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በትግራይ የኬሚካል ርጭት ተጀምሯል ?

(በኤልያስ መሰረት)

EBC : "መንግሥት በደቡባዊ ትግራይ እና በምሥራቅ አማራ የአንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል እርጭት ማካሄድ ጀመረ"

የትግራይ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ : "ይህ ፍፁም ውሸት ነው ፤ ለምን እንደዛ እንደሚሉ አይገባኝም።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#የጥንቃቄ_መልዕክት !

አሮጌው 100 ብር ኖት ከአዲሱ 10 ብር ኖት ጋር በቀለም ተመሳሳይነት እያጭበረበሩ ያሉ አካላት ስለመኖራቸው ብሄራዊ ባንክ መረጃ እንዳለው ገልፆ ፣ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

ህብረተሰቡ በኖቶቹ ለውጥ ላይ በተለያዩ ቋንቋዎች ግንዛቤ እንዲኖረው እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል አዲሱን 100 ብር ኖት በአሮጌው 130 ብር ኖትና ከዚያ በላይ የሚሸጡ አንዳንድ ሰዎች መኖራቸውን በመረጃ እንደተደረሰበት ብሄራዊ ባንክ ገልጿል ፤ ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ነገር ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

#ሼር #SHARE

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች !

የጤና ሚኒስቴር ከጥቅምት 09-13/2013 የብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

• የፈተናው ፕሮግራም
• ቦታ እና ሰዓት ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ማንኛዉም ተፈታኝ ወደ ፈተና ቦታ ሲመጣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (mask) እንዲሁም የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ይዞ መምጣት የሚኖርበት መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ከምዕራብ ሃረርጌ የቲክቫህ አባላት ፦

"ምዕራብ ሀረርጌ ፤ ጭሮ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በከፍተኛ ሁኔታ ሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ህዝቡ ርብርብ ቢያደርግም ምንም መቆጣጠር አልተቻለም።

የሚመለከታቸው አካላት መንጋው አሁን ካለው በላይ እጅግ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ እገዛ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።"

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
2024/09/21 14:35:26
Back to Top
HTML Embed Code: