Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ባቲ ወረዳ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ አሁን ላይ በብሔረሰብ አስተዳደሩ አምስት ወረዳዎች ላይ እየተስፋፋ ነው።

መንጋዉ በ5 ወረዳዎች በሚገኙ 46 ቀበሌዎች የሸፈነ ሲሆን ከ7,200 ሄክታር በላይ ሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።

ከ12,000 በላይ አርሶ አደሮች የችግሩ ሰለባ መሆናቸዉን የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ ዋቢ አድርጎ አብመድ ዘግቧል።

በባቲ ወረዳ ብቻ በአስራ አምስት ቀበሌዎች የሚገኝ ሰብል 'ሙሉ በሙሉ' በሚባል ደረጃ መዉደሙን የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

አሚናት ሙሄ የተባሉ የጨቆሪቲ ቀበሌ ነዋሪ ስላሉበት ሁኔታ ለባቲ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ተከታዩን ብለዋል ፦

"ባለፈው አመት የዘራነውን አዝመራ በሚገባ ሳንንከባከበው ከዚሁ መሬት ላይ አስር ዳውላ ወደ ጉድጓዳችን እየስገባን ነበር።

አሁን እንደምታዩት ለዶሮ የሚረጭኳን ጠፍቶ ማሳው ውስጥ እየፈለግን እየቃረምን ነው፡፡ አሁን አገዳውን እያጨድን ለከብቶቻችን ከምረን እሱንም እንዳይበላብን መጠበቅ እንጂ ምንም ተስፋ የለንም፡፡

ለመከላከል ያላደረግነው ነገር የለም ነገር ግን የአንበጣው ብዛት ሰማዩን ሞልቶ ሰማይና መሬቱን አቧራ ያስመስለዋል የምንይዘው የምንጨብጠው አሳጣን፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,024 የላብራቶሪ ምርመራ 865 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 668 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 82,662 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,271 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 37,102 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !!

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በአሽፋ ባህራ ደረዋ ቀበሌ ሃሰተኛ 80 ሺህ ባለ መቶ የብር ኖት እጅ ከፈንጅ ተይዞ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት፥ እንጅባራ ነዋሪ የሆኑት አቶ ያረጋል ጥላሁን እና አቶ ግርማው ታፈረ በቀን 28/01/2013 ዓ/ም ከቀኑ 12፡00 አሽፋ ገበያ ሃሰተኛ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

በአሁን ሰዓት አንድ ግለሰብ ከ 15,000 ብር በላይ ይዞ መገበያየት ስለማይቻል እነሱ የሚገዙት እቃ 80 ሺህ ብር ስለሆነባቸው በእጅ እንስጥ ብለው በባጃጅ ወጥተው ከመንገድ እንደተቀባበሉት ተገልጿል።

60,000 ብሩ ወዲያውኑ የተያዘ ሲሆን 20,000 ብሩ በዛሬ 29/01/2013 ዓ.ም ደላላ የሆነው ሙሉቀን አለነ የተባለ ግለሰብ አምጥቶ አስረክቧል ተብሏል።

ሁሉም ማህበረሰብ በአሁኑ ሰዓት አዲስ የተቀየረውን የብር ኖት እንዳይጭበረበር ስለብር ኖቶቹ በደንብ አውቆ መንቀሳቀስ እንዳለበት መልዕክት ተላልፏል፡፡

(Guagusa Shikudad Communication)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#NewsAlert

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በተለምዶ አየር አምባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ከምሽቱ 1:30 አካባቢ በተከሰተ እሳት አደጋ እስካሁን የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል። አንድ ሰው ላይ ከባድ ቃጠሎ ደርሷል።

የእሳት አደጋው በአሁን ሰዓት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የአደጋው መነሻ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
Wibet የውፍረት መቀነሻ !

የዉፍረት መቀነሻ ፣የጀርባ፣የትከሻ፣የወገብ ችግር አለቦት ?
0911607446 ወይም 0911284606
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!
የቦርጭ መቀነሻ - 650 ብር              
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 800 ብር
የትከሻ መደገፊያ - 600 ብር
ሙሉ የጀርባ -950
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻ @wibet1 (ሁሉም ክልል ከተሞች ይገኛሉ) @አ.አ = ቦሌ ትሮፒካል ሞል



KTKM ጂፒኤስ ሲስተምስ ትሬዲንግ !

KTKM ጂፒኤስ ሲስተምስ ትሬዲንግ የፍጥነት መገደብያ መሳሪያ ለግለሰብ ፣ ለድርጅት እና ለመኪና አስመጪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ከሁለት አመት ዋስትና ጋር ያቀርባል። አድራሻ : ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ 214 / ቃሊቲ ሸገር ህንጻ 6ተኛ ፎቅ 605 ቢሮ - 0979721265 እና በ 0911306359 ቴሌግራም @ktkmgps
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
POLO TRIP

አዳማ ፣ ሀዋሳ እና ቢሾፍቱ ለመሄድ ሲያስቡ ወደ 6565 ይደውሉ። በPOLO TRIP ምቹ የቤት መኪኖች ካሰቡበት ይድረሱ! ቤትዎ ድረስ ይመጣሉ። POLO TRIP - 6565



Alpha Furniture

ሶፋዎች ከ16,900 - 25,000 ብር
የ2 አመት የጽሑፍ ዋስትና
ከ17+ አመት በላይ ልምድ አላቸው
0979420042 / 0979426642

ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራም ቻናላቸው
👉 @AlphaFurniture 
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ATTENTION📣

በዚህ ቪድዮ የምትመለከቱት በባቲ ወረዳ ውስጥ በጨቆሪቲ ቀበሌ የበረሀ አንበጣ መንጋ እያደረሰ የሚገኘው ጉዳት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
"የአንበጣ መንጋው የአርሶ አደሩን በህይወት የመኖር ተስፋ አጨልሞባቸዋል" - ወረባቦ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ

- በወረባቦ ወረዳ የተከሠተው የአንበጣ መንጋ በቆላማው አካባቢ 11 ቀበሌዎችን አውድሟል፡፡

- የአንበጣ መንጋው 35,195 ሄክታር መሬት ላይ ወረራ በማድረግ 25,154 ሄክታር መሬቶችን በመብላት 48,969 የቤተሠብ አባሉን ሜዳ ላይ ጥሎታል፡፡

- የበረሀ አንበጣው ነሀሴ 29/2012 አካባቢ በቁጥቋጦዎች ላይ ወረራ የጀመረ ሲሆን መስከረም 15 ቀን ጀምሮ መብረርና ሠብሎችን መብላት ጀምሯል። በዚህ የ15 ቀን ቆይታ ውስጥ ፦

• 7368 ሄክታር ሰብሎችን ፤
• 2134 ሄክታር የግጦሺ ሳርን፤
• 4623 ሄክታር ደኖች እንድሁም 11ሺህ 26 ሄክታር ቁጥቋጦዎችን በአጠቃላይ 25,154 ሄክታር መሬቶች በመብላት የአርሶ አደሩን በህይወት የመኖር ተስፋ አጨልሞባቸዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

'መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ' በትግራይ የተለያዩ ወረዳዎች የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል እንዲያግዝ የ2,000,000 ብር እገዛ አድርጓል።

በሌላ በኩል ሌሎች ድርጅቶች ፣ ግለሰቦች ፣ ተቋማት ፣ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ፣ የመንግስት ሰራተኞች የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል የሚሆን እገዛ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
አርቲስት ኣብርሃም ገ/መድህን እና ባለቤቱ አርቲስት ኤደን ገብረስላሴ በራያ ጨርጨር ጣብያ ሓዱሽ ቅኚ የአንበጣ መንጋ ጉዳት እንዳያደርስ በማባረር ማህበረሰቡን አግዘዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አርቲስቶቹ በትግራይ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ የ100 ሺህ ብር እገዛ አድርገዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

የመርሳ ከተማ ወጣቶች የአንበጣ መንጋ ሰብላቸውን በማውደም የተጋረጠባቸውን ወቅታዊ ችግር ከጎን ተሰልፎ ለመከላከል ወደ ሀሮ ከተማ እና አካባቢው በመድረስ መንጋውን በመከላከል ላይ መሆናቸውን የመርሳ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/21 20:14:48
Back to Top
HTML Embed Code: