Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

አርመኒያ እና አዘርባጃን በናጎርኖ - ካራባህ ግዛት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው BBC አስነብቧል።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሁለቱ ሃገራት በሞስኮ ለ10 ሰአታት ከተወያዩ በኋላ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !

በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ የሐሙሲት ፖሊስ ጽ/ቤት በዛሬዉ ዕለት 46,000 (አርባ ስድስት ሽህ ብር) ሀሰተኛ የብር ኖት መያዙን ገልጿል።

የሐሙሲት ፖሊስ ጽ/ቤት እንደገለፀው ፥ ነዋሪነቱ ዛራ ቀበሌ የሆነ ግለሠብ "ግብይት ከፈፀምኩ በኋላ የብር ኖቱን ተጠራጠርኩ' በሚል ወደ ፖሊስ ጣቢያ አምጥቶ ዛሬ ከጧቱ 2:10 ሰዓት ብሩን ለፖሊስ አስረክቧል።

ግለሠቡ በቁጥጥር ስር ዉሎ በምርመራ እየተጣራ መሆኑንም የሐሙሲት ፖሊስ ፅህፈት ቤት አሳውቋል።

ህብረተሠቡ ሀሰተኛ በሆኑ የብር ኖቶች እንዳይሸወድ እንዲሁም ሀሰተኛ የሆኑ የብር ኖቶችን የሚያዘዋዉሩ ግለሠቦችን በመጠቆሞና በማጋለጥ ወንጀልን በጋራ እንዲከላከል ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት የነዳጅ ማጠራቀሚያ ፈንድቶ ቢያንስ አራት ሰዎች ሲሞቱ 20 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል።

ፍንዳታው የተከሰተው ታሪቅ አል ጂዲ በተባለ ጎዳና በርካታ ሰዎች በሚኖሩበት ሰፈር ነው።

እስካሁን ድረስ የእሳቱ እንዴት እንደተነሳ አልታወቀም።

በአካባቢው የተሰማሩት የአደጋ መከላከል ሠራተኞች አሁንም ሰዎችን ከአደጋው የማዳን ሥራቸውን እንደቀጠሉ መሆኑ ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ከነገ ጥቅምት 1/2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ የሚኖረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሊትር ፦

• ቤንዚን 21 ብር ከ87 ሳንቲም፤
• ኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን 21 ብር ከ33 ሳንቲም፤
• ነጭ ናፍጣ እና ኬሮሲን 19 ብር ከ9 ሳንቲም፤
• ቀላል ጥቁር ናፍጣ 16 ብር ከ94 ሳንቲም፤
• ከባድ ጥቁር ናፍጣ ደግሞ 16 ብር ከ51 ሳንቲም

በማስተካከያው በመስከረም ወር በሊትር በ26 ብር ከ97 ሳንቲም ሲሸጥ የቆየው የአውሮፕላን ነዳጅ የ2 ብር ከ60 ሳንቲም ቅናሽ ተደርጎበት በ24 ብር ከ37 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ዛሬ መስከረም 30 በአለም አቀፍ ደረጃ ለ39ኛ፣ በኢትዮጵያ ለ28ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ ይውላል።

የዘንድሮው መሪ ቃል "የአእምሮ ጤና ለሁሉም፤ የበለጠ ሙዓለ ነዋይ ለብዙኅን ተደራሽነት!" የሚል ነው።

የሰው ኃይልን፣ ጊዜንና ሙዓለ ነዋይን ለአእምሮ ጤና የማዋል ጊዜው አሁን ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የትግራይ እርሻ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አትንኩት መዝገቦ ፣ በእስራኤል የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንዲሁም ኤርትራውያን ባዋጡት ገንዘብ በ8 ሺ ዶላር የበርሃ አንበጣ ለመከላከል እንድታግዝ የተገዛች ድሮን አዲስ አበባ ስትደርስ ለሌላ ጉዳይ ትውላለች በሚል ወደ ትግራይ ክልል እንዳትሄድ ተደርጓል ሲሉ ለTMMA ተናግረዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ከፍያለው ተፈራ 1 ድሮን ተይዞ እንደሚገኝ ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።

አቶ ከፍያለው ፥ ድሮሩ ከእስራኤል ሀገር የመጣና ስሪቱ የቻይና መሆኑን ገልፀዋል ፤ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የዛሬ 5 ወር ገደማ እንደነበርና በወቅቱ ተብሎ የነበረው 'አረም ለማስወገድ ይውላል እንደተባለ አስታውሰዋል።

ለምን እንዲያዝ እንደቻለም አቶ ከፍያለው ይህን ተከታዩን ብለዋል ፦

"አሁን ባለው መመርያ መሰረት ወደ ሀገር እንዲገባ የሚፈቀደው ድሮን የመጫን አቅሙ ከ5 ኪሎ ያልበለጠ ነው ፣ ይህ ድሮን ደግሞ ከ25 ኪሎ በላይ መጫን ይችላል፣ ረጅም ርቀትም መጓዝ ይችላል።

ስለዚህ ለሌላ አላማ ሊውል ስለሚችል እንዲጣራ እንዲቆይ ተደርጓል፣ ይህ የፀጥታ ስጋት ሊሆን የሚችል ድሮን ነው። በተጨማሪ ድሮኑ ምንም አይነት ገላጭ መረጃ (description) አብሮት አልመጣም።"

በአሁን ሰዓት ካለው የአንበጣ ችግር አንፃር ስራ ላይ እንዲውል ማረግ አይቻልም? ተብለው የተጠየቁት አቶ ከፍያለው ፦

"የአንበጣ ችግር እንዳለ ይታወቃል ፣ ነገር ግን ለሌላ አላማ እንዳይውል እንደ ግብርና ሚኒስቴር አይነት አካል ሀላፊነቱን ሊወስድ ይገባል።" ብለዋል።

ምንጭ፦ Tigray Mass Media Agency & Ethiopia Check
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#TikvahSport

አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሆላንድ ሄንግሎ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር በአንደኝነት አሸንፏል።

በሌላ በኩል በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ሲፋን ሀሰን በፓውላ ራድ ክሊፍ የተያዘውን የአውሮፓ ሪከርድ በመስበር በበላይነት አጠናቃለች።

ኢትዮጵያዊቷ ፀሀይ ገመቹ ውድድሯን በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችላለች።

@tikvahethiopia @tikvahethsport
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,394 የላብራቶሪ ምርመራ 767 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 581 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 83,429 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,277 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 37,683 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

አዲሱ የብር ኖት መሰራጨት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የግል ባንክ ቅርንጫፎች መሰራጨቱ ተገልጿል !

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፦

- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብሔራዊ ባንክን በመወከል አዲሱን የብር ኖት ለግል ባንኮች ጭምር በማሰራጨት ላይ ነው።

- አዲሱን የብር ኖት ማሰራጨት ከተጀመረ ከመስከረም 6/2013 ዓ ም ጀምሮ አስካሁን ባለው ጊዜ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የግል ባንክ ቅርንጫፎች ተሰራጭቷል። ከዚህ ውስጥ 28 ቢሊዮን ብር ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ተሰራጭቷል።

- 22 ቢሊዮን አሮጌው የብር ኖት ወደ ማዕክል ገቢ ተደርጓል።

- 5 ሺ ብር እና ከዛ በላይ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብር ለመለወጥ የሚመጡ ደንበኞች የብሔራዊ ባንክ መመሪያ በሚያዘው መሠረት በቁጥር 63 ሺ ደንበኞች አዲስ የባንክ አካውንት ከፍተዋል፤ ከ 6.4 ቢሊዮን ብር በላይ ተቆጥቧል።

- በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ 3,700 ኤቲኤም ማሽኖች በሙሉ ማለት በሚያስችል ደረጃ አዲሱን የብር ኖት እንዲከፍሉ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል።

- ከመቶ ሽ ብር በላይ ብር ለሚቀይሩ ደንበኞች ዛሬ (ጥቅምት 1, 2013) ጨምሮ በቀሩት 5 ቀናት ውስጥ ሰንበትን ጨምሮ በመስራት ላይ ወዳሉት የኢትዮጰጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በመምጣት በቀነ ገደቡ ሊጠቀሙ ይገባል። (CBE)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በአዲስ አበባ አንዳንድ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለማስጀመር እንደሚቸገሩ እየገለፁ ይገኛሉ።

የካ አባዶ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሀዲስ አለማየሁ ለአዲስ ዘመን ከገለፁት፦

- በኮሮና ምክንያት ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲልም ያለው የተማሪ ብዛት ለማስተማር አስቸጋሪ ነበር።

- አሁንም የክፍል እጥረቱ ሳይፈታ ተማሪዎችን እየመዘገብን ነው። ችግሩን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አውቆ ተጨማሪ 70 ክፍሎችን ለመስራት ቦታ የተለየና ከሞላ ጎደል እቃዎች ያቀረበ ቢሆንም እስካሁን በተግባር የተሰራ ነገር የለም።

- ወቅቱ አስቸጋሪ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ከ8 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በቀጥታ ወደ ትምህርት ገበታ ማስገባት ይከብዳል።

- 70 ክፍሎች ተሰርተው ለአገልግሎት ከዋሉ በ2 ፈረቃ ተማሪዎችን ማስተማር ይቻላል። ሆኖም እስከ መስከረም 29 ድረስ 6 ሺህ 500 ተማሪዎች የተመዘገቡ ቢሆንም ከ8 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚኖሩ ይገመታል። በዚህም ትልቅ ችግር ይገጥመናል።

- 76 ሺህ ሊትር የሚይዝ የውሃ ታንከር ተዘጋጅቷል ፤ ይህ ከተማሪዎች ብዛት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ በመሆኑም ቆራጥ ውሳኔ ያስፈልገዋል።

- የተማሪዎች የመመገቢያ አዳራሽ ጭራሽ አለመሰራቱ ሌላው ሥጋት በመሆኑ ትምህርት ለማስጀመር እንቸገራለን።

ፈለገ ዮርዳኖስ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ፈንታሁን ሞላ ለአዲስ ዘመን ከገለፁት ፦

• ትምህርት ለመጀመር የኬሚካል ርጭት ከማካሄድ ውጭ እስካሁን መሬት ላይ የወረደ ሥራ የለም።

• አካባቢው የውሃ እጥረት ያለበት በመሆኑ ከዚህ በፊትም ትልቅ ችግር አስከትሏል። ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገርን ቢሆንም እስካሁን መፍትሄ አልተገኘም።

• የውሃ ችግሩ በፍጥነት መፈታት ካልቻለ ትምህርት ለማስጀመር ይከብደናል።

@tikvahethiopiaBoT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

"የአንበጣ መንጋ እህሉ አልበቃ ሲለው በፎቶው እንደምታዪት በዛፎች ላይ እያረፈ ይገኛል። የአርሶ አደሮችን አመታዊ ሰብል አውድሞ የከብቶች መኖ እና ሌሎች ደኖችን በከፍተኛ ሁኔታ እያወደመ ነው።" - መርሳ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ኬሚካል የሚረጩ 5 ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ከውጪ ለማስገባት ጥረት እያደረገ መሆኑ ግብርና ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ከተናገሩት ፦

- የአንበጣ መንጋ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ፣ አማራ ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተከስቷል።

- የመከላከል ሥራው በአውሮፕላን ኬሚካል ርጭት ጭምር በመከናወን ላይ ነው። ችግሩ እየሰፋ በመምጣቱ እና ሥራው ላይ ከነበሩት አውሮፕላኖች ሁለቱ በመከስከሳቸው እስከ ረቡዕ ድረስ ተጨማሪ 5 አውሮፕላኖች ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሠራ ነው።

- መንጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች በስፋት እንዳይዛመት ለማድረግ የመከላከል ሥራውን በጥንቃቄ ለመሥራት ጥረት እየተደረገ ነው።

- በአንበጣው ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደሮች ለመደገፍ የመለየት ሥራ በመከናወን ላይ ነው።

- የግል ባለሀብቱ የአንበጣ መከላከል ሥራውን እንዲያግዝ ጥሪ ቀርቧል። (etv)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ሳወት የ15,000 ብር እገዛ አደርገ !

በትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) በክልሉ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ የ15,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ለአርሶ_አደሩ_እንድረስለት !

በወረባቦ ወረዳ ውስጥ የተከተሰው የአንበጣ መንጋ አርሶ አደሩ ደክሞ ለፍቶ ያፈራውን ሰብል ወደ ጎተራው ሳያስገባ አንበጣ መንጋው እያወደበት ይገኛል።

ይህንን የሰብል ጉዳትም ለመቀነስ በሰው ሃይል የኬሚካል ርጭት ፣ በባህላዊ መንገድ የመባረር እና በሂሊኮፍተር ኬሚካል ርጭት ቢደረግም የአንበጣ መንጋውን መቆጣጠር አልተቻለም።

በመሆኑም የሲቪክ ማህበራት የመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ባለሀብቶች በአንበጣ መንጋው ሰብላቸው የወደመባቸው አርሶ አደሮች እንዲደግፉ የወረባቦ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
"በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች 2.8 ሚሊዮን ማስክ ይከፋፈላል" - ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (Face Mask) ስርጭትን በተመለከተ ክልሎች ለተማሪዎቻቸው ተረክበው እንዲያሰራጩ የሚገልጽ እና ድልድሉንም አስመልክቶ የጊዜ እና የመጠን ዝርዝር ያለው ደብዳቤ ለክልል ትምህርት ቢሮዎች ጽፏል፡፡

በዚህ ደብዳቤ ውስጥ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አልተካተተም፡፡ ይህም በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ ፈጥሯል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጠይቀን ተከታዩ መረጃ ተሰጥቶናል ፦

- የተደረገው ድልድል የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ጭምር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያገኙ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

- በደብዳቤው ላይ ማካተት ያልተቻለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቅርቡ ባሳለፈው ውሳኔ ምክንያት ነው፡፡

- አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ ላሉ 26 ሚሊዮን ተማሪዎች የማስክ አቅርቦት እንዲሟላ እየተሰራ ይገኛል፡፡

- ለትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎችም ይህንን ሥርጭት ለማድረስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከወረዳዎች እና ከዞኖች ጋር ግንኙነት ጀምሯል፡፡ ሥርጭቱም በዚያው በኩል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

- አጠቃላይ ወደ 50 ሚሊዮን ማስክ በዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ 2.8 ሚሊዮን የሚሆነው በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የሚከፋፈል ይሆናል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/21 23:09:49
Back to Top
HTML Embed Code: