Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ለአትሌት ለተሰንበት ግደይ አቀባበል ተደረገላት !

ዛሬ አርብ መስከረም 29 ማለዳ 12፡00 ላይ የስፔን ቫሌንሺያ የ5,000 ሜ ሪከርድ ባለቤትዋት ጀግኒት አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከዋና አሰልጣኟ ኃይሌ እያሱ ጋር በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ስትደርስ ፦

• ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀ/ም/ፕሬዝዳንት

• ኮማንደር አትሌት ማርቆስ ገነቲ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንትና አቶ ቢልልኝ መቆያ የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በስፍራው ተገኝተው አቀባባል አድርገዋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#NobelPeacePrize2020

በዛሬው ዕለት የዓለም የኖቤል የሰላም አሸናፊ ይፋ ይደረጋል ፤ የዘንድሮው የኖቤል የሰላም አሸናፊ ማን ይሆን ? ሰዓቱ ሲደርስ አብረን የምናየው ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#AttorneyGeneral

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሀብትና ንብረታቸውን በወቅቱ ያላስመዘገቡ የመንግሥት ባለሥልጣናት እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ካላስመዘገቡ 'በሙስና ወንጀል' እንደሚከሰሱ ማስጠንቀቁን ኢዜአ ዘግቧል።

ክሱ የሚመሰረተው የፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ እና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ/ም በጻፈው ደብዳቤ 180 የመንግሥት ባለሥልጣናት ሀብት እና ንብረታቸውን በወቅቱ ለማስመዝገብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምርመራ ተጣርቶ ክስ እንዲመሰረትባቸው መፃፉን ተከትሎ ነው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል !

(የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን)

በባህር ዳር አዲሱ ሀሠተኛ የብር ኖት ተያዘ።

በባህርዳር ከተማ አንድ ግለሰብ የ90 ሺህ ብር እህል ተገበያይተዋል።

ነጋዴው ግለሰብ በተሰጠው ብር ላይ ጥርጣሬ ስላደረበት ለባንክ ባለሙያዎች ሲያሳያቸው ሀሰተኛ የብር ኖት መሆኑ ተረጋግጧል።

ግለሰቡም ወዲያውኑ ለባህርዳር ከተማ ፖሊስ አዲሱን የሀሰተኛ ብር ኖት አስረክቧል።

ፖሊስ አሁን ላይ 90 ሺህ ብሩን ሰጥቶት በተሰወረው ግለሰብ ላይ ክትትል እያደረገ ይገኛል።

አሁን ላይ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች አዲሱ የሀሰተኛ የብር ኖት በፖሊስ እየተያዘ ይገኛል።

ስለሆነም ማንኛውም ግብይት በሚደርግበት ጊዜ ብሩ ብዙ ከሆነ የገንዘብ ልውውጡ በባንክ ቢሆን ይመረጣል።

የደህነት መጠበቂያ ምልክቶችንም በደንብ መመልከት ያስፈልጋል።

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#REPOST

አዲሶቹ የብር ኖቶች አይነት እና የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ፦

ተከታታይ ቁጥሮች ፦

የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ።

ማየት ለተሳናቸው እውቅና ምልክት ፦

የብሩን ዋጋ የሚገልፅ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ ምልክት አለው።

ጎርባጣ መስመሮች ፦

የባንክ ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የኖቱ ዋጋ ይታያል።

ደማቅ አንፀባራቂ ምልክት ፦

ገንዘቡ ወደ ላይ ወይም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደህንነት መጠበቂያ ምልክት።

የደህንነት መጠበቂያ ክር ፦

የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮከብ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ውስጥ NBE ፣ ኢብባ እና የገንዘቦቹ አይነት ተፅፎ ይገኛል።

የውሃ ምልክት ፦

ገንዘቡ ወደ ብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላዩ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ የውሃ መልክ ያለው ምልክት ይታያል።

ትይዩ ምልክት ፦

የብር ኖቶች ከብርሃን አቅጣጫ ሲታዩ ኳስ መሳይ ምልክት ከገንዘብ በስተኃላው ካለው ተመሳሳይ ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ።

ፈሎረሰንስ ምልክት ፦

አንበሳው ምስል ራስ ላይ አልትራቫዮሌት ጨረር ሲበራበት ወደ ቢጫነት የሚለወጥ ፍሎረሰንት ምልክት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
አትሌት ለተሰንበት መቐለ ስትገባ ደማቅ አቀባበል ተደረገላት !

ዛሬ ጀግናዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከዋና አሰልጣኟ ኃይሌ እያሱ ጋር መቐለ ስትገባ አቀባበል ተደርጎላታል - (ትእምት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጥቅምት 20 - 30 /2013ዓ.ም ድረስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዕቅድ መያዙን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ተናግረዋል፡፡

የAAU ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገሩት ፦

- ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በ2 ዙር እንዲገቡ ለማድረግ ዕቅድ ይዞ ዝግጅት ቢያደርግም በኮቪድ 19 የሚያዘው ሰው ቁጥር በመጨመሩ ተማሪዎችን በ3 ዙር ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

- በአንድ ክፍል ከ25 በላይ ተማሪዎች እንደማይማሩ እና መምህሩ ደግሞ ከ35 ደቂቃ በላይ ማስተማር እንደሌለበት ተወስኗል።

- ከዚህ ቀደም አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍል (ዶርሚተሪ) ከስምንት እስከ 18 ተማሪዎች ይይዝ ነበር የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ሲባል በአንድ ዶርሚተሪ ለ2 ተማሪዎች ቢበዛ 3 ተማሪዎችን እንዲይዝ ይደረጋል።

- ባለፈው ዓመት ተመራቂ የነበሩ አራት ሺህ የሚሆኑ የቀን ተማሪዎች በመጀመሪያው ዙር ከገቡ በኋላ በ45 ቀን ውስጥ ትምርታቸውን አጠናቀው እንዲመረቁ ይደረጋል።

- የማታ መርሀ ግብር ተማሪዎች ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ።

- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 7 ካምፓሶች በተለይ ከውጭ አገር ለሚመለሱ ዜጎች ለለይቶ ማቆያነት ይጠቀሙባቸው ነበር ከዛሬ ጀምሮ ወደ እነዚህ ካምፓሶች ለለይቶ ማቆያ የሚገባ ሰው እንደማይኖር ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- በዩኒቨርሲቲው በኩል የሚደረገው ዝግጅት ተጠናቋል። በትራንስፖርት እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ይደረጋል።

- ከጥቅምት 20 እስከ 30 /2013 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዕቅድ ተይዟል።

@tikvahethiopiaBOT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእቅድ ደረጃ ከጥቅምት 20 እስከ ጥቅምት 30 ተመራቂ ተማሪዎችን ለመቀበል እየተዘጋጀ ይገኛል !

ዙር አንድ ፦

• 2012 ተመራቂ የነበሩ 4,000 የሚሆኑ የቀን ተማሪዎች ይገባሉ ፤ በ45 ቀን ውስጥ ትምርታቸውን አጠናቀው እንዲመረቁ ይደረጋል።

ዙር ሁለት ፦

• በ2ኛው ዙር 5 ሺህ የሚሆኑ 3ኛ እና 4ኛ ዓመት ተማሪዎች የሚቀበል ይሆናል።

ዙር ሶስት ፦

• በ3ኛው ዙር ደግሞ 1ኛና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች ይቀበላል።

በሌላ በኩል ፦

ተማሪዎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል አድርገው ፤ መስኮቶች ተከፍተው እንዲማሩ እንደሚደረግ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተናግረዋል።

በአሁን ሰዓት ሁሉም ሰራተኛ ወደ ስራው እንዲገባ ተደርጓል፤ በዚህም ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን መቀበል ከሚጀምሩት የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ቀዳሚ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#BREAKING

የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ሆኗል። #NobelPeacePrize2020

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#AtoLidetuAyalew

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝደንት አቶ አዳነ ታደስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት፦

"አቶ ልደቱ አያሌው በድንገት ከቢሾፍቱ ፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወስደዋል። ፖሊስ አቶ ልደቱን ለምን ፖሊስ ወደ ፍርድ ቤት እንደወሰዳቸው እስካሁን ምንም መረጃ የለንም።

የዋስትና መብታቸውን ፖሊስ እንዲያከብር ለመነጋገር ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሰጥቶን እየጠበቅን ባለንበት ሁኔታ ነው ዛሬ ከፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰዳቸውን የሰማነው።

አቶ ልደቱ ምንም አይነት መጥሪያ እንዳልደረዳቸውም ፤ በአንድ ሚዲያ ግን አቶ ልደቱ አያሌው በሌላ ጉዳይ ክስ እንደተመሰረተባቸው የሚያሳይ ዘገባ ወጥቶ ተመልክተናል። በእጅጉ በፍትህ ስርአቱ ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎናል።

አቶ ልደቱ ፖሊስ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰዳቸው በኃላ ስለተፈጠረው ነገር ለማጣራት ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ አዳማ እየተጓዝኩ ነው።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ሌ/ጀ ጌታቸው ጉዲና (የመሀንዲስ ዋና መምሪያ ሀላፊ) በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የቃሊቲ ሴንተራል ዲፖ ፕሮጀክት መጎብኘታቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ይፋዊ ገፅ አሳውቋል።

ስለፕሮጀክቱ ፦

- በ25 ሄክታር ያረፈ ነው፤ 22 ብሎክ የአልባሳት እና ሌላ 22 ብሎክ ደግሞ የመኪና መለዋወጫ ግምጃ ቤት ተገንብቶበታል።

- ባለ 3 ወለል 32 ቢሮዎች የያዘ የአስተዳደር ህንጻም ተሰርቷል፡፡ አንድ የትልቅ የመኪና እና ሁለት የትንንሽ መኪና ማከማቻም ተጠናቋል።

- 3 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው የጊቢው አጥር ዙሪያ 8 የጥበቃ ማማ የተሰራ ተሰርቷል።

- ለ1 ሻምበል አባላት የሚሆን መኖሪያ ፣ መመገቢያ ፣ መጸዳጃ እና መዝናኛ ተገንብቷል፡፡

- ፕሮጀክቱ በአሁኑ ሰአት 97 በመቶ ደርሷል ፤ ቀሪው በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የፕሮጀክቱ ሰራተኞች ርብርብ እያረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
8 የርቀት ትምህርት ተቋማት ህጋዊ ዕውቅናና ፍቃድ የላቸውም ተብሏል !

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ትምህርትና ሥልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ማረጋገጫ ባለሥልጣን ለአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው በከተማው በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ከ5ኛ - 10ኛ ክፍል ለማስተማር የእውቅና ፍቃድ የሌላቸዉና ህጋዊ ያልሆኑ የርቀት የትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም፡-

1. ፓን አፍሪካ
2. ኢትጲስ
3. አልፋ
4. ሰሌክት
5. ሚሽከን
6. ኬኛ
7. ጅግዳን
8. ሉሲ

እውቅና እና ፈቃድ የላቸውም ፤ ማህበረሰቡ እነዚህ ተቋማት ህጋዊ አለመሆናቸው እንዲያውቅ ተብሏል።

ምንጭ፡- የአ/አ ከተማ ትምህርት ቢሮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#DrAmbachewMekonnen

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀድሞ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ለዶክተር አምባቸው መኮንን መታሰቢያ ህንጻ ማሰሪያ የመሬት ካርታ አበረከተ፡፡

ለዶክተር አምባቸው መኮንን መታሰቢያ ህንጻ ማሰሪያ የሚሆን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 2 ሺህ 250 ካሬሜትር ሲሆን የመሬት ካርታ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለሠማዕቱ ቤተሰቦች አስረክበዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከአሁን ቀደም ለዶ/ር አምባቸው መኮንን ፣ አቶ ምግባሩ ከበደ እና አቶ እዘዝ ዋሴ ቤተሰቦችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ሰጥቷል።

በተጨማሪ ለኢታማጆር ሹም ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦች 1 ሺህ ካ.ሜ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ መስጠቱን አስታውሷል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬትሪያት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኦነግ ጉዳይ ያሳለፈው ውሳኔ ፦

" ...በእነ አቶ ዳውድ ኢብሣ የሚመረጥ/የምትመረጥ አንድ ፤ በእነ አቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመረጥ/የምትመረጥ ሌላ አንድ ፤ እንዲሁም እነዚህን ሁለት በባለጉዳዮቹ የሚመረጡትን ባለሙያዎች በሰብሳቢነት የሚመራ/የምትመራ ሌላ አንድ ባለሙያ ቦርዱ መርጦ በመመደብ የባለሙያዎች ጊዜያዊ ጉባኤ እንዲቋቋም መስከረም 28 ቀን 2013 ባደረገው ስብሰባ ወስኗል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

ከትግራይ የቲክቫህ አባላት ፦

"በትግራይ ክልል ራያ አላማጣ፣ ጨርጨር፣ መኮኒ በሌሎች አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ አንበጣም መንጋ ጉዳት እያደረሰ ነው።

ገበሬዎች ፣ የእግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ፣ ማህበረሰቡ ፣ የክልሉ መንግስት አመራሮች የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ቢሆንም ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ ተሰግቷል።

ይህ ጉዳይ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም እና የሚመለከተው አካል ለገበሬው ፣ ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ እጅግ በጣም በአስቸኳይ ሊደርስ ይገባል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/21 22:52:21
Back to Top
HTML Embed Code: