Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
3 ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት መጀመር ይችላሉ ተባለ !

ጎንደር፣ዲላ እንዲሁም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማሩን ሂደት እንደገና ለማስቀጠል የሚያስችል አቋም ላይ እንደሚገኙ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተላከው የምርመራ ቡድን ማረጋገጡን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች (ዲላ፣ አዲስ አበባ፣ ጎንደር) በጤና ሚኒስቴር የወጣውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ በማድረግ የተቋረጠውን ትምህርት የማስጀመር አቋም ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ !

- የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተመርቋል።

- ኢንዱስትሪ ፓርኩ ለሀገራችን አሥራ ሦስተኛ ፣ ለአማራ ክልል ደግሞ ሦስተኛ ነው።

- በአሁን ሰዓት ኢንዱስትሪ ፓርኩ 8 የተሟላ ቁሳቁስ ያላቸውን የማምረቻ ቦታዎች የያዘ ሲሆን ፣ በቅርቡ ሥራ ይጀምራሉ።

- የመጀመሪያ ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ፖርክ 75 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን 2ኛው ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ግንባታ 125 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል ተብሏል።

- ፓርኩ በቅርቡ ከ4,000 በላይ ሠራተኞችን ለመቀበል ልየታ ሰርቷል። በሙሉ አቅሙ በ2 ፈረቃ ሲሠራ 10 ሺህ ለሚደርሱ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

- በአካባቢው ለነበሩ የልማት ተነሺዎች ቅድሚያ የሥራ ዕድል ይሰጣል ተብሏል።

- በፖርኩ እስካሁን ‘ሆፕሉን’ የተባለ ኩባንያ ለጨርቃ ጨርቅ እና ጋርመንት ምርት 8 ሼዶችን ወስዷል። በ1 ሼድ ላይ መሣርያ የገጠመ ሲሆን ሠራተኞችን እያሰለጠነ ይገኛል። ከመጪው መጋቢት ጀምሮ ምርቶቹን ወደ አሜሪካና አውሮፖ ኤክስፖርት ማድረግ ይጀምራል።

#DrAbiyAhmed #AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

በወረባቦ ወረዳ የተከሰተው የበረሀ አንበጣ በ020 ቀበሌ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶ ወደ 013 እና 19 ቀበሌዎች እየተሸጋገረ ይገኛል።

የበራሀ አምበጣውን ከባህላዊ መከላከል ዘዴ አንስቶ እስከ አውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ድረስ ቢደረግም አንበጣው የገበሬውን አዝመራ ማውደሙን እንደቀጠለ ነው።

በዛሬው እለት በ020 ቀበሌ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ በአሁኑ ሰአት ወደ 13፣ 19፣ 09፣ 08 ፣ ቀበሌዎች እየተሸጋገረ ይገኛል።

የበራሀ አንበጣው የገበሬውን አዝመራ እያወደመ በመሆኑና የአንበጣ መንጋው በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ማህበሠሰቡ ተስፋ በመቁረጥ ደረጃ ላይ ደርሷል። (ወረባቦ ኮሚኒኬሽን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

በትግራይ ደቡባዊ ዞን ራያ አላማጣ፣ራያ ጨርጨር እና ራያ ዓዘቦ ወረዳዎች የተከሰተዉ የበረሃ አንበጣ መንጋ በሰብልና ደን ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገበሬዎች እና የግብርና ባለሞያዎች እየገለፁ ናቸዉ።

ምንም እንኳ የአከባቢዉ ህብረተሰብና አመራሩ በቁርጥኝነት በነቂስ መንጋዉን ለመከላከል እየሞከረ ቢገኝም መንጋዉ ከቁጥጥር ዉጭ እየሆነ መምጣቱ በዘንድሮዉ የምርት ዘመን ከፍተኛ ሰብልና ደን ያጠፋል የሚል ስጋትን እየፈጠረ ነዉ።

ሁሉም አካላት በመተባበር በትኩረት ካልሰሩ አደጋዉ የከፋ ነዉ የሚሆነዉ። (Desye Ashenafi)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

ትግራይ ክልል ውስጥ የተለያዩ ወረዳዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል ከፍተኛ ርብርብር እየተደረገ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት የመቐለ 70 እንደርታ የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች የአንበጣ መንጋው ጉዳት እንዳያደረስ እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ።

PHOTO : ወዲ ሃፀይ የውሃንስ፣ ዜማታት 70
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ATTENTION📣

በዚህ ቪድዮ የምታዩት በወረባቦ ወረዳ 020 ኤጀርሳ ቀበሌ ሲባ ዱለቻ ጎጥ የበረሀ አምበጣ መንጋ በአረንጓዴ ሰብል ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የትላንት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ምን ማለት ነው ?

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባሄ አቶ አደም ፋራህ ለetv ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ ፦

- የትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የህግ አስፈፃሚው አካል /ካቢኔ/ ህገመንግስታዊ ቅቡልነት ስለሌላቸው ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ምንም ዓይነት ህጋዊ ግንኙነት ማድረግ አይችሉም።

ይህ ማለት የፌዴራል መንግስት ተቋማት ከትግራይ ክልል ከፍተኛ አስፈፃሚ አካላት (ካቢኔ) ጋር እንደህጋዊ አካላት በመቁጠር፦

• ደብዳቤ መፃፃፍ፣
• መረጃ መላላክ፣
• የፌዴራል ተቋማት ለክልል ተቋማት የሚሰጧቸውን ድጋፎች መስጠት፣
• በፌዴራል ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች ላይ ማሳተፍ የመሳሰሉ ጉዳዮች ማድረግ አይቻልም።

- የትግራይ ምክር ቤት እና ካቢኔ ህጋዊ ሰውነት ስለሌለው የፌዴራል መንግስት የበጀት ድጎማ እንደማያደርግለትም።

- የትግራይ ህዝብ መሰረታዊ የልማት እና የአገልግሎት ተጠቃሚነቱ እንዳይስተጓጎል እንደ ቀበሌ ፣ ወረዳ ፣ ከተማ ካሉ ህጋዊ የክልሉ መዋቅር ጋር ብቻ ግንኙነቱ ይደረጋል።

- የውሳኔ አፈፃፀምም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥናት ላይ ተመስርቶ ይከናወናል።

- በቀጣይ በክልሉ ካሉ የከተማ አስተደሮች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ጋር ስለሚኖር ግንኙነት በተለይ ህዝቡ ማግኘት የሚገባውን መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኝ በጥናት ተመስርቶ ተፈፃሚ ይደረጋል። (ኢቲቪ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#NewsAlert

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግና DSTV ከስምምነት ደርሰዋል !

'ሱፐር ስፖርት' ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካና አጎራባች ደሴቶች ዙሪያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ለማሰራጨት መብት አገኘ።

መልቲ ቾይስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካልቮ ማዌላ፥ “ይህ ስምምነት ከመላው አህጉሪቱ ደጋፊዎችን በመሳብ ለሊጉ የበለጠ እይታን ይሰጣል" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

“ይህ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን ለኢትዮጵያ ተጨዋቾች ብሩህ ተስፋን ይፈጥራል” ሲሉ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ተናግረዋል፡፡

Via @tikvahethsport
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

የአንበጣ መንጋ በወረባቦ ወረዳ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል !

- የበረሃ አንበጣ መንጋው 24 ሺህ ሄክታር የሚሆን መሬት ወሯል ፤ በወረዳው በ11 ወረዳዎች ይገኝ የነበረ ሰብል ላይ ከ10 እስከ 100 በመቶ ጉዳት አድርሷል።

- በመንጋው ከ3,400 በላይ አርሶ አደሮች ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ወድሞባቸዋል።

- የበረሃ አንበጣ መንጋውን ሕዝቡን በማስተባበር በባህላዊ መንገድ ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ነው።

- የመንጋው ቁጥር ከቀን ወደ ቀን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ የመከላከል ሥራው ውጤታማ አልሆነም።

- የኬሚካል ርጭት ስታደርግ የነበረችው ሄሊኮፕተር ከሰሞኑ መከስከሷ መንጋውን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት ፈጥሯል።

- ፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ ኬሚካል ርጭት የሚያደርጉ አውሮፕላኖችን ወደ ስፍራው እንዲያሰማራ ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፦ አቶ ታደሰ ግርማ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#MoSHE

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታዩን ብለዋል ፦

- በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በየደረጃው ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የሚያስችል ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው።

- በቅርቡ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በየተራ ተማሪዎቻቸውን ይቀበላሉ።

- በሀገሪቱ ሁሉም ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ወደዩኒቨርሲቲ ለማምራት #ዝግጅት ማድረግ አለባቸው።

- በ44 ዩኒቨርሲቲዎች በተደረገ ግምገማ አብዛኛዎቹ ኮሮና ቫይረስን በመከላከል የመማር ማስተማሩን ሂደት ማከናወን በሚችሉበት ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

- የቀሩ ጥቂት ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ሳምንት ዝግጅታቸውን እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

- የጤና ፕሮቶኮል እና የሰላም ሁኔታውን የሚያስጠብቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል።

- በተጨማሪም በአመቱ ከክህሎት እና እውቀት በተጨማሪ የስብእና ግንባታ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን በስርአተ ትምህርቱ ይካተታል። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,254 የላብራቶሪ ምርመራ 892 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 710 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 80,895 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,255 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 35,670 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ኢትዮጵያ በ15 ቀናት 139 ዜጎቿን በኮቪድ-19 አጥታለች !

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመስከረም 12/2013 እስከ ዛሬ መስከረም 27/2013 ዓ/ም ባሉት ቀናት 139 የውድ ዜጎቿን ህይወት በኮሮና ቫይረስ አጥታለች።

ከ15 ቀናቱ ውስጥ ከፍተኛው ሞት የተመዘገበው በመስከረም 12/2013 (19 ሰዎች) ሲሆን ሁለተኛው ከፍተኛ ሞት ደግሞ ዛሬ መስከረም 27/2013 ዓ/ም (17 ሰዎች) ተመዝግቧል።

የሰው ልጅ ህይወት ዳግም አይተካም ፤ በየዕለቱ ሰዎች ሲሞቱ መቁጠር ለኛ ቀላል ሊመስል ይችላል ፤ ነገር ከነዚህ ውድ ከሆኑ የሰው ልጆች ጀርባ ስንት ቤተሰብ፣ ተስፋ ፣ እቅድ ፣ ዓላማ፣ ጓደኛ ፣ ወዳጅ ፣ ዘመድ ይኖራል ?

መዘናጋታችን ፣ መሰላቸታችን ሀዘን ቤታችን ስላልገባ ይሁን ? በየዕለቱ ከሚሞቱ ሰዎች ጀርባ ስንት ቤተሰብ ይሁን የተበተነው ? ስንት እናት አባት ይሁኑ ተስፋቸውን ልጆቻቸውን ተነጥቀው በመሪር ሀዘን ውስጥ የሚገኙት ? ስንት ሰው ይሁን የሚወደውንና የሚሳሳለትን ወዳጁን ከጎኑ ያጣው ?

ለአንድ ደቂቃ እንኳን እራሳችንን በሌሎች ወገኖቻችን ቦታ አድርገን እንመልከት ፤ ያን ማድረግ ካልቻልን ህመሙ ፣ ሀዘኑ ፣ ጉዳቱ ፈፅሞ አይሰማንም።

ለሰዎች ሞትና ስቃይ ምክንያት አንሁን ፤ እራሳችንን በተቻለን አቅም ሳንሰላች፣ ሳንዘናጋ እንጠብቅ። ዛሬም ኮቪድ-19 ገዳይ ነው😷

ነፍስ ይማር!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 27/2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
አትሌት ለተሰንበት ግደይ የ5000 ሜትር የዓለም ከብረወሰን ሰበረች !

ጀግናዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በስፔን ቫሌንሲያ በተካሄደ የ5,000 ሜትር ሩጫ በጀግናዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ለ12 አመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ሰበረች።

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የገባችበት ሰዓት 14፡06:62 ሲሆን በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረው ክብረ ወሰን 14፡11፡15 ነው።

@tikvahethsport @tikvahethsport
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#LetesenbetGidey

በጀግናዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን የሰበረችው ጀግናዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከድሉ በኋላ ደስታዋን ስትገልፅ የሚያሳይ ቪድዮ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ላይ የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ሩፋኤል ሽፋረ ለBBC ተከታዩን ብለዋል ፦

- የፌዴሽን ምክር ቤት ውሳኔ ቅቡልነት የሌለው ነው።

- የፌደሬሽን ምክር ቤት ከመስከረም 25 ጀምሮ የሥልጣን ዘመኑ አብቅቷል ፤ ያስተላለፈው ውሳኔ ሕጋዊ መሠረት የለውም፤ ተቀባይነት የለውም፤ ተግባራዊም ሊሆንም አይችልም።

- ከክልል መንግሥት በታች ያሉ የዞን ፣ የወረዳ እና የቀበሌ መዋቅሮች የማደራጀት ሥልጣን የክልሉ ነው። የፌደራል መንግሥት በቀጥታ ወደ ታች ወርዶ ሊሠራ የሚችልበት ሕጋዊ ሥልጣን የለውም፤ ውሳኔው የአሃዳዊነት አስተሳሰብና ተግባር" ነው።

- ምክር ቤቱ ሥልጣኑን ከሕገ መንግሥቱ ውጪ፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም በመስጠት ያራዘመ ስለሆነ፤ ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የለውም።

- የክልል ምክር ቤቶችም ሆኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየ5 ዓመቱ ምርጫ ማካሄድ አለባቸው። በቂ ያልሆነ ምክንያት በማቅረብ ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ሰጥቶ ሥልጣኑን ያራዘመ ስለሆነ ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የለውም።

- ከዚህ በፊት የትግራይ ክልል ምክር ቤት ተወካዮቹ በፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደማይሳተፉ አስታውቀናል። ለዚህ ምክንያቱ የምክር ቤቱ የሥልጣን ዘመን ስላበቃ ፤ አዲስ ምርጫ ተደርጎ ክልሎች ወኪሎቻቸውን ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት መላክ ስላለባቸው ነው።

- ምክር ቤቱ ለሕጋዊ አካል እና ለትግራይ ሕዝብ ያለውን ንቀት ለማሳየት ካልሆነ በስተቀር ከ 2.7 ሚሊዮን በላይ ሰው ምርጫ ላይ ተሳትፎ ተወካዮቹን መምርጧል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT
2024/09/22 04:37:47
Back to Top
HTML Embed Code: