Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው በ40ኛው የለንደን ማራቶን ላይ ስኬትን የተጎናፀፉት አትሌቶቻችን ዛሬ መስከረም 26/2013 ዓ.ም ከማለዳው 1:45 ቦሌ ኤርፖርት በሰላም ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀ/ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ማርቆስ ገነቲ እና አቶ ቢልልኝ መቆያ የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ በስፍራው ተገኝተው የጀግና አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ችሎት!

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል የተከሰሱት ፦

- 1ኛ ጥላሁን ያሚ ባልቻ፣
- 2ኛ ከበደ ገመቹ መገርሳ፣
- 3ኛ አብዲ አለማሁ እና
- 4ኛ ላምሮት ከማል መሃመድ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ክሱ ተነቦላቸዋል፡፡

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉት ተከሳሾች ጠበቃ የማቆም አቅም እንደ ሌላቸው ተናግረዋል፡፡

4ኛ ተከሳሽ የሆነችው ላምሮት ከማል ጠበቃ የማቆም አቅም እንዳላት ገልጻ ሆኖም የሚቆምልኝ ጠበቃ አጥቻለው በማለት ለፍርድ ቤት አስረድታለች፡፡

ፍርድ ቤቱ የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው አዟል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በተነበበላቸው ክስ ላይ መቃወሚያ ካላቸው ለመመልከት ለጥቅምት 4 /2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ከ80 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት ሊያሰራጩ የነበሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ !

በምዕራብ ጎጃም ዞን ወምበርማ ሽንዲ ከተማ ከ80 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት ሊያሰራጩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

አድራሻቸው ከሰከላ ወረዳ እና ከቡሬ ከተማ የሆኑ 2 ግለሰቦች በወምበርማ ወረዳ በሚገኙ ለንግድ ተቋማትና ለህብረተሰቡ ሀሰተኛ የብር ኖት ሊያሰራጩ ሲሉ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

2ቱ ተጠርጣሪዎች ሀሰተኛ የብር ኖቱን ከባህር ዳር እንዳመጡት ፖሊስ ገልጿል። ብሩን በወምበርማ ወረዳ ሊያሰራጩትም ነበር ተብሏል።

የጸጥታ ሃይል ክትትል እንዳለ ሲያውቁ ወደ ቡሬ ከተማ ተመልሰው በመሄድ ለማሰራጨት ሲሞክሩ ፖሊስ ወደ ቡሬ አብሮ በመሄድና ክትትል በማድረግ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንዳደረጋቸው ተገልጿል።

የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት በክትትል እና ስምሪት ላይ ለነበሩት የፖሊስ አባላቱ ምስጋና አቅርቧል።

ምንጭ፦ የወምበርማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

በአሁኑ ሰዓት የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አስከሬን ወደ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እየተሸኘ ይገኛል - EHRC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
“እኔ የምሰራው ሕዳሴው ግድብ ላይ ነው፤ ግድቡ ደግሞ የሁሉም ነው” - ወ/ሮ ሮማን ገ/ሥላሴ

በህወሃት ሪፖርት እንዲያደርጉ ከተባሉት አመራሮች መካከል የሕዳሴው ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሮማን ገ/ስላሴ ጥሪውን እንዳላዩት እና እንዳላነበቡት ለአል ዓይን ተናግረዋል፡፡

“እኔ የምሰራው ሕዳሴው ግድብ ላይ ነው፣ ግድቡ ደግሞ የሁሉም ብሔር ፣ የሁሉም ሕዝብ ሀብት ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ጥሪውን በተመለከተ አስተያየት እንዲሰጡ የጠተጠየቁት ወ/ሮ ሮማን ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

በሌላ በኩል የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን ሪፖርት እንዲያደርጉ ከተጠቀሱት መካከል ሲሆኑ ስለጉዳዩ እንዳልሰሙ ገልጸዋል፡፡

ጥሪ የተደረገው ለምክር ቤት አባላት መሆኑን ነው የማውቀው ያሉት ወ/ሮ አልማዝ መኮንን ትናንትና እስከ ምሽት ሥራ ላይ እንደነበሩና ስለእርሳቸውም ሆነ ስለሌሎች አመራሮች የሰሙት ነገር እንደሌለ ለአል ዓይን ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦላይን ለመፈተን የሚያስችለውን አስፈልጊ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ለባለሙያዎች ስልጠናዎችን መስጠት መጀመሩ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በትምህርት ቤቶች ውስጥ ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ የመብራትና የኔትዎርክ አቅርቦት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የኦንላይ ፈተና ኩረጃን ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ከመሆኑም ባሻገር ለወረቀት እና ፈተናውን ለማረም የሚወጣውን ወጪና ጊዜ ይቆጥባል ነው የተባለው፡፡

ተማሪዎች ፈተናውን በሚወስዱበት ጊዜ የራሳቸው ታብሌት ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲስተም አለው ተብሏል።

ፈተናው የሚሰጥባቸው ታብሌቶችም በቅርቡ ለተማሪዎች እንደሚሰራጩ ተገልጿል።

ተማሪዎች ከቴክኖሎጂው ጋር እንዲተዋወቁ ከሶስር ሣምንት ያላነሰ ጊዜ የሚሰጣቸው ሲሆን ምንም ሳይጨናነቁ ለፈተና እንዲዘጋጁ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል - #MoE

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የፕ/ር መስፍን የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ!

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸው ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ተወካዮቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና አፍቃሪዎቻቸው በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።

#ኢሰመጉ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

11ኛው የኢትዮጵያ ክልል ...

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ላቀረቡት የጋራ ክልል ምስረታ ጥያቄ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈጻሚነት "ህዝበ ውሳኔ" እንዲደራጅ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ዛሬ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ አምስተኛ ዙር የፓርላማ ዘመን ስድስተኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

እስካሁን ድረስ በደቡብ ክልል 13 የሚሆኑ ዞኖች ክልልነት ጥያቄ እያነሱ ሲሆን ጥናታቸው ሲጠናቀቅ እና ስርዓቱን ተከትለው ሲመጡ መልስ እንደሚሰጣቸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ መናገራቸውን ኢቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#AtoLidetuAyalew

ዛሬ የኦሮሚያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ የተፈቀደውን የዋስትና መብት የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ዋስትናቸው ይፈቀድላቸው በማለት ውሳኔ አሳልፏል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ተፈፃሚ እንዲሆን ለቢሸፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ደብዳቤ የፃፈ ቢሆንም ደብዳቤው የደረሰው የፖሊስ መምሪያው ግን የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አክብሬ "አልፈታም" ብሏል።

የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ፥ፖሊስ መምሪያው የፍርድ ቤቱ የውሳኔ ወረቀት ከአዳማ አምጥተን ብንሰጥም በዚህ ወሳኔ አልፈታም ብሎናል በማለት ተናግረዋል።

"የአቶ ልደቱ አያሌው ጉዳይ በፍርድ ቤት እንደማይሆን ነገረናችሗል" አሉን ያሉት አቶ አዳነ ፥ ከዚህ በፊት ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ በአደራ ነው ያሰርሗቸው አደራ የሰጠኝ አካል እስካልነገረኝ ድረስ አለቅም ብሎናል ሲሉ አቶ አዳነ ተናግረዋል።

Via Awlo Media
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
"የአርቲስት ታረቀኝ መኪና እስካሁን አልተለቀቀም" - ጠበቃ ጀምበር አብዶ

አርቲስት ታረቀኝ ሙሉ በዋስ ቢፈታም ነሐሴ 11/2012 ዓ/ም አርቲስቱ በቁጥጥር ሲዉል ሲያሽከረክረዉ የነበረዉ ዘመናዊ አቫንቴ ሀዩንዳይ መኪና አብሮ ታስሮ የነበረ ሲሆን የፌ/መ/ደ/ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ/ም መኪናዉ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ ቢሰጥም እስከ ዛሬ ድረስ መኪናው አለመለቀቁን የአርቲስቱ ጠበቃ ጀምበር አብዶ አሳውቀውናል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ዐቃቤ ህግ መኪናዉን ሊፈልገዉ ስለሚችል በሚል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልፈፅምም ማለቱን ጠበቃ ጀምበር ገልፀውናል። ዐቃቤ ህግ ሲጠየቅ መኪናዉን የያዘዉ ፖሊስ እንጂ እኛ አይደለንም የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ጠበቃ ጀምበር፥ እየታየ ያለው የህግ የበላይትነት አለማክበር ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ እየሆነ እየመጣ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#CDC

የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠርና የመከላከል ማዕከል ፣ ትናንት ባስታወቀው መሰረት የኮሮና ቫይረስ አየር ላይ ለሰዓታት ያክል በመቆየት ሊዛመት እንደሚችል ገልጿል።

በዚሁ መመሪያም መሠረት ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ብዙም የአየር ዝውውር በሌለበት ክፍል ውስጥ ሲሆኑ ከስድስት ጫማ በራቁ ሰዎችም ላይ ቢሆን ቫይረሱን ሊያስተላልፉ እንደሚችል ማስረጃ ማግኘቱን አስታውቋል።

ኮሮና ቫይረስ በዋነኝነት ሊዛመት የሚችለው በአየር በኩል ሊሆን እንደሚችል የአሜሪካ የሳይንስ ጠቢባን የፃፉት ግልፅ ደብዳቤ ትናንት “ሳይንስ” በተባለው የህክምና መጽሄት ላይ ወጥቷል ሲል ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ80 ሺህ አለፉ !

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,278 የላብራቶሪ ምርመራ 566 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 944 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 80,003 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,238 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 34,960 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#NewsAlert

የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ ተላለፈ !

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ አሳልፏል።

ውሳኔው ሊተላለፍ የቻለው ባለፈው ነሃሴ 30 2012 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባዔ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገ ፣ እንዳልተፈጸመ እና እንደማይጸና ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ነው፡፡

ውሳኔውን የሚከታተል የህገ መንግስት ጉዳዮች እና የማንነት ጉዳዮች አጣሪ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ ውሳኔው ባለመፈጸሙ በዛሬው ዕለት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ነው ይህንን ወሳኔ ሊያሳልፍ የቻለው፡፡

ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል መንግስት ላይ 3 ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል። ውሳኔዎቹ ፦

1ኛ. የትግራይ ክልል ያካሄደውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ምርጫ ተከትሎ ከተመሰረቱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት እና ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል ጋር የፌዴራል መንግስት ምንም አይነት ግንኙነት እንደማያደርግ ወስኗል፡፡

2ኛ. የፌደራል መንግስት የትግራይ ህዝብን የልማት እና መሰረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎት ማዕከል በማድረግ የከተማ እና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ህጋዊ ተቋማት ብቻ የስራ ግንኙነት ያደርጋል፡፡

3ኛ. የውሳኔውን አፈጻጸም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ ክትትል መደረግ እንዳለበት ውሳኔ አሳልፏል። (ኢቲቪ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#PASSPORT

- የመደበኛ ፓስፖርት እድሳት እና አዲስ ጥያቄ ከጥቅምት 2/2013 ጀምሮ በሁሉም የኤጀንሲው (INVEA) የክልል ቅርንጫፍ ቢሮዎች አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፤

- በአዲስ አበባ ቢሮ ከህዳር 1/2013 ጀምሮ ሁሉም መደበኛ አገልግሎቶች ይጀምራሉ፤

- በ Online ላይ ፖስፖርት ለማደስ እና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት በጥቅምት 10/ 2013 ይጀምራል፤

- ለውጭ አገር ዜጎች በOnline ቪዛ የማራዘም እና ግዜያዊ መኖሪያ ፍቃድ የማደስ እና አዲስ የመጠየቅ አገልግሎት ጥቅምት 2/2013 ይጀምራል፤

- የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ እድሳትና ጥያቄ መደበኛ አገልግሎት ከጥቅምት 2/2013 እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- የኢማግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/22 06:39:33
Back to Top
HTML Embed Code: