Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለትላንቱ ውድድር ወደ ስፔን (ቫሌንሺያ) ስታመራ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ያጋጠማት ምንድን ነው ?

(በኢትዮጵያ ቼክ የቀረበ)

አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መጉላላት እንደደረሰባት እና የኢትዮጵያ አሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ ኤርፖርት በመገኘት ችግሩ እንዲቀረፍ እንዳደረገች ከምስጋና ጋር ገልፃለች።

አትሌት ደራርቱ ስለተከሰተው ችግር ለኢትዮጵያ ቼክ ተከታዩን ብላለች ፦

"ባለፈው እሁድ ምሽት አትሌት ለተሰንበትና ማናጀሯ ሀይሌ ኤርፖርት ሆነው 'እንዳንሄድ ታግደናል' ብለው ስልክ ደወሉልኝ። ያላሟሉት ዶክመንት እንዳለ ስጠይቃቸው ሁሉም እንዳላቸው ነገሩኝ፣ ከዛም ወደ ኤርፖርት ሄድኩ።

አለመግባባቱ የነበረው ከጤና ሚኒስቴር በተፃፈ ደብዳቤ ዙርያ ነበር። አትሌቷ ደብዳቤውን ይዛ ነበር፣ አሳይቻለሁ አለች፣ ኤርፖርት ያሉት ደግሞ አላሳየችንም ይሉ ነበር።

ጉዳዩ ትልቅ አልነበረም፣ ዋናው እንኳን ተሳካላት። እኔ ልናገር የምፈልገው ስፖርት እና ሌላ ነገር መለያየት አለበት፣ ሁለቱ ቢለያይ ጥሩ ይመስለኛል። አሁን አትሌት ለተሰንበት ወደ ሀገር ትመለሳለች፣ ያኔ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት አካል ካለ ይቅርታ ይጠይቃል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በአዲስ አበባ ከተማ በተከሰተው የስንዴ ዱቄት እጥረት ዳቦ ቤቶች ስራቸው እየተስተጓጎለ መሆኑን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ አመለከቱ።

ከዳቦ ስንዴ ጋር በተያያዘ የሚነሳው ቅሬታ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ምላሽ እንደሚያገኝ የከተማዋ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል - https://telegra.ph/EPA-10-08

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

"በባህላዊ መንገድ በፕሌን የኬሚካል ርጭት ቢደረግም ይሄ ከአቅም በላይ ነው ሰብላችንን ማዳን አልቻልንም እንግዲህ ያዘነ ይርዳን" - የወረባቦ አርሶ አደር

በወረባቦ ወረዳ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ከ11 ቀበሌዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ሰብል አውድሟል።

የወረባቦ ወረዳ አርሶ አደር፣ የወረባቦ ወረዳ አመራር የደቡብ ወሎ ዞን አመራሮች የግብርና ባለሙያዎች የየአካባቢው ወጣቶች የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል በባህላዊ መንገድ እና በፕሌን ርጭት በማድረግ የተለያዩ ጥረቶች ቢያደርጉም ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ተናግረዋል ።

የአካባቢው ሰዎች ፥ በባህላዊ መንገድም በፕሌን የኬሚካል ርጭት ቢደረግም ይሄ ከአቅማችን በላይ ነው ሰብላችንን ከአንበጣ መንጋ ማዳን አልቻልንም እንግዲህ ያዘነ ይድረስልን ብለዋል። (ወረባቦ ኮሚኒኬሽን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#NBE

ብሔራዊ ባንክ መስከረም 27/2013 ዓ/ም ለፋይናንስ ተቋማት ባስተላለፈው መመሪያ በቀን ወጪ ማድረግ የሚቻለው የብር መጠን በግለሰብ ደረጃ 50,000 በተቋም ደረጃ 75,000 እንደሚሆን ወስኗል።

ግንቦት ወር ላይ ወጥቶ የነበረው መመሪያ ለግለሰብ 200 ሺህ ለተቋም 300 ሺህ በቀን ማውጣት ይፈቅድ እንደነበር ይታወሳል።

Via ShegerTimes/Elias Meseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ጦርነቱ ወደ ቀጠናዊ ጦርነት ሊያመራ ይችላል"- ሃሰን ሮሃኒ

አርሜኒያና አዘርባጃን መካከል እየተደረገ የሚገኘው ጦርነት ዛሬ 11 ቀን ሆኖታል።

አርሜኒ እና አዘርባጃን እየተዋጉ የሚገኙት በናጎርኖ-ካራህ ግዛት ላይ ባላቸው የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ነው።

በጦርነቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች እና ወታደሮች እንዳለቁ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ (VOA) ዘግቧል።

በሰሜን ምዕራብ በኩል ከ2ቱም ሀገራት ጋር የምትዋሰነውና ከሀገራቱ ጋር መልካም የሆነ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላት ኢራን ሁኔታው እጅግ እንዳሳሰባት ገልፃለች።

የኢራን ፕሬዜዳንት ሮሃኒ በ2ቱ ሀገራት መካከል የሚደረገው ውጊያ ወደ ሀገሪቱ ድንበሮች ሊስፋፋ እንደሚችል እና ወደቀጠናዊ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ጋሹ ዱጋዝ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ተከታዩን መረጃ ሰጥተዋል ፦

- ከ2 ቀን በፊት በዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ቀበሌ 14 ንጹሃን ዜጎች ተገድለዋል፡፡ 8ቱ ደግሞ ቆስለው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

- የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት ንጹሃን ሰዎች መካከል አንደኛው የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።

- ከሰሞኑን ዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ቀበሌ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ካደረሱ ሃይሎች 14ቱ ተደምስሰዋል፤ 2ቱ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ተይዘዋል።

- ቀጠናውን ከጠላት ነጻ ለማድረግ በዞኑ ተደጋጋሚ ግጭት በሚስተዋልባቸው ዳንጉር እና ጉባ ወረዳዎች ውስጥ በተለይ ገጠር አካባቢ የሚኖረው አርሶ አደር ለግብርናም ሆነ በማናቸውም ጉዳዮች እንዳይንቀሳቀስና ላልተወሰነ ጊዜ ባለበት ማዕከል ተረጋግቶ እንዲቆይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ዛሬ ጠዋት ሁለት መቶ ዘጠና ሰባት (297) የኢትዮጵያ ዜጎች ከሳዐዲ አረቢያ (ጅዳ) ወደ ሀገራቸው በሰላም ተመለሰዋል።

ከዛሬዎቹ 297 ተመላሾች መካከል ሃያ አምስቱ (25) ህጻናት እንደሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ አሳውቀውናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም አረፉ!

በመካ ዳረል ሐዲስ ኸይርያና በመስጂድ አል ሓራም መምህር የነበሩት ኢትዮጵያዊው የእስልምና አስተማሪ በዛሬው እለት መስከረም 28 አርፈዋል። ለቤተሰቦቸው እና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያዊ መፅናናትን እንመኛለን።

[አንዋር ከአፍሪካ TV]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በ2 ወር ውስጥ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባት መድረክ ሊደረግ ነው !

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ፣ ዴስቲኒ ኢትዮጵያ እና የሐሳብ መንገድ በጋር ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያመቻቹት ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክር እንደሚደረግ አል ዓልን ዘግቧል።

የ3ቱ ተቋማት ተወካዮች እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ የተጋረጠ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ምስቅልቅሎሽ ለመመከትን እና ሰላምን በዘላቂነት ለማምጣት ያለመ ምክክር ይደረጋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#GERD

በዛሬው ዕለት መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ከ ወንጌል ተማሪዎቻቸው ጋር በመተባበር 545,000 ብር ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድጋፍ አድርገዋል።

መምህር ግርማ ከግድቡ በተጨማሪ 645,000 ብር ለተፈናቀሉ ወገኖች ለድጋፍ ማዋላቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,668 የላብራቶሪ ምርመራ 902 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 764 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 81,797 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,262 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 36,434 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#EthiopianAirlines

የዓለም የ5,000 ሜትር ሪከርድ ባለቤት አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከፍራንክፈርት ስትነሳ በካፒቴን ዮናታን እንዲሁም በአየር መንገዱ የበረራ እና መስተንግዶ ባልደረቦች አቀባባል ተደርጎላታል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ትኩረት-መስጠት ውስን ሀብት ነው፤ አናባክነው!

በሀገራችን ባለፉት 2 ሳምንታት ብቻ መልሰን የማናገኛቸዉ ክቡር የሆኑ 146 ወንድሞች እና እህቶቻችንን አጥተናል። በህይወት ኖሮ ይህን አስከፊ ጊዜ ማለፍ መቻል፤ ከዚህ በላይ ትኩረት-መሰጠት ያለበት ጉዳይ ያለ አይመስለኝም።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት እስከትላንትናው እለት ድረስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 81,797 እንዲሁም በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸዉን ማጣት ያልነበረባቸዉ ሰዎች ቁጥር 1,262 ደርሷል፣ ይህ እውነታ በጣም ያማል።

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዋጅ በተሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የሚያግዝ ልዩ መመሪያ አውጥተዋል።

መመሪያው ከነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተጨማሪ የተለያዩ የሚከለከሉ እና የተፈቀዱ ክንዋኔዎችን ይዞ ነው የመጣው፤ ሁሉም ቢያነበው የተሻለ ይሆናል።

ይህ መመሪያ ከግለሰብ አንስቶ እንደ ከውጭ ወደ ሀገር ለሚገቡ ሰዎች፣ በመንግስታዊም ሆነ በግል ተቋማት ውስጥ፣ የንግድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የግልም ሆነ የመንግስት ት/ቤቶች ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲዎች፣ የህጻናት ማቆያ ማዕከል እና ለመሳሰሉት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ላላደረገ አገልግሎት መስጠት የከለከለ ነው።

መመሪያው በአግባቡና በትክክል በመከተል ወደቀድሞው ጥንቃቄ እና ትኩረት - መስጠቱ ቢመለስ ባልተገባ የጥንቃቄ ጉድልለት ምክንያት ከሄዱ ሊመለሱ የማይችሉትን ፣ የምንወዳቸውን ፣ የምናስብላቸውን ፣ የምንፈልጋቸውን እና የምናስፈልጋቸውን በአፅንኦት እንጠብቅ።

እባካችሁ ለራሳችንም ሆነ ለሌላው ሰበብ አንሁን፤ የተባልነውን በአግባቡ እንተግብር!

ዶ/ር ያቤፅ ከበደ
መስከረም 29/2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/22 06:20:40
Back to Top
HTML Embed Code: