Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#Irreecha2013

ዛሬ በውስን ተሳታፊዎች የተከበረው የ "ሆራ ፊንፊኔ" የኢሬቻ በዓል አንዳች የጸጥታ ችግር ሳያጋጥም በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በሀዋሳ ከተማ ትምህርት ለማስጀመር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል !

በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት በፈረቃ እንደሚሰጥ ተገልጿል። በዚህም ፦

• አንደኛው ግሩፕ ሰኞ ፣ ረቡዕ እና አርብ ጠዋት እና ከሰዓት በፈረቃ ይማራሉ።

• ሌላኛው ግሩፕ ደግሞ ማክሰኞ ፣ ሀሙስ እና ቅዳሜ ይማራሉ።

የመማሪያ ክፍሎችን በተመከተ የክፍል ስፋታቸው 56 ካሬ የሆነ 25 ተማሪ ብቻ የሚማር ሆኖ በአንድ መቀመጫ አንድ ተማሪ ብቻ በማስቀመጥ ተግባራዊ ይሆናል።

ሌላዉ የትምህርት ቤት ክፍያ በሚመለከት የመንግስት ትምህርት 1-12 ክፍል በነፃ ነው።

የግል ትምህርት ቤቶች በ2013 የትምህርት ዘመን ምንም አይነት የክፍያ ጭማሬ ሳያደርጉ ተማሪዎችን ተቀብለው ማስተማር ይገባቸዋል ተብሏል።

ምንጭ:- የሀዋሳ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ንግድ ባንክ ነገ አገልግሎት ይሰጣል!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አዲሱ የ ብር ኖት ስርጭት ጋር በተያያዘ በነገው ዕለት እሁድ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ/ም በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ አማካኝነት አገልግሎት እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ተጨማሪ መረጃ ፦ ከአዲሱ የብር ቅያሪ ጋር በተያያዘ ህብረት ባንክ ነገ ሙሉ ቀን ደንበኞቹን እንደሚያገለግል አሳውቋል።

ማስታወሻ !

አዲሱን የገንዘብ ኖት የመቀየሪያ ጊዜ ሊያበቃ፦

- ከ100 ሺህ ብር በታች ለሆነ 71 ቀን ቀርቶታል።

- ከ100 ሺህ ብር በላይ ለሆነ 11 ቀን ቀርቶታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በመሬት መንሸራተት አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ውስጥ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት አስታወቁን ኢዜአ ዘገበ።

የመሬት መንሸራተት አደጋው የደረሰው ትናንት ሌሊት ጊዶ መጣላ ቀበሌ ውስጥ በቤታቸው ተኝተው በነበሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ ነው።

በአደጋው ቤቱ እላያቸው ላይ በመደርመሱ ከቤተሰቡ አባላት መካከል የሁለት (2) ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጸዋል።

የዞኑ አደጋ ስጋት አመራር ቡድን እና የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ስራ ኃላፊዎች ወደ አካባቢው በማቅናት የሟቾቹን ቤተሰብ ማፅናናታቸውንና ድጋፍ ማድረጋቸውን ከኢዜአ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,726 የላብራቶሪ ምርመራ 872 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 648 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 77,860 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,214 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 32,325 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በሳዑዲ አረቢያ የኡምራ ጸሎት ከነገ እሁድ ጀምሮ መካሄድ ይጀምራል!

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ላለፉት 7 ወራት ተቋርጦ የነበረው የኡምራ ፀሎት ከነገ ጀምሮ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ለሚገኙ ምዕመናን ክፍት የሚደረግ ይሆናል።

ከነገ በሚጀምረው የኡምራ ፀሎት በየዕለቱ 6,000 ዜጎች የፀሎት ስነ ስርዓት የሚያካሂዱ ይሆናል። ይህ ቁጥር ከጥቅምት 8 ጀምሮ አሁን ካለበት ወደ 75 % እንደሚያድግ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ሳዑዲ አረቢያ ከጥቅምት 22 (Nov 1) ጀምሮ ከተወሰኑ አገራት የሐጅና ኡምራ ተጓዦች የምታስተናግድ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#Irreecha2013

የቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በሠላም ተከበረ።

የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል ከንጋቱ ጀምሮ በሆራ አርሰዴ በተከናወነ ስነስርዓት ተከብሯል።

የበዓሉ ስነ ስርዓት በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባገዳዎች ምርቃት ነው የተጀመረው፡፡

በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሆራ አርሰዴ በማቅናት በባህሉ መሰረት ለፈጣሪያቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል የሆረ አርሰዲ የእሬቻ በዓል አባገዳዎች ባስቀመጡት አቅጣጫ መከበሩን አባገዳ ጎበና ሆላ ገልጸዋል፡፡

አባገዳ ጎበና ሆላ መጪው ዓመት የኮቪድ -19 ወርርሽኝ አልፎ እንደተለመደው ህዝቡ በዓሉን በጋራ እንዲያከብረው ያላቸውን ተስፋ መግለፃቸውን ኢቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የአፋር ህዝብ ፓርቲ በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ !

የአፋር ህዝብ ፓርቲ ትላንት በሰመራ ከተማ በተደረገ ዝግጅት በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

የአፋር ህዝብ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሄሬ ሀመዱ ለክልሉ ፕሬዝደንት ሀጂ አወል አርባ 362,320.00 ብር አስረክበዋል።

አቴ ሄሬ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት፥ "ለህዝባችን ከዚህ በላይ የሚገባው ቢሆንም አቅም በፈቀደው ልክ ለመርዳት ሁልጊዜም ዝግጁ ነን" ብለዋል።

በሌላ በኩል የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለፓርቲው የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክቷል።

በዚህም ጊዜ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ሀጂ አወል አርባ "የአፋር ህዝብ ፓርቲ መንግስት ሳይሆን ከመንግስት በላይ ለህዝብ የሚያስብ ፓርቲ በመሆኑ ሁሉም በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችና በሀገር ደረጃም ያሉ ፓርቲዎች አፋር ህዝብ ፓርቲ ብዙ መማር ይገባቸዋል" በማለት ተናግረው ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርቧል።

የአፋር ህዝብ ፓርቲ ከአሁን በፊት ለኮሮና ወርሽኝ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

Via Mussa Adem Oumer
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በሳዑዲ አረቢያ የኡምራ ፀሎት ለሊት ጀምሯል!

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ላለፉት 7 ወራት ተቋርጦ የነበረው የኡምራ ፀሎት ከለሊት ጀምሮ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ለሚገኙ ምዕመናን ክፍት ተደርጓል።

አሁን ላይ በየዕለቱ 6,000 ምዕመናን የፀሎት ስነ ስርዓት እንዲያደርጉ የተፈቀደ ሲሆን ከጥቅምት 8 ጀምሮ ወደ 75% ያድጋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DonaldTrump

በኮቪድ-19 ተይዘው ሆስፒታል የገቡት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደህና መሆናቸውንና ቀጣዮቹ ቀናት ለጤንነታቸው ወሳኝ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት ጤንነታቸውን አስመልክቶ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎችን ተከትሎ ትላንት በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ነው።

"እዚህ ስመጣ ደህና አልነበርኩም ፤ አሁን ላይ ግን እየተሻለኝ ነው" ብለዋል ትራምፕ። የሚቀጥሉት ቀናት ወሳኝ እንደሆኑ ገልፀው፤ " በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ምን እንደሚፈጠር እናያለን" ብለዋል።

የፕሬዚደንቱ ሐኪም ትራምፕ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና ሕክምናውን ከጀመሩ አንስቶ ለውጥ እያሳዩ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሐኪማቸው ዶ/ር ኮንሊ በሰጡት መግለጫ ላይ ፕሬዚደንቱ ከተጋረጠባቸው አደጋ ሙሉ ለሙሉ ባይላቀቁም ፤ የሕክምና ቡድኑ ግን በሁኔታቸው ተስፋ እንዳለው ተናግረዋል - (BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ በዛሬው ዕለት ፦

- ለዶክተር አፈወርቅ ሙሉጌታ
- ለዶክተር ኢብራሂም ፍትዊ
- ለዶክተር ክንፈ አብርሃ
- ለዶክተር ምሩፅ ሓጎስ
- ለዶክተር ገብረህይወት ታደሰ
- ለዶክተር መሃመድ እስማኤል
- ለዶክተር አለማየሁ ባይራይ እና ለዶክተር ሃፍቱ በርሄ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

Via Mekelle University
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ደስ አለን !

40ኛው የለንደን ወንዶች ማራቶን በኢትዮጵያዊያን የበላይነት ተጠናቋል።

ሹራ ቂጣታ ቶላ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል።

በውድድሩ ተጠብቆ የነበረው ኢሉድ ኪፕ ቾጌ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች እጁን ለኢትዮጵያውያን ጀግኖች አትሌቶች ለመስጠት ተገዷል።

ኪፕ ቾጌ በማራቶን ታሪኩ ያስመዘገበው ዝቅተኛው ውጤት ሆኗል።

Via @tikvahethsport
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በኢትዮጵያውያን ጀግኖች አትሌቶች የበላይነት የተጠናቀቀው የለንደን ማራቶን ፦

1ኛ ሹራ ቂጣታ ቶላ 🇪🇹
2ኛ ቪሴንት ኪፕቹምባ 🇰🇪
3ኛ ሲሳይ ለማ 🇪🇹
4ኛ ሞስነት ገረመው 🇪🇹
5ኛ ሙሌ ዋሲሁን 🇪🇹
6ኛ ታምራት ቶላ 🇪🇹

እንኳን ደስ አለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/22 12:23:24
Back to Top
HTML Embed Code: