Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,475 የላብራቶሪ ምርመራ 730 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 226 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 76,098 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,205 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 31,430 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
መስከረም 21/2013 ዓ/ም

የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 75 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 201 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 41 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 696 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 25 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#DireDawa

በድሬዳዋ 195 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 76 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 211 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 65 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 621 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 36 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 652 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 89 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 2,814 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 286 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#Gambella

በጋምቤላ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 88 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 10 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፤ 7ቱ ኢትዮጵያውያን ፣ 3ቱ ቻይናውያን ናቸው።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 793 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 70 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBOT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ዶናልድ ትራምፕ እና ባለቤታቸው በኮቪድ-19 ተያዙ!

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ቪኦኤ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ላይ እርሳቸው እና ባለቤታቸው በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ገልፀዋል።

የዶናልድ ትራምፕ የቅርብ አማካሪያ በኮሮና ቫይረስ መያዟን ተከትሎ ነው ለእርሳቸው እና ለባለቤታቸው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሚከበርበት ዙሪያ እና አካባቢው ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት 30 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቀ ድረስ በግራ እና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በፍጹም የተከለከለ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

#Irreecha2013
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#Irreecha2013

2ኛው ኢሬቻ ፎረም አባገዳዎች፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳውና ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
"ተማሪዎች ከጥቅምት 9 ጀምሮ ትምህርት ቤት በመገኘት ዝግጅት ማድረግ አለባቸው" - አቶ ማሄ ቦዳ (የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ)

የደቡብ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን የ8ኛ ክፍል ፈተና #በክልል ደረጃ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

የቢሮ ኃላፊው የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ. ም እንደሚሰጥ፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ አስታውሰዋል።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል መሠረት ባደረገ መልክ በኦንላይ ስለሚሆን ከኩረጃ የፀዳ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ማሄ ቦዳ ተማሪዎች ከጥቅምት 9/2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት ቤት በመገኘት ዝግጅታቸውን ማድረግ አለባቸው ሲሉ ማሳስበባቸውን ከቢሮው የ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ማስታወሻ!

ውድ የቲክቫህ አባላት ከዚህ ሰዓት አንስቶ (10:30) የኢሬቻ በዓል እስኪጠናቀቅ ድረስ ከላይ የተዘረዘሩት መንገዶች በሙሉ ዝግ ስለሚሆኑ አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ።

#SHARE #ሼር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ሲኒማ ቤቶች ከመስከረም 29 ጀምሮ ይከፈታሉ!

በኮቪድ-19 ምክንያት ለ7 ወራት ተዘግተው የቆዩት ሲኒማ ቤቶች አስፈላጊውን የመከላከያ እርምጃዎች ተግባራዊ በማድረግ ሊከፍቱ እየተዘጋጁ መሆኑን 'ባላገሩ ቴሌቪዥን' ዘግቧል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጠው የፊልም ፕሮዲዩሰሮች ማህበር ሲኒማ ቤቶች በመዘጋታቸው ሳቢያ ከ40 ያላነሱ አዳዲስ ፊልሞች ለእይታ ሳይቀርቡ እንደቀሩ አሳውቋል።

በዚህም ከ40 እስከ 50 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ኪሰራ በዘርፉ ላይ እንዳጋጠመ ገልጿል።

በተጨማሪም ዘርፉ ከእንቅስቃሴ ውጭ በነበረበት ወቅት በዚህ ስራ ህይወታቸውን የመሰረቱ ከ5,000 ያላነሱ ዜጎች ከስራ ውጭ ስለመሆናቸው ተነስቷል።

የሲኒማ ቤቶችን ስራ ዳግም ለማስጀመር ከጤና ሚኒስቴር እና ከEPHI ጋር 3 ወራት የፈጀ ምክክር እና የደህንነት መመሪያዎችን የማዘጋጀት ስራ ተሰርቷል።

ለአገልግሎት ክፍት የሚሆኑ ሲኒማ ቤቶች ዝግጁነታቸውን በሚመለከት በቅርቡ የቅኝት ስራ የሚሰራ ሲሆን የጥንቃቄ መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቻ ወደ ስራ እንደሚገቡ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የኬሚካል ርጭት በማድረግ ላይ የነበረች አውሮፕላን ተከሰከሰች !

በወረባቦ ወረዳ ለተከሰተው አንበጣ መንጋ የኬሚካል ርጭት በማድረግ ላይ የነበረች አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር ምክንያት 014 ቀበሌ ልዩ ስፍራው 'ፍራንጉል' በተባለ ቦታ ተከሰከሰች።

አውሮፕላኗን የሚያበረው ፖይለት በህይወት የተረፈ ሲሆን ሰመራ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።

ምንጭ፦ የወረባቦ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውጪ ሆኗል !

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በጉጉት ሲጠበቅ ከነበረው የለንደን ማራቶን ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት እንደማይሳተፍ ይፋ አድርጓል።

@tikvahethsport
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,916 የላብራቶሪ ምርመራ 890 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 247 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 76,988 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,208 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 31,677 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በዛሬው ዕለት እና ነገ ጥዋት በረራ ያለባቸው በርካታ ሰዎች ከጥዋት አንስቶ እስካሁን ድረስ በICL (ቡልጋሪያ የሚገኘው) ውጤት በመጠበቅ እየተጉላሉ እንደሆነ ገልፀዋል።

ምሽት 4 ሰዓት ላይ የውጭ በረራ ያለበት የቲክቫህ ቤተሰብ አባል "በቦታው የሚያስተናግደን የለም፣ የሚሰማን አካል አጥተናል፤ መፍትሄ ይፈለግ" ሲል መልዕክቱን አስቀምጧል።

በተጨማሪ ሌላ ነገ በረራ ያለበት የቲክቫህ አባል ፥ "ውጤት አልደረሰም እየተባልን ነው ፣ ለምን እንደዘገየም የሚያስረዳን አላገኘንም ፣ አሁን ያለንበት ሁኔታ ይበልጥ ለኮሮና ቫይረስ በሚያጋልጥ መልኩ ነው" ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
መስከረም 22/2013 ዓ/ም

የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 208 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሰው በኮቪድ-19 መያዙ ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 120 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 23 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 566 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 104 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#DireDawa

በድሬዳዋ 168 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 67 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 311 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 103 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 451 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 135 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 3,274 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 333 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Gambella

በጋምቤላ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 92 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 5 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ትላንት 2 ሰዎች አገግመዋል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 822 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 61 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBOT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#OBN_LIVE

ልዩ የኢሬቻ በዓል የሙዚቃ ኮንሰርት ከአዲስ አበባ በቀጥታ በኦሮሚያ ብሮድስካስቲንግ ኔትዎርክ - OBN TV በቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት በቅርቡ ህመም አጋጥሞት የነበረው አንጋፋው የሀገራችን አርቲስት ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የሙዚቃ ስራውን በማቅረብ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Baga ittiin isin gahe, nu gahe !
እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን !

Ayyaana Gaarii !
መልካም በዓል !
#Irreecha2013

(Tikvah Itoophiyaa)

[3 MB]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#Irreecha2013

የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በውስን ተሳታፊዎች ብቻ እየተከበረ ይገኛል። በበአሉ አባገዳዎች ፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

PHOTO : EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶናልድ ትራምፕ ሆስፒታል ገብተዋል!

በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሆስፒታል መግባታቸውን BBC ዘግቧል።

ፕሬዝዳንቱ ትኩሳት አላቸው። ዋይትሐውስ ትንሽ ድካም ተሰምቷቸው ነው እንጂ መንፈሳቸው ጠንካራ ነው ብሏል።

ዶናልድ ትራምፕ የተወሰዱት ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ ወደሚገኘው የዋልተር ሪድ ብሔራዊ የወታደራዊ ህክምና ማዕከል ነው።

ዶናልድ ትራምፕ አሁን በሆስፒታል ሆነው ገና ሙከራ ላይ ያለውን መድኃኒት እየወሰዱ እንደሆነ ተሰምቷል፤ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ አብረዋቸው እንደሚገኙ BBC አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (etv) ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዶክተር ይናገር ደሴ ተከታዩን ብለዋል ፦

- የብር መቀየር ሂደቱ 2 ሳምንት ሆኖታል፤ እስካሁን በመላው ሀገሪቱ ባሉ የባንክ ቅርንጫፎች 99.9 በመቶ በሚሆኑት አዲሱ የብር ኖት ደርሷል።

- 67 ቢሊዮን ብር አዳዲስ የብር ኖቶች በመላው ሀገሪቱ ባሉ የባንክ ቅርንጫፎች እንዲዳረስ ተደርጓል።

- በብር መቀየር ሂደቱ ወደ 580 ሺህ ሰዎች በ14 ቀናት ውስጥ አዳዲስ የሂሳብ አካውንት ከፍተዋል።

- የብር መቀየሪያው ጊዜ እስኪጠናቀቅ በሚሊዮን የሚቆጠር ሰው አዲስ አካውንት ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል።

- በ14 ቀናት ውስጥ ብቻ አዳዲስ በተከፈቱት 580 ሺህ አካውንቶች 14 ቢሊዮን ብር ገቢ ተደርጓል ፤ (ይሄ በነባር አካውንት የገባውን ሳይጨምር ነው)

- በነባር አካውንቶች ውስጥ የገባው ገንዘብ እየተሰራ ስለሆነ ሲጠናቀቅ ይፋ ይደረጋል።

- በብር ስርጭቱ ወቅት በፀጥታ በኩል እካሁን የጎላ ችግር አላጋጠመም። ህገወጥ ሰዎች ሀሰተኛ ብር ይዘው ወደ ባንክ የሄዱ፣ ሀሰተኛ ዶላር ዝውውር ላይ የተሰማሩ ህገወጥ ሰዎችን መያዝ ተችሏል። ህገወጥ ሰዎችን የማዳከሙ ስራ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው።

- አሁንም ገንዘባቸው ያልቀየሩ በቀረው ጊዜ ሊቀይሩ ይገባል። በኃላ የሚፈጠረውን መጨናነቅ ለማስቀረት በቀረው ጊዜ መቀየር ያስፈልጋል።

- ከ100 ሺህ - 1.5 ሚሊዮን ብር ያላቸው ሰዎች በአንድ ወር ውስጥ እንዲቀይሩ መገለፁ ይታወቃል። ጊዜው ሊጠናቀቅ የተወሰኑ ቀናት ብቻ ስለቀረ በፍጥነት ገንዘባቸውን ሊቀይሩ ይገባል።

@tikvahethiopiaBOT
2024/09/22 14:23:08
Back to Top
HTML Embed Code: