Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

በመተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው ያለባቸው እና በቸልተኝነት ኃላፊነት በአግባቡ ባልተወጡ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ላይ የክልሉ መንግስት ህጋዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልጿል።

እርምጃ ከተወሰደባቸው 45 አመራሮች ውስጥ አንድ የአመራር ሽግሽግ የተደረገ ሲሆን ሌሎቹ በሙሉ ከኃላፊነት እንዲነሱ ተወስኗል። ከመካከላቸው 10ሩ አመራሮች በህግ እንዲጠየቁ እና ምርመራ እንዲጣራባቸው ተደርጓል።

ምንጭ፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ከእስር ቤት ሊያመልጥ የሞከረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በአንኮበር ወረዳ አንኮበር ፖሊስ ጣቢያ ሰው መግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተጣራበት የሚገኘው ደስታ አለሙ የተባለው ግለሰብ ከእስር ቤት ግድግዳ ፈርፍሮ ለማምለጥ ሲሞክር ጥበቃ ላይ በነበሩ የፖሊስ ኦፊሰሮች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ተጠርጣሪው በትላንትናው ዕለት ከምሽቱ 3፡30 ላይ ድርጊቱን መፈፀሙንና በዚህ ላይም የምርመራ ፋይል ተከፍቶ መዝገቡ እየታየ መሆኑን የአንኮበር ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Via Ankober Communication
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (NEBE) ይፋዊ በሆነው የፌስቡክ ገፁ የቦርዱ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙ 40 ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተማሪዎች መገኘታቸው ተገለፀ!

በዚህም የተነሳ አዲሱ የትምህርት ዘመን ሲጀመር በሺህዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ራሳቸውን አግልለው ይቆያሉ ተብሏል።

#1

ዩኒቨርስቲ ኦፍ አብሪስቲዊዝ የኮቪድ-19 ስርጭት ለመግታት በሚል የገጽ ለገጽ ትምህርትን አስቀርቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ተማሪዎች ለገና እረፍት ወደ ቤታቸው መሄድ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

#2

ስኮትላንድ ውስጥ ተማሪዎች ለገና እረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ከመጀመራቸው በፊት የገጽ ለገጽ ትምህርት እንደሚኖር ተነግሯቸው የነበረ ቢሆንም ፤ አሁን ግን በወረርሽኙ ምክንያት ተቋማት ትምህርት በኢንተርኔት አማካይነት ወደ መስጠት አዘንብለዋል።

#3

በማንችስተር ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ለ14 ቀናት በኢንተርኔት አማካኝነት እንደሚማሩ ተገልጿል።

127 ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ እንዳለባቸው ሲረጋገጥ 1,700 ተማሪዎች ደግሞ ለ2 ሳምንት ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ተደርጓል።

#4

በግላስኮ ዩኒቨርስቲ 172 ተማሪዎች ኮሮና ሲገኝባቸው 600 ተማሪዎች ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ተወስኗል።

#5

- በኩዊንስ ዩኒቨርስቲ ቤልፋስት ውስጥ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በመረጋጋጡ የተወሰኑ ተማሪዎች ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ ተደርጓል።

በርካታ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ቅይጥ በሆነ ስልት እንደሚያስተምሩ ታውቋል። ይህም በኢንተርኔትና በገጽ ለገጽ የሚሰጥ ትምህረትን ጎን ለጎን መስጠትን ያካትታል ተብሏል።

ምንጭ ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,747 የላብራቶሪ ምርመራ 612 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 390 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 73,944 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,177 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 30,753 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የትምህርት ተቋማት እደገና የሚከፈቱት የሁሉም ልጆቻችን ደህንነት ማረጋገጥ ስንችል ብቻ ነው" - ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ

ዛሬ መግለጫ የሰጡት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፥ "የትምህርት ተቋማት እንደገና መከፈት ያለባቸው የሁሉም ልጆቻችንን ደህንነት ማረጋገጥ ስንችል ብቻ ነው" ብለዋል።

ፕሬዘዳንት ኡሀሩ ኬንያታ አሁን ትኩረት ልናደርግ የሚገባው 'መቼ ትምህርት ቤቶች ይከፈቱ ?' በሚለው ላይ ሳይሆን 'እንዴት የልጆቻችን ጤና ፣ ህይወት እና ደህንነት ተጠብቆ ትምህርት ተቋማት ይከፈቱ በሚለው ላይ መሆን አለበት' ብለዋል።

ዛሬ ፕዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የትምህርት ተቋማት መከፈቻ ጊዜን ያሳውቃሉ ተብሎ በጠበቅም ይህ ሳይሆን ቀርቷል።

በነገራችን ላይ የኬንያ ትምህርት ሚኒስቴር ከትላንት ጀምሮ መምህራን በየትምህርት ቤታቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳውቆ ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀነኒሳ በቀለ ለንደን ከትሟል!

ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በመጪው እሁድ ለሚያደርገው የለንደን ማራቶን ውድድር ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ጋር ለንደን መከተሙ እና ወደ ተዘጋጀለት ሆቴል መግባቱን የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል። 

@tikvahethsport @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ነገ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች !

ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ ፡-

• በመሳለምያ ፣ በእሳት አደጋ ፣ በሳንባ ነቀርሳ፣ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ፣ በታይዋን ፣ በሆላንድ ኤምባሲ እና አካባቢዎቻቸው፤

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ፡-

• በሃና ማርያም ፣ በሃይሌ ጋርመንት ፣ በቆጣሪ ኮንዶሚኒየም ፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም ፣ በማንጎ ሰፈር ፣ በሳሪስ አቦ ቤተ-ክርስትያን ፣ በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም ፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞርያ ፣ በክሬሸር እና አካባቢዎቻቸው በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል ፤ ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ የኢ/ኤ/አ አሳስቧል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነትን የሚያጣራው ኮሚቴ ወደ ስራ ገብቷል!

ኮሚቴው ከጤና ፣ ከትምህርት ፣ ከአስተዳደር ዘርፍ እንዲሁም ከወላጆች የተወጣጡ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በተለይ ወላጆች በአብላጫው የሚሳተፉበት ነው፡፡

ይህ ኮሚቴ በሚቀጥሉት 3 ሳምንታት ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ሁኔታ የሚገመግም ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር የሚላኩ ቁሳቁሶች መድረሳቸውን የሚያጣራ ፣ ሌሎች ድጋፎችን የሚያስተባብር ነው።

በተጨማሪ ኮሚቴው በትምህርት ቤቶች አስፈላጊው ግብዕቶች መኖራቸውን የሚመለከት እንዲሁም ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ትምህርት ማስኬድ የሚችልበት ሁኔታ ላይ ስለመሆኑ ይገመግማል፡፡

ኮሚቴው የትምህርት ቤቶችን ነባራዊ ሁኔታ ገምግሞ ውሳኔ ሲያስልፍ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱ ሲሆን ትምህርት ቤቶችን የመክፈት ሁኔታ የሚወሰነው የትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጁነቱ ሲኖር መሆኑን ተነግሯል፡፡

በግል ትምህርት ቤቶች ወላጅ ኮሚቴዎች የትምህርት ቤቱ ዝግጁነቱን ካላረጋገጡ እና ካላመኑበት ትምህርት ቤቱ ትምህርት መጀመር አይችልም።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ምርጫ ያሸነፉት በኮቪድ-19 የሞቱት ከንቲባ!

(BBC Amaharic , Euronews)

በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱት የሮማኒያው ከንቲባ በቅርቡ የተደረገውን ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ አሸንፈዋል። 64 በመቶ የመራጮችንም ድምፅ ማግኘት ችለዋል።

በደቡባዊቷ ሮማኒያ በምትገኘው ግዛት ዴቬሴሉ ከንቲባ የነበሩት ኢዮን አሊማን ለሶስተኛ ጊዜ ነው ማሸነፍ የቻሉት።

ከሁለት ሳምንታት በፊት በመዲናዋ ቡካሬስት ህይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ከንቲባ ስም ከተመራጮች ዝርዝር ውስጥ ነበር።

የተመራጮች ዝርዝር ቀድሞ በመታተሙ ስማቸው ማስወገድ እንዳልተቻለ ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። በዚህም ምክንያት የሞተ ሰው ከንቲባ ሆኖ እንደተመረጠም ተገልጿል።

ሌላ ምርጫ እንደሚደረግ ባለስልጣናቱ ለሮይተርስ የተናገሩ ሲሆን በርካታ የግዛቲቷ ነዋሪዎች የቀድሞ ከንቲባቸው ቀብርን በመጎብኘት ሃዘናቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የኢዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ18/1/13 አስቸኳይ ስብሰባ አድርጓል ፤ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይና በፓርቲው ወቅታዊ እና ቀጣይ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ተነጋግሮ አቅጣጫ ማስቀመጡን አሳውቋል።

ወቅታዊ የአገሪቷን ሁኔታ በተመለከተ ከእለት ወደ እለት የአገሪቷ ሁለንተናዊ ችግር እየተባባሰ መምጣቱን መገምገሙን የገለፀው ፓርቲው ፣ ይሄ የአገሪቱ ውስብስብ ችግር በተባባሰበት ሁኔታ ወደ ምርጫ ለመግባት መወሰኑ የበለጠ ወደ ባሰ ቀውስ ውስጥ የሚከት ነው ብሏል።

ኢዴፓ ሀገሪቱን ከዚህ ቀውስ ለመታደግ ሁሉን አቀፍ የእርቅ እና የሽግግር መንግስት መመስረት አለበት ብሏል።

ለዚህ እንዲረዳ ሁሉን አቀፍ የውይይት መድረክ እንዲመቻች ፖርቲው ግፊት ማድረጉን እንዲቀጥል አቅጣጫ አስቀምጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#RayaUniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን ቅበላ አቅም ለማሳደግ የማስፋፊያ ግንባታ ከ333 ሚሊዮን ብር በሚልቅ ወጪ እያካሄደ ነው።

የማስፋፊያ ግንባታው በሰባት (7) ህንጻዎች የተካተተ ነው።

የተቋሙ የማስፋፊያ ግንባታ ሲጠናቀቅም ከአራት ሺህ በላይ ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። ይህም አሁን ካሉት 3 ሺህ 300 ተማሪዎች በተጨማሪ ነው - (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ራስ አሉላ አባ ነጋ እና ሰሜን ኢትዮጵያ ፤ የታሪክ አሻራዎቻቸውና ስብዕናቸው !

"ራስ አሉላ አባ ነጋ እና ሰሜን ኢትዮጵያ ፤ የታሪክ አሻራዎቻቸውና ስብዕናቸው (1819 - 1889 ዓ.ም)" የ19ኛው ክፍለ ዘመን የሰሜን ኢትዮጵያ የጀግንነትና የሉዓላዊነት ታሪክ የሚዳስሱ አንደኛና ሁለተኛ መጽሐፍ ተብለው በሁለት ቅፅ የተዘጋጁ መጻሕፍት ለገበያ ቀርበዋል።

እነዚህ መጻሕፍት እያንዳንዳቸው ከ500 በላይ ገፅ ያላቸው ሲሆኑ ብዙ የተደከመባቸው ናቸው። መፅሃፍቱ በB-5 የወረቀት መጠን ቁመትና ወርድ ባላቸው የተዘጋጁ እና የታተሙ መሆናቸው ተገልጾልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ጉባዔዉን በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማዕከል እያካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በጉባዔዉ የክልሎች ፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር የእስልምና ምክር ቤት አመራሮች እና ከኦሮሚያ ዞኖችና ከተሞች የተውጣጡ የእስልምና ሊቃውንት ተወካዮች ተሳታፊ ናቸው።

ለሁለት ቀናት በሚቆየዉ በዚህ ጉባኤ የምክር ቤቱ ያለፈው ዓመት አፈጻጸምና የ2013 እቅድ ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች!

ፌዴራል ፖሊስ ነገ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት በመስቀል አደባባይ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሰልፍ ትርኢት ያካሄዳል፡፡

በዚህ መሰረት፡-

- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ

- ከመገናኛ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ

- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት

- ከቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አገር አስተዳደር መብራት ወይም ኢሚግሬሽን መ/ቤት አካባቢ

- ከተክለሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ

- ከተክለሀይማኖት፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ የኋላ በር

- ከጌጃ ሰፈር፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ

- ከሳሪስ በጎተራ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ

- ከጦር ኃይሎች፣ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ

- ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ፣ ፖሊስ ሆስፒታል፣ ሜክሲኮ፣ ለገሀር መብራት የሚወስደው ለገሃር መብራት

የይለፍ ፈቃድ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል።

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopiaBOT
2024/09/22 20:18:39
Back to Top
HTML Embed Code: