Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#FDREDefenseForce

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት ሌሊት 10:ዐዐ ላይ ጥቃት መፈጸሙን መረጃ የደረሰው ማለዳ 12:00 እንደሆነ በመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ 22ኛ ክፍለ ጦር ለአብመድ አሳውቋል።

የምዕራብ ዕዝ 22ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል ነገሪ ቶሊና ስለጉዳዩ #ለአብመድ (AMMA) ተከታዩን ብለዋል ፦

- ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት ሌሊት 10:ዐዐ ጥቃት መፈጸሙን መረጃ ያገኘነው ማለዳ 12:00 ነው።

- ሠራዊቱ አካባቢውን በመቆጣጠር ጥቃት አድራሾችን የማሰስ እና እርምጃ የመውሰድ ተግባር ፈፅሟል።

- ሽፍቶች በደፈጣ ውጊያ በማድረግ ከሠራዊቱ ለመሰወር ጥረት አድርገዋል ፤ ሠራዊቱ ስምንት (8) ሽፍቶች ላይ እርምጃ ወስዷል።

- የመከላከያ ሠራዊቱ በአካባቢው ተደራጅተው ንጹሐን ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ሽፍቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የተሰጠውን ሕዝባዊ አደራ በቁርጠኝነት ይወጣል።

PHOTO : FDRE Defense Force (FILE)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት ምን ይመስላል ?

#BahirDarUniversity

- የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል የዝግጅት ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል።

- በተለይ የዶርምተሪ ጥገናዎች ተደርገዋል፤ ተማሪዎች በዶርም ውስጥ የሚኖራቸው ቁጥር በመመሪያው መሰረት ከዛም በተሻለ መልኩ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

- የተለያዩ የግብዓት አቅርቦቶችም እየተሟሉ ይገኛል።

- ዩኒቨርሲቲው ካሉት ካምፓሶች ሁለቱ (2) ብቻ በኳራንቲን ማዕከልነት አገልግለዋል ፤ በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የጽዳት ሥራም ይሰራል።

#DireDawaUniversity

- ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ በኳራንቲን ማዕከልነት እያገለገለ ሲሆን በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ወደ ቀድሞ ተግባሩ ለመመለስ እየተሰራ ነው።

- በዶርም ውስጥ የሚገኙ ፍራሾች በአዲስ የሚተኩ ሲሆን የእድሳት ሥራዎችንም በአጭር ግዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል፡፡

- ትምህርትን በሚመለከት ተመራቂ ተማሪዎች እና የአራተኛ አመት ኢንጂነሪንግ ተማሪዎች በተለይ (አፓረንት) የሚወጡ ተማሪዎች ቀድመው ይጠራሉ።

- ተማሪዎች የአንደኛ (1) ሴሚስተር ፋይናል ፈተና ሳይወስዱ ከግቢ በመውጣታቸው ምክንያት ሲመለሱ የማጠናቀቂያ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

- ሆለስቲክ ፈተናም ይሰጣል።

- በተጨማሪም የተግባር ልምምድ (አፓረንት) በተመለከተ ከፈተናው በኃላ የሚወጡ ይሆናል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ቅድመ ዝግጅት በየጊዜው እየጠየቀ እና እየተከታተለ ለተማሪዎች እንዲሁም ለተማሪ ወላጆች ያሳውቃል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
መስከረም 16/2013 ዓ/ም

አጫጭር የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

- በኮሮና ቫይረስ መባባስ ምክንያት የኢንግላንድ እና የዌልስ መጠጥ ቤቶች ከሃሙስ ጀምሮ ደንበኞቻቸው በጊዜ አስተናግደው እየዘጉ ናቸው።

- በስኮትላንድ ትላንት ጀምሮ ከማታ አራት ሰዓት በኃላ ምግብና መጠጥ ቤቶች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

- ፈረንሳይ ውስጥ ካለፈው ሰኔ ወር ወዲህ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ታመው ጽኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ ህሙማን ቁጥር ሃሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ሽህ አልፏል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በህንድ ተጨማሪ 1,093 ሰዎች ሲሞቱ ፤ 85,468 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ብራዚል ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 836 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 32,670 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሚሊዮን እየተጠጋ ነው፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 32,771,253 ደርሰዋል።

- WHO ክትባት በስፋት ከመሰራጨቱ በፊት በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ሁለት ሚሊዮን ሊደርሱ ይችላሉ ብሏል። የድርጅቱ የድንገተኛ ቡድን መሪ ዶ/ር ማይክ ራየን እንዳሉት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ካልተባበረ የሟቾች ቁጥር ሊጨምርም ይችላል።

- ፈለክ የፊት ማስክ ለኮቪድ-19 መከላከያ የሰራቸው የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ (ማስክ) የውጤታማነት የብቃት ማረጋገጫ አግኝቷል።

(VOA, BBC , WORLDOMETERS)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የደመራ በዓል ውስን ሰዎች በተገኙበት ይከበራል!

የመስቀል ደመራ በዓል ዛሬ ሲከበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ደግሞ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ውስን ሰዎች በተገኙበት ይከበራል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ባስተላለፉት 'እንኳን አደረሳችሁ' መልእክት ሁሉም ማህበረሰብ በመስቀል በዓል አከባበር ስነ-ስርዓት ላይ ለኮሮና ቫይረስ አጋላጭ ከሆኑ ድርጊቶች ራሱን እንዲቆጥብ አሳስበዋል።

ዶ/ር ሊያ ታደሰ “በደመራ ቦታዎች ላይ ርቀትን በመጠበቅ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ በመጠቀም ፣ እጅን በሳሙና እና በውሃ በመታጠብና/ ሳኒታይዘር በመጠቀም የበሽታውን ስርጭት የመከላከል ሃላፊነታችንን እንድንወጣ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል - (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የነበረው ምርመራ መጠናቀቁን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ አስታውቋል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና ኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጉዳዩን አስመልክተው በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ም/አቃቤ ህጉ አቶ ፍቃዱ ጸጋ በመግለጫው ተከታዩን ብለዋል ፦

- በ488 የክስ መዝገብ 5 ሺህ 728 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቶባችዋል።

- 3 ሺህ 377 ተከሳሾች በፌደራል መንግስት ስልጣን ስር የሚወድቅ ወንጀል በመፈጸማቸው ተጠያቂነታቸው በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሲሆን፤ 2 ሺህ 351 ተከሳሾች ደግሞ በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ስር ይሆናል።

- በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተከሳሾች በ114 የክስ መዛግብት ክሳቸው ተደራጅቷል።

- በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ደግሞ በ374 የክስ መዛግብት ክሳቸው ተደራጅቷል።

- የክስ መዝገብ ከተከፈተባቸው መካከል 63 ግለሰቦች በሀረር በፈረሱ ሃውልቶች ምክንያት በሽብር ህጉ መሰረት ተጠያቂ የሚሆኑ ናቸው።

- በኦሮሚያ ክልል ከአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኃላ በተከሰተው ሁከት 167 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፣ 360 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፣ ከ4 ቢሊየን 673 መቶ ሚሊየን ብር በላይ የንብረት ጉዳት ማድረሱ በምርመራ ተጣርቷል። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሰኔ 22/2012 ዓ/ም - መስከረም 8/2013 ብቻ እስከ 150 ሰዎች መገደላቸውን 3 ፓርቲዎች አሳውቀዋል!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሱት ፦

- የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ)
- የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ ነፃነትና ንቅናቄ ለሰላም እና ዴሞክራሲ ድርጅት

ከሰኔ 22/2012 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 8/2013 ዓ/ም ድረስ በጉባ፣ ወንበራና ቡለን ወረዳዎች በታጣቂዎች እና በፀጥታ አካላት በተወሰዱ እርምጃዎች እስከ 150 ሰዎች መሞታቸውን ከ50 በላይ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው በጥናት ማረጋገጣቸውን ለ 'አዲስ ማለዳ' ጋዜጣ አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

ትላንት በተደረገ ግምገማ የዳንጉር ወረዳ የሠላም ግንባታና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመከላከያ ሠራዊት የ22ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥና የዞኑ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴር ጀኔራል ነገሪ ቶሊና አስታወቁ።

የፅህፈት ቤት ኃላፊው በቁጥጥር ስር የዋሉት በንገዝ ቀበሌ ጥቃት ሊከሰት ይችላል የሚያስብሉ የተለያዩ ሁኔታዎችን የተመለከተው የቀበሌው ሊቀ-መንበር ለጽህፈት ቤቱ መረጃ ቢያሳውቅም ፣ ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን ችላ በማለቱና ለጸጥታ ኃይሉ በወቅቱ መረጃ አለማድረሱን ተክትሎ ተገቢው ጥንቃቄ ሳይደረግ ጉዳት በመድረሱ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
እንኳን አደረሳችሁ ፤ እንኳን አደረሰን !

በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የይቅርታ ይሆን ዘንድ እንመኛለን !

መልካም በዓል !
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ከ30 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,679 የላብራቶሪ ምርመራ 527 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 166 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 72,700 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,165 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 30,029 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
መስከረም 17/2013 ዓ/ም

የኮቪድ-19 አጫጭር መረጃዎች ፦

- ህንድ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 1,124 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲሞቱ ፤ 89,010 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓት 737 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ ፣ 43,206 ሰዎች በቫይረሱ ስለመያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት ብራዚል ውስጥ 732 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ 25,536 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ ሞት ከተመዘገበባቸው ሀገራት መካከል ሜክሲኮ (405) ፣ አርጀንቲና (335) እንዲሁም ኢራን (172) ይገኙበታል።

- በመላው ዓለም በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 998,745 ፤ በቫይረሱ የተያዙ 33,058,423 እንዲሁም ያገገሙ 24,409,745 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ለኮቪድ-19 የሚሰጠው ትኩረት መቀነስ አሳሳቢ ነው!

(በዶክተር መክብብ ካሳ)

የዓለም ጤና ድርጅት እንደተነበየው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክትባት በስፋት ጥቅም ላይ እስኪውል የሁለት ሚሊየን ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ይችላል፡፡

በሀገራችን የበሽታው አሳሳቢነት ጨመረ እንጂ አልቀነሰም፤ በየቀኑ የበርካታ ዜጎቻችንን ህይወት እየቀጠፈ ነው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የሚከተሉትን አራት መንገዶች ሀገራት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይመክራል፡፡

1. የቫይረሱን ስርጭት ሊያባብሱ የሚችሉ ኘሮግራሞችን መገደብ፡፡
2. በቀላሉ ሊጎዱ ለሚችሉ ዜጎች ትኩረት መስጠት፡፡
3. ማህበረሰብን ስለ ወረርሽኙ ማስተማርና ማንቃት፡፡
4. Test,Treat,Trace (መመርመር፣ የታመሙት ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ፣ እና ንክኪ ያላቸውን መለየትና መመርመር ናቸው፡፡)

የሚደረገው ምርመራ መቀነስ ፣ ንክኪ ያላቸውን ግለሰቦች ለይቶ የመመርመር ስራ መቀነስ ፣ አርአያ መሆን የሚችሉ ታዋቂ ግለሰቦች የመንግስት እና የግል ተቋማት ተወካዮች የሚያሳዩት ቸልተኝነት እና የሚድያው መሰላቸት ተደማምሮ ወረርሽኙን በቀላሉ መቆጣጠር እንዳንችል የብዙዎችንም ልፋት መና እንዲቀር ያደርጋል፡፡

ትንፋሽ አጥሯቸው የሚሰቃዩትን ወገኖቻችንን እናስባቸው ፤ የእኛ ቸልተኝነት ለራሳችንም ለሌሎችም ህይወት ማለፍ ምክንያት ሊሆን ይችላል ፤ ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ 75 የሕክምና ዶክተሮች ጨምሮ 1,732 ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት አስመርቋል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሓላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎዶፋይ በክብር እንግድነት ተገኝተው እንደነበር ከዩኒቨርሲቲው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,631
በበሽታው የተያዙ - 632
ህይወታቸው ያለፈ - 5
ከበሽታው ያገገሙ - 334

መስከረም 17/2013 ዓ/ም
(ዶክተር ሊያ ታደሰ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን አለፈ!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን አልፏል።

በመላው ዓለም በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ከተያዙት 33 ,212 ,069 ሰዎች መካከል የ 1, 000,588 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ጥንቃቄ አይለየን😷

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
መስከረም 18/2013 ዓ/ም

አጫጭር የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

- ባለፉት 24 ሰዓት ህንድ ውስጥ ተጨማሪ የ1,040 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 82,767 ሰዎች በቫይረሱ ስለመያዛቸው ተረጋግጧል።

- ሜክሲኮ በ24 ሰዓት 399 ሰዎችን አጥታለች። በሀገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ አጠቃላይ ሰዎች 76,243 ደርሰዋል።

- ግሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ስደተኛ የኮቪድ-19 ሟች ተመዝግቧል፤ ሟቹ 61 ዓመት ወንድ ሲሆን ከማልካሳ የስደተኞች መጠለያ ነው ፤ ህይወቱ ያለፈው በአቴንስ ሆስፒታል እንደሆነ ተገልጿል።

- አፍሪካ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 1,467,555 ደርሷል፤ ከነዚህ ውስጥ የ35,215 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 1,213,045 ሰዎች አገግሟል።

- የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ በኬንያ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው የሚመለሱበትን ቀን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት ምን ይመስለል ?

#WolitaSodoUniversity

- ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ከንክኪ ዉጪ የሆነ የእጅ መታጠቢያ ተማሪዎች በብዛት በሚገኙበት አከባቢ ለማኖር ተዘጋጅቷል። የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዝር ፣ ሳሙና እና ዉኃ ተደራሽ የማድረግ ሥራም ይሰራል።

- የካፌ ዝግጅትን በተመለከተ ሁለቱም የተማሪዎች መመግቢያ አዳራሾች ጥገና እና በዘመናዊ ማሽን እየተተካ ነዉ፡፡

- ዶርምን በተመለከተ ካራኒታይን የሆኑ መኝታ ቤቶች የዲስ ኢንፌክት ስራ ከዛሬ ጅምሮ ይካሄዳል፡፡ የዶርምና አከባቢም ፅዳት በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

- ከኮሮና ጋር በተያያዘ ጥግግትን ከመቀነስ አንፃር በአንድ ዶርም 3 ተማሪ የመመደብ ስራ ለመስራት ዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

- አካዳሚክ ጉዳዮችን በተመለከተ ሁሉም መምህራን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአካዳሚክ ዘርፉም ልዩ ትኩርት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል።

#AmboUniversity

- አምቦ ዩኒቨርሲቲው ካለው 4 ካምፓሶች አሁን ላይ የሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ (አዋሮ) በካሯንቲን ማዕከልነት እያገለገለ ይገኛል፡፡

- አምቦ ዩኒቨርሲቲ ዝግጅት ከጀመረ የቆየ ሲሆን ግቢዎችን ዲስኢንፌክት የማድረግ ሥራም ይሰራል ተብሏል፡፡

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ቅድመ ዝግጅት በየጊዜው እየጠየቀ እና እየተከታተለ ለተማሪዎች እንዲሁም ለተማሪ ወላጆች ያሳውቃል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/22 22:37:40
Back to Top
HTML Embed Code: