Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ችሎት!

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ የህገ መንግስት እና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ችሎት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የ4 ተከሳሾችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

በዚሁ መዝገብ 5ተኛ ተከሳሽ የሆኑት ጌትነት በቀለ በ30ሺ ብር ዋስ በውጭ ሆነው ክሳቸውን እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የ7 ተከሳሾች የዋስትና መብት ላይ በቀረበው ክርክር ውሳኔ ለመስጠት ክሱ በግልጽ አልቀረበም በሚል አቃቤ ህግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ለዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በፍርድ ቤቱ በታዘዘው መሰረት ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡን ፍ/ቤቱ ማረጋገጡን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#NewsAlert

የካፋ ዞን ም/ቤት አባላት የካፋ ዞን ከዳውሮ፣ ከሸካ ፣ ከቤንች ሸኮ፣ ከምዕራብ ኦሞ ዞኖችና ከኮንታ ልዩ ወረዳ ህዝቦች ጋር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አንድ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ በሙሉ ድምፅ አፀደቁ።

በምክር ቤቱ የተወሰነ ውሳኔም ለኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በፍጥነት እንዲተላለፍ ተወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የካፋ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የዳውሮ ዞን ምክር ቤት ከደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ጋር በአንድ ክልል የመደራጀት ሀሳብን በሙሉ ድምጽ አፀደቀ!

የዳውሮ ዞን ምክር ቤት በ 4ኛ ዙር 7ኛ ሥራ ዘመን 17 መደበኛ ጉባዔው ከደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ጋር በአንድ ክልል የመደራጀት ሀሳብን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

የዳውሮ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ፀሀይ ገሉ ፥ በሚመሰረተው አዲስ ክልል ዋና ከተሞች በክላስተር የሚደራጁ ሲሆን ህዝቡ ፍትህን በቅርበት እንዲያገኝ ይሰራል ብለዋል። (SRTV)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ትምህርት ሚኒስቴር ሁለት የግል ትምህርት ቤቶችን አገደ!

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ተላልፈው የተገኙ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶች ለግዜው እንደታገዱ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እገዳው የተላለፈባቸው ትምህርት ቤቶች አንድነት ኢንተርናሽናል እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ት/ቤት ናቸው፡፡

ትምህርት ቤቶቹ የታገዱት የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው የወላጅ ኮሚቴዎች ተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረባቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ ከዛሬ ጀምሮ መንግስት ያወጣውን መመሪያ ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ፈጥኖ ሪፖርት እስኪያደርጉ ድረስ ምንም አይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰሩ ታግደዋል። (MoE)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

#1 ምዕራብ ኦሞ ዞን

የምዕራብ ኦሞ ዞን በ5 ዙር 5ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ከደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ጋር በአንድ ክልል የመደራጀት ውሳኔ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቆል ፡፡

ዞኑ በቀድሞ የቤንች ማጂ ዞን ለ2 ሳይካፈል ክልል እንዲሆን የወሰነ ቢሆንም አሁን እራሱን ችሎ የወጣ በመሆኑና መንግስት ጥናት በማድረግ የተሻለ ምክረ ሃሳብ ይዞ በመምጣቱ አዲስ ውሳኔ ማሳለፍ አስፈልጓል ተብሏል።

#2 ሸካ ዞን

የሸካ ዞን ምክር ቤት በ4ተኛ ዙር 5ተኛ አመት የሥራ ዘመን 14ተኛ መደበኛ ጉባዓዉ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች በክልል መደራጀትን አስመልክቶ ለሸካ ዞን ምክር ቤት ለውሳኔ መነሻ ሃሳብ ቀርቦ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል።

#3 ቤንች ሸኮ ዞን

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እንዲደራጅ የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 8ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

#4 ኮንታ ልዩ ወረዳ

የኮንታ ልዩ ወረዳ ም/ቤት በጠራው 4ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ለመደራጀት የቀረበውን ማሻሻያ ሞሽን በአባላት ሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

የደቡብ ክልል ፐ/ሰ/ሰ/ሀ/ልማት ቢሮ ኃላፊና የምክር ቤቱ አባል አቶ ተዘራ ወ/ማሪያም ከሀገራዊ ምርጫ በፊት የክልሎች አደረጃጀት አልቆ ለፌዴሬሽን ም/ቤት ቀርቦ በፌደራል በሚደረገው ጉባኤ ስለሚፀድቅ በሌሎቹም አደረጃጀቱ እየፀደቀ ይገኛል ብለዋል።

ምንጭ፦ የምዕራብ ኦሞ ዞን፣ የኮንታ ልዩ ወረዳ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ችሎት!

በዛሬው ዕለት በደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት ቀድሞ የዎላይታ ዞን አመራሮች ዋስትናቸው ታግዶ ዎላይታ ሶዶ ማረሚያ ይቆዩ ሲል ፍርድ ቤት ወስኗል ፤ ፍርድ ቤቱ ለመስከረም 21/1/2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሌላ የችሎት መረጃ ፦

በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ልደቱ አያሌው አቃቤ ህግ ላቀረበባቸው የዋስትና ክልከላ ውሳኔ ለመስጠት ለመስከረም 26 ቀን 2013 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via Hailemichael T Lemma , EDP
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
አትሌት ደጊቱ እና አሰልጣኝ ሀጂ አዴሎ በኮቪድ ተያዙ!

የአይሪሽ ኢንዲፐንደንቱ ጋዜጠኛ ካቴል ዴንሀይ እንደዘገበው ከሆነ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው እና የአትሌቲክስ አሰልጣኙ ሀጂ አዴሎ "የለንደን ማራቶንን" ለመሳትፍ ወደ ለንደን ከማቅናታችው በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው እና ውድድሩን እንደማይሳተፉ ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቀነኒሳ በቀለና ሌሎች አትሌቶች የጤና ሁኔታ በምን ደረጃ ይገኛል ?

ከቀናት በኋላ በመጪው ዕሁድ ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን ታላለቅ አትሌቶች በተገኙበት ይካሄዳል ።

ከሰዓታት በፊት በዓለም አቀፍ ሚዲያ የወጣውን መረጃ ተመርኩዘን በለንደን የከተሙት አትሌቶቻችን ጤንነት ሁኔታ በተመለከተ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታማኝ የውስጥ ምንጭ ለማጣራት ሞክረናል።

አትሌት ደጊቱ አዝመራው እና የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ ከቀናት በፊት በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጦልናል ።

በለንደን የከተሙት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣ ሞስነት ገረመው እንዲሁም ሌሎች አትሌቶቻችን በሙሉ ጤንነት ላይ ሲገኙ ልምምዳቸውን በመስራት ላይ እንደሚገኙ ቲክቫህ ስፖርት ለማረጋገጥ ችሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethsport
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
መስከረም 19/2013 ዓ/ም

የኮቪድ-19 መረጃዎች፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 63 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 207 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 17 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 5,25 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 24 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል (ከወልዲያ ሆስፒታል)

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 138 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 21 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል (17ቱ ከሀዋሳ ከተማ ናቸው)

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 189 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 92 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 505 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 46 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል (ከመቐለ ህክምና ማዕከል)

#DireDawa

በድሬዳዋ 237 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 76 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 481 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 84 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#Gambella

በጋምቤላ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 451 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 24 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBOT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ባለፉት 24 ሰዓት የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 640 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,284 የላብራቶሪ ምርመራ 640 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 199 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 74,584 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,191 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 30,952 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በዛሬው ዕለት 264 ሴቶች እና 35 ህፃናት ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።

@TIKVAHETHIOPIABOT @TIKVAHETHIOPIA
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

- የሸካ ዞን ምክር ቤት
- የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት
- የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት
- የካፋ ዞን ምክር ቤት
- የዳውሮ ዞን ምክር ቤት
- የኮንታ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 1 ክልል ሆነው ለመደራጀት በየምክር ቤቶቻቸው አፅድቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
"በመልካም ጤንነት ላይ እገኛለሁ" - አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ

በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተገለፀው የአትሌቲክስ አሰልጣኙ ሀጂ አዲሎ ከቲኪቫህ ስፖርት (@tikvahethsport) ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ፥ ያለፉትን ስምንት (8) ቀናት ራሳቸውን አግልለው በመኖሪያ ቤታቸው እንደሚገኙና አሁን በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሆኑ አሳውቀውናል።

@TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHSPORT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#DrTsionFirew

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማብቃት ፥ የኮሮና ቫይረስ ማብቃት ማለት አይደለም። ይልቁንም ማስክ በማድረግ ፥ ርቀታችንን በመጠበቅ እና እጃችንን በመታጠብ ፥ የገጠመንን ተግዳሮት ለመሻገር ራሳችንን በበለጠ እንድንጠብቅ የሚያደርግ ነው።

ከበአላት እና ፌሽታ ጋር ተያይዞ ፥ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሊጨምር እንደሚችል ግልጽ ነው። ይሄ ግዴለሽነት ለጤና ባለሙያዎችን የሚያሳዝን ተግባር ነው!

ቫይረሱ መልከ-ብዙ ነው። ምን ጥሎ ምን አንስቶ እንደሚሄድ ገና አልታወቀምና ራሳችሁን ጠብቁ።

የጤና ባለሙያዎችን ልፋት ፥ የእናት የአባት ጸሎትንም ዋጋ አታሳጡ። እባካችሁ!

ዶክተር ፅዮን ፍሬው
መስከረም 19/2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በ91 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ፕሮፌሰሩ ህይወታቸው ያለፈው ትላንት ምሽት 5 ሰዓት አካባቢ እንደሆነ ቤተሰቦቸው እና የቀርብ ሰዎቻቸው ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን በኮሮና በሽታ ተይዘው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ሆስፒታል ላለፉት 11 ቀናት ህክምናቸውን ሲከታተሉ እንደነበር ልጃቸው መቅደስ መስፍን ተናግረዋል።

እስከ ትላንት ድረስ ከአባታቸው ጋር መነጋገራቸውን የገለጹት መቅደስ መስፍን እስካለፈው ቅዳሜ ድረስ በደህና ሁኔታ ላይ እንደነበሩ አስረድተዋል።

የፕሮፌሰር መስፍን የቀብር ስነ ስርዓት መቼ እንደሚከናወን ገና እንዳልተወሰነ የገለጹት ልጃቸው እርሳቸውን ጨምሮ በውጭ ሀገር የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ወደ ሀገር ቤት ከመጡ በኋላ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚፈጸም ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገፅ ጠቁመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም (1922 -2013)

- ከዛሬ 91 ዓመት በፊት አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፣

- የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እትጌ መነን ተምረዋል፣

- ከ1955 ዓ.ም ጀምሮ በለንደንና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርት ተከታትለዋል፣

- በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ውስጥ በጂኦግራፊ ዲፓርትመንት በመምህርነት ና በትምህርት ክፍሉ ኃላፊነት አገልግለዋል፣

- በጊምቢ አውራጃ አስተዳዳሪነት ሰርተዋል።

- በተለያየ ርዕሰ ጉዳዮች በርካታ መጽሀፍትን አሳትመዋል፣

- ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት አንስቶ መንግስትን በመተቸትና ሂስ በመስጠት የሚታወቁ አንጋፋ የፖለቲካ ሰው ነበሩ ፣

- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) መስራችና ሊቀመንበር ነበሩ፣

- ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲን ከመሰረቱት ሰዎች አንዱ ናቸው፣

- በአደባባይ ምሁርነታቸው፣ በፖለቲካ ተሳትፏቸው፣ በበርካታ ጹሑፎቻቸው፣ በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነታቸው ይታወቃሉ፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/22 22:28:58
Back to Top
HTML Embed Code: