Telegram Web Link
Audio
በብዛት እየተመረቁ የሚወጡት ወጣት ሀኪሞች ሥራ ማግኘት አልቻሉም!

(የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

ከፍተኛ የሀኪሞች እጥረት ካለባቸው ሀገራት አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ የህክምና ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሀኪሞች ተመርቀው ሥራ ማግኘት እንዳልቻሉና አንዳንዶቹም ተስፋ ቆርጠው ሥራ ለመቀየር መገደዳቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው የ2012 ዓ/ም ተመራቂ ሀኪሞች ሥራ በማጣታቸው ለከፍተኛ የኢኮኖሚና ስነ-ልቦና ችግር እንደተጋለጡም ተናግረዋል።

ጤና ሚኒስቴር ችግሩ የተፈጠረው በበጀት አቅም ማነስ ምክንያት ክልሎች ተፈላጊውን የህክምና ባለሙያ መቅጠር ባለመቻላቸው ነው ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
እስካሁን ምን ያህል ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ ?

እስካሁን ድረስ በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ 964 ዜጎቻቸውን ወደ ሀገራቸው እንደሚለሱ መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት 964 ዜጎች መካከል 58 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከሕዳር 1-4 ባለው ጊዜ ውስጥ ይሰጣል!

የ2012 የሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና በኮሮና በሽታ ምክንያት መራዘሙን ተከትሎ ፈተናውን በ2013 ለመስጠት የፍትሕ እና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢኒስትቲውት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ከሕዳር 1-4 ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የወገን ለወገን የቶምቦላ ሎቶሪ ዕጣ ወጥቷል!

የወገን ለወገን የቶምቦላ ሎቶሪ ዕጣ በትላንትናው ዕለት በብሔራዊ ሎቶሪ አዳራሽ ወጥቷል። 

ቶምቦላ ሎተሪው በ2010 ዓ.ም በፀጥታ ችግር ምክንያት ከሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም በኦሮሚያ ልማት ማህበር የተዘጋጀ ነው።

በግንቦት 2010 ዓ.ም ይፋ የተደረገውን ሎተሪ በስድስት (6) ወራት ሸጦ ለማጠናቀቅ ነበር የታሰበው።

ያም ሆኖ ከሁለት ዓመታት በላይ ዘግይቶ ትላንት መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም መውጣት ችሏል።

ተጨማሪ መረጃ ፦

- ሎቶሪው ጊዜዉን ጠብቆ የልወጣው በአገሪቷ የነበረው የፖለቲካ ሁኔታ ነው።

- ከተሰራጨው 39 ሚሊዮን የሎተሪ ትኬት የተሸጠው 12 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሲሆን ይህም 30 በመቶው ነው።

- 12 ሚሊዮን 79 ሺህ 331 ሎተሪ ተሸጦ 241 ሚሊዮን 586 ሺህ 620 ብር ገቢ ተገኝቷል።

- በሎቶሪው ዕጣ 447 ሰዎች ዕድለኞች ሆነዋል።

- ከወጡት ዕጣዎች መካከል በአይነት የመኖሪያ ቤት፣ ገልባጭ ሲኖትራክ፣ ሚኒባስ፣ ባለሶስት እግር ተሸከርካሪ ባጃጅ፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ፎን የሞባይል ስልክና ፍሪጅ ይገኙበታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ማስታወሻ !

አዲሱን የገንዘብ ኖት የመቀየሪያ ጊዜ ሊያበቃ ፦

- ከ100 ሺህ ብር በታች ለሆነ 74 ቀን ቀርቶታል።

- ከ100 ሺህ ብር በላይ ለሆነ 14 ቀን ቀርቶታል።

Via Hibret Bank
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#Irreecha2013

በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለ በኢሬቻ በዓል ወቅት መደረግ ስለባቸው ጥንቃቄዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

ዶ/ር መንግስቱ በመግለጫቸው ተከታዩን ብለዋል ፦

- የኮቪድ 19- ወረርሽኝ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጊዜ በላይ እየተስፋፋ በመሆኑ የሆረ ፊንፊኔም ሆነ የሆረ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ ሰዎች በጥንቃቄ በዓሉን ሊያከብሩ ይገባል።

- በኢሬቻ በዓል የሚሳተፉ ሰዎች አካላዊ ርቀትን ሊጠብቁ እንዲሁም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሊያደርጉ ይገባቸዋል።

- በበዓሉ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጤና ችግሮች ለመከላከል ቢሮው 7 ኮሚቴዎችን አዋቅሮ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል።

- በበዓሉ ወቅት ከጤና ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ችግር እርዳታ ማግኘት የፈለገ ሰው በነፃ 6955 ላይ ደውሎ መረጃ ማግኘት ይችላል። (etv)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
መስከረም 20/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 132 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 243 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 78 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 591 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 40 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።


#DireDawa

በድሬዳዋ 194 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 84 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 182 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 24 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 347 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 26 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ የ1 ሰው ህይወት አልፏል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 287 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 5 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 645 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 109 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 2,926 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 385 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBOT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,139 የላብራቶሪ ምርመራ 784 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 199 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 75,368 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,198 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 31,204 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ጥቆማ!

EBS ቴሌቪዥን እና አፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን የፍሬክዌንሲ ለውጥ አድርገዋል!

ኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዥን ባጋጠመው ቴክኒካል ችግር ምክንያት በአዲስ የሳተላይት ፍሪክዌንሲ እንደተመለሰ አሳውቋል።

ናይልሳት 10971 H (ሆሪዞንታል) SR 27500 ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ ላቅ ባለ HD እና SD ጥራት ደግሞ : በኢትዮ ሳት NSS 12 H (ፍሪክዌንሲ) 11105 SR 45000 ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ።

ለማስተካከል የዲሽ ቴክኒሻኖችን ያነጋገሩ።

በሌላ በኩል ፦

የአፍሪ ሄልዝ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሳተላይት ፍሪክዌንሲ ለውጥ አድርጓል።

በውጡ መሰረት አዲሱ የሳተላይት መገኛው FREQUENCY 11555 , SR-27500 VERTICAL መሆኑን የጣቢያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር ካሣ አያሌው ካሣ ነግረውናል።

የአድራሻ ለውጡ ከዛሬ መስከረም 21/2013 ዓ/ም ጀምሮ ስርጭት ይጀምራል። የጣቢያው ተከታታዮች በዚሁ አዲስ አድራሻው እነዲያገኙት ጣቢያው ጥሪ አቀቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
“ለክብራቸው በሚመጥን መልኩ ይሸኛሉ” - ኮሚቴው

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የቀብር ስነ ስርዓትን ለማስፈፀም ኮሚቴ ተዋቅሮ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ቪኦኤ ዘግቧል።

የቀብር ስነ ስርዓታቸው ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ እንዲከናወን ዝግጅት ተጀምሯል።

ውጭ ሀገር ያሉት 2ቱ ልጆቻቸው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት በያዝነው ሳምንት መጨረሻ እንደሆነ ስለሚጠበቅ ሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያዎቹ ላይ የቀብር ስነ ስርዓታቸው ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

ትክክለኛ ቀኑን እንዲሁም ሰዓቱን ፣ የቀብር ስነ ስርዓታቸው የት እንደሚፈፀም በተመለከተ የቀብር ስነ ስርዓቱን ለማስፈፀም ኃላፊነት የወሰደው ኮሚቴ ለህዝብ እና ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ያደርጋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#Irreecha2013

የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በሆራ ፊንፊኔ እና በሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚገኙ ሰዎች መለየታቸውን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግረዋል።

በእያንዳንዱ ቀን በሚከበረው በዓል ላይ የሚታደመው የሰው ቁጥር ከ5,000 እስከ 6,000 ይደርሳል ተብሏል።

አቶ ጌታቸው የኢሬቻ በዓል ለኮሮና ቫይረስ በማያጋልጥ መልኩ እንደሚከበርም ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።

የፀጥታ ጥበቃውን አስተማማኝ ለማድረግ የክልሉ የፀጥታ አካላት ከአዲስ አበባ እና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ፤ የክልሉ ፀጥታ ጥበቃ በሁሉም ዞኖች እና ከተሞች እየተካሄደ መሆኑን አቶ ጌታቸው አስታውቀዋል።

የኢሬቻ በዓል አከባበርን ወደ ፖለቲካ አጀንዳ ለመቀየር እና በኦሮሚያ ክልል አለመረጋጋት ለመፍጠር የሚያስቡ ወገኖች አሉ ያሉት አቶ ጌታቸው የፀጥታ አካላት በተቀናጀ መንገድ እየሰሩ ስለሆነ የሚያሰጋ ነገር አይኖርም ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ችሎት!

የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን ጨምሮ ለ20 ተጠርጣሪዎች የስር ፍርድ ቤት በፈቀደው ዋስትና ላይ እና ፖሊስ በጠየቀው የምርመራ ቀናት ላይ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 27/2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ በነበረው ችሎት በዋስትናው ጉዳይ እና ተጠርጣሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጹሁፍ ያቀረበውን የመልስ መልስ ተቀብሏል።

ዛሬ በነበረው ችሎት ማናቸውም ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን የ6ቱ ጠበቃ ተመስገን ዋጃና ተናግረዋል።

በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ከተደረጉ 15 ተጠርጣሪዎች ውስጥ አስራ 2ቱ በዛሬው ችሎት የተወከሉት፤ በ3 ጠበቆች መሆኑንም ገልጸዋል። ቀሪዎቹ 3 ተጠርጣሪዎች በራሳቸው የሚከራከሩ ናቸው ብለዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ማክሰኞ በነበረው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት፤ ተጨማሪ 8 ተጠርጣሪዎች በሶዶ ማረሚያ ቤት በእስር እንዲቆዩ መደረጋቸው ይታወሳል።

በማክሰኞው የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ወደ ሶዶ ከተማ ማረሚያ ቤት ከተወሰዱ ተጠርጣሪዎች ውስጥ የቀድሞው የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እና የዞኑ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥበቡ ዩሃንስ ይገኙበታል።

Via Ethiopia Insider
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ችሎት!

አቶ ጃዋር መሃመድ እና 24 ሰዎች ላይ የተመሰረተውን ክስ በዛሬው እለት መሰማት #BBC (ቢቢሲ) ዘግቧል።

ክሳቸው እየተሰማ ያለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ፤ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ ሐምዛ አዳነ ፣ ሸምሰዲን ጠሃ ፍርድ ቤት የተገኙት የማረሚያ ቤቱን ቢጫ ደንብ ልብስ ለብሰው ነው።

ከዚህም በተጨማሪ የሃጫሉ ምስል ያለበት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አድርገው ታይተዋል።

ተከሳሾቹ ለ2 በሰንሰለት ታስረው ችሎት ላይ የቀረቡ ሲሆን አቃቤ ሕጎች ወደ ችሎቱ ሲገቡ እጃቸውን ከፍ አድርገው እንደታሰሩ አሳይተዋል።

በመቀጠልም አቃቤ ሕግ ሰንሰለቱ ከእጃቸው ላይ እንዲፈታ በማዘዙ ተፈትቶላቸዋል። ከዚህ በፊት ሌላ ክስ ስላለባቸው መገኘት ያልቻሉት የኦፌኮ አባሉ አቶ ደጀኔ ጣፋ በዛሬው ዕለት ተገኝተዋል።

ችሎቱ መታየት የጀመረው በፍትሕ አዳራሽ ሲሆን በአዳራሾቹ የተከሳሽ ቤተሰቦችን ጨምሮ ሃያ (20) ሰዎች ተገኝተዋል።

MORE : https://telegra.ph/JM-10-01

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ሹመት!

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አዲስ ዳይሬክተር ሾሟል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር በነበሩት ዶ/ር ሰለሞን በላይ ምትክ አቶ አብዲሳ ይልማ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

ዶክተርር ይሹሩን አለማየሁን ደግሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ላይ ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ እና የተከሳሾችን የክስ መቃወሚያ ምላሽ ለመመልከት ፍርድ ቤቱ ለህዳር 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተገነቡት መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የወጣላቸው 52,229 የዕጣ ዕድለኞች ዛሬ ቁልፍ እንደሚረከቡ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በተጨማሪ 22,915 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችም እንዲሁ ቁልፍ እንደሚረከቡ ከሬድዮ ጣቢያው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የአ/አ ከተማ አስተዳደር የገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ሲያስረክብ ይህ 13ኛው ዙር ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአዲሰ አበባ ማዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ የቁልፍ ፣ የካርታ እንዲሁም የውል ርክክብ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት እይተካሄደ ይገኛል።

#ShegerFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ተማሪዎችን እንዲጠራ ፍቃድ ያገኘ ዩኒቨርሲቲ አለ ?

እስከ አሁን ድረስ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲዎችን ዝግጅት ገምግሞ ተማሪዎችን እንዲጠራ ፍቃድ ሰጠው ተቋም እንደሌለ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ደቻሳ ጉሩሙ አሳውቀውናል።

ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት የሚያረጋግጠውና የሚገመግመው ግብረ ኃይል በተለያየ አቅጣጫዎች ተንቀሳቅሶ እየተደረገ ስለሚገኘው ዝግጅት ከዛሬ ጀምሮ መመልከት መጀመሩንና በአጭር ጊዜ ስራው እንደሚጠናቀቅ የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ገልፀውልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ከነገ ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች!

ለኢሬቻ በዓል ከዋዜማው ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች እና ለእግረኞች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት ነገ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ የሚዘጉት መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፦

- ከቦሌ አየር መንገድ ፣በሚሌኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደምበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ፤

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ማዘጋጃ ጋራዥ ወይም ጋዜቦ አደባባይ፤

- ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድኃኔዓለም ፣በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ፤

- ከፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ፤

- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት ላይ፤

- እንዲሁም ከሳሪስ ፣በጎተራ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ፤

- ከካዛንቺስ በቤተ መንግስት ፍል ውሃ የሚወስደው መንገድ ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ፣ ከዑራኤልና አዋሬ የሚመጡ መንገዶች ካዛንቺስ ቶታል ላይ፤

- በተጨማሪም ከካዛንቺስ ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ግቢ ገብርኤል መስቀለኛው ላይ፤

- ከተክለሃይማኖት፣በሚቲዎሮሎጂ፣ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሚቲዎሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤

- ከተክለሃይማኖት፣በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ የኋላ በር መስቀለኛው ላይ፤

- ከጌጃ ሰፈር፣ጤና ጥበቃ፣ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ የትራፊክ መብራት፤

- ከቄራ ወደ ቂርቆስ የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ፤

- ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ፣ከፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ ያለው መንገድ፤

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopiaBOT
2024/09/22 20:34:04
Back to Top
HTML Embed Code: