Telegram Web Link
ኤሲ ሚላን ለፍፃሜ ደርሰዋል !

የጣልያን ሱፐር ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ሲካሄድ ኤሲ ሚላን ለፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

በአሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ የሚመራው ኤሲ ሚላን ከጁቬንቱስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።

የኤሲ ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ክርስቲያን ፑልሲች እና ጋቲ በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥሩ ለጁቬንቱስ ይልዲዝ ከመረብ አሳርፏል።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ የኤሲ ሚላን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በአሸናፊነት መወጣት ችለዋል።

ኤሲ ሚላን በፍፃሜው የፊታችን ሰኞ ምሽት 4:00 ኢንተር ሚላንን የሚገጥሙ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ የሊጉን መሪነት ተረከበ !

በስፔን ላሊጋ ተስተካካይ መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከቫሌንሽያ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ተረክበዋል።

የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ሉካ ሞድሪች እና ጁድ ቤሊንግሀም ከመረብ ሲያሳርፉ ለቫሌንሽያ ሁጎ ዱሮ አስቆጥሯል።

በጨዋታው ብራዚላዊው የሎስ ብላንኮዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ቪኒሰስ ጁኒየር ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

ሪያል ማድሪድ ሲመራ ቢቆይም በመጨረሻ ደቂቃዎች ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ጣፋጭ ሶስት ነጥብ ማሳካት ችሏል።

የደረጃ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ሪያል ማድሪድ - 43 ነጥብ
1️⃣9️⃣ ቫሌንሽያ   -  12 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ?

ቅዳሜ - ሲቪያ ከ ቫሌንሽያ

እሁድ - ሪያል ማድሪድ ከ ከ ላስ ፓልማስ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ይቅናዎት!
ኦዶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ተደርገዋል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
ታላቅ የገና ስጦታ እስከ ጥር 4 የሚቆይ ቅናሽ

Exchange Available (ባሎት PlayStation ላይ  ጨምረው መቀየር ይችላሉ)

PLAYSTATION 4 Slim jealbreak Version

2 Orginal jestic
5 game installed (FIFA25,PES24...)
500gb Storage
Version jealbreak
Full accessories
1 years waranty

Price=44,000

አድራሻ፦
ቁጥር 1  መገናኛ ሱቅ የአድራሻ ለውጥ በቅርቡ ስለምናደርግ ከመምጣቶ በፊት አስቀድመው ይደውሉ
   
ቁጥር 2   ቦሌ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ  ምድር ላይ


ስልክ፦ 0910529770 ወይም                  0977349492
0914646972  ይደውሉ
Telegram channel ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

9:00 ባሕር ዳር ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ

9:30 ቶተንሀም ከ ኒውካስል ዩናይትድ

12:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

12:00 በርንማውዝ ከ ኤቨርተን

12:00 አስቶን ቪላ ከ ሌስተር ሲቲ

12:00 ክሪስታል ፓላስ ከ ቼልሲ

12:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ዌስትሀም ዩናይትድ

2:00 ፊዮሬንቲና ከ ናፖሊ

2:30 ብራይተን ከ አርሰናል

3:00 ባርባስትሮ ከ ባርሴሎና

🔴 የዛሬው የይግምቱ ሽልማቶቻችን የቼልሲ ፣ ማንችስተር ሲቲ ፣ አርሰናል እና ባርሴሎና ጨዋታዎች ናቸው።

🔴 የዛሬ ሽልማታችን 10:30 ፣ 11:00 ፣ 1:00 ፣ 2:00 ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርሱ ይሆናል።

🔴 መገመት የሚቻለው በተጠቀሰው ሰዓት ላይ ብቻ ነው።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ለቀይ ካርዱ ይግባኝ እንጠይቃለን “ አንቾሎቲ

የሪያል ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ቪኒሰስ ጁኒየር ትላንት ምሽት የተመለከተው ቀይ ካርድ እንደማይገባው ገልጸዋል።

በጨዋታው ቪኒሰስ ጁኒየር የቫሌንሽያውን ግብ ጠባቂ መቶቷል በሚል በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቶ ነበር።

" ቀይ ካርድ አልነበርም " ያሉት ካርሎ አንቾሎቲ ለሁለቱም ቢጫ ካርድ መሰጠት ነበረበት ሲሉ የቫሌንሽያው ግብ ጠባቂ ዲምትሬቭስኪም ጥፋተኛ ነው ብለዋል።

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ አክለውም ሪያል ማድሪድ በቀጣይ በቀይ ካርዱ ጉዳይ ይግባኝ እንደሚጠይቅ አረጋግጠዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ከመሪው ይልቅ ለወራጅ ቀጣናው ቅርብ ነን “ አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድናቸው ያለበትን የመውረድ ስጋት ተጨዋቾቹ መረዳት አለባቸው በማለት ተናግረዋል።

“ ደረጃውን ከተመለከትነው ከሊጉ መሪ ይልቅ ከወራጅ ቀጠናው ክለቦች ቅርብ ነን “ ያሉት ሩበን አሞሪም “ከሊጉ የመውረድ ስጋት አለብን “ ሲሉ አስረድተዋል።

“ አሰልጣኙ አክለውም “ አሁን ላይ ስለዚህ ነገር እያሰብኩ አይደለም ፤ ፍላጎቴ ቀጣዩን ጨዋታ ማሸነፍ ነው ነገርግን ከደጋፊው በተለይ ከተጫዋቾቹ ጋር ግልጽ መሆን አስፈላጊ ነው።“ ብለዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ራሽፎርድ እና ጋርናቾ ለምን ከጨዋታው ውጪ ሆኑ ? ማንችስተር ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በሚያደርገው ተጠባቂ ጨዋታ የማርከስ ራሽፎርድ እና አሌሀንድሮ ጋርናቾን ግልጋሎት አያገኝም። ሁለቱ ተጨዋቾች በተጠባቂው የማንችስተር ደርቢ ጨዋታ ተጠባባቂ ሆነውም #አይጀምሩም። ተጨዋቾቹ ከጨዋታው ውጪ የሆኑት በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ውሳኔ መሆኑ ተገልጿል። ማርከስ ራሽፎርድ እና አሌሀንድሮ ጋርናቾ ጉዳት…
ጋርናቾ ለምን ከሲቲ ጨዋታ ውጪ ሆነ ?

አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ ማንችስተር ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲን ባሸነፈበት ጨዋታ ከቡድኑ ስብስብ ውጪ እንደነበር ይታወሳል።

በወቅቱ አሌሀንድሮ ጋርናቾን ጨምሮ ማርከስ ራሽፎርድ በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ውሳኔ ከጨዋታው ውጪ መሆናቸው ተገልጾ ነበር።

ሩበን አሞሪም ጋርናቾን ከስብስቡ ውጪ ያደረጉት በዩሮፓ ሊግ መርሐግብር ወቅት ትዕዛዝ ሲሰጡት ጀርባውን በመስጠቱ ምክንያት እንደሆነ ዴይሊ ሜል ዘግቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ ቪክቶሪያ ፕሌዘንን ባሸነፈበት ጨዋታ አሌሀንድሮ ጋርናቾ ለአሰልጣኙ ጀርባውን መስጠቱ እና ትዕዛዝ ሲሰጡት ትቷቸው መሄዱ ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ዳኒ ኦልሞ ከምሽቱ ጨዋታ ውጪ ሆነ !

ስፔናዊው አማካይ ዳኒ ኦልሞ ባርሴሎና ዛሬ ምሽት ከባርባስትሮ ጋር ከሚያደርገው የኮፓ ዴላሬ ጨዋታ ውጪ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

ተጨዋቹ ከፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ጋር በተያያዘ በባርሴሎና የተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ አለመቻሉን ተከትሎ በጨዋታው መሳተፍ እንደማይችል ተነግሯል።

ባርሴሎና ዳኒ ኦልሞን ለቀሪው የውድድር አመት ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

በተጨማሪም ሌላኛው ተጨዋች ፓው ቪክቶር በተመሳሳይ ምክትል ከዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ አጥቂ አንፈልግም ማርክ ጉዩ አለን “ ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የፊት መስመር አጥቂ ከማስፈረም ይልቅ ለማርክ ጉዩ እድል መስጠት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

ቼልሲ በጥር አጥቂ ስለ ማስፈረም ያስብ እንደሆነ ጥያቄ የቀረበላቸው ማሬስካ “ በኮንፈረንስ ሊግ ምርጥ ብቃት ያሳየው ማርክ ጉዩ አለን “ ሲሉ መልሰዋል።

“ በፕርሚየር ሊጉ ራሱን እንዲያሳይ እድል አልሰጠሁትም “ ያሉት አሰልጣኙ በቅርቡ ለእሱ በቂ እድል መስጠት እንጀምራለን ብለዋል።

ኢንዞ ማሬስካ አያይዘውም “ አሁን ባለንበት ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ ብሎ የጠበቀ አልነበረም እኔ ግን ደጋግሜ ተናግሬ ነበር “ ሲሉ የቡድኑ አቋም መውረድ የጠበቁት እንደነበር ገልጸዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT (Wanaw Sportswear)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ቶተንሀም ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የቼክ ሪፐብሊኩ ክለብ ስላቪያ ፕራውን ግብ ጠባቂ አንቶኒን ኪንስኪ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ቶተንሀም ግብ ጠባቂውን በ 15 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም መቃረቡ ተነግሯል።

የ 21ዓመቱ ግብ ጠባቂ አንቶኒን ኪንስኪ በአሁን ሰዓት የህክምና ምርመራውን ለማጠናቀቅ ለንደን እንደሚገኝ ተገልጿል።

ግብ ጠባቂው በዘንድሮው የውድድር ዘመን በስፓርታ ፕራ ባደረጋቸው 1️⃣9️⃣ ጨዋታዎች በ 1️⃣2️⃣ቱ ምንም ግብ ሳይቆጠርበት መውጣት ችሏል።

በአመቱ ሰባት ግቦች ብቻ እንደተቆጠሩበት የተነገረው አንቶኒን ኪንስኪ የተሞከረበትን ሙሉ የአየር ላይ ኳሶች መመለስ እንደቻለ ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
5 '

ቶተንሀም 1-0 ኒውካስል ዩናይትድ

ሶላንኬ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
6 '

ቶተንሀም 1-1 ኒውካስል ዩናይትድ

ሶላንኬ ጎርደን

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሜሲ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሽልማት ሊሰጠው ነው !

አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ከነጩ ቤተ-መንግሥት ሽልማት ሊበርከትለት መሆኑ ተገልጿል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሊዮኔል ሜሲ የ “ Presidential Medal of Freedom “ ሽልማት እንደሚያበረክቱ ተነግሯል።

ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ ትልቁ የግለሰቦች ሽልማት ተደርጎ የሚወሰደውን ክብር ሊዮኔል ሜሲን ጨምሮ ለ 19 ግለሰቦች በነጩ ቤተመንግሥት ያበረክታሉ ተብሏል።

ሽልማቱ የሚበረከተው በአሜሪካ በማህበረሰቡ ውስጥ አርኣያ በመሆን አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦች የሚሰጥ መሆኑ ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
42 '

ቶተንሀም 1-2 ኒውካስል ዩናይትድ

ሶላንኬ       ጎርደን
አይሳክ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
እረፍት

ቶተንሀም 1-2 ኒውካስል ዩናይትድ

ሶላንኬ       ጎርደን
                        አይሳክ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የቼልሲ እና ክሪስታል ፓላስን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 12:00 ሰዓት ብቻ ነው።

🔴 ይነበብ

አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
ባርሴሎና ለስፔን መንግሥት ቅሬታ ሊያቀርብ ነው !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዳኒ ኦልሞ እና ፓው ቪክቶርን ለማስመዝገብ ለመጨረሻ ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ መቅረቱ ተገልጿል።

የስፔን ላሊጋ እና የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን በጋራ ባወጡት ይፋዊ መግለጫ ባርሴሎና ተጨዋቾቹን በድጋሜ ለማስመዝገብ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገነዋል ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ ባርሴሎና ጉዳዩን ወደ ስፔን መንግሥት በመውሰድ ቅሬታ ለማቅረብ ማሰባቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

ባርሴሎናዎች ለስፔን መንግሥት ቅሬታ በማቅረብ የመጨረሻ ሙከራቸውን ለማድረግ ማቀዳቸው ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
2025/01/10 12:57:19
Back to Top
HTML Embed Code: