Telegram Web Link
65 ' አርሰናል 4-1 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ             ኮሊንስ
        ንዋኔሪ
ስተርሊንግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TikvahGoal

የጨዋታዎቹን አጫጭር ቪዲዮች እና ጎሎች በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
78 ' አርሰናል 5-1 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ             ኮሊንስ
        ንዋኔሪ
         ስተርሊንግ
ሀቨርትዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
68 ' ማንችስተር ዩናይትድ 1-1 ትዌንቴ

ኤሪክሰን ላመርስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
75 '

ሊቨርፑል 3-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ጆታ             ኳንሳህ ( በራስ ላይ )
ሳላህ

ማንችስተር ዩናይትድ 1-1 ትዌንቴ

        ኤሪክሰን            ላመርስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከቦልተን ጋር ያደረገውን የካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ቀጣዩን ዙሩ ተቀላቅሏል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግብ ንዋኔሪ 2x ፣ ዴክላን ራይስ ፣ ራሂም ስተርሊንግ እና ካይ ሀቨርትዝ ማስቆጠር ችለዋል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ራሂም ስተርሊንግ ለአርሰናል በቋሚነት ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ አንድ ግብ አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ አቀብሏል።

አርሰናል የካራባኦ ካፕ አራተኛ ዙር ተጋጣሚውን ከደቂቃዎች በኋላ በሚወጣ እጣ የሚያውቅ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 '

ሊቨርፑል 4-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ጆታ             ኳንሳህ ( በራስ ላይ )
ሳላህ
ጋክፖ

ማንችስተር ዩናይትድ 1-1 ትዌንቴ

        ኤሪክሰን            ላመርስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ነጥብ ተጋርቷል !

የዩሮፓ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከኔዘርላንዱ ክለብ ትዌንቴ ጋር ያደረገው ማንችስተር ዩናይትድ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።

የማንችስተር ዩናይትድን ግብ ክርስቲያን ኤሪክሰን ሲያስቆጥር ለትዌንቴ ላማርስ ከመረብ አሳርፏል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች የዩሮፓ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ ከፖርቶ ጋር በሚቀጥለው ሳምንት ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከዌስትሀም ጋር ያደረገውን የካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ቀጣዩን ዙሩ ተቀላቅሏል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግብ ዲያጎ ጆታ 2x ፣ ጋክፖ 2x እና መሐመድ ሳላህ ማስቆጠር ሲችሉ ለዌስትሀም ኳንሳህ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

ሊቨርፑል የካራባኦ ካፕ አራተኛ ዙር ተጋጣሚውን ከደቂቃዎች በኋላ በሚወጣ እጣ የሚያውቅ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የስፔን ላሊጋ የሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብሩን ከሄታፌ ጋር አድርጎ 1ለ0 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግብ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ አስቆጥሯል።

ባርሴሎና በመጀመሪያ ሰባት የሊግ ጨዋታዎች በተጋጣሚዎቹ ላይ ሀያ ሶስት ግቦችን አስቆጥሮ ሁሉንም ማሸነፍ ችሏል።

ፖላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ሰባተኛ የላሊጋ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ባርሴሎና :- 21 ነጥብ
1️⃣9️⃣ኛ ሄታፌ :- 4 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ ኦሳሱና ከ ባርሴሎና

ቅዳሜ ሄታፌ ከ ዲፖርቲቮ አላቬስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የካራባኦ ካፕ ተጋጣሚዎች ተለይተዋል !

የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ አራተኛ ዙር ተጋጣሚዎች ከደቂቃዎች በፊት በወጣ እጣ ተለይተው ታውቀዋል።

በዚህም መሰረት :-

- ቶተንሀም ከ ማንችስተር ሲቲ

- ኒውካስል/ዌምበለደን ከ ቼልሲ

- ብራይተን ከ ሊቨርፑል

- ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሌስተር ሲቲ

- ፕሪስተን ከ አርሰናል

- አስቶን ቪላ ከ ክሪስታል ፓላስ

- ሳውዝሀምፕተን ከ ስቶክ ሲቲ

- ብሬንትፎርድ ከ ሼፍልድ ዌንስዴይ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ነገ አዲስ ቀን ነው “ ኤሪክ ቴን ሀግ

“ ራሴን በመስታወት መመልከት ይኖርብኛል “

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቡድናቸው ምሽቱን ባስመዘገበው ውጤት ብስጭታቸውን ገልፀዋል።

“ በምሽቱ ጨዋታ የሚያስተቹ ነገሮች አሉ ያሉት ቴን ሀግ “ ቡድኑ ብቻ ሳይሆን እኔም ራሴን በመስታወት መመልከት ይኖርብኛል “ ብለዋል።

“ በጨዋታው ስህተቶች ነበሩ “ ያሉት ቴን ሀግ “ ተጋጣሚያችን ስህተታችንን ተጠቅሞብናል ፣ የአቻ ውጤቱ ያበሳጫል “ ሲሉም ተናግረዋል።

በጨዋታ ወቅት 99% ብቻ በቂ አለመሆኑን የገለፁት ቴን ሀግ “ ጨዋታዎችን ገድለን መውጣት አለብን “ ብለዋል።

“ ይህ እግር ኳስ ነው ወደፊት መጓዛችንን እንቀጥላለን ፣ ነገ አዲስ ቀን ነው ፣ ነገሮችን እንደ አዲስ እንጀምራለን “ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ድሉ ይገባን ነበር “ ሀንስ ፍሊክ

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ተከታታይ ሰባተኛ ድላቸውን በሊጉ ሲያስመዘግቡ ውጤቱ ተገቢ መሆኑን አሰልጣኙ ተናግረዋል።

“ ድሉ ይገባናል “ ያሉት ሀንስ ፍሊን “ ብዙ ጎሎችን ማስቆጠር እንችል ነበር “ ሲሉም ከጨዋታው በኃላ ተናግረዋል።

የቡድናቸውን ግብ አስቆጣሪ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ ያወደሱት ሀንስ ፍሊክ “ ባለፉት አስር አመታት በዘጠኝ ቁጥር ቦታ እሱ ምርጡ ተጫዋች ነው “ ብለዋል።

“ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ ስራው ግብ ማግባት ነው ፣ ይህንንም እያደረገ ይገኛል “ አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ

አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ ቡድናቸው በሊጉ 2️⃣3️⃣ ጎሎችን ሲያስቆጥር ምንም ነጥብ ሳይጥል በ 4️⃣ ነጥብ ልዩነት ላሊጋውን እየመሩ ይገኛሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ዴቪድ ራያ የጉዳት መጠን ?

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከምሽቱ ጨዋታ በኃላ በሰጡት አስተያየት የቡድኑን ወጣት ተጫዋቾች አወድሰዋል።

“ ኢታን ንዋኔሪ ግብ በማስቆጠሩ ደስ ብሎኛል “ ያሉት አሰልጣኙ “ በአጠቃላይ በምሽቱ ጨዋታ ጥሩ ነበር “ ብለዋል።

“ በምሽቱ ከተመለከትናቸው ታዳጊ ተጫዋቾች ውስጥ አንዳንዶቹ ጠዋት ትምህርት አለባቸው “ ሚኬል አርቴታ

ሚኬል አርቴታ ስለ ግብ ጠባቂያቸው ራያ ሲጠየቁ “ የጡንቻ ህመም “ ነው ሲሉ ከጉዳት የሚመለስበትን ቀን እንደማይታወቅ ተናግረዋል።

ራሂም ስተርሊንግ በምሽቱ ጨዋታ ያሳየውን ብቃት በማድነቅ “ በአካል ብቃት ረገድ እኛ በምንፈልገው ደረጃ መገኘት አለበት “ ብለዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቀጣይ ጨዋታችን ፈታኝ ነው “ አርኔ ስሎት

“ ሽንፈት አይገባንም “ ሎፕቲጌ

የመርሲሳይዱ ክለብ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት እንግሊዝ ውስጥ እያንዳንዱ ጨዋታ ፈታኝ መሆኑን ከምሽቱ ጨዋታ በኃላ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል :-

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አዲሱ ፈራሚ ፍሬድሪኮ ኬይሳ “ ክለቡን መላመድ አለበት “ ሲሉ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል።

ቀጣይ ጨዋታቸው ከባድ መሆኑን የገለፁት አርኔ ስሎት “ ከብራይተን ጋር ፈታኛ መርሐ ግብር ነው “ ብለዋል።

የምሽቱ ተጋጣሚያቸው ዌስትሀም አሰልጣኝ ሎፕቲጌ በበኩላቸው “ ሽንፈት አይገባንም “ ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኙ ቀጥለውም “ ግልፅ የሆነ ከጨዋታ ውጪ የሆነ ጎል ተቆጥሮብናል “ ሲሉ ትችታቸውን ሰንዝረዋል።

አርኔ ስሎት ለዌስትሀም ያላቸውን አድናቆት ሲገልፁ “ ዌስትሀም ብዙ ኳሊቲ ያለው ቡድን ነው “ ብለዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ውጤቱ የሽንፈት ያህል ነው “ ኤሪክሰን

የቀያይ ሴጣኖቹ ተጫዋች ኤሪክሰን ቡድኑ ትላንት ምሽት በሜዳው ባስመዘገበው ውጤት ማዘኑን ገልፆል።

“ ውጤቱ የሽንፈት ያህል ነው “ ሲል የገለፀው ኤሪክሰን “ በሜዳችን በትዌንቴ ይህ ውጤት መፈጠር አልነበረበትም “ ብሏል።

ክሪስቲያን ኤሪክሰን የምሽቱ ጨዋታ ጎል ክለቡን ከተቀላቀለ በኃላ በአውሮፓ መድረክ ያስቆጠረው የመጀመሪያ ጎሉ መሆኑ ተገልፆል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ አቡበከር ናስር አሁን ከእኛ ጋር አይደለም “ ማንቆባ ማንጊቲ ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር ናስር ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ በውሰት ሌላኛውን የደቡብ አፍሪካ ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ እንደሚቀላቀል ተገልጿል። የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አሰልጣኝ ማንቆባ ማንጊቲ ትላንት ምሽት በሰጡት አስተያየት “ አቡበከር ናስር በዚህ ሰዓት ከእኛ ጋር አይደለም “ ብለዋል። “ አቡበክር በአሁኑ ሰዓት…
“ አቡበከር ናስር ለሱፐር ስፖርት ፈርሟል “  ወኪሉ

የኢትዮጵያዊው የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር ወኪል ስቲቭ ካፔሉሺኒክ አቡበከር ናስር ሱፐር ስፖርት ዩናይትድን በቋሚ ውል እንደተቀላቀለ አረጋግጧል።

የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋና አሰልጣኝ ማንቆባ ማንጊቲ አቡበከር ናስር ወደ ስፐር ስፖርት ዩናይትድ ማቅናቱን መግለፃቸው አይዘነጋም።

የአቡበከር ናስር ወኪል በሰጠው አስተያየት “ አቡበከር ናስር ለሱፐር ስፖርት ዩናይትድ የአንድ አመት ውል ፈርሟል አሁን የእነሱ ተጨዋች ነው “ ሲል ተናግሯል።

የደቡብ አፍሪካው ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ እስካሁን የአቡበከር ናስርን ዝውውር በይፋ አላሳወቀም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
መልካም የመስቀል ደመራ በዓል ይሁንላችሁ !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
2024/09/28 03:19:08
Back to Top
HTML Embed Code: