Telegram Web Link
30 '

ስዊዘርላንድ 1-0 ጀርመን

ንዶይ

ስኮትላንድ 0-0 ሀንጋሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ስዊዘርላንድ 1-0 ጀርመን

ንዶይ

ስኮትላንድ 0-0 ሀንጋሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
55 '

ስዊዘርላንድ 1-0 ጀርመን

ንዶይ

ስኮትላንድ 0-0 ሀንጋሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
73 '

ስዊዘርላንድ 1-0 ጀርመን

ንዶይ

ስኮትላንድ 0-0 ሀንጋሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
86 '

ስዊዘርላንድ 1-0 ጀርመን

ንዶይ

ስኮትላንድ 0-0 ሀንጋሪ

- የሀንጋሪ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች በርናባስ ቫርጋ ከባድ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 '

ስዊዘርላንድ 1-1 ጀርመን

ንዶይ ፉልክሩግ

ስኮትላንድ 0-0 ሀንጋሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90+9 ' ስኮትላንድ 0 - 1 ሀንጋሪ

ሶቦዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስዊዘርላንድ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድንን ግብ ዳን ንዶዬ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ፉልክሩግ ጀርመንን በመጨረሻ ደቂቃ አቻ ማድረግ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ በምድቡ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አንደኛ እንዲሁም የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ በመሆን ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።

በምድቡ ሌላኛው ጨዋታ የሀንጋሪ ብሔራዊ ቡድን ከስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በሶቦዝ ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ውጤቱን ተከትየስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን ከአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Croatia-Italy
Albania-Spain
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
" ምንም ጨዋታ ባለመሸነፋችን ደስተኛ ነኝ "

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሙራት ያኪን ቡድናቸው በምሽቱ የጀርመን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ባሳየው እንቅስቃሴ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

" ተጨዋቾቼን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ " ያሉት አሰልጣኙ " ታክቲካል ጨዋታ ነበር በጥሩ ሁኔታ ተፋልመናል ጠንካራ ተጋጣሚ ነበሩ ባደረግነው ጨዋታ ደስተኛ ነኝ ትልቅ ፈተና ነበር " ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኝ ሙራት ያኪን ቀጥለውም ቡድናቸው በምድብ ጨዋታዎች አለመሸነፉ እንዳስደሰታቸው በመግለፅ ለጥሎ ማለፉ ጥሩ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አቻ መውጣት ይገባናል " ኔግልስማን

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ቡድናቸው በትላንት ምሽቱ ጨዋታ አቻ ውጤት እንደሚገባው ገልጸዋል።

ስዊዘርላንድ ጠንካራ ተጋጣሚ እንደነበረች የገለፁት አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን " በመጨረሻም የሚገባንን ነጥብ አግኝተናል በመልሶ ማጥቃት ግብ አስተናግደናል ነገርግን በድጋሜ ወደ ጨዋታ ተመልሰናል አቻ መውጣት ይገባናል።"ብለዋል።

" ጨዋታው አዝናኝ ነበር በታክቲክ ረገድ ጥሩ ነበርን ከተጠባባቂ ወንበር ተንሰተው ወሳኝ ግብ የሚያስቆጥሩ ተጨዋቾች መኖራቸው በጣም አስፈላጊ ነው።" ኔግልስማን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬን ሳውዝጌት ትክክለኛው አሰልጣኝ መሆናቸውን ገለጸ !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሀሪ ኬን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ለሶስቱ አናብስት ትክክለኛው አሰልጣኝ መሆናቸውን እና ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

ባለፉት ስምንት አመታት ሶስቱን አናብስት በሀላፊነት የመሩት አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በአውሮፓ ዋንጫው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ አቻ መለያየታቸውን ተከትሎ ትችት እየቀረበባቸው ይገኛል።

የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ሀሪ ኬን በበኩሉ " ጋሪዝ ሳውዝጌት ትክክለኛው አሰልጣኝ ናቸው " ያለ ሲሆን ደጋፊዎችም ተጨዋቾች እንደሚያደርጉት ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርቧል።

" እንግሊዝን ማሰልጠን ከባድ ነው ሁሉም ሰው ያውቃል ሁልጊዜም እሱን የሚተቹ እና የሚጠራጠሩት ብዙ ሰዎች አሉ ነገርግን ስራዎቹ በራሳቸው ይናገራሉ እሱ ከእኛ ጋር ስኬታማ ነው።" ኬን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሉክ ሾው ወደ ልምምድ ይመለሳል !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የመስመር ተጨዋች ሉክ ሾው ከጉዳቱ በማገገም ዛሬ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ቀሪ ስብስብ ጋር ልምምዱን እንደሚሰራ ተገልጿል።

የማንችስተር ዩናይትዱ ተጨዋች ሉክ ሾው በጉዳት ምክንያት የእንግሊዝ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለት ጨዋታዎች እንዳመለጡት አይዘነጋም።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ነገ ምሽት 4:00 ከስሎቬኒያ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማንን ከአስቶን ቪላ ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ ለ 18ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማን ዝውውር 19 ሚልዮን ፓውንድ ወጪ እንደሚያደርጉ ተነግሯል። ለእንግሊዝ ከ 19ዓመት በታች ቡድን የሚጫወተው ኦማሪ ኬሊማን በቀጣይ የህክምና ምርመራውን አድርጎ በይፋ…
ኦማሪ ኬሊማን ዛሬ የህክምና ምርመራ ያደርጋል !

እንግሊዛዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማን ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ዛሬ የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ የ 18ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማንን ከአስቶን ቪላ በ 19 ሚልዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል።

ተጨዋቹ በክንፍ አጥቂነት ወይም በአጥቂ አማካይ ሚና ተሰልፎ ለቡድኑ ግልጋሎት የመስጠት ክህሎት እንዳለው ተነግሯል።

ለእንግሊዝ ከ 19ዓመት በታች ቡድን የሚጫወተው ኦማሪ ኬሊማን ባለፈው አመት ለአስቶን ቪላ ዋናው ቡድን ስድስት ጨዋታዎች አድርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አልባንያ ተጨዋቿ የጨዋታ ቅጣት ተጣለበት !

የአልባንያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ሚርሊንድ ዳኩ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የሁለት የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች አገዳ እንደተጣለበት ተገልጿል።

ተጨዋቹ የቅጣት ውሳኔው የተላለፈበት አልባንያ ከቀናት በፊት ከክሮሽያ ጋር ካደረገችው ጨዋታ በኋላ ድምፅ ማጉያ ተጠቅሞ ሰርቢያዊያን እና መቄዶኒያዊያንን መሳደቡን ተከትሎ ነው።

በተጨማሪም የአልባንያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ50,000 ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አሁን ሁሉም ስዊዘርላንድን የበለጠ ያከብራል " ዣካ

የስዊዘርላንድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ግራኒት ዣካ ከትላንቱ የጀርመን ጨዋታ በኋላ ቡድናቸው የበለጠ ይከበራል የሚል እምነት እንዳለው ተናግሯል።

ግራኒት ዣካ በንግግሩም " ቀጣይ ጨዋታችን እና ተጋጣሚያችንን በጉጉት እየጠበቅን ነው ከትናንቱ የጀርመን ጨዋታ በኋላ ሁሉም ሰው ለስዊዘርላንድ የበለጠ ክብር እንደሚሰጥ ተስፋ አደርጋለሁ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኮነር ጋራገር በአርኖልድ ቦታ ሊሰለፍ ነው !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌቱ ቡድኑ ከስሎቬኒያ ጋር በሚያደርገው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ የአሰላለፍ ለውጥ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በጨዋታው በመሐል ሜዳ ክፍሉ አሌክሳንደር አርኖልድን በኮነር ጋላገር ተክተው ለማሰለፍ ማሰባቸው ተነግሯል።

የሊቨርፑሉ ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ በብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታዎች በአማካይ ስፍራ ተሰልፎ ባደረጋቸው የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች ተቃውሞዎች ሲቀርቡበት ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሆሴሉ ለሪያል ማድሪድ በቋሚነት ይፈርማል ! ሪያል ማድሪድ በውሰት እየተጫወተ የሚገኘውን ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ ለሚቀጥለው የውድድር አመት በቋሚነት ለማስፈረም መወሰናቸው ተገልጿል። ሎስ ብላንኮዎቹ ሆሴሉን ባለፈው ክረምት በውሰት 500,000 ዩሮ በማውጣት ያስፈረሙት ሲሆን ተጫዋቹም በወሳኝ ጨዋታዎች ግብ በማስቆጠር ለክለቡ ጥሩ ግልጋሎት መስጠት ችሏል። ሪያል ማድሪዶች ተጫዋቹን በውሉ…
ሆሴሉ ሪያል ማድሪድን ሊለቅ ነው !

ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከሪያል ማድሪድ ጋር ላለመቀጠል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ በሆሴሉ የውሰት ውል ውስጥ የተካተተውን አማራጭ ተጠቅመው 1.5 ሚልዮን ዩሮ ወጪ በማድረግ በቋሚነት ለማስፈረም መወስናቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ሆሴሉ ኪሊያን ምባፔ እና ኢንድሪክ ወደ ሪያል ማድሪድ መምጣታቸውን ተከትሎ ሎስ ብላንኮዎቹን ለመልቀቅ ማሰቡ ተገልጿል።

ሆሴሉ በቀጣይ የኳታሩን ክለብ አል ጋራፋ ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/24 13:41:34
Back to Top
HTML Embed Code: