Telegram Web Link
ኪሊያን ምባፔ ጉዳት አጋጠመው !

ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በትላንት ምሽቱ የላሊጋ መርሐግብር ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ኪሊያን ምባፔ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ እስከ ሶስት ሳምንታት ጊዜ እንደሚወስድበት ተገልጿል።

ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድ የፊታችን እሁድ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር የሚያደርገው የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ዛሬ ምሽት በግብ ጠባቂነት ማንን ያሰልፋል ?

አርሰናል ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ መጠነኛ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ለጥንቃቄ ዛሬ ምሽት ከቦልተን ጋር በሚያደርጉት የሊግ ካፕ ጨዋታ እንደሚያሳርፉት ተገልጿል።

በጨዋታው መድፈኞቹ የ 16ዓመቱን የአካዳሚያቸው ግብ ጠባቂ ጃክ ፖርተር በቋሚነት ለማሰለፍ ማሰባቸው ተገልጿል።

የክለቡ ቁጥር ሁለት ግብ ጠባቂ ኔቶ ከበርንማውዝ ጋር በሊግ ካፕ መጫወቱን ተከትሎ ለአርሰናል መሰለፍ እንደማይችል ተነግሯል።

በተጨማሪም በቅርቡ ከአያክስ ያስፈረሙት ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ጉዳት እንዳጋጠመው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ካሴሚሮ በቴንሀግ የታክቲክ እውቀት ተደንቆ ነበር “ ስቲቭ ማክላረን

የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የቀድሞ ምክትል አሰልጣኝ የነበሩት ስቲቭ ማክላረን ካሴሚሮ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የታክቲክ እውቀት ተደንቆ እንደነበር ገልጸዋል።

“ ካሴሚሮ ሁሉንም ነገሮች ሪያል ማድሪድ ውስጥ አይቻለሁ ብሎ ስለሚያስብ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በነበራቸው የጨዋታ ታክቲክ እና አጠቃላይ ስራ ተደንቆ ነበር።“ ሲሉ ስቲቭ ማክ ክላረን ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አክለውም አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጥሩ ታክቲሺያን መሆናቸውን ገልፀው ሌሎች ሜዳ ላይ ሊታዩዋቸው የማይችሉ ነገሮችን መመልከት ይችላሉ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሮድሪ ባሎን ዶር ይገባዋል “ ሎታር ማቲያስ

የቀድሞ ጀርመናዊ ተጨዋች ሎታር ማቲያስ የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት ለስፔናዊው ተጨዋች ሮድሪ እንደሚገባው ገልጿል።

“ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከቪንሰስ ጁኒየር በበለጠ ሮድሪ የባሎን ዶር ሽልማት ይገባዋል “ ሲል ሎታር ማቲያስ አስተያየቱን ሰጥቷል።

እንደ ቀድሞ ተጨዋቹ ሎታር ማቲያስ ገለፃ “ በእኔ የዚህ አመት ምርጥ ተጨዋቾች ደረጃ ቪንሰስ ጁኒየርን ሶስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጠዋለሁ “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

ሰኞ ⏩️  ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

ሐሙስ ⏩️ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አርባምንጭ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሼዝኒ ጓንቱን መስቀሉን አሳወቀ ! ፖላንዳዊው የቀድሞ የአርሰናል እና ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂ ሼዝኒ በ 34ዓመቱ ጓንቱን መስቀሉን በይፋ አስታውቋል። ሼዝኒ በቅርቡ ሰባት የውድድር አመታት ካሳለፈበት የጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየቱ አይዘነጋም። ሼዝኒ በእግርኳስ ህይወቱ ምን አሳካ ? 3️⃣ የጣልያን ሴርያ ፣ የጣልያን ዋንጫ 2️⃣ ኤፌ ካፕ ፣ የጣሊያን ሱፐር ካፕ…
ሼዝኒ ባርሴሎናን ለመቀላቀል ተስማማ !

ፖላንዳዊው የቀድሞ የአርሰናል እና ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂ ሼዝኒ በቅርቡ ጓንቱን መስቀሉን ይፋ ቢያደርግም ተመልሶ ለባርሴሎና ለመጫወት ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

የቴር ስቴገንን መጎዳት ተከትሎ ባርሴሎና በምትኩ ሼዝኒን ለአንድ አመት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

“ አሁን ላይ ወደ እግርኳስ ተመልሼ ባርሴሎናን ለመቀላቀል በንግግር ላይ ነኝ “ ሲል ሼዝኒ ተናግሯል።

“ ባርሴሎና አለማችን ላይ ካሉ ምርጥ ክለቦች አንዱ ነው “ ያለው ሼዝኒ “ በእግርኳስ ህይወቴ ይህንን የመሰለ እድል አልቀበልም ብል ንቀት ይሆናል “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቤንታኩር በእንግሊዝ ኤፍኤ ክስ ቀረበበት ! ዩራጓዊው የቶተንሀም አማካይ ሮድሪጎ ቤንታኩር ከመገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ በቡድን አጋሩ ላይ ያልተገባ ነገር ተናግሯል በሚል ክስ እንደተከፈተበት ተገልጿል። ሮድሪጎ ቤንታኩር ከዩራጓይ መገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ የሰን ሁንግ ሚን ማልያ ማገኘት ከተቻለ ሲጠየቅ “ ምናልባት የአጎቱን ልጅ ምክንያቱም ሁሉም ይመሳሰላሉ “ ሲል መልሶ ነበር።…
“ ቤንታንኩር እያለቀሰ ይቅርታ ጠይቆኛል “ ሰን

ዩራጓዊው የቶተንሀም አማካይ ሮድሪጎ ቤንታንኩር በቅርቡ ለሰጠው አስተያየት የቡድን አጋሩ ሰን ሁንግ ሚንን ይቅርታ ጠይቋል።

ሮድሪጎ ቤንታንኩር በቅርቡ ከዩራጓይ መገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ " ሰን ሁንግ ሚን እና የአጎቱ ልጆች ሁሉም አንድ አይነት ናቸው " ብሎ ተናግሮ ነበር።

በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የሰጠው ሰን " የእንግሊዝ ኤፍኤ ጉዳዩን እያየው ስለሆነ ብዙ አልናገርም ነገርግን ቤንታንኩርን በጣም ነው የምወደው “ ሲል ተደምጧል።

በቀጥታ ይቅርታ ጠይቋል ለእኔም ጉዳዩ ምን እንደሆነ ሳላውቅ ቀድሞ ረጅም መልዕክት ፅፎልኝ ነበር ፣ ወደ ቡድኑ ከተመለሰም በኋላም እያለቀሰ ይቅርታ ብሎኛል ሲል ሰን ተናግሯል።

በኮንትራት ዙሪያ እስካሁን ከክለቡ ጋር ለንግግር አለመቀመጡን የጠቆመው ሰን “ አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቴ ውድድር አመቱ ላይ እና ክለቡ የሚገባውን ነገር ማሳካት ላይ ነው “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ወልቂጤ ከተማ ስድስት ነጥቦች ይቀነሱበታል ! የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የሚጠበቅበትን ህጋዊ መስፈርት አለሟሟላቱን ተከትሎ የስድስት ነጥብ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ወልቂጤ ከተማ ተገቢውን የምዝገባ ሂደት ( ክለብ ላይሰንሲግ ) ባለሟሟላታቸውን እና በውድድሩ ያልተመዘገበ ቡድን ወደ ሜዳ መግባት #አለመቻሉን ተከትሎ ጨዋታው ሳይደረግ ቀርቷል። በአሁን ሰዓት ከ መቻል ጋር መርሐ…
ወልቂጤ ከተማ በተከታታይ ጨዋታ ሳይገኝ ቀርቷል !

የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የሚጠበቅበትን ህጋዊ መስፈርት አለሟሟላቱን ተከትሎ በተከታታይ መርሐግብር ጨዋታውን ሳያደርግ ቀርቷል።

ዛሬ ምሽት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር የወጣለት ወልቂጤ ከተማ ተገቢውን የምዝገባ ሂደት ባለሟሟላቱ ጨዋታው በፎርፌ ለንግድ ባንክ ተሰጥቷል።

ወልቂጤ ከተማ ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ ተገቢውን የምዝገባ ሂደት ባለሟሟላታቸው የመጀመሪያ ሳምንት መርሐግብር በፎርፌ እንደተሰጠባቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ደንብ መሰረት አንድ ክለብ በተከታታይ ጨዋታዎች ሜዳ ላይ የማይገኝ ከሆነ ከውድድሩ እንዲሰረዝ ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዋልያዎቹ ቀጣይ ጨዋታቸውን የት ያደርጋሉ ? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ 2025 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚረዳውን የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ ከጊኒ አቻቸው ጋር የሚያደርጉ ይሆናል። የሁለቱ ሀገራት የደርሶ መልስ ጨዋታ በኮትዲቯር ሊደረግ እንደሚችል ለማወቅ ተችሏል። ከጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እየወጡ ባሉ መረጃዎች ሁለቱንም ጨዋታ በ ኮትዲቯር ለማድረግ የሁለቱ ሀገራት ፌዴሬሽኖች በንግግር…
ዋልያዎቹ በኮትዲቯር እንደሚጫወቱ ይፋ ሆነ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር የሚያደርጋቸውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች ኮትዲቯር ላይ እንደሚያደርግ ይፋ ሆኗል።

የሁለቱ ሀገራት እግርኳስ ፌዴሬሽኖች ጨዋታዎቹን ኮትዲቯር ላይ ለማድረግ በንግግር ላይ እንደሚገኙ መዘገቡ አይዘነጋም።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ ሶስተኛ ጨዋታ ጊኒ ባስመዘገበችው 20,000 ተመልካችን በሚይዘው ያሙሶኩሮ ቻርለስ ኮናን ባኒ ስታዲየም ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር " በሜዳው " የሚያደርገው የምድብ አራተኛ ጨዋታ ደግሞ አቢጃን በሚገኘው ስታድ ደ ኢቢምፔ ስታዲየም እንደሚደረግ ተገልጿል።

የደርሶ መልስ መርሐ ግብሩ ጥቅምት 1 እና ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም የሚደረጉ ይሆናል።

ዋልያዎቹ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ እንዲሁም ጊኒ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው በምድባቸው ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

3:45 አርሰናል ከ ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

Bolton XI: Southwood; Toal, Collins, Santos; Dacres-Cogley, Sheehan, Arfield, Williams, McAtee; Forino-Joseph, Dempsey.

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፎች !

4:00 ሊቨርፑል ከ ዌስትሀም

4:00 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ትዌንቴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
18 '

አርሰናል 1-0 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

ራይስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
35 ' አርሰናል 2-0 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ
ንዋኔሪ

22 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0-0 ትዌንቴ

ሊቨርፑል 0-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ኳንሳህ ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
29 'ሊቨርፑል 1-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ጆታ             ኳንሳህ ( በራስ ላይ )

45 ' አርሰናል 2-0 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ
        ንዋኔሪ

29 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0-0 ትዌንቴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
35 ' ማንችስተር ዩናይትድ 1-0 ትዌንቴ

ኤሪክሰን

35 'ሊቨርፑል 1-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ጆታ             ኳንሳህ ( በራስ ላይ

እረፍት | አርሰናል 2-0 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ
        ንዋኔሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
58 ' አርሰናል 3-1 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ ኮሊንስ
        ንዋኔሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
50 '

ሊቨርፑል 2-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ጆታ             ኳንሳህ ( በራስ ላይ )

ማንችስተር ዩናይትድ 1-0 ትዌንቴ

ኤሪክሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/28 05:19:10
Back to Top
HTML Embed Code: