Telegram Web Link
የፖርቹጋል ሊግ በጎሎች ልክ ዛፍ ሊተክል ነው !

በቅርቡ አስከፊ የሰደድ እሳት ባጋጠማት ፖርቹጋል የሀገሪቱ ሊግ በቀጣይ መርሐ ግብር በሚቆጠር  በእያንዳንዱ ግብ 200 ዛፎችን ለመትከል ማሰቡ ተገልጿል።

ባለፉት ቀናት በፖርቹጋል በተነሳው የሰደድ እሳት ምክንያት ሶስት የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

በቀጣይ የሚደረጉ የፖርቹጋል ሊግ መርሐ ግብሮች የህሊና ፀሎት በማድረግ እንደሚጀምሩ ሲገለፅ የክለቦቹ አምበሎች የእሳት አደጋ ሰራተኞችን የደንብ ልብስ ለብሰው እንደሚገቡ ተዘግቧል።

የሰደድ እሳቱ ከጀመረ አምስት ቀናት ውስጥ ከ 119,000 ሄክታር በላይ መሬት አደጋ እንደደረሰበት የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? ያለፉትን ሁለት ቀናት የተደረጉ የሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ተከትሎ የሳምንቱ ምርጥ አራት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት :- ⏩️ ሀሪ ኬን ፣ ⏩️ፍሎረን ዊርትዝ ፣ ⏩️ጊተንስ እና ⏩️ አንቱዋን ግሪዝማን በእጩነት የቀረቡ አራት ተጫዋቾች ሆነዋል። @tikvahethsport            @kidusyoftahe
የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

ያለፉትን ሶስት ቀናት የተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ተከትሎ የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የባየር ሌቨርኩሰኑ የፊት መስመር ተጨዋች ፍሎረን ቨርትዝ የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።

ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፍሎረን ቨርትዝ በምሽቱ ጨዋታ ሁለት ግቦች ማስቆጠሩ አይዘነጋም።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
ሀድያ ሆሳዕና አመቱን በድል ጀምረዋል !

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ጅማሮውን ሲያደርግ ሀድያ ሆሳዕና ከመቐለ 70 እንደርታ ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሀድያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ግብ እና የሊጉን የመክፈቻ ግብ ሄኖክ አርፊጮ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የሀድያ ሆሳዕናው ተጨዋች አስጨናቂ ሉቃስ የሊጉን የመጀመሪያ ቢጫ እና ቀይ ካርድ የተመለከተው ተጨዋች ሆኗል።

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ሐሙስ ⏩️ ፋሲል ከነማ ከ መቐለ 70 እንደርታ

⏩️ ሀድያ ሆሳዕና በሚቀጥለው ዙር አራፊ ክለብ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ይመለሳሉ💥

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ወደ ጎጆ በማራዘም የዚህን ሳምንት 10 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-SPORT
የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ አዲስ አበባ ላይ ይደረጋል ! የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰኑ ይፋ ተደርጓል። ጉባዔው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ላይ ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ በተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መቀየሩን የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት…
የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ የሚካሄድበት ቀን ታውቋል !

በኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ ላይ የሚካሄደው 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ )  መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የሚደረግበት ቀን ይፋ ተደርጓል።

ይህንንም ተከትሎ 46ኛው የካፍ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል።

ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የካፍን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ያዘጋጀችው እ.ኤ.አ 2017 ከሰባት አመታት በፊት ነበር።

ጉባዔው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ላይ ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ በተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መቀየሩ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቶተንሀም አርሰናልን ማሸነፍ ይገባው ነበር “ ቶማስ ፍራንክ

የብሬንትፎርድ ዋና አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ባለፈው ሳምንት በተደረገው የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ድሉ ለቶተንሀም ይገባ እንደነበር ተናግረዋል።

“ አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ከቶተንሀም ጋር ጥሩ ስራ እየሰሩ ነው ፤ ከአርሰናል ጋር ባደረጉት ጨዋታ ማሸነፍ ይገባቸው ነበር።"ሲሉ አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ገልጸዋል።

ነገ ከቶተንሀም ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ስምንት ተጨዋቾቻቸው አለመኖራቸውን የጠቆሙት አሰልጣኙ ስምንቱም ቋሚ ተሰላፊ ተጨዋቾቻችን ነበሩ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ካልቻልን መሸነፍ የለብንም “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በቀጣይ ሊያሻሽላቸው የሚገቡ የተወሰኑ ነገሮች መኖራቸውን ገልፀዋል።

“ የምናደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ እንፈልጋለን “ የሚሉት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ “ ነገርግን ማሸነፍ የማንችል ከሆነ መሸነፍ የለብንም “ በማለት ተናግረዋል።

የተወሰነ ማሻሻል ያለብን ነገር አለ በማለት ያስረዱት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ “ ቢሆንም እንደ ቡድን ወጥ የሆነ አቋም እያሳየን ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሌክሳንደር አርኖልድ ክለብ ለመግዛት አስቧል ! እንግሊዛዊው የሊቨርፑል የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ የፈረንሳይ ሊጉን ክለብ ናንትስ ለመግዛት በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል። አሌክሳንደር አርኖልድ የስምንት ጊዜ የፈረንሳይ ሊግ አሸናፊውን ክለብ ናንትስ ለመግዛት ከክለቡ ባለቤቶች ጋር መነጋገሩም ተገልጿል። አሌክሳንደር አርኖልድ ክለቡን ለመግዛት ከቀናት በፊት ባለቤቶቹን ማነጋገሩ እና…
“ አርኖልድ ማን እንደሆነም አላውቅም “ የናንትስ ባለቤት

የፈረንሳዩ ክለብ ናንትስ ባለቤት ዋልዴማር ኪታ
እንግሊዛዊው ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ ናንትስን ሊገዛ ነው መባሉ ሀሰተኛ ነው በማለት አስተባብለዋል።

“ የወጣው ዜና መሰረተ ቢስ ነው “ ያሉት የክለቡ ባለቤት ዋልዴማር ኪታ “ አርኖልድ ማን እንደሆነ እንኳን አላውቅም ማንነቱን ጠበቃዬን ጠይቄያለሁ “ ሲሉ ገልጸዋል።

እንግሊዛዊው የሊቨርፑል የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ ናንትስን ሊገዛ ስለመሆኑ ተዘግቦ እንደነበር ይታወሳል።

በተጨማሪም ለአሌክሳንደር አርኖልድ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች የመረጃውን ሀሰተኛነት አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ድሬዳዋ ከተማ አመቱን በድል ጀምሯል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ድሬዳዋ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቻርልስ ሙሴጌ እና መሐመድ ኑር ናስር ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለአርባምንጭ ከተማ አህመድ ሁሴን አስቆጥሯል።

በጨዋታው የአርባ ምንጭ ከተማው አምበል አበበ ጥላሁን በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

እሮብ ⏩️ ኢትዮጵያ መድን ከ አርባምንጭ ከተማ

ቅዳሜ ⏩️ ድሬዳዋ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#SaudiLeague 🇸🇦

በሰዑዲ ዓረቢያ ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አል ነስር አል ኢትፋቅን 3ለ0 ሲያሸንፍ አል አህሊ ከዳማክ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ2 በሆነ ውጤት ረቷል።

የአል ነስርን የማሸነፊያ ግቦች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ናጅዲ እና ታሊስካ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ለአል አህሊ የማሸነፊያ ግቦችን ኢቫን ቶኒ 2x ፣ ሮቤርቶ ፊርሚኖ እና ጋብሬል ቬጋ ሲያስቆጥሩ ለዳማክ አይማን ፋላታህ እና ቻፋይ ከመረብ አሳርፈዋል።

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ 902ኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

ሮናልዶ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለክለቡ እና ሀገሩ ባደረጋቸው ስምንት ጨዋታዎች ሰባት ግቦች አስቆጥሮ ሁለት ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

3️⃣ኛ አል ኢትፋቅ :- 9 ነጥብ
4️⃣ኛ አል ነስር :- 8 ነጥብ
5️⃣ኛ አል አህሊ :- 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

አርብ ⏩️ አል ነስር ከ አል ዌህዳ

እሁድ ⏩️ አል ታዎን ከ አል ኢትፋቅ

አርብ ⏩️ አል ቃዲሲያ ከ አል አህሊ

የሰዑዲ ዓረቢያ ሊግ በነገው ዕለት መደረጉን ሲቀጥል አል ሂላል ከአል ኢትሐድ ጋር የሚደርጉት ጨዋታ ከሚጠበቁ ጨዋታዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዋልያዎቹ ተጫዋች ለሊቢያ ክለብ ለመጫወት ተስማማ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና መቻል እግር ኳስ ክለብ የፊት መስመር ተጫዋች ከንአን ማርከነህ ወደ ሊቢያ ማቅናቱ ታውቋል።

ከንአን ማርከነህ በሊቢያ ሊግ ተሳታፊ ለሆነው አል መዲና ትሪፖሊ እግር ኳስ ክለብ ለመጫወት ከስምምነት መድረሱን አውቀናል።

በትላንትናው ዕለት የሜዲካል ህክምናውን ያለፈው ከንአን በዛሬው ዕለት በክለቡ የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል።

ከዚህ ቀደም የቀድሞ የዋልያዎቹ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ሽመልስ በቀለ በሊቢያ ሊግ መጫወቱ ይታወሳል።

የሊቢያ ሊግ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ ሲገኝ በቀጣይ ጥቂት ሳምንታት ጅማሮውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 146,000 Birr
•512GB = 156,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 114,000 Birr
•512GB = 126,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
⚡️ በዕለታዊ የዳታ ጥቅሎች ቀኑን ሙሉ ፈታ እንበል! 🥳

በM-PESA ላይ ስንገዛ ሁሉም ቅናሽ አላቸው!

በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1wedefit
#Furtheraheadtogether
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

8:30 ዌስትሀም ከ ቼልሲ

10:00 ወልቂጤ ከተማ ከ መቻል

10:30 ወርደር ብሬመን ከ ባየር ሙኒክ

11:00 ሊቨርፑል ከ በርንማውዝ

11:00 አስቶን ቪላ ከ ዎልቭስ

11:00 ሌስተር ሲቲ ከ ኤቨርተን

11:00 ቶተንሀም ከ ብሬንትፎርድ

1:00 ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከ ባሕር ዳር ከተማ

1:00 ጁቬንቱስ ከ ናፖሊ

1:30 ክሪስታል ፓላስ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

4:00 ሪያል ማድሪድ ከ እስፓኞል

4:00 ሬምስ ከ ፒኤስጂ

🔴 የዛሬው የይግምቱ ሽልማታችን የቼልሲ ፣ ሊቨርፑል ፣ ጁቬንቱስ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድ ጨዋታዎች ናቸው።

🔴 የዛሬ አምስት ሽልማቶቻችን 7:00 ፣ 9:30 ፣ 11:30 ፣ 12:00 ፣ 3:00 ሰዓት ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርሱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አርሰናል አራት ዋንጫ ማሳካት ይችላል “ ሀቨርትዝ

የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ካይ ሀቨርትዝ አርሰናል በዘንድሮው የውድድር ዘመን የሚሳተፍባቸውን አራት ውድድሮች ማሸነፍ እንደሚችል ገልጿል።

አርሰናል በዚህ አመት አራቱንም ዋንጫዎች ማሸነፍ ይችላል ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው የመድፈኞቹ ተጨዋቾች ካይ ሀቨርትዝ “ አዎ በእርግጠኝነት “ ሲል መልሷል።

የቡድኑ አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ በበኩሉ “ ይህ ህልማችን ነው መሞከር አለብን ፣ ጠንክረን ሰርተን የሚሆነውን እናያለን “ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨማሪ ተጨዋቾች ለማስፈረም አቅዷል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በሚቀጥሉት የጥር እና ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮቶች ተጨማሪ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ማሰቡ ተገልጿል።

ቼልሲ በአሁን ሰዓት ከማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል ጋር ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ተጨማሪ ተጨዋቾች እንደሚያስፈርም አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ገልጸዋል።

ሰማያዊዎቹ በተጠናቀቀው የክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ለዝውውር 219 ሚልዮን ፓውንድ በማውጣት ቀዳሚ ናቸው።

“ አሁንም ምርጥ ቡድን አለን ነገርግን ከፊታችን ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል እንዳሉ ምንም ጥርጥር የለውም “ ሲሉ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቡድናቸው መጠናከር እንደሚገባው አስረድተዋል።

ቼልሲ ካለፉት አራት የዝውውር መስኮቶች በሶስቱ ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ቀዳሚ ሲሆኑ አዲስ ባለቤት ካገኙ ሁለት አመታት ወዲህ ለዝውውር ከአንድ ቢሊዮን ፓውንድ በላይ አውጥተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ኤሪክ ቴንሀግን ልለምነው ነበር “

ከቀናት በፊት በማንችስተር ዩናይትድ የ 7ለ0 ሽንፈት የገጠማቸው ባርንስሌይ አሰልጣኝ ዳሬል ክላርክ በጨዋታው ወቅት ኤሪክ ቴንሀግን ለመለመን ተቃርቤ ነበር ብለዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ትልቅ ተጨዋቾችን ቀይሮ ሲያስገባ “ ቴንሀግን ቀለል አድርግልን ብዬ ልለምነው ነበር “ ሲሉ አሰልጣኝ ዳሬል ክላርክ ተናግረዋል።

በጨዋታው ማንችስተር ዩናይትድ 5ለ0 እየመራ በነበረበት 62ኛው ደቂቃ ላይ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ፈርናንዴዝ ፣ ዚርኪዜ እና ናስር ማዝራዊን ቀይረው አስገብተው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሲቲን በእርግጠኝነት እንደምናሸንፍ እናምናለን “ ካላፊዮሪ

የመድፈኞቹ የኋላ መስመር ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ቡድናቸው በነገው ተጠባቂ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲን ማሸነፍ እንደሚችል ገልጿል።

“ ማንችስተር ሲቲን በእርግጠኝነት እንደምናሸንፍ እናምናለን “ የሚለው ሪካርዶ ካላፊዮሪ እያንዳንዱን ጨዋታ ማሸነፍ አለብን በማለት ተናግሯል።

“ ስለ ማንችስተር ሲቲ ማውራት አያስፈልግም ራሳችን ላይ ማተኮር ነው ያለብን ስራችንን በተገቢው መልኩ ካሳካን እነሱን ማሸነፍ እንችላለን።“ ሪካርዶ ካላፊዮሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የዌስትሀም እና ቼልሲን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 8:30 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
2024/09/28 23:28:55
Back to Top
HTML Embed Code: