Telegram Web Link
ዴቪድ ራያ የማይታመን ነው “

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች እንደ ፕርሚየር ሊግ አለመሆኑን የገለፁት አርቴታ “ ልዩነት አለው “ ሲሉ ተደምጠዋል።

የፍፁም ቅጣት ምት ያዳነውን ግብ ጠባቂያቸውን “ የማይታመን “ ሲሉ ያወደሱት አርቴታ “ የተሻለ ግብ ጠባቂ አሁን ላይ አይታየኝም ፣ በእርግጥም እሱ ለኛ አስደናቂ በረኛችን ነው “ ብለዋል።

“ በእግር ኳስ ዘመኔ ዴቪድ ራያ ያዳናቸውን ሁለት ምርጥ ሙከራዎች ተመልክቻለሁ “ ሚኬል አርቴታ

ዴቪድ ራያ በበኩሉ በምሽቱ ያዳነውን ኳስ “ በእግር ኳስ ህይወቴ ካዳንኳቸው ምርጥ ሶስት ሙከራዎች ውስጥ አንዱ ነው “ ሲል ገልፆታል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ከዚህ በላይ ማሸነፍ እንችል ነበር “

ትላንት ምሽት በሜዳቸው የካታላኑን ክለብ ባርሴሎና የረቱት ሞናኮ ዋና አሰልጣኝ አዲ ሀተር “ ድሉ ይገባናል “ ሲሉ ተደምጠዋል።

ከጨዋታው በኃላም በሰጡት አስተያየት “ ከዚህ በተሻለ ውጤት ማሸነፍ እንችል ነበር “ ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

ማሸነፍ እንደሚገባቸው የገለፁት አሰልጣኙ “ የቁጥር ብልጫውን እንዴት መጠቀም እንዳለብን አውቀናል “ በማለት ተናግረዋል።

የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ በበኩላቸው “ የቀይ ካርዱ ጨዋታውን ቀይሮብናል “ ሲሉ “ ሞናኮ ድሉ ይገባቸዋል “ ብለዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹

የ 2017ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ጅማሬውን በዛሬው ዕለት ያደርጋል።

በዛሬ መርሐ ግብርም :-

10:00 ⏩️ መቐለ 70 እንደርታ ከ ሀድያ ሆሳዕና

1:00 ⏩️ አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ የሚገናኙ ይሆናል።

የአንድ ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮን መቐለ 70 እንደርታ ከ 1630 ቀናት በኃላ ዳግም በሊጉ የምንመለከታቸው ይሆናል።

አስራ ዘጠኝ ክለቦች ተሳታፊ በሚሆኑበት የዘንድሮው ፕርሚየር ሊግ አምስት ቡድኖች ወደ ከፍተኛ ሊጉ የሚወርዱም ይሆናል።

🔴 ጨዋታዎቹ በዲኤስቲቪ ሱፐር ስፖርት ልዩ ቻናል ( 240 ) የቀጥታ ስርጭት ሽፋን የሚያገኙ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዲናሞ ዛግሬብ አሰልጣኙን አሰናበተ !

በባየር ሙኒክ ከባድ ሽንፈት የገጠማቸው የክሮሽያው ክለብ ዲናሞ ዛግሬብ የቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ሰርጄ ጃኪሮቪች ማሰናበታቸው ተገልጿል።

ቦስንያዊው አሰልጣኝ ሰርጄ ጃኪሮቪች ቡድናቸው ከቀናት በፊት በባየር ሙኒክ የደረሰበት የ 9ለ2 አስከፊ ሽንፈት ለስንብታቸው ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

ዲናሞ ዛግሬብ በባየር ሙኒክ የደረሰበት ሽንፈት በታሪኩ በከፍተኛ ጎል የተሸነፈበት አስከፊው ሽንፈት በመሆን መመዝገቡ ተነግሯል።

አሰልጣኙ ዲናሞ ዛግሬብን ባለፈው አመት ክረምት ተረክበው በመጀመሪያ አመታቸው ክለቡን ለሀገሪቱ ሊግ ዋንጫ እና ለክሮሽያ ካፕ አሸናፊነት ማብቃት ችለው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የተጫዋቾቹን ግልጋሎት ያገኛል ?

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከነገው የክሪስታል ፓላስ ጨዋታ በፊት ስለ ተጨዋቾቻቸው ጉዳት ዜና ተናግረዋል።

እንግሊዛዊው አማካይ ሜሰን ማውንት እና ራስሙስ ሆይሉንድ ከጉዳታቸው በማገገም ወደ ቡድን ልምምድ መመለሳቸውን አሰልጣኙ አረጋግጠዋል።

“ ሜሰን ማውንት እና ራስሙስ ሆይሉንድ በዚህ ሳምንት ወደ ልምምድ ተመልሰዋል ለነገው የክሪስታል ፓላስ ጨዋታ ብቁ ከሆኑ እናያለን “ ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም ሌኒ ዮሮ ፣ ማላሽያ ፣ ቪክቶር ሊንድሎፍ እና ሉክ ሾው አሁንም በጉዳት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሌክሳንደር አርኖልድ ክለብ ለመግዛት አስቧል !

እንግሊዛዊው የሊቨርፑል የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ የፈረንሳይ ሊጉን ክለብ ናንትስ ለመግዛት በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

አሌክሳንደር አርኖልድ የስምንት ጊዜ የፈረንሳይ ሊግ አሸናፊውን ክለብ ናንትስ ለመግዛት ከክለቡ ባለቤቶች ጋር መነጋገሩም ተገልጿል።

አሌክሳንደር አርኖልድ ክለቡን ለመግዛት ከቀናት በፊት ባለቤቶቹን ማነጋገሩ እና 140 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ ገንዘብ ለግዢው ማቅረቡን የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

አርኖልድ ከዚህ በፊት የፈረንሳዩን " Formula 1 " ቡድን አልፊን " F1 " ቡድን አነስተኛ ድርሻ መግዛቱ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የአሊሰንን ግልጋሎት ላያገኝ ይችላል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ነገ ከበርንማውዝ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ግብ ጠባቂው አሊሰን ቤከር መድረሱ አጠራጣሪ መሆኑን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ገልጸዋል።

“ አሊሰን ቤከር ለጨዋታው መድረሱ አጠራጣሪ ነው ዛሬ ልምምድ ከሰራ እናየዋለን ሁኔታውን መጠበቅ እና መመልከት አለብን።“ ሲሉ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር በኤሲ ሚላን ጨዋታ ወቅት የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቀጣይ ኮከቦቻችንን ቪድዮአቸውን ላይክ እያደረግን እናበረታታ! 👏🏽

እስከ መስከረም 20 ብቻ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ

እንዝፈን! እንፖስት! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 146,000 Birr
•512GB = 156,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 114,000 Birr
•512GB = 126,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
" ደጋፊው እንዲያበረታታን የሚፈልገውን ነገር አላሳየንም “ አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው ነገ ከበርንማውዝ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አርኔ ስሎት ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል :-

- “ እኛ እንደ ቡድን ደጋፊዎች ቡድኑን ለማበረታታት የሚያስፈልጋቸው ነገር እንዳለ ልንገነዘብ ይገባል ያንን በበቂ ሁኔታ አላሳየንም።

- በርንማውዝ ጥሩ አጀማመር አሳይተዋል ጎረቤታችን ኤቨርተንን አሸንፈዋል አሰልጣኙ ጥሩ ስራ እየሰሩ ነው ጥሩ ተጨዋቾች አሏቸው ጥሩም ይጫወታሉ።

- በኖቲንግሀም ፎረስት ጨዋታ ከነበረን አቋም የተሻልን ሆነን መቅረብ እንደምንችል ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ።

- ኑኔዝ በቅርቡ የጨዋታ ሰዓት እንደሚያገኝ እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም ብዙ ጨዋታዎች አሉብን ፣ ከእሱ ምን እንደምንፈልግ ያውቃል ከኮፓ አሜሪካ በጥሩ በራስ መተማመን ነው የተመለሰው።

- እኛ መከላከልን መሰረት ያደረጉ ቡድኖችን ለመግጠም ችግር የለብንም ምክንያቱም ኳስ ተቆጣጥረን ነው የምንጫወተው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በሙስና ይከሱኛል እኔ ግን ንፁህ ነኝ “ ሳሙኤል ኤቶ

“ እኛ አፍሪካዊያን ስኬታማ ሰውን እየተፋለምን ሙሰኛን ነው የምንደግፈው “

የካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ ታሪካዊ ተጨዋች ሳሙኤል ኤቶ የሚቀርቡበት ክሶች ሀሰተኛ መሆናቸውን ተናግሯል።

“ በሙስናና በጨዋታ ማጭበርበር ይከሱኛል “ የሚለው ሳሙኤል ኤቶ “ ነገርግን እኔ ንፁህ ሰው ነኝ መላው አፍሪካ ኤቶ ማን እንደሆነ እና ያለውን ታሪክ ያውቀዋል" በማለት ተናግረዋል።

“ እኛ አፍሪካውያን ስኬታማ ሰዎችን አንደግፍም ይልቁንም እንዋጋቸዋለን “ የሚለው ሳሙኤል ኤቶ “ እኛ የምንደግፈው ሙሰኛ እና ስኬት የሌላቸውን ነው " ሲል ወቅሷል።

“ እኛ አፍሪካዊያን የጎደለን ነገር አለ ፣ እግርኳሳችን እንዲያድግ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ እንድንሆን እፈልጋለሁ።“ ኤቶ

“ ነገርግን የአፍሪካ እግርኳስ እንዲያድግ የማይፈልጉ በማይገባቸው ቦታ ላይ የተቀመጡ ሙሰኞች አሉን የሚጨነቁት ስለ ገንዘብ እና ኪሳቸው ብቻ ነው።“ ሲል ኤቶ ተናግሯል።

ሳሙኤል ኤቶ አያይዞም አፍሪካ ውስጥ ለሀገራቸው እግርኳስ እያደረጉ በሚገኙት ትልቅ ስራ ለሞሮኮ ፣ ሴኔጋል እና ሞሪታንያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶች ትልቅ ክብር አለኝ በማለት ተናግሯል።

ሳሙኤል ኤቶ ከዚህ በፊት በጨዋታ ማጭበርበር ፣ አካላዊ ጥቃት በማድረስ ፣ ሁከት በማነሳሳት እና የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ተከሶ ምርመራ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
አዲስ ዓመት፣ አዲስ ፍልሚያ!

🇪🇹 ዋናው ስፖርት አጋር ክለቦቹን እንኳን ለአዲሱ የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የውድድር ዘመን በሰላም አደረሳችሁ ይላል።

🇪🇹 የእናንተን የአጋሮቻችንን የእግር ኳስ ብቃት በሜዳ ላይ ለማሳየት የሚያግዙ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የስፖርት ትጥቆችን ለማቅረብ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑንም ዋናው ለማሳወቅ ይወዳል።

⚽️ መልካም የውድድር ዓመት! ⚽️

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሊዮኔል ሜሲ የፕሮዳክሽን ተቋም ከፈተ !

የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ " 525 Rosario " የተባለ የራሱን የፕሮዳክሽን ተቋም ማቋቋሙ ይፋ ተደርጓል።

የኢንተር ሚያሚው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ የፕሮዳክሽን ተቋሙን " 525 Rosario “ በማለት በትውልድ ስፍራው መታሰቢያ አድርጎ መሰየሙ ተገልጿል።

ሊዮኔል ሜሲ የከፈተው የፕሮዳክሽን ተቋም በቤተሰብ ጉዳይ ፣ በቲቪ ሾው ፣ ፊልም እና ስፖርት ውድድሮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተነግሯል።

“ ሜዳ ላይም ሆነ ከሜዳ ውጪ ለመዝናኛ ልዩ ፍቅር ነበረኝ “ ሲል ሊዮኔል ሜሲ በአዲሱ ተቋሙ መቋቋም ዙሪያ አስተያየቱን ሰጥቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ኤንድሪክ በቀጣይ ቋሚ ይሆናል “ ካርሎ አንቾሎቲ

የሪያል ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የቡድናቸው ወቅታዊ አቋም ጥሩ የሚባል ባይሆንም ገና የውድድር አመቱ መጀመሪያ በመሆን ሀሳብ እንደማይገባቸው ገልጸዋል።

“ ምርጡ አቋማችን ላይ እንዳልሆንን አውቃለሁ “ ያሉት አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ነገርግን በዚህ የአመቱ መጀመሪያ የተለመደ ነው በቀጣይ ወራት ምርጥ አቋማችን ላይ እንሆናለን አሁንም ጥሩ ነን “ ብለዋል።

“ ኢንድሪክ በሚቀጥሉት ጨዋታዎች በአንዱ ቋሚ ሆኖ ይጀመራል በቀጣይም ቋሚ ተሰላፊ ይሆናል ፣ እሱ ብዙ የሚሰራ ትንሽ የሚናገር ትሁት ልጅ ነው እንደዚህ አይነት ተጨዋች እወዳለሁ።" ካርሎ አንቾሎቲ

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ አያይዘውም በጉዳት ላይ የሚገኘው ካማቪንጋ በሚቀጥለው ሳምንት ከቡድኑ ጋር መስራት እንደሚጀምር ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ከሲቲ ጋር ሊወዳደር የሚችል ክለብ የለም “ ጉንዶጋን

ጀርመናዊው የማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢልካይ ጉንዶጋን በአሁኑ ሰዓት በአለም ምርጡ ቡድን ውስጥ በመጫወት ላይ እገኛለሁ በማለት ተናግሯል።

“ በአሁን ሰዓት በአለም ምርጥ በሆነው ክለብ ውስጥ በመጫወት ላይ እገኛለሁ ፣ ከማንችስተር ሲቲ ጋር መወዳደር የሚችል ክለብ አለ ብዬ አላስብም።“ ሲል ኢልካይ ጉንዶጋን ተናግሯል።

" ሚኬል አርቴታ ከፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ሰርቷል እናም ጋርዲዮላ በእሱ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥሯል ፣ እኔም አሰልጣኝ ከሆንክ ተመሳሳይ ይሆናል።" ጉንዶጋን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሬስ ጄምስ ወደ ሜዳ ይመለሳል ?

የሰማያዊዎቹ የኋላ መስመር ተጨዋች ሬስ ጄምስ ወደ ሜዳ የሚመለስበት ጊዜ መዘግየቱን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ገልጸዋል።

“ ዋናው ነገር ሬስ ጄምስ መቶ ፐርሰንት ተሽሎት መመለሱ ነው የማገገሚያ ጊዜው ትንሽ ዘግይቷል ፣ አሁንም ዝግጁ አይደለም “ ሲሉ ኢንዞ ማሬስካ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ማሎ ጉትሶ በጉዳት ምክንያት የዌስትሀም ዩናይትድ ጨዋታ እንደሚያመልጠው ተገልጿል።

አሰልጣኙ አያይዘውም ኢንዞ ፈርናንዴዝ እና ዴውስቡሪ ሀል ወደ ሜዳ መመለሳቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኬቨን ዴብሮይን ለአርሰናል ጨዋታ ይደርሳል ? የማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ተጫዋች የሆነው ኬቨን ዴብሮይን በትላንት ምሽቱ ጨዋታ ባጋጠመው ጉዳት ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል። አሰልጣኝ ፔፕ ጋርድዮላ ለአርሰናል ጨዋታ ስለ መድረሱ ሲናገሩ “ አላውቅም ፣ የበለጠ መረጃ ዛሬ ይኖረኛል “ ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል። የክለቡ የህክምና ባመለሙያዎች ኬቨን ዴብሮይን በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን መቀጠል እንደማይችል…
ዴብሮይን ለአርሰናል ጨዋታ ሊደርስ ይችላል !

የማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ተጫዋች የሆነው ኬቨን ዴብሮይን እሁድ ከአርሰናል ጋር በሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ ሊደርስ እንደሚችል አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ገልጸዋል።

“ ዛሬ ከሰሞኑ የተሻለ ስሜት ላይ ነው ነገርግን ነገ ልምምድ አለን የሚሆነውን እናያለን “ ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

ኬቨን ዴብሮይን ማንችስተር ሲቲ ከኢንተር ሚላን ባደረገው ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይሮ መውጣቱ አይዘነጋም።

ማንችስተር ሲቲ ከ አርሰናል የሚያደርጉት ተጠባቂ መርሐ ግብር እሁድ 12:30 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አርሰናል ምርጥ ቡድን ነው “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ አርሰናል ጥሩ ነገሮች ስናገር " የጭንቅላት ጨዋታ ነው " እባላለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

የእሁዱ ተጋጣሚያቸው አርሰናል “ ጥሩ ቡድን ነው ጥሩ ተጨዋቾች አሏቸው በየአመቱ እየተሻሻሉ እየመጡ ነው።“ ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ገልጸዋል።

“ ስለ አርሰናል ጥሩ ነገር ስናገር የጭንቅላት ጨዋታ እየተጫወተ ነው ወይም ሌላ ነገር ነው የምባለው እኔ የጭንቀት ጨዋታ ላይ ጥሩ አይደለሁም።“ ጋርዲዮላ

ቡድናቸው ከአርሰናል ጋር ሲጫወት “ ሳሊባ እና ጋብሬል ሁልጊዜም ትኩረታቸው ኤርሊንግ ሀላንድ ብቻ ነው “ ሲሉ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

“ አንድ ለአንድ አይደለም ሀለት ለአንድ ነው አንዳንዴም ሶስት ለአንድ ነው “ ሲሉ አጥቂያቸው ላይ ትኩረት መደረጉን ያስረዱት አሰልጣኙ " ለዚህ ነው እነሱን ማጥቃት ከባድ የሚሆነው።" ብለዋል።

ራሂም ስተርሊንግ በእኔ አሰልጣኝነት ታሪክ በጣም አስፈላጊው ተጨዋች ነው ከአርሰናል ጋር ምርጡ እንዲገጥመው እመኝለታለሁ ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ጨምረው ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በሮድሪ አስተያየት አልስማማም “ ጋርዲዮላ

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ሮድሪ በማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል መካከል የአስተሳሰብ ልዩነት እንዳለ መናገሩን እንደማይስማሙበት ገልጸዋል።

ሮድሪ ከዚህ በፊት " ከአርሰናል ጋር ያለን ልዩነት የአስተሳሰብ ነው ፣ እዚህ በመጡበት ወቅት እኛን ማሸነፍ እንደማይፈልጉ ተሰምቶኛል አቻ ነበር የፈለጉት እኛ እንደዚህ አናስብም " ብሎ ነበር።

" ሮድሪ በእኛ እና አርሰናል መካከል ያለው ልዩነት የአስተሳሰብ ነው ብሎ በተናገረው ንግግር በፍጹም አልስማማም “ ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 01:27:34
Back to Top
HTML Embed Code: