Telegram Web Link
“ ከእኛ ጋር መጫወት ቀላል አይደለም “ ቫን ዳይክ

ኔዘርላንዳዊው የሊቨርፑል የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቨርጅል ቫን ዳይክ ከቡድናቸው ጋር መጫወት ቀላል አለመሆኑን ተናግሯል።

ከሽንፈት መልስ ቡድኑ ባሳየው እንቅስቃሴ መደሰቱን የገለፀው ቨርጅል ቫንዳይክ “ በተመዘገበው ድል በጣም ተደስቻለሁ “ ሲል ተደምጧል።

ቨርጅል ቫን ዳይክ አክሎም ከሊቨርፑል ጋር መጫወት ለማንም በጭራሽ ቀላል አይሆንም በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮማ አሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲን አሰናበተ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ሮማ አሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲን ከክለቡ አሰልጣኝነት ማሰናበቱን በይፋ አስታውቋል።

አሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲ ሮማን እየመራ በዚህ አመት ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለ ሲሆን በአንዱ ተሸንፎ በሶስቱ አቻ ተለያይቷል።

በክለቡ አስራ ስምንት ዓመታትን በተጫዋችነት ያሳለፈው ዳንኤል ዲ ሮሲ ባለፈው አመት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆን ተክቶ ሮማን መረከቡ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንቶኒ ማርሻል ወደ ግሪክ አምርቷል !

ፈረንሳዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ማርሻል የግሪኩን ክለብ ኤኢኬ አቴንስ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

የ 28ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ማርሻል ለግሪኩ ክለብ ኤኢኬ አቴንስ እስከ 2027 የሚቆይ የሶስት አመት ውል መፈረሙ ተገልጿል።

አንቶኒ ማርሻል ከስምንት አመታት በኋላ በአመቱ መጨረሻ ውሉ ሲጠናቀቅ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር መለያየቱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የቀድሞ ጣልያናዊ ተጨዋች ሆስፒታል ገባ ! የቀድሞ ጣልያናዊ የጁቬንቱስ እና ኢንተር ሚላን የፊት መስመር ተጨዋች ቶቶ ስኪላቺ ሆስፒታል መግባቱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን አስነብበዋል። የቀድሞ ተጨዋቹ በቅርቡ ከካንሰር ህመም ጋር በተገናኘ ሁለት ጊዜ ቀዶ ጥገና አድርጎ እንደነበር ሲገለፅ አሁን ላይ ሆስፒታል በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆኑ ተነግሯል። ሳልቫቶር ቶቶ ስኪላቺ ጣልያን ሶስተኛ ደረጃን ይዛ…
የቀድሞ ጣልያናዊ ተጨዋች ህይወቱ አለፈ !

የቀድሞ ጣልያናዊ የጁቬንቱስ እና ኢንተር ሚላን የፊት መስመር ተጨዋች ቶቶ ስኪላቺ በ 59ዓመቱ ህይወቱ ማለፉን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ከካንሰር ህመም ጋር በተገናኘ ሁለት ጊዜ ቀዶ ጥገና አድርጎ እንደነበር የተገለፀው የቀድሞ ተጨዋቹ በቅርቡ ሆስፒታል በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆኑ ተነግሮ ነበር።

ሳልቫቶር ቶቶ ስኪላቺ ጣልያን ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ባጠናቀቀችበት የ 1990 አለም ዋንጫ ውድድር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 146,000 Birr
•512GB = 156,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 114,000 Birr
•512GB = 126,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
🙏🏽 ከሳፋሪኮም ወደ ቴሌ መደወል ቀላል ነው! እነዚህን የድምፅ ጥቅሎች እየተጠቀምን ከ07 ➡️ 09 መስመር እንደዋወል! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቦታችንን
https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
“ ሀገራችን ላይ ያሉ ተጫዋቾች ጥሩ ደረጃ ላይ አይገኙም “ አሰልጣኝ ገ/መድን ኃይሌ

“ ከሜዳ ውጪ እየተጫወቱ ውጤት መጠበቅ ከባድ ነው “

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ገብረ መድን ኃይሌ ዋልያዎቹ ከቀናት በፊት ባደረጓቸው ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዙሪያ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

“ ከነበሩን ተጋጣሚዎች ጋር በፊፋ ደረጃ ርቀት አለን ይህ ልዩነታችንን ያሳያል ፤ በብዙ ነገር ሲመዘን ልዩነቶች አሉ።“ ሲሉ አሰልጣኝ ገ/መድን ኃይሌ ገልጸዋል።

“ ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች ብዙ የግብ እድሎችን እያባከንን ነው ሁነኛ ዘጠኝ ቁጥር ተጫዋች የለንም። “ አሰልጣኝ ገ/መድን ኃይሌ

አክለውም “ ተጫዋቾች በሚፈለገው የአካል ብቃት ደረጃ ላይ አይገኙም ነበር “ ያሉት አሰልጣኙ “ ከሜዳ ውጪ እየተጫወቱ ውጤት መጠበቅ ከባድ ነው የሚሆነው “ ብለዋል።

ስለ ወደፊት ቆይታቸው ያነሱት አሰልጣኝ ገ/መድን ኃይሌ “ በቅርቡ ኮንትራቴ ይጠናቀቃል ጊዜው ሲደርስ ይፋ ይደረጋል።“ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ አሁንም በቀጣይ ጨዋታዎች ያለንን አቅም አሟጠን እንጠቀማለን ከሜዳ ውጪ እየተጫወቱ ከፍተኛ ውጤት ማምጣት ከባድ ነው።“ አሰልጣኝ ገ/መድን

“ ወደ ሀላፊነት የመጣሁበት ጊዜ ጥሩ አይደለም “ ሲሉ ሀሳባቸውን የሰጡት አሰልጣኙ “ ሀገራችን ላይ ያሉ ተጫዋቾች ጥሩ ደረጃ ላይ አይገኙም።“ ብለዋል።

በሁለት ሀላፊነት እስከ መቼ ትቀጥላለህ ? የሚል ጥያቄ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው አሰልጣኝ ገ/መድን ኃይሌ “ ለብሔራዊ ቡድንም ሆነ ለክለብ መስራት ሰልችቶኛል “ ሲሉ መልሰዋል።

በሁለት ሀላፊነት መስራትን “ ከድካም ውጪ ምንም ያገኘሁበት ነገር የለም “ ያሉት አሰልጣኙ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለኢትዮጵያ ለማገልገል ግን ዝግጁ ነኝ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሲቲን ለማሸነፍ ሁሉንም እንሰጣለን “ ዊሊያም ሳሊባ

የመድፈኞቹ የኋላ መስመር ተጨዋች ዊሊያም ሳሊባ በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲን ለማሸነፍ ያላቸውን እንደሚሰጡ ገልጿል።

“ የአለም ምርጡ ተከላካይ ለመሆን መንገድ ላይ ነኝ “ የሚለው ዊሊያም ሳሊባ “ አሁን ከምርጦቹ አንዱ ነኝ ብዬ አስባለሁ ፤ አሁን የሚቀረኝ ዋንጫ ማሸነፍ ብቻ ነው “ ብሏል።

የአለም ምርጥ ለመባል ዋንጫ ማሸነፍ አስፈላጊ ነው ብሎ እንደሚያምን የሚናገረው ተጨዋቹ “ በቀጣይ አላማዬ ዋንጫ ነው “ ሲል ተናግሯል።

ሳሊባ አክሎም ቡድናቸው ባለፉት ሁለት አመታት እንዳደረግነው አሁንም ማንችስተር ሲቲን መፎካከር እንደሚፈልግ ገልፆ ነገርግን የበለጠ መስራት እንደሚጠበቅበት አሳስቧል።

“ ሲቲን ብቻ ለማሸነፍ ሳይሆን ሁሉንም ለማሸነፍ ማሰብ አለብን “ ሲል አያይዞ ያሳሰበው ተጨዋቹ “ እሁድ ማሸነፍ እንፈልጋለን ሁሉንም እንሰጣለን ነገርግን የመጨረሻው ጨዋታ አይደለም “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ተጨዋቾቹ ልምምድ ሰርተዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ወሳኝ ተጨዋቾች ቡካዩ ሳካ ፣ ሪካርዶ ካላፊዮሪ እና ዴክላን ራይስ በዛሬው ዕለት ልምምድ መስራታቸው ተገልጿል።

ኖርዌያዊው አማካይ ማርቲን ኦዴጋርድ ፣ አሌክሳንደር ዚንቼንኮ ፣ ሚኬል ሜሪኖ ፣ ቶሚያሱ እና ቴርኔ በቡድኑ ልምምድ አለመሳተፋቸው ተነግሯል።

መድፈኞቹ በነገው ዕለት በሻምፒየንስ ሊጉ ከአታላንታ እንዲሁም እሁድ በሊጉ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ተጠባቂ ጨዋታዎቻቸውን ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፒኤስጂ በርካታ ተከታዮቹን ማጣቱ ተገለጸ !

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ የሊዮኔል ሜሲ ፣ ኔይማር እና ኪሊያን ምባፔን መልቀቅ ተከትሎ በርካታ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተከታዮችን ማጣቱ ተገልጿል።

ፒኤስጂ ካለፈው አመት ወዲህ 10 ሚልዮን የሚጠጉ የኢንስታግራም ማህበራዊ ትስስር ገፅ ተከታዮቹን ማጣቱ ተነግሯል።

በተጨማሪም ከተጨዋቾቹ መልቀቅ በኋላ የክለቡ ማልያ ሽያጭ በእጅጉ መቀነሱ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጥቁር ሰማያዊዎቹ ወደ ኢትሃድ ያቀናሉ!
በቻምፒየንስ ሊጉ አዲስ ፎርማት ለዋንጫ የሚጠበቁት ሲቲዎች ኢንተር ሚላንን በሜዳቸው ይገጥማሉ።
በየሊጋቸው ያልተሸነፉት ሁለቱም ክለቦች 3 ነጥቡን የራስ ለማድረግ ይፋለማሉ።
በጨዋታው ቀድሞ ማን ግብ ያስቆጥራል?
አሁኑኑ Betika.et ላይ ይወራረዱ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ለቸኮለ ከ #ዋናው መላ አለ!

🏃🏾‍♂ #ይምጡ#ትጥቅዎን ይውሰዱ!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
“ አርሰናልን በደንብ አጥንተናል “ ሲያድ ኮላሲናች

ቦስኒያዊው የአታላንታ የመስመር ተከላካይ ሲያድድ ኮላሲናች ነገ በሻምፒየንስ ሊጉ የቀድሞ ክለቡ አርሰናልን ለመግጠም ጥሩ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጿል።

“ አርሰናል ሰሜን ለንደን ደርቢን አሸንፎ ነው የመጣው ጥሩ ተጨዋቾች እና ጠንካራ የተከላካይ ክፍል አላቸው “ ሲል ሲያድ ኮላሲናች ተናግሯል።

“ ይሁን እንጂ ለነገው ጨዋታ በደንብ ተዘጋጅተናል “ የሚለው ሲያድ ኮላሲናች “ አርሰናልን በደንብ አጥንተነዋል “ ብሏል።

“ የቀድሞ የቡድን አጋሮቼን ላገኝ በመሆኑ ተደስቻለሁ ፤ አርቴታ ምርጥ አሰልጣኝ ነው እዛ ጥሩ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል ፤ የእንግሊዝ ክለብ መግጠም አስቸጋሪ ነው ግን በደንብ ተዘጋጅተናል።“ ሲያድድ ኮላሲናች

@tikvahethsport         @Kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጨዋቾቹ ወደ ልምምድ ተመልዋል !

ማንችስተር ዩናይትድ በጉዳት ላይ የነበሩ ተጨዋቾቹ ከጉዳታቸው በማገገም ወደ ቡድን ልምምድ መመለሳቸውን አስታውቋል።

ክለቡ ዛሬ ባደረገው መደበኛ ልምምድ የፊት መስመር አጥቂው ራስሙስ ሆይሉንድ እና ሜሰን ማውንት መካፈላቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ የሊግ መርሐግብሩን ቅዳሜ ከክሪስታል ፓላስ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሮማ አሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲን አሰናበተ ! የጣልያን ሴርያው ክለብ ሮማ አሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲን ከክለቡ አሰልጣኝነት ማሰናበቱን በይፋ አስታውቋል። አሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲ ሮማን እየመራ በዚህ አመት ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለ ሲሆን በአንዱ ተሸንፎ በሶስቱ አቻ ተለያይቷል። በክለቡ አስራ ስምንት ዓመታትን በተጫዋችነት ያሳለፈው ዳንኤል ዲ ሮሲ ባለፈው አመት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆን…
ሮማ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ !

አሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲን በዛሬው ዕለት በይፋ ከሀላፊነት ያሰናበተው የጣልያን ሴርያው ክለብ ሮማ አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት ሾመዋል።

ሮማ በአሰልጣኝ ዲ ሮሲ ምትክ የቀድሞ የቶሪኖ አሰልጣኝ የነበሩትን አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች በአንድ አመት ኮንትራት በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች በቅርቡ ቶሪኖን እየመሩ ከሮማ ጋር ከነበራቸው ጨዋታ አስቀድሞ ምክትል አሰልጣኛቸውን ልከው በድብቅ የሮማን ልምምድ ሲሰልሉ ተይዘው ነበር።

አሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲ ዛሬ ጠዋት ከምክትል አሰልጣኛቸው ጋር ቡድኑን ልምምድ ለማሰራት በዝግጅት ላይ እያሉ በሮማ ባለቤቶች ተጠርተው መባረራቸው እንደተነገራቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማርቲን ኦዴጋርድ ጉዳት መጠን ምን ያህል ነው ?

ኖርዌያዊው የመድፈኞቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ኦዴጋርድ ያጋጠመው ጉዳት ከባድ መሆኑን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገልጸዋል።

“ ማርቲን ኦዴጋርድ በተደረገለት ምርመራ ጉዳት ከበድ ያለ መሆኑ ታውቋል ለተወሰነ ጊዜ እናጣዋለን “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

ማርቲን ኦዴጋርድ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ እስከ ሁለት ወራት ጊዜ ሊወስድበት እንደሚችል ተዘግቧል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አያይዘውም ቡካዩ ሳካ እና ሪካርዶ ካላፊዮሪ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውን እና ለጨዋታ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፎች !

4:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ኢንተር ሚላን

4:00 ፒኤስጂ ከ ጂሮና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሀላንድ እያደረገ ያለውን ነገር አርሰናል ላይ ሲያደርግ ማየት እፈልጋለሁ “ ጆን ኦቢ ሚኬል

የቀድሞ ናይጄሪያዊ የቼልሲ ተጨዋች ጆን ኦቢ ሚኬል ኤርሊንግ ሀላንድ እያሳየ የሚገኘውን አቋም በትልቅ ጨዋታዎች መድገም እንዳለበት ገልጿል።

“ ሀላንድ በትልቅ ጨዋታዎች ከውድድር አመቱ መጀመሪያ ጀምሮ እያደረገ ያለውን ነገር ሲደግም ማየት እፈልጋለሁ ፤ እሁድ በአርሰናል ጨዋታ መድገም አለበት “ ሲል ጆን ኦቢ ሚኬል ተናግሯል።

“ ተጨዋች የሚለካው በትልቅ ጨዋታዎች ነው ፤ ሀላንድ የጎል ማሽን ነው ነገርግን ባለፈው አመት በትልቅ ጨዋታዎች ጠፍቶ ነበር “ ጆን ኦቢ ሚኬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 19:26:01
Back to Top
HTML Embed Code: