Telegram Web Link
እረፍት

ማንችስተር ሲቲ 0-0 ኢንተር ሚላን

ፒኤስጂ 0-0 ጂሮና

ክለብ ብሩጅ 0-0 ዶርትመንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬቨን ዴብሮይን ጉዳት አጋጥሞታል !

ማንችስተር ሲቲ ከኢንተር ሚላን ጋር እያደረገ በሚገኘው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ኬቨን ዴብሮይን ጉዳት አጋጥሞታል።

ተጨዋቹ ከኢንተር ሚላን ግብ ጠባቂ ያን ሶመር ጋር ከነበረ ግጭት በኋላ በፊል ፎደን ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል።

ማንችስተር ሲቲዎች የፊታችን እሁድ ከአርሰናል ጋር ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ አለባቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
67 '

ማንችስተር ሲቲ 0-0 ኢንተር ሚላን

ፒኤስጂ 0-0 ጂሮና

ክለብ ብሩጅ 0-0 ዶርትመንድ

ኮቬንትሪ 1-0 ቶተንሀም ( ሊግ ካፕ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
77 '

ማንችስተር ሲቲ 0-0 ኢንተር ሚላን

ፒኤስጂ 0-0 ጂሮና

ክለብ ብሩጅ 0-1 ዶርትመንድ

ጊቴንስ

ኮቬንትሪ 1-0 ቶተንሀም ( ሊግ ካፕ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88 '

ማንችስተር ሲቲ 0-0 ኢንተር ሚላን

ፒኤስጂ 0-0 ጂሮና

ክለብ ብሩጅ 0-2 ዶርትመንድ

                    ጊቴንስ

ኮቬንትሪ 1-1 ቶተንሀም ( ሊግ ካፕ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 '

ፒኤስጂ 1-0 ጂሮና

ጋዛኒጋ ( በራስ ላይ )

ማንችስተር ሲቲ 0-0 ኢንተር ሚላን

ክለብ ብሩጅ 0-2 ዶርትመንድ

                      ጊቴንስ

ኮቬንትሪ 1-2 ቶተንሀም ( ሊግ ካፕ )

አሳንቴ ስፔንስ
ጆንሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCL

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ ፒኤስጂ እና ዶርትመንድ ሲያሸንፉ ማንችስተር ሲቲ በኢንተር ሚላን ነጥብ ተጋርተዋል።

ማንችስተር ሲቲ በሜዳቸው ከኢንተር ሚላን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ፒኤስጂ ከጂሮና ያደረገውን ጨዋታ የጂሮናው ግብ ጠባቂ ጋዛኒጋ በመጨረሻው ደቂቃ በራሱ ግብ ላይ ባስቆጠረው ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስት ነጥቡን አሳክቷል።

የአምናው የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚ ቦርስያ ዶርትመንድ በበኩሉ ከክለብ ብሩጅ ተጫውቶ ከጊቴንስ 2x እና ሴርሁ ጉራሲ ግቦች 3ለ0 አሸንፏል።

በሌላ ጨዋታ ሴልቲክ ስሎቫን ብራቲስላቫን 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኬቨን ዴብሮይን ጉዳት አጋጥሞታል ! ማንችስተር ሲቲ ከኢንተር ሚላን ጋር እያደረገ በሚገኘው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ኬቨን ዴብሮይን ጉዳት አጋጥሞታል። ተጨዋቹ ከኢንተር ሚላን ግብ ጠባቂ ያን ሶመር ጋር ከነበረ ግጭት በኋላ በፊል ፎደን ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል። ማንችስተር ሲቲዎች የፊታችን እሁድ ከአርሰናል ጋር ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ አለባቸው። @tikvahethsport    …
ኬቨን ዴብሮይን ለአርሰናል ጨዋታ ይደርሳል ?

የማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ተጫዋች የሆነው ኬቨን ዴብሮይን በትላንት ምሽቱ ጨዋታ ባጋጠመው ጉዳት ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርድዮላ ለአርሰናል ጨዋታ ስለ መድረሱ ሲናገሩ “ አላውቅም ፣ የበለጠ መረጃ ዛሬ ይኖረኛል “ ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

የክለቡ የህክምና ባመለሙያዎች ኬቨን ዴብሮይን በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን መቀጠል እንደማይችል ለአሰልጣኙ መናገራቸው ተገልፆል።

ኬቨን ዴብሮይን በእግር ኳስ ህይወቱ 27ኛ ጉዳቱ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን 2023/24 4️⃣1️⃣ ጨዋታዎች በጉዳት አምልጠውታል።

ማንችስተር ሲቲ ከ አርሰናል የሚያደርጉት ተጠባቂ መርሐ ግብር እሁድ 12:30 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አስደናቂ ቡድን ነን “ ፔፕ ጋርዲዮላ

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ትላንት ምሽት በኢንተር ሚላን ጨዋታ ላይ ያሳየው እንቅስቃሴ እንደወደዱት ገልፀዋል።

“ ጥሩ ተጫውተናል “ ያሉት ጋርዲዮላ “ ቡድኔን እወደዋለሁ ፣ አስደናቂ ቡድን ነን “ በማለት የቡድን ስብስባቸውን አወድሰዋል።

ተጋጣሚያቸውን ኢንተር ሚላንን “ በመከላከል የተወጣለት ቡድን “ በማለት ገልፀውታል።

በተከታታይ ጨዋታዎች በእረፍት ሰዓት እያደረጉ ስለሚገኙት ሁለት ቅያሪዎች ሲናገሩም “ ይህ አዲሱ የፔፕ ዘይቤ ነው ፣ በአርሰናል ጨዋታም ላይ ትመለከቱታለችሁ “ ብለዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ተጨዋቾቼ ከአምናው የተሻለ የማድረግ ብቃት አላቸው “ አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ባለፈው አመት በሻምፒየንስ ሊግ ካስመዘገበው ውጤት የተሻለ የማስመዝገብ ብቃት አለው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

“ ጥሩ ነገር የመስራት ብቃቱ አለን “ ያሉት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በእርግጠኝነት ትልቅ የተጨዋቾች ጥራት አለን ይህንን ማረጋገጥ አለብን ብለዋል።

መድፈኞቹ ባለፈው የውድድር ዘመን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ከአመታት በኋላ እስከ ሩብ ፍፃሜ መጓዛቸው አይዘነጋም።

ቡድናቸው ባለፈው አመት ለአመታት አስቸጋሪ ሆኖበት የነበረውን ሩብ ፍፃሜ ማሳካቱን ያስታወሱት አሰልጣኙ “ ነገርግን ይህ አላረካንም በዚህ አመት የበለጠ ነው የምንፈልገው “ ብለዋል።

“ ከአታላንታ ጋር መጫወት በጣም አስቸጋሪ ነው ፣ የአሰልጣኝ ጋስፔሪኒ አድናቂ ነኝ በአታላንታ እና ሌሎች ክለቦች ድንቅ ነገር ነው የሰሩት። “ አርቴታ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሊቢያ ሊግ የተሳታፊ ክለቦች ቁጥሩን ከፍ አደረገ !

የሊቢያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሀገሪቱ ፕርሚየር ሊግ ተወዳዳሪ ክለቦች ቁጥር ከሀያ አንድ ወደ ሰላሳ ስድስት ከፍ እንዲል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል።

ይህ የሀገሪቱ እግርኳስ ጠባቂ አካል ውሳኔ የሊቢያ ፕርሚየር ሊግን በርካታ ተወዳዳሪ ክለቦች ያሉት የአለም ትልቁ ሊግ እንደሚያደርገው ተገልጿል።

የሊቢያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው ለታዳጊዎች እድል ለመስጠት ፣ ተወዳዳሪነቱን ለመጨመር እንዲሁም ትንንሽ ክለቦች ራሳቸውን በሀገሪቱ ትልቅ ሊግ እንዲያሳዩ ያለመ ነው ተብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ከማድሪድ ጨዋታ በኋላ ፊቴ በጋዜጦች ላይ ይሆናል “ አሰልጣኝ ማኖሎ ጎንዛሌዝ

የእስፓኞሉ ዋና አሰልጣኝ ማኖሎ ጎንዛሌዝ ቡድናቸው ቅዳሜ ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚያደርገውን ተጠባቂ የላሊጋ ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

“ ከቅዳሜው የሪያል ማድሪድ ጨዋታ በኋላ ፊቴ በሁሉም ጋዜጦች ላይ ይሆናል “ ሲሉ ለድል መዘጋጀታቸውን አሰልጣኝ ማኖሎ ጎንዛሌዝ ተናግረዋል።

በውድድር አመቱ ተከታታይ ሁለተኛ ድላቸውን ያስመዘገቡት አሰልጣኝ ማኖሎ ጎንዛሌዝ “ ሳንቲያጎ በርናቦ ላይ እንደምናሸንፍ እርግጠኛ ነኝ “ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የምንጫወተው ለማሸነፍ ነው " ጋስፔሪኒ

የጣልያኑ ክለብ አትላንታ ዋና አሰልጣኝ ጂያን ፔሮ ጋስፔሪኒ የዛሬውን የአርሰናል ጨዋታ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ገልጸዋል።

“ አታላንታ ሁልጊዜም የሚጫወተው ለማሸነፍ ነው “ ያሉት አሰልጣኝ ጂያን ፔሮ ጋስፔሪኒ በዛሬው ጨዋታም ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንገባለን ብለዋል።

“ አርሰናል የተዋሃደ እና የተደራጀ የምወደው ቡድን ነው ውጤታቸው በራሱ ይናገራል ፣ አርቴታን በግል ባላውቀውም እንደ አሰልጣኝ ትልቅ ክብር አለኝ ለማየት የሚስብ ቡድን ሰርቷል።“ ጂያን ፔሮ ጋስፔሪኒ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ የፊፋ ደረጃቸው ዝቅ አለ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን " ዋልያዎቹ " በፊፋ ወርሀዊ የብሔራዊ ቡድኖች ደረጃ ሰንጠረዥ በሁለት ደረጃዎች ዝቅ ብለዋል።

ዋልያዎቹ ባለፉት ወርሀዊ ደረጃዎች ከነበሩበት 143ኛ ደረጃ በሁለት ደረጃዎች ዝቅ ብለው 145ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች በአንዱ ተሸንፎ በአንዱ አቻ መለያየቱ ይታወሳል።

በፊፋ ወርሀዊ ደረጃ ከአፍሪካ ሞሮኮ ፣ ሴኔጋል ፣ ግብፅ ፣ ኮትዲቫር እና ቱኒዚያ በተከታታይ ከአንድ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

የወቅቱ የአለም ሻምፒዮን አርጀንቲና በፊፋ ወርሀዊ ደረጃ አንደኝነት ደረጃዋን አስጠብቃለች።

ኳታር አስር ደረጃዎችን ዝቅ በማለት ቀዳሚ ሀገር ስትሆን ሳሞኣ ሰባት ደረጃዎችን ከፍ በማለት ቀዳሚ ሀገር መሆን ችላለች።

ኤርትራ በፊፋ ወርሀዊ ደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ ሳትካተት ቀርታለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሻምፒየንስ ሊጉን ማሸነፍ እንችላለን “ ሀንሲ ፍሊክ

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ቡድናቸው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ እንደሚችል ተናግረዋል።

“ ከምርጥ ቡድኖች ጋር ለመፋለም ዝግጁ ነን “ ያሉት አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ “ ሻምፒየንስ ሊጉን ማሸነፍ እንችላለን ፣ ባርሴሎና ውስጥ ለሁሉም ዋንጫዎች መፋለም አለብህ “ ብለዋል።

ባርሴሎና የመጀመሪያ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት 4:00 ከሜዳው ውጪ ከሞናኮ ጋር ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 146,000 Birr
•512GB = 156,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 114,000 Birr
•512GB = 126,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
🤩የቤቲካ ምርጥ የቀኑ 5 አሸናፊዎች ! 🤩
🌟ደንበኞቻችን ተወራርደው በትልቁ አሸንፈዋል !
🥁ቀጣዩ የእናንተ ተራ ነው !
🌟አሁኑኑ Betika.et ላይ ይወራረዱ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
ሲቲ ከሁሉም ውድድሮች ሊባረር ይችላል !

ማንችስተር ሲቲ በቀረበበት 1️⃣1️⃣5️⃣ የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰት ክሶች ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ከባድ ቅጣት ሊጠብቀው እንደሚችል ቴሌግራፍ አስነብቧል።

ማንችስተር ሲቲ ጥፋተኛ ከተባለ ከእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨምሮ ከሁሉም ከሚካፈልባቸው ውድድሮች ሊባረር እንደሚችል ተነግሯል።

የማንችስተር ሲቲ የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰት ክስ ጉዳይ ባለፈው ሰኞ ጀምሮ መታየት መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ለሚቀጥሉት ሳምንታትም እንደሚቀጥል ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 21:39:31
Back to Top
HTML Embed Code: