Telegram Web Link
“ ደጋፊዎቻችንን ለማስደሰት አቅም አለን “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ያለበትን የጉዳት ሁኔታ ተቋቁሞ ወሳኝ ድል በማሳካቱ እንደተደሰቱ ገልጸዋል።

“ ደጋፊዎቻችንን ለማስደሰት አቅም አለን “ ያሉት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ያንን አሳክተናል ብዬ አስባለሁ ካለው ሁኔታ ጋር ለመላመድ ብንቸገርም ወድጄዋለሁ በማለት ተናግረዋል።

" ሰበብ ከማብዛት ፈተናውን ተጋፍጠነው በጀግንነት ተጫውተናል ፣ ለተከታታይ ሶስት አመት እዚህ መጥተን አሸንፈናል ፣ በቀጣይ ትልቅ ሳምንት እየመጣ ነው ለዛም ብርታት ይሰጠናል።" ሚኬል አርቴታ

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በንግግራቸው ወቅት ስለ ቡካዩ ሳካ ሁኔታ እንደማያውቁ እና ምን እንደገጠመው አለመረዳታቸውን ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የስፔን ላሊጋ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብሩን ከጂሮና ጋር አድርጎ 4ለ1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ላሚን ያማል 2x ፣ ዳኒ ኦልም እና ፔድሪ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለጂሮና ስትዋኒ አስቆጥሯል።

ላሚን ያማል ባለፉት አምስት የላሊጋ ጨዋታዎች አራት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ሲችል ሶስት ግብ አስቆጥሯል።

ባርሴሎና የመጀመሪያ አምስት የሊግ ጨዋታዎችን በተጋጣሚዎቹ ላይ አስራ ሰባት ግቦችን አስቆጥሮ ማሸነፍ ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ባርሴሎና :- 15 ነጥብ
7️⃣ኛ ጂሮና :- 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ -ቪያሪያል ከ  ባርሴሎና

ቅዳሜ - ቫሌንሽያ ከ ጂሮና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ባማቸውም አላፍርም "

“ ደራርቱ ይቅርታ በመጠየቋ አዝኜባታለሁ “ ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ወቅት የአመራሮችን ድምፅ ቀርጾ ማውጣት “ ነውረኝነት ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።

“ ሰው በምሳ ሰዓቱ የፈለገውን ቢናገር ቢጫወት ምንድነው ችግሩ “ ሲሉ የጠየቁት ዶ/ር አሸብር “ ይሄንን አሁን ቁምነገር ብሎ ቀርፆ ያወጣው ሚዲያ ሊያፍር ይገባዋል እውነት ለመናገር “ ብለዋል።

“ ስትሰባሰብ በቤተሰብ መሐል መነጋገር ይኖራል መንግስትን ልታማም ትችላለህ ይሄንን ቁምነገር ብሎ መቅረፅ የኢትዮጵያን ባህል የማይመጥን ነውረኝነት ነው “ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ

“ በተፈጥሮዬ ሀሜት አልወድም እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩንም አምቻቸው ቢሆን አላፍርም የተናገርኩትን ተናግሬያለሁ ባህሪዬ ነው “ ሲሉ ዶ/ር አሸብር ይቅርታ የሚሉት ነገር አለመኖሩንም አንስተዋል።

“ ደራርቱን አዝኜባታለሁ ይቅርታ በመጠየቋ ተገቢ አይደለም “ ያሉት ዶ/ር አሸብር “ እሷ የተናገረችውን እናውቃለን አንድም ገዛኸኝ ላይ ያነጣጠረ ነገር የለም ወይም ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ነገር የለም “ ብለዋል።

የድምጽ ቅጂውን ያወጣውን ግለሰብ “ ይህንን ያደረገው ወራዳ ሰው ነው “ ሲሉ የገለፁት ዶ/ር አሸብር “ እኔ በደራርቱ ቦታ ብሆን ይቅርታ ቀርቶ ምንም አልልም “ ሲሉ ገልጸዋል።

መረጃው የሸገር ስፖርት ሬዲዮ ፕሮግራም ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናፖሊ ድል አድርጓል !

በጣሊያን ሴርያ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ናፖሊ ከካግሊያሪ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የናፖሊን የማሸነፊያ ግቦች ሮሜሉ ሉካኩ ፣ ቅቫራትሼሊያ ፣ ቦንግዮርኖ እና ጂዮቫኒ ዲ ሎሬንዞ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቤልጂየማዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሮሜሉ ሉካኩ ለናፖሊ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ሁለት ግቦች አስቆጥሮ ሁለት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ኛ ናፖሊ :- 9 ነጥብ
1️⃣9️⃣ኛ ካግሊያሪ :- 2 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

አርብ - ካግሊያሪ ከ ኢምፖሊ

ቅዳሜ - ጁቬንቱስ ከ ናፖሊ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 146,000 Birr
•512GB = 156,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 114,000 Birr
•512GB = 126,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
“ ሮናልዶ እንዴት እንዳደረገው ይገርመኛል “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ክርስቲያኖ ሮናልዶ 901 ግቦችን ማስቆጠሩ እንደሚያስገርማቸው ተናግረዋል።

“ እኔ በተጨዋችነት አስራ አንድ አመት አሳልፌ ያስቆጠርኩት አስራ አንድ ግቦች ነው “ ያሉት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ “ ሮናልዶ 901 ግቦች ሲያስቆጥር ሳይ እንዴት እንዳደረገው ይገርመኛል።"በማለት ገልጸዋል።

“ ኤርሊንግ ሀላንድ ግብ በማስቆጠር ረገድ በሊዮኔል ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ደረጃ ነው የሚገኘው የእነሱን ሪከርድ የመስበር እድል አለው።“ ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የቶተንሀም እና አርሰናል ጨዋታ :-

1ኛ. @Neba63
2ኛ. @Solagratia0
3ኛ. @U77681202

የጂሮና እና ባርሴሎና ጨዋታ :-

1ኛ. @Biruk_Baby_21
2ኛ. Abu Liyana
3ኛ. @U77681202

@tikvahethsport
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የበርንማውዝ እና ቼልሲ ጨዋታ :-

1ኛ. @U77681202
2ኛ. @Fairk7
3ኛ. @The_endxyz

የሪያል ሶሴዳድ  እና ሪያል ማድሪድ ጨዋታ :-

1ኛ. @Yohananss
2ኛ. @pavel2446
3ኛ. @Gd20ya

@tikvahethsport
“ አርሰናል በምንም ሁኔታ ማሸነፍ እንደሚችል አሳይቷል “ ቲኦ ዋልኮት

የቀድሞ እንግሊዛዊ የአርሰናል ተጨዋች ቲኦ ዋልኮት መድፈኞቹ በየትኛውም ሁኔታ ተጫውተው ማሸነፍ እንደሚችሉ ማሳየታቸውን ተናግሯል።

“ አርሰናል በምን አይነት ሁኔታ አሸነፈ የሚለው ለውጥ አያመጣም “ የሚለው ቲኦ ዋልኮት አርሰናል በምንም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ተላምዶ ማሸነፍ እንደሚችል አሳይቷል ብሏል።

አርሰናል በትላንቱ የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ እንደ ጆዜ ሞሪንሆ ቡድን አይነት ነበር የተጫወተው እስከ መጨረሻው ደቂቃ ውጤቱን ይዞ ለመውጣት መፋለም ሲል ዋልኮት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ ተጫዋቾቹ ልምምድ ሰርተዋል !

በጉዳት ላይ የነበረው እንግሊዛዊው የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም በዛሬው የቡድኑ መደበኛ ልምምድ ላይ መሳተፉ ተገልጿል።

በተጨማሪም ሌላኛው የሎስ ብላንኮዎቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦርሊየን ቹዋሜኒ በቡድኑ ልምምድ ላይ መሳተፉ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ሁለቱም ተጨዋቾች ሪያል ማድሪድ ነገ ከስቱትጋርት ጋር በሚያደርገው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ተጨዋቹ ጉዳት አጋጥሞታል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ በቀኝ እግሩ ላይ ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ በይፋ አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ እስከ አንድ ወር ጊዜ ሊወስድበት እንደሚችል ተነግሯል።

ተጨዋቹ በቀጣይ ባርሴሎና የሚያደርጋቸው ሰባት ጨዋታዎች ሊያመልጡት እንደሚችል ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ አዲስ አበባ ላይ ይደረጋል !

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰኑ ይፋ ተደርጓል።

ጉባዔው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ላይ ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ በተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መቀየሩን የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ጉባኤው አዲስ አበባ ላይ እንዲካሄድ ጥያቄ አቅርቦ በካፍ ተቀባይነት ማግኘቱን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።

በዚህም መሰረት የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በቀጣይ ጥቅምት ወር በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል።

ካፍ ዛሬ በሰጠው የቅድመ ጠቅላላ ጉባኤ ጋዜጣዊ መግለጫ የ 2024 ቻን አፍሪካ ዋንጫ በሚቀጥለው የካቲት ወር በናይሮቢ ፣ ካምፓላ እና ዳሬ ሰላም እንደሚካሄድ አሳውቋል።

የ 2024 ቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በጥቅምት እና ታህሳስ ወር ውስጥ እንደሚካሄድ ተያይዞ ተገልጿል።

ኬንያ የ 2027 የአፍሪካ ዋንጫን ከዩጋንዳ እና ታንዛኒያ ጋር በጥምረት እንደምታዘጋጅ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🌼 እስከ ጥቅምት 15 ብቻ! 🌼

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
አይታና ቦንማቲ በባርሴሎና ውሏን አራዝማለች !

ያለፈው አመት የሴቶች ባሎን ዶር አሸናፊዋ ስፔናዊ የባርሴሎና የመሐል ሜዳ ተጨዋች አይታና ቦንማቲ በክለቡ እስከ 2028 ለመቆየት ውሏን አራዝማለች።

የ 26ዓመቷ የአለም ሻምፒዮን አይታና ቦንማቲ በአዲሱ ውል መሰረት በአለም የሴቶች እግርኳስ ታሪክ ከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋች ለመሆን እንደበቃች ተገልጿል።

ተጨዋቿ ባርሴሎና ባለፈው የውድድር አመት የሀገር ውስጥ ሶስትዮሽ ዋንጫን ጨምሮ የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ሲያሳካ ወሳኝ ሚና ነበራት።

አይታና ቦንማቲ ባለፈው አመት ስኬታማ የውድድር ዘመን ማሳለፏን ተከትሎ በዚህ አመትም ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊነት ግምት ተሰጥቷታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋቾቹ ልምምድ ሰርተዋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በጉዳት ላይ የሚገኙ ተጫዋቾቹ በዛሬው ዕለት ወደ ቡድን ልምምድ መመለሳቸው ተገልጿል።

በዛሬው የሰማያዊዎቹ የቡድን ልምምድ ላይ ማሎ ጉስቶ ኢንዞ ፈርናንዴዝ እና ሮሚዮ ላቪያ መሳተፋቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ቅዳሜ ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የትኛውንም ተጋጣሚ ማሸነፍ እንችላለን “ ሞራታ

ስፔናዊው የኤሲ ሚላን የፊት መስመር ተጨዋች አልቫሮ ሞራታ ቡድናቸውም ማንኛውንም ተጋጣሚ ማሸነፍ እንደሚችል ተናግሯል።

ከነገው የሊቨርፑል ጨዋታ በፊት አስተያየቱን የሰጠው አልቫሮ ሞራታ “ እኛ ትልቅ አቅም አለን የትኛውንም ተጋጣሚ ማሸነፍ እንችላለን “ ብሏል።

የኤሲ ሚላኑ ዋና አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካ በበኩላቸው “ ሊቨርፑል ከአለም ምርጥ ቡድኖች አንዱ ነው ፣ እንደዚህ አይነት ቡድን ትንሽ ስህተት ከተሰራ እድሉን ተጠቅሞ እንደሚያስቆጥር እናውቃለን “ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሲቲ የማይቀጣ ከሆነ ሊጉ ታማኝነት ያጣል “ ዣቪየር ቴባስ

የስፔን ላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ማንችስተር ሲቲ ላጠፋው ጥፋት የሚገባውን ቅጣት ካልተቀጣ የሊጉ ታማኝነት አደጋ ይገጥመዋል በማለት ተናግረዋል።

“ ማንችስተር ሲቲ ክለብ ብቻ ነው የሊጉ ሀላፊዎች ስራችሁን መስራት አለባችሁ “ ያሉት ዣቪየር ቴባስ ፕርሚየር ሊግ ትልቅ እና ትንሽ ክለቦችን ማበላለጥ የለበትም ብለዋል።

“ ማንችስተር ሲቲ የሊጉ አባል ነው ጥፋት አጥፍቷል ስለዚህ የሚገባውን ቅጣት መቀጣት አለበት “ ሲሉ ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ አሳስበዋል።

የላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ቀጥለውም ማንችስተር ሲቲ የማይቀጣ ከሆነ " የሊጉ ታማኝነት ይጠፋል " በማለት ተናግረዋል።

ማንችስተር ሲቲ የቀረበበት የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰት ክስ በገለልተኛ አካል በዛሬው ዕለት መታየት ጀምሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አራቱንም ዋንጫዎች ማሸነፍ እንፈልጋለን “ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው በዚህ አመት የሚፎካከርባቸውን አራት ውድድሮች ማሸነፍ እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

“ ሁሉንም ውድድሮች በቁምነገር እንወስዳለን “ ሲሉ ከነገው የባርንስሌይ የካራባኦ ካፕ ጨዋታ በፊት የተናገሩት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ “ በአራት ውድድሮች እንሳተፋለን ሁሉንም ማሸነፍ እንፈልጋለን ብለዋል።

በነገው ጨዋታ ማዝራዊ ፣ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ማትያስ ዴሊት ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማውንት እና ሊንድሎፍ እና ሆይሉንድ ለጨዋታው አይደርሱም ብለዋል።

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ሉክ ሾው በበኩሉ በጥሩ መሻሻል ላይ መሆኑን የጠቆሙት አሰልጣኙ ነገርግን የሚመለስበት ቀን በውል እንደማይታወቅ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አዲሱን የሻምፒየንስ ሊግ አቀራረብ ወድጄዋለሁ “ ኡናይ ኤምሬ

የአስቶን ቪላው ዋና አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ አዲሱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር አቀራረብ ከቀድሞው የተሻለ መሆኑን ገልጸዋል።

አስቶን ቪላን ከበርካታ አመታት በኋላ ወደ ሻምፒየንስ ሊግ የመለሱት አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ “ የቀድሞው ሻምፒየንስ ሊግ ለውጥ ያስፈልገው ነበር ፣ የአሁኑን ወድጄዋለሁ የተሻለ ይመስላል " ብለዋል።

አዲሱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር አቀራረብ ለደጋፊዎች የበለጠ ሳቢ እና ፍትሀዊ ይሆናል የሚል እምነታቸውንም አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ገልጸዋል።

“ ለውድድሩ በማለፋችን ሁላችንም ተደስተናል ከረጅም ጊዜ በኋላ ለክለቡ አስደሳች ቅፅበት ነው ፣ ረጅም እንደምንጓዝ ተስፋ አለን ትልቅ ፈተና ይሆናል።" ኡናይ ኤምሬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 04:27:32
Back to Top
HTML Embed Code: