Telegram Web Link
ሊቨርፑል የተጫዋቹን ግልጋሎት ያገኛል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል አዲስ ፈራሚ ፌዴሪኮ ኬሳ በነገው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ እንደሚሳተፍ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ገልጸዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ሲናገሩም “ በቋሚ አሰላለፍ ይገባል ብዬ አልጠብቅም ነገርግን ለመጀመሪያ ጊዜ የጨዋታ ሰዓት ይሰጠዋል “ በማለት ተናግረዋል።

ሊቨርፑል ነገ ምሽት 4:00 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ከኤሲ ሚላን ጋር ስታዲዮ ጁሴፔ ሜዛ ላይ የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 146,000 Birr
•512GB = 156,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 114,000 Birr
•512GB = 126,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
የዛሬ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች !

1:45 ጁቬንቱስ ከ ፒኤስቪ

1:45 ያንግ ቦይስ ከ አስቶን ቪላ

4:00 ኤሲ ሚላን ከ ሊቨርፑል

4:00 ባየር ሙኒክ ከ ዳይናሞ ዛግሬብ

4:00 ሪያል ማድሪድ ከ ስቱትጋርት

4:00 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ባርንስሌይ ( ካራባኦ ካፕ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ እኛ ኤሲ ሚላንን እናከብራለን እንጂ አንፈራም “ አርኔ ስሎቶ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው ተጋጣሚውን ያከብራል እንጂ እንደማይፈራ ገልጸዋል።

ሊቨርፑልን እየመሩ ዛሬ ምሽት የመጀመሪያ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት አሰልጣኝ አርኔ ስሎት “ ኤሲ ሚላን ትልቅ አቅም አላቸው ነገርግን እናከብራቸዋለን እንጂ አንፈራም “ ብለዋል።

በሳምንቱ መጨረሻ በኖቲንግሀም ፎረስት ስለገጠማቸው ሽንፈት ያነሱት አሰልጣኙ “ በሜዳህ እንደዛ አይነት ሽንፈት ከገጠመህ ልክ ያልሆነ ነገር አለ ማለት ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።

" በኖቲንግሀም ጨዋታ ወቅት ብዙ ልናሻሽላቸው የሚገቡ ነገሮች እንዳሉ ተመልክቻለሁ ፣ ዛሬ ከዛ የተለየ ጨዋታ እጠብቃለሁ።" አርኔ ስሎት

ኤሲ ሚላንን በደንብ ለማጥናት ሞክረናል ትኩረታችንን የሳበው ራፋኤል ሊያኦ ነው በማለት አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ለጠበቃቸው ስንት ይከፍላሉ ?

ማንችስተር ሲቲ የሊጉን ፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሷል በሚል የቀረቡበትን ክሶች ለመከላከል እውቁን ጠበቃ ሎርድ ፓኒክ በጥብቅና ለማቆም መቅጠራቸው ይታወቃል።

ታዋቂው ጠበቃ ሎርድ ፓኒክ ትላንት በጀመረው የማንችስተር ሲቲ የክስ ሂደት ከሞያ አጋሮቹ ጋር በመሆን በይፋ ስራውን ጀምሯል።

የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች በሜዳቸው ሲጫወቱ የጠበቃውን ስም በትልቅ ፅሁፎች በማስመልከት ድጋፍ ሲሰጡት መስተዋላቸው ይታወሳል።

ማንችስተር ሲቲ ለጠበቃው በሰዓት 5,000 ዩሮ ክፍያ እንደሚፈፅሙ ተገልጿል።

በተጨማሪም የማንችስተር ሲቲ የክስ ሂደት ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚያመራ ከሆነ ጠበቃው በሰዓት 80,000 ዩሮ እንደሚከፈለው ተነግሯል።

ማንችስተር ሲቲ በክለቡ ውስጥ ከፍተኛ የሚባለውን ደሞዝ የሚከፍለው ለመሀል ሜዳ ተጨዋቹ ኬቨን ዴብሮይነ ሲሆን ጠበቃው ሁለተኛው ከፍተኛ ተከፋይ መሆኑ ተገልጿል።

ጠበቃው ከዚህ በፊት ማንችስተር ሲቲ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ተላልፎበት የነበረውን እገዳ ይግባኝ በመጠየቅ ክለቡን ከተላለፈበት የሁለት አመት እገዳ #ነፃ ማድረጉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሪያል ማድሪድ ሮድሪን ማስፈረም ይፈልጋል ! ሪያል ማድሪድ በሚቀጥለው የክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ስፔናዊውን አማካይ ሮድሪ ማስፈረም የመጀመሪያ አላማቸው ለማድረግ ማሰባቸው ተገልጿል። በሎስ ብላንኮዎቹ በኩል ሮድሪን ከማንችስተር ሲቲ የማስፈረምን ትልቅ እቅድ የክለቡ ሀላፊዎች እንዲሁም ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ እና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ እንደሚጋሩት ተነግሯል። ሮድሪ ከአውሮፓ ዋንጫ ድል በኋላ…
ማንችስተር ሲቲ የሮድሪን ውል ማራዘም ይፈልጋል !

ማንችስተር ሲቲዎች የስፔናዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ ኮንትራት በቻሉት ፍጥነት ማራዘም እንደሚፈልጉ ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

ሪያል ማድሪድ በሚቀጥለው ክረምት ስፔናዊውን አማካይ ሮድሪ የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ለክለቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች መግለፃቸው አይዘነጋም።

ማንችስተር ሲቲ ሪያል ማድሪድ በተጨዋቹ ላይ ፍላጎት ማሳየቱ ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው እና ውሉን ለማራዘም ማሰባቸው ተዘግቧል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ማንችስተር ሲቲ የቀረበበት የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰት ክስ እልባት እስከሚያገኝ እና የመጨረሻ ውሳኔ ላይ እስከሚደረስ መጠበቅ እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

ሪያል ማድሪድ ማንችስተር ሲቲ ጥፋተኛ ከተባለ እና ቅጣት የሚጣልበት ከሆነ ሮድሪን ለማስፈረም ይቀለናል የሚል እምነት እንዳላቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሲቲ እና አርሰናልን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

በአምስተኛ ሳምንት የሊግ መርሐ ግብር የፊታችን እሁድ በማንችስቲር እና አርሰናል መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

ይህንንም ተከትሎ ኢትሀድ ስታዲየም ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ማይክል ኦሊቨር በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታውን ጆን ብሩክስ በቫር ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
📣 ሰምተዋል ℹ️

ለእረፍት ቀንዎ ልዩ ነገር ይዘን መጥተናል 🥁🔥

የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 11 እና እሁድ መስከረም 12 ቀን የሚደረጉትን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዋች ፥ ማን ሲቲ ከ አርሰናል ጨምሮ ሌሎች አጓጊ ጨዋታዎችን በሁሉም የዲኤስቲቪ ፓኬጆች ከ350 ብር ጀምሮ በቀጥታ መመልከት ይችላሉ።

ይህ ልዩ አጋጣሚ አያምልጥዎ !
ዲኮደሩን ይግዙ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Forwarded from WANAW SPORT
⚽️ “ጨዋታ” ⚽️

⛳️ የእግር ኳስ ጨዋታ ወደ ሀገራችን የገባው በ1920ዎቹ መጨረሻ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በ25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉ ላይ ባሳተመው መፅሄት ላይ እንደሚያትተው በመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ጨዋታዎች በዛ ያለው ጊዜ የሚጠፋዉ በጭቅጭቅ ነበር። ለዚህ  ዋነኛው ምክንያት ደግሞ ህጉን በአግባቡ የሚረዱ የጨዋታ ዳኞች ባለመኖራቸው ነበር። በዚህም የተወሰኑ የኳሱን ህግ የሚያውቁ ዳኞች ብዙም ላለመሯሯጥ ፈረስ ላይ ሆነው ያጫውቱ እንደነበረም በመፅሄቱ ላይ ተገልጿል። በዚህ ሁኔታም ውስጥ ሆኖ ቢጀመር እግር ኳስ በኢትዮጵያ ተወዳጅ ስፖርት ሆኗል። ጨዋታውን በትንሽ ዕውቀት በመመራት ጨዋታዎችን የመሩት ዳኞችም አብረው እያደጉ ከአህጉር አቀፍ እስከ ዓለም-አቀፍ እግር ኳስ ጨዋታዎችን መዳኘት የቻሉ ባለሙያዎች ከኢትዮጵያ ተገኝተዋል።

⛳️ ዋናው ስፖርትም ከተወዳጁ ስፖርት - እግር ኳስ ውበት ውስጥ የሚጠቀሱትን የጨዋታ ዳኞች የሚያከብር አዲስ የእግር ኳስ ዳኞች የስፖርት ትጥቅ ዛሬ ይፋ አድርጓል። “ጨዋታ” ብለንም ሰይመነዋል።

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
“ ኢንተር ከእኛ የበለጠ የሻምፒየን ሊግ ዋንጫ አለው “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ነገ ከኢንተር ሚላን ጋር ከሚያደርገው የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምን አሉ ?

- “ ኢንተር ሚላን ብዙ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎች አሉት እኛ አንድ ብቻ ነው ያለን።

- ኤርሊንግ ሀላንድ በአራት ጨዋታ ዘጠኝ ግቦች አስቆጥሯል አንድ ጨዋታ ከጨመረ እኔ በተጨዋችነት ካስቆጠርኳቸው ጎሎች እኩል ይሆናል።

- አዲሱ የሻምፒየንስ ሊግ አቀራረብ እንደ ፕርሚየር ሊግ ነው የደረጃ ሰንጠረዡን አሁን መመልከት የለብንም መጨረሻ ላይ እናየዋለን።

- ኢንተር ሚላን ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ ከእነሱ ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ካደረግን በኋላ አይተናል።

- ላውታሮ ማርቲኔዝ ትልቅ ተጨዋች ነው የአለም ዋንጫ እና ኮፓ አሜሪካ አሸንፏል ፣ ባሎን ዶር ማሸነፍ ይችላል ነገርግን እኔ የሲቲ ተጨዋች ቢያሸንፍ እመርጣለሁ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ተጨዋቹ በድጋሜ ጉዳት አጋጠመው !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፌርሚን ሎፔዝ አጋጥሞት ከነበረው የጡንቻ ጉዳት ቢያገግምም ተጨማሪ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ስፔናዊው አማካይ ፌርሚን ሎፔዝ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ የተጨማሪ ሳምንታት ጊዜ እንደሚያስፈልገው ተነግሯል።

ተጨዋቹ ካጋጠመው የጡንቻ ጉዳት አገግሞ በዚህ ሳምንት ወደ ሜዳ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቅ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ነስር በይፋ አሰልጣኙን አሰናበተ !

የሰዑዲ ዓረቢያው ክለብ አል ነስር ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ሉዊስ ካስትሮ ከሀላፊነት ማሰናበቱን በዛሬው ዕለት በይፋ አስታውቋል።

አል ነስር በዘንድሮው የውድድር ዘመን ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ሲሆን በሶስቱ አቻ ተለያይቷል።

አል ነስር በቀጣይ ጣልያናዊውን የቀድሞ የኤሲ ሚላን አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኦሎምፒክ ማርሴይ ራቢዮን አስፈረመ !

የፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒክ ማርሴይ ፈረንሳዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች አድሪያን ራቢዮን በነፃ ዝውውር ማስፈረማቸው ይፋ ተደርጓል።

የ 29ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አድሪያን ራቢዮ በአመቱ መጨረሻ ከጁቬንቱስ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ክለቡን መልቀቁ አይዘነጋም።

አድሪያን ራቢዮ በማርሴይ ቤት የሁለት አመት ኮንትራት መፈረሙ ሲገለፅ በክለቡ የ ሀያ አምስት ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፎች !

1:45 ጁቬንቱስ ከ ፒኤስቪ

1:45 ያንግ ቦይስ ከ አስቶን ቪላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ጁቬንቱስ 0-0 ፒኤስቪ

ያንግ ቦይስ 0-0 አስቶን ቪላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 07:18:50
Back to Top
HTML Embed Code: