Telegram Web Link
Forwarded from WANAW SPORT
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹 2016 #በዋናው በጥቂቱ - A Glimpse of WANAW in 2016 🇪🇹

በኃብቴ ጋርመንት እና ህትመት ስር ሆኖ በሀገራችን የስፖርት ኢንዱስትሪ ውስጥ በስፖርት ትጥቆች አቅርቦት ሰፊ ስራ እየሰራ ያለው ዋናው የስፖርት ትጥቅ ብራንድ በ2016 ዓ.ም በስፖርት አልባሳት የአቅርቦት ጥራት እና ዋጋ ችግሮችን ለመቅረፍ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች፣ ብሎም በአፍሪካና ሌሎች ክፍለ-አለማት ሀገር በቀል ምርቶቹን በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል፣ ብዙም አሳክቷል።

በሸኘነው 2016 ዓ.ም. እናንተ ደንበኞቻችንና አጋሮቻችን ምርታችንን መርጣችሁ ስለተጠቀማችሁ፣ ገንቢ አስተያየታችሁን እየሰጣችሁ አብራችሁን ስለዘለቃችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Under Habte Garment and Printing, Wanaw sportswear brand has worked extensively in the sports industry in the year 2016 to solve problems of quality and price of sportswear in different areas of our country, in Africa and as well as other regions of the world, by offering its indigenous products at a wide range and at an affordable price. We have done and achieved many things.

We sincerely thank all our customers and partners, for choosing and using our products, giving your constructive feedback and staying with us in 2016 E.C.

Instagram | Facebook | TikTok

ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ላሊጋ ዘረኝነትን በተመለከተ አዲስ አሰራር ይተገበራል !

የስፔን ላሊጋ በዘንድሮው የ 2024/25 የውድድር ዘመን ዘረኝነትን ለመዋጋት ሜዳ ላይ አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በጨዋታ ወቅት የዘረኝነት ጥቃቶች ሲፈፀሙ የጨዋታው ዳኛ ሶስት ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ተነግሯል።

በዚህም መሰረት :-

- በመጀመሪያ ዳኛው ጨዋታውን ማስቆም አለበት

- ጥቃቱ አሁንም የሚቀጥል ከሆነ ጨዋታው በጊዜያዊነት ይቋረጣል

- ጨዋታው ከተቋረጠ በኋላ ጥቃቱ ከቀጠለ ዳኛው ከሚመለከታቸው ጋር መክሮ ጨዋታው እንዲጠናቀቅ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሚኬል አርቴታ ውላቸውን ለማራዘም ተስማሙ ! ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት ያላቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በመድፈኞቹ ቤት ለተጨማሪ ሶስት አመታት ለመቆየት ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። የ 42ዓመቱ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በክለቡ ያላቸው ውል በውድድር አመቱ መጨረሻ የሚጠናቀቅ ቢሆንም በአርሰናል…
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ውላቸውን አራዘሙ !

ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ቤት ያላቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸው ይፋ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በመድፈኞቹ ቤት ለተጨማሪ ሶስት አመታት ለመቆየት ፊርማቸውን ማኖራቸው ይፋ ሆኗል።

" ውሌን በማራዘሜ ከፍተኛ ደስታ እና ኩራት ተሰምቶኛል " ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ውላቸውን ካራዘሙ በኋላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአል ናስር ደጋፊዎች የሮናልዶን ድል ያከብራሉ !

የሰዑዲ ዓረቢያው ክለብ አል ነስር ከአል አህሊ ጋር በሚያደርገው የሊግ መርሐ ግብር ደጋፊዎቹ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ድጋፋቸውን ለማሳየት ማሰባቸው ተገልጿል።

ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ ከ 901 ግቦችን በማስቆጠር አዲስ ታሪክ መፃፉ አይዘነጋም።

የአል ነስር ደጋፊዎች በጨዋታው የክርስቲያኖ ሮናልዶን 900 ግብ ድል የተለየ ፅሁፍ በስታዲየሙ በማስመልከት ለማክበር ማሰባቸውን ገልፀዋል።

አል ነስር ከአል አህሊ የሚያደርጉት ጨዋታ ነገ ምሽት 3:00 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ክስ ቀረበባቸው !

የኢትዮጵያ ቦክስ እና ቴኒስ ፌዴሬሽን እንዲሁም ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ እና አትሌት ገዛኸኝ አበራ በጋራ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ላይ ክስ መመስረታቸው ተገልጿል።

ክስ የተመሰረተባቸው አመራሮች ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ፣ የኮሚቴው ዐቃቤ ነዋይዋ ዶ/ር ኤደን አሸናፊ ፣ ዋና ፀሐፊው አቶ ዳዊት አስፋው እና ምክትል ፀሐፊው አቶ ገዛኸኝ ወልዴ መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ክስ እንደቀረበባቸው ይፋ ተደርጓል።

በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ላይ ከተመሰረቱ ክሶች መካከል :-

- ባልተገባ መልኩ የሰው ዝውውር በማድረግ

- ኦዲት ያልተደረገ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በካሽ እና በአይነት መኖሩ

- ኦሊምፒክ ኮሚቴው ከ 64 ሚልዮን ብር በላይ የሚያወጣ ፋብሪካ እገነባለሁ ብሎ የተገዙት ማሽኖች የት እንዳሉ አለመታወቃቸው።

- በፓሪሱ ኦሊምፒክ ወደ ፈረንሳይ ተጉዘው የቀሩ እና የመጡ ግለሰቦች በምን መመዘኛ ወደ ስፍራው መጓዛቸው።

- ሁለቱ የኦሊምፒክ አመራሮች ለሶስተኛ ግዜ የኢትዮጵያ ዜግነት ሳይኖራቸው መመረጣቸው የሚሉት ይገኙበታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የቀድሞ የሴልታቪጎ አምበል በፆታዊ ጥቃት ጥፋተኛ ተባለ !

የቀድሞ የሴልታቪጎ አምበል ሁጎ ማሎ ከአመታት በፊት ፆታዊ ትንኮሳ አድርጓል በሚል በካታላን ባርሴሎና ፍርድ ቤት ጠፋተኛ መባሉ ተገልጿል።

ተጨዋቹ እ.ኤ.አ 2019 ክለቡ ከእስፓኞል ጋር በነበረው ጨዋታ የእስፓኞል ሴት ሰራተኛ ማስኮት ላይ ፆታዊ ትንኮሳ አድርጓል የሚል ክስ እንደቀረበበት ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተጨዋቹ ለተበዳይ 6,000 ዩሮ ካሳ እንዲከፍል መወሰኑ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በበኩሉ ምንም መጥፎ ነገር አስቦ አለማድረጉን በመግለፅ ይግባኝ እንደሚጠይቅ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ምባፔ ፒኤስጂ ደሞዝ እንዳልከፈለው ለዩኤፋ አሳወቀ ! የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የቀድሞ ክለቡ ፒኤስጂ ቀሪ ደሞዝ እና ጉርሻ እንዳልከፈለው ለዩኤፋ እና ለፈረንሳይ እግርኳስ ፌዴሬሽን ማሳወቁ ተገልጿል። ተጨዋቹ ፒኤስጂን የጠየቀው የገንዘብ መጠን ከ 55 ሚልዮን ዩሮ በላይ መሆኑን በመጥቀስ ለሁለቱ የእግርኳስ ጠባቂ አካላት ማሳወቁን ሌሞንዴ አስነብቧል። ፒኤስጂ በበኩሉ እስካሁን…
ኪሊያን ምባፔ ደሞዙ እንዲከፈለው ተወሰነለት !

የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በቀድሞ ክለቡ ፒኤስጂ ያልተከፈለው ቀሪ ደሞዙ እና ጉርሻ እንዲከፈለው እንደተወሰነለት ተገልጿል።

ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድን ከመቀላቀሉ በፊት ፒኤስጂ የሶስት ወር ደሞዝ እና ጉርሻ እንዳልከፈለው ለዩኤፋ እና ለፈረንሳይ እግርኳስ ፌዴሬሽን ማሳወቁ አይዘነጋም።

አሁን ላይ የፈረንሳይ እግርኳስ ፌዴሬሽን ህግ ኮሚቴ ምባፔ ያልተከፈለው 55 ሚልዮን ዩሮ እንዲከፈለው ለፒኤስጂ ማሳወቁን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የተጫዋቹን ግልጋሎት ያገኛል !

ዩራጓዊው የቀያይ ሴጣኖቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ለቅዳሜው የሳውዝሀምፕተን ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ገልጸዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም ራስሙስ ሆይሉንድ እና ሉክ ሾው በጉዳት ለጨዋታው ዝግጁ አለመሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ይሁን እንጂ ሁለቱም ተጨዋቾች ከጉዳታቸው በጥሩ ሁኔታ በማገገም ላይ መሆናቸውን አሰልጣኙ ጠቁመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሮናልዶ ከዩናይትድ ርቆ ነው ያለው “ ቴንሀግ

ቅዳሜ በምሳ ሰዓት መርሐ ግብር ከሳውዝሀምፕተን ጋር የሚጫወቱት ማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ምን አሉ ?

-" ሮናልዶ ማንችስተር ዩናይትድ የፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ አይችልም ብሏል እሱ ከዩናይትድ ርቆ ሳውዲ አረቢያ ነው ያለው አሰተያየት መስጠት መብቱ ነው።

- የሳውዝሀምፕተንን ጨዋታ ብቻ ሳይሆን የምናደርጋቸውን ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ አለብን።

- ግንቦት ላይ የት እንደምንሆን እናያለን ውድድሩ አሁንም ገና ነው ፣ ዋንጫ ስለማሸነፍ ነው በሊጉ የተቻለንን ሁሉ ማድረግና ሁሉንም ጨዋታዎች ለማሸነፍ መጣር አለብን።" ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በሲቲ ጨዋታ አንድ ነገር እናደርጋለን “ ቶማስ ፍራንክ

የብሬንትፎርድ ዋና አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ በቅዳሜው የማንችስተር ሲቲ ጨዋታ " አንድ ነገር እናደርጋለን " በማለት ተናግረዋል።

ቅዳሜ 11:00 ሰዓት ኢትሀድ ላይ ብሬንትፎርድን እየመሩ ማንችስተር ሲቲን የሚገጥሙት አሰልጣኙ " በጨዋታው አንድ ነገር አድርገን የምንወጣ ይመስለኛል " ብለዋል።

" ሀላንድን ማስቆም ከባድ ነው “ የሚሉት አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ብዙ ክለቦች ተፅእኖውን ለመቀነስ ጥረዋል እሱ አስደናቂ ተጨዋች ነው በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ክስ ቀረበባቸው ! የኢትዮጵያ ቦክስ እና ቴኒስ ፌዴሬሽን እንዲሁም ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ እና አትሌት ገዛኸኝ አበራ በጋራ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ላይ ክስ መመስረታቸው ተገልጿል። ክስ የተመሰረተባቸው አመራሮች ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ፣ የኮሚቴው ዐቃቤ ነዋይዋ ዶ/ር ኤደን አሸናፊ ፣ ዋና ፀሐፊው አቶ ዳዊት አስፋው እና ምክትል ፀሐፊው አቶ ገዛኸኝ…
“ ሀገርን ለማስቀጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል “ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ

“ ከሳሾች ፍርድ ቤቱን በማሳሳታቸው ራሳቸው በህግ የሚጠየቁበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም “

በፕሬዝዳንቱ ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፍርድ ቤት የቀረበበትን ክስ ተከትሎ ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል።

“ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር መሰረት ሀላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል “ ያለው ኮሚቴው በመግለጫው “ ይሁን እንጂ በተቋሙ አሰራር የሚደሰት እና ቅሬታ ያለው ይኖራል ይህም ተፈጥሯዊ ነው “ ብሏል።

“ ተቋሙ በስፖርት መድረክ አለመግባባቶች እና ቅራኔዎች ሲኖሩ የሚስተናገዱበት መንገድ  በመተዳደሪያ ደንቡ በግልፅ ተቀምጧል “ ኦሎምፒክ ኮሚቴ

ኦሎምፒክ ኮሚቴው ማናቸውም ቅራኔዎች ወይም ከስፖርት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሲያጋጥሙት ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጪ ለችግር አፈታት በሚቋቋም የፍትህ አካል እንደሚፈታ ገልጿል።

በአሁን ሰዓት “ ሀገርን ለማስቀጣት የሚደረገው እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል “ ሲል ኦሎምፒክ ኮሚቴው አሳስቧል።

“ አንዳንድ የሚዲያ ባለሙያዎች ከግለሰቦች ጋር በጥቅም በመተሳሰር ሚዛናዊ ያልሆኑ የአንድ ወገንን መረጃ በማቅረብ የስፖርት ቤተሰቡን እያሳሳቱት ይገኛሉ “ ያለው ኮሚቴው ለዚህም ማስረጃ አለን ብሏል።

ይሄንን ጉዳይ እስካሁን ብናልፍም ተቋሙን እና ሀገርን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ በህግ እንጠይቃቸዋለን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም እናሳስባለን ብሏል።

“ ከሁሉም በላይ እነዚህ ከሳሾች በውሸት ቃለመሀላ ፍርድ ቤት ያሳሳቱ በመሆናቸው ራሳቸው በህግ የሚጠየቁበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን እንረዳለን “ ኦሎምፒክ ኮሚቴ

ምንጭ - ጋዜጠኛ ዮሴፍ ከፈለኝ እና ስፖርት ዞን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 146,000 Birr
•512GB = 156,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 114,000 Birr
•512GB = 126,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
የሲቲ ክስ ጉዳይ ሰኞ መታየት ይጀምራል !

ማንችስተር ሲቲ ባለፉት አመታት የፕርሚየር ሊጉን የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰዋል በሚል ምርመራ ሲደረግባቸው እንደነበር ይታወቃል።

አሁን ላይ የማንችስተር ሲቲ የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰት ክስ ጉዳይ በሚቀጥለው ሳምንት ሰኞ ጀምሮ በገለልተኛ አጣሪ መታየት እንደሚጀምር ተገልጿል።

የሊጉ ገለልተኛ አጣሪ ፍርድ ቤት ሰኞ የፍርድ ሂደቱን የሚጀምርበት ቦታ እንደማይታወቅ ቢቢሲ ዘግቧል።

የፍርድ ሂደቱ ለሚቀጥሉት አስር ሳምንታት እንደሚቀጥል ሲነገር በ 2025 መጀመሪያ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ዚርኪዜ ፕርሚየር ሊግ አስቸግሮታል “ ፋብዮ ካፔሎ

የቀድሞ ጣልያናዊ ተጨዋች ፋቢዮ ካፔሎ የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርኪዜ በፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ሲቸገር ማስተዋሉን ገልጿል።

ከጁቬንቱስ ሊቨርፑልን የተቀላቀለው ፌዴሪኮ ኬሳ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ለማድረግ የሚሆን ፍጥነት እንዳለው ፋብዮ ካፔሎ ተናግሯል።

“ ዚርኪዜ ግን በፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ሲቸገር አስተውያለሁ “ ያለው ፋብዮ ካፔሎ “ ምክንያቱም እሱ አሁንም ጣልያን ሊግ ውስጥ በነበረው ፍጥነት መጫወት እንደሚችል ስለሚያስብ ነው።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ከቪንሰስ ጋር ለባሎን ዶር መፎካከር አኩርቶኛል “ ሮድሪ

ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ የባሎን ዶር ሽልማት ማሸነፍ ህልሙ መሆኑን ገልጿል።

“ በመንገዶች ላይ ስዘዋወር ሰዎች ባሎን ዶር ማሸነፍ እንደሚገባኝ ይነግሩኛል ይህ ለእኔ እንደ ማሸነፍ ነው ባሎን ዶር ህልሜ ነው።“ ሲል ሮድሪ ተናግሯል።

“ የቪንሰስ ጁኒየር አድናቂ ነኝ “ የሚለው ሮድሪ “ እሱ አስደናቂ ተጨዋች ነው ከእሱ ጋር ለባሎን ዶር መፎካከር እንድኮራ አድርጎኛል “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ስለ ተጨዋቾች ኮንትራት ማራዘም ማውራት አልፈልግም “ አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው ነገ ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ከሚያደርገው የሊግ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ምን አሉ ?

- “ ኬለር መጫወት መፈለጉ ተፈጥሯዊ ነው ተጠባባቂ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ ሙሉ እድሜዬን እዚህ እቆያለሁ እንዲል አልጠብቅም።

- በእርግጠኝነት አሊሰን ቤከር ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂያችን ይሆናል ነገርግን ኬለር በብዙ ጨዋታዎች ላይ ይሰለፋል።

- ማክ አሊስተር ትላንት አብሮን ልምምድ ሰርቷል ለኖቲንግሀም ፎረስት ጨዋታ ዝግጁ ሊሆን ይችላል።

- ስለ ተጨዋቾች ኮንትራት እዚህ መናገር አልችልም ሙሉ ትኩረቴ ቡድኑ ላይ ነው ከስራዬ እንዲያዘናጋኝ አልፈልግም።

- ፌዴሪኮ ኬሳ ለተወሰኑ ቀናት አብሮን ልምምድ ሰርቷል ዛሬም ይሰራል ለነገው ጨዋታ ስለመድረሱ አይተን እንወስናለን።“ ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጁድ ቤሊንግሀም መቼ ወደ ሜዳ ይመለሳል ? ጁድ ቤሊንግሀም በሚቀጥለው ሳምንት ሪያል ማድሪድ ከሪያል ሶሴዳድ ጋር በሚያደርጉት የላሊጋ ጨዋታ ወደ ሜዳ ይመለሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል። እንግሊዛዊው አማካይ ጁድ ቤሊንግሀም በቅርቡ ባጋጠመው የጡንቻ ጉዳት ምክንያት ከሜዳ ርቆ እንደሚገኝ ይታወቃል። የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች የአምስት እረፍት እንደተሰጣቸው የተገለፀ ሲሆን ጁድ ቤሊንግሀም ግን እስከ…
ማድሪድ የተጫዋቾቹን ግልጋሎት አያገኝም !

በጉዳት ላይ የነበረው እንግሊዛዊው የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም በዛሬው የቡድኑ መደበኛ ልምምድ ላይ አለመሳተፉ ተገልጿል።

በተጨማሪም ሌላኛው የሎስ ብላንኮዎቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦርሊየን ቹዋሜኒ ልምምድ አለመስራቱ ተዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ ሁለቱም ተጨዋቾች ሪያል ማድሪድ ነገ ከሪያል ሶሴዳድ ጋር የሚያደርገው የላሊጋ ጨዋታ እንደሚያመልጣቸው ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 እጅግ ልዩ የአዲስ ዓመት የሽያጭ ብስራት!

🌼
#ዛሬውኑ ይዘዙን! 🌼

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
2024/10/01 17:33:02
Back to Top
HTML Embed Code: