Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዘመን የሊጉ የመጀመሪያ ወር ምርጥ ተጨዋች #ስምንት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ብሪያን ምቤሞ ፣ አማዱ ኦናና ፣ ኮል ፓልመር ፣ ዴቪድ ራያ ፣ ቡካዩ ሳካ ፣ መሐመድ ሳላህ እና ዳኒ ዌልቤክ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸዉ። የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል…
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዘመን የሊጉ የመጀመሪያ ወር ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ኖርዌያዊው የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የነሐሴ ወር ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በወሩ ባደረጋቸው ሶስት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሁለት ሀትሪክ ሲሰራ አጠቃላይ ሰባት ግቦች አስቆጥሯል።

" ይህንን ሽልማት በአመቱ መጀመሪያ በማሸነፌ በጣም ተደስቻለሁ ድምፅ የሰጡኝን ሁሉ አመሰግናለሁ " ሲል ሀላንድ ከሽልማቱ በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል የ 2024/25 የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ #አራት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ፣ ፔፕ ጋርዲዮላ ፣ ፋብያን ሁርዜለር እና አርኔ ስሎት የሊጉ የመጀመሪያ ወር ምርጥ አሰልጣኝ እጩ በመሆን የቀረቡ አሰልጣኞች ናቸዉ። የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ታውቋል !

የ 2024/25 የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የብራይተኑ ዋና አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር የሊጉ የመጀመሪያ ወር ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን መመረጥ ችለዋል።

አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር በወሩ ውስጥ ቡድናቸውን እየመሩ ካደረጓቸው ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ሁለቱን አሸንፈው በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።

የ 31ዓመቱ አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማት ያሸነፈ በታሪክ በእድሜ ትንሹ አሰልጣኝ ሆነዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ የተጫዋቹን ውል ለማራዘም ተስማማ ! ሴኔጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮላስ ጃክሰን በቼልሲ ቤት ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት ውሉን ለማራዘም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። ኒኮላስ ጃክሰን በሰማያዊዎቹ ቤት ለማቀጥሉት ዘጠኝ አመታት ለመቆየት ውሉን እስከ 2033 ለማራዘም ዝግጁ መሆኑን ዘ አትሌቲክስ አስነብቧል። ሰማያዊዎቹ የ 23ዓመቱን የፊት መስመር አጥቂ ኒኮላስ ጃክሰን እንደ ወሳኝ የፊት…
ቼልሲ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮላስ ጃክሰን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 23ዓመቱ የፊት መስመር አጥቂ ኒኮላስ ጃክሰን በሰማያዊዎቹ ቤት የተጨማሪ ሁለት አመታት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

ይህንንም ተከትሎ ኒኮላስ ጃክሰን በሰማያዊዎቹ ቤት ለማቀጥሉት ዘጠኝ አመታት የሚቆይ ይሆናል።

“ አዲስ ኮንትራት በመፈረሜ በጣም ተደስቻለሁ ፣ ክለቡ በእኔ ላይ እምነት እንዳለው ማየት በጣም አስደሳች ነው።" ሲል ጃክሰን ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
ሲቲ ተጨዋቹ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል !

ኔዘርላንዳዊው የማንችስተር ሲቲ ተከላካይ ናታን አኬ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት እስከ ቀጣዩ የብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ገልጸዋል።

ናታን አኬ ከቀናት በፊት ኔዘርላንድ ከጀርመን ጋር ባደረገችው የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታ ጉዳት ማስተናገዱ አይዘነጋም።

" ናታን አኬ ተጎድቶ በመመለሱ እድለኛ አልነበርንም ሁልጊዜም እሱ ወደዛ ከሄደ ተጎድቶ ነው የሚመለሰው “ ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

ተጨዋቹ በጉዳት ምክንያት ቀጣይ ሰባት የማንችስተር ሲቲ ጨዋታዎች የሚያመልጡት ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የሲቲ ክስ ሊታይ መሆኑ አስደስቶኛል " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ክለቡ ላይ የቀረቡ 115 የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ክሶች ሰኞ ሊታዩ መሆኑ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

“ ሰው ምን እየጠበቀ እንደሆነ አውቃለሁ “ ያሉት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምን እንደሚፈጠር ጠብቀን እናያለን በማለት ተናግረዋል።

“ ገለልተኛ ፍርድ ቤቱ ሂደቱን በፍጥነት እንደሚያጠናቅቅ ተስፋ እናደርጋለን ፣ ውሳኔውን በጉጉት እየጠበቅን ነው።“ ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አያይዘው ገልጸዋል።

"ሁሉም ሰው ወንጀለኛ መሆኑ በፍርድ ቤት እስካልተረጋገጠበት ድረስ ንፁህ ነው የሚሆነውን እናያለን።" ጋርዲዮላ

ስለ ነገው የብሬንትፎርድ ጨዋታ ያነሱት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ “ ሁልጊዜም ከብሬንትፎርድ እና ቶማስ ፍራንክ ጋር የሚደረጉ ጨዋታዎች ከባድ ናቸው “ ብለዋል።

በነገው የብሬንትፎርድ ጨዋታ ሮድሪ እና ፊል ፎደን ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አያይዘው ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ የተጨዋቹን ግልጋሎት አያገኝም !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በነገው የበርንማውዝ ጨዋታ የቀኝ መስመር ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ማሎ ጉስቶን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ገልጸዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም ሬስ ጄምስ ወደ ሜዳ ለመመለስ ተጨማሪ ረጅም ጊዜ እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል።

የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ሮሚዮ ላቪያ በበኩሉ በቅርቡ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ አሰልጣኙ አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሪያል ማድሪድ የግብ ጠባቂውን ውል ማራዘሙ ተገለፀ ! ሎስ ብላንኮዎቹ የግብ ጠባቂያቸውን አንድሬ ሉኒን ኮንትራት ለተጨማሪ ሶስት አመታት ማራዘማቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል። በኮንትራቱ ላይ የአንድ አመት ቀሪ ኮንትራት የነበረው ሉኒን በሳንቲያጎ በርናቦ እስከ 2028 የውድድር ዘመን ለመቆየት ከስምምነት ደርሷል። የ 25ዓመቱ ግብ ጠባቂ ያለፈውን አመት የቲቡዋ ኩርቱዋን መጎዳት ተከትሎ የክለቡ ቁጥር…
ሪያል ማድሪድ የግብ ጠባቂውን ውል አራዘመ !

ሎስ ብላንኮዎቹ የግብ ጠባቂያቸውን አንድሬ ሉኒን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

በኮንትራቱ ላይ የአንድ አመት ቀሪ ኮንትራት የነበረው ሉኒን በሳንቲያጎ በርናቦ እስከ 2030 የውድድር ዘመን ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።

የ 25ዓመቱ ግብ ጠባቂ ያለፈውን አመት የቲቡዋ ኩርቱዋን መጎዳት ተከትሎ የክለቡ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ በመሆን ግልጋሎት ሰጥቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ጋብሬል ጄሱስ ዝግጁ ይሆናል “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ጋብሬል ጄሱስ በእሁዱ የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ዝግጁ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ብራዚላዊው አጥቂ ጋብሬል ጄሱስ በጉዳት ምክንያት ያለፉት የሊግ ጨዋታዎች እንዳለፉት የሚታወቅ ሲሆን “ ሁሉም በጥሩ ሁኔታ ከሄደ ለእሁዱ የቶተንሀም ጨዋታ ዝግጁ ይሆናል “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

ሴለ ማርቲን ኦዴጋርድ ጉዳት ያነሱት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ “ ተጨማሪ ምርመራዎች ያስፈልጉታል ፣ በሚቀጥሉት ቀናት የሚፈጠረውን እንይ በእሱ በኩል ጥሩ ምልክቶች ይታያሉ “ ብለዋል።

" ራሂም ስተርሊንግ ብዙ ሀይል እና አቅም ያለው ተጨዋች ነው ይህንን ሜዳ ላይ ማስመስከር ይፈልጋል።" አርቴታ

በቶተንሀም በኩል በእሁዱ የሰሜን ለንደን ደርቢ ሪቻርልሰን የማይሳተፍ ሲሆን ዶምኒክ ሶላንኬ እና ቫን ዴቪን ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
⚽️አጓጊው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቅዳሜ ወደ ሜዳ ይመለሳል!!

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ወደ ሜዳ ያሳድጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
🌼 እንቁጣጣሽን ከእኛ ጋር🌼
 
በሽ በሽ በቴሌግራም ስጦታ! ልዩ ልዩ የዳታ ጥቅሎችን እየገዛን በነፃ የቴሌግራም ስጦታ እንንበሽበሽ!
 
የአዲስ አመት ምኞቻችንን ለወዳጅ ዘመዶቻችን እንግለፅ!🌼🌻
 
#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
“ ሀያ አራት ተጨዋቾች ብቻ ናቸው ያሉን “ ማሬስካ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በአሁን ሰዓት እየሰሩ የሚገኙት ከሀያ አራት ተጨዋቾች ጋር ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

“ ከጅምሩ ከሀያ አምስት ወይም ሀያ ስድስት ተጨዋቾች ጋር ብቻ ነው ስሰራ የነበረው “ ያሉት አሰልጣኙ “ በአሁን ሰዓት አርባ ሳይሆን ሀያ አራት ተጨዋቾች ብቻ ናቸው ያሉን “ ብለዋል።

" ተሰላፊ ተጨዋቾችን የምወስነው እኔው ብቻ ነኝ ፣ ጄደን ሳንቾ የመሰለፍ እድሉ ልምምድ ላይ በሚያሳየው አቋም ነው ፣ እድል ለመስጠት ትክክለኛውን ጊዜ እንጠብቃለን።" ኢንዞ ማሬስካ

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ አያይዘውም ብቻውን እየሰራ ከሚገኘው  ከቺል ዊል ጋር እንደሚነጋገሩ እና ወደ ቡድናቸው ሊቀላቅሉት እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቶኒ ክሩስ የራሱን አካዳሚ ይከፍታል ! ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ  በቀጣይ ስፔን ማድሪድ ውስጥ የራሱን አካዳሚ ለመክፈት እየሰራ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል። ቶኒ ክሩስ በቀጣይ ጫማውን ከሰቀለ በኋላ በሚከፍተው የራሱ አካዳሚ መስራት እንደሚጀምር ገልጿል። ቶኒ ክሩስ በሪያል ማድሪድ አካዳሚ ስራ እንደሚጀመር ተገልፆ የነበረ ቢሆንም ዜናው " የትርጉም ስህተት " እንደነበረው እና የራሱን…
ቶኒ ክሩስ የራሱን አካዳሚ በይፋ ከፈተ !

በቅርቡ ከእግር ኳስ ራሱን ያገለለው ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ማድሪድ ውስጥ የራሱን አካዳሚ ከፍቷል።

የታዳጊዎች እግርኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚው 200 ህፃናትን በመያዝ መክፈቱ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

ስኬታማ የሚባል የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወት ያሳለፈው ቶኒ ክሩስ በቀጣይ በራሱ አካዳሚ እንደሚሰራ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮኔል ሜሲ ወደ ሜዳ ይመለሳል !

አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ከጉዳቱ በማገገም በቀጣይ ጨዋታ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ተገልጿል።

ክለቡ ኢንተር ሚያሚ ነገ ሌሊት ከፊላደልፊያ ጋር በሚያደርገው የሊግ ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ ዝግጁ እንደሚሆን አሰልጣኝ ታታ ማርቲኖ አረጋግጠዋል።

ሊዮኔል ሜሲ በኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ጨዋታ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ላለፉት ሶስት ወራት ከሜዳ ርቆ መቆየቱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሜሪካ በይፋ አሰልጣኝ ቀጠረች ! አሜሪካ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖን የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በማድረግ መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል። ከኮፓ አሜሪካ የምድብ ስንብት በኃላ አሰልጣኝ እያፈላለጉ ይገኙ የነበሩት አሜሪካዎች ፖቼቲኖን እስከ 2026 የአለም ዋንጫ ድረስ በሀላፊነት ሾመዋል። ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ብሔራዊ ቡድኑን እየመሩ በቀጣይ ወር በወዳጅነት ጨዋታ ከፓናማ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ…
“ አሜሪካ አለም ዋንጫ እንደምታሸንፍ ማመን አለብን “ ፖቼቲኖ

የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድንን በሀላፊነት የተረከቡት አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ በቀጣይ አላማቸው ትልቅ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

“ ማሸነፍ እንደምንችል ማመን አለብን “ የሚሉት አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ “ ጨዋታዎችን ብቻ ሳይሆን አሜሪካ የአለም ዋንጫ ማሸነፍ እንደምትችል ማመን አለብን “ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ወር የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ራፊንሀ የስፔን ላሊጋ የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።

ራፊንሀ በወሩ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ሶስት ግቦችን ሲያስቆጥር ሁለት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ባርሴሎናዎች የነሐሴ ወር የላሊጋ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ፣ ምርጥ ወጣት ተጨዋች እና ምርጥ ተጨዋች ሽልማቶችን ማሸነፍ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮናልዶ በደጋፊዎች የክብር አቀባበል ተደርጎለታል !

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ 900 ግቦች ማስቆጠሩን ተከትሎ በአል ናስር ደጋፊዎች የክብር አቀባበል ተደርጎለታል።

አል ናስር በአሁን ሰዓት ከአል አህሊ ጋር የሰዑዲ ዓረቢያ ሊግ ጨዋታውን በማድረግ ላይ ይገኛል።

ጨዋታውን ለመከታተል እና ቪድዮችን ለማግኘት የጎል ቻናላችንን መቀላቀል ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ነስር ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል !

በሰዑዲ ዓረቢያ ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አል ነስር ከአል አህሊ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የአል አህሊን ግብ ፍራንክ ኬሲ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል የአል ነስርን የአቻነት ግብ አልሁራይጂ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሯል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

6ኛ. አል ነስር :- አምስት ነጥብ
9ኛ. አል አህሊ :- አራት ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

አርብ - አል ኢትፋቅ ከ አል ነስር

አርብ - አል አህሊ ከ ዳማክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 19:22:24
Back to Top
HTML Embed Code: