Telegram Web Link
አንድሬ ኦናና በዩጋንዳን ደማቅ አቀባበል ተደረገለት !

ካሜሮናዊው ግብ ጠባቂ በትላንትናው ዕለት ሀገሩ ከዚምቧቡዌ ጋር በዩጋንዳ ማንዴላ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በተለይም በዩጋንዳ የሚገኙ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች የክለቡን ማልያ በመልበስ በስታዲየም ተገኝተው ከፍተኛ ድጋፍ ሲሰጡ ተስተውለዋል።

ደጋፊዎች የተለያዩ ፅሁፍ በመያዝ ለግብ ጠባቂው ፣ ለአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ እና ለክለቡ መልዕክቶቻቸውን ሲያስተላልፉ ታይቷል።

ኦናና ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ ከቡድን አጋሮቾ ተነጥሎ በተዘጋጅለት የግል መኪና በከፍተኛ ጥበቃ ከስታዲየም ለመውጣት ችሏል።

ካሜሮን በጨዋታው ከዚምቧቡዌ ጋር ያደረገችውን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት አጠናቃለች።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
መልካም አዲስ አመት
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 146,000 Birr
•512GB = 156,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 114,000 Birr
•512GB = 126,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
አርሰናል በተጠባቂ ጨዋታ ማንን ሊያሰልፍ ይችላል ?

የመድፈኞቹ አምበል መጎዳትን ተከትሎ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ለሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ የተለያዩ አማራጮችን ለመመልከት ይገደዳሉ።

መድፈኞቹ ከመጀመሪያ ሶስት የመሐል ሜዳ ተመራጮቻቸው ዴክላን ራይስ ፣ ሚኬል ሜሪ እና ኦዴጋርድ ውጪ ተጠባቂ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ልምድ ባላቸው ተጫዋቾቻቸው ላይ እምነት ያሳድራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም መሰረት ከዚህ ቀደም የኦዴጋርድን መጎዳት ተከትሎ በቦታው የተሰለፈው ሀቨርትዝ በዚህ ሳምንት በተለየ ሚና ልናየው እንደምንችል ተጠቁሟል።

ይህንንም ተከትሎ በመሐል ሜዳው ላይ ቶማስ ፓርቴ ፣ ጆርጂንሆ እና ካይ ሀቨርትዝ የሚኬል አርቴታ ተቀዳሚ ተመራጮች እንደሚሆኑ ተነግሯል።

በሀገራት ጨዋታ ወቅት ልምምዱን ሲሰራ የቆየው ራሂም ስተርሊንግ በዚህ ሳምንት ለመድፈኞች የመጀመሪያውን ጨዋታ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ክለብ ያለ እውቀት አይገነባም “ ሮናልዶ

የቀድሞ የቀያይ ሴጣኖቹ የፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ክለቡ የቀድሞ ተጫዋቾቹን ማድመጥ እንደሚገባው ገልፆል።

እንደ ሮናልዶ ንግግር “ ክለቡ ከዚህ ቀደም የነበሩ ተጫዋቾቾን ማዳመጥ አለበት “ ሲል ሪዮ ፈርንዲናንድ ፣ ሮይ ኪን ፣ ፖል ሶኮልስ እና ጋሪ ኔቭልን በአብነት አንስቷል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቫን ኒስትሮይን ካደመጠ በብዙ መንገድ ይረዳዋልም ብሏል።

ክለቡ ለውጥ እንደሚያስፈልገው ያስረዳው ሮናልዶ “ አሁንም የአለማችን ምርጡ ክለብ ነው ፣ ይህ ክለብ ለውጥ ያስፈልገዋል “ ሲል ገልፆል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
በወር 20,000 ብር 💸💵💰💰 ማግኘት ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ
🚴‍♀️ ብስክሌት
🏍 ሞተር
🛵 E-bike ካልዎት ምን ይጠብቃሉ ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ።

💰ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን ብስክሌት ፥ ሞተረ እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል።

የሥራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ

ለመመዝገብ:-
ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት

✴️https://www.tg-me.com/DriversRegistration_bot
ወይም
☎️ +251923344444 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሰን!

ዋናው ስፖርት በ2017 ዓ.ም የስፖርት ትጥቆችን አሁንም በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ መዘጋጀቱን እያበሰረ፣ አዲሱ ዓመት ሀገራችን ሰላም የምትሆንበት፣ ሰርተን የምናተርፍበት፣ የስኬት ዓመት ያድርግልን ሲል ይመኛል።

🌼 መልካም አዲስ አመት! 🌼

Instagram | Facebook | TikTok

ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
ኢትዮጵያዊቷ አጥቂ በርካታ ጎሎች አስቆጠረች ! የታንዛኒያውን ክለብ ያንግ አፍሪካ ሴቶች ቡድን የተቀላቀለችው ኢትዮጵያዊቷ ተጨዋች አርየት ኦዶንግ የክለቡ የመጀመሪያ ጨዋታዋን አድርጋለች። ያንግ አፍሪካ ፕሪንስስ ዛሬ በዝግ ስታዲየም ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ ተጋጣሚያቸው ምቶኒ ኪዊንስን 16ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። ከስፍራው መረጃ ለማግኘት እንደተሞከረው በጨዋታው ኢትዮጵያዊቷ ተጨዋች…
ኢትዮጵያዊቷ አጥቂ ግብ ማግባቷን ቀጥላለች !

ለታንዛኒያው ያንጋ ፕሪንሰስ ፊርማዋን ያኖረችው የሉሲዎቹ የፊት መስመር ተጫዋች በታንዛኒያ የተሳካ ጅማሮን በማድረግ ላይ ትገኛለች።

ቡድኑ በቅድመ ውድድር ዝግጅት በዛሬው ዕለት ባደረገው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አርየት ኦዶንግ አራት ጎሎችን ማስቆጠር ችላለች።

አርየት ኦዶንግ ለያንግ ፕሪንሰስ ተሰልፋ በተጫወተችባቸው ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች አስራ አንድ ጎሎችን አስቆጥራለች።

ከዊስደም ኩዊንስ ጋር ጨዋታቸውን ያደረጉት ያንጋ ፕሪንሰስ 8ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ያለኝን ሰጥቻለሁ “

የቀድሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በብሔራዊ ቡድን ቆይታቸው የተቻላቸውን ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በትክክለኛው ሰዓት ከሀላፊነት መልቀቃቸውን የገለፁት የቀድሞ አሰልጣኝ “ በአሰልጣኝነት ዘመኔ ለብሔራዊ ቡድኑ ያለኝን ሁሉ ሰጥቻለሁ “ ብለዋል።

ስለ ቀጣይ የአሰልጣኝነት ህይወታቸው ፍንጭ የሰጡት ጋሪዝ ሳውዝጌት በእግር ኳስ አልያም ከኳስ ውጪ ልንመለከታቸው እንደምንችል ጠቁመዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
በቅርቡ ራሴን ከአሰልጣኝነት አላገልም “

የቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የአሰልጣኝነት ዘመናቸውን በቅርቡ የማጠናቀቅ ሀሳብ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

ከፌነርባቼ ጋር የሁለት አመት ኮንትራት ያላቸው ጆዜ ሞሪንሆ “ የአሰልጣኝነት ዘመኔ ከፌነርባቼ ቆይታዬ በኃላም ይቀጥላል “ ብለዋል።

በታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች በርከት ያሉ ዋንጫዎችን ማሸነፍ የቻሉት ጆዜ ሞሪንሆ “ ለቀጣዮቹ አስር አመታት በአሰልጣኝነት ትመለከቱኛላችሁ “ ሲሉ ተደምጠዋል።

ጆዜ ሞሪንሆ የአሰልጣኝነት ህይወታቸው የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በፈረንጆቹ አዲስ አመት በኔትፍሊክስ አመካኝነት ለተመልካት እንደሚቀርብ አሳውቀዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ የግብ ጠባቂውን ውል ማራዘሙ ተገለፀ !

ሎስ ብላንኮዎቹ የግብ ጠባቂያቸውን አንድሬ ሉኒን ኮንትራት ለተጨማሪ ሶስት አመታት ማራዘማቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

በኮንትራቱ ላይ የአንድ አመት ቀሪ ኮንትራት የነበረው ሉኒን በሳንቲያጎ በርናቦ እስከ 2028 የውድድር ዘመን ለመቆየት ከስምምነት ደርሷል።

የ 25ዓመቱ ግብ ጠባቂ ያለፈውን አመት የቲቡዋ ኩርቱዋን መጎዳት ተከትሎ የክለቡ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ በመሆን ግልጋሎት ሰጥቷል።

ሪያል ማድሪድ በአዲስ የውድድር ዘመን ባደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች አንድሬ ሉኒን በተጠባባቂ ወንበር ላይ ነበር።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሴርያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል የ 2024/25 የውድድር ዘመን የጣሊያን ሴርያ የወርሀ ነሐሴ ምርጥ ተጨዋች #ስድስት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት ኮኮ ፣ ቅቫራስኬሊያ ፣ ማን ፣ ሬቴጉይ ፣ ማርከስ ቱራም እና ቭላሆቪች የሊጉ የመጀመሪያ ወር ምርጥ ተጨዋች እጩ በመሆን የቀረቡ ተጨዋቾች ናቸዉ። የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል @tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሴርያ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ታውቋል !

የጣልያን ሴርያ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ወር የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የኢንተር ሚላን የፊት መስመር ተጫዋች ማርከስ ቱራም የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጫዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።

ማርከስ ቱራም በወሩ ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች አራት ጎሎችን ለክለቡ አስቆጥሯል።

ኢንተር ሚላን በሴርያው ሰባት ነጥቦችን በመሰብሰብ ሴርያውን እየመሩ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 146,000 Birr
•512GB = 156,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 114,000 Birr
•512GB = 126,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
“ ደጋፊዎችን ይቅርታ እጠይቃለሁ “ ቪንሰስ ጁኒየር

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ብሔራዊ ቡድኑ በገጠመው ሽንፈት ደጋፊውን ይቅርታ ጠይቋል።

በሪያል ማድሪድ ያሳየውን ብቃት ለሀገሩ ማሳየት አልቻለም በሚል እየተተቸ የሚገኘው ቪንሰስ ጁኒየር “ አውሮፓ ያሉ ጨዋታዎች ከዚህ የበለጠ ፈጣን ናቸው “ ሲል ገልጿል።

በሜዳው ምክንያት ኳስ በፍጥነት እንደምትንቀሳቀስ ያስረዳው ቪንሰስ ጁኒየር " እዚህ ጨዋታዎችን ለማሸነፍ በተሻለ መጫወት መላመድ አለብን “ ብሏል።

ቡድኑ ጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የገለፀው ቪንሰስ ጁኒየር ለዚህም ደጋፊውን ይቅርታ መጠየቅ እንደሚፈልግ እና በቅርቡ እንደሚሻሻሉ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ዶኩ ከሳካ የተሻለ ተጨዋች ነው “ ሮበርት ፒርስ

የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች ሮበርት ፒርስ እንግሊዛዊው ፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ “ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ይጎለዋል “ በማለት ተናግሯል።

የሲቲው ተጨዋች “ ዶኩ ከቡካዩ ሳካ በተወሰነ መልኩ የተሻለ ተጨዋች ነው “ የሚለው ሮበርት ፒርስ “ ዶኩ ኳስ በማንከባለል ብቃቱ እና ፈጣሪነቱ ከሳካ የተሻለ ነው “ ብሏል።

የቀድሞ ተጨዋቹ አክሎም በእሱ አስተያየት ቡካዩ ሳካ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት እንደሚጎለው በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሚኬል አርቴታ ውላቸውን ለማራዘም ተስማሙ !

ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት ያላቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በመድፈኞቹ ቤት ለተጨማሪ ሶስት አመታት ለመቆየት ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

የ 42ዓመቱ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በክለቡ ያላቸው ውል በውድድር አመቱ መጨረሻ የሚጠናቀቅ ቢሆንም በአርሰናል ቤት ለአመታት ይቀጥላሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች !

የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የ 20ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ተጋጣሚዎቹን አውቋል።

በማጣሪያው ዘጠኝ ብሔራዊ ቡድኖች ሲሳተፉ ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከዩጋንዳ ፣ ደቡብ ሱዳን እና ቡሩንዲ ጋር ተደልድላለች።

በማጣሪያ ውድድሩ ከምድቦቹ ሁለት ሀገራት ግማሽ ፍፃሜ የሚቀላቀሉ ይሆናል።

የውድድሩ ሁለት ምርጥ ብሔራዊ ቡድኖች በሚቀጥለው አመት በሚካሄደው የ 20ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞንን በመወከል ይሳተፋሉ።

የ 20ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥነው የላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት ሮድሪጎ ፣ ቪንሰስ ጁኒየር ፣ ቫልቬርዴ ፣ ኪሊያን ምባፔ ፣ ብራሂም የወርሀ ነሐሴ የሪያል ማድሪድ ወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥነው የላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ዩራጓዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፌዴ ቫልቬርዴ የወርሀ ነሐሴ የሪያል ማድሪድ ወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤንታኩር በእንግሊዝ ኤፍኤ ክስ ቀረበበት !

ዩራጓዊው የቶተንሀም አማካይ ሮድሪጎ ቤንታኩር ከመገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ በቡድን አጋሩ ላይ ያልተገባ ነገር ተናግሯል በሚል ክስ እንደተከፈተበት ተገልጿል።

ሮድሪጎ ቤንታኩር ከዩራጓይ መገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ የሰን ሁንግ ሚን ማልያ ማገኘት ከተቻለ ሲጠየቅ “ ምናልባት የአጎቱን ልጅ ምክንያቱም ሁሉም ይመሳሰላሉ “ ሲል መልሶ ነበር።

ተጨዋቹ በክሱ ጥፋተኛ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ጨዋታዎች ሊቀጣ እንደሚችል ተነግሯል።

ሮድሪጎ ቤንታኩር በቀረበበት ክስ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጥ የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር መጠየቁ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 19:22:59
Back to Top
HTML Embed Code: