Telegram Web Link
82 ’

ስፔን 1 - 1 እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

ኒኮ ዊሊያምስ           ፓልመር

- ኮል ፓልመር በአውሮፓ ዋንጫው ምንም ጨዋታ በቋሚነት ሳይጀምር ለእንግሊዝ አንድ ግብ አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
87 ’

ስፔን 2 - 1 እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

ኒኮ ዊሊያምስ           ፓልመር
ኦያርዛባል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🏆🏆 CHAMPION 🏆🏆

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

ለስፔን ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ኒኮ ዊሊያምስ እና ሚኬል ኦያርዛባል ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ኮል ፓልመር ማስቆጠር ችሏል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የአውሮፓ ዋንጫ ውድድርን አራት ጊዜ በማሸነፍ የመጀመሪያው ብሔራዊ ቡድን መሆን ችሏል።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በውድድሩ ታሪክ ሁለት የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ የተሸነፉ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆነዋል።

ሀሪ ኬን ፣ ዳኒ ኦልሞ ፣ ሙሲያላ ፣ ኮዲ ጋክፖ ፣ ሽራንዝ እና ሚካውታድዝ በሶስት ግቦች የውድድሩን የወርቅ ጫማ ተጋርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የውድድሩ ምርጥ ተጨዋቾች ይፋ ሆኑ !

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ የዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጡ ይፋ ሆኗል።

ወጣቱ የስፔን ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ምርጥ ወጣት ተጨዋች በመሆን መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

የ 17ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በውድድሩ አራት ለግብ የሆኑ ኳሶች ማቀበል ሲችል አንድ ግብ በማስቆጠር ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ ችሏል።

ሮድሪ እና ላሚን ያማል የውድድሩ ምርጥ ተጨዋች ሽልማቱን ከዩኤፋ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን መቀበል ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በፍፃሜ መሸነፍ በጣም ከባድ ነው “ ሀሪ ኬን

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሀሪ ኬን በፍፃሜው የገጠማቸው ሽንፈት ሀዘኑ ከባድ መሆኑን ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

“ በፍፃሜ መሸነፍ በጣም ከባድ ነው “ ሲል የገለፀው ሀሪ ኬን ጥሩ ተጫውተናል የአቻነት ግብ አስቆጥረን ወደ ጨዋታው ተመልሰንም ነበር ነገርግን ልንጠቀምበት አልቻልንም " ሲል ተናግሯል።

ቡድናቸው ኳስ ተቆጣጥሮ መቆየት ሳይችል ቀርቶ ግብ ማስተናገዱን ያስረዳው ሀሪ ኬን " ምንም እንኳን እግርኳስ ቢሆንም ህመሙ ጥልቅ ነው " ሲል በውጤቱ ማዘኑን ገልጿል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሀሪ ኬን እስካሁን ስድስት የፍፃሜ ጨዋታዎች ማድረግ ቢችልም ምንም ዋንጫ ማሳካት አልቻለም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአውሮፓ ሻምፒዮኖቹ ምን አሉ ?

የ 2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር አሸናፊው የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከድሉ በኋላ ተከታዩን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

- ኒኮ ዊሊያምስ :- " እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል አሁን የአውሮፓ ሻምፒዮን ሆነናል በቀጣይ የአለም ሻምፒዮን መሆን እንፈልጋለን።"

- ሮድሪ :- " ምናልባት ዛሬ የእግርኳስ ህይወቴ ምርጡን ቀን ነው ያሳለፍኩት ትልቅ ታሪክ ፅፈናል በዚህ ብቻም አናቆምም "

- ላሚን ያማል :- " ህልሜ እውን ሆኖልኛል እስካሁን ከተቀበልኳቸው የልደት ስጦታዎች ሁሉ ይሄኛው የተለየ እና ትልቁ ነው።

- ኡናይ ሲሞን :- " የሽልማት ሜዳልያዬን ለወላጅ እናቴ ሰጥቻታለሁ ምክንያቱም እሷ ከዚህ በፊት ልትመለከተኝ መጥታ አታውቅም ነበር። "

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#CopaAmerica2024

የኮፓ አሜሪካ የፍፃሜ ውድድር በመካሄድ ላይ ሲገኝ ኮሎምቢያ እና አርጀንቲና እያደረጉ የሚገኙት መርሐ ግብር ያለ ግብ 0ለ0 በሆነ ውጤት መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቋል።

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ባጋጠመው ጉዳት ተቀይሮ ሲወጣ በተጠባባቂ ወንበር ላይ በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆኖ ተይቷል።

የጨዋታው መጀመሪያ ሰዓት በደጋፊዎች ችግር ምክንያት ለሶስት ጊዜያት ሊቀያየር ችሏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርጀንቲና ሻምፒዮን ሆነዋል!

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በሀገረ አሜሪካ የተዘጋጀውን የኮፓ አሜሪካ ውድድር አሸናፊ በመሆን አጠናቀዋል።

120 ደቂቃዎችን በፈጀው መርሐ ግብር አርጀንቲና በላውታሮ ማርቲኔዝ ብቸኛ ግብ ኮሎምቢያን 1ለ0 መርታት ችላለች።

በአሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ የሚመሩት አርጀንቲናዎች ውድድሩን ለተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ ችለዋል።

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የኮፓ አሜሪካን ሲያሸንፍ በታሪክ ለአስራ ስድስተኛ ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል።

ላውታሮ ማርቲኔዝ በኮፓ አሜሪካው አምስት ጎሎችን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኗል።

አርጀንቲና ኮፓ አሜሪካውን ማሸነፏን ተከትሎ በፊናሌሲማ የዋንጫ ጨዋታ የዩሮ አሸናፊዋን ስፔን የምትገጥም ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባሎንዶር ለሮድሪጎ ስጡት “

የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዋ ስፔን ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላፉንቴ ባሎን ዶር ሮድሪጎ እንደሚገባው ከድሉ በኋላ በሰጡት አስተያየት ተደምጠዋል።

አሰልጣኙ “ ባሎን ዶርን ለሮድሪጎ ስጡት “ ሲሉ ሲደመጡ የአለማችን ምርጡ ተጫዋቾች በስብስቤ ውስጥ አሉኝ “ በማለት የቡድኑን አባላት አድንቀዋል።

የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሮድሪጎ በበኩሉ “ ስፔናዊ ተጫዋች ባሎንዶር ቢያሸንፍ ደስ ይለኛል ፣ የስፔን እግር ኳስ ደረጃን አሳይተናል “ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኦባምያንግ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያመራ ይችላል !

ጋቦናዊው የኦሎምፒክ ማርሴይ የፊት መስመር ተጨዋች ኦባምያንግ በቀጣይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ ሊያመራ እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል።

ተጫዋቹን ለማስፈረም በቅርቡ ናቾን ከሪያል ማድሪድ በይፋ ያስፈረመው የሳውዲ ሊጉ ክለብ አል ቃዲሲያ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ማርሴይ ኦባምያንግን ማቆየት እንደሚፈልጉ ቢገለፅም የወደፊት ቆይታው የሚወሰነው በራሱ በተጨዋቹ እንደሚሆን ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሙለር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ሊያገል ነው ! የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ለማግለል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል። የ 34ዓመቱ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል። ቶማስ ሙለር ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር አንድ የአለም ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶማስ ሙለር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል።

ከአስራ አራት አመታት በላይ ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት የሰጠው ቶማስ ሙለር አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ጨዋታዎችን ማድረግም ችሏል።

የ 34ዓመቱ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር አንድ የአለም ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሁዋን ጋምፐር ዋንጫ መቼ ይደረጋል ?

በካታላኑ ክለብ ባርሴሎና አዘጋጅነት ለሀምሳ ዘጠነኛ ጊዜ የሚካሄድው የሁዋን ጋምፐር ዋንጫ ውድድር የሚደረግበት ቀን ታውቋል።

የዘንድሮው የባርሴሎና የሁዋን ጋምፐር ዋንጫ ውድድር ተጋጣሚ የፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታው ነሐሴ 6/2016 ዓ.ም በስታድ ሉዊስ ኮምፓኒ እንደሚደረግ ተገልጿል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ተጫዋቹን ሊሸጥ ነው ! ማንችስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊ ካምብዋላ ለስፔኑ ክለብ ቪያሪያል ለመሸጥ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ቪያሪያል ተጨዋቹን በ10 ሚልዮን ዩሮ ለመግዛት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። ተጨዋቹ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን በማድረግ ቪያሪያልን በይፋ ለመቀላቀል ቀጠሮ እንደተያዘለት ተዘግቧል። @tikvahethsport    …
ዩናይትድ ከተጫዋቹ ጋር በይፋ ተለያየ !

ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊ ካምብዋላ ማንችስተር ዩናይትድን በመልቀቅ የስፔኑን ክለብ ቪያሪያል መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ማንችስተር ዩናይትዶች ከተጨዋቹ ዝውውር አጠቃላይ11.5 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ እንደሚቀበሉ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት አንድ አመት ውል ቀርቶት የነበረ ሲሆን ውሉን ለማራዘም የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ እንደነበር ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/03 19:24:53
Back to Top
HTML Embed Code: